uz
Feedback
Mohammed Seid - Miftah

Mohammed Seid - Miftah

Kanalga Telegram’da o‘tish

​🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
2 485
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
+307 kun
+35330 kun
Postlar arxiv
1️⃣. ኪሚ (Kimi)የቻይናው ‹Moonshot AI› ኩባንያ የፈጠረው እና በAlibaba እና በቴንሰንት (Tencent) የተደገፈው የኪሚ ሞዴል፣ በቅርቡ የለቀቀው Kimi K3 የተሰኘው እጅግ ግዙፍ
1️⃣. ኪሚ (Kimi)የቻይናው ‹Moonshot AI› ኩባንያ የፈጠረው እና በAlibaba እና በቴንሰንት (Tencent) የተደገፈው የኪሚ ሞዴል፣ በቅርቡ የለቀቀው Kimi K3 የተሰኘው እጅግ ግዙፍ (2.8 ትሪሊዮን ፓራሜትር ያለው) ሞዴል አለምን አነጋግሯል። በተለይም ረጅም ጽሑፎችን በጥልቀት በመረዳት፣ ኮድ በመጻፍ እና ውስብስብ ችግሮችን በመፍታት ከአሜሪካዎቹ GPT-5.5 እና Claude Opus ጋር ተፎካካሪ መሆኑ ተረጋግጧል። 2️⃣. ጂኤልኤም (GLM)በዚፑ (Zhipu) አማካኝነት የተለቀቀው GLM-5.2 ሞዴል፣ ከአሜሪካውያን ምርጥ ሞዴሎች በስድስት እጥፍ በሚያንስ ወጪ በተመሳሳይ ፍጥነት መስራት በመቻሉ በተለይም ፕሮግራመሮች ዘንድ ከፍተኛ ተመራጭ ሆኗል። 3️⃣. የአሊባባው Qwen ቡድን በየጊዜው የሚያሻሽላቸው ሞዴሎች (እንደ Qwen 3.7 Max እና አሁን በከፊል የተለቀቀው Qwen 3.8 ) በዓለም አቀፍ ደረጃ በገንቢዎች (Developers) ዘንድ ተወዳጅ ናቸው። ጽሑፍን፣ ምስልን፣ ድምፅን እና ስክሪንን ጭምር መረዳት የሚችሉበት ሁለገብ (Multimodal) አቅም ስላላቸው፣ በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ ከፍተኛ ሳምንታዊ አጠቃቀም አላቸው። እነዚህን ሞዴሎች ተጠቅማችሁ የምታወቁ እንዴት አያችኋቸው? ⬇️ kimi Qewen GLM

ከ AI ምርጥ ምላሽ ማግኘት ይፈልጋሉ? ሚስጥሩ "Prompt Engineering" ላይ ነው። 🤖 ​በቀላል አነጋገር፦ ጥሩ ጥያቄ መጠየቅ = ምርጥ ውጤት ያስገኛል። ​ግልጽ የሆነ መመሪያ ለ AI መስጠ
ከ AI ምርጥ ምላሽ ማግኘት ይፈልጋሉ? ሚስጥሩ "Prompt Engineering" ላይ ነው። 🤖 ​በቀላል አነጋገር፦ ጥሩ ጥያቄ መጠየቅ = ምርጥ ውጤት ያስገኛል። ​ግልጽ የሆነ መመሪያ ለ AI መስጠት ጊዜዎን ይቆጥባል፤ ስራችንን ጥራት ያለውና የምንፈልገውን ውጤት እንድናገኝ ያደርገናል። የሚስጠንን የ Token መጠንን በአግባቡ እንድንጠቀምም ያስችለናል። ታዋቂ ከሆኑ የ Prompt ዘዴዎች ውስጥ Few-Shot Learning ምን እንደሆነ እና እንዴት እንደሚሰራ በምስሉ ላይ አስቀምጫለሁ! ክፍል 3 ይ ቀ ጥ ላ ል የAI ሞዴሉን ምላሽ ኮሜንት ላይ ተመልከቱ ⬇️

