es
Feedback
WANOS MESFIN - ዋኖስ መስፍን

WANOS MESFIN - ዋኖስ መስፍን

Ir al canal en Telegram

WANOS MESFIN - ዋኖስ መስፍን @WanosMesfin @WanosMesfinChat  +251919484604 - @WanosM

Mostrar más
871
Suscriptores
-124 horas
-37 días
-330 días
Archivo de publicaciones
ትናንት ኢኮ ኦቲዝም ኢትዮጵያ ከአሊ ቢራ ፋውኔዴሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የአቅም ግንባታና የሙያ ማሻሻያ፣ የዓለም-አቀፍ እና የሀገር-አቀፍ ትሥሥር እና የ4 ወር የሥልጠና ፕሮግራም የመጀመሪያ ክ
+4
ትናንት ኢኮ ኦቲዝም ኢትዮጵያ ከአሊ ቢራ ፋውኔዴሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የአቅም ግንባታና የሙያ ማሻሻያ፣ የዓለም-አቀፍ እና የሀገር-አቀፍ ትሥሥር እና የ4 ወር የሥልጠና ፕሮግራም የመጀመሪያ ክፍለ-ጊዜ ተጀምሯል። መምህር ሃሌሉያ አየለ ይህንን ዕድል እንዳገኝ ስለረዳኸኝ ከልብ አመሠግናለሁ።

ትናንት በአዳማ (ናዝሬት) ሊዲያ የቴራፒ እና የሥልጠና አገልግሎት በደይ ሳታር አካዳሚ ለ1 ወር በተዘጋጀው የልዩ ፍላጎት ልጆች የሰመር ካምፕ የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ ተገኝቼ ለወላጆች ልጆቻቸውን በቤ
+2
ትናንት በአዳማ (ናዝሬት) ሊዲያ የቴራፒ እና የሥልጠና አገልግሎት በደይ ሳታር አካዳሚ ለ1 ወር በተዘጋጀው የልዩ ፍላጎት ልጆች የሰመር ካምፕ የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ ተገኝቼ ለወላጆች ልጆቻቸውን በቤት ውስጥ እንዴት ማገዝ፣ ቴራፒ መሥጠት እንደሚችሉ የግማሽ ቀን ሥልጠና ሰጥቻለሁ፤ በአዳማ ከተማ ያለው የልዩ ፍላጎት አገልግሎት እየተስፋፋ በመምጣቱ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ።

ተወዳጅ አልበሞች | Wanos's favorite albums 🎵 'ለራስህ ነው' - ጃኖ ባንድ 🎵 'የኔ ዜማ' - ዳዊት ፅጌ 🎵 'ያምራል ሀገሬ' - ስለሺ ደምሴ (ጋሽ አበራ ሞላ) 🎵 'ከበራፍ' - ሮቤል ሚደቅሳ 🎵 'ጋፊ ኮ' - ጉቱ አበራ 🎵 'አስቻለ' - አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) 🎵 'ኢትዮጲክስ' - እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ 🎵 'አኹን' - ኃይሉ አመርጋ 🎵 'የማ' - የማርያም (የማ) 🎵 'ዝምታ' - ቴዎድሮስ ታደሠ 🎵 'ኢቶሪካ' - ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) #favorite_Albums #Collections ዋኖስ መስፍን | @WanosMesfin

የ2ኛ ዙር የ3 ወር የኦቲዝም ሥልጠና ተጠናቀቀ ለ3 ወር የኦቲዝም ትምህርትና ቴራፒ ላይ በ11 የተለያዩ ኮርሶች ሲማሩ የቆዩ ሠልጣኞች እሑድ - 03/12/2018 ዓ/ም የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠ
+9
የ2ኛ ዙር የ3 ወር የኦቲዝም ሥልጠና ተጠናቀቀ ለ3 ወር የኦቲዝም ትምህርትና ቴራፒ ላይ በ11 የተለያዩ ኮርሶች ሲማሩ የቆዩ ሠልጣኞች እሑድ - 03/12/2018 ዓ/ም የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠናቋል። ሥልጠናው በአካል ቅዳሜና እሑድ የተሠጠ ሲሆን የወላጆችንና የባለሞያዎችን የሙያ ብቃት፣ የአቅም ግንባታና ግንዛቤ ለማሻሻል የላቀ አስተዋጽኦ አድርጓል። ሥልጠናውን ከዚህ በታች በቀረቡት አማራጮች በመመዝገብ መሠልጠን ይችላሉ፦ 1. ቅዳሜ እና እሑድ በጠዋት ፈረቃ - ከ3:00 - 6:00 2. ቅዳሜና እሑድ በከሰዓት ፈረቃ - ከ7:ዐ0 - 10:00 3. በኦንላይን - ምሽት ማክሰኞ፣ ሐሙስ፣ ቅዳሜ - ከ1:30 - 4:00 ለበለጠ መረጃና ለመመዝገብ እነዚህን አማራጮች መጠቅም ይችላሉ፦ በስልክ፡ +251952118642 | +251717484604 በቴሌግራም፡ @MelaSpecialNeedsServiceaccount

