قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
الذهاب إلى القناة على Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
910
المشتركون
-324 ساعات
-157 أيام
+4830 أيام
أرشيف المشاركات
👉መስከረም 25 መስገባ ይዘጋል
📢 አስደሳች ዜና ለጠቅላላው የሙስሊም ማህበረሰብ!
ኢኽላስ የቁርኣን እና የተርቢያ ማዕከል የ10 ወር የቆይታ ጊዜ ያለው የበጋ ልዩ ኮርስ ማዘጋጀቱን በታላቅ ደስታ ይገልፃል!
💡 የፕሮግራሙ ልዩነት፦
በዚህ 10 ወር ውስጥ ማንኛውም የእውቀት ፈላጊ ጧሊበል ዒልም ሊቀራቸው የሚገቡ መሠረታዊ የሸሪዐ የትምህርት ፈኖችን ልዩ የእውቀት ማዕድ ተዘጋጅቶልዎታል!
ልጆቻችሁን እና እራሳችሁን በቁርኣን፣ በስነ-ምግባር እና በእስልምና እውቀቶች ለማነፅ እና ለማበልፀግ የቀረበ ወርቃማ አጋጣሚ!
የትምህርቱ
በወንድም አብዱረዛቅ አል-ባጂ አስተምህሮ የሚሰጥ ይሆናል።
📚 የሚቀሩት ፈኖች
● ዓቂዳህ
● ፊቅህ አሻፊኢይ
● ኡሱሉል ፊቅህ
● ቀዋዒዱል ፊቅሂ
● አዳብ እና ሱሉክ
📖 በተጨማሪ፦ በቆይታው ውስጥ የተለያዩ ጠቃሚ የሸሪዐ መትኖች ይተሐፈዛሉ እያንዳንዱ ቂርዐት እራሱን የቻለ ፈተና ይኖረዋል።
⚠️ ማሳሰቢያ፦ ለፕሮግራሙ የተቀመጠው የቦታ መጠን የተገደበ በመሆኑ ቦታ ሳይሞላቦት ፈጥነው በመመዝገብ ቦታዎን ያስይዙ!
📍 አድራሻ
አድራሻ፦ ቦሌ ሚካኤል — ከእግረኛ ድልድዩ ወደ ውስጥ 50 ሜትር ገባ ብሎ
https://maps.app.goo.gl/29NH6VZjdLRNRVyE9?g_st=atm
ስልክ ቁጥሮች፦
📞 0911119260
📞 0919829850
User name
@bajjiz
Repost from Abu useymin (Mohammed Ali)
👉ዑመር ኢብኑል ኸጧብ አላህ መልካም ስራዉን ይዉደድለትና እንዲህ ብለዋል፦
ነጋዴ ብሆን ኖሮ የሽቶ ንግድን እንጂ ሌላን አልመርጥም ነበረ፣
ምክንያቱም ትርፉን ባላገኝ እንኳ፣ደስ የሚል መዓዛውን ግን አላጣውምና።
📚الآداب الشرعية ( 3 /392)
Repost from Muhammed Sultan (أبو عائشة) Channel
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
🕌 የዒልም ማዕድ ጥሪ — በሑዘይፋ መስጂድ! 📚
የዲንዎን
እውቀት ለማሳደግ እና የነቢያችንን (ﷺ) ሱና በትክክለኛው መንገድ ለመረዳት የዘወትር የእሁድ ፕሮግራማችንን እንዳያመልጥዎ!
🗓 ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ | ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ ሑዘይፋ መስጂድ
📖 የምንቀራቸው ታላላቅ ኪታቦች፦
መንሃጁስ ሳሊኪን (منهج السالكين)
በፊቅህ ትምህርት ዙሪያ
ኩን ሰለፊየን ዓለል ጃዳህ (كن سلفيا على الجادة) — በትክክለኛው የሰለፎች መንገድ ላይ መፅናት
ሚን አሱሊ ዐቂደቲ አህሊሱና - ለሼኽ ፈውዛን (من أصول عقيدة أهل السنة) — በሶሂህ አቂዳ ዙሪያ
💡 ዒልም መፈለግ በምእመናን ላይ የተጣለ ግዴታ ነው! እርስዎም ተገኝተው ይካፈሉ፤ ለሌሎችም በማጋራት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ።
📲 ሼር (Share) በማድረግ የኸይር ጥሪውን ያዳርሱ!
