የቀጠናው ተመልካች
Відкрити в Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
4 310
Підписники
-524 години
-227 днів
-8430 днів
Архів дописів
4 310
🇵🇰🇮🇷🇺🇸 'ሊያበላሹት ይፈልጋሉ'
- የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻባዝ ሸሪፍ፣ የአሜሪካ-ኢራን ውይይቶችን ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ሀገራትን አስጠንቅቀዋል
‹‹አንዳንድ ደስተኛ ያልሆኑ ሀገራት ግራ መጋባትን፣ ጥርጣሬን እና እርግጠኛ አለመሆንን እየፈጠሩ ነው››
‹‹ወንድማማቾቻችን እንደ ብረት ቅጥር በእነርሱ ላይ ይቆማሉ››
*-*-*-
ማንን እያለ እንደሆነ የሚጠፋው የለም መቼስ። ፖርታ ሪኮን ይሆን?
4 310
+5
🇪🇹⚡️ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የእገታ እና ጠለፋ ካፒታል እየሆነች ነው። የባዕዳን ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያን ሰው ለመጥለፍ ተመራጭ አድርገዋታል።
በዜግነት ፖኪስታናዊ የሆኑ ግለሰቦች፣ በአዲስ አበባ ቤት ተከራይተው ሰው ሲጠልፉና ሲያግቱ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።
እነዚህ ተጠርጣሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ለምን ጉዳይ እንደሚመጡ የማይታወቁ ሕንዳዊያንንና ባንግላዴሻዊያንን እያፈኑ ወደ ተከራዩት ቤት በመውሰድ፣ አስረው እየደበደቡና ቪዲዮ እያነሱ ለቤተሰቦቻቸው በመላክ ገንዘብ ሲቀበሉ ቆይተዋል፣ ብሏል ፖሊስ።
ተጠርጣሪዎቹ በአሁኑ ሰዓት ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝ እና በእስር ላይ እንዳሉ ተነግሯል።
4 310
+1
🇺🇸🇮🇷 CNN ብቻ ባገኘው ዘገባ መሠረት፣ በጦርነቱ ወቅት በኢራን የተከሰከሰው ፓይለት ለአሜሪካ ደህንነት አባላት የሰጠውን ቃል አዳምጧል።
ፓይለቱ አይሮፕላኑ ከመከስከሱ በፊት ያየው ነገር እጅግ ያስደነገጠው እንደነበር፣ ከዚህ በፊትም እንዳላየ ተናግሯል።
የኢራን ድሮኖች በአንድ ተጣምረው በሰማይ ላይ እንደ ግዙፍ ጄሊፊሽ ሲንሳፈፉ እንዳየ፣ ትልልቅ ድሮኖች ከላይ፣ ትንንሽ ድሮኖች ከታች እንደ እግር ሆነው ሲጠጉት እንደተመለከተ ተናግሯል።
እጅግ ያስፈሩ እንደነበርና "ኤልያን እንደመሰሉት" ቃሉን ሰጥቷል።
የደህንነት ባለስልጣናቱ፣ ጤናውን በመጠራጠር "እርግጠኛ ነህ ይሄን አይተሃል?" እያሉ ጠይቀውታል፣ ቅዠት ነው፣ አእምሮው ጧ ብሎ ነው ብለው በማሰብ።
የሚለው እውነት ከሆነ ይላሉ እኒህ የደህንነት ባለስልጣናት፣ "ጉዳችን ፈልቷል፣ ኢራን ካሰብነው በላይ በድሮን ቴክኖሎጂ ሄዳለች።"
ፖይለቱ በሰጠው ቃል ላይ ተመርኩዘው የደህንነቱና የፔንታገን ባለስልጣናት ከፍተኛ መደነጋገጥና ሰጣ ገባ ውስጥ ገብተዋል። ብሏል ዘገባው።
ኢራን አሳየች የተባለው ቴክኖሎጂ አሜሪካ አልደረሰችበትም።
*-*-*-
ሙሉውን የCNN መረጃ ብትችሉና ብታነበት ጥሩ ነው። ኢራን ዛሬ ላይ በድሮን ቴክኖሎጂ በዓለም ግንባር ቀደም ሆናለች።
4 310
🇵🇰🇮🇷 የኢራን ፕሬዝዳንት ወደ ፖኪስታን ሲገባ፣ የፖኪስታን አየር ኃይል እጀባ አድርጎለታል።
ሕንዶች፣ ፖኪስታን ከ$300 ቢሊዮን ዶላሩ ላይ ይቦጨቅልኛል ብላ ቋምጣለይ ይላሉ።
4 310
🇮🇱🇵🇸⚡️ - የእስራኤል ዲያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር አሚቻይ ቺክሊ፡
- ፈጣሪ አይበለውና ይሄ Clown (ናፍታሊ ቤኔት) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆነ የፍልስጤም መንግስት ይመሰረታል።
በዚህ መንግሥት የተከናወነው ነገር ሁሉ፣ ከነችግሮቹ እና ተግዳሮቶቹ፣ ገደል ይገባል።
4 310
🇮🇱🇺🇸⚡️ - የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት -
እስራኤል ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ "እስራኤል" የሚለው ብራንድ ስም በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያለው ተወዳጅነት ኔጌቲቭ ገብቷል። ይሄ ክስረት ነው፣ ከስረት ነው!
