uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

SU|ኤስዩ

SU|ኤስዩ

Відкрити в Telegram

የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር [Scripture Union Ethiopia] #ኤስ.ዩ፣ ከ1957 ጀምሮ የኃይስኩል ተማሪዎችን እያገለገለ ይገኛል። #ራዕያችን "ኢየሱስን እየተከተሉ፤ በቃሉ እየታነፁ፤ ማኅበረሰባቸውን የሚያገለግሉ ተማሪዎችን ማየት" ነው በዚህ ቻናል:— በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት አገልግሎት ነክ መረጃዎች ይተላለፍበታል።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
672
Підписники
+324 години
+57 днів
+330 днів
Архів дописів
#የተማሪ_ሕብረት_ማደራጀት ----- ---- ----- ------ ከቃለ—እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ) ተልዕኮ መካከል ቀዳሚው ተማሪዎች ለፀሎትና የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት የሚሰባሰቡበ
+3
#የተማሪ_ሕብረት_ማደራጀት ----- ---- ----- ------ ከቃለ—እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስ.ዩ) ተልዕኮ መካከል ቀዳሚው ተማሪዎች ለፀሎትና የእግዚአብሔርን ቃል ለማጥናት የሚሰባሰቡበትን #ሕብረት_ማደራጀት ነው። ትላንት ዓርብ ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም የሆነውም ይኸው ነው። በአዲስ አበባ ኤስ.ዩ፣ ምስራቅ ዞን የ MALD ትምህርት ቤት #የተማሪዎች_ፌሎሽፕ ተመስርቷል። #ወላጆች፣ የተማሪ ሕብረት አስፈላጊነት ላይ መክረው፣ ተማሪዎች የሚሰባሰቡበትን ቦታ ፈልገው አግኝተው፣ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው፣ ስለ ሕብረት አስፈላጊነት ከእግዚአብሔር ቃል እንዲሁም ካሣለፉት ግለ—ሕይወት ምስክርነት አቅርበው መሆኑ ነገሩን ለየት ያደርገዋል። በምስረታው ቀን እግዚአብሔር ለኃይስኩል ያለው ልብ ምን እንደሆነ መልዕክት አቅርበናል። የኤስ.ዩን የአገልግሎት ኃላፊነት ለተማሪዎችና ለወላጆች አስረድተናል። ከተማሪዎቹ ጋር ደስ የሚል የሕብረት ጊዜም አሳልፈናል። በዕለቱ ፣ ወንድም እሸቱ (የአዲስአበባና ዙሪያው ክልላዊ ቢሮ አስተባባሪ) እና እህት ምዕራፍ በዞኑ የኤስዩ አሶሼት ተገኝተው ከወላጆችና ከልጆች ጋር ተዋውቀዋል። ከዚህ በኋላ ሣምንታዊ ፕሮግራም ይቀጥላል። ተማሪዎቹን እና እነሱን የሚያገለግሉትን አሶሼቶች ፀሎት አስቧቸው። ወላጆች እና ተማሪዎች ሕብረቱ በመመስረቱ በጣም ደስ እንደተሰኙ ነገረውናል። እግዚአብሔር ተማሪዎች ለሕይወትና ለተልዕኮ የሚታጠቁበትን እንዲህ ያሉ የተማሪ ሕብረቶችን ያብዛልን። ፍላጎታችን በየኃይስኩሉ የተማሪ ሕብረቶች እንዲመሰረቱ ነው! ( Every High School— A fellowship..!) #ኤስ_ዩ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