ባረከላሁ ፊኩም!
እንባ ከአንጀቴ ሞልቶ ሲፈሰኝ
ሆዴ ሲባባ ሀዘን ሲያፈርሰኝ
ተስፋዬ ባክኖ እያዋለለኝ
ማነው ካላንተ አለሁ የሚለኝ!
ኢላሂ....💔💔💔
🌿
አንዳንድ ሰዎች…🌿 በመጨረሻም አንዳንድ ሰዎች የተፃፉልን ዕድል ሳይሆኑ፣ የተማርንባቸው ትምህርቶች እንደነበሩ እንረዳለን። 🌿 አንዳንዶች ወደ ሕይወታችን የመጡት ለዘላለም ሊቆዩ አይደለም፤ አንድ ነገር አስተምረውን ከዚያ ሊሄዱ ነው። 🌿 አንዳንዶች ደስታን ያመጣሉ፣ አንዳንዶች ሕመምን፤ አንዳንዶች ፍቅርን ያስተምሩናል፣ ሌሎች ደግሞ ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን ያሳዩናል። 🌿 አንድ ቀን ወደኋላ ተመልሰን ስናይ፣ በእነሱ ላይ ያፈሰስነው እንባ ሁሉ ምክንያት እንዳልነበረው እንረዳለን። የተሰበረው ልብ ምናልባት የተሻለ ሰው ለመሆን የከፈልነው ዋጋ ነበር። አንዳንድ መለያየቶች ቅጣት አይደሉም፤ ጥበቃ ናቸው። አንዳንድ የተዘጉ በሮች ኪሳራ አይደሉም፤ አላህ ከማናውቀው ነገር የሚጠብቀን መንገድ ናቸው። 🌿አንዳንድ የተሰበሩ ተስፋዎችም ልባችንን ወደ እውነተኛው ተስፋ እንድናዞር ያደርጉናል። ስለዚህ የሄዱትን ሁሉ በእንባ አንያዛቸው፤ የተማርነውን ትምህርት እንያዝ። የሰጡንን ትዝታ እናመስግን፣ የወሰዱብንንም ልባችን እንልቀቅ። 🌿እና በመጨረሻ… የተፃፈልን ሰው ከሆነ ርቆ ቢሄድም መንገዱ እንደገና ያገናኘዋል፤ ያልተፃፈልን ከሆነ ግን ምንም ያህል ብንይዘው የሚቆይ አይሆንም። 🌿 ሰዎች አንዳንዴ የሕይወታችን መድረሻ አይደሉም፤ መንገዱን ያስተማሩን ምዕራፎች ናቸው። እና አንድ ቀን ያንን ምዕራፍ በእንባ ሳይሆን በምስጋና እንዘጋዋለን። 🌿 t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
رسالة فيديو00:21
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
⭕️ وضع #اليدين خلف #الظهر أثناء المشي هيئة دخيلة ومخالفة #للمروءة
⭕️ قال العلامة حمود التويجري -رحمـه الله-:
«وهذا الفعل السخيف من أفعال الأفرنج وأضرابهم من أعداء الله تعالى، وقد تلقى ذلك عنهم كثير من سفهاء المسلمين».
⭕️ وقال -رحمـه الله-:
«إنه فعل مستقبح عند ذوي المروءات والشيم، وكيف لا يكون قبيحا بالرجل أن يضع يده على دبره ثم يمشي بين الناس»
📚 الإيضاح والتبيين لما وقع فيه الأكثرون من مشابهة المشركين، [صـ ١٨٧-١٨٩] .
⭕️ #الخلاصة:
احرص على حسن الهيئة وكمال المروءة، وابتعد عن الهيئات الدخيلة التي استقبحها أهل العلم، ولا تجعل ما يفعله الناس عادة سببا في ترك الآداب الحسنة.
•┈┈┈❁┈•✿❁📚❁✿•┈❁┈┈┈•
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
አቋም የቀየረው ማን ነው? እነ ሸይኽ አብዱል ሀሚድ ወይስ እነ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር?
እስኪ አስተዋይ የሆናችሁ በመረጃ ፍረዱ!?