4 310
🇮🇱⚡️ - የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት፡
የተበላሸውን እስራኤልን ገጽታ ለመቀልበስ ከፊታችን ትልቅ ሥራ አለብን።
በእስራኤል መንግሥት ውስጥ ከቀን ወደ ቀን ለማንም የማይጠቅሙ፣ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ እና ውድ የፖለቲካ ካፒታልን የሚያሟጥጡ እና የሚያባክኑ አልባሌ ንግግሮችን የሚናገሩ ጨቅላ ሚኒስትሮችን በመተካት ይጀምራል።
4 310
🇷🇺⚡️ምዕራባውያን ሩሲያን ከግዛታቸው ለመምታት የሚያመነቱት፤ የሞስኮን የአጸፋ ምላሽ ስለሚያውቁ ነው - ፑቲን
*-*-*
ሞኝ ናቸው እንዴ ከግዛታቸው እርስዎን የሚመቱት? የእንግሊዝ ተንኮል ጠፍትዎ አይሆንም መቼስ። ዩክሬን አለች አይደለም እንዴ? ከዚያ እየመትዎ ነው።
4 310
🇺🇸🇮🇷New York Post አሜሪካ ከኢራን ጋር የደረሰችውን ስምምነት ኮንኗል። Easy Mullah.
New York Post Republican ዘመም የትራምፕ ደጋፊ ጋዜጣ ነው።
Oh yea, Easy Money, Baby እያሉ ይመስላሉ፣ የተከበሩ ሙላ።
4 310
🇮🇷🇴🇲 ኢራን እና ዖማን፡ ከእንግዲህ ወዲያ የሆርሙዝ ወሽመጥ የእኛ ሆኗል። ባለቤቶቹ እኛ ነን፣ ያለኛ ፈቃድ መርከብ በበራችን መንቀሳቀስ አይችልም። ከእኛ የይለፍ ሳያገኝ እና ክፍያውን ሳይከፍል ማለፍ ክልክል ነው። ክፈሉ፣ እለፉ ብለዋል፣ በጋራ ባወጡት የስምምነት መግለጫ።
4 310
🇷🇺⚡️ላቭሮቭ፡ ዛሬ ብሪታንያም ሆነ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት የናዚ ኪየቭ አገዛዝን በጦር መሳሪያ እና በገንዘብ ፍሰት መደገፋቸውን ቀጥለዋል። የገዥው አካል ማንኛውንም የወንጀል ድርጊትቶችንም፣ 'ይበል የሚያሰኝ ነው' እስከማለት ደርሰዋል።
4 310
🇷🇺⚡️ላቭሮቭ፡ አውሮፓ በድርድሩ ላይ ጣልቃ እየገባች፣ ጦርነትን እንጂ ሰላምን አንሻም እያለች እና በትራምፕ አስተዳደር የታዩትን የማስተዋል ቡቃያዎችን ሁሉ እየረገጠች ነው።
4 310
🇷🇺⚡️ላቭሮቭ፡ የአውሮፓ ልሂቃን እና የኪየቭ ደንበኞቻቸው ተንኮል ቢኖርም፣ የልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ግቦች እና ዓላማዎች ሁሉ ይሳካሉ።
4 310
+2
