uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Mohammed Seid - Miftah

Mohammed Seid - Miftah

Відкрити в Telegram

​🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
2 570
Підписники
-224 години
+77 днів
+10430 днів

Завантажуємо дані

Схожі канали
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Хмара тегів
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Вхідні та вихідні згадування
---
---
---
---
---
---
Залучення підписників
жовт '26
жовтень '26
+123
в 1 каналах
вересень '26
+2 508
в 3 каналах
Дата
Залучення підписників
Згадування
Канали
20 жовтня+1
19 жовтня+2
18 жовтня+6
17 жовтня+1
16 жовтня+4
15 жовтня+3
14 жовтня+1
13 жовтня+3
12 жовтня+7
11 жовтня+17
10 жовтня+28
09 жовтня+9
08 жовтня0
07 жовтня0
06 жовтня+4
05 жовтня+9
04 жовтня+9
03 жовтня+8
02 жовтня0
01 жовтня+11
Дописи каналу
ኤአይን (AI) ከመጠቀምዎ በፊት ሊያውቋቸው የሚገቡ 5 ወሳኝ ጉዳዮች! አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የዕለት ተዕለት ህይወታችንና ስራችንን እያቀለለልን ይገኛል። ነገር ግን በዘርፉ ላይ ያልሆንን ሰዎች ኤአይን ከመጠቀማችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ 5 ቁልፍ ነጥቦች አሉ፦ 1️⃣ ኤአይ ማሰብ አይችልም! ኤአይ እንደ ሰው የራሱ የሆነ አእምሮ፣ ስሜት ወይም እውነተኛ ማስተዋል የለውም። እሱ የሚሰራው የቃላት ወይም የምስል ቅጦችን (patterns) በማጥናትና በማቀናበር ነው። የሚሰጥዎት ምላሽ በጣም ትክክለኛ ቢመስልም፣ ነገሩን ስላወቀው ሳይሆን ከዚህ በፊት ካየው መረጃ በመነሳት የሚቀጥለውን ቃል “በመገመት” የሚሰጥዎት ነው። 2️⃣ ሁልጊዜ ትክክል አይደለም (ይቃዣል!) ኤአይ አንዳንድ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የተሳሳቱ ወይም የሌሉ መረጃዎችን እውነተኛ አስመስሎ ሊያቀርብ ይችላል። ይህ በቴክኖሎጂው ዓለም "Hallucination" (ማቃዠት) ይባላል። ስለዚህ በህክምና፣ በህግ፣ ወይም በማንኛውም ወሳኝ ጉዳይ ላይ ኤአይ የሚሰጥዎትን መረጃ ከመጠቀምዎ በፊት ሁልጊዜ እውነተኛነቱን ማረጋገጥ (Double-check) ግዴታ ነው! 3️⃣ የግል ሚስጥርዎን ይጠብቁ! ለኤአይ የሚያስገቡት ማንኛውም መረጃ ስርዓቱን ይበልጥ ለማሰልጠን ሊያገለግል ይችላል። ይህ ማለት የእርስዎ ሚስጥራዊ መረጃ በሌላ ሰው እጅ የመግባት እድል አለው። ስለዚህ በፍጹም የግል ሚስጥራዊ መረጃ ፣ ፎቶ፣ የባንክ መረጃ ወይም የድርጅት ሚስጥራዊ መረጃዎችን በፍፁም አያስገቡ። 4️⃣ ውጤቱ የሚወሰነው በትእዛዝዎ ጥራት ነው ከኤአይ የሚፈልጉትን ምላሽ ለማግኘት የሚሰጡት ትዕዛዝ (Prompt) ግልጽ እና ዝርዝር መሆን አለበት። አጠቃላይ ጥያቄ ከመጠየቅ ይልቅ፣ ኤአይው ምን አይነት ሚና እንዲጫወት እንደሚፈልጉ (ለምሳሌ፡ "እንደ ማርኬቲንግ ባለሙያ ሆነህ ፅሁፍ ጻፍልኝ") በግልጽ መንገር የተሻለ ውጤት ያስገኛል። 