قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Відкрити в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
912
Підписники
-224 години
-127 днів
+5130 днів
Архів дописів
ያ ረቢ! ከሃሳብ ክብደትና ከልብ ጭንቀት አቅልልልኝ፤ ነገሬን ሁሉ ላንተ አደራ ሰጥቻለሁ።ጌታዬ ሆይ! እኔ በሚታየኝ ሳይሆን አንተ ለኔ መልካም ነው ብለህ በምታየው ነገር ልቤን አረጋጋው።
ያ ረቢ! ከሃሳብ ክብደትና ከልብ ጭንቀት አቅልልልኝ፤ ነገሬን ሁሉ ላንተ አደራ ሰጥቻለሁ። ጌታዬ ሆይ! እኔ በሚታየኝ ሳይሆን አንተ ለኔ መልካም ነው ብለህ በምታየው ነገር ልቤን አረጋጋው።
ያ ረቢ! ከሃሳብ ክብደትና ከልብ ጭንቀት አቅልልልኝ፤ ነገሬን ሁሉ ላንተ አደራ ሰጥቻለሁ። ጌታዬ ሆይ! እኔ በሚታየኝ ሳይሆን አንተ ለኔ መልካም ነው ብለህ በምታየው ነገር ልቤን አረጋጋው።
t.me/ibrahim_furii
Repost from ስለ ቀልባችን
🤍ቀልብ እረፍት የምታገኘው፣ ወጣትነትም ከፈተና የሚጠበቀው በሐላል ጎጆ (በትዳር) ጥላ ስር ነው።
በአላህ ፈቃድ በዚሁ «ስለ ቀልባችን» ቻናላችን ላይ፤
✔️ ወደ ትዳር ለመግባት ላሰቡ፣
✔️ ትዳር ለዘገየባቸው፣
✔️ በትዳር ውስጥ ላሉና ቤታቸውን በሰኪና መምራት ለሚፈልጉ ሁሉ...
🌸ከትዳር ማሰብ ጀምሮ እስከ ስኬታማ የትዳር ሕይወት አመራር ድረስ የሚያመላክት አንዲት ድንቅና አጭር ኪታብ በቅርቡ እንጀምራለን፣ ኢንሻ አላህ!
🎯የቻናላችን ዋነኛ ዓላማ ቀልብን ማስተካከል እስከሆነ ድረስ፣ ወጣቱን ከዝሙት ታድጎ ወደ ሐላል ጎጆ ማመላከት የትምህርቱ ትልቁ አካል ነው ብለን እናምናለን።
በዚህ ሐሳብ ላይ ምን ትላላችሁ? 👍
📱➔ t.me/Sle_qelbachn1
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
ትንሽ ደግነት፤ ትንሽ መረዳት
ለአንዱ የመታፈን ያክል ስቃይ የሆነው ነገር፣ ለሌላው የመተንፈስ ያክል የነፃነት ማዕበል ነው። ስቃይ አንፃራዊ ነው። ማን በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለ አናውቅም።
የማንንም ስቃይ ልንረዳ አንችልም። የሰዎችን ስቃይ ሙሉ በሙሉ መረዳት አይታሰብም። ይህም በሁለት ምክንያት ነው። አንድ፣ እንርሱን መሆን አንችልም። ሁለት፣ እነርሱ ያሉበት ሁኔታ ውስጥ መግባት ይሳነናል። የእነርሱ ሁኔታ ውስጥ ብንገባ እንኳን፣ እንርሱን መሆን መቼም አንችልም፤ ተፈጥሮ ነውና!
ስለዚህ መፍትሔውም ሁለት ነው። ሰው ምንም «ክፉ» ይሁን ከመውቀሳችን በፊት፣ ትንሽ ደግንት፤ ትንሽ መረዳት እንስጣቸው። እኛ እነርሱ የዋሉበት አልዋልንምና፣ ባለፉበት አላልፍንምና፣ ከምንም በላይ እነርሱን አይደለንምና!
