uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Mesalemiya Betel Congregation

Mesalemiya Betel Congregation

Відкрити в Telegram

መሳለሚያ ቤቴል መካነየሱስ

Показати більше
265
Підписники
Немає даних24 години
+17 днів
+130 днів
Архів дописів
የእግዚአብሔር_ፈቃድና_ዓላማ_ፓስተር_ተድላ_ሲማ_Pastor_Tedla_Sima_New_Ethio_Amharic.m4a21.05 MB

የእግዚአብሔር ፈቃድና ዓላማ በሚል ርዕስ በፓስተር ተድላ ሲማ የቀረበ መልዕክት

የእግዚአብሔር ፈቃድና ዓላማ

ሰላም ለእናንተ ይሁን!!! በክርስቶስ ፍቅር ልብን መጠበቅ!!! ፈተናዎቻችንን ሳይባክኑ እንድንጠቀምባቸው እንዲሁም ፈተናዎቻችንን ወደ ድል የምንቀይርባቸው ና የመከራዎቻችንን ጊዜ የምናሳጥርባቸው አስተማማኝ ምላሾች አሉን? ትላንትን አለመርሳት- ዛሬን መታገስ- በክርስቶስ ፍቅር ልብን እየጠበቁ ና እርሱን እየፈሩ ነገን መመልከት:: በክርስቶስ ፍቅር ልብን መጠበቅ!!! በመከራችን ናበፈተናችን ጊዜ እግዚአብሔር አንዱ የሚያድሰው ፍቅራችንን ነው:: የመከራውና የፈተናው እሳት የመከፉቱን- የቅይማቱን- የቅሬታውን ና የጥላቻውን ገለባ ይበላዋል:: ፍቅር የጥላቻን መርዝ ያመክነዋል:: ጌታችን የዼጥሮስን ክህደት የይሁዳን ጌታውን መሸጥ የሌሎቹንም በመከራ ቀን አብሮ አለመቆም የመከተው በፍቅር ነው:: የወደዳቸውን እስከመጨረሻ ወደዳቸው:: በመከራና በፈተናችን ሰዓት ተፈትኖ የሚወጣው እውነተኛ ፍቅር ነው:: ወደ ላይ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ወደ ጎን ለሰዎች ያለን ፍቅር:: በእርግጥ እግዚአብሔርን በፍፁም ልቤ በፍፁም አሳቤ እወደዋለው? ባልንጀራዬንስ በተወደድኩበት ፍቅር አየዋለው? ጌታችን የመስቀሉን እፍረትና ውርደት እንዴት ናቀው? ሲጀምር መስቀል ያሳፍራል በተለይ ለአፍቃሪው ጌታ የተገባ አይደለም:: ታምኖ ሲከዳ በገበታው የበላ ተረከዙን ሲያነሳበት አፍቅሮ ሲጠላ ያሳፍራል- ያስደነግጣል:: ሐዋርያትም ስለተቀበሉት መከራ ክብራችን ነው እንጂ ውርደት አይደለም- አናፍርም ማለታቸው የጌታቸውን ፈለግ መከተላቸው ይሆን? አምነንየተከዳን- አፍቅረን የተጠላን- አጉርሰን የተነከስን እንኖር ይሆን? በእንዲህ ዐይነት የመከራና የፈተና ጊዜ ምን እናድርግ? በጌታችን ላይ ከደረሰ በሐዋርያት ላይ ከደረሰ በእኛ ላይ አይደርስም? ለጥላቻው- ለክህደቱ- ለመነከሱ የሰጡት ምልሽስ ምንነበር? በተለይ በመተው ጊዜ በመረሳት ጊዜ እጅግ እንፈተናለን:: ጌታችን መተውንም- መረሳትንም ያውቃል:: የሚያልፍትንም ሊረዳቸው ይችላል ይህ ተስፉ ነው የእምነታችንም መልዕቅ ነው:: ፍቅር ኃያል ነው!! ፍቅር ብርቱ ነው!! ሐዋርያት ፈተናን- መከራን እንዴት ይመለከቱት ነበር? “እንግዲህ በእምነት ስለ ጸደቅን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋራ ሰላም አለን። በርሱም በኩል አሁን ወደ ቆምንበት ጸጋ በእምነት መግባት ችለናል፤ የእግዚአብሔርንም ክብር ተስፋ በማድረግ ሐሤት እናደርጋለን። በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ ምክንያቱም መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን። ትዕግሥት ጽናትን፣ ጽናት የተፈተነ ባሕርይን፣ የተፈተነ ባሕርይ ተስፋን፤ ይህም ተስፋ ለዕፍረት አይዳርገንም፤ እግዚአብሔር በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ ፍቅሩን በልባችን አፍስሷልና። ገና ደካሞች ሳለን፣ ልክ ጊዜው ሲደርስ፣ ክርስቶስ ስለ ኀጢአተኞች ሞቷልና። ለጻድቅ የሚሞት ሰው ማግኘት እጅጉን ያዳግታል፤ ለደግ ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል። ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል። አሁን በደሙ ከጸደቅን፣ ይልቁንማ በርሱ በኩል ከእግዚአብሔር ቍጣ እንዴት አንድንም! የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከርሱ ጋራ ከታረቅን፣ ዕርቅን ካገኘን በኋላ፣ በሕይወቱማ መዳናችን እንዴት የላቀ አይሆንም! ይህ ብቻ አይደለም። ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ ሐሤት እናደርጋለን።” ሮሜ 5 : 1 - 11 “ልጆች ሆይ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፤ እነርሱንም አሸንፋችኋቸዋል፤ ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል። እግዚአብሔር ፍቅሩን በመካከላችን የገለጠው እንዲህ ነው፤ እኛ በርሱ አማካይነት በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ። ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው። ወዳጆች ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፣ እኛም እርስ በእርሳችን መዋደድ ይገባናል።” 1 ዮሐንስ 4 : 4 , 9 - 11 መደምደሚያ:- በፍቅር ጉዳይ?? በፍቅር ጉዳይ በእግዚአብሔር ተቀድመናልና የእርሱን ፈለግ እንከተል!!! "ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው።" ሄኖክ ኃ/ማርያም

