ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

SU|ኤስዩ

SU|ኤስዩ

الذهاب إلى القناة على Telegram

የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር [Scripture Union Ethiopia] #ኤስ.ዩ፣ ከ1957 ጀምሮ የኃይስኩል ተማሪዎችን እያገለገለ ይገኛል። #ራዕያችን "ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት" ነው በዚህ ቻናል:— በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ነክ መረጃዎች ይተላለፍበታል።

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
672
المشتركون
+324 ساعات
+57 أيام
+330 أيام
أرشيف المشاركات
#የኤስዩ_አሶሼትስ_የምክክር_ፕሮግራም ----- ----- ------ ምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ፣ የኃይስኩል ፌሎሽፕ አገልግሎትን በልዩ ልዩ መንገድ የሚደግፉ ጠንካራ ወጣቶች ያሉባት ከተማ ነች። ቅዳሜና እሁድ በነበረን የስልጠና እና ጉብኝት ወቅት የተመለከትንውም ይኸንንው ነው። በኃይስኩል አገልግሎት እንዲሁም በኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ውስጥም ንቁ ተሳትፎ የነበራቸው ወጣቶችን አግኝተናል። በአጥቢያቸው እንዲሁም በልዩ ልዩ የአገልግሎት አደረጃጀቶች ውስጥ ተሰጥተው ያገለግላሉ። ከእነዚህ ወጣቶች ጋር በኤስዩ አገልግሎት ውስጥ አሶሼትስ እና በጎ ፈቃደኛ አገልጋይ ስለመሆን ግንዛቤ አስጨብጠናል። በጥያቄና መልስ የዳበረ ውይይትም አድርገናል። በምዕራብ ክልል ስላለው የመካከለኛ እና 2ኛ ደረጃ ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት ያለንን ሸክም አጋርተናቸዋል። ከአገልግሎቱ ጋር አብረው ለመስራት ያላቸውን የልብ ፈቃደኝነት ተመልክተናል። እግዚአብሔር ለምዕራብ ኤስዩ ክልል ብሎም ለሀገር አቀፉ የኤስዩ አገልግሎት ሸክም ያላቸውን ወንዶችና ሴቶችን እንደሚያስነሳ ተስፋ ሰንቀናል። እግዚአብሔር ፀጋቸውን፣ ልዩ ልዩ ሞያቸውን፣ ችሎታቸውን፣ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውን በመስጠት በክልላዊ ቢሮው እያገለገሉ ያሉትን የኤስዩ አሶሼትስ እና በጎ ፈቃደኞችን አብዝቶ ይባርክ! ======== Sagantaa SU Associates ——————————————— East Wellega—Nekemte magaalaa dargaggoota of kennanii fi humna qaban kanneen tajaajila High School Fellowship karaa adda addaatiin dammaqinaan deeggaraniin badhaatedha. Kun yeroo leenjii fi daawwannaa dhuma torbee keenyaa irratti ifatti mul’ateera. Dargaggootaa fi shamarran bara mana barumsaa sadarkaa lammaffaa, kolleejjii fi yunivarsiitii isaaniitti tajaajila irratti dammaqinaan hirmaatan waliin wal barre. Hedduun isaanii amma waldoota naannoo isaanii fi tajaajila adda addaa keessatti amanamummaadhaan tajaajilu. Sagantaa kana irratti gahee fi waamicha hiriyoota fi tajaajiltoota tola ooltotaa tajaajila SU keessatti qaban irratti hubannoo ifa ta’e qoodne. Kana booda gaaffii fi deebii kan nama hawwatuu fi wal-qunnamsiisu gaggeeffameera. Akkasumas tajaajila waldaa barattoota kiristaanaa mana barumsaa giddu galeessaa fi lammaffaa Naannoo Dhihaatti ba’aa keenya qooddanne, akkasumas fedhii fi qophii hirmaattonni tajaajila waliin tumsuuf qaban jajjabeeffanne. Waaqayyo dhiirotaa fi dubartoota tajaajila SUf ba’aa gadi fagoo baatanii deeman, Naannoo Lixaa fi sadarkaa biyyaatti akka kaasu abdii fi kadhannaa qabna. Waaqayyo hiriyoota SU fi tola ooltota waajjira naannoo keessatti amanamummaadhaan tajaajilan-kennaa isaanii, dandeettii isaanii, deeggarsa maallaqaa isaanii fi yeroo gatii guddaa qabu tajaajilaaf tarkaanfachiisuuf dhiyeessan baay’ee haa eebbisu. ======== SU Associates Program ——————————————— East Wellega—Nekemte is a town rich with committed and energetic young people who actively support the High School Fellowship ministry in various ways. This was clearly evident during our weekend training and visit. We met young men and women who were actively involved in ministry during their high school, college, and university years. Many of them now serve faithfully in their local churches and various ministries. During the program, we shared a clear understanding of the role and calling of associates and volunteer ministers within the SU ministry. This was followed by an engaging and interactive question-and-answer session. We also shared our burden for the middle and secondary school Christian student fellowship ministry in the Western Region, and we were encouraged by the participants’ willingness and readiness to partner with the ministry. We are hopeful and prayerful that God will raise up men and women who carry a deep burden for SU ministry, both in the Western Region and at the national level. May God richly bless the SU associates and volunteers who serve faithfully in the regional office—offering their gifts, talents, financial support, and valuable time for the advancement of the ministry. --------------------- #ኤስ_ዩ #ምዕራብ_ክልል #ነቀምቴ #ኢየሱስን_እየተከተሉ #በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ #ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎች_ማየት

