uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Dn Abel Kassahun Mekuria

Dn Abel Kassahun Mekuria

Відкрити в Telegram

ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው። ይወዳጁን ለፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL ለyoutube https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_ ለInstagram https://www.instagram.com/abelkassahunm?igsh=OW

Показати більше

📈 Аналітичний огляд Telegram-каналу Dn Abel Kassahun Mekuria

Канал Dn Abel Kassahun Mekuria (@dnabel) у мовному сегменті Амхарська є активним учасником. На даний момент спільнота об'єднує 18 665 підписників, посідаючи 4 317 місце в категорії Релігія і духовність та 1 932 місце у регіоні Ефіопія.

📊 Показники аудиторії та динаміка

З моменту свого створення невідомо, проект продемонстрував стрімке зростання, зібравши аудиторію у 18 665 підписників.

За останніми даними від 02 листопада, 2026, канал демонструє стабільну активність. Хоча за останні 30 днів спостерігається зміна кількості учасників на 104, а за останні 24 години на -4, загальне охоплення залишається високим.

  • Статус верифікації: Не верифікований
  • Рівень залученості (ER): Середній показник залученості аудиторії становить 40.30%. Протягом перших 24 годин після публікації контент зазвичай збирає 10.95% реакцій від загальної кількості підписників.
  • Охоплення публікацій: В середньому кожен допис отримує 7 523 переглядів. Протягом першої доби публікація в середньому набирає 2 044 переглядів.
  • Реакції та взаємодія: Аудиторія активно підтримує контент: середня кількість реакцій на один пост – 228.

📝 Опис та контентна політика

Автор описує ресурс як майданчик для висловлення суб'єктивної думки:
“ይህ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያገኙበት በባለቤቱ የተከፈተ ቻነል ነው። ይወዳጁን ለፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12?mibextid=ZbWKwL ለyoutube https://youtu.be/s6Cn-jMYjrk?si=Tw7lXr62xkGQtL9_ ለInstagram https://www.instagram.com/abelkassahunm?ig...”

Завдяки високій частоті оновлень (останні дані отримано 03 листопада, 2026), канал підтримує актуальність та високий рівень охоплення публікацій. Аналітика показує, що аудиторія активно взаємодіє з контентом, що робить його важливою точкою впливу в категорії Релігія і духовність.

18 665
Підписники
-424 години
-67 днів
+10430 днів
Архів дописів
“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፡ በመዳንም ቀን ረዳሁህ፡ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው” 2ኛ ቆሮ 6:2
“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፡ በመዳንም ቀን ረዳሁህ፡ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው” 2ኛ ቆሮ 6:2

ቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ለ4ኛ ጊዜ ታትሟል። መጽሐፉን ፈልጋችሁ አጥታችሁት የነበራችሁ ሁሉ አሁን በየመጻሕፍት መደብሩ ታገኙታላችሁ። መልካም ንባብ! አምላከ ጳውሎስ ይታረቀን!
ቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ለ4ኛ ጊዜ ታትሟል። መጽሐፉን ፈልጋችሁ አጥታችሁት የነበራችሁ ሁሉ አሁን በየመጻሕፍት መደብሩ ታገኙታላችሁ። መልካም ንባብ! አምላከ ጳውሎስ ይታረቀን!

ሰው አያከብርህም? ሰው ሲሰድብህ ትናደዳለህ? የሚያዋርድ እና አንገት የሚያስደፋ ነገር ቢያደርግብህስ በቁጣ ትገነፍላለህ? ግን አንድ ጊዜ ቆም ብለህ እስኪ ራስህን ጠይቅ? ከአንተ በላይ አንተን የሰደበ፣ ከአንተ በላይ አንተን ያዋረደ እና አንገት የሚያስደፋ ነገር ያደረገብህ አለ? ከአንተ በላይ አንተነትህን ዋጋ ቢስ ያደረገ ማን ነው? አንተ አይደለህ? አንተው መልስ! ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚለው ለሰው ጠላቱ ማንም አይደለም፤ ራሱ ነው። የሕይወትን ዛፍ ቸል ብሎ ወደ እጸ በለስ የሚሮጠው፣ የብርሃኑን ልብሱን ጥሎ ቅጠል ማገልደም የሚያምረው፣ ከወንድሙ ጋር በሰላም ከመኖር ይልቅ ደሙን አፍስሶ ዚቅበዘበዝ መኖር የሚመርጠው ሰው ራሱ ነው። ሌላውን ከመውቀስህ በፊት መጀመሪያ አንተ ራስህን ታከብራለህ? በአንተ ዘንድ የአንተነትህ ዋጋው ስንት ነው? ከልብስ ይልቅ ሰውነትህን ከመብልስ በፊት ነፍስህን ታስቀድማለህ? አንተ ራስህን በክፋት እና በበደል እንዲህ እያጎሳቆልክ “ማንም አያከብረኝም” እንዴት ትላለህ? ዲያቆን አቤል ካሣሁን abelzebahiran@gmail.com https://t.me/Dnabel