አላዋቂዎችን በባዶ ፕሮፖ ገንዳ የሰለፊይ ኡስታዞቻችንን አቋም ቀይረዋል በማለት ማምታት ከያዛችሁና ንፁሀን ኡስታዞቻችንን ሙመይዕ ሁነዋል እያለችሁ መጮህ ከጀመራችሁ አመታቶችን አስቆጠራችሁ።
ግን እስኪ ከመረጃ አንፃር የትኛውን አቋም ነው የቀየሩት?
በቃ በሆኑ አካላቶች ላይ የሆነ ፍርድ ስፈርዱ ስላልተቀበሏችሁ ብቻ እንድህ ንፁሀንን በለሉበት ስወቅሱ ትንሽ አይሰቀጥጣችሁም እንኳ!?
ለምሳሌ በጣም በሰፊው የምታራግቡት የጀርህ ወተዕዲልን መስአላ የጅቲሀድ መስአላ ነው ብለዋልነው።
እሺ ይህን አቋም አድስ የያዙት አቋም ነው ወይንስ በፊትም ከነርሱው ጋር በነበራችሁበትም ጊዜ እንድሁ ነበር አቋማቸውን በመረጃ እንየው እስኪ
አቋማቸውን ቀይረዋል እያሉ ከሚወቅሷቸው ኡስታዞች አንዱ ኡስታዝኢብኑ ሙነወር ነው። እውን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ጀርሕ ወተዕዲልንየጅቲሃድ መስአላ ነው የሚለውን አቋም አድስ ነው የያዘውን?
ልብ በሉ አቋም ቀይሯል ማለት ድሮ "ጀርሕ ወተዕዲል እጅቲሃድን የሚያስተናግድ መስአላ አይደለም ብሎ ዛሬ ደግሞ ነው ቢል" ነበር አቋም ቀይሯል የሚባለው ። እውን በፊት አቋሙ ሌላ ዛሬ ሌላ ነውን? ? ከዚህ በስተፊት ከፃፋቸው መፀሐፍ እና ፅሁፎቹ እስኪ በመረጃ እንመልከት፦
በ2008 ዓ ል "አልበያነን ጀምዒያ ሱሪናየተብዲዕ ህግጋት" በማለት ያዘጋጀውን መፀሐፍ
ምዕራፍ ሶስት ውስጥ (( "ሙብተዲዕን ሙብተዲዕ ያላለ ሙብተዲዕ ነው" የሚል ኢልዛም አደጋ ሊያስከትል ይችላል)) የሚለውን ንዑስ ክፍል ከገፅ (200–208) በደንብ እናንብበው። የዛኔም ከዛሬ አስራ ዘጠኝ አመት በስተፊት አቋሙ ምን እደነበር በግልፅ ታያላችሁ ማን አቋምም እንደቀየረ ታረጋግጣላችሁ። ሰዎቹ ያለምንም መረጃ ንፁሃንን በሌሎበት እየወነጀሉ መሆናቸውን ትታዘባላችሁ።
የተወሰኑትን የመፀሐፉን ገፆች በዚህ ሊንክ እየገባችሁ ማንበብ ትችላላችሁ:-
╭─┅──•••••─═ঊঊঈ═─•••••──┅─╮
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1073
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1074
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1075
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1076
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1077
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1078
╰─┅──•••••─═ঊঊঈ═─••••••──┅─╯
በዚሁ መፀሐፍ ገጽ 203 ላይ በግልፅ የጀርሕ ወተዕዲል መስኣላ የጅቲሃድ መስአላ እንደሆነ በግልፅ አማረኛ በማያሻማ ገለፃ እንዲህ ሲል አስቀምጧል «የሂስና የሙገሳ ዘርፍ በራሱ የኢጅቲሃድ ርእስ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።»
በዚህ ገብታችሁ አንብቡት {{ t.me/IbnuMuhammedzeyn/1078 }}
ታዲያ የዛኔ እሄን ካለ ዛሬ አቋም ቀይሯል ማለቱን ምን አመጣው? ውሸት አይሆንባችሁምን? አላህን አትፈሩምን??