photo content
+5

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

Bahaa wallaggaa— Leenjii fi Daawwannaa Hooggantoota Feelooshippii Mana Barumsaa Sadarkaa Lammaffaa Nekemte ----- ----- ----- ------- Sagantaan Leenjii fi Daawwannaa geggesitotaa Feelooshippii Mana Barumsaa Sadarkaa Lammaffaa Waajjira  nannoo lixaa SU magaalaa Nekemte, godina Wellega Bahaa keessatti gaggeeffame, Wiixata, 5/4/2018  milkaa’inaan xumurame. Sagantaa leenjii guyyoota lamaaf turu kana irratti hoggantoonni waldaa mana barumsaa sadarkaa lammaffaa torba (7) irraa hirmaatan. Sagantaan kun ergaa humna guddaa qabu kan Dubbii Waaqayyoo irraa Pastor Oliqaa  qoodameen kan baname yoo ta’u, 1 Ximotewos 4 irratti hundaa’uun barattoonni carraa Waaqayyo isaaniif qopheessetti ogummaadhaan akka itti fayyadaman jajjabeessuun ergaa isaa kadhannaa eebbaatiin xumureera. Leenjichi seensa macaafa Seera Uumamaatiin kan jalqabe yoo ta’u, boqonnaa 1 irratti kan xiyyeeffate yoo ta’u, barattoonni haala naannoo isaaniitti utuu hin ta’in amantii isaanii Waaqayyo irratti akka kaa’anii fi kallattii jireenyaa hundumaa keessatti qajeelfama isaa akka amanan jajjabeeffamaniiru. Hirmaattonni mul’ata, ergama, gatiiwwan, xiyyeeffannoo tajaajilaa, fi adeemsa hojii tokkummaa kanaa irratti barsiisa bal’aa argataniiru.  Hoggantoonni fellowship seenaa fellowship mana barumsaa isaaniis kan qooddatan yoo ta’u, seenaa ministeera fellowship barattootaa idil-addunyaa fi biyyaalessaa lamaan isaanii wajjin wal barsiisaniiru. Sagantaa kana keessatti kaayyoo ijoo tajaajila waldaa mana barumsaa sadarkaa lammaffaa, caasaa gurmaa’insaa isaa fi qabiyyee sagantichaa irratti mariin gaggeeffameera.  Qaawwa qabatamaa fi hojii furuufis leenjiin kennameera.  Sagantaa torbanitti idilee ta’een alatti, hirmaattonni tajaajila waldaa qindeessuu irratti leenjii seensa karaa moodeelota garee maatii argataniiru. Leenjiin dabalataa gahumsa barnootaa fi damee barnootaa filachuu irratti kennamee, barattootaaf ilaalcha macaafa qulqulluu ifa ta’e barnootaa fi barumsa irratti kenneera. Kadhannaan, waldaa fi nyaanni waliin nyaatan qaama sagantichaa kan hin taane yoo ta’u, tokkummaa hirmaattoota gidduu jiru cimseera. Leenjii guyyoota lamaaf kenname kanarratti barattoonni bu'aa guddaa akka argatan ragaa ba'aniiru.  Leenjiin kun sagantaalee walta’iinsa barattootaa bu’a qabeessa ta’e karoorsuu fi hojiirra oolchuuf akka isaan gargaaru ibsaniiru. Baayyeen isaanii moodeelli walta’iinsa garee maatii keessumaa gargaaraa akka ta’e kan hubatan yoo ta’u, manneen barnootaa isaanii keessatti hojiirra oolchuuf waadaa galan qoodaniiru.  Leenjiin gahumsa barnootaa irratti kennamu guddina barnootaa fi hafuuraa isaaniif faayidaa olaanaa akka qabus hirmaattonni ragaa ba’aniiru. Barattoonni leenjii fi gorsa argataniif galateeffannaa fi gammachuu isaanii ibsaniiru, qajeelfamaa fi qophii Waaqayyoo saganticha guutuu keessatti nuuf kenneef beekamtii kennaniiru.   Dirree tajaajilaa balʼaa naannoo sana jirus beekamtii kennaniiru.  Tajaajiltoota yeroo guutuu fi gargaaraa tajaajiltoota Gamtaa Caaffata Qulqullaa’oo Itoophiyaa waajjira naannoo isaanii keessatti amanamummaadhaan tajaajilan, akkasumas waldoota naannoo isaanii irratti eebba Waaqayyoo kadhachuudhaan xumuran.   ======= @suethio