ከ AI ምርጥ ምላሽ ማግኘት ይፈልጋሉ? ሚስጥሩ "Prompt Engineering" ላይ ነው። 🤖 ​በቀላል አነጋገር፦ ጥሩ ጥያቄ መጠየቅ = ምርጥ ውጤት ያስገኛል። ​ግልጽ የሆነ መመሪያ ለ AI መስጠ
ከ AI ምርጥ ምላሽ ማግኘት ይፈልጋሉ? ሚስጥሩ "Prompt Engineering" ላይ ነው። 🤖 ​በቀላል አነጋገር፦ ጥሩ ጥያቄ መጠየቅ = ምርጥ ውጤት ያስገኛል። ​ግልጽ የሆነ መመሪያ ለ AI መስጠት ጊዜዎን ይቆጥባል፤ ስራችንን ጥራት ያለውና የምንፈልገውን ውጤት እንድናገኝ ያደርገናል። የሚስጠንን የ Token መጠንን በአግባቡ እንድንጠቀምም ያስችለናል። ታዋቂ ከሆኑ የ Prompt ዘዴዎች ውስጥ Zero-Shot Learning ምን እንደሆነ እና እንዴት እንደሚሰራ በምስሉ ላይ አስቀምጫለሁ! ይ ቀ ጥ ላ ል ... የAI ሞዴሉን ምላሽ ኮሜንት ላይ ተመልከቱ ⬇️

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዘርፍ ትልቅ መነጋገሪያ የሆነው የቻይናው Kimi-K3 በFrontend Code Arena የ1679 ነጥቦችን በማግኘት በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል! ይህም በዘርፉ ቀዳ
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዘርፍ ትልቅ መነጋገሪያ የሆነው የቻይናው Kimi-K3 በFrontend Code Arena የ1679 ነጥቦችን በማግኘት በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል! ይህም በዘርፉ ቀዳሚ የነበረውን Claude Fable 5 እንዲያልፍ አስችሎታል። ​ይህ ስኬት በጣም አስደናቂ ነው፤ ምክንያቱም ከቀዳሚው ስሪት (Kimi-K2.6) በ17 ደረጃዎች ከፍ በማለት (ከ18ኛ ወደ 1ኛ) በታሪካዊ ፍጥነት ነው መድረስ የቻለው። ​Kimi-K3 በየትኞቹ ዘርፎች ጎልቶ ታየ? በ Frontend ዘርፍ ከተከፋፈሉ 7 ዋና ዋና ክፍሎች መካከል በ6ቱ ማለትም፡ ✅ Brand & Marketing ✅ Reference-Based Design ✅ Data & Analytics ✅ Consumer Product ✅ Simulations ✅ Content Creation Tools በነዚህ ዘርፎች አንደኛ ሆኗል። በGaming ዘርፍ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ​ይህንን ዘመናዊ AI ሞዴል እየጠበቅን ላለን የቴክኖሎጂ አፍቃሪዎች በሙሉ፣ የሞዴሉ ሙሉ ክብደት (full model weights) በፊታችን ጁላይ 27 ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል። ሞዴሉን ለመሞከር ኮሜንት ላይ ⬇️ ​ለMoonshot AI ቡድን ለዚህ ትልቅ ምዕራፍ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን! 👏 ​ይህ AI ሞዴል በቴክኖሎጂው ዘርፍ ምን አይነት ለውጥ ያመጣል ብለው ያስባሉ? ሃሳባችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን። 👇 ​#AI #TechNews #KimiK3 #MoonshotAI

