uk
Feedback
Mohammed Seid - Miftah

Mohammed Seid - Miftah

Відкрити в Telegram

​🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
2 483
Підписники
+224 години
+677 днів
+35330 днів
Архів дописів
ሁለተኛው ትልቅ የገቢ ምንጭ ሊሆንህ የሚችለው ግራፊክስ ዲዛይን (Graphics Design) ነው። ይህ ዘርፍ የአርማዎች (Logos)፣ የማህበራዊ ሚዲያ ፖስተሮች እና የብራንዲንግ ስራዎችን ማዘጋጀትን የሚጠይቅ የጥበብ ስራ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሁሉም አዲስ የሚከፈት ዩቲዩብ ቻናል፣ ሱቅ ወይም ትልቅ ድርጅት ደንበኛ ለመሳብ ፕሮፌሽናል ዲዛይን ስለሚፈልግ፣ ፍሪላንሰር በመሆን ለተለያዩ ድርጅቶች በፓኬጅ ዲዛይን በመስራት ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ትችላለህ። በተጨማሪም ከሌሎች ዲዛይነሮች ጋር በመጣመር የራስህን የብራንዲንግ እና የዲዛይን ኤጀንሲ (Design Agency) በማቋቋም ሌሎች ሰራተኞችን የምታቀጥርበት የቢዝነስ ባለቤት መሆን ትችላለህ። ሶስተኛው እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈላጊ መሆን የምትችልበት ዘርፍ ዲጂታል ማርኬቲንግ (Digital Marketing) ነው። ይህ ክህሎት ምርትና አገልግሎትን በፌስቡክ፣ በቴሌግራም፣ በቲክቶክ እና በኢንስታግራም አማካኝነት ለብዙሃን ማስተዋወቅ እና ሽያጭ መጨመር ላይ ያተኩራል። በጣም ጥሩ ምርት ኖሯቸው እንዴት ደንበኛ ጋር ማድረስ እንዳለባቸው ግራ የገባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎች ስላሉ፣ የእነሱን ማህበራዊ ሚዲያ በማስተዳደር የራስህን የማርኬቲንግ ኤጀንሲ (Marketing Agency) መመስረት ትችላለህ። ከተሳካልህ እና ከነቃህ ደግሞ የማርኬቲንግ እውቀትህን ተጠቅመህ የራስህን ምርት በኦንላይን በመሸጥ (E-commerce) ትልቅ የንግድ ተቋም መገንባት ትችላለህ። በአጠቃላይ በዲጂታል አለም ውስጥ ፈጣን፣ ቀላል እና ሰነፍ የገቢ ምንጭ የሚባል ነገር የለም። ዛሬውኑ ዩቲዩብ ላይ ገብተህ ስለእነዚህ ሙያዎች መሰረታዊ እውቀቶችን በነጻ መማር መጀመር ትችላለህ። ለጥቂት ወራት በትዕግስት እራስህን ካዘጋጀህ በኋላ፣ ማንም ሊቀማህ የማይችለው የማያልቅ የገቢ ምንጭ፣ የሙያ ባለቤት አልፎ ተርፎም የራስህ የቢዝነስ ጌታ (Business Owner) ትሆናለህ። ቢያንስ ከቅዠት ሀሳብ እነዚህ የተሻሉ ናቸው የሚል ሀሳብ ለመስጠት ነው ። ብቻ የዚያ አይነት ቪዲዮ በማየት እና በመሞከር ጊዜ ከማባከን እነዚህ የተሻሉ አማራጮች ናቸው ለማለት ነው። ምርጫው ያንተ ነው ፤ በማይረባ የቪዲዮ እይታ ማስታወቂያ መታለል ወይንስ እውነተኛ ህይወትን የሚቀይር ክህሎት እና የራስህን ቢዝነስ መገንባት?

