uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Відкрити в Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
193
Підписники
-224 години
-47 днів
-630 днів
Архів дописів
مَن أَرَاد أن ينْجُو ..."فليَتُب . إبن الجوزي

መርጦ አልቃሹ ኤርሚያስ ለገሰ
መርጦ አልቃሹ ኤርሚያስ ለገሰ

🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿 🍃ቢያንስ ከራሳችን እንማር "ብልጥ ከሌሎች ይማራል፤ ሞኝ ከራሱ ይማራል" ይባላል። የመጀመሪያውን ብስለት ባለማስተዋል፣ ራስን ባለመቆጣጠር አልፈነዋል። ቢያንስ ከራሳችን ድክመት ብንማር ጥሩ ነው። ከደረሱትና ከሚደርሱት እንማር። በምን መልኩ? 🔻1. ወደራሳችን በጥልቀት እንመልከት። ራስን ጥሎ ሁሌ ሌሎችን ማሳደድ ኣኺራን ይጎዳል፣ ቡድንተኝነትን ያወርሳል። የልብ ድርቀትን ያስከትላል። 🔻2. የዑለማኦችን አካሄድ የምንፈልገውን እየመረጥን ሳይሆን ወይም በሌሎች የተመረጠልንን ሳይሆን ከነፍሲያ ወጥተን ከሁሉም አቅጣጫ እንመልከት። ነጠላ ንግግሮቻቸውን ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ አፈፃፀማቸውንም እናጥና። የእውነት እኛ በምናደርገው መጠን ሰው ላይ በማክ * ፈርም ይሁን ተብዲዕ በማድረግ ላይ የተናጠል ፍርድ ለመስጠት ይቸኩላሉ ወይ? በጭራሽ! 🔻3. በምናራምዳቸው እርምጃዎች ላይ የደዕዋችንን መስለሐ በሚገባ እናጢን። ደዕዋችንን የሚያሳጣን፣ መስጂዶቻችንን የሚያስነጥቀን ከሆነ ጩኸታችን ምን ፋይዳ አለው? አካሄዳችን የሰለፊያን ደዕዋ የሚያጠለሽ ከሆነ ወደድንም ጠላንም የጠላትን አጀንዳ እየፈፀምን ነው። 🔻4. ከሱና ዑለማኦች ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ላይ አንገደብ። ይሄ አካሄድ አንዳንዶችን ተ0ሱብና ጉሉው ላይ ሲጥላቸው እያየን ነው። እውነታውን የማያምኑት ችግሩ ስለሸፈናቸው ነው። 🔻5. ተዝኪየተ ነፍስ ላይ እናተኩር። ለችግሩ መስፋት አንዱ ትልቅ ሰበብ የተቅዋ፣ የወረዕ መሳሳት ነው። ሌሎች ላይ ዋሽቶ መክሰስ፣ ሳያረጋግጡ በግምት መወንጀል፣ በጥላቻ ድንበር ማለፍ፣ የራስን ነውር እየደበቁ ሌሎችን መናከስ፣ ... አላህን መፍራት እንደሌለ ወይም እንደሳሳ የሚያጋልጥ ነው። እና እራሳችንን አንርሳ። 🔻6. አቅማችንን እንወቅ። ከቁመታችን በላይ የሆኑ ርእሶችን አናቡካ። 🔻7. ወደ ኢስላም ጠቅልለን እንግባ። አኽላቅም፣ ዙህድም፣ ወረዕም፣ ሲራም፣ ተርጊብና ተርሂብም የኢስላም አካል መሆናቸውን ከምላስ ባለፈ በተግባር እናረጋግጥ። ሰለፎች ከነዚህ ነጥቦች አንፃር የነበሩበትን የላቀ ደረጃ እናጥና። 🔻8. ሰው ተከትለን ገደል እንዳንገባ እንጠንቀቅ። በየመንደሩ የወደድኩትን ውደዱ፣ የጠላሁትን ጥሉ የሚሉ የሹም ዶሮዎች ይኖራሉ። እናስተውል! እነዚህ አካላት አብረውን ቀብር አይገቡም። እጃችንን ይዘው ሲራጥ አያሻግሩንም። እርቃናችንን ብቻችንን ለሒሳብ እንደምንቆም እናስብ። ነገ ከመመርመራችን በፊት ዛሬ ራሳችንን፣ አካሄዳችንን እንመርምር። እናስተውል! ከአንዳንዶች መናከሶች ጀርባ በሱና ስም የሚቀርብ የተዳፈነ የግል ቅሬታ አለ። የአንዳንዶቹ ጉልበት ጭፍን ጭፍራቸው ስለሆነ ገለል በማለት ራሳችንንም እናድን፣ እነሱንም እናስተንፍስ። ይጠቅማቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም። 🔻9. የታየ ሁሉ ባደባባይ አይወራም። ጥፋት የመሰለን ነገር ጊዜ ስንወስድ እንዳሰብነው ላይሆን ይችላል። ክፍተትም ቢሆን መናገሩ ችግር የሚያባብስ ከሆነ አያያዛችንን ማጤን ያስፈልጋል። 🔻10. ለሰፊው ህዝብ እንዘን። በመጯጯህ ከሱና፣ ከዒልም፣ ከመስጂድ የምናርቃቸው እንዳይኖሩ ጥንቃቄ እናድርግ። 🔻11. የመንሀጅ ጥንካሬ ብዙ በመጮህ፣ ብዙ በመዝለፍ፣ ሳያጣሩ በግምት በመወንጀል፣ ንግግር እየቆለመሙ በመፈረጅ አይደለም የሚለካው። ስንወድም፣ ስንጠላም፣ ስናወድስም ስንተችም በልክ በሚዛን ሊሆን ይገባል። ይሄ ቁርኣናዊ መርህ ነው። ማሳሰቢያ፦ የፅሁፌ አላማ ራሴን ከችግሩ ነፃ አድርጌ ሌሎችን መንካት አይደለም። ይልቁንም ሰከን ብሎ በማጤን ለራሳችንም፣ ለወገናችንም፣ ለደዕዋችንም እንዘን፣ ሁላችንም እናስተውል የሚል ነው። አላህ ያለለት ሰው፣ ጎድቶም ተጎድቶም የኋላ ኋላ ሊነቃ ይችላል። በጊዜ ብንነቃ ግን ጉዳት እንቀንሳለን። ደግሞም ሳይመለሱ መሄድም አለ። በሰው ሐቅ ላይ ድንበር መተላለፍ ደግሞ ለመመለስም እንቅፋት ሊሆን ይችላል። አላህ ማስተዋሉን ያድለን። ✍IbnuMunewor

