uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

SU|ኤስዩ

SU|ኤስዩ

Відкрити в Telegram

የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር [Scripture Union Ethiopia] #ኤስ.ዩ፣ ከ1957 ጀምሮ የኃይስኩል ተማሪዎችን እያገለገለ ይገኛል። #ራዕያችን "ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት" ነው በዚህ ቻናል:— በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ነክ መረጃዎች ይተላለፍበታል።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
672
Підписники
+324 години
+57 днів
+330 днів
Архів дописів
photo content
+9

photo content
+9

photo content
+4

#ጅግጅጋ_እና_ባቢሌ ---- ----- ------ በምስራቅ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ፣ ጅግጅጋ እና ባቢሌ ከተሞች፣ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ጉብኝት ተካሂዷል። #ጅግጅጋ በጅግጅጋ የጉብኝቱ አካል የሆኑት ስድስት(6) የተማሪ ህብረቶች ናቸው። በተጨማሪም ከ አጠቃላይ የከተማ የተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት መሪዎች ( GF leaders) ጋር ገንቢ የሆነ አገልግሎት ነክ ውይይት እና ምክክር ለማድረግ ተችሏል። በጅግጅጋ ሰባት የተደራጁ የተማሪዎች ሕብረት አሉ። በአንፃሩ ማደራጀት የሚፈልግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ትምህርት ቤቶች አሉ። ከመሪዎች እና በከተማው ተማሪዎችን ከሚያገለግሉ አሶሼት ጋር በነበረን ውጤታማ የምክክር ጊዜ፣ የተደራጁትን ሕብረቶች ማጠናከር እንዲሁም ተጨማሪ ሕብረቶችን ስለማደራጀት ምክክር አድርገናል። በጥር ወር አጋማሽ ላይ አካበቢያዊ የመሪዎች ጉባኤ (Area Leadership Summit) ማዘጋጀት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተነጋግረናል። #ባቢሌ በባቢሌ ከተማ ቁጥራቸው ስልሳ (60) የሚደርስ የተነቃቁ ክርስቲያን ተማሪዎች አሉ። ነገር ግን እስከ አሁን መደበኛ የሆነ ሣምንታዊ ፕሮግራም ማድረግ አልጀመሩም። ከግቢ ውጪ ሕብረት ማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታ የመፍጠር ሥራ ከአብያተክርስቲያናት መሪዎች ጋር መስራት ይጠበቅብናል። ለተማሪዎች አስፈላጊ የሆኑ ስልጠናዎችን ስለ መስጠት እንዲሁም የተማሪ ሕብረት አገልግሎትን በተመለከተ ለቤተክርስቲያን መሪዎቸ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረግ ስለ ማዘጋጀት ከአብያተክርስቲያናት መሪ እና ከተማሪ መሪዎች ጋር ምክክር ተደርጓል። በባቢሌ እና ጅግጅጋ፣ ተማሪዎችን በትጋት እያገለገሉ የሚገኙ አሶሼትስን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸው! ወንድማችን ግዛው በክልላዊ ቢሮው የጅግጅጋውን እና ባቢሌን ጨምሮ በሌሎቹም ከተሞች ላይ የተማሪ አገልግሎትን ጎን ለጎን በትጋት እያከናወነ ነው። እግዚአብሔር እሱንም አብዝቶ ይባርከው። ፀጋንም ይጨምርለት። በፀሎት አብራችሁን ሁኑ፦ 👉🏿 በባቢሌ እና ጅግጅጋ የተጀመረው መልካም የተማሪዎች እንቅስቃሴ እንዲቀጥል 👉🏿እግዚአብሔር በባቢሌ የሚገኙ አብያተክርስቲያናትን ለተልዕኮ እንዲያበረታ 👉🏿 በባቢሌ እና ጅግጅጋ እያገለገሉ ያሉትን አሶሼትስን እንዲባርክ ======== #ኤስ_ዩ #ምስራቅ_ክልል #ጅግጅጋ #ባቢሌ #ኢየሱስን_እየተከተሉ #በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ #ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎች_ማየት

