cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ዜና ቅዱሳን

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
842
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
-430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🕤🕤የየካቲት ፳፬ ስንክሳር🕗🕗 🍀🍀ዜና ቅዱሳን🍀🍀 🍁#ቅዱስ አጋቢጦስ ኤጲስቆጶስ 🍁# ❇️#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!❇️ 🌿🌿# እንኳን ለከበረ አባት ለንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ወታደር አለቃ ለነበረው ብዙ ተአምራትን ላደረገ፤ ብዙ ሰዎችን ያጠፋውን ታላቅ ከይሲ በጸሎቱ ለገደለው ለኤጲስቆጶስ ቅዱስ አጋቢጦስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ በጋዛ ሰማዕት ከሆኑ ከጢሞቴዎስ፣ ከቆጵሮስ ከአገረ ከሚናስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።🌿🌿# ❇️#ይህም አባት በከሀድያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን ነበር። ወላጆቹም ደጎች ምእመናን ነበሩ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምረውት ዲቁና ተሾመ። ከዚያም በኋላ እናትና አባቱን ትቶ ወደ አንድ ገዳም ሔደ የሸመገሉ መነኰሳትን አገለገለ። ከእርሳቸውም በጎ አምልኮትን አገለገለ። ከእርሳቸው በጎ አምልኮትን ተማረ አረጋውያኑንም እያገለገለ በገድል ተጠመደ ያለ ማቋረጥም በጾም በጸሎትና በስግደት ይተጋል ከጥዋትም እስከ ምሽት በመጾም የሽንብራ አሠር የሚመገብ ሆነ። ከእንቅልፍም ጋር ሊታገል በወደደ ጊዜ ከሽምብራ አሠር ጋር አመድ እየተመገበ ሰማንያ ቀን ኖረ ከዚህም ተጋድሎ ውስጥ እያለ ኃይሉ ግን ይጨመርለት ነበር። ለአረጋውያንም አገልግሎቱን አላስታጐለም ሲጠራቸው ጌቶቼ ይላቸዋል የጽድቅንና የትሩፋትን ሥራ ሁሉ ፈጸመ። ❇️#እግዚአብሔርም የሚያስደንቁ ብዙዎች የሆኑ ታላላቅ ተአምራቶችን በእጆቹ ገለጠ። ከእርሳቸውም አንዲቷን ብላቴና አዳናት እርሷም እንደ ዕንጨት የደረቀች እስከምትሆን ብዙ ዘመን ጭንቅ በሆነ ደዌ ታማ የኖረች ናት። ዳግመኛም ብዙ ሰዎችን ያጠፋውን ታላቅ ከይሲ በጸሎቱ ገደለው። ከሰውና ከእንስሳም፡አስጨናቂ የሆኑ በሽታዎችን አስወገደ። የተጋድሎውና፡የኃይሉ ጽናት ወሬው በተሰማ ጊዜ ስሙ ሉክያኖስ፡የሚባል መኰንን ወደርሱ ልኮ አስመጥቶ ያለ ውዴታው በግድ የጭፍራ አለቃ አድርጎ ሾመው እርሱ ግን ተጋድሎውን አልተወም ጾምንም ጸሎትንም የትሩፋትን ሥራ የሚጨምር ሆነ እንጂ የቀደመ ሥራውን አልተወም በጥቂት ቀኖችም ዲዮቅልጥያኖስ መክስምያኖስን እግዚአብሔር አጠፋቸው አምላክን የሚወድ ጻድቅ ሰው ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ነገሠ ይህም ቅዱስ ከጭፍራ ውስጥ ይወጣ ዘንድ ምክንያት የሚሻ ሆነ። ❇️#ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ እጅግ የሚወደው መልከ መልካም የሆነ ወጣት ብላቴና ነበር ክፉ ጋጌንም ተጫነበት በቀንም በሌሊትም ታላቅ ሥቃይን የሚያሠቃየው ሆነ ቅዱስ አጋቢጦስንም ከሚያውቁት ውስጥ አንድ ሰው በአየው ጊዜ "የወታደር አለቃ አጋቢጦስ ቢመጣ በአዳነህ ነበር" አለው የታመመውም "እርሱ በንጉሥ ጭፍራ ሥርዓት ውስጥ ያለ፡፡ በውኑ ይህን ሥራ መሥራት ይችላልን" አለ ሰውዬውም ገድሉንና ሥራውን ሁሉ አስረዳው። ጋጌን ያደረበትም "በእውነት ሊያድነኝ ዘንድ የወታደር አለቃ አጋቢጦስን ፈጥናችሁ አምጡልኝ" አለ። ንጉሥም ይህን በአወቀ ጊዜ ቅዱስ አጋቢጦስን እንዲአመጡት አዘዘ በመጣ ጊዜም በወጣቱ ላይ ጸለየ በከበረ መስቀልም አማተበው በዚያንም ጊዜ በእግዚአብሔር ኃይል ዳነ ንጉሡም በዚህ ደስ ብሎት ቅዱስ አጋቢጦስን አከበረው "ምን እንዳደርግልህ ትሻለህ?" አለው እርሱም ንጉሡን "ከወታደርነት ውስጥ አሰናብተኝ" አለውና አሰናበተው አስቀድሞ ወደ ነበረባትም ቦታው ተመለሰ ብዙ ዘመናትም እጅግ እየተጋደለ ኖረ። ❇️#ከዚህም በኋላ የዚያች አገር ኤጲስቆጶስ ይዞ ቅስና ሾመው ይህም ኤጲስቆጶስ በሞተ ጊዜ ቅዱስ አጋቢጦስን ይሾምላቸው ዘንድ ሕዝቡ ሊቀ ጳጳሳቱን ለመኑት እርሱም ሾመላቸው መልካም ተናጋሪዎች የሆኑትን የክርስቶስን መንጋዎች በበጎ አጠባበቅ ጠበቃቸው። እግዚአብሔርም የትንቢትን ጸጋ የተሠወረውንም የማወቅ ድንቆች ተአምራቶችንም የማድረግ ሀብትን ሰጠው። በሥውር ኃጢአትን ሆነ የሚሠሩትን ኃጢአተኞች የሚገሥጻቸው ሆነ በንስሐም እስኪመለሱ ከመቅደስ ያርቃቸዋል። ❇️#ዳግመኛም በገድሉ መጽሐፍ ተጽፎ የተገኘ የታላቅ ወንዝ ወራጅ ውኃን በመስቀሉ አቁሞ ወደ ሌላ መንገድ መለሰው የዕውር ዐይኖችንም ገለጠ ለምጻሞችንም አነጻ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳነ። ያማረና መልካም የሆነ ተጋድሎውንና አገልግሎቱን ፈጽሞ በዚህች ዕለት የካቲት24 ዐረፈ፡፡ 🙏🙏# ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አጋቢጦስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።🙏🙏 #ምንጭ፦ የየካቲት24 ስንክሳር። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔔 https://t.me/zenaakidusan 🔔 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 🔔...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
Mostrar todo...
ዜና ቅዱሳን

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Photo unavailableShow in Telegram
Mostrar todo...
✝የቅዱስ ሙሴን አምላክ እናመስግን✝✝ሰላም ለሙሴ ዘተሰብሐ ገጹ፤ወተለዓለ ድምጹ፤ወዘሠነየ ምርዋጹ!

Repost from ዜና ቅዱሳን
Repost from ዜና ቅዱሳን
Photo unavailableShow in Telegram
Repost from ዜና ቅዱሳን
🕤🕤የየካቲት ፲፯ ስንክሳር🕗🕗 🍀🍀ዜና ቅዱሳን🍀🍀 🍁#አባ ሚናስ መነኰስ ወሰማዕት🍁# ❇️#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!❇️ 🌿🌿#እንኳን ከላይኛው ግብጽ ከአክሚም መንደር ለሆነ ስለ እግዚአብሔር አብ አባትነት ስለ ወልድ ልጅነት መስክሮ በእስላሞች መኰንን እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለ ለታላቁ ጻድቅ ወሰማዕት ለመነኰስ አባ ሚናስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን።🌿🌿# ❇️#የዚህም ቅዱስ፡ ወላጆቹ ምድርን የሚያርሱ ክርስቲያን ገበሬዎች ናቸው። እርሱም ይህን ዓለም ንቆ ትቶ በአገረ አክሚም በሚገኝ በአንድ ገዳም መነኰሰ ለመብልና ለመጠጥ ሳይገዛ በየሁለት ቀን እየጾመ ብዙ ቀኖችን ኖረ ከዚያም ወጥቶ ወደ እስሙናይን አገር ሒዶ በአንድ ገዳም ውስጥ እያገለገለና እየተጋደለ ከገዳሙ ደጃፍ ሳይወጣ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ። ❇️#እስላሞችም በግብጽ አገር በነገሡ ጊዜ ለእግዚአብሔር ከርሱ ጋር ለዘላለሙ ህልው የሆነ የባሕርዩ የተወለደ ልጅ የሚሠርፅ መንፈስ ቅዱስም የለውም እንደሚሉ ሰማ ስለዚህም ነገር እጅግ አዘነ። ከአበ ምኔቱም ቡራኬ ተቀበለ ወደ እስሙናይን ከተማ ወጥቶ ሔደ የእስላሞች ሠራዊት አለቃ በሆነ በመኰንኑ ፊት ቁሞ እንዲህ አለው "እናንተ ለእግዚአብሔር ከባሕርዩ የተወለደ ልጅ እንደ ሌለው አድርጋችሁ የምትናገሩ እውነት ነውን?" መኰንኑም "አዎን ልጅ አለው ማለትን ከእግዚአብሔር እናርቃለን" አለ። አባ ሚናስም "ያለ ልጅ ልታምኑ አይገባም እርሱም ያለ ዘር ያለ ሩካቤ የሆነ ነው ከባሕርዩ ተወለደ እንጂ" አለው። መኰንኑም "ልጅ አለው ማለት በሕጋችን ክህደት ነው" አለ። አባ፡ሚናስም እንዲህ አለው "መኰንን ሆይ እወቅ የከበረ ወንጌል በወልድ ያመነ የዘላለም ሕይወት አለው በእግዚአብሔር ልጅ በወልድ ያላመነ ሕይወትን አያይም የእግዚአብሔር ቊጣ በላዩ ይወርዳል እንጂ ብሏልና"። ስለዚህም መኰንኑ እጅግ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡ ሥጋውንም በየቊርጥራጭ ቆራርጠው ከባሕር እንዲጥሉት አዘዘ ምእመናንም ሥጋውን ወስደው በበጎ አገናነዝ ገንዘው ቀበሩት መታሰቢያውንም አደረጉ። 🙏🙏#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።🙏🙏 #ምንጭ፦ የየካቲት17 ስንክሳር። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔔 https://t.me/zenaakidusan 🔔 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 🔔...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
Mostrar todo...
ዜና ቅዱሳን

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Repost from ዜና ቅዱሳን
🕤🕤የየካቲት ፲፯ ስንክሳር🕗🕗 🍀🍀ዜና ቅዱሳን🍀🍀 🍁#ሊቀ-ነቢያት ቅዱስ ሙሴ🍁# ❇️#በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!❇️ 🌿🌿#እንኳን የእግዚአብሔር ሰው ለሆነ ለየዋህ ለትሑቱ ለቢያት አለቃ ለቅዱስ ሙሴ ለዕረፍቱ መታሰቢያ ለበዓል፣ በሰላም አደረሰን።🌿🌿# ❇️#ይህ ነቢይ ነፍሱን ስለእርሳቸው አሳልፎ እስከ መስጠት ደርሶ ከእግዚአብሔር ወገኖች ጋር የደከመ ነው እርሱም በግብጽ አገር በኤርትራ ባሕርም ድንቆች ተአምራትን ያደረገ ነው። ይህም ስለ ፈርዖን ትእዛዝ ወላጆቹ በግብጽ ወንዝ ውስጥ በጣሉት ጊዜ አውጥታ ላሳደገችው ለፈርዖን ልጅ ለተርሙት ልጅዋ መባልን አልወደደም። እርሱ ፈርዖን የዕብራውያንን ወንዶች ልጆች ይገድሏቸው ዘንድ አዝዞ ነበርና። በአገኘችውም ጊዜ ለርሷ ልጅ ሊሆናት ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው። ❇️#አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አንዱን ዕብራዊ የግብጽ ሰው የሆነ ሲያጠቃው አየ ለዕብራዊው ተበቅሎ ግብጻዊውን ገደለው። በማግሥቱ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አያቸው ሊያስታርቃቸውና በመካከላቸው ሰላምን