photo content

እግዚአብሔርም በአደባባይ የማይወቅሰን ፍቅር እንጂ እልህ እንዳያሸንፈን ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ: “ጥፋተኛን ሰው የፈለገ ብትወቅሰው የኅሊናውን ያህል ግን ከሳሽ ልትሆንበት አትችልም” ይላል። አ
እግዚአብሔርም በአደባባይ የማይወቅሰን ፍቅር እንጂ እልህ እንዳያሸንፈን ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ: “ጥፋተኛን ሰው የፈለገ ብትወቅሰው የኅሊናውን ያህል ግን ከሳሽ ልትሆንበት አትችልም” ይላል። አንተ ስታገኘው ይሆናል “እንዲ አደረግህ” ብለህ ጥፋቱን የምትነግረው፤ ሕሊናው ግን የትም ሸሽቶ ሊያመልጠው በማይችል በማያቋርጥ ጩኸት ቀን እና ሌት ይወነጅለዋል። https://t.me/Dnabel

የአርሲ ክርስቲያኖችን (ራሳችንን) ባሰብን ጊዜ! #በተደጋጋሚ ክርስቲያን ወንድም እና እኅቶቻችን ላይ እየሆነ ያለውን ሳስብ፣ ከግሪካዊው ኤዞፕ ተረቶች አንዱ ትዝ ብሎኝ ይህን ግጥም አስጫረኝ። አንድ
የአርሲ ክርስቲያኖችን (ራሳችንን) ባሰብን ጊዜ! #በተደጋጋሚ ክርስቲያን ወንድም እና እኅቶቻችን ላይ እየሆነ ያለውን ሳስብ፣ ከግሪካዊው ኤዞፕ ተረቶች አንዱ ትዝ ብሎኝ ይህን ግጥም አስጫረኝ። አንድ ጊዜ ቀበሮ በግን ምግቤን ሰርቃ በላችብኝ ብሎ በሐሰት በመክሰስ ሸንጎ ፊት አቆማት። በጓም እየተገረመች “ኸረ እኔ ሣር እንጂ ሥጋ አልበላም። ምን ብዬ የእርሱን ምግብ እሰርቃለሁ” አለች። ነገር ግን የፍርድ ቤቱ ዳኛ ተኩላ ስለ ነበር፤ “አንቺ በግ ምንም ምግቡን ባትበይ እንኳ መከራከሪያሽ አሳማኝ አይደለምና ጥፋተኛ ነሽ። ስለዚህ ሥጋዋ ታርዶ ለፍርድቤቱ አባላት ይከፋፈል። ቆዳዋ ደግሞ ለከሳሽ ቀበሮ ይሰጥ” ብሎ ፈረዱባት።(ታሪኩን ካነበብሁ ስለቆየሁ በብዥታ ነው የተረክሁት) ፍትሕ ከወዴት ትምጣ?! https://t.me/Dnabel

“እግዚአብሔር እረኛዬ ነው!”
“እግዚአብሔር እረኛዬ ነው!”

“ ‘ወዳጄ ሆይ፥ የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?’ አለው እርሱም ዝም አለ” ማቴ 22:12 እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ይህን የይቅርታ ልብስ ካለበስን ወደ ሰርጉ አንገባም። ጌታ ሆይ ለዚህ
“ ‘ወዳጄ ሆይ፥ የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?’ አለው እርሱም ዝም አለ” ማቴ 22:12 እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ይህን የይቅርታ ልብስ ካለበስን ወደ ሰርጉ አንገባም። ጌታ ሆይ ለዚህ የሰርግ ልብስ የተገባን አድርገን!!!

የምቹ ጊዜ እና የሰንበት ብቻ ክርስቲያን አንሁን!
የምቹ ጊዜ እና የሰንበት ብቻ ክርስቲያን አንሁን!