5️⃣ የሰውን ልጅ አይተካም ረዳት ነው! ኤአይ ስራን በፍጥነት ለማከናወን እና ሃሳቦችን ለማፍለቅ እጅግ ግሩም ረዳት ነው። ነገር ግን የሰውን ልጅ የፈጠራ ችሎታ፣ ስነ-ምግባር እና ውሳኔ ሰጪነት ሙሉ በሙሉ መተካት አይችልም። ኤአይን የእርስዎን ስራ የሚያቀላጥፍ ታማኝ ረዳት አድርገው ይውሰዱት እንጂ ሙሉ በሙሉ አይመኑት። በተጨማሪ ሁሉንም ነገር (ማሰብን፣ መጻፍን፣ ማቀድና መወሰንን) ለኤአይ ሙሉ በሙሉ አሳልፈን መስጠት የለብንም። የራሳችንን አእምሮ ካላሰለጠንነውና በራሳችን ማሰብ ካቆምን፣ የማስታወስ፣ የመተንተን እና የፈጠራ ችሎታችን እየቀነሰ ይሄዳል። ኤአይ የአእምሮአችን መተኪያ ሳይሆን ማገዣ ብቻ መሆን አለበት። እርስዎስ ኤአይን ለምን አይነት ስራዎች ተጠቅመው ያውቃሉ? ያጋጠማችሁ አስቂኝ ወይም ጠቃሚ ነገር ካለ ኮሜንት ላይ አጋሩን! ተጨማሪም ካለ ሼር አድርጉን 👇 📌 Telegram: https://t.me/miftahcode #ArtificialIntelligence #TechTips

2
ቀደም ሲል ለሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች ዋናው ፈተና "የደህንነት ስህተቶችን ማግኘት" ነበር። አሁንስ? ይህ የ IBM X-Force ሪፖርት ምላሽ አለው! 👇https://www.ibm.com/think/x-force/ai-vulnerability-discovery
232
3
ከ EAII ተቋማችን በዋናነት ከምንጠብቃቸው ቁልፍ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ በ AI፣ ማሽን ለርኒንግ እና ዳታ ሳይንስ ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን በማካሄድ ለህብረተሰቡ እና ለኢንዱስትሪው የሚጠቅሙ ተግባራዊ መፍትሄዎችን እንዲያቀርብ ነው። ተቋማችን በዚህ ዘርፍ ላይ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች ምን ይመስላሉ? [High 3, Medium 2, Low 1] የዘርፉ ባለሙያዎች ሀሳባችሁን ሼር አድርጉን👇
314
4
ስራ አትፈልግ... ስራ የሚፈልግህ ሰው ሁን! ደፋር እና ራሳችንን ልንፈትሽበት የሚገባ ነጥብ ይመስለኛል! 😍
478
5
ነፃ የ Cisco Ethical Hacking ኮርስ ​ለሳይበር ደህንነት (Cybersecurity) እና ለኢቲካል ሃኪንግ ፍላጎት አለዎት? ​Cisco networking academy በነፃ ማንም ሰው ሊማረ
ነፃ የ Cisco Ethical Hacking ኮርስ ​ለሳይበር ደህንነት (Cybersecurity) እና ለኢቲካል ሃኪንግ ፍላጎት አለዎት? ​Cisco networking academy በነፃ ማንም ሰው ሊማረው የሚችል Ethical Hacker ኮርስ አዘጋጅቷል። ​💡 ኮርሱ የሚያካትታቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡ ☑️ ​Ethical Hacking & Penetration Testing: የሲስተም ክፍተቶችን (Vulnerabilities) እንዴት ማግኘት እና መጠገን እንደሚቻል ☑️ ​Web & Network Security: የዌብሳይቶች እና የኔትወርክ ደህንነትን የመጠበቅ ስልቶች ☑️ ​Hands-on Labs: በተግባር የተደገፉ ልምምዶች ​🎓 ደረጃ (Level): Intermediate 📜 የምስክር ወረቀት: ኮርሱን ሲያጠናቅቁ ኦፊሴላዊ የ Cisco ባጅ/ሰርተፊኬት ያገኛሉ። ​📌 አሁኑኑ ይመዝገቡ: 🔗 Cisco Ethical Hacker Course ​#EthicalHacking #Cybersecurity