#ምስራቅ_ወለጋ_ነቀምቴ #የኃይስኩል_ፌሎሽፕ_መሪዎች_ስልጠና_እና_ጉብኝት ---- ----- ----- ------ በምዕራብ የኤስዩ ክልላዊ ቢሮ፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ የነበረን የስልጠና እና የጉብኝት መርሐ ግብር ትላንት እሁድ 5/4/ 2018 ዓም ፍፃሜውን አግኝቷል። ለሁለት ቀን በነበረው ፕሮግራም ከሰባት (7) የኃይስኩል ትምህርት ቤት ፌሎሽፕ የመጡ መሪዎች ተሣታፊ ሆነውበታል። በፕሮግራሙ መክፈቻ መጋቢ ዋሊቃ የእግዚአብሔርን ቃል ከ 1ኛ ጢሞ 4 ላይ ድንቅ መልዕክት አካፍሏል። ተማሪዎች እግዚአብሔር ያዘጋጀላቸውን እድል እንዲጠቀሙበት አበረታቷል። በፀሎት ባርኳቸዋል። መርሐ ግብሩ፣ የዘፍጥረት መጽሐፍ ትውውቅ በማድረግ ከምዕራፍ 1 ድንቅ መልዕክት ቀርቧል። እምነታቸውን ዙሪያቸው ባለው ነገር ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ እንዲያደርጉ የቃሉን ምክር ተቀብለዋል። የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረት የአገልግሎት ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሤት፣ የትኩረት አቅጣጫ እንዲሁም አሰራርን በተመለከተ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል። የፌሎሽፕ መሪዎች የራሳቸውን የትምህርት ቤት ሕብረት ታሪክ ለማካፈል እድል አግኝተዋል። ስለ ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ የተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ታሪክም እንዲያውቁ ተደርጓል። በቆይታችን የኃይስኩል ፌሎሽፕ አገልግሎት መሰረታዊ ዐላማ፣ የአደረጃጀት ቅርጽ የፕሮግራም ይዘት የተመለከቱ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። የልምምድና የአሰራር ችግሮች በታዩባቸው ጉዳዮች ክፍተቱን የሚሞላ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። መደበኛ ሣምንታዊ የጋራ ፕሮግራም በትልቅ ቁጥር ከመሰባሰብ በተጨማሪ የፌሎሽፕ አገልግሎትን በቤተሰብ ቡድን (Family Group) በማደራጀት እንዴት መምራት እንደሚችሉ ቀዳሚ ትምህርት ተሰጥቷቸዋል። ተሳታፊ የፌሎሽፕ መሪዎች፣ የትምህርት ልኅቀት እና የትምህርት መስክ ምርጫ በሚል ርዕስ ተጨማሪ ስልጠና እንድወስዱ ተደርጓል። ስልጠናው፣ ተማሪዎች የትምህርትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምልከታ እንዲረዱ የሚያስችል ነው። አብሮ መፀለይ፣ ሕብረት ማድረግ እና ማዕድ አብሮ መቁረስ የፕሮግራሙ አካል ነበር። በነበረው የሁለት ቀን ቆይታ ተማሪዎች ብዙ እንደተጠቀሙ መስክረዋል። ስልጠናው፣ የተማሪ ሕብረት አገልግሎት ትክክለኛ ቅርጽ እና ይዘት ለማስያዝ እንደሚጠቅማቸው ተናግረዋል። ጨምረው፣ የቤተሰብ ቡድን አገልግሎት ስልት ጠቃሚ መሆኑን ጠቅሰው እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል። ስለ ትምህርት ልኅቀት የተሰጠው ስልጠና በእጅጉ እንደሚጠቅማቸው መስክረዋል። በነበረን የስልጠና እና የጉበኝት ፕሮግራም ተማሪዎችም።እኛም። ደስተኞች ነን። እግዚአብሔር በብዙ ረድቶናል። በአካባቢው ሰፊ የአገልግሎት እርሻ እንዳለም ተገንዝበናል። በአካባቢያዎ ቢሮ በትጋት እያገለገሉ ያሉትን የኤስዩ ሙሉ ጊዜ እና አሶሼት አገልጋዮች እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸው። አጥቢያ ቤተክርስቲያናትንም እግዚአብሔር ጨምሮ ይባርካቸው። ======= #ኤስ_ዩ #ምዕራብ_ክልል #ነቀምቴ #ኢየሱስን_እየተከተሉ #በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ #ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎች_ማየት @suethio

