uk
Feedback
WANOS MESFIN - ዋኖስ መስፍን

WANOS MESFIN - ዋኖስ መስፍን

Відкрити в Telegram

WANOS MESFIN - ዋኖስ መስፍን @WanosMesfin @WanosMesfinChat  +251919484604 - @WanosM

Показати більше
875
Підписники
+224 години
+77 днів
+130 днів
Архів дописів
ከስርዐት አልባ ዘፈቀዳዊ ድምፆች ቋንቋ የሚባል ክስተት ነጥሮ ሊወጣ የቻለው እንዴት ነው? ማሰብ ስለቻልን ነው ቋንቋን ያስገኘነው ወይስ ቋንቋ ስላለን ነው ማሰብ የቻልነው?

ጎርፍና ግፍ ተራኪ፡ ዋኖስ መስፍን ፀሐፊ፡ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት @WanosMesfin

የሰው እከክ!
+3
የሰው እከክ!

If you've met one person with autism, you've met one person with autism
If you've met one person with autism, you've met one person with autism

For All parents This is from Mela Special needs Service 30 Inclusive Schools in Addis Abeba 1. Champions Academy 2. ICS 3. Ca
For All parents This is from Mela Special needs Service 30 Inclusive Schools in Addis Abeba 1. Champions Academy 2. ICS 3. Cambridge International School 4.  Harmony hills Academy 5. Mald International School 6. Glory Academy 7. Andenet International School  8. Flippers International School 9. British International School  10. Hillside academy 11. Lebawi International Academy 12. Fasika academy 13. Young roots International School 14. Future talent Academy 15. Agatos Academy 16. Greek School 17. RICE International School 18. Sonnenlnad International School 19. Step Up Academy 20. Addis New Pride Academy 21. Kelem International school 22. Lion Hearts Academy 23. Maya International School 24. Tree Hill Academy 25. NEPs Academy 26. Green land Academy 27. St. Mark Academy 28. Bingham International School 29. Sanford International School 30. Mag School Source: Wanos Mesfin (Founder of Mela Special Needs Service)

ይህን ባየሁ ጊዜ ረካሁ ብሏል ሃሌሉያ ❝ ማውዝ አይጥ ነው እኮ ሚስተር ዋኖስ ❞ ሲለኝ አስታውሳለሁ። አኹን ኮምፒውተርን ይዘውረዋል።
ይህን ባየሁ ጊዜ ረካሁ ብሏል ሃሌሉያ ❝ ማውዝ አይጥ ነው እኮ ሚስተር ዋኖስ ❞ ሲለኝ አስታውሳለሁ። አኹን ኮምፒውተርን ይዘውረዋል።

🔔 በቅርብ ቀን! ትምህርት ቤት አጥተዉ ተቸግረዋል !!! የልጅዎ የቴራፒ፣ የድጋፍ አገልግሎት በመደበኛ ሰዓት እና ከትምህርት በኃላ  ት/ቤት እያሰሱ ከሆነ መላ ልዩ ፍላጎት አገልግሎት 'አለን' እንልዎታለን። ልዩ መደበኛ ትምህርት ልዩ ፍላጎት ላላቸው  በኦቲዝም ጥላ ሥር ለሚኖሩ ልጆች እና ለሌሎቾ 👉 እንዲሁም ለ መደበኛ ተማሪዎች !! 📆 Coming Soon! 📌 Stay tuned! 🤳 +251952118642 https://t.me/melaspecialneedservice

We can now say definitively that autism is genetic. For a long time, we have only been able to say that this was likely, but
+7
We can now say definitively that autism is genetic. For a long time, we have only been able to say that this was likely, but now we have looked at all the evidence and the answer is clear: autism is genetic. Read Dr Judith's blog to learn more: bit.ly/why-autism-matters https://www.facebook.com/100081200442946/posts/1105664308816907/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