481
6
Hawlet Ahmed እንደከተበችው 👏 የኮምፒውተር ኪቦርድ ቁልፎች መጠናቸው ስታንዳርድ አለው። አንድ ጣቱ በጣም ወፍራም የሆነ ሰው ሁለት ቁልፎችን የመጫን ወይም ያልተፈለገ ፊደል ወይም ቁጥር የመንካት ዕድሉ ሰፊ ነው። በዚህም ስህተት ይፈጠራል። በፋይናንስ ገበያ ውስጥ የወፍራም ጣት ጦስ ''Fat Finger Error'' የሚባል ነገር አለ። 😄 ኪቦርድ በመጠቀም መረጃ ሲገባ ስህተት መፈጸም ወይም በማውስ (mouse) ያልተፈለገ ቁልፍ ክሊክ በማድረግ የሚፈጸም ስህተትን ይወክላል። ለምሳሌ 1,000 ለመጻፍ 10,000 ብሎ data ማስገባት ሊሆን ይችላል። ወይም ቦታ ማቀያየር ሊሆን ይችላል። የ 'ወፍራም ጣት ጦስ' (Fat Finger Error) አንድ ኪሳራ ምሳሌ ላንሳላችሁ። የዛሬ 21 ዓመት ገደማ የጃፓኑ ሚዙሆ ሰኪውሪቲስ አንዱ ብሮከር የደንበኛቸውን (J- Com Co.) 14,500 አክሲዮኖች ገበያ ላይ ለመሸጥ የአንዱን አክሲዮን ዋጋ 610,000 የን (Japanese Yen) መረጃ ቋት ውስጥ ማስገባት ሲጠበቅበት በስህተት 610,000 አክሲዮኖች (40 እጥፍ) በ 1 የን እንደሚሸጡ አድርጎ ዳታውን አስገባ። ይሄ almost ነፃ የሆነ ግዢ ነው። ሕዝቡ ተረባረበና በ 1 የን መግዛት ጀመረ። ሲስተሙ ያኔ Cancel ለማድረግ የማይችል ስለነበር ምንም ማድረግ አልተቻለም። ስለሆነም J-Com የራሱን አክሲዮኖች መልሶ እየገዛ እንደገና መልሶ እየሸጠ የገዢዎችን ፍላጎት ማሟላት ነበረበት። በዚህም ከሽያጩ ሳይጠቀም በ Fat finger error ምክንያት የ40 ቢሊየን የን (225 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር) ግዙፍ ኪሳራ ደርሶበታል። በፋይናንሺያል ማርኬት ውስጥ እንዲህ ያሉ ስህተቶች ይህን ስያሜ ያገኙት ወፍራም ጣት ያልሆነ ቁልፍ ነክቶ ጉዳት ማምጣቱ ጋር ተቀራራቢ ስለሆነ ነው። እንጂ ከጣት መወፈር ጋር የሚያያይዘው አንዳች ነገር የለም። 😂 ከሰሞኑ አንድ የተከበረ ሐኪም ስሙ እየተነሳ ሲጣል አይተናል። ለሚታዘብ ሰው እንኳን ይረብሻል። ራሱ ደግሞ እንዴት እንደሚከፋው መገመት ይቻላል። Unless የሚመጣውን እያወቀ ተናግሮ ካልሆነ በስተቀር። እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው እንደ ወፍራም ጣት መን'ነካት የሌለበት ቁልፍ አትጫኑ። ወይም ከመጫናችሁ በፊት አንድ ሁለቴ ብታስቡ፤ ንግግርም ቢሆን ከተቻለ ሳንሱር ብታስደርጉ ለማለት ነው። በአሁኑ ወቅት የአክሲዮን ገበያዎች ከላይ የጠቀስነው ዓይነት ኪሳራ እንዳይከሰት የጥንቃቄ ፕሮቶኮል ዘርግተዋል። ስንት የተለፋበት እና የተደከመት ስም ከደቂቃዎች ባልረዘመ ዕድሜ ባለው ንግግር እንዳይጠለሽ እኛም የጥንቃቄ 'ፕሮቶኮል' ቢኖረን ለማለት ነው። በፕሮፌሽናችን ቋንቋ ስንገስጽ! 👍
514
7
ቴክኖሎጂ ከ Tool ወደ Agent 😱
450
8
Start narrow, expand systematically! አማዞን (Amazon) ዛሬ እንደሚታየው ግዙፍ አለም አቀፍ የንግድ፣ የክላውድ ኮምፒዩቲንግ እና የሎጂስቲክስ ኢምፓየር ከመገንባቱ በፊት ቅድሚያ መጽሐፍት ሽያጭ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ እንደጀመረ ያውቃሉ? ይህ ለሀገራችን ስታርታፖችና ሥራ ፈጣሪዎች ትልቅ ትምህርት ነው። በአንድ ግልጽ ችግርና በተወሰነ የገበያ ክፍል በአነስተኛ ደረጃ ጀምሮ የንግዱን መሠረት ካጠናከሩ በኋላ ደረጃ በደረጃ ወደ ትልቁ ስኬት መስፋፋት ይቻላል!