“እርሱ ግን መሐሪ ነው፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፤ ቍጣውንም መመለስ አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም” መዝሙር 78:38

እንደማይድን የተነገረንን የሥጋ ቁስል እንኳ “በምናልባት” ተስፋ የምንንከባከብ ከሆነ፣ የሚድነውን የነፍስ ቁስል ቶሎ ለማድረቅ እንዴት ዳተኞች ሆንን?
እንደማይድን የተነገረንን የሥጋ ቁስል እንኳ “በምናልባት” ተስፋ የምንንከባከብ ከሆነ፣ የሚድነውን የነፍስ ቁስል ቶሎ ለማድረቅ እንዴት ዳተኞች ሆንን?

አሜን፤ አእምሯችን ሁልጊዜ ያልለመደውን ወይም አዲስ የሆነን ነገር ስናስተምረው በቀላሉ ለመቀበል ዝግጁ አይሆንም። ዝግጁ አለመሆኑን ወይም መጨናነቅ እንደማይፈልግ ደግሞ ከሚያሳይባቸው መንገዶች መካከል
አሜን፤ አእምሯችን ሁልጊዜ ያልለመደውን ወይም አዲስ የሆነን ነገር ስናስተምረው በቀላሉ ለመቀበል ዝግጁ አይሆንም። ዝግጁ አለመሆኑን ወይም መጨናነቅ እንደማይፈልግ ደግሞ ከሚያሳይባቸው መንገዶች መካከል አንዱ መፍዘዝ እና ቶሎ ተዳክሞ እንቅልፍ እንቅልፍ ማለት ነው። በአጭሩ “ተወኝ” ማለቱ ነው። ታዲያ ለዚህ ጥያቄው መልሳችን መጽሐፉን አጥፎ ወደ አልጋ መሄድ ከሆነ አእምሯችን መጽሐፍ ማንበብን መቼም ሊለምደው እና ሊቀበለው አይችልም። ነገር ግን እየታገልን የቻልነው ድረስ ለመሄድ ከጣርን ግን “እሺ” እንዳላልነው ስለሚረዳ በጊዜ ከንባብ ጋር ለመስማማት ራሱን ዝግጁ ያደርጋል። ንባብ ለአእምሮ: ፊደላትን ከመለየት እና ገጣጥሞ ቃል እና ዓረፍተ ነገር አድርጎ ከማንበብ ጀምሮ፣ ትርጉሙን ማውጠንጠን እና መጨረሻም ላይ ጭብጡን ለመረዳት መሞከር የሚጠይቅ ከባድ ተግባር ነው። ለዚያ ነው መጀመሪያ “ተዉኝ! አታድክሙኝ” የሚለው 😊

