uk
Feedback
ሳይንስኛ ️️

ሳይንስኛ ️️

Відкрити в Telegram

Business + Tech + Science + Inspiration + Psychology

Показати більше
2 254
Підписники
Немає даних24 години
+37 днів
-930 днів
Архів дописів
📘ዘ ሊን ስታርት-አፕ (The Lean Startup) 🔗 በEric Ries የተጻፈው The Lean Startup የተሰኘው ዝነኛ መጽሐፍ፣ አዲስ ንግድ (Startup) ወይም ፕሮጀክት ሲጀመር ከፍተኛ ሀብትና ጊዜ ሳያባክኑ፣ በፈጣን ሙከራ እና ከደንበኛ በሚገኝ እውነተኛ መረጃ (Validated Learning) ላይ ተመስርቶ እንዴት ስኬታማ መሆን እንደሚቻል የሚያስተምር ድንቅ መመሪያ ነው። 🖇 1. የፈጠራ ምልልስ፦ ስራ ➔ ለካ ➔ ተማር (Build-Measure-Learn) አዲስ ሀሳብ ሲኖርህ ሙሉ ምርቱን ለመጨረስ ወራት አትፍጅ። ሀሳብህን በፍጥነት ወደ ምርት ቀይር፤ ደንበኞች እንዴት እንደሚጠቀሙበት ለካ፤ ከውጤቱም ተምረህ ምርትህን አሻሽል። 📘ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ “The fundamental activity of a startup is to turn ideas into products, measure how customers respond, and then learn whether to pivot or persevere.” (የስታርትአፕ ዋና ተግባር ሀሳቦችን ወደ ምርት መቀየር፣ ደንበኞች የሚሰጡትን ምላሽ መለካት፣ እና በመቀጠል መቀየር (Pivot) ወይም መቀጠል (Persevere) እንዳለበት መማር ነው።) 🖇 2. አነስተኛ ጠቃሚ ምርት (MVP - Minimum Viable Product) ምርትህን ሙሉ በሙሉ ፍጹም ለማድረግ አትጠብቅ። የችግሩን ዋና መፍትሔ ብቻ የያዘ አነስተኛ ምርት (MVP) በመስራት በፍጥነት ለገበያ አቅርበው፤ የደንበኞችን እውነተኛ አስተያየት ሰብስብ። 📘ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ “The Minimal Viable Product is that version of a new product which allows a team to collect the maximum amount of validated learning about customers with the least effort.” (አነስተኛ ጠቃሚ ምርት ማለት በጥቂት ጥረት ስለ ደንበኞች ከፍተኛ እውነተኛ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የመጀመሪያው የምርት ደረጃ ነው።) 🖇 3. አቅጣጫ መቀየር ወይስ መቀጠል? (Pivot or Persevere) የሰራኸው ምርት ወይም ያቀድከው የቢዝነስ ሞዴል ከደንበኞች ፍላጎት ጋር ካልተጣጣመ፣ በግትርነት ከመቀጠል ይልቅ በፍጥነት አቅጣጫህን ቀይር (Pivot)። አቅጣጫ መቀየር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ከተማርከው እውነት አንፃር ስትራቴጂህን ማስተካከል ማለት ነው። 📘ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ “A pivot is a structured course correction designed to test a new basic hypothesis about the product, strategy, and engine of growth.” 🖇 4. እውነተኛ ትምህርት (Validated Learning) በወረቀት ላይ የተጻፈ ግምት ወይም በግል አስተያየት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አደገኛ ነው። እውነተኛ ስኬት የሚለካው ከገበያው በእውነተኛ መረጃ በተረጋገጠ ትምህርት ነው። 📘ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ “The only way to win is to learn faster than anyone else.” (ለማሸነፍ ያለው ብቸኛው መንገድ ከማንም በላይ በፍጥነት መማር ነው።) 🛠 አዲስ ቢዝነስ ሲታሰብ ትልቁ አደጋ «ምርቱ አይሸጥም» ብሎ መስጋት ሳይሆን፣ ማንም የማይፈልገውን ምርት በጥራትና በከፍተኛ ወጪ ሰርቶ ማጠናቀቅ ነው። ስለዚህ ሀሳብህን በፍጥነት በትንሽ ወጪ ስራ፣ ለገበያ አቅርበህ ፈትነው፣ ከደንበኞችህ ምላሽ እየተማርክ አሳድገው። #book © ሳይንስኛ

