en
Feedback
Mohammed Seid - Miftah

Mohammed Seid - Miftah

Open in Telegram

​🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
2 481
Subscribers
+224 hours
+237 days
+35530 days
Posts Archive
🚀 አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በዓለም ዙሪያ ለምን መነጋገሪያ ሆነ? ብዙዎቻችን ስለ AI እንሰማለን፤ ግን "ማሽን ለርኒንግ"፣ "ዲፕ ለርኒንግ" እና "ጄኔሬቲቭ AI" ያላቸው ልዩነት ምንድነው? ዛሬ ሁሉንም በአንድ ላይ፣ በቀላሉ እንያቸው!👇 1️⃣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence - AI) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማለት ማሽኖች እንደ ሰው ልጅ የማሰብ፣ የመማር እና ውሳኔ የመስጠት ችሎታ እንዲኖራቸው የማድረግ ጠቅላላ ሳይንስ ነው። ይህ ዘርፍ ሁሉንም ንዑስ ክፍሎች በአንድ ላይ በውስጡ የሚይዝ ትልቁ የትምህርት ክፍል ነው። 2️⃣ ማሽን ለርኒንግ (Machine Learning - ML) ይህ የAI ሞተር ነው። እያንዳንዱን ነገር በኮድ ለኮምፒውተሩ ከመንገረግ ይልቅ፣ ማሽኑ በተሰጠው ከፍተኛ መረጃ (Data) እና ስታቲስቲክስ አማካኝነት ራሱን የሚያስተምርበት ዘርፍ ነው። ዳታ በመገብነው ቁጥር፣ ቅጦችን (Patterns) የመለየት እና ትክክለኛ ግምቶችን የመስጠት አቅሙ እየጨመረ ይሄዳል። 3️⃣ ኒውራል ኔትወርክ (Neural Network) የሰውን ልጅ የአንጎል የነርቭ ሴሎች (Neurons) አወቃቀር በመምሰል የተሰራ የሂሳብ ሞዴል ነው። መረጃዎችን በተለያዩ ንብርብሮች (Layers) ውስጥ በማሳለፍ ያቀናጃል። ኮምፒውተሮች እንደ ምስል እና ድምፅ ያሉ የተወሳሰቡ መረጃዎችን እንዲረዱ የሚያስችላቸው መሠረታዊ የግንባታ ጡብ ይህ ነው። 4️⃣ ዲፕ ለርኒንግ (Deep Learning - DL) እጅግ በጣም ብዙ የኒውራል ኔትወርክ ንብርብሮችን በመጠቀም ግዙፍና ያልተዋቀሩ መረጃዎችን የሚተነትን የላቀ የማሽን ለርኒንግ ክፍል ነው። ማሽኑ ያለ ሰው እገዛ እጅግ ረቂቅ የሆኑ ምስሎችን እና ድምፆችን በራሱ ይለያል። ለፊት መለያ (Face ID) እና ለራስ-ነጂ መኪናዎች እምቅ አቅም መሠረቱ ይህ ቴክኖሎጂ ነው። 5️⃣ ጄኔሬቲቭ ኢ.አይ (Generative AI) ይህ ደግሞ መረጃን ከመተንተን ባለፈ፣ እንደ ሰው ልጅ አዳዲስ ይዘቶችን (Content) የመፍጠር አቅም ያለው የAI ክፍል ነው። ካሉት ነባር መረጃዎች በመነሳት አዳዲስ ፅሁፎችን (እንደ ChatGPT)፣ አስደናቂ ምስሎችን (Midjourney) እና ቪዲዮዎችን በሰከንዶች ውስጥ ማመንጨት ይችላል ። ይህ መረጃ ከጠቀማችሁ ለሌሎች ሼር አድርጉት! #AI #MachineLearning #DeepLearning #GenerativeAI #TechInnovation #AmharicTech