ንባብ እና እንቅልፍ (ላነብ መጽሐፍ ስይዝ እንቅልፌ ይመጣል ምን ተሻለኝ?) የሚያነቡ ሰዎች በበጎ ያስቀኑህና ንባብ ልትጀምር ለራስህ ትወስናለህ፡፡ ከዚያም በዕረፍትህ ቀን ሰዓት አመቻችተህ ልታነብ ገና ከመቀመጥህ ከየት እንደ መጣ የማታውቀው ኃይለኛ እንቅልፍ በዓይንህ ዙሪያ ያንዣብባል፡፡ አንዴ ከመጽሐፉ አንዴ ከገዛ እጅህ ጋር እያጋጨ መከራህን ያሳይሃል፡፡ በመጨረሻም ትግሉ ሲሰለችህ ልታነብ ያነሣኸውን መጽሐፍ ተንተርሰኸው ለጥ ትላለህ፡፡  ቆይ ንባብና እንቅልፍን የሚያያይዛቸው ነገር ይኖር ይሆን? ከሥራ ብዛት ወይም በኑሮ መክበድ ምክንያት የአእምሮ ውጥረት (Stress) ላጋጠማቸው ሰዎች ውጥረቱን ለመቀነስ በሥነ ልቡና ባለሙያዎች ከሚመሰጣቸው ምክሮች ውስጥ አንዱ ‹መጻሕፍትን አንብቡ› የሚል ነው፡፡ በዚህ ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች መጻሕፍትን በሚያነቡበት ጊዜ ከቆዩበት ጭንቀት ለመውጣት መጽሐፍቱ እንደ በር ስለሚያገለግሏቸው ተወጣጥሮ የነበረው ኅሊናቸው ነጻ የመሆን እድል ያገኛል፡፡ ሰውነትህ ደግሞ ከውጥረት ነጻ መሆኑን ከሚገልጽባቸው ምልክቶቹ ውስጥ አንዱ እንቅልፍ ነው፡፡ ስለዚህ ንባብ አንዳንድ ጊዜ ለአእምሮ ውጥረት መድኃኒት በመሆን ከእንቅልፍ ጋር ሊተሳሰር ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ከውጥረት ለመውጣትም ቢሆን መጀመሪያ መጽሐፉ ሊነበብ ይገባል፡፡ ሳታነብ እንቅልፍ የሚወስድህ ከሆነ ግን ይህ ንባብ ያልለመደ ሰውነት ምልክት ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ነገሮች በዝግታ አጢን ➢ ለመጻሕፍት ንባብ ገና ጀማሪ ከሆንክ የመጽሐፍ ምርጫህን አስተካክል፡፡ የምታነበው መጽሐፍ ብዙ ቁም ነገር ቢኖረውም አቀራረቡና ሥነ ጽሐፋዊ ውበቱ ብዙም ካልሆነ፣ ውስጥህ ጭል ጭል የሚለውን ትንሽ የንባብ ብርሃን እስከ መጨረሻው አጥፍቶ ከመጻሕፍት እንዳይለይህ ቶሎ እርምጃ ውሰድ፡፡ በአቀራረባቸው የተመሰገኑ መጻሕፍትን እንዲጠቁሙህ የንባብ ልምድ ያላቸውን ሰዎች አማክር፡፡ እነርሱንም አስቀድም፡፡ ➢ ለንባብ የሚሆን ደመቅ ያለ ብርሃን ያለበትና ምቹ ቦታ መምረጥ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን የተጋነነ ምቾት ወደ እንቅልፍ ሊወስድህስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ጋደም ከማለት ይልቅ ቁጭ ብለህ ማንበብ የበለጠ ንቁ ያደርግሃል፡፡ ደግሞ መንፈሳዊ መጻሕፍትን እንደ ታመመ ሰው ተኝተህ ማንበብ አግባብ አይደለም፡፡ በል ቶሎ ተነሥ፡፡ ➢ ሰይጣን የሚጸልዩ ሰዎችን የሚፈትነውን ያህል የሚያነቡ ሰዎችንም ይዋጋል፡፡ ለጸሎት በቆመ ሰው ዓይኖች ላይ የእንቅልፍ ሽፋሽፍትን እንደሚያመጣ፣ መንፈሳዊ መጻሕፍትን ለማንበብ በተዘጋጁ ዓይኖች ላይም እንቅልፍ እንዲከብድ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ስትሆን ፈጥነህ ለጸሎት ተነሥ፡፡ የሚቃወምህን ክፉ መንፈስ ‹‹እክህደከ ሰይጣን›› በማለት ገስጸው፤ አውግዘው፡፡ አንብበህ ተለውጠህ ፈጣሪህን እንዳታስደስት የሚቃወምህን ረቂቅ ባላጋራ ‹ንባብህን ትተህ በመተኛት› ደስ አታሰኘው፡፡ መላልሰህ እየተጋህ ተስፋ አስቆርጠው፡፡ ዲያቆን አቤል ካሣሁን abelmekuria2@gmail.com

ነገ!!!
ነገ!!!

“ከኃጥአን የኀዘንን ሸክም የሚያቀለው ደስታ ከአንቺ ተወለደ” “ዘያቀልል እምኃጥአን ፆረ ኀዘን እስመ እምኔኪ ፍስሐ ተወልደ” መልካም የማኅሌተ ጽጌ ቁመት!!!

እስኪ የርእሰ ማዕምራን መሪጌታ ብርሃኑ ውድነህን ውድ መዝሙር ልጋብዛችሁ። እጅግ በሚመስጥ ግጥም እና በሚያራራ ዜማ የተከሸነ ነው። ስሙት እና ውቀሱኝ! https://youtu.be/ufcU-6jLDxU?si=P881REKjOEGWM5ZP

እመቤታችን ታዛችን፣ መደገፊያ የሃይማኖት በትራችን ከመውደቅ ትሰውረን። ከወደቅንም ፈጥና ታንሣን፤ አትተወን!!!
እመቤታችን ታዛችን፣ መደገፊያ የሃይማኖት በትራችን ከመውደቅ ትሰውረን። ከወደቅንም ፈጥና ታንሣን፤ አትተወን!!!