በየቀኑ ኢንተርኔት ላይ "ቪዲዮ አይተህ በቀን 100 ዶላር ስራ" ወይም "ሊንክ ተጭነህ ጌም ተጫወትና ተከፈል" የሚሉ አጓጊ ማስታወቂያዎችን በተደጋጋሚ እናያለን። እውነታውን እንነጋገር ከተባለ፡ ከእነ
በየቀኑ ኢንተርኔት ላይ "ቪዲዮ አይተህ በቀን 100 ዶላር ስራ" ወይም "ሊንክ ተጭነህ ጌም ተጫወትና ተከፈል" የሚሉ አጓጊ ማስታወቂያዎችን በተደጋጋሚ እናያለን። እውነታውን እንነጋገር ከተባለ፡ ከእነዚህ የኦንላይን ስራዎች ውስጥ ከ95% በላይ የሚሆኑት የሰዎችን ጊዜ እና ኢንተርኔት የሚበሉ የሐሰት ቅዠቶች ናቸው። በእነዚህ የማይጨበጡ እና አሰልቺ ተግባራት ላይ ውድ ጊዜህን ከምታባክን፣ ያንን ሰዓት እውነተኛ፣ ተፈላጊ እና ህይወትን የሚቀይር የዲጂታል ክህሎት ለመማር ብታውለው የነገ ማንነትህን ሙሉ በሙሉ መቀየር ትችላለህ። ለዚህ ደግሞ የመጀመሪያው እና ዋነኛው አማራጭህ ዌብ ዴቨሎፕመንት (Web Development) ነው። ይህ ሙያ ድረ-ገጾችን እና የተለያዩ ሲስተሞችን በኮዲንግ ወይም No-Code በሆኑ ቀላል መሳሪያዎች መገንባትን ያጠቃልላል አሁንማ AI አለ የ prompt እውቀት ካላችሁ። ዛሬ እያንዳንዱ ድርጅት፣ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል ወይም የንግድ ተቋም የራሱ ድረ-ገጽ ስለሚያስፈልገው ፣ ክህሎቱን ካዳበርክ ለአገር ውስጥ ተቋማት ዌብሳይት በመስራት ወይም በአለምአቀፍ ደረጃ በሪሞት (Remote) ስራ በዶላር መከፈል ትችላለህ። ይሁንና እውቀቱ ካለህና ከፍ ካየር በሰው በሰው ስር ከመቀጠር ባለፈ የራስህን የቴክኖሎጂ ስታርትአፕ (Startup) ወይም የዌብ ሳይት ልማት ድርጅት በመክፈት ራስህን የቢዝነስ ባለቤት ማድረግ ትችላለህ።