photo content
+3

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+4

#ጅግጅጋ_እና_ባቢሌ ---- ----- ------ በምስራቅ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ፣ ጅግጅጋ እና ባቢሌ ከተሞች፣ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ጉብኝት ተካሂዷል። #ጅግጅጋ በጅግጅጋ የጉብኝቱ አካል የሆኑት ስድስት(6) የተማሪ ህብረቶች ናቸው። በተጨማሪም ከ አጠቃላይ የከተማ የተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት መሪዎች ( GF leaders) ጋር ገንቢ የሆነ አገልግሎት ነክ ውይይት እና ምክክር ለማድረግ ተችሏል። በጅግጅጋ ሰባት የተደራጁ የተማሪዎች ሕብረት አሉ። በአንፃሩ ማደራጀት የሚፈልግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ትምህርት ቤቶች አሉ። ከመሪዎች እና በከተማው ተማሪዎችን ከሚያገለግሉ አሶሼት ጋር በነበረን ውጤታማ የምክክር ጊዜ፣ የተደራጁትን ሕብረቶች ማጠናከር እንዲሁም ተጨማሪ ሕብረቶችን ስለማደራጀት ምክክር አድርገናል። በጥር ወር አጋማሽ ላይ አካበቢያዊ የመሪዎች ጉባኤ (Area Leadership Summit) ማዘጋጀት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተነጋግረናል። #ባቢሌ በባቢሌ ከተማ ቁጥራቸው ስልሳ (60) የሚደርስ የተነቃቁ ክርስቲያን ተማሪዎች አሉ። ነገር ግን እስከ አሁን መደበኛ የሆነ ሣምንታዊ ፕሮግራም ማድረግ አልጀመሩም። ከግቢ ውጪ ሕብረት ማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታ የመፍጠር ሥራ ከአብያተክርስቲያናት መሪዎች ጋር መስራት ይጠበቅብናል። ለተማሪዎች አስፈላጊ የሆኑ ስልጠናዎችን ስለ መስጠት እንዲሁም የተማሪ ሕብረት አገልግሎትን በተመለከተ ለቤተክርስቲያን መሪዎቸ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረግ ስለ ማዘጋጀት ከአብያተክርስቲያናት መሪ እና ከተማሪ መሪዎች ጋር ምክክር ተደርጓል። በባቢሌ እና ጅግጅጋ፣ ተማሪዎችን በትጋት እያገለገሉ የሚገኙ አሶሼትስን እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸው! ወንድማችን ግዛው በክልላዊ ቢሮው የጅግጅጋውን እና ባቢሌን ጨምሮ በሌሎቹም ከተሞች ላይ የተማሪ አገልግሎትን ጎን ለጎን በትጋት እያከናወነ ነው። እግዚአብሔር እሱንም አብዝቶ ይባርከው። ፀጋንም ይጨምርለት። በፀሎት አብራችሁን ሁኑ፦ 👉🏿 በባቢሌ እና ጅግጅጋ የተጀመረው መልካም የተማሪዎች እንቅስቃሴ እንዲቀጥል 👉🏿እግዚአብሔር በባቢሌ የሚገኙ አብያተክርስቲያናትን ለተልዕኮ እንዲያበረታ 👉🏿 በባቢሌ እና ጅግጅጋ እያገለገሉ ያሉትን አሶሼትስን እንዲባርክ ======== #ኤስ_ዩ #ምስራቅ_ክልል #ጅግጅጋ #ባቢሌ #ኢየሱስን_እየተከተሉ #በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ #ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎች_ማየት

photo content
+4