ጉብኝት እና ስልጠና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልል ------- ------ ------- ባሳለፍነው ቅዳሜና ዕሁድ፣ ህዳር 13 እና 14/2018 ዓ.ም ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የቃለ እግዚአብሔር አ
+9
ጉብኝት እና ስልጠና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልል ------- ------ ------- ባሳለፍነው ቅዳሜና ዕሁድ፣ ህዳር 13 እና 14/2018 ዓ.ም ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልላዊ ቢሮ ፣ ሆሣዕና እና ዱራሜ ከተማ የሚገኙ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶችን የመጎብኘት እና የማስታጠቅ ተግባራት ተከናውኗል። በሆሣዕና የኃይስኩል ፌሎሽፕ መሪዎች ጋር የዘፍጥረት መጽሐፍ በጋራ ተጠንቷል። በተጨማሪም፣ የፌሎሽፕ መሪዎች፣ አገልጋይ—መሪነት እና ወዳጃዊ ወንጌልን የማድረስ ስልት ( PCS) ሴሚናር ተካፍለዋል። ከተማሪ ሕብረት መሪዎች ባሻገር፣ ለአጠቃላይ የተማሪ ሕብረት አባላት በትምህርት ልኅቀት ( Academic Excellence) ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ተሰጥቷል። ይህ ስልጠና ተማሪዎች የትምህርትን ክርስቲያናዊ ንጽረተ—ዓለም መገንዘብ እንዲችሉ ያግዛቸዋል። በምላሹ፣ የትምህርት ተሳትፎና ውጤታቸው ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል። ከሆሣዕና በተጨማሪ በዱራሜ ከተማ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) አገልግሎትን በተመለከተ ራዕይ የማካፈል ፕሮግራም ተካሂዷል። በዚህ ፕሮግራም የኃይስኩል ተማሪዎች ፌሎሽፕ መሪዎች እንዲሁም የቤ/ክ መሪዎች ተካፋይ ሆነዋል። ቃለ—እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ)፣ ትኩረቱን በመለስተኛ እና 2ኛ ደረጃ ክርስቲያን ተማሪዎች ላይ በማድረግ፣ ለቤተክርስቲያን ተልዕኮ መሳካት፣ ከቤተክርስቲያን ጋር ለቤተክርስቲያን፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚሰራ አገልግሎት ነው። ------- ----- ----- #ኤስ_ዩ #ማዕከላዊ_ኢትዮጵያ_ክልል #ሆሣዕና #ዱራሜ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

photo content
+3

photo content
+9

photo content
+9

photo content
+9

የተማሪ ሕብረት በአጋሮ ከተማ በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በአጋሮ ከተማ፣ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ተደራጅቷል፡፡ ሕብረቱ ከዚህ በፊት በተደራጀ መልኩ ሲካሄድ ቢቆይም ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ ቆይ
+9
የተማሪ ሕብረት በአጋሮ ከተማ በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በአጋሮ ከተማ፣ የኃይስኩል ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ተደራጅቷል፡፡ ሕብረቱ ከዚህ በፊት በተደራጀ መልኩ ሲካሄድ ቢቆይም ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ የምሥረታ ፕሮግራሙ በአጋሮ ምስጋና ቤተ ክርስቲያን የተካሄደ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ ተማሪዎች እና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ተገኝተዋል። የተማሪዎች ህብረት ፕሮግራም ሁልጊዜ ዓርብ፣ በምስጋና አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ይቀጥላል። በተማሪዎች ሕብረት አገልግሎትን በልዩ ልዩ መንገድ እየደገፉ ያሉትን አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካቸው ለማለት እንወዳለን፡፡ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ራዕይ፣ ተማሪዎች፣ “ “ኢየሱስን_እየተከተሉ_በእግዚአብሔር_ቃል_እየታነፁ_ማህበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ” ሆነው ማየት ነው፡፡ ከተልዕኮ መካከልም ቀዳሚው ተማሪዎች ለፀሎትና የእግዚአብሔርን ቃል በጋራ ለማጥናት የሚሰባሰቡበትን ፌሎሽፕ ማደራጀት ሲሆን፤ የተደራጁትን ለደቀመዝሙር ሕይወትና ለወንጌል ተልዕኮ ማስታጠቅ ይገኝበታል፡፡ በተጨማሪ ፣ የሕብረቱ መሪዎች አገልጋይ-መሪነትን እንዲለማመዱ፤ ከቤታቸውን ጀምሮ፤ቤተክርስቲያንን፤ትምህርት ቤታቸውን እንዲሁም ሰፊውን ማኅበረሰብ እንዲያገለግሉ ማዘጋጀት የሚሉት የተልዕኮ አካላችን ነው፡፡ __________ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ኤስ_ዩ