📘 The Lean Startup Book Review
📘 The Lean Startup Book Review

🎞 The Mother Of Monster Movie! (ትምህርት ታገኙበታላችሁ!) #movie © ሳይንስኛ

📗 የ80/20 መርህ (The 80/20 Principle) 📎 በRichard Koch የተጻፈው The 80/20 Principle (ፓሬቶ መርህ) የተሰኘው መጽሐፍ፣ በህይወታችን እና በስራችን ውስጥ ከምናወጣው ጥረት 20% የሚሆነው አብዛኛውን 80% የሚሆነውን ውጤት እንደሚያስገኝ የሚያስረዳና አነስተኛ ጉልበት በማውጣት ከፍተኛ ውጤት ማምጣት የምንችልበትን መንገድ የሚያሳይ ድንቅ መመሪያ ነው። 🔗 1. አነስተኛ ጥረት፣ ከፍተኛ ውጤት (Less Effort, More Results) በማንኛውም መስክ 80% የሚሆነው ስኬት የሚመጣው ከ20% ቁልፍ ድርጊቶችህ ነው። ስለዚህ ብዙ መስራት ሳይሆን ትክክለኛውን 20% መለየትና ትኩረት መስጠት ያሸንፋል። 📗 ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ “The 80/20 Principle asserts that a minority of causes, inputs, or effort usually leads to a majority of the results, outputs, or rewards.” (የ80/20 መርህ እንደሚያረጋግጠው አነስተኛ ቁጥር ያላቸው መንስኤዎች፣ ጥረቶች ወይም ግብአቶች አብዛኛውን ውጤት ወይም ጥቅም ያስገኛሉ።) 🔗 2. በንግድና በስራ ላይ የሚኖረው ጥቅም በማንኛውም ቢዝነስ ውስጥ 80% የሚሆነው ትርፍ የሚመጣው ከ20% ደንበኞች ወይም ምርቶች ነው። 80% የሚሆነው ችግር ደግሞ ከ20% ደንበኞች ወይም አሰራሮች ይመጣል። ትኩረትህን ትርፋማ በሆኑት 20% ላይ አድርግ። 📗ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ፦ “Identify the 20 percent of products or customers that generate 80 percent of profits, and focus relentlessly on them.” 🔗 3. ብልህ እና ሰነፍ ሁን (The Smart -Lazy Approach) እውነተኛ ውጤታማነት ማለት ያለ እረፍት ደክሞ መስራት ሳይሆን፣ ትልቁን ለውጥ የሚያመጡ ጥቂት ነገሮችን አጥብቆ መፈለግና በእነሱ ላይ ብቻ ማተኮር ነው። 📗ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ “Work less, earn more, and enjoy life more by focusing only on what matters most.” 🪭 ከስራህ፣ ከስኬትህ ወይም ከደስታህ 80% የሚሆነውን ድርሻ የሚይዙት ጥቂቶቹ 20% ነገሮች የትኞቹ እንደሆኑ ለይተህ እወቅ። የተቀሩትን ጊዜ በላ ነገሮች በመቀነስ፣ ጥረትህን ከፍተኛ ውጤት በሚሰጡህ ቁልፍ ነገሮች ላይ ብቻ አውለው። 80% (action) ➡️ 20% (result) #book © ሳይንስኛ