አስቸኳይ የሥራ ማስታወቂያ ብዛት፦ 20 የሥራ መደቡ መጠሪያ፦ የልዩ-ፍላጎት ረዳት መምህር (Special Needs Assistant Teacher / One On One Aide) የሥራ ቦታ፦ ሐርመኒ ሒልስ
አስቸኳይ የሥራ ማስታወቂያ ብዛት፦ 20 የሥራ መደቡ መጠሪያ፦ የልዩ-ፍላጎት ረዳት መምህር (Special Needs Assistant Teacher / One On One Aide) የሥራ ቦታ፦ ሐርመኒ ሒልስ አካዳሚ ብዛት፦ 1 ፆታ፦ አይለይም የሥራ መስክ/ዘርፍ፦ ሥልጠና የወሰደ፣ ልዩ-ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ፣ የሥነ-ልቦና ዘርፎች፣ የህፃናት ዕድገት፣ ትምህርት እና እንክብካቤ እና ተያያዥ መስኮች የትምህርት ደረጃ፦ ዲፕሎማ፣ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ የቅጥር ሁኔታ፦ የወላጅ ቅጥር የልምድ ደረጃ፦ ከ0 ዓመት ጀምሮ ደሞዝ/ክፍያ፦ ከ10,000 - 15,000 ብር ማስታወቂያ የወጣበት ቀን፦ 05/01/2019 የማመልከቻ ማብቂያ ቀን፦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ተከታታይ 3 ቀናት።
ልዩ-ፍላጎት ያላቸው ልጆችን ለማገዝ እና ለውጥ ለማምጣት ታታሪ የሆኑ ሥራውን ለማግኘት የላቀ አስተዋፅዖ አለው።
ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ! የሥራውን ዝርዝር ለማግኘት እና ለማመልከት፦ በቴሌግራም፦ @MelaSpecialNeedsServiceaccount         በስልክ፦ 🤳 0717484604

