uk
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Відкрити в Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
4 298
Підписники
+124 години
-157 днів
-8430 днів
Архів дописів
🇮🇷⚡️🇦🇪- ሳይረን እና ፍንዳታዎች ዱባይን አናውጠዋል።

🇮🇷/🇰🇼 ሰበር ዜና፦ ኢራን በከስም ደሴት ላይ የተደረገ የአሜሪካ የአየር ጥቃትን እና የኢራን የነዳጅ መርከብ መጠለፍን ለመበቀል፣ የአሜሪካ ኃይሎች በሚገኙበት በኩዌቱ የአሊ አል-ሳሌም አየር ኃይል ማዕከልን ዒላማ ያደረጉ 6 ባሊስቲክ ሚሳይሎችን ተኩሳለች። ተጨማሪ ሦስት ሚሳይሎች በIRGC ባሕሬን በሚገኝ የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ተተኩሰዋል። ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ተጨማሪ ሚሳይሎች መተኮሳቸው ሪፖርት ተደርጓል። በአሁኑ ሰዓት በኩዌት ላይ የአየር መቃወሚያ ስርዓቶች ሚሳዬሎቹን ለመጣል እየተዋከቡ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች በርካታ ጥቃቶች መደርሰባቸውን ሪፖርት አድርገዋል። የአደጋ ሳይረኖችም ያለ ማቋረጥ እየጮሁ ናቸው።

🇮🇷⚔️🇺🇸🇰🇼🏴‍☠️ 2 ከባድ ፍንዳታዎች አሁን በኩዌት ተሰምተዋል።

🇮🇷⚔️🇺🇸🇧🇭🏴‍☠️አሁን: ፍንዳታዎች ባሕሬንን እየናጧት ነው።

🇮🇷🇺🇸🇰🇼❗️— ሰበር ዜና፦ የኢራን IRGC አሜሪካውያን የከሽም ደሴትን ዒላማ ካደረጉ በኋላ፣ ኃይሎቻቸው በአጸፋው በኩዌት በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፖች ላይ ሚሳይሎችን እንደተኮሱ ተናግሯል።

—❗️🇮🇷/🇧🇭 ሰበር ዜና፡ በባሕሬን ሳይረኖች እየጮሁ ናቸው። ሚሳዬሎችም በሰማይዋ እየበረሩ ታይተዋል። እንደ አንዳንዶች መረጃ፣ ፍንዳታዎች አሉ።
+1
—❗️🇮🇷/🇧🇭 ሰበር ዜና፡ በባሕሬን ሳይረኖች እየጮሁ ናቸው። ሚሳዬሎችም በሰማይዋ እየበረሩ ታይተዋል። እንደ አንዳንዶች መረጃ፣ ፍንዳታዎች አሉ።

— 🇺🇸/🇰🇼/🇮🇷 ኩዌታዊው የኢራንን በራሪ ሚሳዬሎች እቀርፃለሁ ብሎተጋጨ። (እየነዳህ አትቅረፅ ሐቢቢ)

🇰🇼🇺🇸⚡️🇮🇷 የኩዌት አየር መቃወሚያዎች፣ የኢራንን ሚሳዬሎች ለመጣል እየጣሩ ናቸው።

🇵🇾 በMrBeast የውድድር ቪዲዮ ላይ አውሮፕላን ያሸነፈው አብራሪ፣ በፓራጓይ በ$3.6 ሚሊዮን የአደንዛዥ ዕፅ ማዘዋወር ወንጀል ተይዟል። ፖሊስ ከMiami በመጣ የግል አውሮፕላን ውስጥ ወደ 360 ኪሎ ግራም የሚጠጋ ማሪዋና አግኝቷል። ከተያዙት መካከል የMrBeast "100 Pilots Fight For A Private Jet" ውድድር አሸናፊ የሆነውና የአይሮፕላኑ ባለቤት ጃባሪ ብራውን ይገኝበታል። “ለአእምሮ ቅንጭራሞች ዕድል ስትሰጡ፣ ምንም ይሁን ምን ያበላሸዋል” የሚለውን የፈረንጅ አባባል የሚያጠናክር ማስረጃ ነው። አዎ፣ ለደደቦች ዕድሎችን አትስጡ!