በሁምቦ ጠበላ የኤስዩ የተማሪ ህብርት ስልጠና ----- ----- ------- ------- በደቡብ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ ወላይታ ሶዶ አካባቢያዊ ቢሮ #ሁምቦ_ጠበላ ከተማ የኃይስኩል ተማሪዎች
+7
በሁምቦ ጠበላ የኤስዩ የተማሪ ህብርት ስልጠና ----- ----- ------- ------- በደቡብ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ ወላይታ ሶዶ አካባቢያዊ ቢሮ #ሁምቦ_ጠበላ ከተማ የኃይስኩል ተማሪዎች ስልጠና ተካሂዷል፡፡ በስልጠናው በከተማው የሚገኙ ክርስቲያን ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በዕለቱ የትምህርት ልህቀት (Academic Excellence) ላይ ያተኮረ ሴሚናር ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም የኤስ.ዩ የተማሪዎች አገልግሎትን በተመለከተ ቪዥን ዶክመንቱ በተብራራ መልኩ ቀርቧል፡፡ ----------------------- #ኤስ_ዩ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

በአምቦ አካባቢዉ ኤስዩ የተማሪ ህብረቶች ስልጠና ----- ----- ------- ------- በአዲስ አበባ እና ዙርያው ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ በአምቦ እና አካባቢው የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረቶች ስልጠ
+8
በአምቦ አካባቢዉ ኤስዩ የተማሪ ህብረቶች ስልጠና ----- ----- ------- ------- በአዲስ አበባ እና ዙርያው ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ በአምቦ እና አካባቢው የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረቶች ስልጠና ተካሂዷል፡፡ ህዳር 13 በተካሄደው ስልጠናው በከተማው እና ዙርያው ያሉ የተማሪዎች ብረቶች ተሳታፊ ሆነዋል። በዕለቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እና በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ ሊኖረን ስለሚገባ Conviction እና Motivation የተነሳ ሲሆን የInductive bible Study ስልትን ስልጠና ወስደዋል። በተጨማሪም የኤስ.ዩ የተማሪዎች አገልግሎትን በተመለከተ እንዲሆም በቀጣይ በአካባቢው ስለሚኖረው አገልግሎት እና አደረጃጀት ምክክር ----------------------- #ኤስ_ዩ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

የዕውቅና እና የምስጋና ጊዜ! _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ ወንድማችን ዶ/ር አለም ባዘዘው ለኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ያለውን አስተዋጽዎ በተመለከተ ሁሉም በየፈ
+9
የዕውቅና እና የምስጋና ጊዜ! _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ ወንድማችን ዶ/ር አለም ባዘዘው ለኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ያለውን አስተዋጽዎ በተመለከተ ሁሉም በየፈርጁ የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በ Scripture Union በሁለተኛ ደረጃ ክርስቲያን ተማሪዎች ኅብረት አገልግሎት ውስጥ የተሰማራን በመስካችን በሙሉ ልብ፥ በተቀበለው ጸጋ፥ በፍቅር፥ በትጋት አበርክቶት ስለ ነበረው ዘመን ተሻጋሪ አገልግሎት ከቤተሰቡ ጋር አብረነው እግዚአብሔርን እንድናመሰግን እድል ተሰጠን። ተባረክን ደስ አለን። ከእርሱ ጋር ልትታሰቡ የሚገባችሁ ሁሉ በልባችን የከበራችሁ ናችሁ። ይህንን ስትመለከቱ የሚኖራችሁን ደስታ ስናስብ ስላገኘነው እድል አምላካችንን ጨምረን እናመሰግናለን። _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ _ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ኤስ_ዩ @suethiopia_57