#የኃይስኩል_ተማሪዎች_ሕብረት #በወራኢሉ_እና_ጃማ ----- ---- ----- ------ #በወረኢሉ እና #ጃማ ከተማ የክርስቲያን_ተማሪዎች_ህብረት ጉብኝት፣ ምክክር እና የስልጠና መርሐ ግብር ተካሂዷል። በሰሜን ምስራቅ ኤስዩ ክልል፣ #ደቡብ_ወሎ_አካባቢያዊ_ቢሮ፣ ዓርብ፣ ህዳር 26/2018 ዓ.ም #በወረኢሉ ኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት መደበኛ ፕሮግራም ላይ የእግዚአብሔር ቃል ጥናት ተደርጓል። የጸሎትም መርሐ ግብርም ተካሂዷል። በተማሪ ሕብረት አገልግሎት ዙሪያም ከመሪዎች ጋር ምክክር ተካሂዷል። በማለዳ መርሐ ግብር፣ የእግዚአብሔር ልብ ለኃይስኩል (God's Vision for High school) በሚል ርዕስ ለተማሪዎች መልዕክት ቀርቧል። በቀረበው መልዕክት ተማሪዎች የእግዚአብሔር ቅንዓት ተካፋዮች እንዲሆኑ ፣ የተማሪ ሕብረት ዐላማን እንዲረዱ ፣ እንዲሁም ስለሚማሩበት ትምህርት ቤት ማሕበረሰብ እንዲያስቡ ተሞግተዋል። ወረኢሉ ፣ ከደሴ የሦስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ (3:30) የመኪና ጉዞ ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። #ጃማ_ከተማ ----- ---- ---- ቅዳሜ፣ ህዳር 27 /2018 ዓ.ም ፥ ከጃማ ኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት አባላት ጋር አገልግሎትን በተመለከተ ሰፊ ምክክር ተደርጓል። እንዲሁም ከሕብረቱ መሪዎች ጋር የጋራ የእግዚአብሔር ቃል ጥናት እና የፀሎት መርሐ ግብር ተካሂዷል። ጃማ ከተማ ከወረኢሉ የአንድ ሰዓት (1:00) መንገድ ሲርቅ፣ የክልላዊ ቢሮ መቀመጫ ከሆነችው ደሴ ከተማ የአራት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ (4:30) የመኪና ጉዞ ርቀት ላይ ይገኛል። ሁለቱም አካባቢዎች በሰላም እጦት ፣ በጦርነት ስጋት ውስጥ የሚገኙ ናቸው። አልፎ አልፎ ትምህርት ቤቶች የመዘጋት እጣፋንታ ይገጥማቸዋል። በሁለቱም ከተሞች የሚገኙ ክርስቲያን ተማሪዎች በቋሚነት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግላቸው ተባባሪ የኤስዩ አገልጋይ (Associate Staff) ይፈልጋሉ። አካባቢያዊ ተግዳሮት በበዛበት እንዲሁም ብዙ የቅርብ ክትትል በሌለበት ሁኔታ መሪዎች ሕብረቱን ለማስቀጠል እና ለማገልገል የሚያሳዩት ትጋት አስደናቂ ነው። የዕረፍት ሰዓት መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መቀጠሉም ደስ ያሰኛል፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያዳበሩት መልካም ግንኙነትም የሚመሰገን ነው። ጉብኝቱ፣ ተማሪዎች የሚጎበኛቸው እና የሚያበረታታቸው ሰው በሚፈልጉበት ወሳኝ ወቅት በመካሄዱ ደስ ተሰኝተዋል። ለአገልግሎት መነሣሣት ፈጥሮላቸዋል። #ፀሎት እግዚአብሔር አካባቢያችንን ሰላም እንዲያደርግ፣ አዳዲስ የተመሰረቱ ህብረቶች እንዲጸኑና ፍሬያማ እንዲሆኑ ጸልዩልን የሚል ጥያቄም አቅርበዋል። ይኸን አገልግሎት በትጋት እያገለገሉ ያሉትን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካቸው! ፀጋን ያብዛላቸው! ------ ------ ------ ------- #ኤስ_ዩ #ሰሜን_ምስራቅ_ክልል #ደቡብ_ወሎ_አካባቢያዊ_ቢሮ #ወረኢሉ_ክርስቲያን_ተማሪዎች_ህብረት #ጃማ_ክርስቲያን_ተማሪዎች_ህብረት #ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ_ተማሪዎች_ማየት

