ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

መረጃ ዘመደመር

መረጃ ዘመደመር

Открыть в Telegram
1 033
Подписчики
-124 часа
-27 дней
+230 дней
Архив постов
ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ የነበሩ 6 ቁልፍ የህወሓት አመራሮች ተያዙ‼️ የቡድኑ አመራሮች በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 28/2019 ዓ.ም በራማ አካባቢ ወደ ኤርትራ ሊሻገሩ ያሰቡ የቀድሞ የህወሃት ስድስት ቁልፍ አመራሮች ከተደበቁበት በርሃ በተሰጠ ጥቆማ መሠረት በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል። እነሱም 👇 1ኛ = ተወልደ ብርሃን የክልል ሰላም እና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ የነበረ፤ 2ኛ = ገ/ፃድቃን ገ/ስላሴ የክልሉ የሚሊሺያ ዘርፍ ሃላፊ የነበረ፤ 3ኛ = ገ/ኪዳን ኪዳኑ የክልሉ የፀጥታ ዘርፍ መረጃ ሃላፊ የነበረ፤ 4ኛ = አባዲ ገብሩ የክልል ፀጥታ ዘርፍ ምክትል ሃላፊ የነበረ፤ 5ኛ = ወልዱ መስፍን የክልሉ ሚሊሺያ ፅህፈት ቤት ሠራተኛ የነበረ፤ 6ኛ = አማኑኤል ዘርዑ ሹፌር ሲሆኑ በመከላከያ ተይዘዋል። እነኝህ ሲቪል አመራሮች 04 ክላሽ፣ 05 ሽጉጥ፣ 01 ሳታላይት ስልክ እና 134,000 (አንድ መቶ ሠላሳ አራት ሺህ ብር) ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

photo content

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ባሉ 25 የሰንበት ገበያዎችና ኢ-መደበኛ የንግድ ስፍራዎች የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መዓዛ መንግሥቱ እና የክፍለ ከተማው የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አበራ ተዘዋውረው ተመልክተው በቦታው ሲገበያዩ የነበሩ ሸማቾችን አነጋግረዋል፡፡ ገበያዎቹንም የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ኃይሌ አስጎብኝተዋል፡፡

photo content

photo content

photo content

በአዲስ አበባ ሁለንተናዊ ለውጥ ላይ ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያላቸው ድርሻ የጎላ ነው። አዲስ አበባ በከተማ ገጽታ፣ በመሠረተ ልማት፣ በአረንጓዴ ልማት፣ በመንገድ እና በሕዝብ አገልግሎት ዘርፎች የሚታዩ ለውጦችን እያስተናገደች ትገኛለች። በእነዚህ የለውጥ ጉዞዎች ውስጥ የክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አመራርና የሥራ ተሳትፎ የጎላ ድርሻ አለው። የከተማዋን ውበት፣ ዘመናዊነትና የነዋሪዎቿን የኑሮ ጥራት ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች ትኩረት የሚስቡ ናቸው። አዲስ አበባ የለውጥ፣ የውበትና የተስፋ ከተማ #አዲስአበባ #ከተማልማት #አዳነችአቤቤ #ሁለንተናዊለውጥ

photo content

የሦስተኛው ዙር የኮሪደር ልማት የለውጥ ጉዟችንን በግልጽ የሚያሳይ ተግባራዊ እመርታ ነው። ከጎሮ–ኮዬ ፈጬ እስከ ቱሉ ዲምቱ የሚዘልቀው 15 ኪ.ሜ. ርዝመትና 114 ሜትር ስፋት ያለው የመንገድ ልማት፣ ሰፋፊ የእግረኛና የሳይክል መንገዶች፣ 70 ሄክታር የመንገድ ዳር አረንጓዴ ልማት እንዲሁም የውኃና የፍሳሽ መሠረተ ልማቶች የዚህ ጥምር ልማት አካል ናቸው። በተመሳሳይ ከካራ – ቦሌ አየር ማረፊያ መንገድ በጎሮ እስከ አቃቂ የሚዘልቀው 22 ኪ.ሜ. የወንዝ ዳርቻ ልማት 324 ሄክታር መሬትን በሚሸፍን የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት፣ በጋቢዮንና በእርከን ሥራዎች እየተፋጠነ ይገኛል። https://t.me/ProsperityFirst

🌾🇪🇹 #የስንዴ_ልማት_ለሀገር_ሉዓላዊነትና_ለምግብ_ዋስትና! የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አሊ (ዶ/ር) በስንዴ ልማት ዘርፍ ለተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶች የሰጡት ትኩረት ለሀገራችን የምግብ ዋስትናና የግብርና ለውጥ ትልቅ አቅም ይዞ መጥቷል። በሜካናይዜሽን፣ በዘመናዊ አሰራርና በገበሬዎች ተሳትፎ የስንዴ ምርትን ማሳደግ ለኢትዮጵያ ተስፋ የሚሰጥ ጉዞ ነው። ግብርናችን ሲያድግ ኢትዮጵያ ትጠናከራለች! ከምርት ወደ ብልጽግና! 🇪🇹🌾 #Ethiopia #WheatDevelopment #FoodSecurity #Agriculture #የስንዴልማት #ኢትዮጵያ

photo content

መከላከያ ሰራዊታችን ሁሌም ለጠላት ስጋት ለሀገሩና ለህዝቡ ደግሞ የኩራት የክብርና የመተማመን ምልክት ነው። የሀገርን ሉአላዊነት ለማስጠበቅ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ በትጋት በቁርጠኝነትና በከፍተኛ የሀገር ፍቅር የሚያገለግል ታላቅ ተቋም ነው። መከላከያ ሰራዊታችን ጠ/ሚ/ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ሀገሪቱ አመራር ከመጡ ወዲህ በተለይ በተቋማዊ ሪፎርም በዘመናዊ ትጥቅና ቴክኖሎጂ አቅም በሙያዊ ብቃትና በሰው ሀይል ልማት ረገድ የለውጥ ጥረቶች ተካሂደዋል። አላማውም የዘመኑን የደህንነት ስጋቶች በብቃት መመከት የሚችል የሀገርን ሉአላዊነት የሚያስጠብቅና የህዝብን ደህንነት የሚያረጋግጥ ዘመናዊ መከላከያ መገንባት ነው።

photo content

ጠንካራ መካለከያ ሃይል ሰላምን በማረጋገጥ የብልጽግና ከፍታ ጉዞን እንደሚያሳልጥ የተገነዘቡት አርቆ አሳቢው ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ፣ የብልጽግና ከፍታ ጉዞውን ለማሳካት በአፍሪካ ቀንድ በሃያልነቱ አቻ የሌለው የመከላከያ ሰራዊት ገንብተዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዓላማው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የወሰን አንድነትና ሰላም ማስከበር መሆኑን የተገነዘበ፤ የላቀ ወታደራዊ ብቃት ያለው፣ የዘመኑን የረቀቀ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ የታጠቀ ሃይል ነው። መከላከያ ሰራዊቱ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ቀንድና ለቀይ ባህር ቀጠና ሰላምና መረጋጋት ዋስትና የመሆን አቅም ያለው ነው።

photo content