📗 The 80/20 Principle Book Review
📗 The 80/20 Principle Book Review

🛡አንድ ሎጎ (አርማ) ለአንድ ድርጅት፣ ምርት ወይም ግለሰብ ከተራ ምስል ያለፈ ትልቅ ትርጉም አለው። ዋና ዋና ጥቅሞቹ የሚከተሉት ናቸው፦ ☑️ 1. የድርጅቱ መታወቂያ (Identity) ነው አንድ ሰው ሲወለድ ስም እንደሚሰጠው ሁሉ፣ ለአንድ ቢዝነስም ሎጎው ዋነኛ ምስላዊ መታወቂያው ነው። ደንበኞች ድርጅቱን ወይም ምርቱን በቀላሉ እንዲያውቁትና እንዲያስታውሱት ያደርጋል። ☑️ 2. የመጀመሪያ ግምት (First Impression) ይፈጥራል ደንበኞች ስለ ድርጅቱ ጥራት፣ ዘመናዊነት ወይም ሙያዊ ብቃት መጀመሪያ የሚረዱት ሎጎውን አይተው ነው። በሚገባ የተሰራ ሎጎ የድርጅቱን ጥንካሬ እና ታማኝነት ወዲያውኑ ያስመሰክራል። ☑️ 3. ከተፎካካሪዎች ለመለየት (Differentiation) በገበያ ላይ ተመሳሳይ ምርት ወይም አገልግሎት የሚሰጡ ብዙ ድርጅቶች አሉ። ሎጎ የእርስዎን ቢዝነስ ከሌሎቹ ለይቶ ለደንበኛው ለብቻው ጎልቶ እንዲታይ ያደርገዋል። ☑️ 4. የብራንድ ታማኝነትን (Brand Loyalty) ይገነባል ቢዝነሱ እያደገ ሲሄድ ደንበኞች በሎጎው ላይ እምነት ያሳድራሉ። ለምሳሌ የሰዎችን ልብስ ወይም ስልክ ላይ ያሉ ታዋቂ ሎጎዎችን ስናይ ወዲያውኑ ጥራቱን እንደምናምነው ሁሉ፣ ሎጎ የደንበኞችን ታማኝነት ያጠናክራል። ☑️ 5. የድርጅቱን መልዕክት እና እሴት ያስተላልፋል ጥሩ ሎጎ በቅርጹ፣ በቀለሙ እና በዲዛይኑ የድርጅቱን አላማ ይገልጻል። ለምሳሌ የፈጣን መላኪያ (Logistics) ድርጅቶች በሎጎአቸው ውስጥ ወደፊት የሚያሳይ ቀስት ወይም የፍጥነት ምልክት በመጠቀም አገልግሎታቸውን ሳይናገሩ በምስል ያስረዳሉ። 🛡ሎጎ የቢዝነስዎ "ፊት" ነው። ሰዎች የእርስዎን ስም ከመያዛቸው በፊት ቀድመው የሚያስታውሱት የሎጎዎን ምስል ነው።
🌬 ዘመኑ ያወጀ LOGO ለማሰራት 📲 አሁኑኑ ያናግሩን የዲጂታል ጉዞዎን አንድ ደረጃ ከፍ ያድርጉ!
🔖 እኛን ለማግኘት፦ 📞 ስልክ ቁጥር፦ 0904002487 📥 ቴሌግራም ቦት: @ElectrospaceBot 🌐 ዌብሳይት: www.electrospacex.com

7 Types of Logo Design Styles
+6
7 Types of Logo Design Styles

📔ዚሮ ቱ ዋን (Zero to One) 🔗 በPeter Thiel (የPaypal መስራች) እና Blake Masters የተጻፈው Zero to One የተሰኘው ዝነኛ መጽሐፍ፣ ነባር ነገሮችን ከመቅዳት ይልቅ ሙሉ በሙሉ አዲስ እና አብዮታዊ የሆኑ ነገሮችን ፈጥሮ ስኬታማ መሆን እንደሚቻል የሚያስተምር ድንቅ የንግድና የፈጠራ መመሪያ ነው። 📎 1. ከዜሮ ወደ አንድ ተጓዝ (0 to 1 vs. 1 to n) ያለውን ነገር ደግሞ መስራት (ከ1 ወደ n መሄድ) አለምን አዲስ ቦታ አያደርሳትም። እውነተኛ እድገትና ስኬት የሚመጣው ማንም ያላደረገውን አዲስ ነገር ከዜሮ ተነስተህ ስትፈጥር (ከ0 ወደ 1 መሄድ) ብቻ ነው። 📍ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ፦ “Doing what we already know how to do takes the world from 1 to n, adding more of something familiar. But every time we create something new, we go from 0 to 1.” (ቀደም ሲል የምናውቀውን ነገር ማድረግ አለምን ከ1 ወደ n ይወስዳታል፤ አዲስ ነገር በፈጠርን ቁጥር ግን ከ0 ወደ 1 እንሄዳለን።) 📎 2. አነስተኛ ሞኖፖሊ (Monopoly) ፍጠር ከሰዎች ጋር በከባድ ውድድር ውስጥ ከመግባት ይልቅ፣ በትንሽ ቦታ/ገበያ (Niche) ላይ ትኩረት አድርገህ ያንን ገበያ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረው። ውድድር የትርፍ ጠላት ነው። 📍ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ፦ “All happy companies are different: each one earns a monopoly by solving a unique problem. All failed companies are the same: they failed to escape competition.” (ስኬታማ ኩባንያዎች በሙሉ የተለያዩ ናቸው—እያንዳንዳቸው ልዩ ችግር በመፍታት ሞኖፖሊ ይሆናሉ፤ የወደቁት በሙሉ ግን አንድ ናቸው—ከውድድር ማምለጥ አልቻሉም።) 📎 3. የራስህ «ሚስጥር» (Secret) ይኑርህ ታላላቅ ቢዝነሶች የሚገነቡት ሌሎች ሰዎች ባላስተዋሉት ወይም ባልተረዱት እውነት/ሚስጥር ላይ ነው። «አብዛኛው ሰው የማይስማማበት አንተ የምታምነው እውነት ምንድን ነው?» የሚለው ጥያቄ የፈጠራ መሰረት ነው። 📍ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ፦ “Brilliant thinking is rare, but courage is in even shorter supply than genius.” (ድንቅ አስተሳሰብ ብርቅ ነው፤ ነገር ግን ድፍረት ከብልህነት ይልቅ እጅግ አናሳ ነው።) 📎 4. የ10 እጥፍ ብልጫ (10x Advantage) አዲስ ምርት ወይም አገልግሎት ስታቀርብ፣ ከነባሩ አሰራር ወይም ተወዳዳሪ በትንሹ የተሻለ ሳይሆን ቢያንስ በ10 እጥፍ የሚበልጥ (10x better) መሆን አለበት። ያኔ ሰዎች አዲሱን ነገር ለመቀበል አይቸገሩም። 📍ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ፦ “As a rule of thumb, proprietary technology must be at least 10 times better than its closest substitute in some important dimension.” 🔗 የሌሎችን ስኬት በመቅዳት ቀጣዩን ቢል ጌትስ፣ ማርክ ዙከርበርግ ወይም ስቲቭ ጆብስ መሆን አትችልም። ስኬት የሚመጣው በውድድር ውስጥ በመሰለፍ ሳይሆን፣ አዲስ እሴት በመፍጠርና ማንም የሌለበትን የራስህን ሞኖፖሊ በመገንባት ነው። #book © ሳይንስኛ