ሊአደርግ ወደደ። አንዱ ዐመፀኛም "ትላንት ግብጻዊውን እንደገደልከው ልትገድለኝ ትሻለህን" አለው። ስለዚህም ነገር ሙሴ ፈርቶ ወደ ምድያም አገር ሸሸ በዚያም ሚስት አግብተሸ ሁለት ልጆችን ወለደ በዚያም አርባ ዓመት ኖረ በጳጦስ ቊጥቋጦ ውስጥ እግዚአብሔር ተናገው። ወደ ግብጽ አገርም ሒዶ የእስራኤልን ልጆች ከዚያ እንዲያወጣቸው አዘዘው። ❇️#ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አወጣቸው የኤርትራንም ባሕር ከፍሎ በውስጡ አሳለፋቸው የባሕሩንም ውኃ በጠላቶቻቸው በፈርንና በሠራዊቱ ላይ ገልብጦ አሠጠማቸው። ከዚህም በኋላ በምድረ በዳ ውስጥ አርባ ዓመት ሙሉ መና አወረደላቸው ውኃንም ከአለት አፈለቀላቸው ይህን ሁሉ በጎ ሥራ በዚህ በደግ ነቢይ ሙሴ እጅ እግዚአብሔር አደረገላቸው እነርሱ ግን ይዘልፉት ነበር ብዙ ጊዜም በድንጊያ ሊወግሩት ሽተው ነበር። እርሱ ግን በእነርሱ ላይ ልቡን አስፍቶ በመታገሥ ስርሳቸው ወደ እግዚአብሔር ይማልዳል። እነርሱንም አብዝቶ ከመውደዱ የተነሣ እግዚአብሔርን "አቤቱ የዚህን ሕዝብ በደሉን ይቅር ካላክ ከሕይወት መጽሐፍህ ሰርሰዘኝ" አለው። ❇️#ሰው ከወዳጁ ጋር እንደሚነጋገር አምስት መቶ ሰብዓ ቃላትን ከእግዚአብሔር ጋር እንደተነጋገረ መጽሐፍ ምስክር ሆነ። የእስራኤል ልጆችም በሚያዩት ጊዜ እንዳይሞቱ ፊቱን እስከ መሸፈን ድረስ በእግዚአብሔር በጌትነቱ ብርሃን ፊቱ በራ። ❇️#መቶ ሃያ ዓመት የሆነ ዕድሜውም በተፈጸመለት ጊዜ ለአገልጋዩ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ ሕዝቡን እርሱ እንዲጠብቃቸው በእጁ ውስጥ እንዲአስረክበው እግዚአብሔር ሙሴን ለኢያሱ አስረክብ ብሎ አዘዘው። ሙሴም ኢያሱን ጠርቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አዘዘው ሕጉንም እንዲጠብቅ ሕዝብንም ለኢያሱ በእጁ አስረከባቸው ወደ ምድረ ርስት እርሱ እንደ ሚአስገባቸው አረጋገጠላቸው። ❇️#ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በምስክር ድንኳን ውስጥ የሚሠራውን ሁሉ ሠርቶ ከአዘጋጀ በኋላ በናባው ተራራ ውስጥ ዐረፈ በዚያም በመላእክት እጅ በሥውር ተቀበረ። የእስራኤል ልጆች ወስደው እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን ሥጋ ሠወረ። በእስራኤል ልጆች ውስጥ እንደ ሙሴ ያለ ደግ የዋህ ቅን የሆነ ነቢይ እንደማይነሣ መጽሐፍ ምስክር ሆነ። ❇️#ሰይጣንም የሙሴን ሥጋ ለእስራኤል ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ሐዋርያው ቅዱስ ይሁዳ በጻፈው መጽሐፍ እንደመሰከረ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ገሠጸው ከዚህም ሥራ ከለከለው። የእስራኤል ልጆች አርባ ቀን አለቀሱለት። 🙏🙏#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሊቀ ነቢያት በቅዱስ ሙሴ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።🙏🙏 #ምንጭ፦ የመስከረም 8 ስንክሳር። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 🔔 https://t.me/zenaakidusan 🔔 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 🔔...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
Mostrar todo...
