1 029
المشتركون
+124 ساعات
+17 أيام
+130 أيام
أرشيف المشاركات
1 029
በምግብ ራስን መቻል የሀገርን ክብርና ነፃነት ከማጠናከር ባለፈ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የስራ እድልን ለማስፋፋትና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና አለው።
በምግብ ራሷን የቻለች የምግብ ሉዓላዊነቷን ያረጋገጠችና ለዜጎቿ የተሻለ ነገ የምትገነባ ኢትዮጵያን መፍጠር በጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ የሚመራው የለውጥ መንግስት ካስቀመጣቸው የልማት አላማዎች መካከል ዋነኛው ነው።
የለውጡ መንግስት ህልምና ራዕይ ድህነትን ድል የነሳች በምግብ እራሷን የቻለች ከተረጂነት ወደ ረጂነት የተሸጋገረች እድገት ብልፅግናዋን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን በአፍሪካ ምድረ እውን ማድረግ ነው
1 029
በጀግናው ጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ የምትመራውና ባለፉት አመታት በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ እድገት እያሳየች የምትገኘው ኢትዮጵያ ሀገራችኝ የምግብ ሉአላዊነቷን ለማረጋገጥና በምግብ ራሷን ለመቻል ለግብርና ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ቀን ከሌት ተግታ እየሰራች ትገኛለች።
የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ የመስኖ ልማትን ማስፋፋት ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምና የምግብ አቅርቦትን ማረጋጋት የዚህ ጥረት ዋና አቅጣጫዎች ናቸው።
ይህም የምግብ ዋስትናን ከማጠናከር ባለፈ የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሳደግ ለስራ እድል ፈጠራና ለዘላቂ ሀገራዊ ብልፅግና ወሳኝ አስተዋፅኦ ያበረክታል።
የምግብ ሉአላዊነት የሀገራዊ ነፃነትና የዘላቂ ብልፅግና መሰረት መሆኑን በሚገባ የሚያውቀውና የሚረዳው የለውጡ መንግስት ለግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል።
1 029
የቅዳሴ ስነ-ስርዓት ወቅት፣ የኢየሱስ ምስል ያለበት መስቀል በላያቸው ላይ የወደቀባቸው አንድ ካህን ህይወታቸው አለፈ።
በኢኳዶር ውስጥ አንድ የካቶሊክ ቄስ ቅዳሴ ላይ እያሉ መስቀል በላያቸው ላይ በመውደቁ ሕይወታቸው አልፏል፤ በወቅቱም ሥነ ሥርዓቱ በቀጥታ ስርጭት ሲተላለፍ ነበር።
በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት የተጋራ አንድ ምስል እንዳሳየው፣ በጓያኪል የሚገኘው የ«ፐርፔቱኦ ሶኮሮ» ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አባት ፓትሪሲዮ አልፍሬዶ ሳንቼዝ ሞሊናሪ፣ ቅዳሜ ዕለት ለምእመናኑ ንግግር እያደረጉ ሳለ፣ በመስቀል ላይ የተሰቀለው የክርስቶስ ምስል ወድቆ በእሳቸው ላይ ሲያርፍ ያሳያል።
የጓያኪል ሊቀ ጳጳስ እሁድ ዕለት አባ ሞሊናሪ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በጻፉት ጽሁፍ እንዳረጋገጡት “በቤተክርስቲያኑ ቄስ ሆነው ያገለገሉት የተወደዱት አባ ፓትሪሺዮ አልፍሬዶ ሳንቼዝ ሞሊናሪ፣ ወደ አባታችን ቤት መሄዳቸውን እናሳውቃለን።”፥ “የዘላለም ዕረፍት ይሁንለት፣ ጌታ ሆይ። የዘላለም ብርሃንም በእርሱ ላይ ይብራ። በሰላም ያድርሰው። አሜን።” ሲሉ መልዕክት አጋርተዋል።
1 029
ለሀገር ውለታ ሳይታክት ቀን ከሌት
ለሚሰራው ስራ ተቸሮት አክብሮት
ቢሆን ነበር መልካም
እንኳን ተተችቶ ተመስግኖ አልበቃም
ጥሎብን ሆነ እንጂ መቸኮል ለስድብ
በዋለው ውለታ በሚሰራው ስራ
መስፈር ነበረበት በታላቁ ስፍራ
1 029
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቆይታን ነገ ሰኞ ምሽት 2፡30 ይጠብቁን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) ጋር በትግርኛ ቋንቋ ያደረጉትን ቆይታ ነገ ምሽት 2:30 ይጠብቁን።
1 029
ኢትዮጵያ ከለውጡ ወዲህ ጠንካራና ዘመናዊ የፀጥታ ተቋማትን ለመገንባት ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች። ከእነዚህ ተቋማት መካከል የሀገራችን መከላከያ ሰራዊት ቁልፍ ሚና ይይዛል።