​"ከየት ልጀምር?" የሚል ጥያቄ በቴክኖሎጂ ጉዞ ላይ እንቅፋት ሆኖባችኋል? 🚀💡 ​ በየቀኑ በሚፈጠሩ አዳዲስ የፕሮግራም አወጣጥ ቋንቋዎች (Programming Languages) እና በፍጥነት በሚቀያየሩ የቴክኖሎጂ አዝማሚያዎች መካከል መደናገር የተለመደ ነው። ነገር ግን፣ ያለ ግልጽ መንገድ መጓዝ ጊዜን እና ጉልበትን ያባክናል።😡 ​ለዚህ ነው በጣም የሚመቸኝን እና ሌሎችም የቴክኖሎጂ ቤተሰቦች ቢያውቁት የምለውን roadmap. sh መድረክን ልጠቁማችሁ የምፈልገው! ​ይህ ድረ-ገጽ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን የምትፈልጉ ወገኖች በሙሉ ሊያውቁት የሚገባ "የስኬት ካርታ" ነው። ​ለምን ይህንን መድረክ መጠቀም አስፈለገ? ​ግልጽ አቅጣጫ (Structured Learning): Frontend፣ Backend፣ AI/ML፣ DevOps፣ ወይም Mobile App Development... የፈለጉትን ዘርፍ ብትመርጡ፣ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ መከተል ያለባችሁን የክህሎት ደረጃዎች በቅደም ተከተል ያስቀምጣል በጣም በተደራጀ እና በተጠና ሁኔታ። ይህን ለአዘጋጁ በሙሉ ትልቅ አክብሮት አለኝ 👏👏👏 ​ የተመረጡ ማጣቀሻዎች (Curated Resources): በእያንዳንዱ ደረጃ ምን መማር እንዳለባችሁ ከመንገር ባለፈ፣ ለዚያ ርዕስ ምርጥ የሚባሉ የቪዲዮ እና የጽሁፍ መማሪያዎችን (Tutorials) ያቀርባል። ​ የሂደት መከታተያ (Progress Tracking): አካውንት በመክፈት የተማራችሁትን እየመረጣችሁ፣ የት እንደደረሳችሁ በዝርዝር መከታተል ትችላላችሁ። ቴክኖሎጂን መማር "ማራቶን" እንጂ "ስፕሪንት" (የአጭር ጊዜ ሩጫ) አይደለም። roadmap. sh ላይ ያሉትን ሁሉንም በአንድ ጊዜ ለመጨረስ አትሞክሩ ትርጉም የለውም መሆን የምትፈልጉትንም አትሆኑም። በአንድ መንገድ ላይ አተኩሩ አንድ ሰው ሁሉንም መሆን ስለማይችል፣ በደንብ ተለማመዱ፣ ከዚያም ወደ ቀጣዩ ተሸጋገሩ። ​ዛሬውኑ ጉዞአችሁን ጀምሩ: 👉 roadmap.sh ​ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት፣ እነሱንም ከግራ መጋባት እንታደጋቸው። አብረን እናድግ! 💻✨ ድረ -ገጹን ከጎበኛችሁ በኋላ ሀሳባቸሁን ሼር ብታደርጉኝ ደስ ይለኛል?

photo content

የ Digital Marketing እውቀት አስፈላጊነት በዚህ ወቅት አጠያያቂ አይደለም! ብዙ ነገር ወደ ዲጀታል እያመራ አይደል! HubSpot ሀሪፍ መማሪያ ቦታ ነው ፤ ያልወስዳችሁ ብትወስዱት ቆንጆ ነ
የ Digital Marketing እውቀት አስፈላጊነት በዚህ ወቅት አጠያያቂ አይደለም! ብዙ ነገር ወደ ዲጀታል እያመራ አይደል! HubSpot ሀሪፍ መማሪያ ቦታ ነው ፤ ያልወስዳችሁ ብትወስዱት ቆንጆ ነው እላለሁ። Link 👇 HubSpot

