uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

መረጃ ዘመደመር

መረጃ ዘመደመር

Відкрити в Telegram
1 030
Підписники
+124 години
+17 днів
+130 днів
Архів дописів
የ #No_More_ስጋ ዘመቻ በአዲስ አበባ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ትልቅ መነጋገሪያ እየሆነ ይገኛል። በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን ከልክ ያለፈ የስጋ ዋጋ ጭማሪ ለመቃወም በማህበራዊ ሚዲያዎች የተጀመረው “የስጋ ዋጋ ይቀንስ no more ስጋ” የተሰኘ የቦይኮት ንቅናቄ የብዙዎችን ትኩረት እየሳበ ይገኛል። ዘመቻው በቲክቶክ እና በፌስቡክ መድረኮች በስፋት እየተሰራጨ የሚገኝ ሲሆን፣ የዋና ከተማዋ ነዋሪዎች ከፍተኛ የሆነውን የዋጋ ጭማሪ በመቃወም ድምፃቸውን እያሰሙበት ይገኛሉ። ሸማቾች የስጋ ቤቶች የጣሉትን ተገቢ ያልሆነ ዋጋ እንዲያስተካክሉ ግፊት ለማድረግ፣ ጥያቄው እስኪመለስ ድረስ ስጋ አለመግዛትና ፍጆታን ማቆም እንደ አማራጭ እንዲወሰድ እየጠየቁ ይገኙበታል የከተማ አስተዳደሩ የገበያ መረጋጋት ለመፍጠር የተለያዩ እርምጃዎችን ቢወስድም፣ በተለይ በትልልቅ የሉካንዳ ቤቶች እና ሬስቶራንቶች የሚቀርበው የስጋ ዋጋ ማርገብ አልቻለም። በአንዳንድ ታዋቂ የከተማዋ ስጋ ቤቶች የአንድ ኪሎ ግራም ስጋ ዋጋ እስከ 6 ሺህ ብር መድረሱ መነገሩ የህብረተሰቡን ቁጣ አባብሶታል። ይህንን ተከትሎ የዘመቻው ተሳታፊዎች ህብረተሰቡ ፊቱን ወደ ጥራጥሬና አትክልት ምርቶች እንዲያዞር ጥሪ በማድረግ ላይ ናቸው። ይህ የዲጂታል አንድነት በስጋ አቅራቢዎችና ሻጮች ላይ የገበያ ግፊት በመፍጠር ዋጋውን ወደ መደበኛ እንዲያመጣው ይጠበቃል። ምን ይመስላችኋል? በከተማችን የታየውን የዋጋ ጭማሪ ለመቋቋም እንዲህ ያሉ የቦይኮት ዘመቻዎች ምን ያህል ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ? 🥩 🥩 🥩

photo content

#ከቴክኖሎጂ_የተኳረፈችው_ሀገር! “ሲም ካርድ ከማግኘት ወርቅ ማውጣት ይቀላል፣ ገንዘብ ቢያስፈልግዎት ከኤቲኤም እወስዳለሁ ማለት ዘበት ነው፣ ኤቲኤም ማሽን የሚባል የለምና፣ ባለንበት ዘመን ሲም ካርድ ለማግኘት በቱሪዝም ሚኒስቴር በኩል ሰነዶችን ማቅረብ ግድ የሚልባት የዓለማችን ብቸኛዋ ሀገር ሳትሆን አትቀርም፡፡” ይህን የሚሉት “ከዓለም የተገለለችና የተቆለፈች፣ በድሮ ዘመን ላይ የቆመች” ሲሉ የሚጠሯት ሀገረ ኤርትራ ላይ የተገኙ በሚሊየኖች ተከታይ ያላቸው ተጓዥ ጋዜጠኛና ዩቱበሮች ናቸው፡፡ ሕዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲና ፍትሕ ( #ህግደፍ ) ብቸኛው ፓርቲ የሆነባት፣ 19 89 ዓ.ም የጸደቀው ሕገ መንግሥትም በተግባር ያልዋለባት፣ የዚህችን ሀገር ዋና ከተማ “ትንሿ ሮም” ሲሉ ጠርተው ሀገሪቱን “አፍሪካዊቷ ሰሜን ኮሪያ” ያሏት እነዚሁ ጋዜጠኛና ዩቱበሮች ስለዚህች ሀገር ያዩትንና የታዘቡትን ሲናገሩ ለሰማ እውነት ነው ብሎ ለማመን የሚከብድ ጭምር ነው፡፡ ኤርትራን የጎበኙ ጋዜጠኞች ምልከታን የሚያሳየውን መሰናዶ በተከታዩ የመሿለኪያ ትዩብ ሊንክ ይመልከቱት!! 👇👇👇 https://www.youtube.com/@Meshualekia

photo content

በምግብ ራስን መቻል የሀገርን ክብርና ነፃነት ከማጠናከር ባለፈ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የስራ እድልን ለማስፋፋትና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና አለው። በምግብ ራሷን የቻለች የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠችና ለዜጎቿ የተሻለ ነገ የምትገነባ ኢትዮጵያን መፍጠር በጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ የሚመራው የለውጥ መንግስት ካስቀመጣቸው የልማት አላማዎች መካከል ዋነኛው ነው። የለውጡ መንግስት ህልምና ራዕይ ድህነትን ድል የነሳች በምግብ እራሷን የቻለች ከተረጂነት ወደ ረጂነት የተሸጋገረች እድገት ብልፅግናዋን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን በአፍሪካ ምድረ እውን ማድረግ ነው