photo content
+4

#የኃይስኩል_ተማሪዎች_ሕብረት #በወራኢሉ_እና_ጃማ ----- ---- ----- ------ #በወረኢሉ እና #ጃማ ከተማ የክርስቲያን_ተማሪዎች_ህብረት ጉብኝት፣ ምክክር እና የስልጠና መርሐ ግብር ተካሂዷል። በሰሜን ምስራቅ ኤስዩ ክልል፣ #ደቡብ_ወሎ_አካባቢያዊ_ቢሮ፣ ዓርብ፣ ህዳር 26/2018 ዓ.ም #በወረኢሉ ኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት መደበኛ ፕሮግራም ላይ የእግዚአብሔር ቃል ጥናት ተደርጓል። የጸሎትም መርሐ ግብርም ተካሂዷል። በተማሪ ሕብረት አገልግሎት ዙሪያም ከመሪዎች ጋር ምክክር ተካሂዷል። በማለዳ መርሐ ግብር፣ የእግዚአብሔር ልብ ለኃይስኩል (God's Vision for High school) በሚል ርዕስ ለተማሪዎች መልዕክት ቀርቧል። በቀረበው መልዕክት ተማሪዎች የእግዚአብሔር ቅንዓት ተካፋዮች እንዲሆኑ ፣ የተማሪ ሕብረት ዐላማን እንዲረዱ ፣ እንዲሁም ስለሚማሩበት ትምህርት ቤት ማሕበረሰብ እንዲያስቡ ተሞግተዋል። ወረኢሉ ፣ ከደሴ የሦስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ (3:30) የመኪና ጉዞ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። #ጃማ_ከተማ ----- ---- ---- ቅዳሜ፣ ህዳር 27 /2018 ዓ.ም ፥ ከጃማ ኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት አባላት ጋር አገልግሎትን በተመለከተ ሰፊ ምክክር ተደርጓል። እንዲሁም ከሕብረቱ መሪዎች ጋር የጋራ የእግዚአብሔር ቃል ጥናት እና የፀሎት መርሐ ግብር ተካሂዷል። ጃማ ከተማ ከወረኢሉ የአንድ ሰዓት (1:00) መንገድ ሲርቅ፣ የክልላዊ ቢሮ መቀመጫ ከሆነችው ደሴ ከተማ የአራት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ (4:30) የመኪና ጉዞ ርቀት ላይ ይገኛል። ሁለቱም አካባቢዎች በሰላም እጦት ፣ በጦርነት ስጋት ውስጥ የሚገኙ ናቸው። አልፎ አልፎ ትምህርት ቤቶች የመዘጋት እጣፋንታ ይገጥማቸዋል። በሁለቱም ከተሞች የሚገኙ ክርስቲያን ተማሪዎች በቋሚነት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግላቸው ተባባሪ የኤስዩ አገልጋይ (Associate Staff) ይፈልጋሉ። አካባቢያዊ ተግዳሮት በበዛበት እንዲሁም ብዙ የቅርብ ክትትል በሌለበት ሁኔታ መሪዎች ሕብረቱን ለማስቀጠል እና ለማገልገል የሚያሳዩት ትጋት አስደናቂ ነው። የዕረፍት ሰዓት መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መቀጠሉም ደስ ያሰኛል፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያዳበሩት መልካም ግንኙነትም የሚመሰገን ነው። ጉብኝቱ፣ ተማሪዎች የሚጎበኛቸው እና የሚያበረታታቸው ሰው በሚፈልጉበት ወሳኝ ወቅት በመካሄዱ ደስ ተሰኝተዋል። ለአገልግሎት መነሣሣት ፈጥሮላቸዋል። #ፀሎት እግዚአብሔር አካባቢያችንን ሰላም እንዲያደርግ፣ አዳዲስ የተመሰረቱ ህብረቶች እንዲጸኑና ፍሬያማ እንዲሆኑ ጸልዩልን የሚል ጥያቄም አቅርበዋል። ይኸን አገልግሎት በትጋት እያገለገሉ ያሉትን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካቸው! ፀጋን ያብዛላቸው! ------ ------ ------ ------- #ኤስ_ዩ #ሰሜን_ምስራቅ_ክልል #ደቡብ_ወሎ_አካባቢያዊ_ቢሮ #ወረኢሉ_ክርስቲያን_ተማሪዎች_ህብረት #ጃማ_ክርስቲያን_ተማሪዎች_ህብረት #ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ_ተማሪዎች_ማየት