🇷🇺⚡️ፑቲን ምዕራባውያንን ከሩሲያ ጋር ለጦርነት በግልፅ እየተዘጋጁ ነው ሲል ከሷል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን የምዕራባውያን ሀገራት ከሩሲያ ጋር ለጦርነት ዝግጅት በግልፅ እየተወያዩ እና ወታደራዊ በጀታቸውን እየጨመሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኔቶ እና የአውሮፓ ህብረት መሪዎች አክራሪ ወታደራዊነትን እና ወጪን ለማስረዳት የሩስያ ወታደር ስጋት እንደሆነባቸው ውሸትን ይነዛሉ ብሏል።
ፑቲን ቀለል ባለ መልኩ እቅዳቸውን ገልፆታል። ምዕራባውያን ዛቻን ይፈጥራሉ፣ ሩሲያ እራሷን ለመከላከል እንድትሠራ ያስገድዷታል፣ ከዚያም ሩሲያ ጠበኛ ፖሊሲዋን ቀጠለች ብለው ይወቅሳሉ።
*-*-*-
'ጦርነት' ብሎ ለማወጅ ምን አስፈራው? 'አውሮፓዊን እየተዘጋጁብን ነው' ሲል፣ አይደለም sir፣ ተሳስተዋል። አውሮፓዊያን ላለፉት አራት ዓመታት እየተዋግዎት ነው፣ የት ነዎት፣ እርሶ? ምን ማለትዎ ነው? ለምን ጦርነት አውጀው በኃይል አይጨርሱትም። ኪየቭን ለምን አይመቱም? እጅዎን የያዘው ምንድነው? meanwhile ጠላት ትልቁን የጋዝ የነዳጅ ኢንዱስትሪዎቻችንን አውድሟል፣ የልብ ልብ ተሰምቷቸው ያደሙን ጀምረዋል … ሩሲያዊያን በከፍተኛ ድምፅ ውስጥ ውስጡን የሚጠይቁት ነው። የታመቀ የመሬት መንቀጥቀጥ ክሬምሊን ሥር በመላወስ ላይ ነው።
ትናንት ጀምሮ ዩክሬን በሩሲያ ያወደመችውን ብትሰሙ ትደነግጣላችሁ።
4 310
🇺🇸 🇬🇧🇮🇹🇩🇪 ትራምፕ ስለ ኔቶ:
እርዳታቸውን ሲጀመር አልፈለግኩትም። ስታርመር ከጎናችን አልነበረም እና የእንግሊዝ ሕዝብ ይሄን አልወደደለትም፣ እናም አወረዱት። ጠይቄው ነበር ስትራመርን፣ ከጎናችን የምትሆነው መቼ ነው? ብዬ። ስታሸንፉ ከጎናችን እንሆናለን ነው ያለኝ። ስናሸንፍማ ምን ታረግልኛለህ ነው ያልኩት። ጥልያን ቆሻሻ ናት፣ ጀርመንም እንደዚያው የወረደች ናት። እነሱ እኮ ጭራሽ፣ ጌታው፣ እርዳታ የማይታሰብ ነው፣ ነው ያሉኝ። Stupid ነገር ነው፣ እንዲህ አይባልም። ምክኒያቱም እኛም ልንላቸው እንችላለን፣ አንለውም ግን፣ ቆይ እንዲያውም ልንለው እንችላለን።
4 310
⚡🇺🇸🇮🇷 በእስራኤል ቻናል 14 ላይ፣ አንድ እስራኤላዊ ሳይኪክ፣ ኢራን ዝቅተኛ ፍሪኩዌንሲ ኤሌክትሮማግኔቲክ መሳሪያ እየተጠቀመች ትራምፕ በኢራን እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን የመግባቢያ ስምምነት እንዲቀበል አእምሮው ላይ ተጽእኖ እያሳደረች ነው ሲል ተናግሯል። በዚሁ መሳሪያ፣ ትራምፕ ኔታንያሁ ጋር እንዲጣላ እያደረገች ነው ብሏል።
