uk
Feedback
Mohammed Seid - Miftah

Mohammed Seid - Miftah

Відкрити в Telegram

​🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
2 485
Підписники
Немає даних24 години
+307 днів
+35330 днів
Архів дописів
What is Portfolio?
What is Portfolio?

ትምህርት --> ተግባር ---> ወደ ገቢ መቀየር

#Nice_gram #mobo_gram❌ የቴሌግራም አካውንታችሁ ሀክ ከመደረጉ በፊት ትክክለኛውን የቴሌግራም application ተጠቀሙ! የቴሌግራም ትክክለኛውና ኦፊሻል application link ኮሜንት
#Nice_gram #mobo_gram❌ የቴሌግራም አካውንታችሁ ሀክ ከመደረጉ በፊት ትክክለኛውን የቴሌግራም application ተጠቀሙ! የቴሌግራም ትክክለኛውና ኦፊሻል application link ኮሜንት ላይ አስቀምጥላችኋለሁ! ሊንኩን ተጭናችሁ ወደ #playstore በምትገቡበት ጊዜ Open ወይም update የሚል ከሆነ የምትጠቀሙት application ትክክለኛ ነው። Download የሚል ከሆነ ግን ትክክለኛውን መተግበሪያ በማውረድ እንደገና በትክክለኛው መተግበርያ አካውንት ክፍቱ! የማረጋገጫ መልእክት በኤስኤምኤስ ከደረሳችሁ እሰየው ማረጋገጫውን በማስገባት አካውንት መክፈታቸውን አጠናቀ በስምስ ካልደረሳችሁ ግን የማረጋገጫ መልክት የሚላክላቸው የቀድሞ application ላይ ስለሆነ ቀድማችሁ አታጥፉት ልክ የማረጋገጫ መልክት እንደደረሳችሁ እና በትክክል ወደዚህኛው መግባታቸሁን ስታረጋግጡ ያንኛውን አፕሊኬሽን አጥፉ! ከ official ውጪ ያሉ መተግበርያዎች ብዙዎችን አደጋ ላይ እየጣሉ ነው ። ቴሌግራምም ሌሎች ከ official official ውጪ ያሉትን እንዳንጠቀም መመሪያ አስቀምጧል አካውንታችን አደጋ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ፕሮፋይላችን ከስር መልዕክት እያስቀመጠ ነው !

የትኛውንም የውጭ የትምህርት እድል ፣ ጉዞ ፣ የኦላይን የትምህርት ሳይቶች ፣ ኢሜይል መፍጠር እና ሌሎች የውጭ ፎርሞች ስትሞሉ #Last_name ወይም #surname መሙላት ያለባቸሁ የአባት ሳይሆን
+1
የትኛውንም የውጭ የትምህርት እድል ፣ ጉዞ ፣ የኦላይን የትምህርት ሳይቶች ፣ ኢሜይል መፍጠር እና ሌሎች የውጭ ፎርሞች ስትሞሉ #Last_name ወይም #surname መሙላት ያለባቸሁ የአባት ሳይሆን የአያት ስም ነው። ለበለጠ #ፓስፖርት ወይም #NationalID ያችሁን ተመልከቱ !