477
9
ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ #Startups እንዲያድጉ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ያስፈልጋል። ነገር ግን ለውጡ በፍጥነት እንዲመጣ የመጀመሪያውን ተፅዕኖ ፈጣሪ እርምጃ መውሰድ ያለበት የትኛው አካል ነው ብለው ያስባሉ? [መንግስት, ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት, ኩባንያዎች, ተቋማት] ከባለድርሻ አካላቱስ ምን ይጠበቃል?
483
10
ትልቅ ተቋም ስለ እነ Google , Apple እና OpenAI ዜና ማጋራቱ ፋይዳው ምንድን ነው? አስፈላጊ አይደለም ማለቴ ሳይሆን የ EAll ሚናው ይሄ ነው ወይ? እኛ ከተቋሙ የምንጠብቀው ዘገባ ነው
ትልቅ ተቋም ስለ እነ Google , Apple እና OpenAI ዜና ማጋራቱ ፋይዳው ምንድን ነው? አስፈላጊ አይደለም ማለቴ ሳይሆን የ EAll ሚናው ይሄ ነው ወይ? እኛ ከተቋሙ የምንጠብቀው ዘገባ ነው ወይ? ስለዚህ የእኔ እይታ የ EAII ​ ተቋማችን የውጭ ቴክኖሎጂ ዘገባው ለሌሎች በማስተላለፍ የራሳችንን የ AI አቅም መገንባትና ሀገር በቀል ፈጠራዎችን ማበልጸግ ቀዳሚ ትኩረት ሊሆን ይገባል! ዘገባውም ሙሉ በሙሉ እነዚህ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት! ተቋሙ የሰራው ስራ የለም እያልኩ አይደለም በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ነገር ግን እኛ የምንጠብቀው ከዚህም በላይ ነው። ​እናንተስ ምን ታስባላችሁ? 👇 ​#Ethiopia #ArtificialIntelligence
558
11
"ጠፋህ በሰላም ነው?" የሚል አንድም ሰው የለም! ዘመድ እንዲህ ነው ግን?! 😂 ​ለማንኛውም ሰላም እና ጤና ለሁላችሁም ተመኘሁ፣ ተመልሻለሁ! ⤴️👋
608
12
በአለም አቀፍ ደረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ የበላይነት ዙሪያ በአሜሪካ እና በቻይና መካከል የሚደረገው ውድድር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተፋፋመ መጥቷል። የብሉምበርግ ኢንተለጀንስ (Bloo
በአለም አቀፍ ደረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ የበላይነት ዙሪያ በአሜሪካ እና በቻይና መካከል የሚደረገው ውድድር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተፋፋመ መጥቷል። የብሉምበርግ ኢንተለጀንስ (Bloomberg Intelligence) የቅርብ ጊዜ ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ “አሜሪካ በAI አፈጻጸም በቻይና ላይ የነበራት የነጥብ ብልጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየቀነሰ መጥቷል። በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው የቴክኖሎጂ ክፍተት በ2026 መጀመሪያ ላይ 15 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ በግንቦት ወር ወደ 9 በመቶ፣ አሁን ላይ ደግሞ ወደ 3 በመቶ ብቻ ዝቅ ማለት ችሏል።” ​ይህ ፈጣን ለውጥ እንዲመጣ ምክንያት የሆነው ዋነኛ ክስተት ቻይና በሴፕቴምበር ወር ላይ ይፋ ያደረገችው DeepSeek ‘V4.1 Flash’ ሞዴል ነው። አዲሱ የቻይና ሞዴል በዓለም አቀፉ የLiveBench መመዘኛ 81.1 ነጥብ በማስመዝገብ ከአሜሪካ ግንባር ቀደም የAI ሲስተሞች ጋር ትከሻ ለትከሻ የሚገጥም አፈጻጸም አሳይቷል። ይህ ስኬት ቻይና የላቁ የAI ሞዴሎችን በጥራት ደረጃ ብቻ ሳይሆን እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ የዋጋ ቅናሽ ማምረት መቻሏን የሚያሳይ ነው። ​አሜሪካ አሁንም በFrontier AI ሞዴሎች ልማት፣ በግዙፍ የኮምፒውቲንግ አቅም (Computing Capacity) እና በላቁ የሴሚኮንዳክተር ቴክኖሎጂዎች መሪነቷን አስጠብቃ በመሄድ ላይ ትገኛለች። በሌላ በኩል ቻይና የአሜሪካ ማዕቀቦች የሚፈጥሩትን ጫና ለመቋቋም የሁዋዌ (Huawei) ቺፖችን መሰረት ያደረጉ የራሷን የሃርድዌር ስነ-ምህዳሮች በመገንባት ላይ ትገኛለች። ይህ ስልት በተለይም ከአሜሪካው የNvidia CUDA ሶፍትዌር ጥገኝነት ለመላቀቅ ላደረገችው ጥረት ትልቅ እገዛ አድርጎላታል። 📌 ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/miftahcode
1 030
13
የዲጂታል ማንነትዎ ዋጋ፡ የሊንክድኢን አካውንት ይከራያል? በአሁኑ የቴክኖሎጂ ዘመን ማህበራዊ ሚዲያዎች እና የሙያ መድረኮች የሰዎች ዲጂታል ማንነት ማሳያ ሆነዋል። ሆኖም ግን፣ በቅርብ ጊዜ “የሊንክድኢን (LinkedIn) ወይም የፌስቡክ አካውንትዎን አከራይተው በወር ተጨማሪ ገቢ ያግኙ” የሚሉ አታላይ ጥሪዎች በስፋት እየተስተዋሉ ይገኛሉ። ብዙዎችም ለዚህ አታላይ ጥሪ እጅ ሰጥተዋል። ይህ ለአጭር ጊዜ የሚገኝ ቀላል ገንዘብ እና ገቢ ሲሆን፣ ከጀርባው ግን ለዓመታት የደከሙበትን የሙያ ስም እና የዲጂታል ደህንነት ሙሉ በሙሉ አደጋ ላይ የሚጥል ትልቅ ወጥመድ ነው። ​ 1️⃣ የህግ እና የወንጀል ተጠያቂነት አካውንትዎን አሳልፈው ሲሰጡ የሚፈጠረው ትልቁ አደጋ የህግ እና የስም ተጠያቂነት ነው። አካውንቱን የተከራዩት ወገኖች በእርስዎ ስም እና ምስል በመጠቀም ያልተረጋገጡ የንግድ ማስታወቂያዎችን ሊለጥፉ፣ የፋይናንስ ማጭበርበር ሊፈጽሙ ወይም የሳይበር ጥቃት ሊሰነዝሩ ይችላሉ። በህግ እና በመድረኮቹ መመሪያ ፊት ድርጊቱ የተፈጸመው በእርስዎ ማንነት በመሆኑ፣ የሚመጣውን ማንኛውንም የህግ እና የወንጀል ተጠያቂነት ሙሉ በሙሉ የሚሸከሙት እርስዎ ነዎት። ​ 2️⃣ የሙያ ስም