📔 ZERO to ONE BOOK REVIEW
📔 ZERO to ONE BOOK REVIEW

💸 «የገንዘብ ስነ-ልቦና» (The Psychology of Money) በMorgan Housel የተጻፈው The Psychology of Money የተሰኘው ዝነኛ መጽሐፍ፣ ስለ ገንዘብ ያለው እውቀት (Math/Logic) ሳይሆን ሰዎችን ስኬታማ የሚያደርገው ባህሪያቸውና ስነ-ልቦናቸው (Behavior) እንደሆነ የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ ነው። ⚙ Morgan Housel «The Psychology of Money» መጽሐፍ ውስጥ ያሉት 20 ምዕራፎች/የሀብት መመሪያዎች ናቸው። ከታች የተጠቀሱት ከመጽሐፉ የተወጣጡ ዋና ዋና የገንዘብ ስነ-ልቦና ህጎች ናቸው። 🧰 1. ከሀብታምነት ይልቅ ደህንነት ይበልጣል (Staying Wealthy vs. Getting Rich)ገንዘብ ማግኘት ድፍረትና አደጋ መውሰድን ይጠይቃል፤ ሀብትን ጠብቆ ማቆየት ግን ትህትናንና ትጋትን ይጠይቃል። 📿 ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ፦ “Getting money is one thing. Keeping it is another.” (ገንዘብ ማግኘት አንድ ነገር ነው፤ ይዞ ማቆየት ግን ሙሉ በሙሉ ሌላ ነገር ነው።) 🧰 2. የሁለትዮሽ ድምር ተአምር (Compound Interest) በገንዘብ አለም ውስጥ ትልቁ ኃይል ጊዜ ነው። የዋረን ባፌት ታላቅነት የኢንቨስትመንት ብልህነቱ ብቻ ሳይሆን፣ ኢንቨስት ማድረግ የጀመረው ገና በ10 ዓመቱ በመሆኑና ለብዙ አስርት ዓመታት በመቀጠሉ ነው። 📿 ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ፦ “Time is the most powerful force in investing. It turns small amounts into huge sums.” 🧰 3. የ«ይበቃኛል»ን መስመር ማወቅ (Knowing When is Enough) የገንዘብ ውድቀት ዋናው መንስኤ ከሰዎች ጋር ራስን ማወዳደርና ግቡን (Goalpost) በየጊዜው ወደፊት ማንቀሳቀስ ነው። «ይበቃኛል» ማለት ካልቻልክ ውድቀትህ አይቀሬ ነው። 📿 ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ፦ “There is no reason to risk what you have and need for what you don’t have and don’t need.” (የ አለህንና የሚያስፈልግህን ነገር፣ የሌለህንና የማያስፈልግህን ነገር ለማግኘት ስትል አደጋ ላይ የምትጥልበት ምንም ምክንያት የለም።) 🧰 4. ሀብት ማለት የማይታየው ነገር ነው (Wealth is What You Don't See) ሰዎች በውጭ የሚያዩት ውድ መኪና፣ ቤትና ልብስ «ወጪን» (Spending) እንጂ ሀብትን አይደለም። ሀብት ማለት ያልተወጣ፣ ያልተገዛና ለወደፊት ነፃነት የተቀመጠ ገንዘብ ነው። 📿 ከመጽሐፉ የተወሰደ ጥቅስ፦ “Spending money to show people how much money you have is the fastest way to have less money.”   💵 የገንዘብ ነፃነት ማለት የፈለግከውን ነገር ለመግዛት መቻል ሳይሆን፤ የፈለግከውን ነገር፣ ከፈለግከው ሰው ጋር፣ በፈለግከው ቦታ እና ሰዓት ማድረግ የመቻል ነፃነት ነው። ☑️ ሰዎች አንተ የምታሸከረክረውን መኪና እንጂ አንተን አያደንቁህም! #book © ሳይንስኛ