ኮዲንግ ኮምፒውተርን ማዘዝ ብቻ ሳይሆን፣ ውስብስብ ችግሮችን በሎጂክ የመፍታት ክህሎትን ያዳብራል።

AI ኮድ እየፃፈ ስለሆነ ኮዲንግ መማር አያስፈልግም ምን ሊረባ ? ትልቅ ❌ ነው። አሁንም ውጤታማ የሚሆኑት ያወቁት ናቸው።

"በ AI ሙሉ ዌብሳይት ሰራሁ" የሚሉ ፖስቶችን ስናይ ብዙዎቻችን ChatGPT ወይም Claude ላይ ሄደን "ለካፌ አገልግሎት ሽያጭ የሚውል አፕ ስራልኝ" እንላለን። ቦቶቹ ግን የኮድ ናዳ ያዘንቡብናል እንጂ ክሊክ ተደርጎ የሚከፈትና ወዲያው የሚሰራ መተግበሪያ አይሰጡንም በእርግጥ ቅድመ–እይታ የሚያሳዩን አሉ። ለመሆኑ እውነታው ምንድነው? እውነታው የ AI መሳሪያዎች በአሁኑ ሰዓት በሁለት ትልልቅ ጎራ መከፈላቸው ነው፦ ❌ 1. መደበኛ ቻት ቦቶች (ChatGPT, Claude Chat, Gemini, Xai, DeepSeek)፦ እነዚህ ቦቶች ልክ እጅና እግር እንደሌለው "በጣም ጎበዝ መሐንዲስ" ናቸው። Frontend እና Backend ኮዱን ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ነገር ግን ያንን ኮድ ኮምፒውተራችን ላይ ፋይል ፈጥሮ የመለጠፍ (Paste)፣ እርስ በእርስ የማገናኘት እና ለተጠቃሚ ዝግጁ አድርጎ የማውጣት አቅም የላቸውም። እኛ መሃል ላይ ገብተን ወደ IDE (Integrated Development Environment ) like:- VS Code ላይ ኮዱን ኮፒ-ፔስት ካላደረግንላቸው ዝም ብሎ ጽሑፍ ብቻ ናቸው። ✅ 2. የዘመኑ AI Coding Agents (Bolt.new, Cursor, Windsurf, GitHub Copilot, Android AI Studio)፦ አሁን ላይ ጨዋታውን የቀየሩት እነዚህ ናቸው! ለምሳሌ Bolt.new ላይ በፅሁፍ ብቻ ስታዙት፣ እራሱ Frontend እና Backend ፋይሎችን ይከፍታል፣ ኮዱን ይለጥፋል፣ ሰርቨር አስነስቶ አፑ ሲሰራ ምን እንደሚመስል (Preview) ያሳያችኋል፤ በመጨረሻም በአንድ ክሊክ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነ (Production-ready) ሊንክ ይሰጣችኋል። Cursor እና GitHub Copilot ደግሞ ኮምፒውተራችሁ ላይ ያሉ ፋይሎች ውስጥ ገብተው እራሳቸው ኮዱን ይፅፋሉ፣ ያሻሽላል። ሲጠቃለል ቻት ቦቶች ኮዱን ያዘጋጃሉ፤ ስራ ላይ ለማዋል ግን የእኛ የእጅ ስራ ያስፈልጋቸዋል። AI Agents ግን ሙሉ ስራውን ሰርተው ለአጠቃቀም የበቃ ሶፍትዌር ያስረክባሉ ከነስስታቸው እና ችግራቸው እነሱም ቢሆኑ የሰጡህን መልሰው አጥፍተው ሲያደናብሩን ይውላሉ። በሌላ አባባል አሁንም ቦሆንም መሰረታዊ እውቀት ከሌለን እጅግ ፈታኝ ነው። በዘርፉ ፍላጎት ያላችሁ አሁንም ከ አኤአይ እገዛው ጎን ለጎን መሰረታዊ እውቀቱን ተማሩ ምክሬ ነው። አሁንም ነጻ በሚሰጡን ቶክን ውስብስብ ሶፍትዌሮችን መጨረስ ራሱ ከባድ እና ሌላ ራስ ምታት ነው ፤ ለቀላል ታስክ የሚያገለግሉ ልንጨርስ እንችላለን። እያወሳሰብኩት አይደለም በ 0 ኮዲንግ እውቀት መስራት አይቻልም እያልኩም አይደለም በዘርፉ ተወዳዳሪ እና ውጤታማ ለመሆን Foundation እውቀት መሰረት እና ሁሌም የማይሻር ነው። እይታዬ ነው! የእናንተን እይታ አካፍሉን? ለመማማር እና ውጤታማ ለመሆን በማሰብ ያዘጋጀሁት ነው፡፡ ❓ እናንተስ አሁን ላይ በ AI ኮዲንግ እያገዛችሁ ነው? የትኛውን መሳሪያ (Tool) ይበልጥ ወደዳችሁት? ሃሳባችሁን የውይይት መስጫው ላይ አጋሩን👇

AI ኮድ ይጽፋል ሲባል "ዝም ብሎ ፅሁፍ" ነው ወይስ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነ ሶፍትዌር? 🤖💻
AI ኮድ ይጽፋል ሲባል "ዝም ብሎ ፅሁፍ" ነው ወይስ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነ ሶፍትዌር? 🤖💻