መፀሐፉ የሌላችሁ ከዚህ ማውረድ ትችላላችሁ
{{ t.me/IbnuMuhammedzeyn/1080 }}
እንድሁም (ሰኔ 10/2008 ወንድማዊ ምክር) በሚል ርእስ የፃፈው ጠቃሚ ምክር ላይም እንድሁ አንዱ ሌላውን በተብዲዕ መስአላ ሊያስገድድ እንደማይገባም አካቱ ፅፏል እዚያው ፅሁፉ ላይ እንድህ ይላል «ትላንት ሰለፎቻችን፣ ዛሬም ታላላቅ ዑለማዎቻችን አንዳቸው በቢድዐ የፈረጁትን አካል ሌላቸው ሲከላከሉለት ያጋጥማል፡፡ ግና “እንዴት እኔን ተከትለህ አልፈረጅክም” ብለው አንዳቸው በሌላው ላይ አልዘመቱም፡፡» ሙሉውን የፈለገ በዚህ ሊንክ ገብቶ ማንበብ ይችላል
{{ t.me/IbnuMunewor/93 }}
የት ነው የተቀየረው አቋም ድሮም ሆነ ዛሬ በዚህ ርእስ ላይ አቋሙ አንድ ነው።
እንድሁም ኡስታዝ ኸድር አሕመድም ከዚህ በስተፊት ቀደም ሲል በሐጁሪ አንጃዎች ላይ ረድ ሲያደርግ በዚህ መስአላ ላይ ኢልዛም ማድረግ እንደማይገባ የኢልዛምን ቢድዐ የጀመረው ሐጁሪ እንደሆነ ከዘመኑ ዑለሞች እያጣቀሰ በደንብ አስተምሯል።
___
ከዚህ በላይ የጠቀስኳቸው ሐቅ ለሚፈልግ ሰው ማን አቋም እንደቀየረ ማን በድሮው አቋሞ ላይ እንዳለ በመረጃ ግልፅ ያደርጋሉ።
ለራሳችሁ አቋም ቀይራችሁ ንፁሃን ኡስታዞችን ኡማውን የዲኑን ጉዳይ እንዳያስተምሩ አቋም ቀይራችሗል እያላችሁ መወንጀል አግባብ አይደለም።
ካወራችሁ ላይቀር ማውራት ያለባችሁ አቋም ቀይረናል እኛ የስከዛሬው አቋማችን ትክክል አልነበረም ጥፋት ላይ ነበርን ከስከዛሬው አቋማችን ወደ አላህ እንመለሳለን እናንተም እንደኛው ከስከዛሬው አቋማችሁ ወደ አላህ ተመለሱ ነበር ማለት ያለባችሁ። "ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል" አሉ እራሳችሁ አቋም ቀይራችሁ እራሳችሁ አቋም ቀየሩ ብላችሁ ትጮሃላችሁ። ግን ለምን በራሳችሁ ጊዜ አስተዋዬች በአቅላችሁ ላይ እንዲስቁ ትፈቅዳላችሁ።
ለምን በሌለ ችግር ኺላፍ እየፈጠራችሁ የሰለፊያ ደዕዋ በሀገራችን ማደግ ባለበት ደረጃ እንዳያድግ እንቅፋት ትሆናላችሁ?
=
የቴሌግራም ቻናል፦
@IbnuMuhammedzeyn
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
Repost from Mohammed Siraj Al kemissie
ስሙትትትትት👂
اتفاق بين مشايخنا السلفيين.....
من كذب؟ من وجد بكلمته؟ استمع بعناية إلى السجل الذي لدينا.
አንድ የቀረ መሻይኽ የለም ሁሉም የተስማሙት በዚህ በምትሰሙት ነበር!
" وماذا بعد الحق إلا الضلال"
☞ ይህን ስምምነት ፈፅመው በሰው ዘንዳ ግን የበላይ ለመምሰል ተወያይተን መከርናቸው እያሉ ሲዋሹ ነበር! አላህ ውሸታቸውን ይኸው አጋለጠባቸው!
☞ አሀ ለካ ጀግና ኡስታዞቻችን እንዲህ አድርገው በውይይት ስለዘጓቸው ነው ድጋሜ ውይይት ላለመወያየት ላይ ታች ሲሮጡ የነበሩት የሚለው ዛሬ ትዝዝዝዝዝዝ አለኝ!