📘 The Psychology of Money Review
📘 The Psychology of Money Review

📘«ብሉ ኦሽን ስትራቴጂ» (Blue Ocean Strategy) ☑️ በ W.Chan Kim እና Renée Mauborgne የተጻፈው ይህ መፅሐፍ፣ ከባድ ውድድር ባለበት ገበያ ውስጥ ከመታገል ይልቅ ውድድር የሌለበት አዲስ የገበያ ሜዳ (Uncontested Market Space) እንዴት መፍጠር እንደሚቻል የሚያስተምር ድንቅ መፅሐፍ ነው። 🛡1. ውድድሩን አላስፈላጊ አድርገው ከተወዳዳሪዎችህ የተሻለ ለመሆን አትታገል፤ ይልቁንም አዲስ መንገድ በመክፈት ውድድሩን ትርጉም አልባ አድርገው። 📘ከመፅሐፉ የተወሰደ ጥቅስ “The only way to beat the competition is to stop trying to beat the competition.” (ውድድርን ማሸነፍ የሚቻለው ውድድርን ለማሸነፍ የሚደረገውን ጥረት በማቆም ብቻ ነው።) 🛡2. የእሴት ፈጠራ እና የዋጋ ቅናሽ (Value Innovation) አብዛኛው ኩባንያ «ጥራት ከጨመርኩ ዋጋ መጨመር አለብኝ» ብሎ ያስባል። የብሉ ኦሽን ስትራቴጂ ግን ለደንበኛ የሚሰጠውን ጥቅም (Value) እጅግ እየጨመሩ፣ የወጡ ወጪዎችን ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል ይላል። 📘ከመፅሐፉ የተወሰደ ጥቅስ “Value innovation is the cornerstone of blue ocean strategy.” (የእሴት ፈጠራ የብሉ ኦሽን ስትራቴጂ መሰረት ነው።) 🛡3. አላስፈላጊ ወጪዎችን ቀንስ፤ አዳዲስ እሴቶችን ጨምር ቀደም ሲል በኢንዱስትሪው ውስጥ «ግዴታ ናቸው» ተብለው የሚታሰቡ ነገር ግን ብዙ ወጪ የሚያወጡ ነገሮችን አስወግድ ወይም ቀንስ፤ በተቃራኒው ደግሞ ማንም ያላቀረበውን አዲስ ደስታ ለደንበኛ ፍጠር። 📘ከመፅሐፉ የተወሰደ ጥቅስ “Focus on the big picture, not the numbers.” (በትንሽ አሃዞችና ዝርዝሮች ላይ ሳይሆን በትልቁ ምስል ላይ ትኩረት አድርግ።) 🛡4. ገበያ የሌላቸውን ደንበኞች ሳብ (Non-customers) ነባር ደንበኞችን ለመንጠቅ ከመታገል ይልቅ፣ እስካሁን ምርቱን/አገልግሎቱን የማይጠቀሙ ሰዎችን ፍላጎት ተረድተህ አዲስ ገበያ ፍጠር። 📘ከመፅሐፉ የተወሰደ ጥቅስ “Go beyond existing demand.” (ከነባሩ የገበያ ፍላጎት ባሻገር ተሻግረህ ተመልከት።) 🗝 በደም በተበከለውና ውድድር በበዛበት «ቀይ ውቅያኖስ» (Red Ocean) ውስጥ ከሰዎች ጋር ከመሰላለፍ፣ አዲስ አስተሳሰብና እሴት በመፍጠር ማንም የሌለበትን ጥራት ያለው «ሰማያዊ ውቅያኖስ» (Blue Ocean) መፍጠር የረጅም ጊዜ ስኬት ቁልፍ ነው። #book © ሳይንስኛ

📘 Blue Ocean Strategy Book Review!
📘 Blue Ocean Strategy Book Review!