በጠ/ሚ/ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አመራር በመከላከያው ዘርፍ በተደረገው ሪፎርም የሰራዊቱን ተቋማዊ አቅም ሙያዊ ብቃት የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና ዘመናዊ የመከላከል አቅም ለማጠናከር ጥረቶች ተደርገዋል።
የእነዚህ ሪፎርሞች ዋና አላማ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት መጠበቅ የሚችል በሙያዊ ብቃትና በተቋማዊ ሀላፊነት የተገነባ ሰራዊት ማጠናከር ነው።
1 029
ኢንዱስትሪ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ መሰረት ነው።
ጥሬ እቃዎችን ወደ ተጠቃሚ ምርቶች በመቀየር የስራ እድል በመፍጠርና የሀገርን ምርታማነት በማሳደግ ለልማት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል።
በጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ የምትመራው ሀገራችን ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፏን በማሳደግ የዜጎቿን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የውጭ ምርት ጥገኝነትን ለመቀነስና የወጪ ንግድን ለማሳደግ ባለፉት አመታት ትልቅ ስራ ስተሰራ ቆይታለች።
በተለይም በግብርና በጨርቃጨርቅ በምግብ ማቀነባበሪያ በመድሀኒት ማምረቻና በግንባታ እቃዎች ምርት ዘርፎች ያላትን አቅም በመጠቀም የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችላለች።
የኢንዱስትሪ እድገት ለወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ የቴክኖሎጂ እውቀትን የሙያ ክህሎትንና የምርት ጥራትን ያሳድጋል።
እንዲሁም የሀገር ውስጥ ምርቶች በአለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያግዛል።
1 029
የጎንደር ሕዝብ ሁኔታዎችን በጥልቀት ይረዳል፤ የሚደግፈውንም በግልጽ ያሳያል! 🇪🇹💪
ጎንደር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላትን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጸች ነው!
የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሠራዊትና ለአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ያላቸውን ድጋፍና አጋርነት በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ነው።
ትናንት የከተማዋ የታክሲ ማኅበራት ለሠራዊቱ ያላቸውን ድጋፍ በሰልፍ ሲያሳዩ፣ ዛሬ ደግሞ የከተማዋ ነዋሪዎች በመሳተፍ ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው።
ለሀገር ሰላም፣ ለሕዝብ ደህንነትና ለሀገራዊ አንድነት በጋራ እንቁም! 🇪🇹
#ጎንደር
#ሰላም
#ሀገራዊአንድነት #የሀገርመከላከያሠራዊት
1 029
የኢትዮጵያ የባህር በር ተደራሽነትና የቀይ ባህርን በህጋዊና በፍትሀዊ መንገድ የመጠቀም ጥያቄ በቀላሉ የሚተው ወይም የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም።
ይህ በሀገራዊ ጥቅም በኢኮኖሚያዊ ልማትና በትውልድ ተስፋ ላይ የተመሰረተ ራዕይ ሲሆን በልጆቿ ፅናት እውቀት ትጋትና በሰላማዊ ዲፕሎማሲ ጥረት እውን ሊሆን የሚችል ሀገራዊ አላማ ነው።
በጠ/ሚ/ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሚመራው የለውጥ መንግስት የኢትዮጵያን የባህር በር ተደራሽነት ጉዳይ በዲፕሎማሲ በሰላማዊ ውይይትና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሰረተ ስምምነት ለማሳካት ተግቶ በመስራት ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያ የባህር በር ተደራሽነቷን ለማሳደግ ያላትን ህጋዊና ሰላማዊ ጥረት በማጠናከር ሀገራዊ ጥቅሟን እያስጠበቀች ከቀጠናው ሀገራት ጋር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በመስራት ላይ ትገኛለች።