😘የሞባይሌ Adobe Photoshop or Illustrator ብዙ ጊዜ በሶሻል ሚዲያ ገጾቼ ላይ የምታዩትን የግራፊክስ ስራዎች ተመልክተው ሰዎች፤ 'በምን አይነት ሶፍትዌር ነው የምትሰራው?' ብለው ይ
😘የሞባይሌ Adobe Photoshop or Illustrator ብዙ ጊዜ በሶሻል ሚዲያ ገጾቼ ላይ የምታዩትን የግራፊክስ ስራዎች ተመልክተው ሰዎች፤ 'በምን አይነት ሶፍትዌር ነው የምትሰራው?' ብለው ይጠይቁኛል። እውነታው ግን ለብዙዎች አስገራሚ ሊሆን ይችላል... ይሄን ሁሉ ውበት የምፈጥረው ሁልጊዜ በእጄ ላይ ባለው ስልኬ እና Ibis Paint በተባለው አፕሊኬሽን ብቻ ነው! በጣም ነው የምወዳት የሞባይሌ አዶቤ ፎቶሾፕ ብያታለሁ ስእል (Illustration) ሁሉ መሳል ትችላላችሁ! ለግራፊክስ ላፕቶፕ የለኝም ብላችሁ አትጨነቁ! አስፈላጊ ከሆነ ስለ አጠቃቀሟ YouTube video እሰራላችኋለሁ ! የግራፊክስ APP ወይም ሶፍትዌር ሞክሮ ለማያቅ ትንሽ ወሰብሰብ ልትል ትችላለች እኔ እራሱ በየቀኑ እየተጠቀምኩበት በቀን የማወቀው አዲስ ቱል አለ! ለሶሻል ሚዲያ Content creator ብትጠቀሙባት ሀሪፍ ነው ብዬ አስባለሁ! 🔗 Link 👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=jp.ne.ibis.ibispaintx.app

በኤአይ አብዮት ዘመን በማንኛውም ሙያ ውስጥ ውጤታማ ሆኖ ለመቀጠል ቁልፉ የያዙትን እውቀት በቴክኖሎጂ ማገዝ እና ማላመድ (Adaptability) ብቻ ነው ፤ ምክንያቱም ኤአይ የተለመዱና ተደጋጋሚ ስራዎችን ሙሉ በሙሉ ሲረከብ ፣ ሰዋዊ ክህሎት እና ስልታዊ ውሳኔ የሚጠይቁትን ክፍሎች ግን ለባለሙያው (ለእኛ) ይተዋሉ። ስለዚህ እንደ መምህር፣ ሾፌር፣ አካውንታንት፣ የጤና ባለሙያ ወይም ሶፍትዌር ኢንጂነር ወይንም ሌላ ስኬታማ ለመሆን “ኤአይ ስራዬን ይወስደዋል” ከሚል ስጋት ወጥተን ፣ በየሙያ መስካችን ያሉትን አዳዲስ የኤአይ መሳሪያዎች(እድገት) ቀድመን በመላመድ ስራችንን የምናፋጥንበትና ጥራቱን የምንጨምርበት እንደ ዋና ረዳታችን በማድረግ ልንጠቀምበት ይገባል። ምንም ጥያቄ የለውም አሁን የምናውቀው የስራ ባህል ይቀየራል በአይናችን እያየነውም ነው፡፡ ቴክኖሎጂ ጋር የተላመዱ እና የሚጠቀሙ ወደፊት በመውጣት ቦታውን ይረከባሉ! በተለዋዋጭው የቴክኖሎጂ ዘመን ተፈላጊ ሆኖ ለመቀጠል ብቸኛው ግልጽ መፍትሄ ትናንት በተማርነው ብቻ ሳንወስን ሁልጊዜ ራሳችንን ለአዳዲስ እውቀቶች ክፍት ማድረግ እና ከዘመኑ ጋር አብሮ መዘመን ነው። እናንተስ በዚህ ሀሳብ ትስማማላችሁ? ወይስ ተጨማሪ ምክረ ሀሳብ አላችሁ? ሀሳብ ሼር አድርጉን አሰተምሩን የሚታረም ካለም አርሙን ? #ShareThisPost በፌስቡክ መረጃዎቼን ለመከታተል 👇👇👇 https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/