ትምህርት ቤት ሲከፈት የልዩ-ፍላጎት ያላቸው ልጆች ወላጆች ሊያውቋቸውና ሊተገብሯቸው የሚገቡ 10 ወሳኝ ነጥቦች
      🙏ትዛዙ አበበ🙏 እንደሚታወቀው የያዝነው ሳምንት በርካታ ትምህርት ቤቶች የአመቱን የትምህርት ዘመን የሚጀምሩበት ሳምንት ነው። ይህን በማያያዝም ልዩ-ፍላጎት ያላቸው ልጆች ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚችሉ መጨነቃቸው አይቀሬ ነው ምክንያቱም ትምህርት ቤት ሲከፈት ለአንድ የልዩ-ፍላጎት ልጅ ያለው ወላጅ ነገሩ እንዲሁ ደብተርና ዩኒፎርም ገዝቶ መሸኘት ብቻ አይደለም ይልቁንም የፍርሃት፣ የጭንቀት፣ የረጅም ዝግጅት እና የትግል ጅምር እንጂ። ልጃችን አዲሱን አካባቢ እንዴት ይለምደዋል? መምህራኑ ይረዱት ይሆን? ፍላጎቱን በአግባቡ ያስረዳል? የሚሉ ጥያቄዎች ጭንቅላታችን ውስጥ ይመላለሳሉ። ሆኖም ግን ዝግጅታችንን ከቤታችን በመጀመርና በተደራጀ መንገድ በመንቀሳቀስ አዲሱን የትምህርት ዘመን ለልጆቻችንም ለኛም የስኬት ዘመን ማድረግ እንችላለን! ትምህርት ቤት ሲከፈት ልናደርጋቸው የሚገቡ 10 ዋና ዋና ተግባራት፦ 1. የእንቅልፍና የጊዜ ሰሌዳን ማስተካከል፦ ከትምህርት ቤት መከፈት በፊት (ወይም እንደተከፈተ ወዲያውኑ) የእንቅልፍ፣ የመነሻ እና የምግብ ሰዓትን በስዕላዊ መርሃ-ግብር (Visual Schedule) በማስደገፍ ማስተካከል፤ ይህም የልጆችን የሽግግር (Transition) ጭንቀት ይቀንሳል። 2. አካባቢውንና መንገዱን አስቀድሞ ማስተዋወቅ፦ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ወይም በእረፍት ቀናት ትምህርት ቤቱን፣ መጫወቻውን፣ መጸዳጃ ቤቱን እና ክፍሉን አብሮ መጎብኘት 3. የእረፍትና የጥናት ቦታ ማዘጋጀት፦ ልጅዎ ከትምህርት ቤት ሲመለስ አእምሮውን የሚያሳርፍበት፣ ከከፍተኛ ድምፅና ጫጫታ የጸዳ (Sensory-friendly) የሆነ የራሱ ቦታ በቤት ውስጥ ማዘጋጀት። 4. የ1-ገፅ ግለ-ታሪክ (Profile) ማዘጋጀት፦ የልጃችንን ማንነት፣ የሚወዳቸውንና የሚጠላቸውን ነገሮች፣ የመግባቢያ መንገዱን (በቃል፣ በምልክት ወይም በስዕል/PECS)፣ የሚያበሳጭበትን (Triggers) እና ሲበሳጭ የሚያረጋጉትን ዘዴዎች የያዘ አጭር መረጃ አዘጋጅቶ ለመምህራኑና ለረዳቶቻቸው መስጠት። 5. የግል ትምህርት ዕቅድን (IEP) መከለስ፦ ባለፈው ዓመት የተቀመጡ ግቦች፣ የሚያስፈልጉ የትምህርት ድጋፎችና የቴራፒ አገልግሎቶች (የንግግር፣ የባህሪ ወይም ሌላ ድጋፍ) በአዲሱ ክፍል ውስጥ በትክክል መካተታቸውን ማረጋገጥ። 6. የመረጃ ፎልደር/ፋይል ማደራጀት፦ የልጆቻችንን የህክምና ማስረጃዎች፣ የቴራፒ ግምገማዎችና ከትምህርት ቤት ጋር የሚደረጉ ውይይቶችን በየጊዜው የምንመዘግብበት አንድ ፋይል አዘጋጅተን መያዝ። 7. የዕለት ተዕለት መረጃ መለዋወጫ ዘዴ መዘርጋት፦ ልጅዎ በቀን ውስጥ ያሳለፈውን ሁኔታ ለማወቅ ከክፍሉ መምህር ጋር የመልእክት ልውውጥ (Communication Notebook) ወይም የስልክ/መልእክት መንገድ አስቀድሞ መወሰን። 8. የጤናና የትራንስፖርት ሁኔታዎችን ማረጋገጥ፦ ልጅዎ የሚወስደው መድኃኒት ካለ፣ አለርጂ ወይም ድንገተኛ የጤና ሁኔታ ካጋጠመው ምን መደረግ እንዳለበት ለትምህርት ቤቱ ነርስ፣ ለመምህራንና ለትራንስፖርት አጋዦች ግልጽ መመሪያ መስጠት። 9. ቅድመ-ግምገማ ቀጠሮ መያዝ፦ ትምህርት ከተጀመረ ከ2-3 ሳምንታት በኋላ ልጆቻችን ከአዲሱ ክፍል ጋር እንዴት እንደተላመዱ ለመገምገም ከመምህራኑ ጋር አጭር ውይይት ማድረግ። 10. ከትምህርት ቤቱ ድጋፍ ሰጪዎች ጋር መተዋወቅ፦ ከዋናው መምህር በተጨማሪ የልዩ ፍላጎት አስተባባሪውን (Coordinator)፣ የትምህርት ቤቱን ሳይኮሎጂስት እና የቴራፒስቶች አስቀድሞ በማናገር ግንኙነት መፍጠር። ለወላጆች 👇👇👇 ልጅዎ የራሱ የሆነ የዕድገት ፍጥነት አለው! ከሌሎች ልጆች ጋር አያወዳድሩት። ትንንሽ ለውጦቹንና ስኬቶቹን ያከብሩ። እርስዎ የልጅዎ የመጀመሪያውና ዋናው አስተማሪ በመሆንዎ ስለ ልጃችሁ መብትና ፍላጎት ለመጠየቅና ለመሞገት ፈጽሞ አያመንቱ! መልካም አዲስ አመት! መልካም የትምህርት ዘመን! ይህን መረጃ ሌሎች ወላጆች እንዲጠቀሙበት ሼር (Share) በማድረግ ይተባበሩ! https://t.me/gohcenters

