uk
Feedback
Neros' School Key To Success

Neros' School Key To Success

Відкрити в Telegram

ሰላም የኔሮስ ስኩል ቤተሰቦች ይህ ቻናል ስለ ኔሮስ ስኩል መረጃዎች የሚለቀቅበት ነው

Показати більше
2 341
Підписники
Немає даних24 години
+107 днів
+5330 день
Архів дописів
📢 እንኳን ለ2018 የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 🎉 ✍ ​የተከበራችሁ የትምህርት ቤታችን ወላጆች/አሳዳጊዎች ፣ ትላንት ሰኔ 19/2018 ዓ.ም የዚህ ዓመት ትምህርት በይፋ ተጠናቋል። ​የተማሪዎቻችንን የመዝጊያ በዓልና የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ይበልጥ ደማቅ ለማድረግ ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ዝርዝር ፕሮግራሞችና አስፈላጊ መረጃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡- ​🗓 1. የምርቃት ፕሮግራም ​🎓 የፕሪፓራቶሪ ተማሪዎች የምርቃት ፕሮግራም፦ቀን: ቅዳሜ ሰኔ 27/2018 ዓ.ም ​ሰዓት: ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ​ቦታ: በጀነራል ሆስፒታል አዳራሽ ​🎓 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ምርቃት ፕሮግራም፦ቀን: እሁድ ሰኔ 28/2018 ዓ.ም ​ሰዓት: ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ​ቦታ: በኮሌጅ 1ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ​🏆 በዕለቱ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ይካሄዳል። እባክዎ ሰዓት አክብረው በመገኘት የልጆችዎን ደስታ ይጋሩ። ​👗 2. የጋውን (Gown) አወሳሰድ እና አመላለስ ​🛑 የጋውን አወሳሰድ: እስካሁን ጋውን ያልወሰዳችሁ ተመራቂዎች በሚቀሩት ቀናት 400 ብር በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ። (በበዓሉ ዕለት ይዞ መምጣት እንዳይረሳ)። ​🔄 የጋውን መመለሻ ቀን: ከሐምሌ 1 እስከ ሐምሌ 3/2018 ዓ.ም ነው። ​🔖 3. የክረምት ማጠናከሪያ (Tutorial) ትምህርት ​📚 ለማን: በትምህርት ቤቱ ለምትገደዱ እና ማጠናከሪያ ለምትፈልጉ ከአጸደ ህጻናት (KG) እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች። ​📅 የሚቆይበት ጊዜ: ከሐምሌ 13/2018 እስከ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም። ​📝 ምዝገባ: ከሐምሌ 2/2018 ዓ.ም ጀምሮ። ​📝 4. የ2019 የትምህርት ዘመን አዲስና ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ​👶 ለአዲስ የPre-KG ተማሪዎች (ለነባር ተማሪዎች እህት/ወንድም): ሌሎች ተማሪዎችን ከመመዝገባችን በፊት ከሐምሌ 2/2018 ዓ.ም ጀምሮ (ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን)። ​🔄 ለነባር ተማሪዎች ምዝገባ: ከሐምሌ 2/2018 እስከ ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም (የልጆን 1 ጉርድ ፎቶ ይዘው ይምጡ)። የአዳዲስ ተማሪዎች ቅበላችንን እንድንወስን በወቅቱ ብቻ እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን። እንዲሁም ሁሉም ተማሪዎች በነባር ግቢያቸው የሚመዘገቡ ይሆናል። ​🔄 የቅርንጫፍ ለውጥ መመሪያ (ወደ 1ኛ ክፍል ለሚገቡ): ✅ ​የቦሌ ቅርንጫፍ ተማሪዎች ➡️ በኮሌጅ ቅርንጫፍ ✅ ​የአውራ ጎዳና ቅርንጫፍ ተማሪዎች ➡️ በ180 ቅርንጫፍ ✅ ​የ180 ቅርንጫፍ ተማሪዎች ➡️ በ180 1ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ይመዘገባሉ። 💳 (የክፍያ መረጃ ከሪፖርት ካርድ ጋር አብሮ ይላካል)። ⚠️ ማሳሰቢያ፡ ምዝገባው በተጠቀሱት ቀናት ብቻ የሚከናወን ይሆናል። ​🏃‍♂️ 5. ትምህርት ቤት ለሚቀይሩ (መልቀቂያ) ​📄 ትምህርት ቤት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ለምትለቁ ተማሪዎች 1 ፎቶግራፍ በመያዝ ከሐምሌ 2 እስከ ሐምሌ 10/2018 ዓ.ም መልቀቂያ መውሰድ ትችላላችሁ። ​📞 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን ይደውሉ፡ ​📍 አውራ ጎዳና ቅርንጫፍ: 0222126586 / 0994918501 ​📍 ኮሌጅ ቅርንጫፍ: 0927249501 / 0984981092 / 0981773691 / 0981751046 ​📍 ቦሌ ቅርንጫፍ: 0941435180 / 0994819283 ​📍 180 ቅርንጫፍ: 0977776561 / 0962502870 #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #Closingday #Ceremony