እና የታማኝነት ማጣት በሙያ ዓለም ውስጥ ትልቁ ሀብት "ታማኝነት" እና የገነቡት መልካም ስም ነው። አካውንትዎን ለሶስተኛ ወገን አሳልፈው ሲሰጡ፣ ተከራዮቹ በኔትወርክዎ ውስጥ ላሉ የቅርብ ወዳጆች እና የስራ ባልደረቦች አላስፈላጊ ወይም አታላይ መልዕክቶችን ሊልኩ ይችላሉ፤ ይህም ለዓመታት የገነቡትን ሙያዊ አክብሮት ያጠፋዋል። ​ 3️⃣ የአካውንት ሙሉ በሙሉ መታገድ (Permanent Ban) የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ማንነትን አሳልፎ መስጠትን እና አካውንት ማከራየትን በጥብቅ ይከለክላሉ። ይህ ህግ ጥሰት በስርዓቱ ሲደረስበት አካውንትዎን በዘላቂነት ይዘጋሉ (Ban ያደርጋሉ)፤ ይህም ወደፊት በገዛ ስምዎ አዲስ አካውንት ከፍተው እንዳይጠቀሙ ሊያደርግዎ ይችላል። በነገራችን ላይ የሊንክድኢን አካውንት ያከራዩ አካውንታቸውን ሙሉ በሙሉ አናተዋል። የገጠማችሁ ምስክር ናችሁ! በነገራችን ላይ ከዚህ የከፋ ሌሎች ብዙ አደጋዎችም አሉት። 🤔 ቆይ ግን የግል መታወቂያ ፣ የግል ማንነት እንዴት ይሽጣል? ንቁ እንሁን እንጂ ጎበዝ! በዲጂታሉ ዓለም ውስጥ ዘላቂ ስኬት እና ገቢ የሚገኘው በአቋራጭ መንገድ ሳይሆን እውነተኛ ክህሎትን በማሳደግ፣ ጠቃሚ ይዘቶችን በማመንጨት እና አስተማማኝ የሙያ ግንኙነት (Networking) በማጠናከር ነው! በጊዜያዊ ጥቅሞች ሳይታለሉ የራስዎን ማንነት እና ደህንነት ይጠብቁ። በእንደዚህ አይነት የማህበራዊ ሚዲያ ጥሪዎች ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው? አጋጥሞዎትስ ያውቃል? አስተያየትዎን ኮሜንት ላይ አጋሩን! 📌 ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/miftahcode ​#DigitalSafety #ProfessionalEthics #CyberSecurity
820
14
Did you know that you are the first line of defense against a cyber attack? እንዴት እንደሆኑ ለመረዳት 👇 🎓 ይህንን በ Cisco የቀረበ ነፃ እና ሰርተፊኬት ያለው ኮርስ ይውሰዱ! Introduction to Cybersecurity
586
15
ማህበራዊ ሚዲያ ከሌለኝ የኦንላይን ማንነት (Online Identity) የለኝም ብለው ያስባሉ? 🤔 ብዙ ሰዎች ፍፁም ማህበራዊ ሚዲያ ወይም አካውንት ከሌላቸው በኢንተርኔት ዓለም ውስጥ “ዲጂታል ማንነት” የለንም ብለው ያስባሉ። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው! ኢንተርኔት በመጠቀም ድረ-ገፆችን የምንጎበኝ፣ መረጃዎችን የምንፈልግ ወይም ቪዲዮዎችን የምንመለከት ከሆነ፤ አስበነውም ይሁን ሳናውቅ የራሳችን የሆነ የኦንላይን ማንነት (Online Identity) ይኖረናል! 🌐 የኢንተርኔት አጠቃቀማችን እና ዲጂታል አሻራችንን በጥንቃቄ መያዝ ሁልጊዜም አስፈላጊ ነው!