AI በስልጠና ሂደት ውስጥ በኢንተርኔት አለሙ ውስጥ ያለውን መጽሐፍት፣ የድረ-ገጽ ጽሁፎች፣ የኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ኮዶች እና የተለያዩ መረጃዎች ወ.ዘ.ተ ያልበላው አለ ለማለት ይቸግረኛል። ፍቃድ ይኑርም አይኑርም That is Pre-training model. እነ #OpenAI ክስ ከሚቀርብባቸው መካከል አንዱ ያለፈቃድ ዳታ ተጠቅመዋል አይደል! ሌላኛው ከጊዜ ወደ ጊዜ ሞዴሉን እንዴት እንዳሰለጠኑት ግልፅ እያደረጉ አይደለም ይህ ሁሉንም የ AI ሞዴል ይመለከታል ! እነ #DeepSeek ሆነ #Gemini መጽሐፍ ስትሰጣቸው ለምን በደስታ የሚቀበሉ ይመስልሀል የ ኤአይ Ethics የሚባለው ለዚያ ነው። ችግሩ ቢወጣስ ማን ያከብረው ይሆን? ማነውስ ተቆጣጣሪው?

በሴፍቲ በኮዲንግ እና በፕሪሲሽን ምርጥ ነው የተባለለት የኤአይ ሞዴል ሀገራችን ላይ መስራት ይጀምራል👇 ለበለጠ YouTube አካውንቴን ተመልከቱ: https://youtu.be/VLnQ1LDGdIc