(በል በደንብ አድርገህ ስማና አቋም የቀየረውን ለይተህ እወቅ ውሸትና ተንኮላቸው ከዚህ ሪከርድ ቡሀላ ካልገባህ መቼም አይገባህ ሀቢቢ)
✍ أبو ماهر الأثري..
https://t.me/ibnuidris_teppi
ያ ረቢ! ከሃሳብ ክብደትና ከልብ ጭንቀት አቅልልልኝ፤ ነገሬን ሁሉ ላንተ አደራ ሰጥቻለሁ።ጌታዬ ሆይ! እኔ በሚታየኝ ሳይሆን አንተ ለኔ መልካም ነው ብለህ በምታየው ነገር ልቤን አረጋጋው።
ያ ረቢ! ከሃሳብ ክብደትና ከልብ ጭንቀት አቅልልልኝ፤ ነገሬን ሁሉ ላንተ አደራ ሰጥቻለሁ። ጌታዬ ሆይ! እኔ በሚታየኝ ሳይሆን አንተ ለኔ መልካም ነው ብለህ በምታየው ነገር ልቤን አረጋጋው።
ያ ረቢ! ከሃሳብ ክብደትና ከልብ ጭንቀት አቅልልልኝ፤ ነገሬን ሁሉ ላንተ አደራ ሰጥቻለሁ። ጌታዬ ሆይ! እኔ በሚታየኝ ሳይሆን አንተ ለኔ መልካም ነው ብለህ በምታየው ነገር ልቤን አረጋጋው።
t.me/ibrahim_furii
Repost from ስለ ቀልባችን
🤍ቀልብ እረፍት የምታገኘው፣ ወጣትነትም ከፈተና የሚጠበቀው በሐላል ጎጆ (በትዳር) ጥላ ስር ነው።
በአላህ ፈቃድ በዚሁ «ስለ ቀልባችን» ቻናላችን ላይ፤
✔️ ወደ ትዳር ለመግባት ላሰቡ፣
✔️ ትዳር ለዘገየባቸው፣
✔️ በትዳር ውስጥ ላሉና ቤታቸውን በሰኪና መምራት ለሚፈልጉ ሁሉ...
🌸ከትዳር ማሰብ ጀምሮ እስከ ስኬታማ የትዳር ሕይወት አመራር ድረስ የሚያመላክት አንዲት ድንቅና አጭር ኪታብ በቅርቡ እንጀምራለን፣ ኢንሻ አላህ!
🎯የቻናላችን ዋነኛ ዓላማ ቀልብን ማስተካከል እስከሆነ ድረስ፣ ወጣቱን ከዝሙት ታድጎ ወደ ሐላል ጎጆ ማመላከት የትምህርቱ ትልቁ አካል ነው ብለን እናምናለን።
በዚህ ሐሳብ ላይ ምን ትላላችሁ? 👍
📱➔ t.me/Sle_qelbachn1
Repost from ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
ትንሽ ደግነት፤ ትንሽ መረዳት
ለአንዱ የመታፈን ያክል ስቃይ የሆነው ነገር፣ ለሌላው የመተንፈስ ያክል የነፃነት ማዕበል ነው። ስቃይ አንፃራዊ ነው። ማን በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለ አናውቅም።
የማንንም ስቃይ ልንረዳ አንችልም። የሰዎችን ስቃይ ሙሉ በሙሉ መረዳት አይታሰብም። ይህም በሁለት ምክንያት ነው። አንድ፣ እንርሱን መሆን አንችልም። ሁለት፣ እነርሱ ያሉበት ሁኔታ ውስጥ መግባት ይሳነናል። የእነርሱ ሁኔታ ውስጥ ብንገባ እንኳን፣ እንርሱን መሆን መቼም አንችልም፤ ተፈጥሮ ነውና!
ስለዚህ መፍትሔውም ሁለት ነው። ሰው ምንም «ክፉ» ይሁን ከመውቀሳችን በፊት፣ ትንሽ ደግንት፤ ትንሽ መረዳት እንስጣቸው። እኛ እነርሱ የዋሉበት አልዋልንምና፣ ባለፉበት አላልፍንምና፣ ከምንም በላይ እነርሱን አይደለንምና!
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444.