Голосове повідомлення12:15

በወንድም ብርአኑ ታደለ የቀረበ ዝማሬ

Голосове повідомлення18:58

በወንድም ብርአኑ ታደለ የቀረበ ዝማሬ

Голосове повідомлення53:19

ትላንት እሁድ በነበረው አምልኮ ፕሮግራም “እግዚአብሔርን መስማት” በሚል ርዕስ በቄስ አስቻለው ሲማ የቀረበ መልእክት

ሰላም ለእናንተ ይሁን!!!      ምስጋናና ሴይፍ “ቅዱሳን በክብር ይመካሉ፤ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ። የእግዚአብሔር ምስጋና በጕሮሮአቸው ነው፤ ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጃቸው ነው።” መዝሙር 149፥5–6 እኛ ሰዎች የምንመካበትን  ስናስብ  የተሰጡን እንጂ የራሳችን ባልሆኑ ነገሮች በራሳችን ጥረት እንዳደረግን ወይም እንደሆነ በማድረግ እንመካለን ። ይሁን እንጂ የምንነጠቀው ወይም የሚወሰድብን እንደሆነ ልናስብ ይገባል። ሰው በተሰጠው ሥልጣን የመካል፣ ሊሻር እንደሚችል የሚያውቅ አይመስልም። አንዳንዱ በተሰጠው ገንዘብ ይመካል ። እንደሚመነምንና እንደሚያጣም የሚያውቅ አይመስልም። ....  እነዚህ  የምንመካባቸው ሊሆኑ አይገባም። መዝሙረኛው የእግዚአብሔር ሕዝብ ማንነትና አኗኗር እንዴት መሆን እንዳለበት ያሳያል። በአንድ በኩል በአፋቸው ምስጋና አለ፤ በሌላ በኩል በእጃቸው ሰይፍ አለ። እኛ የጌታ ተከታዮች   ምስጋና ብቻ የሚናደርግ ሳንሆን፣ ተግባራችን እንደ እግዚአብሔር ቃል  መሆን እንዳለበት ክፍሉ ይነግረናል። ከዚህም የተነሳ ፦  ደስታና ኩራታችን በእግዚአብሔር ላይ በመሆኑን በእርሱ "ክብር እንመካለን" " ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ። " — ወደ ገላትያ ሰዎች 6:14 ምኬታችን  በራሳችን ችሎታ፣ ሀብት ወይም ስኬት አይደለም  በጌታ  እንጂ። ደስታችን ሁኔታዎች  ሲስተካከሉ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ተስፋችን በጌታ ላይ ስለሆነ በችግርም ጊዜ እርሱን ልናመሠግን ይገባል። ምስጋና በልብ ብቻ ተደብቆ የሚቀር ነገር አይደለም፤ በአፍም ይገለጣል። "እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው። " ይላል። — መዝሙረ ዳዊት 34:1 የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። — ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:17 ወገኖቼ ፦ ምስጋና በአፋችን፤ ቃሉ በልባችን፤ መታዘዝ በሕይወታችን ይገለጡ ። አሜን። ተባረኩ ወንድም አባይነህ ሽፈራው

Голосове повідомлення07:27

በምስክር መዘምራን የቀረበ ዝማሬ

Голосове повідомлення08:22

በምስክር መዘምራን የቀረበ ዝማሬ

Голосове повідомлення53:41

ትላንት አርብ በነበረው የፈውስ ፕሮግራም በቄስ አስቻለው ሲማ ቀረበ መልዕክት

እግዚአብሔርን_መፈለግ_መጋቢ_ተድላ_ሲማ_Ethiopian_Christian_sibket_preaching128k.m4a33.66 MB

እግዚአብሔርን መፈለግ በሚል ርዕስ በፓስተር ተድላ ሲማ የቀረበ መልዕክት

Голосове повідомлення10:19