To register Use the link below https://forms.gle/gwQHxtjKe12YKrCv9
To register Use the link below https://forms.gle/gwQHxtjKe12YKrCv9

#በፀሎት_አብረናቸው_እንሁን "… የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።" ያዕቆብ 5:16 ----- ----- ----- ከማርበርግ ቫይረስ ጋር ተያይዞ አሳሳቢ የሆነውን ወቅታዊ የጤ
#በፀሎት_አብረናቸው_እንሁን "… የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።" ያዕቆብ 5:16                ----- ----- ----- ከማርበርግ ቫይረስ ጋር ተያይዞ አሳሳቢ የሆነውን ወቅታዊ የጤና ሁኔታ ሁላችንም እንገነዘባለን። ችግሩ ቀድሞ በተከሰተበት በጅንካ እና አካባቢው  በወቅታዊው የጤና ስጋት ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ፌሎሽፕ  መደበኛ ሕብረት ማድረግ አቁመዋል። ችግሩን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትራንስፖርትን ጨምሮ የማኅበራዊ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል። የቁጥጥር ሥራው ውጤት እያስገኘም እንደሆነ እየሰማን ነው። በእንዲህ ዐይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለፉ ለሚገኙት ተማሪዎችና አጠቃላይ ማሕበረሰብ በፀሎት አብረናቸው ልንቆም ይገባል። 🙏 እግዚአብሔር ይኸን ገዳይ በሽታ ከምድሪቱ እንዲጠርገው፣ 🙏 በበሽታ ስጋት ውስጥ ላሉት የእግዚአብሔር ጥበቃ እንዲበዛላቸው፣ 🙏 ወገኖቻቸውን በዚሁ በሽታ ምክንያት በሞት ያጡትን የእግዚአብሔር ማጽናናት እንዲበዛላቸው፣ 🙏 ለተማሪዎች ተስፋ እንዳይቆርጡ ፤ በእምነት እንዲበረቱ፣ እንፀልይላቸው🙏 @suethio