📢 ፈተና ተጠናቀቀ! 🎉 ✍ ​ክቡራን ወላጆች/አሳዳጊዎች ፦ ​እንኳን ለፈተና ማጠናቀቂያ ቀን በሰላም አደረሰን! የ2018 ዓ.ም የሁለተኛው መንፈቅ አመት (የአራተኛው ሩብ ዓመት) ማጠቃለያ ፈተናችን
+1
📢 ፈተና ተጠናቀቀ! 🎉 ✍ ​ክቡራን ወላጆች/አሳዳጊዎች ፦ ​እንኳን ለፈተና ማጠናቀቂያ ቀን በሰላም አደረሰን! የ2018 ዓ.ም የሁለተኛው መንፈቅ አመት (የአራተኛው ሩብ ዓመት) ማጠቃለያ ፈተናችንን ዛሬ በድል አጠናቀናል። ​ከፈተና በኋላ ስላለው መርሃ-ግብር፦ ​📅 ሰኞ ሰኔ 22/2018 ዓ.ም  📅 ​📝 የፈተና እርማት እና ውጤት፦ ተማሪዎች የፈተና ወረቀታቸውን የሚያዩበት፣ እርማት የሚወስዱበት እና የፈተና ውጤት የሚሰጥበት ዕለት ይሆናል። ​🕛 የትምህርት ሰዓት፦ በዕለቱ ትምህርት ግማሽ ቀን ብቻ መሆኑን እንገልጻለን። ​መልካም ውጤት ለተማሪዎቻችን! 🙏 #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #FinalExam #Closingday