ጀሮ-ገብ ሽሮፖች 🎧 🎶 ዱንያ - አንተነህ ምናሉ 🎶 ከተራራው ማዶ እና እንግዳ - ሃይሉ አመርጋ 🎶 ስሚያቸው - ታረቀኝ ሙሉ 🎶 እንደ ቀልድ - ሮቤል ሚደቅሳ 🎶 ችግርሽ በእኔ አልፏል - አለማየሁ እሸቴ 🎶 ሰው መሠረቱ እና አካሌ - ኤፍሬም ስዩም 🎶 በመስኮቱ እና ማን ዘንድ ይደር - ቴዎድሮስ ካሳሁን 🎶 ሰምቶ ዝም አለ እና አልቦ - ቴዎድሮስ ታደሠ 🎶 ነን በርባዳ - ጉቱ አበራ 🎶 የዘገየሽበት - ስለሺ ደምሴ 🎶 አንገር ወሎ እና ዊያ ዊያ - አስቻለው ፈጠነ 🎶 ጉብልዬ - ማስተዋል እያዩ 🎶 እየተኙ ነቁ - ፍሬው ኃይሉ 🎶 ደስ አለኝ እና ቃልኪዳን - ዳዊት ፅጌ 🎶 እንጃ - አዲስ ለገሠ #Wanos_playlist ዋኖስ መስፍን | @WanosMesfin