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እና ዘመናዊ ትምህርት ሙስሊሙ ማህበረሰብ አንድም ተገፍቶ፣ ሁለትም ተቸግሮ፣ ሶስትም ሰግቶ ከትምህርት አለም ሗላ ቀረና የእንሰሳት ጭራ እየተከተለ ሌላ ቦታ ደግሞ አፈር እየገፋ እና ከብት እያረባ ወይም በቁጥር ትንሽ ሆኖ በከተማ የሚኖረው ደግሞ እየነገደ "በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ" ውስጥ እየኖረ ይገኛል።በዚህ ምክንያት በአለማዊ ትምህርት እንዲቀደም ተደረገ። በዚህ ጊዜ ራሱን መግለጽ ተቸገረ።ከዚያም ለከተማ አኗኗር ባእድና እራሡን መግለጽ የማይችል ሁኖ ከረመ። በእነዚህ ጥቂት ከተሜ ሙስሊሞች በቡዙሀኑ ይኑር ይሙት በማይታወቀው የገጠሩ ሙስሊም እስልምና ለመዳኘት እና ለመገመት በቃና ኢትዮጵያን ሙስሊሞች ሗላ ቀር በሆነው ማህበረሰብ ውስጥ ለዘላለም የበለጠ ኋላቀር ተደርገው ተሳሉ። አሁንም አየሩን የሞላው ይሄው ሗላቀር አመለካከት ነው። ኢትዮጵያን ሙስሊሞች በተለይ በትምህርት ዘርፍ እንዲርቁ የተደረገበት ስልት በቅኝ ግዛት ዘመን በተለይ በሌሎች የአፍሪካ ሐገራት ሙስሊሙ ከሌላው ጥቁር ወገኑ እንኳን ተለይቶ እንዳይማር የተደረገበት የማግለል ዘዴ ቢብስ እንጅ ያንሳል ብየ አላምንም። ፒው የምርምር ማእከል 2016 ባወጣው ዘገባ በአፍሪካ (ከሰሐራ በታች) ለመማር የታደለው የሙስሊሙ ቁጥር ከክርስቲያኖች አንፃር ሲነፃፀር በግማሽ ያንሳል። ለምሳሌ በጋና ፕሮቴስታንቱ በዋነኛነት ቀጥሎም ካቶሊክ ክርስቲያኖች ከደረሱበት የትምህርት ደረጃ አንጻር ሙስሊሙ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። በምዕራብ አፍሪካም ሆነ በሀገራችን ሙስሊሙ ማህበረሰብ እንዳይማር የሆነው በቅኝ ግዛት ዘመን የትምህርት ስርአቱ በሚሽነሪዎች የተቀመረ እና የተነደፈ በመሆኑ አላማውም እምነትን ማስቀየር ስለነበረ ነው። በ20ኛው ክፍለዘመን የመጀመሪያዎቹ አስርተ አመታት ሚሽነሪዎች(የሐይማኖት ሰባኪዎች) በትምህርት አሳበው እያሳሳቁ ነበር ብዙ የምዕራብ አፍሪካ ሙስሊሞችን ወደ ክርስትና መውሰድ የቻሉት። ስለዚህ የኛን ሀገር ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሙስሊሞች ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት መላክ ክህደት እንደመፈጸም አድርጎ ቆጥሮት ሰነባበተ ማለት ነው። .... ይቀጥላል

أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَهَهُ هَوَاهُ ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን.... الفرقان43

አቡደርዳእ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፦ "ዓሊም ሁን፣ አልያም ተማሪ አልያም ዓሊም ወዳጅ አልያም የዓሊም ተከታይ ሁን ፤ አምሰተኛ እንዳትሆን ትጠፋለህ።" ሐሰን አልበስሪይ አምስተኛው  እርሱ ሙብተዲዕ ነው ብለዋል። [አልኣዳቡ አሸሪዓህ (2/35)]

ሸይኽ፣ ኡስታዝ ሆይ! ~ ዛሬ ዛሬ የታይታና የወሬ ድግሶች በዝተዋልና አስተውል። ኪታብህን አስተምር። ደዕዋ ላይ አተኩር። ማለቂያ የሌለው ሹራ፣ ስብሰባ፣ ስልጠና፣ የሽልማት ፕሮግራም በሚሉ ነገሮች ነጋ ጠባ አትጠመድ። ከሚሰሩት ይልቅ የሚያወሩት የበዛ ከሆኑ ሰዎች ጋር ያለህን ቁርኝት በጊዜ መላ በለው። ከመድረክ ሱስ ተጠንቀቅ። በካሜራ ፍቅር አትለከፍ። ስልጠና፣ ስብሰባ እያልክ የሆቴል ድግስ አታሳድ። አብዛኞቹ እነዚህ ስልጠና፣ ስብሰባ እያሉ የሚያሳድዱ አካላት ቁጭ ብለው የሚሰጡት ደርስ የላቸውም። እኔ አንድ የክፍለ ሃገር ከተማ ውስጥ ነጋ ጠባ ሹራ እየተባለ በስርአት መቅራት ሲያቅታቸው ደረሶች የተበተኑበት አውቃለሁ። ደርስ ላይ አስተማሪው ቀሪ ካበዛ ያለ ጥርጥር እየተቀዛቀዘ፣ ታዳሚው እየተመናመነ ነው የሚሄደው። = ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

"የዲን ፈተና ከዱንያ ፈተና ይበልጥ የከፋ ነው።" ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁሏህ [ شرح العقيدة الواسطية ص٤٨٦]

