cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ዜና ቅዱሳን

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Більше
Рекламні дописи
842
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

🕤🕤የየካቲት ፳፬ ስንክሳር🕗🕗 🍀🍀ዜና ቅዱሳን🍀🍀 🍁#ቅዱስ አጋቢጦስ ኤጲስቆጶስ 🍁# ❇️#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!❇️ 🌿🌿# እንኳን ለከበረ አባት ለንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ወታደር አለቃ ለነበረው ብዙ ተአምራትን ላደረገ፤ ብዙ ሰዎችን ያጠፋውን ታላቅ ከይሲ በጸሎቱ ለገደለው ለኤጲስቆጶስ ቅዱስ አጋቢጦስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ በጋዛ ሰማዕት ከሆኑ ከጢሞቴዎስ፣ ከቆጵሮስ ከአገረ ከሚናስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።🌿🌿# ❇️#ይህም አባት በከሀድያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን ነበር። ወላጆቹም ደጎች ምእመናን ነበሩ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምረውት ዲቁና ተሾመ። ከዚያም በኋላ እናትና አባቱን ትቶ ወደ አንድ ገዳም ሔደ የሸመገሉ መነኰሳትን አገለገለ። ከእርሳቸውም በጎ አምልኮትን አገለገለ። ከእርሳቸው በጎ አምልኮትን ተማረ አረጋውያኑንም እያገለገለ በገድል ተጠመደ ያለ ማቋረጥም በጾም በጸሎትና በስግደት ይተጋል ከጥዋትም እስከ ምሽት በመጾም የሽንብራ አሠር የሚመገብ ሆነ። ከእንቅልፍም ጋር ሊታገል በወደደ ጊዜ ከሽምብራ አሠር ጋር አመድ እየተመገበ ሰማንያ ቀን ኖረ ከዚህም ተጋድሎ ውስጥ እያለ ኃይሉ ግን ይጨመርለት ነበር። ለአረጋውያንም አገልግሎቱን አላስታጐለም ሲጠራቸው ጌቶቼ ይላቸዋል የጽድቅንና የትሩፋትን ሥራ ሁሉ ፈጸመ። ❇️#እግዚአብሔርም የሚያስደንቁ ብዙዎች የሆኑ ታላላቅ ተአምራቶችን በእጆቹ ገለጠ። ከእርሳቸውም አንዲቷን ብላቴና አዳናት እርሷም እንደ ዕንጨት የደረቀች እስከምትሆን ብዙ ዘመን ጭንቅ በሆነ ደዌ ታማ የኖረች ናት። ዳግመኛም ብዙ ሰዎችን ያጠፋውን ታላቅ ከይሲ በጸሎቱ ገደለው። ከሰውና ከእንስሳም፡አስጨናቂ የሆኑ በሽታዎችን አስወገደ። የተጋድሎውና፡የኃይሉ ጽናት ወሬው በተሰማ ጊዜ ስሙ ሉክያኖስ፡የሚባል መኰንን ወደርሱ ልኮ አስመጥቶ ያለ ውዴታው በግድ የጭፍራ አለቃ አድርጎ ሾመው እርሱ ግን ተጋድሎውን አልተወም ጾምንም ጸሎትንም የትሩፋትን ሥራ የሚጨምር ሆነ እንጂ የቀደመ ሥራውን አልተወም በጥቂት ቀኖችም ዲዮቅልጥያኖስ መክስምያኖስን እግዚአብሔር አጠፋቸው አምላክን የሚወድ ጻድቅ ሰው ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ነገሠ ይህም ቅዱስ ከጭፍራ ውስጥ ይወጣ ዘንድ ምክንያት የሚሻ ሆነ። ❇️#ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እጅግ የሚወደው መልከ መልካም የሆነ ወጣት ብላቴና ነበር ክፉ ጋጌንም ተጫነበት በቀንም በሌሊትም ታላቅ ሥቃይን የሚያሠቃየው ሆነ ቅዱስ አጋቢጦስንም ከሚያውቁት ውስጥ አንድ ሰው በአየው ጊዜ "የወታደር አለቃ አጋቢጦስ ቢመጣ በአዳነህ ነበር" አለው የታመመውም "እርሱ በንጉሥ ጭፍራ ሥርዓት ውስጥ ያለ፡፡ በውኑ ይህን ሥራ መሥራት ይችላልን" አለ ሰውዬውም ገድሉንና ሥራውን ሁሉ አስረዳው። ጋጌን ያደረበትም "በእውነት ሊያድነኝ ዘንድ የወታደር አለቃ አጋቢጦስን ፈጥናችሁ አምጡልኝ" አለ። ንጉሥም ይህን በአወቀ ጊዜ ቅዱስ አጋቢጦስን እንዲአመጡት አዘዘ በመጣ ጊዜም በወጣቱ ላይ ጸለየ በከበረ መስቀልም አማተበው በዚያንም ጊዜ በእግዚአብሔር ኃይል ዳነ ንጉሡም በዚህ ደስ ብሎት ቅዱስ አጋቢጦስን አከበረው "ምን እንዳደርግልህ ትሻለህ?" አለው እርሱም ንጉሡን "ከወታደርነት ውስጥ አሰናብተኝ" አለውና አሰናበተው አስቀድሞ ወደ ነበረባትም ቦታው ተመለሰ ብዙ ዘመናትም እጅግ እየተጋደለ ኖረ። ❇️#ከዚህም በኋላ የዚያች አገር ኤጲስቆጶስ ይዞ ቅስና ሾመው ይህም ኤጲስቆጶስ በሞተ ጊዜ ቅዱስ አጋቢጦስን ይሾምላቸው ዘንድ ሕዝቡ ሊቀ ጳጳሳቱን ለመኑት እርሱም ሾመላቸው መልካም ተናጋሪዎች የሆኑትን የክርስቶስን መንጋዎች በበጎ አጠባበቅ ጠበቃቸው። እግዚአብሔርም የትንቢትን ጸጋ የተሠወረውንም የማወቅ ድንቆች ተአምራቶችንም የማድረግ ሀብትን ሰጠው። በሥውር ኃጢአትን ሆነ የሚሠሩትን ኃጢአተኞች የሚገሥጻቸው ሆነ በንስሐም እስኪመለሱ ከመቅደስ ያርቃቸዋል። ❇️#ዳግመኛም በገድሉ መጽሐፍ ተጽፎ የተገኘ የታላቅ ወንዝ ወራጅ ውኃን በመስቀሉ አቁሞ ወደ ሌላ መንገድ መለሰው የዕውር ዐይኖችንም ገለጠ ለምጻሞችንም አነጻ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳነ። ያማረና መልካም የሆነ ተጋድሎውንና አገልግሎቱን ፈጽሞ በዚህች ዕለት የካቲት24 ዐረፈ፡፡ 🙏🙏# ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አጋቢጦስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።🙏🙏 #ምንጭ፦ የየካቲት24 ስንክሳር። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔔 https://t.me/zenaakidusan 🔔 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 🔔...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
Показати все...
ዜና ቅዱሳን

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Фото недоступнеДивитись в Telegram
Показати все...
✝የቅዱስ ሙሴን አምላክ እናመስግን✝✝ሰላም ለሙሴ ዘተሰብሐ ገጹ፤ወተለዓለ ድምጹ፤ወዘሠነየ ምርዋጹ!