📝 የፈተና መርሃ-ግብር እና ወሳኝ ማሳሰቢያ! 📝 ​ክቡራን ወላጆች/አሳዳጊዎች ፦ ✍ ​የኔሮስ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት (Neros' International School) የ2018 ዓ.ም የሁለተኛው
+2
📝 የፈተና መርሃ-ግብር እና ወሳኝ ማሳሰቢያ! 📝ክቡራን ወላጆች/አሳዳጊዎች ፦ ✍ ​የኔሮስ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት (Neros' International School) የ2018 ዓ.ም የሁለተኛው መንፈቅ አመት (የአራተኛው ሩብ ዓመት) ማጠቃለያ ፈተና ሰኔ 16/2018 ዓ.ም ይጀምራል። ከፈተናው ጋር በተያያዘ ወሳኝ መረጃዎችን ከዚህ በታች እንደሚከተሉት እናቀርባለን፦ ​💰 የትምህርት ቤት ክፍያን በተመለከተ 💰       ⚠️ ከፈተና ቀናት በፊት እስከ ሰኔ ወር ያለውን የትምህርት ቤት ክፍያ ማጠናቀቅ ግዴታ ነው።       ​🚫 ይህንን ያላደረጋችሁ ወላጆች በአስቸኳይ እንድታጠናቅቁ እያሳሰብን፣ ማንኛውም ዓይነት ክፍያ ያለበት ተማሪ ፈተና ላይ መቀመጥ የማይችል መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን። ​⏰ የፈተና ቀናት የትምህርት ሰዓት ⏰ 📅 ከሰኔ 16/2018 እስከ ሰኔ 19/2018 ዓ.ም፦      🎒 ትምህርት ግማሽ ቀን ብቻ ይሆናል።      🕒 በመሆኑም ልጆችዎን በ 6:30 መጥተው እንዲወስዱ እናሳስባለን። ​📚 በትምህርት ቤት የጥናት ፕሮግራም ለሚከታተሉ ተማሪዎች፦      ​📅 ከማክሰኞ ሰኔ 16/2018 እስከ ሐሙስ ሰኔ 18/2018 ዓ.ም ድረስ።      🕒 ልጆችዎን በ 7:30 መጥተው እንዲወስዱ እናሳስባለን። ​📅 የፈተና ወረቀት መረከቢያ እና የመዝጊያ ፕሮግራም       ​📝 ሰኞ ሰኔ 22/2018 ዓ.ም፦       ​📄 ተማሪዎች የፈተና ወረቀታቸውን እና የፈተና እርማት የሚወስዱበት ቀን ይሆናል።       ​🕛 በዕለቱ ትምህርት ግማሽ ቀን መሆኑን እንገልጻለን። ​🏆 የመዝጊያ በዓል እና የሰርተፍኬት ቀን፦        ​📢 የፈተና ማጠናቀቂያ ቀን ላይ የምናሳውቅ ይሆናል። መልካም ፈተና! 🙏 #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #Exam #Schedule

photo content
+4

photo content
+7

photo content
+2

photo content
+9

​🌟 የዕለቱ ደማቅ ትውስታ 🌟ዛሬ እና ትላንት በትምህርት ቤታችን ያካሄድነው የመማር ማስተማር እና የሰልፍ ዝግጅት በስኬት ተጠናቋል! 🎉✨ 👉 ​ጥሪያችንን አክብራችሁ በጠዋት በመገኘት፣ የልጆቻችንን የሰልፍ ሥነ-ሥርዓትና የመማር ማስተማር ሂደቱን በቅርበት ለታዘባችሁልን ክቡራን ወላጆች በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን። የእናንተ አብሮነትና ድጋፍ ለልጆቻችን ሁልጊዜም ትልቅ ብርታት ነው! 🙏🏫 ​የልጆቻችንን ታዛዥነት፣ ሥነ-ሥርዓትና ንቁ ተሳትፎ የተመለከትንበት ይህ ዕለት በትምህርት ቤታችን ልዩ ድባብን ፈጥሮ ውሏል። 📸 ​የዛሬውን ውብ ውሎ የሚያሳዩ ጥቂት ምስሎችን (ፎቶዎችን) እነሆ!👇 “ለተሻለ ነገ ዛሬን እንገነባለን!” 🎓📚 #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #Discipline #Education

photo content
+6

Orientation ፕሮግራም ለ 8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን! 🌟 ✍ ​የ 8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን የሚኒስትሪ ፈተናን በብልሀት እና በልበ-ሙሉነት ማለፍ እንዲችሉ የ Orientation ፕሮግራም ዛሬ ተሰቷቸዋል። 👉 ​በስልጠናው ላይ ተማሪዎቻችን ጥያቄዎችን በጥንቃቄ የመረዳት፣ ጊዜን በአግባቡ የመጠቀም እና በፈተና ወቅት ትኩረትን ሰብስቦ መስራት ተምረዋል። ይህ ስልጠና ተማሪዎቻችን የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ለሚያደርጉት ጉዞ ትልቅ ስንቅ ይሆናቸዋል። 📌 ​ውድ ወላጆች፣ ተማሪዎቻችን ቀሪዎቹን ቀናት በትጋትና በትኩረት እንዲዘጋጁ የበኩላችሁን የሞራል እና የክትትል ድጋፍ እንድታደርጉላቸው አደራ እንላለን። 🙏 ​ለተማሪዎቻችን በሙሉ መልካም ዕድል እና የላቀ ውጤት እንመኛለን! 🏅📚 #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #Grade8 #Orientation