ኮርስ አልሰራልን አለ ብላችሁ ለጠየቃችሁኝhttps://youtu.be/6s0-aiCiZiA?si=zolB9Ds0wvVg9gYV

ፖርትፎሊዮ፦ ከቃላት ባለፈ በተግባር የመመስከር ጥበብ! ዛሬ ብዙዎቻችንን በሙያ ጉዞአችን ሊያግዘን ስለሚችል አንድ ወሳኝ ጉዳይ ላጫውታችሁ ወደድኩ። በተለይ በቴክኖሎጂውም ሆነ በሌሎች የፈጠራ ዘርፎች ለምትሰሩ ጀማሪ ባለሙያዎች ይህ መረጃ የጨዋታ ለውጥ (Game Changer) ሊሆንላችሁ ይችላል። ስለ "ፖርትፎሊዮ" እናነሳለን። ትናንት ፓርቲፎሊዮ ምንድን ነው ብዬ ጥያቄ ባነሳም ከዚህ በፊት እንደነበሩት ውይይቶች ብዙም ተሳትፎ አላየሁበትም ይህ ደግሞ ምናልባትም ለጉዳዩ እንግዳ ሆነንም ሊሆን ስለሚችል ጥያቄውን ሊመልስ መልኩ እንደሚከተለው አሰናድቻለሁ። ፓርቲፎሊዮ ምንድን ነው? ፖርትፎሊዮ ማለት የአንድን ባለሙያ የክህሎት ደረጃ፣ ስኬቶች እና የተግባር ስራዎች የሚያሳይ የሰነዶች ስብስብ ነው። ብዙ ጊዜ በስራ ፍለጋ ወቅት እንደ "ማስረጃ" የሚያገለግል ሲሆን፣ የሰለጠኑበትን ወይም የሚወዱትን ሙያ በተግባር ምን ያህል እንደሚችሉበት ለቀጣሪ ወይም ለደንበኛ የሚያረጋግጡበት መንገድ ነው። ፖርትፎሊዮ ስራዎን ለማሳየት ብቻ ሳይሆን፣ ባለፉት ጊዜያት በሙያዎ ምን ያህል እንዳደጉ ለመገምገምም ይጠቅማል። ቀለል ባለ ምሳሌ እንየው፡ ብዙ ጊዜ በስራ ፍለጋ ወቅት ሲቪ (CV) እናዘጋጃለን፤ እሱም ማንነታችንን በወረቀት ይገልፃል። ፖርትፎሊዮ ግን ከዚያ ይሻገራል። ልዩነቱን እንዲህ እንየው፦ ሲቪ "ምግብ ማብሰል እችላለሁ" የሚል ፅሁፍ ሲሆን፣ ፖርትፎሊዮ ግን ያበሰልነውን ምግብ ፎቶ፣ አዘገጃጀቱንና የተመገቡ ሰዎችን ምስክርነት ለዓለም ማሳየት ነው። ባጭሩ "እችላለሁ" ከማለት ይልቅ "ይኸው የሰራሁት!" ብሎ በተግባር ማረጋገጫ ማቅረብ ማለት ነው። የት እና እንዴት እናዘጋጅ? አሁን ባለንበት የዲጂታል ዘመን ፖርትፎሊዮ ለማዘጋጀት የግድ ባለሙያ መሆን አይጠበቅብንም። ለምሳሌ፦ ➡️በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለምትሰሩ GitHub የኮድ ስራችሁን ለማሳየት ወደር የለውም። ➡️ለዲዛይንና ለፈጠራ ስራዎች Behance ወይም Canva በጣም ቀላሉ አማራጮች ናቸው። ➡️ምንም አይነት የቴክኒክ እውቀት ከሌላችሁ ደግሞ የሰራችሁትን ስራ በምስልና በፅሁፍ አደራጅታችሁ ወደ PDF በመቀየር ወይም በ LinkedIn "Featured" ክፍል ላይ በማስቀመጥ መጀመር ትችላላችሁ። መጀመሪያ አካባቢ "የማሳየው ትልቅ ስራ የለኝም" ብለን ልንሰጋ እንችላለን። ነገር ግን ዋናው ነጥብ የፕሮጀክቱ ትልቅነት ሳይሆን እናንተ የሄዳችሁበት "ሂደት" ነው። በትምህርት ቤት የሰራችሁት ትንሽ ፕሮጀክት ቢሆንም እንኳ፣ ምን አይነት ችግር ለመፍታት እንደሞከራችሁና ምን አይነት መሳርያዎችን እንደተጠቀማችሁ ግልፅ አድርጋችሁ አቅርቡት። ጥራት ከብዛት እንደሚበልጥም አትዘንጉ። በመጨረሻም፣ ፖርትፎሊዮ አንድ ጊዜ ተዘጋጅቶ የሚያልቅ ሰነድ ሳይሆን ከእርስዎ ጋር አብሮ የሚያድግ ህያው መረጃ ነው። ዛሬውኑ የሰራችሁት ትናንሽ ስራዎች ማደራጀት ጀምሩ፤ ምክንያቱም እድሎች መጥተው ሲያንኳኩ ዝግጁ ሆኖ መገኘት ትልቁ ስኬት ነው። ይህ መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ለሌሎችም እንዲደርስ "Share" ማድረጋችሁን አትርሱ። #ProfessionalGrowth #Portfolio #CareerTips #Innovation #TechLife #Ethiopia #PersonalBranding #Skills

What is Portfolio?
What is Portfolio?