🇮🇱❌🇵🇸— የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር ቤን-ግቪር፣ ከመስጊዶች የሚሰራጨውን ጮክ ያለ የእስልምና የጸሎት ጥሪ የሚከለክለውን ሕግ፣ የሚያስተዋውቅ ቪዲዮ ለቋል። የታቀደው ሕግ፣ የእስራኤል ፖሊስ የመስጊድ የድምፅ ማጉያ ሥርዓቶችን በቁጥጥር ሥር እንዲያውል እና አዛን (የእስልምና የጸሎት ጥሪ) የሚያሰሙ አካላትን እስከ 50,000 ሼኬል (ወደ 13,500 የአሜሪካ ዶላር ገደማ) የሚደርስ ቅጣት እንዲቀጣ የሚያስችል ሕግ ነው። ቤን-ግቪር፣ 'የድምጽ ብክለትን' ለመቀነስ የሚደረግ ጥረት ነው፣ ያለ ሲሆን፣ ቢሮው፣ በተገለጸው ሕግ መሠረት ፖሊስ እርምጃ መውሰድ እንዲጀምር መመሪያ መስጠቱን ተናግሯል።

🇮🇱🇱🇧⚡️እስራኤል በሊባኖስ በታይር ከተማ የሚገኝ የክርስቲያን መንደርን በቦንብ እንደምትደበድብ ማስፈራሪያ ሰጥታለች። ነዋሪዎቹ አሁን ማስጠንቀቂያውን ተቀብለው በመውጣት ላይ ሲሆኑ ቤታቸው ሊወ
🇮🇱🇱🇧⚡️እስራኤል በሊባኖስ በታይር ከተማ የሚገኝ የክርስቲያን መንደርን በቦንብ እንደምትደበድብ ማስፈራሪያ ሰጥታለች። ነዋሪዎቹ አሁን ማስጠንቀቂያውን ተቀብለው በመውጣት ላይ ሲሆኑ ቤታቸው ሊወድም እንደሚችል ፈርተዋል።

ድሮስ ታዲያ!? እቺንማ ማንም ያውቃል።
ድሮስ ታዲያ!? እቺንማ ማንም ያውቃል።

⚡️🇷🇺 የሩሲያ ወታደሮች በቤልጎሮድ ግዛት በዩክሬን የተተኮሱ ድሮኖችን፣ Yolka በተባለው አዲሱ የሩሲያ ፀረ- ድሮን መሳሪያ መትተው ሲጥሉ ዛሬ ታይተዋል። መሳሪያውን ለመሥራት በእያንዳንዱ $500 ዶላር አካባቢ ያስወጣል የተባለ ሲሆን፣ እግረኛ ጦሯን መሳሪያውን ለማስታጠቅ አቅዳለች ተብሏል። Yolka፣ እንደሌሎቹ ፈንጂ ወይም ተቀጣጣይ ነገር አይሸከምም፣ Kinatic Energy ወይም መትቶ መጣል የሚችል ኃይል ብቻ ነው ያለው።

— 🇮🇶/🇮🇶 አዲስ፦ የኢራቅ ሺዓ ሚሊሻ 'አሳኢብ አህል አል-ሃቅ' ከኢራቅ ጦር ሃይሎች ጋር ሙሉ በሙሉ እንደሚዋሃድ አስታውቋል። በሙቅታዳ አል-ሳድር ከሚመራው ሳራያ አል-ሳላም ቀጥሎ ይህን የሚ
— 🇮🇶/🇮🇶 አዲስ፦ የኢራቅ ሺዓ ሚሊሻ 'አሳኢብ አህል አል-ሃቅ' ከኢራቅ ጦር ሃይሎች ጋር ሙሉ በሙሉ እንደሚዋሃድ አስታውቋል። በሙቅታዳ አል-ሳድር ከሚመራው ሳራያ አል-ሳላም ቀጥሎ ይህን የሚያደርጉት ሁለተኛው ሚሊሻ ናቸው። የሚሊሻው መሪ እንደተናገረው፣ 'ኢራቅ አሁን ትክክለኛ መንግስት አላት፣ ሰለፊ ወሃቢው ISIS ከአሁን በኋላ የለም፣ ተደምስሷል። ስለዚህ እንደ ቡድን ገለልተኛ መሆን ከአሁን በኋላ ምንም ዓላማ የለውም።'