በቤትዎ ሆነው የአለም አቀፍ ሰርተፊኬት ባለቤት ይሁኑ! 🎓💻 ​የቴክኖሎጂ እውቀትዎን ማሳደግ ይፈልጋሉ? ወይስ አዳዲስ የዲጂታል ክህሎቶችን ተምረው በስራው አለም ተፈላጊ መሆን? እንግዲያውስ ስለ Atingi ሊያውቁ ይገባል! ​Atingi ምንድነው? Atingi በጀርመን መንግሥት (GIZ) የበለፀገ፣ በተለይም እንደ እኛ ባሉ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ለሚገኙ ተማሪዎች እና ባለሙያዎች ነፃ የዲጂታል ትምህርት የሚያቀርብ ታላቅ ፕላትፎርም ነው። ​ለምን Atingi ን ይመርጣሉ? ​✅ 100% ነፃ ኮርሶች፡ ከ550 በላይ ጥራት ያላቸው ኮርሶችን ያለ ምንም ክፍያ መማር ይችላሉ። ✅ ታማኝ ሰርተፊኬት፡ ኮርሶቹን ሲያጠናቅቁ ለስራ ማመልከቻ የሚሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ያገኛሉ። ✅ ከኢንተርኔት ነፃ (Offline) መማር፡ የAtingi አፕሊኬሽንን በመጠቀም ኮርሶችን ዳውንሎድ አድርገው ኢንተርኔት በሌለበት ቦታም መማር ይቻላል። ✅ በማንኛውም ቋንቋ፡ ትምህርቶቹ ከ22 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የቀረቡ ናቸው። ​ምን ምን ይማሩበታል? ​Artificial Intelligence (AI)፦ የዘመኑ ቀዳሚ ቴክኖሎጂ AI መሰረታዊ እውቀትና አጠቃቀም። ​የስራ ፈጠራ (Entrepreneurship)፦ የራስዎን ቢዝነስ ለመጀመር የሚረዱ ስልጠናዎች። ​ዲጂታል ክህሎት (Digital Skills)፦ የዳታ አያያዝ፣ የኮምፒውተር ጥገና እና የሳይበር ደህንነት። ​አመራርና አስተዳደር (Management & Leadership)፦ ለተማሪዎችና ለወጣት ባለሙያዎች። ​እንዴት መጀመር ይቻላል? ​ወደ www.atingi.org ይግቡና በኢሜይልዎ በነፃ ይመዝገቡ። ​የሚፈልጉትን ኮርስ ይምረጡ። ​ትምህርቱን ተከታትለው ሲጨርሱ ሰርተፊኬትዎን ይቀበሉ! ​ በተለይ በቴክኖሎጂ እና በኢኖቬሽን ዘርፍ ለተሰማራችሁ ተማሪዎች፣ ይህ ፕላትፎርም እውቀታችሁን ለማሳደግ ወርቃማ እድል ነው። ዛሬውኑ ጀምሩ! ​📍 ጥያቄ ካላችሁ ኮሜንት ላይ አሳውቁኝ! ለጓደኞቻችሁ እንዲደርስ Share ማድረጋችሁን እንዳትረሱ። ​#Atingi #DigitalLearning #EthiopiaTech #AI #FreeCourses #Innovation #InnovationWithMehammed #SelfDevelopment

Atingi Online learning platform.
Atingi Online learning platform.

#DigitalInclusion - (ዲጂታል አካትችነት)፡ ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! 🌐 ኢንተርኔት የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል ቢሆንም፣ አሁንም ብዙዎች ከዚህ ዕድል ተገልለዋል። ዛሬ
#DigitalInclusion - (ዲጂታል አካትችነት)፡ ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! 🌐 ኢንተርኔት የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል ቢሆንም፣ አሁንም ብዙዎች ከዚህ ዕድል ተገልለዋል። ዛሬ ላይ ኢንተርኔት መጠቀም ብቻ በቂ አይደለም፤ መረጃን መመገብ (Consumer) ብቻ ሳይሆን መረጃን መፍጠር (Creator) የሚጠበቅብን ደረጃ ላይ ደርሰናል። የደጀታል እድሉን ተጠቅመን የራሳችን ቀጣይነት ያለው ገቢም ጨምር መፍጠር ይኖርብናል። ዲጂታል አካትችነት በሶስት ዋና ምሰሶዎች ላይ ይቆማል፦ ✅ ተደራሽነት (Access)፦ ቴክኖሎጂው በሁሉም ቦታ እና በተመጣጣኝ ዋጋ መገኘት አለበት። ✅ ተግባራዊነት (Adoption)፦ የዲጂታል እውቀት (Digital Literacy) እና ደህንነት ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። ✅ አጠቃቀም (Application)፦ ቴክኖሎጂውን ለጤና፣ ለትምህርት እና ለኢኮኖሚ እድገት ማዋል! ዲጂታል ዓለም ለጥቂቶች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም መሆን አለበት! እነዚህ 3ቱ የዲጂታል አካታችነት ምስሶሶዎች በሀገራችን ደረጃ ምን ደረጃ ላይ ናቸዉ ብላችሁ ታስባላችሁ?👇 Mohammed Seid #DigitalInclusion #TechForAll #Ethiopia #DigitalLiteracy #EthiopiaTech