📣 ማስታወቂያ ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ​🗓 ነገ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም ​የ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን በሚኒስትሪ ፈተና ዙሪያ አስፈላጊ የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ይሰጣል። 📍 ሁሉም ተማሪዎች እስከ 2:00 ሰዓት ባለው ጊዜ በትምህርት ቤታችን ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲገኙ በጥብቅ እናሳስባለን። 🎓📝 ​⏰ Orientation የሚሰጠው ከጠዋቱ 2:00 እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ ነው። #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #Grade8

📢 ለወላጆች 👨‍👩‍👧‍👦 ✍ የፊታችን ዕረቡ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በአውራጎዳና ቅርንጫፍ እና የፊታችን ሐሙስ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም.180 ቅርንጫፍ እና በቦሌ ቅርንጫፍ የሰልፍ ሥነ-ሥርዓታችንን እንዲሁም የመማር ማስተማር ሁኔታውን እንዲያዩልን በአክብሮት ጠርተንዎታል:: ​📌 አስፈላጊ ማሳሰቢያ፦ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚቆዩበት ጊዜ ከጠዋቱ 2:15 እስከ 3:30 ብቻ ስለሆነ፣ ሰዓት አክብረው እንዲገኙና እንዳያረፍዱብን በጥብቅ እናሳስባለን። ​🎓 ለፕሪፓራቶሪ ተመራቂ ተማሪዎች 🧒👧 ​ ​📅 የምርቃት ቀናት፦ ✅ ​ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም.፦ የፕሪፓራቶሪ (Preparatory) ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ✅ ​ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም.፦ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ​📍 የምረቃው ቦታ፦ በፕሮግራሙ የጥሪ ካርድ ላይ የሚገለጽ ይሆናል። ​⚠️ የመመረቂያ ጋውን (Gown) አወሳሰድን በተመለከተ፦ ☑️ ተማሪዎች የመመረቂያ ጋውናቸውን ከሰኔ 10 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ባሉት ቀናት ውስጥ፤ በልጅዎ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ብር 400 (አራት መቶ ብር) 💵 በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን። ​🔄 ጋውን መመለሻ ቀን ከሐምሌ 1—3 መሆኑን እንገልጻለን:: #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #Graduation