በሥነ-ልቦናው ዓለም ከሚያስገርሙኝ ኀልዮቶች (Theories) መካከል በሥነ-ሰብዕ ዕድገት ላይ በስፋት የሚታወቀው ጂያን ፒያዤ Cognitive Development theory አንዱ ነው። በዚህ ንድፈ-ሐሳብ እና የጥናት ውጤት መሠረትም ሕፃናት ወደዚህች ዓለም ከመጡ በኃላ ዓለምን፣ ተፈጥሮን (Physical World) የሚረዱበትን - እያወቁ የሚመጡበትን መንገድን ዘርዝሯል። ሕፃናት በለጋነታቸው ምንም ነገር እንደ ስፖንጅ - ያለ ዕውቀት እያዳበሩ አይመጡም፤ ይልቁንስ ሲድሁ፣ ሲነካኩ፣ እሳት ሲፈጃቸው፣ ያንንም-ይሄንንም ሲቀምሱ፣ በሁሉም የስሜት ሕዋሶቻቸው መረጃ ሲቃርሙ ዓለምን የበለጠ እየተረዷት ይመጣሉ። የፅንሰ-ሐሳቡ ባለቤት ፒያዤ ይህ የዕድገት ምዕራፍ እስከ 6 - 8 ዓመት ድረስ ይዘልቃል ይለናል። የዕድገት ምዕራፎች በሕፃናት 1.  በስሜት ሕዋሶች በኩል ዓለምን መተዋወቅ (The Sensorimotor stage)፡ በዚህ የዕድገት ምዕራፍ ከውልደት እስከ 2 ዓመት ያለውን ያካትታል። ዓለምን በስሜት ሕዋሶቻቸው በኩል ያገኟታል። መንቀሳቀሳቸው ደግሞ ዋነኛው የመረዳታቸው Pillar ነው። ◦ለድንገቴ ተግባራት አረዳዳቸው እያደገ መሄድ ( Reflexes to intentional Actions) ◦በመሞከርና በመሳሳት መማር (Trial and Error Exploration) ልጆች በዚህ ጊዜ ከተለያዩ ዕቃዎች ጋር እየበጠሱ፣ እየሰበሩ፣ እየጣሉ፣ እየገነጠሉ የሚማሩበት ጊዜ ነው። ◦ አንድ ዕቃ መጀመሪያ የተቀመጠበት ቦታ ብቻ ነው የሚገኘው ብሎ ማሰብ (Object permanence) ◦ በአዕምሯቸው የተለያዩ ነገሮችን መሳል የሌለን ነገርንም ቢሆን ለምሳሌ፦ ስልክ ሲይዙ እናታቸውን እየወሩ ሲመስላቸው (Mental Representation) 2. The PreOperational Stage ከ2-7 ዓመት ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሲኾን ልጆች ቋንቋን በምልክቶችና ከግዑዝ አካላት ጋር በማያያዝ ወይም በመወከል እየተረዱ ይመጣሉ፤ ምንም እንኳ ያልበሰለ ቢሆንም Abruptly 1. Symbolic Function ሁሉን ነገር በSymbol መወከል፣ መግለፅ ወይም በዐይን የማይታዩ በአካል ያላዩትን በሌላ ዕቃ አስመስሎ መግለፅ። ለምሳሌ፦ በመኪና ፈንታ በማንኛውም ካርቶን ቭቭቭቭቭ.. እያረጉ በእጅ መንዳት፣ በጎራዴ ቦታ በትንሽ እንጨት መጫወት ወዘተ 2. Egocentrism ልጆች የሌሎች ሰዎችን ዕይታ (point of view) መረዳት ሲቸገሩ ለምሳሌ፦ የተደበቁ መስሏቸው ወይም አያዩኝም ብለው ፊትለፊት ከሚገኝ ሰው ጀርባ መደበቅ፣ ተደብቄያለሁ ብሎ በማሰብ ፊትን በእጅ መሸፈን 3. Animism ልጆች ሕይወት የሌላቸው ነገሮችን ማለትም ዕቃዎች፣ ቁሳቁሶች እና ማንኛውም ነገሮችን ሕይወት እንዳላቸው፣ እንደ ሰው ስሜት እንዳላቸው አድርጎ ማሰብ። ለምሳሌ ፀሐይ እየተከተለቻቸው ሲመስላቸው፣ ደመናው እየተከተላቸው ሲመስላቸው፣ ያደናቀፋቸው ዕቃ እንዲቀጣ በመፈለግ ሲመታ (ቱ.. በል ይኸው መታሁልህ ) ሲባሉ የእውነት ሲመስላቸው ወዘተ 4. Centration ልጆች ትኩረት የሚሠጡት ትኩረት ለሳባቸው ሲሆን ለምሳሌ በሁለት ብርጭቆ ላይ ተመሣሣይ መጠን ያላቸው ውሃ ቀድተን ብናስቀምጥ አንዱ ብርጭቆ ቁመቱ ረዘም ያለ እና ጠባብ ሌላኛው አጭርና ሰፊ ቢሆን ልጆች ግን ብዙ ውሃ ያለው ረዥሙ ላይ ነው ብለው ማሰብ 5. Lack of conservation ስለመጠን እና ብዛት አለመረዳት ዋኖስ መስፍን | @WanosMesfin

ዋኖስ ሆይ ዘመኑ ከፍቷል! ራስህን ከNew Ager ከCult ከHypnotist ከCiropracter ከPsudio Prophet ከPsudio Scence ልምምዶች ራስህን ጠብቅ!