የ GCI World 2026 ጉዞዬን ዛሬ በይፋ ጀምሬያለሁ! 🚀 ⛩️ ​በጃፓን የሚገኘው የ University of Tokyo (Matsuo-Iwasawa Laboratory) ባዘጋጀው የ GCI World 20
የ GCI World 2026 ጉዞዬን ዛሬ በይፋ ጀምሬያለሁ! 🚀 ⛩️ ​በጃፓን የሚገኘው የ University of Tokyo (Matsuo-Iwasawa Laboratory) ባዘጋጀው የ GCI World 2026 April Program ላይ ለመሳተፍ ተመርጬ፣ ፕሮግራሙን ዛሬ በይፋ መጀመራችንን ለወዳጆቼ ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው። ​ይህ ፕሮግራም በ Data Science፣ Python እና Machine Learning ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በዘርፉ ካሉ የዓለም ምርጥ ባለሙያዎች ጋር የምንገናኝበት ትልቅ ዕድል ነው። ከተለያዩ የአለማችን ክፍል ከተውጣጡ ተማሪዎች ጋርም ለመገናኘት እድል ይፈጥርልኛል። ​እንደ ኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪነቴ እና በጤና መረጃ (Health Data) ላይ እንደሚሰራ ባለሙያ፣ በዚህ ፕሮግራም የማገኘውን የ AI እና የዳታ ትንተና እውቀት ወደፊት በአገራችን የጤና ስርአት ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን በቴክኖሎጂ ለመፍታት እና በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን ለማሳለጥ እጠቀምበታለሁ። በፕሮግራሙ Outstanding ሆነው የሚያጠናቅቁ ወደ ቶክዮ ሄዶ የመማር እድል እና ሌሎች ምቹ አጋጣሚዎች ይፈጠርላቸዋል። እኔም Outstanding ሆኖ ለመገኘት የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ። አብራችሁኝ ቆዩ 😍 ​ አዳዲስ ነገሮችን እየተማርኩ የማካፍላችሁ ይሆናል። ​#GCIWorld2026 #UniversityOfTokyo #DataScience #MachineLearning #EthiopiaTech #miftahcode

የቻት ጂፒቲ ድብቅ Setting: https://www.facebook.com/share/r/18WWevrkan/

🤖 Generative AIን በአጭር ጊዜ ለመረዳት! #Introductory_course ​የቴክኖሎጂው ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተለወጠ ነው። በተለይ Generative AI (እንደ ChatGPT እና G
🤖 Generative AIን በአጭር ጊዜ ለመረዳት! #Introductory_course ​የቴክኖሎጂው ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተለወጠ ነው። በተለይ Generative AI (እንደ ChatGPT እና Gemini ያሉ) በዕለት ተዕለት ስራችን እና በፈጠራው ዘርፍ ትልቅ አብዮት እየፈጠረ ይገኛል። ​ይህንን አዲስ ቴክኖሎጂ በቀላሉ ለመረዳት #Google ኩባንያ ባዘጋጀው በዚህ ነፃ የ30 ደቂቃ ኮርስ ውስጥ የሚከተሉትን መሰረታዊ ነጥቦች ይማራሉ፡ ◽️​Generative AI ምንድን ነው? (ከባህላዊው Machine Learning በምን ይለያል?) ◽️​እንዴትስ ጥቅም ላይ ይውላል? ◽️​የራሳችሁን የGen AI መተግበሪያዎች ለመስራት የሚረዱ የGoogle መሳሪያዎች የትኞቹ ናቸው? ​💡 ኮርሱን እንደጨረሳችሁ ዲጂታል ባጅ (Badge) ታገኛላችሁ! ​🔗 ለመጀመር ሊንኩን ይጫኑ፡ https://www.skills.google/paths/118/course_templates/536/preview