ትምህርት --> ተግባር ---> ወደ ገቢ መቀየር

#Nice_gram #mobo_gram❌ የቴሌግራም አካውንታችሁ ሀክ ከመደረጉ በፊት ትክክለኛውን የቴሌግራም application ተጠቀሙ! የቴሌግራም ትክክለኛውና ኦፊሻል application link ኮሜንት
#Nice_gram #mobo_gram❌ የቴሌግራም አካውንታችሁ ሀክ ከመደረጉ በፊት ትክክለኛውን የቴሌግራም application ተጠቀሙ! የቴሌግራም ትክክለኛውና ኦፊሻል application link ኮሜንት ላይ አስቀምጥላችኋለሁ! ሊንኩን ተጭናችሁ ወደ #playstore በምትገቡበት ጊዜ Open ወይም update የሚል ከሆነ የምትጠቀሙት application ትክክለኛ ነው። Download የሚል ከሆነ ግን ትክክለኛውን መተግበሪያ በማውረድ እንደገና በትክክለኛው መተግበርያ አካውንት ክፍቱ! የማረጋገጫ መልእክት በኤስኤምኤስ ከደረሳችሁ እሰየው ማረጋገጫውን በማስገባት አካውንት መክፈታቸውን አጠናቀ በስምስ ካልደረሳችሁ ግን የማረጋገጫ መልክት የሚላክላቸው የቀድሞ application ላይ ስለሆነ ቀድማችሁ አታጥፉት ልክ የማረጋገጫ መልክት እንደደረሳችሁ እና በትክክል ወደዚህኛው መግባታቸሁን ስታረጋግጡ ያንኛውን አፕሊኬሽን አጥፉ! ከ official ውጪ ያሉ መተግበርያዎች ብዙዎችን አደጋ ላይ እየጣሉ ነው ። ቴሌግራምም ሌሎች ከ official official ውጪ ያሉትን እንዳንጠቀም መመሪያ አስቀምጧል አካውንታችን አደጋ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ፕሮፋይላችን ከስር መልዕክት እያስቀመጠ ነው !

የትኛውንም የውጭ የትምህርት እድል ፣ ጉዞ ፣ የኦላይን የትምህርት ሳይቶች ፣ ኢሜይል መፍጠር እና ሌሎች የውጭ ፎርሞች ስትሞሉ #Last_name ወይም #surname መሙላት ያለባቸሁ የአባት ሳይሆን
+1
የትኛውንም የውጭ የትምህርት እድል ፣ ጉዞ ፣ የኦላይን የትምህርት ሳይቶች ፣ ኢሜይል መፍጠር እና ሌሎች የውጭ ፎርሞች ስትሞሉ #Last_name ወይም #surname መሙላት ያለባቸሁ የአባት ሳይሆን የአያት ስም ነው። ለበለጠ #ፓስፖርት ወይም #NationalID ያችሁን ተመልከቱ !