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
Repost from Abu~Mahi Channel
ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ ሀብት ወይም ስልጣን አይስፈልግህም።
ለተከፋው ሰው አፅናኝ ቃል መናገር ቅንነት ነው።
መንገድ ለተሳሳተው አቅጣጫ መጠቆም ቅንነት ነው።
በችግር ላይ ላለ ሰው የቻሉትን ያህል እጅ መዘርጋት ቅንነት ነው።
ለሌሎች ስኬት ከልብ መደሰት ታላቅ ቅንነት ነው።
ዓለምን የበለጠ ውብ እና መኖሪያ ለማድረግ ትልቁ መሳሪያ በእጃችን ያለው ቅንነት ነው። ዛሬ የምንዘራው የቅንነት እና የመረዳዳት ዘር፣ ነገ ፍሬ አፍርቶ የብዙዎችን ህይወት ይታደጋል።
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_IdrisRepost from ABU MUSLIM A-DUROOS
📢 ማስታወስ
🔶 ዛሬ ማታ በአላህ ፈቃድ በቀጥታ ስርጭት በቴሌግራም እና በዩቱብ ኪታብ ደርስ ይኖረናል።
📚 المستوى التمهيدي - الأذكار والآداب
📚 አል-ሙስተዋ አል-ተምሂዲ - አል-አዝካር ወል-አዳብ
(የመግቢያ ደረጃ - ዚክሮች እና ስነ-ምግባራት)
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
🗓 ቅዳሜ ረቢኡል አኺር 08/1447 ሂጅሪ, (መስከረም 09,2019),
⏰ ሰዐት: ማታ 3፡00 (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር)።
🕌 ቦታ: ቀጥታ ስርጭት በቴሌግራም (Telegram) እና በዩቱብ (YouTube)
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
🎙 الأُسْتَاذُ أَبُو مُسْلِمٍ عُمَرُ بنُ حَسَنٍ الْعَرُوسَيّ
🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)
📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/AbumuslimAlarsi
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"እኛ ከአቡበክር፣ ከዑመር እና ከዓኢሻህ ጋር ጦርነት ላይ ነው ያለነው" ይላል ይሄ ሑሢ። አዎ ጥላቸውና ጥላቻቸው የዐሊይን ስልጣን ነጥቀዋል ከሚሏቸው ኸሊፋዎች፣ ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰላም ሶሐቦች እና እነሱን ከሚወዱ ሱኒ ሙስሊሞች ጋር ነው። አንዳንድ ሞኞች ግን ጦርነቱ የሃይማኖት አይደለም ይላሉ። ጦርነቱ የሃይማኖት እንደሆነ ራሳቸው ሑሢዮቹ በቃልም በተግባርም ደጋግመው አሳይተዋል። በርካታ የሱኒ መስጂዶችን አጥቅተዋል፣ መጨፈሪያ አድርገው አርክሰዋል። ከደማጅ እነ ሸይኽ የሕያን እና ተማሪዎቹን አፈናቅለዋል። ከመሪዎቹ ጀምሮ የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰላም ሶሐቦች ባደባባይ ዘልፈዋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ተጫጭተናል ማለት ተጋብተናል ማለት አይደለም!