🌼 እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም፣ በፍቅር፣ በአንድነት አደረሳችሁ አደረሰን! © ሳይንስኛ
🌼 እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም፣ በፍቅር፣ በአንድነት አደረሳችሁ አደረሰን! © ሳይንስኛ

🌟 ለቢዝነስዎ እና ለስራዎ ስኬት የተሟላ ዝግጅት! የቢዝነስዎን ተደራሽነት ለማስፋት ዘመናዊ ድረ-ገጽ (Website) እና ብራንድዎን በጉልህ የሚያሳይ ሎጎ (Logo) ማሰራት አስበዋል? ወይስ አሰሪ
🌟 ለቢዝነስዎ እና ለስራዎ ስኬት የተሟላ ዝግጅት! የቢዝነስዎን ተደራሽነት ለማስፋት ዘመናዊ ድረ-ገጽ (Website) እና ብራንድዎን በጉልህ የሚያሳይ ሎጎ (Logo) ማሰራት አስበዋል? ወይስ አሰሪዎችን በቀላሉ ሊስብ የሚችል ጥራቱን የጠበቀ CV ይፈልጋሉ?  እንግዲያውስ ትክክለኛው ቦታ ላይ ነዎት! እኛ ጋር ሲመጡ...... 🛡ለብራንድዎ፡ የድርጅትዎን ራዕይ እና ማንነት የሚገልጽ፣ ፈጠራ የታከለበት ማራኪ ሎጎ (Logo) እናዘጋጃለን። 🫧 ለድርጅትዎ፡ ደንበኞችን የሚስብ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የድርጅትዎን ገጽታ የሚመጥን ፕሮፌሽናል ዌብሳይት (Website) እንገነባለን። 📰 ለግልዎ፡ የትምህርት ዝግጅትዎን፣ ልምድዎን እና ብቃትዎን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ፕሮፌሽናል ሲቪ (CV) እናዘጋጅልዎታለን። በጥራት፣ በፍጥነት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክባለን። 🗣 አሁኑኑ ያነጋግሩን፤ ድረ-ገጻችንን በመጎብኘት ተጨማሪ መረጃዎችን ያግኙ 🌐 www.electrospacex.com 👉 @ElectrospaceBot

🦁 አንበሳን መያዝ ስትፈልግ 🥩 ስጋን ተጠቀም! 🐒 ጦጣን መያዝ ስትፈልግ 🍌 ሙዝ ተጠቀም! 🐶 ውሻን መያዝ ስትፈልግ 🦴 አጥንትን ተጠቀም! 🐁 አይጥን መያዝ ስትፈልግ 🧀 አይብን ተጠቀም!
🦁 አንበሳን መያዝ ስትፈልግ 🥩 ስጋን ተጠቀም! 🐒 ጦጣን መያዝ ስትፈልግ 🍌 ሙዝ ተጠቀም! 🐶 ውሻን መያዝ ስትፈልግ 🦴 አጥንትን ተጠቀም! 🐁 አይጥን መያዝ ስትፈልግ 🧀 አይብን ተጠቀም! 🥸 ወንድን መያዝ ስትፈልግ 👧 ሴትን ተጠቀም! 💸 ሀብትን መያዝ ስትፈልግ 🧠 አዕምሮህን ተጠቀም! ➡️ ሁሉም ነገር መፍትሔ አለው!! 🕹 Antman © ሳይንስኛ