ውድ ቤተሰቦቼ በተለይ የልዩ-ፍላጎት ማህበረሰብ በሙሉ እንደሚታወቀው በልዩ-ፍላጎት አገልግሎቶች ላይ ሳይንሳዊ እና የውጭ ቋንቋዎችን ወደ አማርኛ ቋንቋ መመለሱ/መተርጎሙ አስቸጋሪ እና በተግባቦት ላይ
ውድ ቤተሰቦቼ በተለይ የልዩ-ፍላጎት ማህበረሰብ በሙሉ እንደሚታወቀው በልዩ-ፍላጎት አገልግሎቶች ላይ ሳይንሳዊ እና የውጭ ቋንቋዎችን ወደ አማርኛ ቋንቋ መመለሱ/መተርጎሙ አስቸጋሪ እና በተግባቦት ላይ ጉራማይሌ እየፈጠረ ይገኛል። ምንም እንኳን በርካታ የኢንግሊዘኛና ሳይንሳዊ ቃላትን/ሐረጎችን መተርጎም ከባድ ቢሆንም ለእኛ ሀገር በሚሆን መልኩ አስማምቶ፣ ከቋንቋና ሥነ-ፅሑፍ ሙያተኞች፣ ከዘርፉ ልዩ ልዩ ባለሞያዎች በማሠባጠር አገባባዊ ፍቺያቸው የሰላ፣ ተስማሚ የሆኑ ትርጉም ማበጀት ያሻናል። በመኾኑም በግሌ በቻልኩት መጠን በየቀኑ 10 የሚደርሱ ከኦቲዝምና ሌሎች የአዕምሮ ዕድገት ኹኔታዎች ጋር የተያያዙ ቃላትን ከሙያ ባልደረቦቼ ጋር እየመከርኩ የማጋራችሁ ይሆናል። ለዛሬ 10 ቃላትን እንመልከት፦ ፩ | Special need፡ ልዩ-ፍላጎት ፪ | Autism spectrum disorder፡ ኦቲዝም ኅብር የአዕምሮ ዕድገት መዛባት ፫ | Neurodevelopmental Disorders፡ የአዕምሮ ዕድገት እክሎች ፬ | Intellectual developmental disorder፡ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ፭ | Attention deficit-hyperactivity disorder፡ ትኩረት የማጣትና ያለመረጋጋት እክል ፮ | Communication disorders፡ የተግባቦት እክሎች ፯ | Inclusive education፡ የአካቶ ትምህርት ፰ | Specfic learning Disorder፡ የመማር እክሎች ፱ | Developmental Delay፡ የዕድገት መዘግየት ፲ | Motor Disorders፡ የእንቅስቃሴ እክሎች
ሁሉም ትክክል ላይሆኑ ይችላሉ፤ በእኔ ዕውቀትና ዕይታ ላይ ብቻ የተመሠረቱ ናቸው። ማረም ወይም ማስተካከል ትችላላችሁ!
ዋኖስ መስፍን | @WanosMesfin

Session 2 training for our volunteers on ABA Therapy techniques by Mr. Wanos mesfin Mela special need service co-founder and
+7
Session 2 training for our volunteers on ABA Therapy techniques by Mr. Wanos mesfin Mela special need service co-founder and general manager

Cinema 🫶
Cinema 🫶

የረቂቅ ሙዚቃ ቀማሪዋ የእማሆይ ፅጌ ማርያም (የውብዳር ገብሩ) ሁለት ተወዳጅ የፒያኖ ሙዚቃዎችን ያከተተ የሕንድ (Malayalam cinema industry) ፊልም ነው All we Imagine as l
የረቂቅ ሙዚቃ ቀማሪዋ የእማሆይ ፅጌ ማርያም (የውብዳር ገብሩ) ሁለት ተወዳጅ የፒያኖ ሙዚቃዎችን ያከተተ የሕንድ (Malayalam cinema industry) ፊልም ነው All we Imagine as light (2024) ከቅርብ ጊዜ ወዲኽ በሕንዳውያን የሲኒማ ታሪክ ውስጥ የራሳቸውን አሻራ እያኖሩ ያሉት የማላያላም (Malayalam) ቋንቋ ተናጋሪዎች ሥራዎች ናቸው። የፊልም ዘውግ፣ አተራረክና ፍልስፍናዎቻቸው በጥቂቱም ቢኾን ካየዃቸው የኢራን ፊልሞች ይመሳሰሉብኛል። በአጭር ጊዜ ውስጥም ተቀባይነትና ተመራጭ ፊልሞችን እያቀረቡልን ነው። ፓያል ካፓዲያ የ'ዚህ ፊልም ቀማሚ ናት። ዝግጅቷ አስደማሚ ነው (በተለይ ለ'Existentialism' እና Stoicዎች :) ያው በሥራዎቿ 'Post-Modernist'ና 'Feministic Perspective' ቢኖሩም። (በላውራ መልቪ ተነሽጣ ይኾን?) ተመልካቾች የተለያየ ሒስና አስተያየት ቢሠጡም አዘጋጇ ማስተላለፍ የፈለገቸው 'Sociological Theme' እንዳለ ይሰማኛል፤ ኢንደስትሪው ላይም ማስጀመር የፈለገቸው የሥነ-ራዕይ የአተራረክ ቅርፅና አወቃቀር (Narrative Style and structure) ይኖራል። የተዋናዮቹ ብቃት የሚደነቅ ነው፤ በተለይ በ'Chhaya Kadam' በ'Laapataa ladies , Andhadun' እና ሌሎች ስለምወዳት ፊልሙ ዝግ ያለ የትዕይንት ፍጥነት፣ ዝቅተኛ አያያዥ ታሪኮች መጠን (Subplot)፣ ምናልባትም ለአንዳንዶች አወዛጋቢ የታሪክ አቀራረብ እንዳለው በስፋት ተገልጿል። ചിത്രം കാണുക - chithram kaanuka

ፀሎተ ልድያ.mp31.64 MB

ሳይንስ የተረጋገጠ እውቀት እንጂ፣ ያልሠለጠኑ ሰዎች የፈጠራ ትርክት አይደለም!