🎧 የዋኖስ የ2018 ዓ/ም ምርጥ አልበሞች 🎶 ፩ | ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) = ኢቶሪካ ፪ | ኃይሉ አመርጋ (ኃይሉ ጃኖ) = አኹን ፫ | ሮቤል ሚደቅሳ = ከበራፍ ፬ | ቤተልሔም ሸርፈዲን
🎧 የዋኖስ የ2018 ዓ/ም ምርጥ አልበሞች 🎶 ፩ | ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) = ኢቶሪካ ፪ | ኃይሉ አመርጋ (ኃይሉ ጃኖ) = አኹን ፫ | ሮቤል ሚደቅሳ = ከበራፍ ፬ | ቤተልሔም ሸርፈዲን = ደስተኛ ፭ | ተዓምር ግዛው = በፍቅር በ2019 ዓ/ም በጉጉት የምጠብቃቸው አልበሞች፦ 🎵 የድምፃዊ ኢሳያስ ታምራት = ታድዬ (መስከረም 08) 🎵 የድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ከወራት በኃላ የሚለቀቀው አልበም #favorite_Albums #Album_of_the_year ዋኖስ መስፍን | @WanosMesfin

እናንተም ለመተባበር ታግዙኛላችሁ!
እናንተም ለመተባበር ታግዙኛላችሁ!

እንኳን ለ2019 ዓ/ም የዘመን መለወጫ አደረሳችሁ! ውድ ቤተሰቦቼ፦ 🌼 በአዲስ ዓመት፦ የተዘጉ በሮች ፥ የተከለከሉ ደጆች ይከፈቱ፣ በቤት ውስጥ የቀሩ ፥ የታሠሩ እጆች ይፈቱ። 🌼 በአዲስ ዓመት፦
እንኳን ለ2019 ዓ/ም የዘመን መለወጫ አደረሳችሁ! ውድ ቤተሰቦቼ፦ 🌼 በአዲስ ዓመት፦ የተዘጉ በሮች ፥ የተከለከሉ ደጆች ይከፈቱ፣ በቤት ውስጥ የቀሩ ፥ የታሠሩ እጆች ይፈቱ። 🌼 በአዲስ ዓመት፦ የተዛባ አመለካከት ፥ ትኩረት መንፈግና ማግለል፣ አለማካተትና አለማሣተፍ ፥ ይተኩ በመቀበል። 🌼 በአዲስ ዓመት፦ የልጆቻችን የተስፋ ብርሃን ይብራ፣ በጋራ ቆመን ለለውጣቸው እንሥራ። ልዩ-ፍላጎት ያላቸው ዜጎች በአዲስ ዓመት የተሻለ ትምህርት፣ ሕክምና፣ የሥራ ዕድል፣ የማኅበረሰብ ተቀባይነትና ተሣታፊነት የሚረጋገጥበት እንዲሁም የሁሉም ማኅበረሰብ ግንዛቤ የሚሻሻልበት እንዲሆን እየተመኘው፤ ውድ ወላጆች፣ ተንከባካቢዎች፣ ባለሞያዎች፣ ባለድርሻ አካላት እና ወዳጆቼ ዓመቱ የሰላም፣ የደስታ፣ የትብብርና ለልጆቻችን በጋራ ሆነን የምንሠራበት እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ። ዋኖስ መስፍን | @WanosMesfin