ሙሸቢህ ማለት ሙታንን የሚማፀን ነው ! ሙታንን የሚማፀን በሶስቱም የተውሒድ ክፍሎች አጋርቷል ... ከደርስ የተቆረጠ ... https://t.me/msirage4

በአሏህ ላይ መጥፎን አትጠርጥር በነፍስህ ላይ መጥፎን ጠርጥር ከደርስ የተቆረጠ ... https://t.me/msirage4

ሸይኽ ሙሐመድ አብዱል ወሓብ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "አንዳንድ ጃሂል ፦"ተውሒድን ተረድተዋናል።" የሚሉት  አባባል ከትላልቅ ጅሕልና እና ከሸይጣን ተንኮሎች አንዱ ነው። [መጅመዐል ሙአለፋት አሸይኽ (1/175)]

ተውሒድ ይለያያል እያሉ ትምህርት እንዳይሰጥ የሚከለክሉ ሰዎች በመስጂዶች ላይ ኮሚቴም ሆነ ኃላፊ ሊደረጉ አይገባም። የመስጂድ ጉዳይ እጅግ በጣም ትልቅ ኃላፊነት ነው። እንዲህ አይነት ሰዎችን መስጂዶች ላይ ኃላፊ ማድረግ ህዝብ ላይ በደል መፈጸም ነው። ተውሒድ የዒልም ሁሉ ቁንጮ ነው። ችግሩ እነሱ እንደሚያስቡት ከተውሒዱ ሳይሆን ከተሸከሙት የጅህልና በሽታ ነው። የአቀራረብ ችግር ካለ መመካከር ወይም አስተካክሎ ማስተማር እንጂ በር መዝጋት አይደለም መፍትሄው። በአቀራረብ እያመሀኙ ከነጭራሹ በር መከርቸም ግን አጉል ሰበብ መፈለግ እንጂ ለተውሒድ ደንታ ቢስ መሆን እንዳለ እንዲሁም ለህዝብ ሐቀኛ መቆርቆር እንደሌለ ነው የሚያሳየው። እንዲያውም በተውሒድ ትምህርት ሰበብ የሚነሳ ግርግር ካለ ትምህርቱ በጣም እንደሚያስፈልግ የሚያሳይ ጠቋሚ ምልክት ነው። ስለዚህ መፍትሄው ግርግሩ እስኪቆም፣ ብዥታው እስከሚገፈፍ ወጥሮ መስራት እንጂ "እንዳትለያዩን ተውሒድ አታስተምሩ" ማለት አይደለም። = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor t.me/IbnuMunewor

لا بأس أن يعمل المرءُ لدنياه ولكن دون أن ينسى آخرته ولا بأس أن يجعل بيته جميلاً ولكن دون أن ينسى قبره

🌴 የወሊድን ምጥ የሚያቀሉ የተምር ሚስጥሮች 🌴 👉አብዛኛዎቹ ነፍሰ ጡር እናቶች ለ"ቀላል ምጥ" በሚባሉ ውድ ነገሮች ላይ ገንዘባቸውን ያባክናሉ፤ ነገር ግን ገበያ ውስጥ በቀላሉ የሚገኘውን ትልቅ ጥቅም ያለው ምግብ ይዘነጋሉ። ወተት አይደለም፣ ዝንጅብል ወይም የእፅዋት ሻይ አይደለም። 👉 እሱም ተምር (Dates) ነው! አዎ ማማ፣ ተራ ተምር! ጥቅሙን ላብራራሽ 👇 🔥 ከ37ኛው ሳምንት ጀምሮ በቀን 6 ተምር የሚበሉ እናቶች እነዚህን ጥቅሞች የማግኘት ዕድላቸው ሰፊ ነው፦ ✔️ ሆስፒታል ሲደርሱ የማህፀን በር ክፍተት (Dilation) ቀድሞ የተዘጋጀ የመሆን ዕድል ✔️ የንቁ ምጥ (Active labor) ጊዜን መቀነስ ✔️ ለመገፍተር የሚያስችል ጠንካራ ጉልበት እንዲኖር ማድረግ ✔️ በቀዶ ጥገና (C-section) የመውለድ ዕድልን መቀነስ ተምር በሰውነትሽ ውስጥ በምስጢር የሚሰራው ስራ፦ 🍯 የማህፀን በርን (Cervix) በማለስለስ ለወሊድ ማዘጋጀት 🍯 ማህፀን ለምጥ ትዕዛዞች (Contractions) ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ መርዳት 🍯 የተፈጥሮ ኦክሲቶሲን (Oxytocin) ሆርሞንን ማነቃቃት 🍯 በምጥ ወቅት የማይዝል ጉልበት መስጠት አንዳንድ እናቶች ሆስፒታል ሲደርሱ ነርሷ "ማማ፣ ቀድሞውኑ 5-6 ሳንቲ ሜትር ተከፍቷል" ብላ የምታስደንቃቸው ለዚህ ነው! 😳 ጭንቀት የለም፣ መድኃኒት የለም፣ ፍርሃት የለም። መመሪያው ቀላል ነው፦ 📌 ከ37ኛው ሳምንት ጀምሮ → በቀን 6 ተምር መመገብ ርካሽ፣ ተፈጥሯዊ፣ ጣፋጭ እና ውጤታማ።