To register Use the link below https://forms.gle/gwQHxtjKe12YKrCv9
To register Use the link below https://forms.gle/gwQHxtjKe12YKrCv9

#በፀሎት_አብረናቸው_እንሁን "… የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።" ያዕቆብ 5:16 ----- ----- ----- ከማርበርግ ቫይረስ ጋር ተያይዞ አሳሳቢ የሆነውን ወቅታዊ የጤ
#በፀሎት_አብረናቸው_እንሁን "… የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።" ያዕቆብ 5:16                ----- ----- ----- ከማርበርግ ቫይረስ ጋር ተያይዞ አሳሳቢ የሆነውን ወቅታዊ የጤና ሁኔታ ሁላችንም እንገነዘባለን። ችግሩ ቀድሞ በተከሰተበት በጅንካ እና አካባቢው  በወቅታዊው የጤና ስጋት ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ፌሎሽፕ  መደበኛ ሕብረት ማድረግ አቁመዋል። ችግሩን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትራንስፖርትን ጨምሮ የማኅበራዊ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። የቁጥጥር ሥራው ውጤት እያስገኘም እንደሆነ እየሰማን ነው። በእንዲህ ዐይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለፉ ለሚገኙት ተማሪዎችና አጠቃላይ ማሕበረሰብ በፀሎት አብረናቸው ልንቆም ይገባል። 🙏 እግዚአብሔር ይኸን ገዳይ በሽታ ከምድሪቱ እንዲጠርገው፣ 🙏 በበሽታ ስጋት ውስጥ ላሉት የእግዚአብሔር ጥበቃ እንዲበዛላቸው፣ 🙏 ወገኖቻቸውን በዚሁ በሽታ ምክንያት በሞት ያጡትን የእግዚአብሔር ማጽናናት እንዲበዛላቸው፣ 🙏 ለተማሪዎች ተስፋ እንዳይቆርጡ ፤ በእምነት እንዲበረቱ፣ እንፀልይላቸው🙏 @suethio

ጉብኝት እና ስልጠና በሰሜን ምዕራብ ኤስ.ዩ ክልል ------- ------ ------- ባሳለፍነው ቅዳሜ ህዳር 20፣ ሰሜን ምዕራብ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልላዊ ቢሮ ፣ ደብረማርቆስ
+6
ጉብኝት እና ስልጠና በሰሜን ምዕራብ ኤስ.ዩ ክልል ------- ------ ------- ባሳለፍነው ቅዳሜ ህዳር 20፣ ሰሜን ምዕራብ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልላዊ ቢሮ ፣ ደብረማርቆስ ከተማ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶችን የመጎብኘት እና የማስታጠቅ ተግባራት ተከናውኗል። በተጨማሪም በደብረማርቆስ ከተማ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) አገልግሎትን በተመለከተ ራዕይ የማካፈል ፕሮግራም ተካሂዷል። በዚህ የግማሽ ቀን ፕሮግራም የአጥቢያ ቤ/ክ መሪዎች ተካፋይ ሆነዋል። ዝግጅቱ፣ ተሣታፊ የነበሩ መሪዎች፣ የኤስ.ዩን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሤት፣ የትኩረት አቅጣጫ፣ ስልትና አሰራር በተገቢው ሁኔታ ለመገንዘብ አስችሏቸዋል። ቃለ—እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ)፣ ትኩረቱን በመለስተኛ እና 2ኛ ደረጃ ክርስቲያን ተማሪዎች ላይ በማድረግ፣ ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ መሳካት፣ ከቤተክርስቲያን ጋር ለቤተክርስቲያን፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራ አገልግሎት ነው። እግዚአብሔር አካባቢውን ሰላም እንዲያደርግ፣ አዳዲስ ህብረቶች እንዲመሰረቱ፣ እንዲጸኑና ፍሬያማ እንዲሆኑ ጸልዩልን። ------- ----- ----- #ኤስ_ዩ #ሰሜን_ምዕራብ_ክልል #ደብረማርቆስ #ባህርዳር #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት @suethio