~
በነገራችን ላይ...እጮኝነት ማለት ኒካህ አይደለም! እጮኝነት ማለት «ወደፊት ልንጋባ አስበናል» የሚል የተስፋ ቃል ብቻ ነው።
ኒካህ እስከሌለ ድረስ እሷ ላንተ አጅነቢይ ናት፤ አንተም ለእሷ ባዕድ ወንድ ነህ። ብዙዎች አያስተውሉትም እንጂ፣ በርካታ ትዳሮች ገና በጠዋቱ የሚፈርሱት፣ የተሳኩ እንዳይሆኑ የሚቀሰፉት ከተጫጩ በኋላ በሚሰሩት ስህተት ምክንያት ነው።
ሸይጧን ወደ ዝሙት የሚያስገባው በአንድ ጀምበር አይደለም፤ ደረጃ በደረጃ ነው።
➔ መጀመሪያ «እሱኮ የወደፊት ባልሽ ነው ማውራት ትችላላችሁ» ይላችኋል።
➔ ቀጥሎ ከእኩለ ሌሊት የስልክ ወሬዎች ጋር ድንበር የለሽ የፍቅር ቃላት ይጀመራሉ።
➔ ከዚያም በአይንም፣ በልብም፣ በምላስም ዝሙት ውስጥ ትወድቃላችሁ።
➔ በመጨረሻም ገደቡ ተሰብሮ አካላዊ ዝሙት ላይ ይደረሳል።
ታድያ በአላህ ቁጣና በሀራም የተበከለ ግንኙነት በምን ሂሳብ ሰላማዊ ትዳርን ሊወልድ ይችላል?!
ፍቅር ልክ እንደ ንፁህ ፍሬ ነው። ሰዓቱን ሳይጠብቁ ጥሬውን በሀራም የለቀሙት እንደሆነ፣ ሰርጉ ቀን ሲደርስ የሚበላ
ጣፋጭ ፍሬ አይገኝም። ለትዳር የተጠበቀው ናፍቆት፣ ክብርና ሀያዕ በእጮኝነት ዘመን ይሟጠጣል። ሰርግ ተብሎ ወደ አንድ ቤት ሲገቡ ፍቅሩ አልቋል፤ ወንጀሉ ልብን አድርቆታል፤ በረካውም ርቋል። መጨረሻው ወይ በፀፀት ማልቀስ፣ ወይ በትንሽ ነገር መጣላትና ወደ ፍቺ መሮጥ ይሆናል።
እሳትን እቅፍ ውስጥ አስገብቶ «አይፈጅም» አይባልም። ወጣትነት፣ ስሜት እና የሸይጧን ጉትጎታ ተደምረው እንዳያጠፏችሁ ብልሆች
ሁኑ!
◇ ከተዋደዳችሁና ቤተሰብ ከወሰነ — ወዲያው ኒካህ እሰሩ!
◇ «ሰርግ ለማዘጋጀት ጊዜ ይፈልጋል፣ ቤት አልተሟላም፣ ድግስ አለብን...» የሚሉ ሰበቦች የሸይጧን ቀዳዳዎች ናቸው። ድግሱና ሰርጉ አመቺ በሆነ ቀን፣ አቅም ሲፈቅድ ይሁን፤ ነገር ግን ኒካሁ አስቀድሞ ይታሰር!
◇ ኒካህ የታሰረለት ግንኙነት ጥበቃ አለው፤ የአላህ እዝነትና በረካ አለበት። ወንጀል የለም፣ ፍርሃት የለም፣ የሕሊና ፀፀት የለም።
መልእክቱ ግልጽ ነው! የወደፊት ህይወታችሁን በሀራም መሰረት ላይ አትገንቡ። ሀላል ሲዘገይ ለሀራም በር ይከፈታል። ፍቅራችሁ ሳይረክስ፣ ክብራችሁ ሳይጎድፍ፣ የነገው ትዳራችሁ መርገምት ሳይሆን በረካ እንዲሆን ከፈለጋችሁ እጮኝነትን አሳጥሩ፤ ኒካህን
አስቀድሙ!
--
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
Repost from 💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
🔖የወንጀል ተፅእኖና ውጤቱ!
قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله
اعلم أن للمعاصي آثارا على الأخلاق وعلى الأعمال، قال الله تعالى: "فلما زاغوا أزاغ الله قلوبهم"، فقوله تعالى: "فلما زاغوا" هذا عمل سيئ نتيجته: "أزاغ الله قلوبهم" فالأعمال السيئة لها آثار وخيمة؛ ولهذا يجب على الإنسان إذا صدرت منه السيئة أن يبادر بالتوبة، حتى لا تبقى هذه الجرثومة في قلبه فتؤثر عليه.