Repost from Abu~Mahi Channel
ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ ሀብት ወይም ስልጣን አይስፈልግህም።
ለተከፋው ሰው አፅናኝ ቃል መናገር ቅንነት ነው።
መንገድ ለተሳሳተው አቅጣጫ መጠቆም ቅንነት ነው።
በችግር ላይ ላለ ሰው የቻሉትን ያህል እጅ መዘርጋት ቅንነት ነው።
ለሌሎች ስኬት ከልብ መደሰት ታላቅ ቅንነት ነው።
ዓለምን የበለጠ ውብ እና መኖሪያ ለማድረግ ትልቁ መሳሪያ በእጃችን ያለው ቅንነት ነው። ዛሬ የምንዘራው የቅንነት እና የመረዳዳት ዘር፣ ነገ ፍሬ አፍርቶ የብዙዎችን ህይወት ይታደጋል።
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_IdrisRepost from ABU MUSLIM A-DUROOS
📢 ማስታወስ
🔶 ዛሬ ማታ በአላህ ፈቃድ በቀጥታ ስርጭት በቴሌግራም እና በዩቱብ ኪታብ ደርስ ይኖረናል።
📚 المستوى التمهيدي - الأذكار والآداب
📚 አል-ሙስተዋ አል-ተምሂዲ - አል-አዝካር ወል-አዳብ
(የመግቢያ ደረጃ - ዚክሮች እና ስነ-ምግባራት)
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
🗓 ቅዳሜ ረቢኡል አኺር 08/1447 ሂጅሪ, (መስከረም 09,2019),
⏰ ሰዐት: ማታ 3፡00 (በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር)።
🕌 ቦታ: ቀጥታ ስርጭት በቴሌግራም (Telegram) እና በዩቱብ (YouTube)
•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
🎙 الأُسْتَاذُ أَبُو مُسْلِمٍ عُمَرُ بنُ حَسَنٍ الْعَرُوسَيّ
🎙 በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ኡመር ሐሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁላህ)
📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/AbumuslimAlarsi
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"እኛ ከአቡበክር፣ ከዑመር እና ከዓኢሻህ ጋር ጦርነት ላይ ነው ያለነው" ይላል ይሄ ሑሢ። አዎ ጥላቸውና ጥላቻቸው የዐሊይን ስልጣን ነጥቀዋል ከሚሏቸው ኸሊፋዎች፣ ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰላም ሶሐቦች እና እነሱን ከሚወዱ ሱኒ ሙስሊሞች ጋር ነው። አንዳንድ ሞኞች ግን ጦርነቱ የሃይማኖት አይደለም ይላሉ። ጦርነቱ የሃይማኖት እንደሆነ ራሳቸው ሑሢዮቹ በቃልም በተግባርም ደጋግመው አሳይተዋል። በርካታ የሱኒ መስጂዶችን አጥቅተዋል፣ መጨፈሪያ አድርገው አርክሰዋል። ከደማጅ እነ ሸይኽ የሕያን እና ተማሪዎቹን አፈናቅለዋል። ከመሪዎቹ ጀምሮ የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰላም ሶሐቦች ባደባባይ ዘልፈዋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ተጫጭተናል ማለት ተጋብተናል ማለት አይደለም!
~
በነገራችን ላይ...እጮኝነት ማለት ኒካህ አይደለም! እጮኝነት ማለት «ወደፊት ልንጋባ አስበናል» የሚል የተስፋ ቃል ብቻ ነው።
ኒካህ እስከሌለ ድረስ እሷ ላንተ አጅነቢይ ናት፤ አንተም ለእሷ ባዕድ ወንድ ነህ። ብዙዎች አያስተውሉትም እንጂ፣ በርካታ ትዳሮች ገና በጠዋቱ የሚፈርሱት፣ የተሳኩ እንዳይሆኑ የሚቀሰፉት ከተጫጩ በኋላ በሚሰሩት ስህተት ምክንያት ነው።
ሸይጧን ወደ ዝሙት የሚያስገባው በአንድ ጀምበር አይደለም፤ ደረጃ በደረጃ ነው።
➔ መጀመሪያ «እሱኮ የወደፊት ባልሽ ነው ማውራት ትችላላችሁ» ይላችኋል።
➔ ቀጥሎ ከእኩለ ሌሊት የስልክ ወሬዎች ጋር ድንበር የለሽ የፍቅር ቃላት ይጀመራሉ።
➔ ከዚያም በአይንም፣ በልብም፣ በምላስም ዝሙት ውስጥ ትወድቃላችሁ።
➔ በመጨረሻም ገደቡ ተሰብሮ አካላዊ ዝሙት ላይ ይደረሳል።
ታድያ በአላህ ቁጣና በሀራም የተበከለ ግንኙነት በምን ሂሳብ ሰላማዊ ትዳርን ሊወልድ ይችላል?!