Repost from Jafer Books 📚
" የማይናገረው ልዑል " የተሰኘው መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል :: መጽሐፉን በሁሉም መደብሮቻችን ያገኙታል !
" የማይናገረው ልዑል " የተሰኘው መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል :: መጽሐፉን በሁሉም መደብሮቻችን ያገኙታል !

ትርጉም አልባ ግጥም ሰሞኑን ግጥም - ግጥም ብሎኛል የበረከት በላይነህ 'የመንፈስ ከፍታ' ይሁናል የነሸጠኝ። ስሙኝማ? ግጥም አልችልም፤ በቃ ምንም አላውቅም፣ እና ይህንን ከዚህ በታች ያለ ትርጉም አልባ ዝባዝንኬ ግጥም እንደ አጉል ግጥመኛ ( 😂 ይቅርታ ለካ ገጣሚ ነው ) ፣ ግጥም ላይ እንደሚራቀቅ ሰው ተሞዳምጃለሁ። የሚገርመው አጉል የተመሠጥኩ ያህል የሚሰማኝ ነገር ነው። 😁 Even ቃላቱን 'ራሱ አላውቃቸውም።                  ሀገር ፡ እንደ ፡ ልምቅ፣              ክስቴ ፡ ተቀርድዶ ፡ ሊደቅ፣             ፍቅረ-ንዋይ ፥ ሲንደቀደቅ፣                      ባሕረ ፥ ስላቅ፣                     አዋዘ ፥ ሰንደቅ። መግፍዔ ፡ ክስቴ፦                ሐሩር ፡ ላይ ፡ ጎኅ ፡ ሲቀድ፣           ወለል ፡ ላይ ፡ ተነጥፎ ፡ ሲወድቅ። እንዲኽ ሞሸረ፦              ❝ በአንድ ፡ ቀና ፡ ቀን ፡ ቅኔ ፡ ተቀኝቼ፣     ቀና ፡ ስል ፡ ደስ ፡ አለኝ ፡ ቅን ፡ ሰው ፡ ተመልክቼ ❞                   ክስው፥ድልው              ለሀገር ፡ እንድደምቅ፣          ፃዕር ፡ ላይ ፡ እንዳልወድቅ።       ኑባሬ ፡ ብርሃን፤ እንደ ፡ መብረቅ፣     ነፋሰ-ፅልመት ፡ ሲገረድድ ፥ ሲለቅ።                        ፨፨፨      ክሴተ-ልዑል ፡ መግፍዔ ፡ ሲራይ፣        አዋዝ-ግስው ፡ ክስት ፡ ለድይ። መፍክሬ ፥ ክስቴ፦        ፅቡቅ ፡ ፅቡቅ ፡ አለ ፡ ሲዠምር!   ብቅ፥ብቅ ፡ ድሳዌ ፡ ወእንበለ ፡ ሕብር፣   ሥርወ፣ ግስወ ፡ ሀቤየ ፡ ኩሉ ፡ ክብር፣     ሠርቀ፣ አንቀ ፡ ወበ-ዲለ ፡ ድንበር። ቀጠለናም፦ ግርምከ ፥ ግሩምከ!              ፀላዖ ፡ ፅላሎት!      ድርምባ ፡ ድርባቦት! ( ባ'ናቱ ፡ ከናንቦ! )          ቅርፋዔ ፡ ቲና ፡ ዘለከ፣     በንተለ ፡ ቅስትና ፡ አመንከ              ምጣኒ፣ ጽባኒ.. ንቡዔ ፡ ልቡከ ፡ ከመ ፡ ምስትርድምና |ቀባመ። ዋኖስ መስፍን | @WanosMesfin

ርዕስ፡ እንደነገርኩሽ ነው። ገጣሚ/ፀሐፊ፡ በረከት በላይነህ አንባቢ፡ ዋኖስ መስፍን በልምምድ ላይ..