— 🇮🇷 የፋርስ ባሕረ መተላለፊያ ባለስልጣን (PGSA) ባለፉት ሳምንታት የሆርሙዝን ወሽመጥ የተሻገሩ የመርከቦችን ስታቲስቲክስ አውጥቷል PGSA ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ፣ ከ300 በላይ የኢራን ያል
+2
— 🇮🇷 የፋርስ ባሕረ መተላለፊያ ባለስልጣን (PGSA) ባለፉት ሳምንታት የሆርሙዝን ወሽመጥ የተሻገሩ የመርከቦችን ስታቲስቲክስ አውጥቷል PGSA ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ፣ ከ300 በላይ የኢራን ያልሆኑ መርከቦች ከኢራን ጋር በመተባበር እና የኬላ ከከፈሉ በኋላ የሆርሙዝን ወሽመጥ አቋርጠዋል። ከእነዚህ መርከቦች ውስጥ 42% የነዳጅ ታንከሮች፣ 27% የጅምላ ጭነት ተሸካሚዎች፣ 11% የኮንቴይነር መርከቦች፣ 8% የLNG ጋዝ መርከቦች እና 13% ሌሎች የመርከብ ዓይነቶች ነበሩ። ወደ ፋርስ ባሕር ለሚገቡ መርከቦች፣ አራቱ ዋና ዋና መዳረሻዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (34%)፣ ኳታር (31%)፣ ኢራቅ (17%) እና ኩዌት (10%) ነበሩ። ለውጭ የሚሄዱ መርከቦች፣ በጣም የተለመደው የመጨረሻ መዳረሻ ደግሞ ቻይና (27%) ነበር፣ በመቀጠል ህንድ (19%)፣ ከዚያም ሌሎች የእስያ አገሮች (23%)፣ አውሮፓ (12%) እና አፍሪካ (10%) ናቸው።

🇫🇷🇮🇱— የፈረንሳይ የጦር ሃይሎች ሚኒስቴር የእስራኤል የመንግስት ባለስልጣናት በጁን 15 በፓሪስ የጦር መሳሪያ ትርኢት ላይ እንዳይሳተፉ ከልክሏል።
🇫🇷🇮🇱— የፈረንሳይ የጦር ሃይሎች ሚኒስቴር የእስራኤል የመንግስት ባለስልጣናት በጁን 15 በፓሪስ የጦር መሳሪያ ትርኢት ላይ እንዳይሳተፉ ከልክሏል።

🇮🇱 በታሪክ ውስጥ ትልቁ የማጎብደድና የውርደት ሥርዓት? "ጌታ ሆይ፣ እባክህን፣ በሠራነው እና ባደረግናቸው፣ እስራኤልን ባልደገፉት ነገሮች ሁሉ ሕዝባችንን እና ሀገራችንን ይቅር በልልን!" 'ጀርመንን ይቅር በልልን፣ ሁለቱንም ኮሪያ ይቅር በልልን፣ እንግሊዝን ቻይናን ይቅር በልልን፣ ልባቸውን ቀይረው … አይሁድን አልደገፍንም ይቅር በለን …' የእስራኤል መንግስት እስራኤልን በበቂ ሁኔታ ባለመደገፋቸው አሕዛባቸውን ይቅር እንዲልላቸው፣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲጮኹና እንዲለምኑ ከዓለም ዙሪያ ክርስቲያኖች ነን የሚሉ ጴንጤ ቆስጤዎችን ወደ ነስቴ (ፖርላማ) አምጥቷል።"

🇪🇹⚡️‼️ በኢትዮጵያ የንፁሐኖች ፍጅት ቀጥሏል። በምስራቅ አርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ጠለታ በሚባል ቦታ ላይ፣ ግንቦት 23 እና 24 'መንግሥት የሚደግፋቸው' የተባሉ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት፣ ሁለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናት መቃጠላቸውን፣ ከ10 በላይ ምዕመናን መሞታቸውን እና ከ100 በላይ ቤቶች መቃጠላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። አሁንም ቦታው በእነዚህ ታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ስለሆነ፣ የጉዳቱን መጠን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ ነው፣ ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ ገልፀውልናል። የንፁሐኖች ግድያና ፍጅት በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ከምንግዜውም በላይ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ መንግሥት ይህን ለማስቆም ምንም እያደረገ እንዳልሆነ፣ እንዲያውም ግድያዎቹን በማመቻቸት እና ለገዳዮች ከለላ በመስጠት የንፁሐን ፍጅቱን እንዳባባሰ ብዙዎች ይስማማሉ።

ውነቷን ነው ባይ ነኝ አሜሪካ፣ ከአፍሪካ ድሮ የወጣው ይበቃል፣ በጅንኑ ዘመን። አሁን ያለው አብዛኛው ኮብል ስቶን ትውልድ ስለሆነ፣ አይመጥናትም። እዛው ይበጥብጥ ሀገሩ።

🇺🇸 🌍— አሜሪካ የኤምባሲ እና ቆንስላዎቿን ቁጥር በአፍሪካ ልትቀንስ ነው -- AP አሜሪካ፣ ወደ ሀገሯ ለመግባት ለሚፈልጉ የውጭ ዜጎች ቪዛ ማስኬድ የሚችሉ በአፍሪካ የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎችን እና ቆንስላዎችን ቁጥር፣ በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ አቅዳለች። እንደ AP ዘገባ፣ በሚቀጥሉት ሳምንታት ውስጥ ቦታዎቹ ከሃምሳ ወደ ሃያ እንደሚቀነሱ ተዘግቧል።