photo content

በጀግናው ጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ የምትመራውና ባለፉት አመታት በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ እድገት እያሳየች የምትገኘው ኢትዮጵያ ሀገራችኝ የምግብ ሉአላዊነቷን ለማረጋገጥና በምግብ ራሷን ለመቻል ለግብርና ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ቀን ከሌት ተግታ እየሰራች ትገኛለች። የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ የመስኖ ልማትን ማስፋፋት ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምና የምግብ አቅርቦትን ማረጋጋት የዚህ ጥረት ዋና አቅጣጫዎች ናቸው። ይህም የምግብ ዋስትናን ከማጠናከር ባለፈ የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ ለስራ እድል ፈጠራና ለዘላቂ ሀገራዊ ብልፅግና ወሳኝ አስተዋፅኦ ያበረክታል። የምግብ ሉአላዊነት የሀገራዊ ነፃነትና የዘላቂ ብልፅግና መሰረት መሆኑን በሚገባ የሚያውቀውና የሚረዳው የለውጡ መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል።

photo content

የ19 ዓመቱ ኤርትራዊ ሚስጥሩን ለ AI ነግሮ የተፈጠረውን አስደንጋጭ መጨረሻ ተመልከቱ 👆👆👆

የቅዳሴ ስነ-ስርዓት ወቅት፣ የኢየሱስ ምስል ያለበት መስቀል በላያቸው ላይ የወደቀባቸው አንድ ካህን ህይወታቸው አለፈ። በኢኳዶር ውስጥ አንድ የካቶሊክ ቄስ ቅዳሴ ላይ እያሉ መስቀል በላያቸው ላይ በመውደቁ ሕይወታቸው አልፏል፤ በወቅቱም ሥነ ሥርዓቱ በቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ ነበር። በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት የተጋራ አንድ ምስል እንዳሳየው፣ በጓያኪል የሚገኘው የ«ፐርፔቱኦ ሶኮሮ» ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አባት ፓትሪሲዮ አልፍሬዶ ሳንቼዝ ሞሊናሪ፣ ቅዳሜ ዕለት ለምእመናኑ ንግግር እያደረጉ ሳለ፣ በመስቀል ላይ የተሰቀለው የክርስቶስ ምስል ወድቆ በእሳቸው ላይ ሲያርፍ ያሳያል። የጓያኪል ሊቀ ጳጳስ እሁድ ዕለት አባ ሞሊናሪ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በጻፉት ጽሁፍ እንዳረጋገጡት “በቤተክርስቲያኑ ቄስ ሆነው ያገለገሉት የተወደዱት አባ ፓትሪሺዮ አልፍሬዶ ሳንቼዝ ሞሊናሪ፣ ወደ አባታችን ቤት መሄዳቸውን እናሳውቃለን።”፥ “የዘላለም ዕረፍት ይሁንለት፣ ጌታ ሆይ። የዘላለም ብርሃንም በእርሱ ላይ ይብራ። በሰላም ያድርሰው። አሜን።” ሲሉ መልዕክት አጋርተዋል።

ለሀገር ውለታ ሳይታክት ቀን ከሌት ለሚሰራው ስራ ተቸሮት አክብሮት ቢሆን ነበር መልካም እንኳን ተተችቶ ተመስግኖ አልበቃም ጥሎብን ሆነ እንጂ መቸኮል ለስድብ በዋለው ውለታ በሚሰራው ስራ መስፈር ነበረበት በታላቁ ስፍራ

photo content

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቆይታን ነገ ሰኞ ምሽት 2፡30 ይጠብቁን። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ጋር በትግርኛ ቋንቋ ያደረጉትን ቆይታ ነገ ምሽት 2:30 ይጠብቁን።

photo content

ኢትዮጵያ ከለውጡ ወዲህ ጠንካራና ዘመናዊ የፀጥታ ተቋማትን ለመገንባት ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች። ከእነዚህ ተቋማት መካከል የሀገራችን መከላከያ ሰራዊት ቁልፍ ሚና ይይዛል። በጠ/ሚ/ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አመራር በመከላከያው ዘርፍ በተደረገው ሪፎርም የሰራዊቱን ተቋማዊ አቅም ሙያዊ ብቃት የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና ዘመናዊ የመከላከል አቅም ለማጠናከር ጥረቶች ተደርገዋል። የእነዚህ ሪፎርሞች ዋና አላማ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት መጠበቅ የሚችል በሙያዊ ብቃትና በተቋማዊ ሀላፊነት የተገነባ ሰራዊት ማጠናከር ነው።

photo content

ኢንዱስትሪ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ መሰረት ነው። ጥሬ እቃዎችን ወደ ተጠቃሚ ምርቶች በመቀየር የስራ እድል በመፍጠርና የሀገርን ምርታማነት በማሳደግ ለልማት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል። በጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ የምትመራው ሀገራችን ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፏን በማሳደግ የዜጎቿን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የውጭ ምርት ጥገኝነትን ለመቀነስና የወጪ ንግድን ለማሳደግ ባለፉት አመታት ትልቅ ስራ ስተሰራ ቆይታለች። በተለይም በግብርና በጨርቃጨርቅ በምግብ ማቀነባበሪያ በመድሀኒት ማምረቻና በግንባታ እቃዎች ምርት ዘርፎች ያላትን አቅም በመጠቀም የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችላለች። የኢንዱስትሪ እድገት ለወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ የቴክኖሎጂ እውቀትን የሙያ ክህሎትንና የምርት ጥራትን ያሳድጋል። እንዲሁም የሀገር ውስጥ ምርቶች በአለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያግዛል።

photo content