photo content
+3

photo content
+9

የትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ጥናት ----- -------- ----- ----- በቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) #የደቡብ_ምስራቅ ክልላዊ ቢሮ (ሐዋሳ) የተዘጋጀው የሁለት ቀን ዎርክሾፕ ተጠና
+7
የትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ጥናት ----- -------- ----- ----- በቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር (ኤስዩ) #የደቡብ_ምስራቅ ክልላዊ ቢሮ (ሐዋሳ) የተዘጋጀው የሁለት ቀን ዎርክሾፕ ተጠናቋል።            ህዳር 6 እና 7 በሐዋሳ በተካሄደው #የትንቢተ_ዮናስ_መጽሐፍ ዎርክሾፕ በሐዋሳና አካባቢው የሚገኙ የኤስ.ዩ አሶሼት ስታፎች ተሣታፊ ሆነዋል። የዮናስ መጽሐፍ ዎርክሾፕ፣ የተማሪ አገልጋዮች፣ ሕይወት ለዋጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ከማጥናት ባሻገር ታማኝ የቃሉ አገልጋዮች የመሆን ክህሎታቸውን ያሣድጋል። በቃሉ ላይ የተመሰረተ በራስ መተማመንናቸው እንዲጨምርም ያደርጋል። ሰልጣኞቹ እንደመሰከሩት፣ የትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ዎርክሾፕ የእግዚአብሔር የተልዕኮ ልብ የተገለጠበት ሆኖ አግኝተውታል። ከጥናቱ በኋላ፣ ስለ መጽሐፍ አንኳር መልዕክት የነበራቸው የቀደመ አስተሳሰብ በእጅጉ እንደተለወጠም ተናግረዋል። በዎርክሾፑ ተሳታፊ የነበሩ አሶሼትስ፣ ለተማሪ ሕብረቶች እና ለአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው በረከት እንደሚሆኑ እምነታችን ነው። የዎርድ ፓርትነርስ ስልጠና፣ ሥነ አፈታት፤ሥነ አሰባበክና ገላጭ ስብከት አዘገጃጀትን አጣምሮ የያዘ ጠቃሚ ስልጠና ነው። ----------------------- #ኤስ_ዩ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ

photo content
+9

በዶዶላና አካባቢዉ የተማሪ ህብረት መሪዎች ስልጠና (ALS) ----- ----- ------- ------- በደቡብ ምስራቅ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ በዶዶላ እና አካባቢው የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረት የመሪዎ
+9
በዶዶላና አካባቢዉ የተማሪ ህብረት መሪዎች ስልጠና (ALS) ----- ----- ------- ------- በደቡብ ምስራቅ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ በዶዶላ እና አካባቢው የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረት የመሪዎች ስልጠና ተካሂዷል፡፡ ጥቅምት 29 እና 30 በተካሄደው በዚህ የመሪዎች ስልጠና ከአራት ከተሞች ፡- ዶዶላ፣ወርቃ፣አዳባ እና አሳሳ የተወጣጡ የተማሪ ህብረት መሪዎች ተሣታፊ ሆነዋል፡፡ በዕለቱ ከ#ዘፍጥረት መጽሐፍ መልዕክት ቀርቧል፡፡ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ ሕብረት ስለማድረግ ሴሚናር ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም የኤስ.ዩ የተማሪዎች አገልግሎትን በተመለከተ ቪዥን ዶክመንቱ በተብራራ መልኩ ቀርቧል፡፡ ከተማሪ ሕብረት መሪዎች ባሻገር፣ ከዶዶላ #አብያተክርስቲያናት_መሪዎች ጋር የምክክርና ራዕይ የማጋራት መርሐ ግብርም ተካሂዷል። ----------------------- #ኤስ_ዩ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