#ትኩረት
#ትኩረት

#Ethiocoders Certificate 🤔
#Ethiocoders Certificate 🤔

@ #ML
@ #ML

❇️ የሰው ሰራሽ ብልህነት (AI) ጎህ - ከቱሪንግ ህልም እስከ ዲጂታል አብዮት 🤖 በ መሀመድ ሰይድ (ሚፍታህ) – የሳይቴክ ይዘት አዘጋጅ እና የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ ዛሬ የምንገኝበት ዘመን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እንደ "ታላቁ የዲጂታል ህዳሴ" ሊጠቀስ ይችላል። በየጠረጴዛው፣ በየቢሮው እና በየፖለቲካው መድረክ "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ" (AI) የሚለው ሐረግ እንደ ማዕበል እየናኘ ነው። ነገር ግን ይህ ቴክኖሎጂ በአንድ ምሽት የበቀለ እንጉዳይ አይደለም። ከጀርባው የዘመናት ፍልስፍና፣ የአሥርተ ዓመታት የሒሳብ ስሌት እና የሰው ልጅ የፈጠራ ጥማት ውጤት ነው። በዚህ የመጀመሪያ ቀን ይዘታችን ፣ የኤአይን መሠረት እና አሁን ለደረሰበት ደረጃ ያበቁትን ቁልፍ ሁነቶች በጥልቀት እንመረምራለን። 1️⃣. የመጀመሪያው ጥያቄ፡ "ማሽኖች ማሰብ ይችላሉን?" እ.ኤ.አ. በ1950፣ እንግሊዛዊው የሒሳብ ሊቅ እና የኮምፒውተር ሳይንስ አባት አላን ቱሪንግ (Alan Turing) አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ለዓለም አቀረበ። ቱሪንግ በወቅቱ የነበሩት ኮምፒውተሮች እጅግ ጥሬ ቢሆኑም፣ ወደፊት ግን የሰውን ልጅ አእምሮ ሊመስሉ እንደሚችሉ አስቀድሞ ገምቶ ነበር። ቱሪንግ "The Imitation Game" በሚለው ጥናቱ፣ አንድ ማሽን ብልህ (Intelligent) ተብሎ ለመጠራት የግድ የሰውን አእምሮ ባዮሎጂያዊ አወቃቀር መያዝ የለበትም፤ ይልቁንም "እንደ ሰው ምላሽ መስጠት ከቻለ በቂ ነው" የሚል መከራከሪያ አቀረበ። ይህ ዛሬ የምንጠቀምባቸው እንደ ChatGPT ያሉ ሞዴሎች መሠረታዊ ፍልስፍና ነው። ቱሪንግ በወቅቱ "እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ድረስ ኮምፒውተሮች ተራውን ሰው ግራ እስኪያጋቡ ድረስ የማሰብ አቅማቸው ያድጋል" ብሎ ተንብዮ ነበር። ዛሬ እየሆነ ያለው ይህ ነው። 2️⃣. የዳርትማውዝ ታሪካዊ ስብሰባ (1956) "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ" የሚለው ቃል በይፋ የተፈጠረው እ.ኤ.አ. በ1956 በዳርትማውዝ ኮሌጅ በተካሄደ የሁለት ወራት የምርምር ስብሰባ ላይ ነው። ጆን ማካርቲ (John McCarthy)፣ ማርቪን ሚንስኪ (Marvin Minsky) እና ክላውድ ሻነን (Claude Shannon) የተባሉ ሳይንቲስቶች የኤአይን ፍቺ እንዲህ ሲሉ አስቀመጡት፦ "እያንዳንዱ የመማር ሂደት ወይም የማሰብ ችሎታ በማሽን ሊገለጽና ሊመሰል ይችላል"። ይህ በራስ መተማመን የታየበት መግለጫ የዘርፉን ጉዞ ጀመረው። ሆኖም ግን፣ በወቅቱ የነበረው የኮምፒውተር አቅም ከሳይንቲስቶቹ ህልም ጋር አልተመጣጠነም። ይህም ዘርፉ "የኤአይ ክረምት" (AI Winter) ወደተባለ ተስፋ መቁረጥ እና የገንዘብ ድጋፍ ማጣት ውስጥ ለዓመታት እንዲዘፈቅ አድርጎት ነበር። 3️⃣. ለምን አሁን? የሦስቱ ኃይሎች መገጣጠም ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ AI ከላብራቶሪ ወጥቶ ወደ እጃችን የገባው ለምንድነው? የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር አንድሪው ንግ (Andrew Ng) AIን "አዲሱ ኤሌክትሪክ" (The New Electricity) ሲሉ ይጠሩታል። እንደ እሳቸው አገላለፅ፣ ኤሌክትሪክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማኑፋክቸሪንግን፣ ትራንስፖርትንና ጤናን እንደቀየረው ሁሉ፣ AIም ዛሬ ያንኑ እያደረገ ነው። ይህ እንዲሆን ያደረጉት ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው፦ 🟧የቢግ ዳታ (Big Data) ፍንዳታ፦ AI እንደ ሕፃን ልጅ ነው። ለመማር መረጃ ያስፈልገዋል። ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኢንተርኔት አማካኝነት የተከማቸው ግዙፍ መረጃ (ጽሁፎች፣ ምስሎች፣ ድምጾች) ለኤአይ ሞዴሎች እንደ ትልቅ መጽሐፍት ቤት አገልግለዋል። 🟧የማስላት አቅም (Compute Power)፦ ግዙፍ የሆኑ የሂሳብ ቀመሮችን በሰከንድ ውስጥ ማከናወን የሚችሉ ቺፖች (በተለይም GPUs) መፈጠራቸው። 🟧Deep Learning (ጥልቅ ትምህርት)፦ የሰውን አእምሮ የነርቭ ሴሎች (Neurons) አሠራር የሚመስሉ ሰው ሰራሽ ኔትወርኮች መገንባታቸው። 4. የተቋማት እና የምሁራን ስጋትና ተስፋ እንደ MIT (Massachusetts Institute of Technology) ያሉ ተቋማት AIን የሰው ልጅን አቅም ማሳደጊያ (Augmentation) አድርገው ሲመለከቱት፣ ሌሎች ደግሞ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ይላሉ። የታዋቂው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ኒክ ቦስትሮም (Nick Bostrom) እንደሚሉት፣ AI "የሰው ልጅ የመጨረሻው የፈጠራ ውጤት" ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም አንድ ጊዜ ራሱን የሚያሻሽል AI ከተፈጠረ፣ የሰው ልጅን ብልህነት በከፍተኛ ፍጥነት ሊበልጥ ይችላል። 🚩ማጠቃለያ የመጀመሪያው ቀን ትምህርታችን የሚያሳየን AI ድንገት የመጣ ሳይሆን፣ የሰውን ልጅ አእምሮአዊ አቅም በማሽን የመቅዳት ረጅም ጉዞ ውጤት መሆኑን ነው። ዛሬ የምንጠቀመው AI "Narrow AI" ይባላል—አንድን ስራ (ለምሳሌ ጎግል ትርጉም፣ ምስል መለየት) ብቻ በጥራት የሚሰራ። ነገር ግን ወደፊት "General AI" (እንደ ሰው ሁሉንም ነገር ማሰብ የሚችል) የመፍጠር ህልሙ ገና ቀጥሏል። ይሳካ ይሆን? 📅 በክፍል ሁለት፦ ማሽኖች መምህር ሳይኖራቸው እንዴት በራሳቸው ይማራሉ? የ AI "አንጎል" ተብሎ የሚጠራውን ማሽን ለርኒንግ (Machine Learning) በዝርዝር እንፈትሻለን። የእርስዎ ስልክ የእርስዎን ድምፅ ሲያውቅ ወይም ፎቶግራፍ ላይ ያሉ ጓደኞችዎን ሲለይ ምን ይሰማዎታል? ይህ በሕይወትዎ ላይ ያመጣው ትልቁ ለውጥ ምንድነው? ሐሳብዎን በኮሜንት መስጫ ላይ ያጋሩን።❓ ↪️መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉት🙏 #DigitalEthiopia #Ethiocoders #miftah ©️Mohammed Seid