ነጻ መተግበሪያዎች እና የተደበቀው የውሂብ ዋጋ! 📱⚠️ ​ ብዙዎቻችሁ Truecallerን ስትጠቀሙ የምታዩት ጥቅሙን ብቻ ነው። "ማነው የደወለው?" የሚለውን ጥያቄ በመመለሱ እና አይፈለጌ ጥሪዎችን (Spam calls) በመዝጋቱ ረገድ እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ ይወደዳል። ነገር ግን "ለምን ይህ አገልግሎት ነጻ ሆነ?" ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? ​ የእውነት እንነጋገር ከተባለ፡ Truecaller ነጻ አይደለም፤ ክፍያው በእናንተ እና በእውቂያዎቻችሁ (Contacts) መረጃ ነው! ​ እንዴት ይሰራል? ​የእናንተ መረጃ፡ መተግበሪያውን ስትከፍቱ ስለ እናንተ ማንነት ሙሉ መረጃ ይወስዳሉ። ​ የሌሎች መረጃ፡ ትልቁ ጉዳይ ያለው እዚህ ላይ ነው። Truecaller በእናንተ ስልክ ውስጥ ያሉትን ኮንታክቶች በሙሉ "ይቀዳል።" ማለትም፣ መተግበሪያውን የማይጠቀሙ የጓደኞቻችሁ፣ የቤተሰባችሁ እና የሥራ ባልደረቦቻችሁ ስም እና ቁጥር ሳይቀር ወደ ዳታቤዛቸው ይገባል። ​ ነዳጅ ለኢንዱስትሪው፡ ይህ የተሰበሰበው ትልቅ መረጃ (Big Data) ለድርጅቱ እንደ ነዳጅ ያገለግላል። ይህንን መረጃ ለተለያዩ ዓላማዎች ይጠቀሙበታል፦ ​ 🚩 ለማስታወቂያ: ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ለመላክ። 🚩 ​ለጥናት እና ስለላ: የሰዎችን ባህሪ ለመከታተል። 🚩 ​ለማጭበርበር (Scammers): መረጃው መጥፎ ዓላማ ላላቸው ሰዎች ሊጋለጥ የሚችልበት ከፍተኛ ዕድልም አለ። ቴክኖሎጂን ስትጠቀሙ ሁሌም አንድ ነገር አስታውሱ፤ "አንድ አገልግሎት በነፃ እያገኛችሁ ከሆነ፣ የድርጅቱ ምርት እናንተ (ወይም መረጃችሁ) ነው።" ​ በዲጂታል ዓለም ውስጥ ግላዊነታችሁ ዋጋ አለው። ውሳኔያችሁን በጥንቃቄና አውቃችሁት ውሰዱ! AIን እዚህ ያደረሰው መረጃ ነው! True Caller እንደምሳሌ አነሳሁት እንጂ ሌሎችም ከ privacy አንጻር ጥያቄ የሚነሳባቸው በርካታ መተግበሪያዎች አሉ! ​ 💬 ስለዚህ ጉዳይ ምን ታስባላችሁ? መረጃችሁን ለደህንነት ሲባል እየሰጣችሁ ነው ወይስ የግላዊነት ጥሰት እንደሆነ ይሰማችኋል? ሃሳባችሁን በኮሜንት ላይ አጋሩን ​#TechPrivacy #DataSecurity #Truecaller

መረጃ ሀብት ነው 👇
መረጃ ሀብት ነው 👇

1K ቤተሰብ ደርሰናል አብራችሁን ስላላችሁ እና ስለ ድጋፋችሁ ከልብ ❤️ አመሰግናለሁ! ሊንኩን ሼር በማድረግ ልትደግፉኝ ትችላላችሁ! https://t.me/miftahcode