በቤትዎ ሆነው የአለም አቀፍ ሰርተፊኬት ባለቤት ይሁኑ! 🎓💻 ​የቴክኖሎጂ እውቀትዎን ማሳደግ ይፈልጋሉ? ወይስ አዳዲስ የዲጂታል ክህሎቶችን ተምረው በስራው አለም ተፈላጊ መሆን? እንግዲያውስ ስለ Atingi ሊያውቁ ይገባል! ​Atingi ምንድነው? Atingi በጀርመን መንግሥት (GIZ) የበለፀገ፣ በተለይም እንደ እኛ ባሉ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ለሚገኙ ተማሪዎች እና ባለሙያዎች ነፃ የዲጂታል ትምህርት የሚያቀርብ ታላቅ ፕላትፎርም ነው። ​ለምን Atingi ን ይመርጣሉ? ​✅ 100% ነፃ ኮርሶች፡ ከ550 በላይ ጥራት ያላቸው ኮርሶችን ያለ ምንም ክፍያ መማር ይችላሉ። ✅ ታማኝ ሰርተፊኬት፡ ኮርሶቹን ሲያጠናቅቁ ለስራ ማመልከቻ የሚሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ያገኛሉ። ✅ ከኢንተርኔት ነፃ (Offline) መማር፡ የAtingi አፕሊኬሽንን በመጠቀም ኮርሶችን ዳውንሎድ አድርገው ኢንተርኔት በሌለበት ቦታም መማር ይቻላል። ✅ በማንኛውም ቋንቋ፡ ትምህርቶቹ ከ22 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች የቀረቡ ናቸው። ​ምን ምን ይማሩበታል? ​Artificial Intelligence (AI)፦ የዘመኑ ቀዳሚ ቴክኖሎጂ AI መሰረታዊ እውቀትና አጠቃቀም። ​የስራ ፈጠራ (Entrepreneurship)፦ የራስዎን ቢዝነስ ለመጀመር የሚረዱ ስልጠናዎች። ​ዲጂታል ክህሎት (Digital Skills)፦ የዳታ አያያዝ፣ የኮምፒውተር ጥገና እና የሳይበር ደህንነት። ​አመራርና አስተዳደር (Management & Leadership)፦ ለተማሪዎችና ለወጣት ባለሙያዎች። ​እንዴት መጀመር ይቻላል? ​ወደ www.atingi.org ይግቡና በኢሜይልዎ በነፃ ይመዝገቡ። ​የሚፈልጉትን ኮርስ ይምረጡ። ​ትምህርቱን ተከታትለው ሲጨርሱ ሰርተፊኬትዎን ይቀበሉ! ​ በተለይ በቴክኖሎጂ እና በኢኖቬሽን ዘርፍ ለተሰማራችሁ ተማሪዎች፣ ይህ ፕላትፎርም እውቀታችሁን ለማሳደግ ወርቃማ እድል ነው። ዛሬውኑ ጀምሩ! ​📍 ጥያቄ ካላችሁ ኮሜንት ላይ አሳውቁኝ! ለጓደኞቻችሁ እንዲደርስ Share ማድረጋችሁን እንዳትረሱ። ​#Atingi #DigitalLearning #EthiopiaTech #AI #FreeCourses #Innovation #InnovationWithMehammed #SelfDevelopment

Atingi Online learning platform.
Atingi Online learning platform.

#DigitalInclusion - (ዲጂታል አካትችነት)፡ ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! 🌐 ኢንተርኔት የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል ቢሆንም፣ አሁንም ብዙዎች ከዚህ ዕድል ተገልለዋል። ዛሬ
#DigitalInclusion - (ዲጂታል አካትችነት)፡ ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! 🌐 ኢንተርኔት የዕለት ተዕለት ሕይወታችን አካል ቢሆንም፣ አሁንም ብዙዎች ከዚህ ዕድል ተገልለዋል። ዛሬ ላይ ኢንተርኔት መጠቀም ብቻ በቂ አይደለም፤ መረጃን መመገብ (Consumer) ብቻ ሳይሆን መረጃን መፍጠር (Creator) የሚጠበቅብን ደረጃ ላይ ደርሰናል። የደጀታል እድሉን ተጠቅመን የራሳችን ቀጣይነት ያለው ገቢም ጨምር መፍጠር ይኖርብናል። ዲጂታል አካትችነት በሶስት ዋና ምሰሶዎች ላይ ይቆማል፦ ✅ ተደራሽነት (Access)፦ ቴክኖሎጂው በሁሉም ቦታ እና በተመጣጣኝ ዋጋ መገኘት አለበት። ✅ ተግባራዊነት (Adoption)፦ የዲጂታል እውቀት (Digital Literacy) እና ደህንነት ግንዛቤ ሊኖረን ይገባል። ✅ አጠቃቀም (Application)፦ ቴክኖሎጂውን ለጤና፣ ለትምህርት እና ለኢኮኖሚ እድገት ማዋል! ዲጂታል ዓለም ለጥቂቶች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም መሆን አለበት! እነዚህ 3ቱ የዲጂታል አካታችነት ምስሶሶዎች በሀገራችን ደረጃ ምን ደረጃ ላይ ናቸዉ ብላችሁ ታስባላችሁ?👇 Mohammed Seid #DigitalInclusion #TechForAll #Ethiopia #DigitalLiteracy #EthiopiaTech