በደሴ እና አካባቢዉ የተማሪ ህብረት መሪዎች ስልጠና (AHLS) ----- ----- ------- ------- በሰሜን ምስራቅ ኤስዩ ክልል፣ በደቡብ ወሎ አካባቢያዊ ቢሮ፣ #ከሃይቅ፣ #ከኩታበርና #ከደሴ
+7
በደሴ እና አካባቢዉ የተማሪ ህብረት መሪዎች ስልጠና (AHLS) ----- ----- ------- ------- በሰሜን ምስራቅ ኤስዩ ክልል፣ በደቡብ ወሎ አካባቢያዊ ቢሮ፣ #ከሃይቅ፣ #ከኩታበርና #ከደሴ ለተውጣጡ የሃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት መሪዎች ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው ቅዳሜ፣ ህዳር 20 የተካሄደ ሲሆን፤ አገልጋይ መሪነት (Servant Leadership)፣ ተልዕኮ መር የተማሪ ህብረት ( Missional School Fellowship) ፣ የትምህርት ልህቀትና የትምህረት ምርጫ (Acedamic Excellence and Choice) እና የቡድን ስራ (Team Work) ርዕሶች ላይ የተሰጠ ሲሆን፤ በተጨማሪም የጸሎት፣ የአምልኮና የህብረት ግዜ ነበረ። ክብር ለጌታ ይሁን🤲🤲 እግዚአብሔር አካባቢውን ሰላም እንዲያደርግ፣ አዳዲስ የተመሰረቱ ህብረቶች እንዲጸኑና ፍሬያማ እንዲሆኑ ጸልዩልን። ----------------------- #ኤስ_ዩ #ሰሜን_ምስራቅ_ክልል #ደሴ_ደቡብ_ወሎ_አካባቢያዊ_ቢሮ #ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ_ተማሪዎች_ማየት

#የተማሪ_ሕብረት_ማደራጀት ----- ---- ----- ------ ከቃለ—እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ) ተልዕኮ መካከል ቀዳሚው ተማሪዎች ለፀሎትና የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት የሚሰባሰቡበ
+3
#የተማሪ_ሕብረት_ማደራጀት ----- ---- ----- ------ ከቃለ—እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ) ተልዕኮ መካከል ቀዳሚው ተማሪዎች ለፀሎትና የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት የሚሰባሰቡበትን #ሕብረት_ማደራጀት ነው። ትላንት ዓርብ ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም የሆነውም ይኸው ነው። በአዲስ አበባ ኤስ.ዩ፣ ምስራቅ ዞን የ MALD ትምህርት ቤት #የተማሪዎች_ፌሎሽፕ ተመስርቷል። #ወላጆች፣ የተማሪ ሕብረት አስፈላጊነት ላይ መክረው፣ ተማሪዎች የሚሰባሰቡበትን ቦታ ፈልገው አግኝተው፣ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው፣ ስለ ሕብረት አስፈላጊነት ከእግዚአብሔር ቃል እንዲሁም ካሣለፉት ግለ—ሕይወት ምስክርነት አቅርበው መሆኑ ነገሩን ለየት ያደርገዋል። በምስረታው ቀን እግዚአብሔር ለኃይስኩል ያለው ልብ ምን እንደሆነ መልዕክት አቅርበናል። የኤስ.ዩን የአገልግሎት ኃላፊነት ለተማሪዎችና ለወላጆች አስረድተናል። ከተማሪዎቹ ጋር ደስ የሚል የሕብረት ጊዜም አሳልፈናል። በዕለቱ ፣ ወንድም እሸቱ (የአዲስአበባና ዙሪያው ክልላዊ ቢሮ አስተባባሪ) እና እህት ምዕራፍ በዞኑ የኤስዩ አሶሼት ተገኝተው ከወላጆችና ከልጆች ጋር ተዋውቀዋል። ከዚህ በኋላ ሣምንታዊ ፕሮግራም ይቀጥላል። ተማሪዎቹን እና እነሱን የሚያገለግሉትን አሶሼቶች ፀሎት አስቧቸው። ወላጆች እና ተማሪዎች ሕብረቱ በመመስረቱ በጣም ደስ እንደተሰኙ ነገረውናል። እግዚአብሔር ተማሪዎች ለሕይወትና ለተልዕኮ የሚታጠቁበትን እንዲህ ያሉ የተማሪ ሕብረቶችን ያብዛልን። ፍላጎታችን በየኃይስኩሉ የተማሪ ሕብረቶች እንዲመሰረቱ ነው! ( Every High School— A fellowship..!) #ኤስ_ዩ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