618
16
🔐 በሳይበር ደህንነት (Cybersecurity) ዘርፍ ብቁ ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ? ​በአለም ደረጃ የዲጂታል ግንኙነቶች በጨመሩ ቁጥር የሳይበር ጥቃቶች ስጋትም አብሮ እየሰፋ ይገኛል። ድርጅቶችን ከእነዚህ ጥቃቶች እንዴት መከላከል እንደሚችሉ በመማር በዘርፉ ተፈላጊ የሆኑ ክህሎቶችን ማዳበር እና አዲስ የሙያ እድል መክፈት ይችላሉ። ​ ይህ በ Cisco Networking Academy የቀረበው Junior Cybersecurity Analyst የሙያ መንገድ (Career Path) ለጀማሪዎች ተስማሚ በሆነ መልኩ የተዋቀረ ነው። ስልጠናው አጠቃላይ 120 ሰአታትን የሚወስድ ሲሆን፣ በቀጥታ ለአለም አቀፍ የሙያ ሰርተፊኬት (Certification Aligned) የሚያዘጋጁ ተግባራዊ እውቀቶችን የያዘ ነው። በውስጡ ያሉ ኮርሶች አለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፍኬት እና ባጅ አላችው! ​ የሳይበር ደህንነት ጉዞዎን ዛሬውኑ በመጀመር እራስዎን ለስራ አለም ብቁ ያድርጉ! ​🔗 ጉዞውን ለመጀመር 👇 Junior Cybersecurity Analyst 📌 ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/miftahcode
789
17
ከጥቂት አሥርተ ዓመታት በፊት በሀገራችን ኢንተርኔት መጠቀምም ሆነ መረጃ ማግኘት ቀላል አልነበረም። ስልክ ለመደወል እንኳን ወደ ቴሌ ሴንተር መሄድ ግድ የነበረበት ጊዜ አሁንም ድረስ በብዙዎቻችን ትዝታ ውስጥ አለ፤ ያችኑ ደካማ ኢንተርኔት ለመጠቀም እንኳን ወዴት እናመራ እንደነበር ትዝታውን ለእናንተ ትቻለሁ። በዚያን ጊዜ ስማርትፎን የሚባል ነገርም አልነበረም። ዛሬ ግን በየቤታችን እና በየኪሳችን ባሉ ስማርት ስልኮች አማካኝነት የመላው ዓለም እውቀት፣ መረጃ እና ግንኙነት በእጃችን ላይ ይገኛል። ​ይህ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ለውጥ የመጣው በድንገት ሳይሆን፣ ‘ዓለምን መቀየር እችላለሁ’ ብለው ያመኑ ጥቂት ወጣቶች በአንድ ትንሽ ጋራዥ ውስጥ ሌሊቱን ሙሉ በትጋት በመስራታቸው ነው። የዛሬዎቹ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ሁሉ መነሻ ከአንድ ትንሽ ሃሳብ እና ‘እችላለሁ’ በሚል የጸና እምነት ነው። ​የቴክኖሎጂው ዓለም አሁንም አዳዲስ ሃሳቦችን ይፈልጋል። ምናልባት ቀጣዩን ዓለም ወይም ደግሞ ሀገራችንን የሚቀይር የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤት እርስዎ ሊሆኑ ይችላሉ። ​መቼም ቢሆን መጀመርን አይፍሩ! 📌 ቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል https://t.me/miftahcode
804
18
AI (አርተፊሻል ኢንተለጀንስ) ነገሮችን በፍጥነት የሚያነበውና የሚመልሰው እያሰበ ይሆን?🤔
858
19
የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሞዴሎችን ስንጠቀም ትክክለኛ እና አስተማማኝ ምላሽ ለማግኘት የምንሰጠው ጥያቄ ወይም ትዕዛዝ (Prompt) አወቃቀር በጣም ወሳኝ ነው! ምርታማነታችሁን የሚጨምሩ 7 የመልካም አጠቃቀም ህጎች፦ 1️⃣ ግልጽ ሚና መስጠት (Assign a Role) AIው ከማን አንጻር ማሰብ እንዳለበት መንገር። ለምሳሌ፦ "እንደ ልምድ ያለው የሶፍትዌር ኢንጂነር/የማርኬቲንግ ባለሙያ ሆነህ መልስልኝ" በማለት የሚፈልጉትን የዕውቀት ደረጃና የድምጸ-መልስ (Tone) ጥራት ማረጋገጥ ። 2️⃣ የሁኔታውን ዝርዝር ማስረዳት (Provide Context) ምን እየሰራችሁ እንደሆነና የትኛው ደረጃ ላይ እንዳላችሁ ከጀርባ ያለውን ታሪክ ማብራራት። ለምሳሌ፦ "ለአዲስ ጀማሪ ተማሪዎች የሚሆን የፕሮግራሚንግ ትምህርት ማጠቃለያ እያዘጋጀሁ ነው..." 3️⃣ የውጤቱን ቅርጽ መወሰን (Specify Output Format) ምላሹ በምን አይነት ፎርማት እንዲቀርብላችሁ የምትፈልጉትን መንገድ ማስቀመጥ። ለምሳሌ፦ "በሰንጠረዥ (Table)፣ በአጫጭር ነጥቦች (Bullet points) ወይም በ3 አንቀጽ አቅልለህ አቅርብልኝ" ማለት። 4️⃣ ደረጃ በደረጃ እንዲያስብ ማድረግ (Chain-of-Thought) ቀጥታ ወደ መጨረሻው ድምዳሜ ከመሄድ ይልቅ የመልሱን ሂደት በቅደም ተከተል እንዲያሰላስል ማዘዝ። ለምሳሌ፦ "መልሱን ከመጻፍህ በፊት ደረጃ በደረጃ ተንትነህ አስብበት" ማለት AIው የሌለ መረጃ (Hallucination/ቅዠት) እንዳይፈጥር ይረዳል:: 5️⃣ ገደቦችን ማስቀመጥ (Constraints) በምላሹ ውስጥ መካተት የሌለባቸውን ወይም የግድ መኖር ያለባቸውን ድንበሮች መወሰን። ለምሳሌ፦ "ከባድ የቴክኒክ ቃላትን አትጠቀም" ወይም "ከ200 ቃላት ባልበለጠ አጭር ጽሁፍ አዘጋጅ"። 6️⃣ ምሳሌዎችን ማካተት (Few-shot Prompting) የምትፈልጉትን ውጤት አይነት በአንድ ወይም በሁለት አጭር ምሳሌ ማሳየት። ለምሳሌ፦ "የምፈልገው የጽሁፍ ስልት ልክ እንደዚህ አይነት ነው፦ [ምሳሌ እዚህ አስገቡ]" ብሎ ማሳየት ውጤቱ ልክ እንዳሰባችሁት እንዲሆን ያደርገዋል። 7️⃣ ተመልሶ ጥያቄ እንዲጠይቅ ማዘዝ (Interactive) ወዲያውኑ ሙሉ መልስ ከመስጠት ይልቅ ያልተብራራ ነገር ካለ ጠይቆ እንዲረዳ ማድረግ። ለምሳሌ፦ "ምላሹን ከመስጠትህ በፊት የተሻለ ውጤት እንድትሰጠኝ የሚረዱህን 3 ጥያቄዎች ጠይቀኝ" ማለት። እነዚህን ህጎች በመጠቀም ከ ChatGPT፣ Claude፣ Gemini እና ከሌሎች የLLM ሞዴሎች የተሻለና የጠራ ውጤት ማግኘት ይቻላል! 📌 ሶስት ጥሩ ምሳሌዎችን ኮሜንት ላይ አስቀምጫለሁ 👇 እስካሁን በብዛት የምትጠቀሙበት የ Prompt ስልት የትኛው ነው? አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ ያጋሩን! Telegram: https://t.me/miftahcode
945
20
Ask Al: "How to stop you from killing my critical thinking?" ሁላችንም መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ነው! ChatGPT ለእኔ በሰጠኝን ምላሽ ላይ "እኔን መጠቀም ማቆም አ
Ask Al: "How to stop you from killing my critical thinking?" ሁላችንም መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ነው! ChatGPT ለእኔ በሰጠኝን ምላሽ ላይ "እኔን መጠቀም ማቆም አያስፈልግህም ይልቁን መቀየር ያለብህ እኔን እንዴት መጠቀም እንዳለብህ ነው።" በማለት ሰባት የአጠቃቀም ህግ አስቀምጦልኛል! ሙሉ ምላሹን ኮሜንት ላይ ታገኙላቸሁ! የእናንተንም ሼር አድርጉን👇
714