📅 የ2018 ዓ.ም (2026) የኦሮሚያ ክልል የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ ✍ ​ውድ ወላጆች እና ተማሪዎች፣ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ያወጣውን ይፋዊ የፈተና ፕሮግራም እንደሚከተለው እናሳውቃለን። ​🔴 የ6ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ፕሮግራም (Grade 6)ሰኔ 08/2018 ዓ.ም (ሰኞ) ​🌅 ጠዋት: ​3:00 – 4:00 | አማርኛ ​4:00 – 5:00 | እንግሊዘኛ ( English ) ​☀️ ከሰዓት: ​8:00 – 9:00 | ሂሳብ ​ሰኔ 09/2018 ዓ.ም (ማክሰኞ) ​🌅 ጠዋት: ​3:00 – 4:00 | አካባቢ ሳይንስ ​4:00 – 5:00 | ግብረ-ገብ ​🔵 የ8ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ፕሮግራም (Grade 8)ሰኔ 11/2018 ዓ.ም (ሐሙስ) ​🌅 ጠዋት : ​3:00 – 4:00 | አማርኛ ​4:00 – 5:00 | እንግሊዘኛ ( English ) ​☀️ ከሰዓት: ​8:00 – 9:00 | ሂሳብ ​9:00 – 10:00 | ዜግነት ​ሰኔ 12/2018 ዓ.ም (አርብ) ​🌅 ጠዋት : ​3:00 – 4:00 | የተቀናጀ ሳይንስ (General Science) ​4:00 – 5:00 | ህብረተሰብ ​☀️ ከሰዓት: ​8:00 – 9:00 | አፋን ኦሮም ​⚠️ ለተማሪዎች የተሰጡ ጠቃሚ ማሳሰቢያዎች፡ 1⃣ ​ተማሪዎች ለጠዋት ፈተና ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ላይ፣ ለከሰዓት ፈተና ደግሞ ከቀኑ 7:00 ሰዓት በፊት በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት በፈተና ክፍላቸው ፊት ለፊት ተሰልፈው መገኘት አለባቸው። 2⃣ ​ለፈተና የተመደበውን ሰዓት መጨመርም ሆነ መቀነስ በፍጹም አይቻልም። 3⃣ ​የፈተናው ሰዓት አቆጣጠር በሀገራችን (በኢትዮጵያ) የሰዓት አቆጣጠር መሠረት ነው። 4⃣ ​ማንኛውም የፈተና ጥያቄ ወረቀት በተማሪው እጅ ተይዞ ከፈተና ክፍል መውጣት አይቻልም። ፈተናው ሲያልቅ በጥንቃቄ ተሰብስቦ ለትምህርት ቤቱ መረከብ አለበት። 🙏 ​ለሁሉም ተማሪዎቻችን መልካም የፈተና ጊዜና ከፍተኛ ውጤት እንመኛለን! ✨ #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #Minstry #Schedule #Grade6 #Grade8

photo content
+8

photo content
+9

photo content
+4

📣 የ Orientation ፕሮግራም ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን! ✍ በዛሬው እለት ​ሰኔ 7/2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን የሚኒስትሪ ፈተናን በከፍተኛ የራስ መተማመን እና ስኬት መጋፈጥ እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀው የ Orientation ፕሮግራም ዛሬ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። በ Orientation ፕሮግራሙ ላይ ተማሪዎቻችን፦ 👉 በፈተና ወቅት ጊዜን በአግባቡ የመጠቀም እና ጥያቄዎችን በጥንቃቄ የመረዳት 👉 በፈተና ወቅት የሚፈጠሩ የተለመዱ ስህተቶችን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ፣ 👉 የፈተና ጭንቀትን (Exam Anxiety) እንዴት መቆጣጠር እንዳለባቸው ሰፊ ግንዛቤ አግኝተዋል። 📍 ​ይህ ስልጠና ተማሪዎቻችን የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ለሚያደርጉት ጉዞ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሮላቸዋል። ​ውድ ወላጆች፣ ተማሪዎቻችን ቀሪዎቹን ቀናት በትጋት እንዲያጠኑ እና በትኩረት እንዲዘጋጁ የበኩላችሁን ድጋፍ እንድታደርጉላቸው አደራ እንላለን። ​መልካም ዕድል ለሚያበሩት ኮከቦቻችን! 🌟🎓 #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #Orientation #6thgrade

​🎵 🎸 "አዝማች" — የሙዚቃ ቡድናችን! 🎤 ✍ ​"አዝማች" ማለት የሙዚቃ ተደጋግሞ የሚባለው ዋናው የመጀመሪያው ግጥም ነው። ልክ እንደ ስሙ ሁልጊዜም በልባችን የሚቀሩ ድንቅ ትዕይንቶችን ለማቅረ
+6
​🎵 🎸 "አዝማች" — የሙዚቃ ቡድናችን! 🎤 ✍ ​"አዝማች" ማለት የሙዚቃ ተደጋግሞ የሚባለው ዋናው የመጀመሪያው ግጥም ነው። ልክ እንደ ስሙ ሁልጊዜም በልባችን የሚቀሩ ድንቅ ትዕይንቶችን ለማቅረብ በ180 ቅርንጫፍ ግቢ ውስጥ የተለያዩ ክህሎቶችን እና መዝናናትን በመፍጠር ጠንካራ ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ✅ የ"አዝማች" የሙዚቃ ቡድን አባላትን አዳዲስ ትዕይንቶች፣ ልምምዶች እና ዝግጅቶች ከላይ ባለው ምስል ይመልከቱ!  📸👆 #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ ​#አዝማች #የሙዚቃቡድን