ጉብኝት እና ስልጠና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልል ------- ------ ------- ባሳለፍነው ቅዳሜና ዕሁድ፣ ህዳር 13 እና 14/2018 ዓ.ም ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የቃለ እግዚአብሔር አ
+9
ጉብኝት እና ስልጠና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልል ------- ------ ------- ባሳለፍነው ቅዳሜና ዕሁድ፣ ህዳር 13 እና 14/2018 ዓ.ም ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልላዊ ቢሮ ፣ ሆሣዕና እና ዱራሜ ከተማ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶችን የመጎብኘት እና የማስታጠቅ ተግባራት ተከናውኗል። በሆሣዕና የኃይስኩል ፌሎሽፕ መሪዎች ጋር የዘፍጥረት መጽሐፍ በጋራ ተጠንቷል። በተጨማሪም፣ የፌሎሽፕ መሪዎች፣ አገልጋይ—መሪነት እና ወዳጃዊ ወንጌልን የማድረስ ስልት ( PCS) ሴሚናር ተካፍለዋል። ከተማሪ ሕብረት መሪዎች ባሻገር፣ ለአጠቃላይ የተማሪ ሕብረት አባላት በትምህርት ልኅቀት ( Academic Excellence) ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ተሰጥቷል። ይህ ስልጠና ተማሪዎች የትምህርትን ክርስቲያናዊ ንጽረተ—ዓለም መገንዘብ እንዲችሉ ያግዛቸዋል። በምላሹ፣ የትምህርት ተሳትፎና ውጤታቸው ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል። ከሆሣዕና በተጨማሪ በዱራሜ ከተማ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) አገልግሎትን በተመለከተ ራዕይ የማካፈል ፕሮግራም ተካሂዷል። በዚህ ፕሮግራም የኃይስኩል ተማሪዎች ፌሎሽፕ መሪዎች እንዲሁም የቤ/ክ መሪዎች ተካፋይ ሆነዋል። ቃለ—እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ)፣ ትኩረቱን በመለስተኛ እና 2ኛ ደረጃ ክርስቲያን ተማሪዎች ላይ በማድረግ፣ ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ መሳካት፣ ከቤተክርስቲያን ጋር ለቤተክርስቲያን፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራ አገልግሎት ነው። ------- ----- ----- #ኤስ_ዩ #ማዕከላዊ_ኢትዮጵያ_ክልል #ሆሣዕና #ዱራሜ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

photo content
+3

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

የተማሪ ሕብረት በአጋሮ ከተማ በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በአጋሮ ከተማ፣ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ተደራጅቷል፡፡ ሕብረቱ ከዚህ በፊት በተደራጀ መልኩ ሲካሄድ ቢቆይም ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ ቆይ
+9
የተማሪ ሕብረት በአጋሮ ከተማ በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በአጋሮ ከተማ፣ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ተደራጅቷል፡፡ ሕብረቱ ከዚህ በፊት በተደራጀ መልኩ ሲካሄድ ቢቆይም ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ የምሥረታ ፕሮግራሙ በአጋሮ ምስጋና ቤተ ክርስቲያን የተካሄደ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ተማሪዎች እና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ተገኝተዋል። የተማሪዎች ህብረት ፕሮግራም ሁልጊዜ ዓርብ፣ በምስጋና አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ይቀጥላል። በተማሪዎች ሕብረት አገልግሎትን በልዩ ልዩ መንገድ እየደገፉ ያሉትን አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካቸው ለማለት እንወዳለን፡፡ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ራዕይ፣ ተማሪዎች፣ “ “ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ” ሆነው ማየት ነው፡፡ ከተልዕኮ መካከልም ቀዳሚው ተማሪዎች ለፀሎትና የእግዚአብሔርን ቃል በጋራ ለማጥናት የሚሰባሰቡበትን ፌሎሽፕ ማደራጀት ሲሆን፤ የተደራጁትን ለደቀመዝሙር ሕይወትና ለወንጌል ተልዕኮ ማስታጠቅ ይገኝበታል፡፡ በተጨማሪ ፣ የሕብረቱ መሪዎች አገልጋይ-መሪነትን እንዲለማመዱ፤ ከቤታቸውን ጀምሮ፤ቤተክርስቲያንን፤ትምህርት ቤታቸውን እንዲሁም ሰፊውን ማኅበረሰብ እንዲያገለግሉ ማዘጋጀት የሚሉት የተልዕኮ አካላችን ነው፡፡ __________ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ኤስ_ዩ