(شرح فتح رب البرية / ص17)~እወቅ ወንጀል በስነምግባር ፦በስራችን የሚያሳድረዉ ተፅእኖ ፋና አለዉ ። ~ወንጀል ስነምግባርን ያበላሻል። ~ወንጀል ሰርተን ሰዉነታችን ለኢባዳ አይነሳሳም። فلما زاغوا أزاغ الله قلوبهم"، ~ሲዘነበሉ (ቅናቸዉን መንገድ ሲለቁ) አላህ ልባቸዉን አዘነበለዉ። t.me/https_Asselfya
Repost from فوائد الشيخ صالح بن فوزان الفوزان
قال العلامة صالح الفوزان حفظه الله:
الواجب على المسلم قبل أن يتكلم أن يزن كلامه، وينظر عواقبه وآثاره قبل أن ينطق به، وأن يزن كلامه بالميزان الصحيح، إن كان كلامه يسبب الخير يتكلم، وإن كان كلامه يسبب الشر يمسك شره عن النّاس .
🗞 شرح كتاب الفتن والحوادث (ص239)
🔗رابط القناة على التيليجرام :
https://t.me/fawayidalfawzan
Repost from ስለ ዲናችን
🎙በኡስታዝ አረቡ ሰዒድ ሀፊዘሀሏህ
ስለ ኢልም
🕌በደገር ከተማ ዑሙ አይመን መስጂድ የተደረገ
ሸር ይደረግ ይደመጥየቴሌግራም ቻናል https://t.me/Yedeger_selefioch_jemea
Repost from N/a
📔ሀዲሶች፣ቁርዐን እና ልብ የሚነኩ ዲናዊ ምክሮች የሚያገኙበት ተወዳጅ ቻናል ተጋበዙልኝ🙌
✨ሙስሊም ፈፅሞ አይዋሽም✨❕🗯
ኡስታዛችን ሙሐመድ አህመድ ሙነወር(ኢብኑ ሙነወር) አላህ ይጠብቀው እና፦የብዙ ወጣቶች ተምሳሌት፤ የሱና ጀግና የቢድዐ ጠላት፤ ሱናን በብዕሩ ሀይ ያደረጋት፤
ቢድዐን እና ሙብተድዕን ከመሬት ያስገባት፤ ሀገራችን ካገኘቻቸው ድንቅ የተውሂድ ተጣሪያን ውስጥ #አንዱ ነው። ኡስታዝ ሙሐመድ አህመድ ሙነወር ምርጥ የሱና ኡስታዛችን ነው። እናከብረዋለን። እንወደዋለን። አላህ በዕዝነቱ ይጠብቅልን። ጀዛውንም እጥፍ ድርብ ያድርግለት። መሰሎቹንም ያብዛልን። ከዚህም በላይ ገና ብዙ ነገር እንጠብቃለን።ኢንሻ አላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
@IbnuMunewor
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
Repost from ኑ የራያ ሰለፍዩችን መስጅድ በጋራ እንገንባ
⏰የወቅት አሳሳቢነት🎧
🥀በኡስታዝ አቡ ዓምር🥀
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/+yxwTU-Sx-7szZGVk
Repost from « ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም፡፡
⚠️ተውሒድ ማለት እንዲሁ የምንሸመድደው የመጽሐፍ ገጽ፣ በብዕር የምንከትበው ቃል ወይም በሚንበሮች ላይ የሚደረግ ደረቅ ንግግር ብቻ አይደለም። ተውሒድ ማለት ከልብ ጥልቀት የሚመነጭ፣ በደም ስራችን ውስጥ የሚፈስና ሙሉ ሕይወታችንን ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ብቻ የምናስገዛበት የታላቅነት መገለጫ ነው። ተውሒድ ማለት በልብ ውስጥ ከአንድ አምላክ ከአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ውጭ ሌላን ኃይል አለማስገባት፣ በምክንያቶች ሳይሆን በምክንያቶች ፈጣሪ ላይ ብቻ