የ GCI World 2026 ጉዞዬን ዛሬ በይፋ ጀምሬያለሁ! 🚀 ⛩️ ​በጃፓን የሚገኘው የ University of Tokyo (Matsuo-Iwasawa Laboratory) ባዘጋጀው የ GCI World 20
የ GCI World 2026 ጉዞዬን ዛሬ በይፋ ጀምሬያለሁ! 🚀 ⛩️ ​በጃፓን የሚገኘው የ University of Tokyo (Matsuo-Iwasawa Laboratory) ባዘጋጀው የ GCI World 2026 April Program ላይ ለመሳተፍ ተመርጬ፣ ፕሮግራሙን ዛሬ በይፋ መጀመራችንን ለወዳጆቼ ሳበስር በታላቅ ደስታ ነው። ​ይህ ፕሮግራም በ Data Science፣ Python እና Machine Learning ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በዘርፉ ካሉ የዓለም ምርጥ ባለሙያዎች ጋር የምንገናኝበት ትልቅ ዕድል ነው። ከተለያዩ የአለማችን ክፍል ከተውጣጡ ተማሪዎች ጋርም ለመገናኘት እድል ይፈጥርልኛል። ​እንደ ኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪነቴ እና በጤና መረጃ (Health Data) ላይ እንደሚሰራ ባለሙያ፣ በዚህ ፕሮግራም የማገኘውን የ AI እና የዳታ ትንተና እውቀት ወደፊት በአገራችን የጤና ስርአት ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን በቴክኖሎጂ ለመፍታት እና በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን ለማሳለጥ እጠቀምበታለሁ። በፕሮግራሙ Outstanding ሆነው የሚያጠናቅቁ ወደ ቶክዮ ሄዶ የመማር እድል እና ሌሎች ምቹ አጋጣሚዎች ይፈጠርላቸዋል። እኔም Outstanding ሆኖ ለመገኘት የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ። አብራችሁኝ ቆዩ 😍 ​ አዳዲስ ነገሮችን እየተማርኩ የማካፍላችሁ ይሆናል። ​#GCIWorld2026 #UniversityOfTokyo #DataScience #MachineLearning #EthiopiaTech #miftahcode

የቻት ጂፒቲ ድብቅ Setting: https://www.facebook.com/share/r/18WWevrkan/

🤖 Generative AIን በአጭር ጊዜ ለመረዳት! #Introductory_course ​የቴክኖሎጂው ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተለወጠ ነው። በተለይ Generative AI (እንደ ChatGPT እና G
🤖 Generative AIን በአጭር ጊዜ ለመረዳት! #Introductory_course ​የቴክኖሎጂው ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተለወጠ ነው። በተለይ Generative AI (እንደ ChatGPT እና Gemini ያሉ) በዕለት ተዕለት ስራችን እና በፈጠራው ዘርፍ ትልቅ አብዮት እየፈጠረ ይገኛል። ​ይህንን አዲስ ቴክኖሎጂ በቀላሉ ለመረዳት #Google ኩባንያ ባዘጋጀው በዚህ ነፃ የ30 ደቂቃ ኮርስ ውስጥ የሚከተሉትን መሰረታዊ ነጥቦች ይማራሉ፡ ◽️​Generative AI ምንድን ነው? (ከባህላዊው Machine Learning በምን ይለያል?) ◽️​እንዴትስ ጥቅም ላይ ይውላል? ◽️​የራሳችሁን የGen AI መተግበሪያዎች ለመስራት የሚረዱ የGoogle መሳሪያዎች የትኞቹ ናቸው? ​💡 ኮርሱን እንደጨረሳችሁ ዲጂታል ባጅ (Badge) ታገኛላችሁ! ​🔗 ለመጀመር ሊንኩን ይጫኑ፡ https://www.skills.google/paths/118/course_templates/536/preview