✅ የተክፊር አደጋ (ክፍል 01) 🎙 محاضرة بعنوان: "بيان براءة الأئمة النبلاء، عما وصمهم به التكفريون الجُهلاء، من أنهم وقعوا فى بدعة الإرجاء، ➡️ በቅርቡ ሙስጠፋ ዓብደላህ በሱና ዑለማኦች ላይ የቀጠፈበትና ያለ እውቀት በኢርጃእ የገለፀበት ሪከርድ ላይ የተሰጠ ረድ። ↪️ የሙርጂአዎች እና የአህለ'ስሱናዎች መሰረታዊ ልዩነቶች፤ ↪️ ቀደምቶች "አንድ አካል ከኢርጃእ የጠራ መሆኑን" የሚያረጋግጡበት ሚዛን፤ ↪️ ሸይኽ ረቢዕ ሙርጂእ ናቸውን!? ሸይኽ ፈውዛንስ ሸይኽ ረቢዕን ሙርጂእ ብለዋልን?፤ ↪️ ዑዝር ቢል ጀህል የሚሰጥን ሰው ሙርጂእ ስለሚሉት ሓዳዲዮች ኢብኑ ዑሠይሚን ምን አሉ?፤ ↪️  ሸይኽ ረቢዕ ስለ ኢማን ያላቸው አቋም ምንድነው? እውነት ዓመልን "ሸርጡል ከማል ነው" ብለዋልን?፤ ↪️"ዓመል ሸርጡ ሲሓ ነው ለኢማን? ወይስ ሸርጡል ከማል?" ስለሚለው ዑለማኦች ምን አሉ? ↪️ እና መሰል ነጥቦች የተዳሰሱበት በድምፅ ማስረጃ የተደገፈ ሙሐደራ ነው። 🗓ጥር 01,2018/ረጀብ 20,1447 = የቴሌግራም ቻናል ✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy ✈️ t.me/Abu_lmran_Alaseriy

0ምር ብኑ ቀይስ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ "ከረመዳን በፊት ራሱን ያስተካከለ ሰው ምንኛ ያማረ እድል አለው!" [ለጧኢፉል መዓሪፍ፡ 138] = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/Ibnu
0ምር ብኑ ቀይስ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ "ከረመዳን በፊት ራሱን ያስተካከለ ሰው ምንኛ ያማረ እድል አለው!" [ለጧኢፉል መዓሪፍ፡ 138] = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

⎘ጥያቄ፦ ሙስጠፋ የመልክተኛው ﷺ ስም ነውን? 🎙በኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸድር አሕመድ አል-ኸሚሴ «ሐፊዘሁሏህ»  T.me/Ustaz_Kedir_ahmed_2

የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦ “ነሷራዎች የመርየም ልጅ ኢሳን ከደረጃው በላይ ከፍ ከፍ እንዳደረጉት እኔንም ከፍ አታድርጉኝ፡፡ እኔ ባሪያ ነኝ፡፡ የአላህ ባሪያው እና መልክተኛው ነው በሉ”፡፡