Repost from ዜና ቅዱሳን
Repost from ዜና ቅዱሳን
🕤🕤የየካቲት ፲፯ ስንክሳር🕗🕗 🍀🍀ዜና ቅዱሳን🍀🍀 🍁#አባ ሚናስ መነኰስ ወሰማዕት🍁# ❇️#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!❇️ 🌿🌿#እንኳን ከላይኛው ግብጽ ከአክሚም መንደር ለሆነ ስለ እግዚአብሔር አብ አባትነት ስለ ወልድ ልጅነት መስክሮ በእስላሞች መኰንን እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለ ለታላቁ ጻድቅ ወሰማዕት ለመነኰስ አባ ሚናስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን።🌿🌿# ❇️#የዚህም ቅዱስ፡ ወላጆቹ ምድርን የሚያርሱ ክርስቲያን ገበሬዎች ናቸው። እርሱም ይህን ዓለም ንቆ ትቶ በአገረ አክሚም በሚገኝ በአንድ ገዳም መነኰሰ ለመብልና ለመጠጥ ሳይገዛ በየሁለት ቀን እየጾመ ብዙ ቀኖችን ኖረ ከዚያም ወጥቶ ወደ እስሙናይን አገር ሒዶ በአንድ ገዳም ውስጥ እያገለገለና እየተጋደለ ከገዳሙ ደጃፍ ሳይወጣ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ። ❇️#እስላሞችም በግብጽ አገር በነገሡ ጊዜ ለእግዚአብሔር ከርሱ ጋር ለዘላለሙ ህልው የሆነ የባሕርዩ የተወለደ ልጅ የሚሠርፅ መንፈስ ቅዱስም የለውም እንደሚሉ ሰማ ስለዚህም ነገር እጅግ አዘነ። ከአበ ምኔቱም ቡራኬ ተቀበለ ወደ እስሙናይን ከተማ ወጥቶ ሔደ የእስላሞች ሠራዊት አለቃ በሆነ በመኰንኑ ፊት ቁሞ እንዲህ አለው "እናንተ ለእግዚአብሔር ከባሕርዩ የተወለደ ልጅ እንደ ሌለው አድርጋችሁ የምትናገሩ እውነት ነውን?" መኰንኑም "አዎን ልጅ አለው ማለትን ከእግዚአብሔር እናርቃለን" አለ። አባ ሚናስም "ያለ ልጅ ልታምኑ አይገባም እርሱም ያለ ዘር ያለ ሩካቤ የሆነ ነው ከባሕርዩ ተወለደ እንጂ" አለው። መኰንኑም "ልጅ አለው ማለት በሕጋችን ክህደት ነው" አለ። አባ፡ሚናስም እንዲህ አለው "መኰንን ሆይ እወቅ የከበረ ወንጌል በወልድ ያመነ የዘላለም ሕይወት አለው በእግዚአብሔር ልጅ በወልድ ያላመነ ሕይወትን አያይም የእግዚአብሔር ቊጣ በላዩ ይወርዳል እንጂ ብሏልና"። ስለዚህም መኰንኑ እጅግ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡ ሥጋውንም በየቊርጥራጭ ቆራርጠው ከባሕር እንዲጥሉት አዘዘ ምእመናንም ሥጋውን ወስደው በበጎ አገናነዝ ገንዘው ቀበሩት መታሰቢያውንም አደረጉ። 🙏🙏#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።🙏🙏 #ምንጭ፦ የየካቲት17 ስንክሳር። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔔 https://t.me/zenaakidusan 🔔 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 🔔...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
Показати все...
ዜና ቅዱሳን

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Repost from ዜና ቅዱሳን
🕤🕤የየካቲት ፲፯ ስንክሳር🕗🕗 🍀🍀ዜና ቅዱሳን🍀🍀 🍁#ሊቀ-ነቢያት ቅዱስ ሙሴ🍁# ❇️#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!❇️ 🌿🌿#እንኳን የእግዚአብሔር ሰው ለሆነ ለየዋህ ለትሑቱ ለቢያት አለቃ ለቅዱስ ሙሴ ለዕረፍቱ መታሰቢያ ለበዓል፣ በሰላም አደረሰን።