እግዚአብሔር የሚፈራ ሰው ምን ያስፈራዋል?! አምላካችን “እግዚአብሔር ማን ነው?” ብለው የተገዳደሩት ትዕቢተኞቹ እነ ፈርዖንን ያስጨነቀው በምድር ላይ በጣም ትንሽ በሆኑ እና በሚናቁ እንደ ዝንብ እና እንቁራሪት ባሉ ነፍሳት ነው። በፊቱ ራሳቸውን ዝቅ ያደረጉ እነ ዳንኤል ግን ለተራቡ አናብስት ቢሰጡ፣ ሦስቱ ወጣቶች ደግሞ ወደሚንቀለቀል እሳት ቢጣሉም ልባቸው ለደቂቃ እንኳ አልደነገጠም። እግዚአብሔርን የሚደፋፈሩ ሰዎች በጥቂት ነገር ሲፈሩ ሲጨነቁ ይታያሉ። እርሱን የሚፈሩ ግን በምድር ሌላ ምንም የሚያስፈራቸው ነገር የለም። “አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም” መዝ 23:4 ዲያቆን አቤል ካሣሁን መስከረም 26 - 2019 ዓ. ም. (የትኛው ድርሳኑ ላይ እንዳነበብሁት አሁን ከተዘነጋኝ የሂፖው ሊቀ ጳጳስ አውግስጢኖስ የተገኘ ምክር)

+++ በዚህ ንጉሥ ታምናለህ? +++ በሐዲስ ኪዳን ከተጻፉ እና ስለ እምነት ሲነሣ በጣም ከሚያስደንቁኝ ታሪኮች መካከል አንዱ የሰብአ ሰገል ታሪክ ነው። ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠው ወደ ቤተልሔም ዋሻ የመጡት ሰዎች የሩቅ ምሥራቅ ነገሥታት ነበሩ። የንግሥናን ምንነት እና ክብር ሲወራ ሰምተው ወይም ከመጻሕፍት አንብበው ሳይሆን በመሆን ያውቁታል። በብዙ ሠራዊት ታጅበው ከያሉበት የወጡትም “የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ” ፍለጋ ነበር። ይሁን እንጂ ንጉሡን ያገኙት ግን በጦር አለቆች ተከቦ፣ ባማረ እልፍኝ ውስጥ ቅንጡ አልጋ ላይ ተኝቶ፣ ውድ በሆነ የተልባ እግር ጨርቅ ተሸፍኖ አልነበረም። ምስኪኗ ድንግል ማርያም ታቅፋው፣ ደካማው ሽማግሌ ዮሴፍ ከፊቱ ቆሞ፣ እንስሳት ከበውት፣ ባረጀ ጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ነው ያዩት። ታዲያ ይህን በመመልከታቸው ንጉሥነቱን አልተጠራጠሩም። ለምን? ብለውም የምርምር ጥያቄም አላቀረቡም። በዝምታ ውስጥ ያለ ጠንካራ እምነታቸውን እንደ ያዙ ወድቀው ለጌትነቱ ሰገዱለት። እጅ መንሻም አቀረቡለት። ልዑሉን አምላክ በትሕትናው ወራት አለመጠራጠር እንዴት ያለ እምነት ነው? እነዚህ የሩቅ ምሥራቅ ነገሥታት ለእኔ ከጥበብ ሰውነታቸው በላይ የእምነት ሰውነታቸው ይበልጥብኛል። እነሆ እግዚአብሔር ስለ እኛ ድኅነት ሲል ራሱን ባዶ ያደረገ ሰው በመሆን አንድ ጊዜ ዝቅ ካደረገ በኋላ እንግዲህስ ሁለተኛ ተዋርዶ የለበትም። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔርን ልዕልና እና ትሕትና የምታየው በአንተ ሕይወት ውስጥ ነው። ከፍፍ ሲያደርግህ ልዕልናውን፣ በመናቅ እና በመረሳት ውስጥ እንድታልፍ ሲያደርግህ ደግሞ ትሑት አምላክ መሆኑን ትረዳለህ። ነገር ግን አንተ በየትኛው ሁኔታ ብታየው ነው ንጉሡን የምታምንበት? ሁልጊዜ ተአምር ሲያደርግ፣ ከእሳት ነጥቆ ሲያወጣህ እና በከፍታው ላይ ሲያቆምህ ብቻ ነው ወይስ በሕመም እና በደዌ፣ በብዙ ውርደት እና መናቅ፣ በበረት ውስጥ እንደ ማደር እና ብጫቂ እንደ መልበስ ባዶ ሲያደርግህም ጭምር እንደ ሰብአ ሰገል በዝምታ ውስጥ ታምነዋለህ? ወድቀህስ ትሰግድለታለህ? ዲያቆን አቤል ካሣሁን መስከረም 24 - 2019 ዓ. ም. ቻይና፣ ጓንዡ