🟢 መላ ልዩ-ፍላጎት ላላቸው ታዳጊዎች! 🟡 መላ ለወላጆች! 🟢 መላ ለሁሉም አካል-ጉዳተኞች! 🟡 መላ ለሀገራችን የትምህርትና የሕክምና ሥርዓቶቻችን! 🟢 መላ ለማህበረሰባችን ግንዛቤ! መላ - መ
+1
🟢 መላ ልዩ-ፍላጎት ላላቸው ታዳጊዎች! 🟡 መላ ለወላጆች! 🟢 መላ ለሁሉም አካል-ጉዳተኞች! 🟡 መላ ለሀገራችን የትምህርትና የሕክምና ሥርዓቶቻችን! 🟢 መላ ለማህበረሰባችን ግንዛቤ! መላ - መፍትሔ - ለውጥ
በአዲስ ዓመት በአዲስ ነገር ይጠብቁን! 🌼
አቶ ዋኖስ መስፍን የመላ የልዩ-ፍላጎት አገልግሎት (Mela Special Needs Service) መሥራች 🤳 0919484604 | 0717484604 ቴሌግራም | ፌስቡክ | ቲክቶክ | ዩቲዩብ

As a part of my advocacy works i have completed the preparation of making AI music album. I kindly invite you to be part of i
As a part of my advocacy works i have completed the preparation of making AI music album. I kindly invite you to be part of it by joining me " the press release" live streaming program. Have your questions with you and attend the program. Please invite others if you thought this is worth attending. Namaste 🙏

ዛሬ በመዓከላችን የአመቱን ፕሮግራም አጠቃለልን! በአመቱ ከልጆቻችን ጋር የተጓዝነው ጉዞ ከማስተማርም በላይ፤ የፅናት፣ የፍቅር እና የየዕለት ትናንሽ ድሎች ማዕበል ነበር። እያንዳንዱ ልጅ የራሱ የሆነ
+4
ዛሬ በመዓከላችን የአመቱን ፕሮግራም አጠቃለልን! በአመቱ ከልጆቻችን ጋር የተጓዝነው ጉዞ ከማስተማርም በላይ፤ የፅናት፣ የፍቅር እና የየዕለት ትናንሽ ድሎች ማዕበል ነበር። እያንዳንዱ ልጅ የራሱ የሆነ ልዩ ዓለም፣ ልዩ ፍጥነት እና ልዩ ችሎታ እንዳለው በመገንዘብ፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንጓዝ አሳልፈናል። ዛሬ የዚህን ዓመት የሥራ ዘመን በደማቅ ሁኔታ ስንጠቃለል፤ ልጆቻችን ያሳዩትን አስደናቂ ለውጥ ስናይ ልባችን በኩራት ተሞልቷል። ይህ ስኬት የእኛ ብቻ ሳይሆን የማዕከላችን ቀናተኛ ባለሙያዎች፣ በየዕለቱ ከእኛ ጋር አብረው የተጉት የልጆቻችን ቤተሰቦች እና ለዚህ መልካም አላማ አብረውን ለቆሙ አጋሮቻችን ሁሉ የተጋራ ድል ነው። ለልጆቻችን ፍቅርን፣ ጊዜንና ትዕግስትን ለሰጣችሁ ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን። ውድ ልጆቻችን ደግሞ በእረፍት ሰዓታቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መልካም ጊዜ እንዲያሳልፉ እንመኛለን። በአዲስ ጉልበት፣ በታደሰ ተስፋና በላቀ ዝግጅት ለሚቀጥለው ዓመት (መስከረም 4) እንገናኛለን! #specialneeds #inclusion #gohcenter#addisababa #childrenlove #empoweringeveryChild #embracingeveryNeeds