🌿🌿# ❇️#ይህ ነቢይ ነፍሱን ስለእርሳቸው አሳልፎ እስከ መስጠት ደርሶ ከእግዚአብሔር ወገኖች ጋር የደከመ ነው እርሱም በግብጽ አገር በኤርትራ ባሕርም ድንቆች ተአምራትን ያደረገ ነው። ይህም ስለ ፈርዖን ትእዛዝ ወላጆቹ በግብጽ ወንዝ ውስጥ በጣሉት ጊዜ አውጥታ ላሳደገችው ለፈርዖን ልጅ ለተርሙት ልጅዋ መባልን አልወደደም። እርሱ ፈርዖን የዕብራውያንን ወንዶች ልጆች ይገድሏቸው ዘንድ አዝዞ ነበርና። በአገኘችውም ጊዜ ለርሷ ልጅ ሊሆናት ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው። ❇️#አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አንዱን ዕብራዊ የግብጽ ሰው የሆነ ሲያጠቃው አየ ለዕብራዊው ተበቅሎ ግብጻዊውን ገደለው። በማግሥቱ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አያቸው ሊያስታርቃቸውና በመካከላቸው ሰላምን ሊአደርግ ወደደ። አንዱ ዐመፀኛም "ትላንት ግብጻዊውን እንደገደልከው ልትገድለኝ ትሻለህን" አለው። ስለዚህም ነገር ሙሴ ፈርቶ ወደ ምድያም አገር ሸሸ በዚያም ሚስት አግብተሸ ሁለት ልጆችን ወለደ በዚያም አርባ ዓመት ኖረ በጳጦስ ቊጥቋጦ ውስጥ እግዚአብሔር ተናገው። ወደ ግብጽ አገርም ሒዶ የእስራኤልን ልጆች ከዚያ እንዲያወጣቸው አዘዘው። ❇️#ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አወጣቸው የኤርትራንም ባሕር ከፍሎ በውስጡ አሳለፋቸው የባሕሩንም ውኃ በጠላቶቻቸው በፈርንና በሠራዊቱ ላይ ገልብጦ አሠጠማቸው። ከዚህም በኋላ በምድረ በዳ ውስጥ አርባ ዓመት ሙሉ መና አወረደላቸው ውኃንም ከአለት አፈለቀላቸው ይህን ሁሉ በጎ ሥራ በዚህ በደግ ነቢይ ሙሴ እጅ እግዚአብሔር አደረገላቸው እነርሱ ግን ይዘልፉት ነበር ብዙ ጊዜም በድንጊያ ሊወግሩት ሽተው ነበር። እርሱ ግን በእነርሱ ላይ ልቡን አስፍቶ በመታገሥ ስርሳቸው ወደ እግዚአብሔር ይማልዳል። እነርሱንም አብዝቶ ከመውደዱ የተነሣ እግዚአብሔርን "አቤቱ የዚህን ሕዝብ በደሉን ይቅር ካላክ ከሕይወት መጽሐፍህ ሰርሰዘኝ" አለው። ❇️#ሰው ከወዳጁ ጋር እንደሚነጋገር አምስት መቶ ሰብዓ ቃላትን ከእግዚአብሔር ጋር እንደተነጋገረ መጽሐፍ ምስክር ሆነ። የእስራኤል ልጆችም በሚያዩት ጊዜ እንዳይሞቱ ፊቱን እስከ መሸፈን ድረስ በእግዚአብሔር በጌትነቱ ብርሃን ፊቱ በራ። ❇️#መቶ ሃያ ዓመት የሆነ ዕድሜውም በተፈጸመለት ጊዜ ለአገልጋዩ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ ሕዝቡን እርሱ እንዲጠብቃቸው በእጁ ውስጥ እንዲአስረክበው እግዚአብሔር ሙሴን ለኢያሱ አስረክብ ብሎ አዘዘው። ሙሴም ኢያሱን ጠርቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አዘዘው ሕጉንም እንዲጠብቅ ሕዝብንም ለኢያሱ በእጁ አስረከባቸው ወደ ምድረ ርስት እርሱ እንደ ሚአስገባቸው አረጋገጠላቸው። ❇️#ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በምስክር ድንኳን ውስጥ የሚሠራውን ሁሉ ሠርቶ ከአዘጋጀ በኋላ በናባው ተራራ ውስጥ ዐረፈ በዚያም በመላእክት እጅ በሥውር ተቀበረ። የእስራኤል ልጆች ወስደው እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን ሥጋ ሠወረ። በእስራኤል ልጆች ውስጥ እንደ ሙሴ ያለ ደግ የዋህ ቅን የሆነ ነቢይ እንደማይነሣ መጽሐፍ ምስክር ሆነ። ❇️#ሰይጣንም የሙሴን ሥጋ ለእስራኤል ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ሐዋርያው ቅዱስ ይሁዳ በጻፈው መጽሐፍ እንደመሰከረ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ገሠጸው ከዚህም ሥራ ከለከለው። የእስራኤል ልጆች አርባ ቀን አለቀሱለት። 🙏🙏#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሊቀ ነቢያት በቅዱስ ሙሴ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።🙏🙏 #ምንጭ፦ የመስከረም 8 ስንክሳር። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔔 https://t.me/zenaakidusan 🔔 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 🔔...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
Показати все...