ዜና ቅዱሳን

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Repost from ዜና ቅዱሳን
Repost from ዜና ቅዱሳን
🕝🕝የካቲት 16🕝🕝 🍀ጻድቁ ንጉሥ ገብረ ማርያም/ሐርበይ/🍀 🌿🌿እንኳን ለኢትዮጵያዊው ለጻድቁ ንጉሥ ለላሊበላ ታላቅ ወንድም ለሆነው ለቅዱስ ገብረ ማርያም ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣በሰላም አደረሳችሁ🌿🌿 📚📚የላስታ ገሥታት የዘር ሐረጋቸው ከንጉሥ ሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡ ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ገደማ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ "የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት "ወይም" የላስታ መንግሥት" በመባል ይታወቃል፡፡ ከላስታ(ከዛጉዌ)ነገሥታት መካከል ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ቅዱስ ገብረ ማርያም፣ ቅዱስ ላሊበላና ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ እነዚህ አራቱ ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ(ዘፍ14፥18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሰውንም በቅድስናና፡ በንጽሕና አገልግለው አልፈዋል፡፡ 📚📚ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ገብረማርያም በሌላኛው ስማቸው ሐርቤይ እየተባሉ የሚጠሩ ሲሆን የቅዱስ ላሊበላ ታላቅ ወንድም ናቸው፡፡ ታላቁን ጻድቅ ንጉሥ ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብን ወልደዋል፡፡ አባታቸው ዣን ስዩም 40ዓመት ከነገሡ በኋላ በ76ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ልጃቸው ገብረ ማርያም ንግሥናውን ተቀብለዋል፡፡ ከእርሳቸው ቀጥሎ ታናሽ ወንድማቸው ቅዱስ ላሊበላ ተወልዶ እንደሚነግስ በትንቢት ተነግሮ፡ ነበር፡፡ ይህን ጊዜ ከላሊበላ ጋር በአባት እንጂ በእናት ይለያዩ ነበርና የበጎ ነገር ጠላት የሆነ ክፉ ሰይጣን የእኅታቸው ክፉ ምክር ተጠቅሞ በወንድማቸው በላሊበላ ላይ በቅናት ክፉ እንዲያስቡ አድርጓቸዋል፡፡ስለ ንግሥናቸው ሲሉ ምንም እንኳን በወንድማቸው ላይ ክፉ አስበው የነበረና በእኅታቸውም ክፉ ምክር መርዝ የሰጡት ቢሆንም በኋላ በክፉ ሀሳባቸው እጅግ ተፀፅተው "አምላኬንም ወንድሜንም አሳዘንኩ" በማለት ወንድማቸውን ይቅርታ በመጠየቅ ላሊበላን አንግሠውት እርሳቸው መንኵሰው ገዳም ገብተዋል፡፡ 📚📚ቅዱስ ላሊበላ ካለበት አክሱም ድረስ ሄደው በዕንባና በልቅሶ ይቅርታ ጠይቀው ወደ አገራቸው ሮሐ ከተማ ይዘውት በመምጣት መንግሥታቸውን አስረክበውት ነው የመነኑት፡፡ በምንኵስናም ሆነው በታላቅ ተጋድሎ በጾም በጸሎት በመትጋት እግዚአብሔርን እያገለገሉ እያለ ጌታችን ተገልጦላቸው "ክብሩ እንደ መላእክት የሆነ ታላቅ ልጅ ትወልዳለህና ወደቤትህ ተመለስ" ብሎ ከነገራቸው በኋላ ወደቤታቸው ተመልሰው ቅዱስ ነአኵቶ ለአብን ወልደዋል፡፡ 📚📚ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያም በዘመናቸው ከነበሩት ከእስክንድሪያ ሊቀ ጳጳሳት ከአባ ዳንኤል ጋር መልእክት በመላላክ "ከሀገሬ ሊቃውንት መነኰሳት የሕዝቡን ቋንቋ የሚሰሙና የሚያስተምሩ ጳጳስ ይሹሙልን" በማለት ለእስክንድሪያ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ 📚📚ምንም እንኳን የእስክንድሪያ ሲኖዶስ በወቅቱ ኢትዮጵያ የራሷንልጆች እንድትሾም ስላልፈለጉና በወቅቱ ፈቃደ እግዚአብሔርም ስላልነበረ የቅዱስ ገብረ ማርያምን ጥያቄ ንግሥት ዘውዲቱና ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድጋሚ በመጠየቅ ፍጻሜውን እንዲያገኝ ቢያደርጉትም መሠረቱን ግን የጣሉት ዐፄ ገብረ ማርያም ናቸው 📚📚በዘመናቸው ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንም ያሠሩ ሲሆን ጊዜ ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታችን ተገልጦላቸው "የእኔን መከራ እያሰብክ ከዓይንህ ዕንባ ሳያቋርጥ በጾም በጸሎት ተወስነህ ስላገለገልኸኝ በአንተ ስም ለተራበ ያበላውን፣ ለተጠማ ያጠጣውን፣ ለታረዘ ያለበሰውን ምሬልሃለሁ" በማለት ትልቅ ቃልኪዳን ሰጥቷቸው በካቲት16 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ ጻድቁን፡ንጉሥ ዐፄ ገብረ ማርያምን ሚያዝያ10 ቀን የሚነበበው ስንክሳር በሰፊው ይጠቅሳቸዋል፡፡ 🙏🙏ከጻድቁ ከአቡነ ገብረ ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን! ። 🙏🙏 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧 💧https://t.me/zenaakidusan 💧💧 💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧 .......... የቴሌግራም ቻናላችንን በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣የዜና ቅዱሳን ቤተሰብ ይሁኑ!!!
Mostrar todo...
ዜና ቅዱሳን

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.