📣 የሰኔ ወር እሴት (Moral Value of the Month) 🌟 እውቅናን መስጠት | RECOGNITION 🌟 ✍ እውቅና መስጠት (Recognition)፦ "We rise by lifting others
📣 የሰኔ ወር እሴት (Moral Value of the Month) 🌟 እውቅናን መስጠት | RECOGNITION 🌟 ✍ እውቅና መስጠት (Recognition)፦ "We rise by lifting others." እንደሚባለው፣ ሌሎችን ወደ ላይ በመሳብና እውቅና በመስጠት እንጂ ሌላውን በማሳነስ ማደግ አይቻልም። የሰዎችን ስኬት ማክበር የእኛን ማንነት ከፍ ያደርገዋል። ​👉 ሌሎች ከእኛ የሚሻሉበት ነገር እንዳለ ማመን መቻል ሁልጊዜ ከሰዎች ለመማር ዝግጁ እንድንሆን ያደርገናል። ማንም ሰው በሁሉም ነገር ሙሉ ሊሆን አይችልም። ​🏫 በትምህርትም ሆነ በስራ ቦታ፣ አብረውን ያሉትን ሰዎች ጥረት እያየን እውቅና የመስጠት ባህልን እናሳድግ! ​ መልካም ቀን! ☀️ #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #MoralValueoftheMonth #የሰኔወርእሴት

​🎉 የስብሰባ ማጠቃለያ እና ምስጋና 🎉 ​ለተከበራችሁ የኔሮስ ተማሪ ወላጆች በሙሉ፤ 👉 ​ትናንት ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በቦሌ የኪንደርጋርተን ቅርንጫፋችን የተካሄደው የወላጆችና የትምህር
+8
​🎉 የስብሰባ ማጠቃለያ እና ምስጋና 🎉ለተከበራችሁ የኔሮስ ተማሪ ወላጆች በሙሉ፤ 👉 ​ትናንት ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በቦሌ የኪንደርጋርተን ቅርንጫፋችን የተካሄደው የወላጆችና የትምህርት ቤቱ ማኔጅመንት የጋራ ውይይት በጣም ፍሬያማ በሆነ እና በጥሩ መልኩ ተጠናቋል! 🤝✨ ✍ ​በስብሰባው ላይ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትን ይበልጥ ለማረጋገጥ፣ በተከናወኑ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች እና በተለያዩ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ሰፊና ገንቢ ውይይት ተደርጓል። ✅ ​ስራና የግል ጉዳዮቻችሁን መስዋዕት በማድረግ፣ በሰዓቱ ተገኝታችሁ በልጆቻችሁ የወደፊት የትምህርት ጉዞ ላይ ያሳያችሁትን ከፍተኛ ተነሳሽነት፣ ያጋራችሁትን ውድ ሃሳብና አስተያየት ትምህርት ቤታችን በታላቅ አክብሮት ያደንቃል። ለነበረን ቆይታ እና ስኬታማ ውይይት ከልብ የመነጨ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን! 🙏❤️ 📌 ​የጋራ ጥረታችን እና የእናንተ ያልተቆጠበ ድጋፍ ለልጆቻችን የተሻለ ነገን ለመቅረጽ ትልቅ አቅም ይሆነናል። #ኔሮስስኩልየስኬትቁልፍ #ስብሰባ