🥨 ከሰው ልጅ አካል እስከ ኢትዮጵያዊነት የሰው ልጅ አካል ተአምራዊ የምህንድስና ውጤት ነው። በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙት 78ቱ የአካል ክፍሎች (Organs) እያንዳንዳቸው የየራሳቸው የሆነ ልዩ ተግባር እና ኃላፊነት አላቸው። 🫀 ልብ ደም ሲረጭ፣ 🫁 ሳንባ አየር ያመላልሳል፣ ኩላሊት ደም ያጣራል፣ ቆዳ ደግሞ ሙሉ አካላችንን ይሸፍናል። እነዚህ አካላት መጠናቸው ወይም ቅርጻቸው ቢለያይም፣ አንዱ ከሌላው አይበልጥም። አንዳቸው ያለ ሌላው ህልውና ሊኖራቸው አይችልም። አንዱ አካል ቢታመም ወይም ቢጎድል፣ ሙሉ ሰውነታችን ህመም ይሰማዋል። አንዱ organ ከሌለ ሙሉ የሰው ልጅ ህይወትና ሙሉነት እንደሚጓደለው ሁሉ፣ የኢትዮጵያም ህልውና ከዚሁ የተለየ አይደለም። 🇪🇹 ኢትዮጵያ የ85 በላይ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የጋራ ቤት ናት። እያንዳንዱ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ፣ ዜማ እና የሕይወት እሴት ያለው የዚህች ታላቅ ሀገር አስፈላጊ “አካል” ነው። ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ሶማሌ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ አፋር፣ ጉራጌ፣ ጋሞ፣ አኙዋክ፣ ኑዌር፣ ጉሙዝ... እና ሌሎችም እያንዳንዳቸው የሀገሪቱ የደም ስሮች እና የሕይወት እስትንፋሶች ናቸው። 💥 የህብረ ቀለማችን ውበት፣ የታሪካችን ጥንካሬ እና የባህላችን ሀብታምነት የሚመነጨው ከዚሁ ስብጥር ነው። የአንድ ብሔረሰብ ባህል ወይም ማንነት ከኢትዮጵያ ቢቀነስ፣ የታሪካችን ገጽ ይጎድላል፤ የባህላችን ህብረ-ቀለም ይጠፋል፤ የሀገራችንም ምሉዕነት ይሸረሸራል። 👤እንደ ሰው ልጅ አካል ሁሉ፣ በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥም "ትንሽ" ወይም "ትልቅ"፣ "አስፈላጊ" ወይም "ኢ-አስፈላጊ" የሚባል ብሔረሰብ የለም። አንዱ ቢጎዳ ሌላው ይቸገራል፤ አንዱ ቢከበር ሙሉ ሀገሪቱ ትከበራለች። 👥 አካላችን 78ቱን ብልቶች አስተባብሮ ሙሉ ሰብዕና እንደሚፈጥረው ሁሉ፣ ኢትዮጵያም የሁሉም ብሔረሰቦቿ ድምር ውጤት ናት። አንድነታችን በጥላቻ ሳይሆን በመከባበር፣ ልዩነታችን በጠብ ሳይሆን በውበት ከተቃኘ፣ ሀገራችን እንደ ጤናማ ሰው ሙሉ ጥንካሬዋን አግኝታ ለዘላለም ትኖራለች። 🗣"ኢትዮጵያ ማለት የሁላችንም ድምር ናት፤ አንዱ ከሌለ ሙሉ ኢትዮጵያ ልትኖር አትችልም።" ⁉️ ከልብ እና ከሳንባ ለመኖር በጣም የሚያስፈልገው Organ የቱ ነው? ጥያቄው ግን መልስ የለውም! #Ethiopia © ሳይንስኛ

photo content

🌟 ለቢዝነስዎ እና ለስራዎ ስኬት የተሟላ ዝግጅት! የቢዝነስዎን ተደራሽነት ለማስፋት ዘመናዊ ድረ-ገጽ (Website) እና ብራንድዎን በጉልህ የሚያሳይ ሎጎ (Logo) ማሰራት አስበዋል? ወይስ አሰሪ
🌟 ለቢዝነስዎ እና ለስራዎ ስኬት የተሟላ ዝግጅት! የቢዝነስዎን ተደራሽነት ለማስፋት ዘመናዊ ድረ-ገጽ (Website) እና ብራንድዎን በጉልህ የሚያሳይ ሎጎ (Logo) ማሰራት አስበዋል? ወይስ አሰሪዎችን በቀላሉ ሊስብ የሚችል ጥራቱን የጠበቀ CV ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ትክክለኛው ቦታ ላይ ነዎት! እኛ ጋር ሲመጡ...... 🛡ለብራንድዎ፡ የድርጅትዎን ራዕይ እና ማንነት የሚገልጽ፣ ፈጠራ የታከለበት ማራኪ ሎጎ (Logo) እናዘጋጃለን። 🫧 ለድርጅትዎ፡ ደንበኞችን የሚስብ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የድርጅትዎን ገጽታ የሚመጥን ፕሮፌሽናል ዌብሳይት (Website) እንገነባለን። 📰 ለግልዎ፡ የትምህርት ዝግጅትዎን፣ ልምድዎን እና ብቃትዎን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ፕሮፌሽናል ሲቪ (CV) እናዘጋጅልዎታለን። በጥራት፣ በፍጥነት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክባለን። 🗣 አሁኑኑ ያነጋግሩን፤ ድረ-ገጻችንን በመጎብኘት ተጨማሪ መረጃዎችን ያግኙ 🌐 www.electrospacex.com 👉 @ElectrospaceBot