የአርባምንጭ እና አካባቢዉ ኤስዩ የተማሪ ህብረት መሪዎች ስልጠና ----- ----- ------- ------- በደቡብ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ አርባምንጭ እና አካባቢው የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረ
+9
የአርባምንጭ እና አካባቢዉ ኤስዩ የተማሪ ህብረት መሪዎች ስልጠና ----- ----- ------- ------- በደቡብ ኢትዮጵያ ኤስ.ዩ ክልላዊ ቢሮ አርባምንጭ እና አካባቢው የኃይስኩል ተማሪዎች ሕብረት የመሪዎች ስልጠና ተካሂዷል፡፡ ጥቅምት 29 በተካሄደው በዚህ የመሪዎች ስልጠና ሶስት ከተሞች ፡- ከአርባምንጭ፣ ከጨንቻና ሻራ የተወጣጡ የተማሪ ህብረት መሪዎች ተሣታፊ ሆነዋል፡፡ በዕለቱ የቤተሰብ ቡድን፣ አገልጋይ መሪነት የሚሉ ሴሚናሮች በተጨማሪም የኤስ.ዩ የተማሪዎች አገልግሎትን በተመለከተ ቪዥን ዶክመንቱ በተብራራ መልኩ ቀርቧል፡፡ በአገልግሎቱ ዙርያ ከተማሪ መሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል። ከአርባምንጭ እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአብያተክርስቲያናት_ህብረት_መሪዎች ጋር የምክክርና ራዕይ የማጋራት መርሐ ግብርም ተካሂዷል። ከ #ኢቫሱ አገልጋዮች ጋር በአጋርነት በሚሰሩ ጉዳዮች ዙርያ ገንቢ ውይይት ተደርጓል። በተጨማሪም ጥቅምት 30 ከኤስዩ አሶሼት አገልጋዮች ጋር የምክክር እና የስልጠና ጊዜ ነበረ። ----------------------- #ኤስ_ዩ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

photo content
+9

photo content
+9

ለቤተክርስቲያን የልጆች አገልጋዮች የተሰጠ ስልጠና ———————————————————- ኤስዩ ከቤተክርስቲያን ጋር በአጋርነት ሲያገለግል የቆየ አገልግሎት ነው። የዚህ አካል የሆነ ለቤተክርስቲያን የልጆች
+8
ለቤተክርስቲያን የልጆች አገልጋዮች የተሰጠ ስልጠና ———————————————————- ኤስዩ ከቤተክርስቲያን ጋር በአጋርነት ሲያገለግል የቆየ አገልግሎት ነው። የዚህ አካል የሆነ ለቤተክርስቲያን የልጆች አገልጋዮች አሻንጉሊትን በመጠቀም ልጆችን ማስተማር በሚል ርዕስ የተዘጋጅ ስልጠና ተሰጥቷል። በስልጠናው በአዲስ አበባ ከሚገGኡ የተውሰኑ አጥብያዎች የተወጣቱ የልጆች አገልጋዮች ተሳትፈውበታል። ስልጠናው እጅግ አሳታፊና በቤተክርስቲያን የልጆች አገልግሎት እድሜያቸውን ያማከሉ ስልቶችን ለመጠቀም የሚረዳ መሆኑን ተሳታፊዎች ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ የዕሴቶች ትምህርት በሚል በዩጋንዳ ኤስዩ ተዘጋጅቶ ለመካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሰጥ ትምህርት የአሰልጣኝ መምሪያ በአዲስ አበባ እና ዙርያው ለተወጣጡ የኤስዩ አገልጋዮች ተሰጠቷል። ስልጠናው ከ ኤስዩ ዩጋንዳ እንዲሁም ከካናዳ እና አሜሪካ በመጡ አስልጣኞች ነው የተሰጠው። ———————————————————- #ኤስ_ዩ #ኢየሱስን_የሚከተሉ #በእግዚአብሄር_ቃል_የታነፁ #ማሕበረሰባቸውን_የሚያገለግሉ #ተማሪዎችን_ማየት

photo content
+9