እንዳልከፋ ተራኪ፡ ዋኖስ መስፍን @WanosMesfin

Голосове повідомлення03:50

Голосове повідомлення03:50

የእርስዎ የወላጅነት ዘዴና ዘይቤ (Parenting Style) ልዩ-ፍላጎት ባለው ልጅዎ ላይ ተፅዕኖ እንዳለው አስተውለዋል? ወላጆች/አሳዳጊዎች ለልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት ቁልፍ ሚና አላቸው። የወላጆችና የልጆች ግንኙነት (Parent-Child Relationship) በተለይም በልጆች የቀዳማይ የልጅነት ወቅት (Early Childhood Period) ጤናማና የተጠናከረ ካልኾነ መዘዙ አስቸጋሪና ከባድ ይኾናል። ብዙ-ጊዜ ልዩ-ፍላጎት ያለው ልጅ መኾኑ ሲታወቅ ሊደርሱ የሚችሉ ሥነ-ልቦናዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ማለትም፦ ለረዥም ጊዜያት/ዓመታት ችግሩን ሳይቀበሉ መቅረት፣ የቤተሰብ መበታተን፣ የተረጋጋና የተጠና ጥረት አለማድረግ ወ.ዘ.ተ በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች የልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት፣ ተገቢ ድጋፍ/ቴራፒ (Intervention) የማግኘት ዕድል በእጅጉ ይቀንሳል። በዕድገተ-ሰብዕ የሥነ-ልቡና ጥናት (Developmental Psychology) ዋና ዋና የልጆች የአስተዳደግ ዘይቤዎች፦ 1. ወላጅ-መር የአስተዳደግ ዘይቤ እነዚህ ወላጆች ልዩ-ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ፍላጎት፣ ዝንባሌ እና ጥያቄ የማያዳምጡ ብሎም ጥንካሬና ድክመቶቻቸውን ሳይለዩ እንደነሱ ፍላጎት ብቻ የሚያሳድጉ ናቸው። በዚህም ልጆቹ የሰው ጥገኛ፣ ከሰው የሚጠብቁ ይኾናሉ። 2. ነፃነት የበዛበት የአስተዳደግ ዘይቤ እነዚህ ወላጆች ልጆች በተሣሣተ ሩቲን ውስጥ ሲገቡ የማያርሙ፣ አላስፈላጊ ባህርይ ሲያሳዩ ችላ የሚሉ፣ አብዝተው ነፃነት የሚሠጡ ናቸው። 3. አሣታፊያዊ የአስተዳደግ ዘይቤ እነዚህ ወላጆች የልጆቻቸውን ጥያቄ የሚያስተናግዱ፣ የሚያሣትፉ፣ ሚዛናዊ የሆኑና ሕይወታቸውን በፍላጎታቸው ላይ ተመርኩዘው እንዲኖሩ የሚያስችሉ ናቸው። 4. ቁብ-የለሽ የአስተዳደግ ዘይቤ ልጆቹ ቴራፒ እንዳያገኙ በቤት ውስጥ የሚተዉ፣ እክሎቻቸው ለመቅረፍ ምንም የማይጥሩ፣ በልጃቸው ላይ ምንም ፍላጎትና ፍቅር የሌላቸው ናቸው። ሌሎች፦ Helicopter Parenting, Attachment Parenting, Gentle Parenting, Tiger Parenting, SnowPlow Parenting, Free-Range Parenting, Neglectful Parenting, Blending Parenting, Single parent, Nuclear Family, Extended Family, Stepfamily ... ተጠቃሽ ናቸው። ታድያ ለልጅዎ ምን አይነት ዘይቤ/ዘዴ አለዎት? አሉታዊ የአስተዳደግ ዘይቤ ልዩ-ፍላጎት ባላቸው ልጆች ላይ የሚከተሉትን ተፅዕኖዎች ሊያሳድር ይችላል፦ ▹ በፍጥነት ቅድመ-መፍትሔ (Early Intervention) እንዳይሰጥ፣ ▹ ችግሩ/እክሉ እንዲባባስ፣ ▹ ተጓዳኝ እክሎች እንዲከሱቱ፣ ▹ ድርብርብ/ውስብስብ ዕድገት እንዲኖር፣ ▹ ለረዥም ጊዜ የማይፈታ መዘዝ፣ ▹ ቴራፒው/ትምህርቱ ላይ ተፅዕኖ ይፈጥራል። በመኾኑም ሁሉም ወላጅ ለተሳካ እና ጤናማ የወላጅነትና የአስተዳደግ ዘዴ የወላጅ ውጤታማ ማድረጊያ ሥልጠና (Parent Effectiveness Training-PET) ቢሠለጥኑ፣ ባለሞያ ቢያማክሩ እና አጠቃላይ የግልና የቤተሰብ ደኅንነታቸውን በመጠበቅ ለልጆቻቸው ዕድገትና ድጋፍ (Intervention) ሊሠሩ ይገባል።