-2147483648_-210302.webp0.29 KB

አዲሱ የChatGPT የድምፅ (GPT-Live) ተለቋል! 🎙️✨ ​ከአሁን በኋላ ከChatGPT ጋር የሚኖረን ውይይት እንደ ማሽን ሳይሆን፣ እንደ ሰው ተፈጥሯዊ ይመስላል ተብሏል። ​✅ ምን አዲስ ነገር አለው? • Full-Duplex: እየተናገርን ማቋረጥ ወይም መደራረብ እንችላለን። • የበለጠ ተፈጥሯዊ: የሰው ልጅን የማመንታትና የማዳመጥ ባህሪን ይጋራል፤ በአፍታ መቆራረጦች አይዘናጋም። • በቅጽበት የመተርጎም እና ውስብስብ መረጃዎችን የማቅረብ አቅም አለው። ​ከዛሬ ጀምሮ በiOS፣ በአንድሮይድ እና በድረ-ገጽ ላይ ሞክሩት! 🚀 ​#ChatGPT #GPTLive #AI #TechInnovation #OpenAI #EthiopiaTech

OpenAI እና Anthropic ጠንካራ ተፎካካሪ ገጠማቸው! በቻይና Z.AI የተለቀቀው GLM-5.2 ሞዴል የ AI ውድድሩን እየቀየረ ነው። • ከምዕራባውያን ሞዴሎች በ5-7 እጥፍ ያነሰ ዋጋ መኖሩ •
OpenAI እና Anthropic ጠንካራ ተፎካካሪ ገጠማቸው! በቻይና Z.AI የተለቀቀው GLM-5.2 ሞዴል የ AI ውድድሩን እየቀየረ ነው። • ከምዕራባውያን ሞዴሎች በ5-7 እጥፍ ያነሰ ዋጋ መኖሩ • የአሜሪካ ካምፓኒ ቺፕ ሳይጠቀም በራሷ በቻይና (Huawei Ascend ብቻ) የተሰራ እና ለሁሉም ክፍት መሆኑ ውድድሩን የተቀላቀለ ሲሆን የአሜሪካ ኩባንያዎችን አስደንግጧል። በተለይም በኮድ አፃፃፍ (coding) እና ውስብስብ የሆኑ ስራዎችን በራስ-ገዝ በመስራት (agentic capabilities) ችሎታው ከፍተኛ አድናቆትን እያገኘ ነው። ሞክሩት 😍👇https://chat.z.ai/

ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላችሁ ስራ ፈጣሪዎች እድል ይዞ መጥቷል! ​ሃሳባችሁን ወደ ተጨባጭ ምርት (MVP) ለመቀየር የምትፈልጉ፣ በኢኖቢዝ-ኬ (Innobiz-K) 🇪🇹
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላችሁ ስራ ፈጣሪዎች እድል ይዞ መጥቷል! ​ሃሳባችሁን ወደ ተጨባጭ ምርት (MVP) ለመቀየር የምትፈልጉ፣ በኢኖቢዝ-ኬ (Innobiz-K) 🇪🇹 ኢንኩቤሽን ማዕከል አማካኝነት የቴክኖሎጂ ድጋፍ በነጻ ማግኘት ትችላላችሁ። ሀሳብ ያላችሁ እና ይህን እድል መጠቀም የምትፈልጉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ ተመዝገቡ። 👇 Registration Link