ጉብኝት እና ስልጠና በሰሜን ምዕራብ ኤስ.ዩ ክልል ------- ------ ------- ባሳለፍነው ቅዳሜ ህዳር 20፣ ሰሜን ምዕራብ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልላዊ ቢሮ ፣ ደብረማርቆስ
+6
ጉብኝት እና ስልጠና በሰሜን ምዕራብ ኤስ.ዩ ክልል ------- ------ ------- ባሳለፍነው ቅዳሜ ህዳር 20፣ ሰሜን ምዕራብ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልላዊ ቢሮ ፣ ደብረማርቆስ ከተማ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶችን የመጎብኘት እና የማስታጠቅ ተግባራት ተከናውኗል። በተጨማሪም በደብረማርቆስ ከተማ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) አገልግሎትን በተመለከተ ራዕይ የማካፈል ፕሮግራም ተካሂዷል። በዚህ የግማሽ ቀን ፕሮግራም የአጥቢያ ቤ/ክ መሪዎች ተካፋይ ሆነዋል። ዝግጅቱ፣ ተሣታፊ የነበሩ መሪዎች፣ የኤስ.ዩን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሤት፣ የትኩረት አቅጣጫ፣ ስልትና አሰራር በተገቢው ሁኔታ ለመገንዘብ አስችሏቸዋል። ቃለ—እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ)፣ ትኩረቱን በመለስተኛ እና 2ኛ ደረጃ ክርስቲያን ተማሪዎች ላይ በማድረግ፣ ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ መሳካት፣ ከቤተክርስቲያን ጋር ለቤተክርስቲያን፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራ አገልግሎት ነው። እግዚአብሔር አካባቢውን ሰላም እንዲያደርግ፣ አዳዲስ ህብረቶች እንዲመሰረቱ፣ እንዲጸኑና ፍሬያማ እንዲሆኑ ጸልዩልን። ------- ----- ----- #ኤስ_ዩ #ሰሜን_ምዕራብ_ክልል #ደብረማርቆስ #ባህርዳር #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት @suethio

በደሴ እና አካባቢዉ የተማሪ ህብረት መሪዎች ስልጠና (AHLS) ----- ----- ------- ------- በሰሜን ምስራቅ ኤስዩ ክልል፣ በደቡብ ወሎ አካባቢያዊ ቢሮ፣ #ከሃይቅ፣ #ከኩታበርና #ከደሴ
+7
በደሴ እና አካባቢዉ የተማሪ ህብረት መሪዎች ስልጠና (AHLS) ----- ----- ------- ------- በሰሜን ምስራቅ ኤስዩ ክልል፣ በደቡብ ወሎ አካባቢያዊ ቢሮ፣ #ከሃይቅ፣ #ከኩታበርና #ከደሴ ለተውጣጡ የሃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት መሪዎች ስልጠና ተሰጥቷል። ስልጠናው ቅዳሜ፣ ህዳር 20 የተካሄደ ሲሆን፤ አገልጋይ መሪነት (Servant Leadership)፣ ተልዕኮ መር የተማሪ ህብረት ( Missional School Fellowship) ፣ የትምህርት ልህቀትና የትምህረት ምርጫ (Acedamic Excellence and Choice) እና የቡድን ስራ (Team Work) ርዕሶች ላይ የተሰጠ ሲሆን፤ በተጨማሪም የጸሎት፣ የአምልኮና የህብረት ግዜ ነበረ። ክብር ለጌታ ይሁን🤲🤲 እግዚአብሔር አካባቢውን ሰላም እንዲያደርግ፣ አዳዲስ የተመሰረቱ ህብረቶች እንዲጸኑና ፍሬያማ እንዲሆኑ ጸልዩልን። ----------------------- #ኤስ_ዩ #ሰሜን_ምስራቅ_ክልል #ደሴ_ደቡብ_ወሎ_አካባቢያዊ_ቢሮ #ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ_ተማሪዎች_ማየት