መመካት ነው።
እወቁ... ከአላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى በስተቀር አድራጊ የለም! የሚጠቅመውም፣
የሚጎዳውም፣ የሚያከብረውም፣ የሚያዋርደውም፣ የሚያበለጽገውም፣ የሚያደኸየውም፣ ሕይወት የሚሰጠውም፣ የሚገድለውም እርሱ ብቻ ነው። ፍጡራን ሁሉ ደካሞች ናቸው፤ ሐኪሞች ይታመማሉ፣ መሐንዲሶች ይሳሳታሉ፣ ኃያላን ይወድቃሉ። አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ግን የዓለማቱ ጌታ፣ የሰማያትና የምድር ብቸኛ አስተናባሪ ነው። ፀሐይን ያለ ስህተት በምህዋሯ የሚያስኬደው፣ ሰማያትን ያለ ምሰሶ የጠበቃቸውና አንዲት ቅንጣት እንኳ የማታመልጠው ሐፊዝ (ጠባቂ) የሆነው ጌታ እርሱ ነው። አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ለነቢዩ ሙሳ عَلَيْهِ السَّلَامُ እንዳለው፦ "ሙሳ ሆይ! እኔ ብተኛ ኖሮ ሰማያት
በምድር ላይ ይወድቁ ነበር።" ነገር ግን እርሱ የማይተኛ፣ የማይረሳና ሁልጊዜም ከባሮቹ ጋር የሆነ ኃያል ጌታ ነው።
አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ካንተ ጋር ከሆነ ከማን ትሰጋለህ? በሕመምህ ሰዓት ወደ አላህ ተጠጋ። የትዳር አጋርህ ስታስቀይምህ ወደ አላህ ጩህ። ልጅህ ሲከዳህ ወደ አላህ ተመለስ። ጭንቀትህ ሲበዛና ሲሳዩ ሲጠብብህ የመውጫውን በር ከአላህ ዘንድ ፈልገው። ሰዎች ቢርቁህ ወደ አላህ ቅረብ፤ ምክንያቱም የሁሉ ነገር ቁልፍ ያለው በእርሱ እጅ ብቻ ነውና። እነዚያ ‹ኃያላን ነን›
ያሉትን ፈርዖንንና ሰሙድን አላህ የት እንዳደረሳቸው ታሪክ ምስክር ነው? በእርሱ ፊት የትኛው ምድራዊ ኃይል ይቆማል ነገር ግን? አላህ የፈለገውን ሰሪ ነው። የእርሱ ትእዛዝ አይመለስም፣ የእርሱ ኃይል አይገታም።
ስለዚህ በየትኛውም የሕይወት አጣብቂኝ ውስጥ ብንሆን፣ ልክ ነቢዩ መሐመድ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ በዋሻ ውስጥ ሆነው ለጓደኛቸው ለአቡ በክር رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ እንዳሉት እኛም ለነፍሳችን እንዲህ እንበላት፦ "አትዘን! አላህ ከእኛ ጋር ነው!"።
እውነተኛ ተውሒድ ይኸው ነው! ሰላም
የሚገኘው ወደ አላህ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى በመቃረብና በእርሱ ውሳኔ በመርካት ውስጥ ብቻ ነው። ዛሬም ነገም
ለስኬትና ለደስታ የሚበቃው አላህን ብቻ መከታ ያደረገ ልብ ነው።
ኢላሒ..! በልባችን ውስጥ እውነተኛውን ተውሒድ ዝራብን። ካንተ ውጭ ላለ ማንኛውም ኃይል እንዳንሰግድና እንዳንዋረድ በእምነታችን አጽናን። መጨረሻችንንም በተውሒድ ቃል አሳምርልን።
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
አሰላሙ ዓለይኩም
ተቋርጠው የነበሩ ደርሶች ዛሬ ይጀመራሉ ኢንሻአላህ ለነበረው የቂርአት መቆራራጥ በድጋሜ ይቅርታ ለማለት እወዳለሁ።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከዝምታህና ከመናገርህ የትኛው ይበልጣል?