ኢኮደርስን በተመለከተ ፡ ዛሬም አዲስ Application እየተቀበለ አይደለም ። እንደሚታወቀው ቁጥሩ ከ 5 ሚሊዮን ወደ 7 ሚሊዮን ያደገ ቢሆንም ኮርሱን የሚያቀርበው Udacity እስከ አሁን አዲስ
ኢኮደርስን በተመለከተ ፡ ዛሬም አዲስ Application እየተቀበለ አይደለም ። እንደሚታወቀው ቁጥሩ ከ 5 ሚሊዮን ወደ 7 ሚሊዮን ያደገ ቢሆንም ኮርሱን የሚያቀርበው Udacity እስከ አሁን አዲስ ምዝገባ እየተቀበለ አይደለም። ቁጥሩ መጨመሩን መንግስትም በ Ministry of Innovation and Technology - Ethiopia በኩል ይፋ አድርጓል። አንዳንድ ነገሮች ተስተካከለው ወደ ስራ እስከሚመለስ በትዕግስት ተጠባበቁ። አዲስ Application መቀበል እንደጀመረ ኢንሻአላህ መረጃ ሼር ስለማደርጋችሁ እስከዚያው ከዚህ በፊት ሼር ሳደርጋቸው የነበሩ እና ሌሎች ነፃ የኦላይን ኮርሶችን ተከታተሉ። Stay Connected 🥰

ብያችሁ ነበር ! 😱
ብያችሁ ነበር ! 😱

ማሽኖች መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔው የሰው መሆን አለበት!" - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ 🚨🤖 ​በጄኔቫ በተካሄደው የመጀመርያው የተባበሩት መንግሥታት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አስተዳደር ዓለም አቀፍ ውይይት ላይ፣ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በቴክኖሎጂው ዙሪያ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ ቁጥጥር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። ​ዋና ጸሐፊው በንግግራቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡ ​🔹 "ገዳይ ሮቦቶች"፦ ለሰላማዊ አገልግሎት የተፈጠሩ ኃይለኛ የAI ቺፖች ወደ ጦር ሜዳ እየገቡ መሆናቸው አደገኛ አዝማሚያ መሆኑን ገልጸዋል። በራስ ገዝ የሚንቀሳቀሱ "ገዳይ ሮቦቶች" በአሁኑ ወቅት የተለመዱ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ የዓለም መንግሥታት የቴክኖሎጂውን አጠቃቀም በሕግ ሊገድቡ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል። ​🔹 የሕጻናት ደህንነት ቅድሚያ ይስጠው፦ "ምንም ሕጻን ለተቆጣጠርነው የAI ቴክኖሎጂ የሙከራ አይጥ መሆን የለበትም" ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ኩባንያዎች የAI ምርቶቻቸውን ለሕጻናት ከማቅረባቸው በፊት ደህንነታቸው የተረጋገጠ መሆኑን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል። በተለይም ሕጻናትን የሚያካትቱ የወሲብ ይዘቶች ላይ "ዜሮ መቻቻል" (Zero Tolerance) ሊኖር እንደሚገባ አስምረውበታል። ​🔹 የሰው ልጅ ውሳኔ፦ AI በፍትህ፣ በጤና እና በፖሊስ ዘርፎች መረጃ ሊሰጥ ቢችልም፣ የመጨረሻው ውሳኔ ሰጪና ተጠያቂ የሰው ልጅ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። ​🔹 የዲጂታል ክፍፍልን ማጥበብ፦ AI የሀብታሞች ብቻ መሆን የለበትም። በማደግ ላይ ያሉ አገራት የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዓለም አቀፍ የትብብር መረብ እንዲቋቋም ጥሪ አቅርበዋል። ​🔹 አካባቢ ጥበቃ፦ በ2030 ሁሉም የAI መረጃ ማዕከላት (Data Centres) በታዳሽ የኃይል ምንጭ እንዲሰሩ ጉቴሬስ ጥሪ አቅርበዋል። ​ቴክኖሎጂው ለሰው ልጅ ትልቅ ዕድል ቢሆንም፣ በአግባቡ ካልተያዘ ግን አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተመልክቷል። ​ለበለጠ መረጃ እና ዝርዝር ጉዳዮች፣ ይህንን የUN News ሊንክ ይመልከቱ፡ https://news.un.org/en/story/2026/07/1167873

ማሽኖች መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔው የሰው መሆን አለበት!" - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ
ማሽኖች መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔው የሰው መሆን አለበት!" - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