ፍቅር ልክ እንደ ንፁህ ፍሬ ነው። ሰዓቱን ሳይጠብቁ ጥሬውን በሀራም የለቀሙት እንደሆነ፣ ሰርጉ ቀን ሲደርስ የሚበላ
ጣፋጭ ፍሬ አይገኝም። ለትዳር የተጠበቀው ናፍቆት፣ ክብርና ሀያዕ በእጮኝነት ዘመን ይሟጠጣል። ሰርግ ተብሎ ወደ አንድ ቤት ሲገቡ ፍቅሩ አልቋል፤ ወንጀሉ ልብን አድርቆታል፤ በረካውም ርቋል። መጨረሻው ወይ በፀፀት ማልቀስ፣ ወይ በትንሽ ነገር መጣላትና ወደ ፍቺ መሮጥ ይሆናል።
እሳትን እቅፍ ውስጥ አስገብቶ «አይፈጅም» አይባልም። ወጣትነት፣ ስሜት እና የሸይጧን ጉትጎታ ተደምረው እንዳያጠፏችሁ ብልሆች
ሁኑ!
◇ ከተዋደዳችሁና ቤተሰብ ከወሰነ — ወዲያው ኒካህ እሰሩ!
◇ «ሰርግ ለማዘጋጀት ጊዜ ይፈልጋል፣ ቤት አልተሟላም፣ ድግስ አለብን...» የሚሉ ሰበቦች የሸይጧን ቀዳዳዎች ናቸው። ድግሱና ሰርጉ አመቺ በሆነ ቀን፣ አቅም ሲፈቅድ ይሁን፤ ነገር ግን ኒካሁ አስቀድሞ ይታሰር!
◇ ኒካህ የታሰረለት ግንኙነት ጥበቃ አለው፤ የአላህ እዝነትና በረካ አለበት። ወንጀል የለም፣ ፍርሃት የለም፣ የሕሊና ፀፀት የለም።
መልእክቱ ግልጽ ነው! የወደፊት ህይወታችሁን በሀራም መሰረት ላይ አትገንቡ። ሀላል ሲዘገይ ለሀራም በር ይከፈታል። ፍቅራችሁ ሳይረክስ፣ ክብራችሁ ሳይጎድፍ፣ የነገው ትዳራችሁ መርገምት ሳይሆን በረካ እንዲሆን ከፈለጋችሁ እጮኝነትን አሳጥሩ፤ ኒካህን
አስቀድሙ!
--
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
Repost from 💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
🔖የወንጀል ተፅእኖና ውጤቱ!
قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله
اعلم أن للمعاصي آثارا على الأخلاق وعلى الأعمال، قال الله تعالى: "فلما زاغوا أزاغ الله قلوبهم"، فقوله تعالى: "فلما زاغوا" هذا عمل سيئ نتيجته: "أزاغ الله قلوبهم" فالأعمال السيئة لها آثار وخيمة؛ ولهذا يجب على الإنسان إذا صدرت منه السيئة أن يبادر بالتوبة، حتى لا تبقى هذه الجرثومة في قلبه فتؤثر عليه.
(شرح فتح رب البرية / ص17)~እወቅ ወንጀል በስነምግባር ፦በስራችን የሚያሳድረዉ ተፅእኖ ፋና አለዉ ። ~ወንጀል ስነምግባርን ያበላሻል። ~ወንጀል ሰርተን ሰዉነታችን ለኢባዳ አይነሳሳም። فلما زاغوا أزاغ الله قلوبهم"، ~ሲዘነበሉ (ቅናቸዉን መንገድ ሲለቁ) አላህ ልባቸዉን አዘነበለዉ። t.me/https_Asselfya