~
ሸይኽ ወይም ኡስታዝ ነህ? ለጠየቀህ ሁሉ አትመልስ። በቅንነት የሚጠይቅ እንዳለ ሁሉ ብዙ ተንኮለኛም አለ። መልሱ የሚጠቅመው እንዳለ ሁሉ የሚጎዳውም አለ። "እነ እከሌ እንዲህ አሉ" "እከሌ እንዲህ አለ" ሲሉት ለአፍታ እንኳ ፋታ ወስዶ ሳያጣራ በደመነፍስ መደንፋቱን ጀብድ የሚያደርግ ብዙ ሰባኪ አለ። ትምህርት ከጥሩዎች ብቻ ሳይሆን ከመጥፎዎች ሁኔታም ይወሰዳል።
አንዳንዴ ጥያቄው የቀረበበትንም ድባብ ማየት ጥሩ ነው። ህዝብ ፊት የቀረበ ጥያቄ ለጠያቂው ቢያሳስብም ለታዳሚው ህዝብ ፈተና ሊሆን ይችላል። ከመመለስህ በፊት ምን ሊያሳድር እንደሚችል መዝነው። በአንድ ወቅት ኢማሙ ሻፊዒይ ረሒመሁላህ ስለ አንድ ጉዳይ ተጠየቁ። ግን ትንሽ ዝም ብለው ቆዩ። "አትመልስምንዴ?" አሏቸው። "ዝምታዬ ነው ወይስ መልስ መስጠቴ ነው የሚሻለው የሚለውን እስከምለይ ነው" አሉ። [ኢዕላሙል ሙወቂዒን፡ 6/124]
የህዝብን ስሜት እየተከተልክ እንድትፈስ፣ የሚያስደስታቸውን ብቻ እየመረጥክ እንድታወራ አይደለም የምነግርህ። ይሄማ አስተዋይነት ሳይሆን አስመሳይነት ነው። ሺርክና ቢድዐ ከተንሰራፋበት ህዝብ መሀል እየኖርክ ሁሌ እንዳላየህ በማለፍ በንፅፅር ዝቅ ባሉ ርእሶች ላይ የምትሞቅ እና አልፎም ይህንን አካሄድህን እንደ ጥበብ እየቆጠርክ ሌሎችን የምታጣጥልበት ከሆነ ይሄ አላህን መፍራትም ለወገን መቆርቆርም አይደለም።
ባይሆን የምታውቀውን ሁሉ፣ የተጠየቅከውን ሁሉ በየቦታው አትዘርግፍ። የተጠየቀውን ሁሉ የሚመልስ ሰው ጤነኛ አይደለም። የማታውቀውን አላውቅም ለማለት አትፈር። ታላቁ ኢማም ሸዕቢይ ረሒመሁላህ የሆነ ጥያቄ ሲጠየቁ "አላውቀውም" አሉ። "የዒራቅ ህዝብ ሊቅ ሆነህ ሳለ 'አላውቅም' ስትል አታፍርም?!" አሏቸው። ምላሻቸው ግን እጅግ የሚገርም ነበር። እንዲህ ነበር ያሉት:-
لكن الملائكة لم تستحي حين قالت: {سبحانك لا علم لنا إلا ما علمتنا}
"ነገር ግን መላእክት: 'ጥራት ይገባህ! አንተ ካሳወቅከን ውጭ እውቀት የለንም' ሲሉኮ አላፈሩም።" [ተዕዚሙል ፉትያ፣ ኢብኑል ጀውዚይ: 86]