#artificialintelligence@miftahcode
#artificialintelligence@miftahcode

የወደፊቱ ስራ እና AI የ Nvidia መስራችና CEO ጄንሰን ሁዋንግ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፦ "AI will not take your job. The person who uses AI will ta
የወደፊቱ ስራ እና AI የ Nvidia መስራችና CEO ጄንሰን ሁዋንግ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፦ "AI will not take your job. The person who uses AI will take your job." (AI ስራህን አይቀማህም። ነገር ግን AIን የሚጠቀም ሰው ስራህን ይቀማሃል።) ይህ ንግግር ትልቅ መልዕክት አለው። ብዙዎቻችን "AI ስራ ያሳጣናል" በሚል ስጋት ውስጥ ነን። ነገር ግን እውነታው AI በራሱ መጥቶ ስራችንን አይወስድብንም፤ ይልቁንም የ AIን ቴክኖሎጂ በሚገባ ታጥቆ የመጣ ሌላ ሰው፣ እኛ በሳምንት የምንሰራውን ስራ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በማጠናቀቅ ገበያውን ይረከበዋል። የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪም ሆንክ የንግድ ሰው ፣ ዛሬውኑ AIን መለማመድ መጀመር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው! እናንተስ በስራችሁ ላይ AIን መጠቀም ጀምራችኋል? ኮሜንት ላይ ሀሳባችሁን አጋሩኝ 👇 #AI #Innovation #TechEthiopia #miftahcode #digitalethiopia

#Ethiocoders #FAQs@miftahcode
#Ethiocoders #FAQs@miftahcode

#DigitalSkills
#DigitalSkills