ዜና ቅዱሳን

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Repost from ዜና ቅዱሳን
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Repost from ዜና ቅዱሳን
Repost from ዜና ቅዱሳን
🕒🕒የካቲት 16🕒🕒 🍀🍀እግዝእትነ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት🍀🍀 🌼🌼እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የኪዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🌼 📚📚7ቱ ኪዳናት 📚📚 🌿🌿ተካየደ' ማለት 'ተስማማ: ተማማለ' እንደ ማለት ሲሆን 'ኪዳን' በቁሙ 'ውል: ስምምነት' እንደ ማለት ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው:: 🌿🌿እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ 7 እንደ ሆኑ ታስተምራለች:: ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን እነዚሁን 7 ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን:: 🌿🌿"ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ" "ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" (መዝ. 88:3) 1. 🔑🔑 ኪዳነ አዳም 🔑🔑 👉👉አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት: የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው:: እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: (ዘፍ. 3:1) 👉👉አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን ተቀበሉ:: (ቀሌምንጦስ: ገላ. 4:4) 2. 🔑🔑ኪዳነ ኖኅ🔑🔑 👉👉ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት 10 ትውልድ ዓለም በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች:: ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: (ዘፍ. 9:12) 3. 🔑🔑ኪዳነ መልከ ጼዴቅ 🔑🔑 👉👉መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ15 ዓመቱ መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን ያስታኩት ነበር:: 👉👉እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: (ዘፍ. 14:17, ዕብ. 7:1) 4. 🔑🔑ኪዳነ አብርሃም🔑🔑 👉👉ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ" አለው:: (ዘፍ. 12:1) የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: (ዘፍ. 17:1-14) 5. 🔑🔑ኪዳነ ሙሴ🔑🔑 👉👉ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ: የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት (የዋህ) ሰው ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ለ40 ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት ተቀብሏል:: (ዘጸ. 20:1, 31:18) 6. 🔑🔑ኪዳነ ዳዊት🔑🔑 👉👉ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ" (መዝ. 131:11) ሲል ምሎለታል:: አክሎም ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት እንመለከታለን:: (መዝ. 88:35) 7. 🔑🔑ኪዳነ ምሕረት🔑🔑 👉👉በብሉይ ኪዳን የነበሩ 6ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማሕጸን አደረ:: 👉👉በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ: ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት (የምሕረት ኪዳን) የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው:: 👉👉የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ: ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ: መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት:: 👉👉የእርሷ ኪዳን 6ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ የኪዳናት ማሕተም ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና:: መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው:: 👉👉እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ 2ሺ ዓመታት ሆኑ:: ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን በጥላዋ ሥር እንኖራለን:: 👉👉ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ: ማርያም እሙ ለእግዚእነ: በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ::" 👉👉ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::" 👉👉የአርያም ንግሥት: የሰማያውያንና ምድራውያን ኁሉ እመቤት: የአምላክ እናት: ቅድስት: ስብሕት: ክብርት: ልዕልት: ቡርክት: ፍስሕትና ጥዕምት የሆነች ድንግል ማርያም የድኅነታችን መሠረት: ላመኑባት አንገት የማታስደፋ እውነተኛ አማላጅ ናት:: 👉👉በዚህች ዕለት የካቲት 16 ስለ ወገኖቿ የሰው ልጆች ፍቅር በእንባ ያቀረበችውን ልመና የባሕርይ አምላክ የሆነ ልጁዋ ተቀብሎ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላታል:: በስምሽ ያመነ በቃል ኪዳንሽ የተማመነ እሳት አያይም ብሏታል:: 🙏🙏🙏ቸሩ ልጇ ከበረከተ ኪዳኗ አይለየን:: በዓሉንም የሰላም: የፍቅርና የበረከት ያድርግልን::🙏🙏🙏 :- መ/ር ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧 💧https://t.me/zenaakidusan 💧💧 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧 .......... የቴሌግራም ቻናላችንን በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣የዜና ቅዱሳን ቤተሰብ ይሁኑ!!!
Показати все...
ዜና ቅዱሳን

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.