የስታርባክስ (Starbucks) ታሪክ "ከቡና ፍሬ ሻጭነት እስከ ዓለም አቀፍ የካፌ ባህል ፈጣሪነት" የተጓዘ እጅግ አስደናቂ የስኬት ጉዞ ነው። በአጭሩ ሂደቱ ይህንን ይመስላል...... ☕️ #1. ጅምሩ፦ የቡና ፍሬ ብቻ መሸጥ (1971) ስታርባክስ እ.ኤ.አ. በ1971 በሲያትል አሜሪካ የተመሰረተው በሶስት ጓደኛሞች (ሁለት አስተማሪዎች እና አንድ ጸሐፊ) ነበር። በወቅቱ የታሸገ ቡና መሸጥ እንጂ የተቀናጀ የቡና መጠጥ (እንደ ላቴ ወይም ካፑቺኖ) አይሸጡም ነበር፤ ስራቸው ጥራት ያለው የተቆላ የቡና ፍሬ እና የቡና ማፊያ እቃዎችን መሸጥ ብቻ ነበር። ☕️ #2. ህይወቱን የቀየረው የጣሊያን ጉዞ (1983) በ1982 ሃዋርድ ሹልትዝ (Howard Schultz) የተባለ ወጣት የማርኬቲንግ ሀላፊ ሆኖ ስታርባክስን ተቀላቀለ። በ1983 ወደ ሚላን ጣሊያን የተጓዘው ሃዋርድ፣ በጣሊያን የካፌ ባህል (ሰዎች ተሰብስበው ቡና እያፈሉ የሚያወሩበት እና የሚያርፉበት ቦታ) እጅግ ተደመመ። ይህንን አሰራር ወደ አሜሪካ ለማምጣት ቢፈልግም የመስራቾቹን እሺታ ማግኘት አልቻለም። ☕️ #3. ኩባንያውን መግዛት እና የ"ሶስተኛው ቦታ" ራዕይ (1987) ሃዋርድ ከስታርባክስ ለቆ የራሱን ካፌ ከፈተ። በ1987 ዓ.ም ግን የመጀመሪያዎቹ መስራቾች ስታርባክስን ሊሸጡ ሲሉ ሃዋርድ ባለሀብቶችን አስተባብሮ ስታርባክስን በ3.8 ሚሊዮን ዶላር ገዛው። ከዚያም የስታርባክስን ራዕይ ቀየረው፦ "ከቤት እና ከስራ ቦታ ውጪ ሰዎች የሚያርፉበት ሶስተኛው ቦታ (Third Place)" አደረገው። ☕️ #4. ፈጣን መስፋፋት እና የንግድ ምልክት መሆን (1990ዎቹ) ስታርባክስ ፈጣን የካፌ መጠጦችን (እንደ Frappuccino) ማስተዋወቅ ጀመረ። ነፃ ዋይፋይ (Wi-Fi)፣ ምቹ ወንበሮች እና ዘመናዊ የሙዚቃ ከባቢ በመፍጠር ሰዎችን ሳበ። በ1992 ኩባንያው አክሲዮኑን ለህዝብ ይፋ ካደረገ በኋላ በየቀኑ አዳዲስ ካፌዎችን በመክፈት በመላው አሜሪካ፣ በመቀጠልም ወደ እስያ እና አውሮፓ በፍጥነት ተስፋፋ። ☕️ #5. የዓለም የበላይነት (ዛሬ)ዛሬ ላይ ስታርባክስ ከቀላል የቡና ፍሬ ሱቅነት ተነስቶ በዓለም ዙሪያ ከ38,000 በላይ ካፌዎች ያሉት፣ በቀን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን የሚያስተናግድ እና የዘመናዊ ከተማ ህይወትና የቡና ባህል መግለጫ የሆነ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ብራንድ ሆኗል። #Starbuck © ሳይንስኛ