በሁምቦ ጠበላ የኤስዩ የተማሪ ህብርት ስልጠና ----- ----- ------- ------- በደቡብ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ ወላይታ ሶዶ አካባቢያዊ ቢሮ #ሁምቦ_ጠበላ ከተማ የኃይስኩል ተማሪዎች
+7
በሁምቦ ጠበላ የኤስዩ የተማሪ ህብርት ስልጠና ----- ----- ------- ------- በደቡብ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ ወላይታ ሶዶ አካባቢያዊ ቢሮ #ሁምቦ_ጠበላ ከተማ የኃይስኩል ተማሪዎች ስልጠና ተካሂዷል፡፡ በስልጠናው በከተማው የሚገኙ ክርስቲያን ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በዕለቱ የትምህርት ልህቀት (Academic Excellence) ላይ ያተኮረ ሴሚናር ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም የኤስ.ዩ የተማሪዎች አገልግሎትን በተመለከተ ቪዥን ዶክመንቱ በተብራራ መልኩ ቀርቧል፡፡ ----------------------- #ኤስ_ዩ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

በአምቦ አካባቢዉ ኤስዩ የተማሪ ህብረቶች ስልጠና ----- ----- ------- ------- በአዲስ አበባ እና ዙርያው ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ በአምቦ እና አካባቢው የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረቶች ስልጠ
+8
በአምቦ አካባቢዉ ኤስዩ የተማሪ ህብረቶች ስልጠና ----- ----- ------- ------- በአዲስ አበባ እና ዙርያው ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ በአምቦ እና አካባቢው የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረቶች ስልጠና ተካሂዷል፡፡ ህዳር 13 በተካሄደው ስልጠናው በከተማው እና ዙርያው ያሉ የተማሪዎች ብረቶች ተሳታፊ ሆነዋል። በዕለቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ ሊኖረን ስለሚገባ Conviction እና Motivation የተነሳ ሲሆን የInductive bible Study ስልትን ስልጠና ወስደዋል። በተጨማሪም የኤስ.ዩ የተማሪዎች አገልግሎትን በተመለከተ እንዲሆም በቀጣይ በአካባቢው ስለሚኖረው አገልግሎት እና አደረጃጀት ምክክር ----------------------- #ኤስ_ዩ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

የዕውቅና እና የምስጋና ጊዜ! _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ ወንድማችን ዶ/ር አለም ባዘዘው ለኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ያለውን አስተዋጽዎ በተመለከተ ሁሉም በየፈ
+9
የዕውቅና እና የምስጋና ጊዜ! _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ ወንድማችን ዶ/ር አለም ባዘዘው ለኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ያለውን አስተዋጽዎ በተመለከተ ሁሉም በየፈርጁ የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በ Scripture Union በሁለተኛ ደረጃ ክርስቲያን ተማሪዎች ኅብረት አገልግሎት ውስጥ የተሰማራን በመስካችን በሙሉ ልብ፥ በተቀበለው ጸጋ፥ በፍቅር፥ በትጋት አበርክቶት ስለ ነበረው ዘመን ተሻጋሪ አገልግሎት ከቤተሰቡ ጋር አብረነው እግዚአብሔርን እንድናመሰግን እድል ተሰጠን። ተባረክን ደስ አለን። ከእርሱ ጋር ልትታሰቡ የሚገባችሁ ሁሉ በልባችን የከበራችሁ ናችሁ። ይህንን ስትመለከቱ የሚኖራችሁን ደስታ ስናስብ ስላገኘነው እድል አምላካችንን ጨምረን እናመሰግናለን። _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ኤስ_ዩ @suethiopia_57