ስለዚህ አላውቅም የእውቀት ግማሽ ነውና አትፈርበት። የተጠራጠርክበትን ደግሞ እስከምታረጋግጥ ቆይ። ከምታውቀውም ውስጥ በሆነ ምክንያት ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያደላ ከሆነ ወይ ለጊዜው አቆየው፤ ወይ ሁነኛ ቦታ ምረጥለት። አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ግን የወቃሽ ወቀሳ አያቁምህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
♦️♦️በሰዎች መካከል ብቻህን
📌ወላሂ፣ ለራሱ ብቻ ከሚያስብ፣ የራሱን ምቾት ብቻ ከሚፈልግ፣ የአንተን ስሜት ለመረዳት የማይሞክር ሰው ጋር ከመኖር፣ ብቸኝነት እጅግ ይሻላል።
📍ከሰው ጋር መኖር ማለት አንድ ቤት ውስጥ ብቻ መኖር አይደለም፤ አንድ ልብ መሸከም፣ በደስታ አብሮ መደሰት፣ በሐዘን ጊዜ ከጎን መቆም፣ ሳትናገር ስትሰቃይ የልብህን ህመም መረዳት ነው።
📍አንዳንድ ጊዜ ከጎንህ የሚቀመጥ ሰው፣ ከሩቅ ካለ ሰው ይልቅ ልብህን የበለጠ ሊያሳዝን ይችላል። አንድ ቤት ውስጥ ሆነህ ማንም እንደሌለ መሰማት፣ አንድ ሰው ከጎንህ እያለ የልብህን ህመም ለማንም መናገር አለመቻል—ይህ እጅግ ከባድ የሆነ ብቸኝነት ነው።
📍ሰው ሁልጊዜ ብዙ ሰዎች አያስፈልገውም፤ አንድ በቂ ነው። አንድ ሰው—ስትደክም የሚያሳርፍህ፣ ስታዝን የሚያዝንልህ፣ ስትወድቅ የሚያነሳህ፣ እና ምንም ሳትናገር የልብህን ሁኔታ የሚረዳህ።
📍ነገር ግን ሁልጊዜ “እኔ” ብቻ የሚል፣ “አንተስ?” ብሎ የማይጠይቅ፣ “እንዴት ነህ?” ብሎ የማይጨነቅ፣ በህመምህ ጊዜ ከጎንህ የማይቆም ሰው ከሆነ፣ ከእንዲህ ያለ ሰው ጋር ከመኖር ብቻህን መኖር ይሻላል።
📍ምክንያቱም ብቸኝነት ሰውን አንድ ጊዜ ሊያሳዝነው ይችላል፤ ነገር ግን ከማይረዳህ፣ ከማያዝንልህ እና የልብህን ህመም ከማይሰማ ሰው ጋር መኖር በየቀኑ በዝምታ ሊሰብርህ ይችላል።
📍ስለዚህ ከሰዎች መካከል መኖር ብቻ አንፈልግ፤ በልብ የሚያኖረንን፣ የሚረዳንን፣ የሚያከብረንን እና በችግራችን ጊዜ ከጎናችን የሚቆምን ሰው እንፈልግ።
📍ከጎናችን ያለ ሰው ሁሉ ከእኛ ጋር አይደለም፤ አንዳንዶች በአጠገባችን ናቸው፣ ግን በልባችን ውስጥ ብቻችንን እንሆናለን።
አላህ የሚተሳሰብ፣ የሚዋደድ፣ የሚተጋገዝ፣ ለሌላውም እንደራሱ የሚያስብ ሰው ያድርገን። ልባችንን ለሌሎች ርኅራኄ ያድርግ፤ ለራሳችን ብቻ እንዳንኖር ከራስ ወዳድነት ይጠብቀን። አሚን።
ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ
https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