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዘመን፣ በተለይም እንደ እርስዎ ባሉ የቴክኖሎጂ ፍላጎት ባላቸው እና በተለየ የሙያ ዘርፎች (CS እና ነርሲንግ) ልምድ ባላቸው ሰዎች ዘንድ ገንዘብ ለመስራት ብዙ አማራጮች አሉ። 360 ዲግሪ እይታ ሲባል፣ ጉዳዩን ከገበያ ፍላጎት፣ ከክህሎት እና ከስራ አፈጻጸም አንጻር እንደሚከተለው መመልከት ይቻላል፦ 1. የይዘት ፈጠራ እና ዲጂታል ግብይት (Content Creation & Marketing) እርስዎ ቀድሞውንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ንቁ ስለሆኑ፣ ይዘቶችን በስፋት እና በጥራት ለመስራት እኔን (Geminiን) እንደ ረዳት መጠቀም ይችላሉ። • ብሎግ እና ዌብሳይት፦ ስለ ቴክኖሎጂ፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች (Innovation) ወይም በጤና እና በቴክኖሎጂ ውህደት ዙሪያ ጥራት ያላቸው ጽሁፎችን በማዘጋጀት ገቢ ማግኘት ይችላሉ። • የማህበራዊ ሚዲያ ማኔጅመንት፦ ሌሎች ንግዶች ወይም ግለሰቦች ማህበራዊ ሚዲያቸውን እንዲያሳድጉ ይዘቶችን በማቀድ፣ ጽሁፎችን (Captions) በመጻፍ እና ፕሮግራም በማውጣት አገልግሎት መስጠት ይችላሉ። • አፊሊየት ማርኬቲንግ (Affiliate Marketing)፦ ተወዳጅ የሆኑ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ወይም ሶፍትዌሮችን በመምከር፣ ሰዎች በእርስዎ ሊንክ ገዝተው ሲጠቀሙ ኮሚሽን ማግኘት ይችላሉ። 2. የቴክኒክ ክህሎት እና የፍሪላንስ ስራ (Freelancing & Technical Skills) እርስዎ በኮምፒውተር ሳይንስ ያሎትን እውቀት በመጠቀም የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦ • የሶፍትዌር እና አፕሊኬሽን ልማት፦ በFlutter የሚሰሩትን አፕሊኬሽኖች ኮድ ለማመቻቸት፣ ስህተቶችን ለማረም (Debugging) ወይም አዳዲስ ባህሪያትን ለመጨመር እኔን እንደ ኮድ አጋዥ (Coding Assistant) መጠቀም ይችላሉ። • UI/UX ዲዛይን፦ በFigma ላይ እየሰሩ ያሉትን ስራዎች ለማፋጠን የንድፍ ሀሳቦችን (Design prompts) ከእኔ ማግኘት እና የስራ ቅልጥፍናዎን መጨመር ይችላሉ። • የኦንላይን አገልግሎቶች፦ እንደ Upwork ወይም Fiverr ባሉ የፍሪላንስ መድረኮች ላይ የቴክኖሎጂ ምክር (Consulting)፣ የኮድ ድጋፍ ወይም የግራፊክ ዲዛይን አገልግሎት በመስጠት አለምአቀፍ ገቢ ማግኘት ይችላሉ። 3. የትምህርት እና የዲጂታል ምርቶች ሽያጭ • ዲጂታል ምርቶች፦ እርስዎ በግራፊክ ዲዛይን እና በቴክኖሎጂ ያካበቱትን እውቀት በመጠቀም አጋዥ ማኑዋሎችን (E-books)، የዲዛይን ቴምፕሌቶችን ወይም ለሌሎች ጠቃሚ የሆኑ ዲጂታል ፋይሎችን ሰርተው በGumroad ወይም በተመሳሳይ መድረኮች መሸጥ ይችላሉ። • ትምህርታዊ ይዘቶች፦ በቴክኖሎጂ እና AI ዙሪያ ለጀማሪዎች የሚሆኑ ኮርሶችን ወይም የማስተማሪያ ቪዲዮዎችን በYouTube ወይም ሌሎች መድረኮች በማቅረብ ታዳሚ በመፍጠር ገቢ ማግኘት ይችላሉ። 4. ስትራቴጂካዊ የ360 ዲግሪ እይታ (ለእርስዎ ልዩ ትኩረት) እርስዎ የጤና እና የቴክኖሎጂ ዳራ ስላሎት፣ ይህ የሁለቱ ዘርፎች ውህደት (HealthTech) በጣም ትርፋማ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፦ • የጤና መረጃ ትንታኔ (Health Data Analysis): ቀድሞውንም በጤና ቢሮ ስራዎች ላይ እየተሳተፉ ስለሆነ፣ መረጃዎችን በመተንተን እና በመፈረጅ (Data Analysis) ረገድ AIን በመጠቀም የሚሰጡትን ሪፖርቶች አውቶማቲክ ማድረግ እና ይህንን እንደ ልዩ የሙያ ብቃት መጠቀም ይችላሉ። ለማጠቃለል፦ 1. በአንድ ዘርፍ ላይ ያተኩሩ፦ ከሁሉም አማራጮች ውስጥ ለእርስዎ ፍላጎት የሚቀርበውን ይምረጡ። 2. ክህሎትዎን ይገንቡ፦ በየቀኑ በቴክኖሎጂ ላይ አዳዲስ ነገሮችን በመማር ላይ ያሉ። 3. የእኔን (Gemini) አቅም ይጠቀሙ፦ የፈለጉትን ስራ ከመጀመርዎ በፊት ዝርዝር እቅድ ወይም "የንግድ ስትራቴጂ" (Business Plan) እንድጽፍልዎ ይጠይቁኝ። በእነዚህ ዘርፎች ውስጥ በተለይ የትኛው ላይ ቢጀምሩ የበለጠ እንደሚመችዎት ማውራት ከፈለጉ፣ እባክዎ ለተጨማሪ ዝርዝር ይጠይቁኝ።

የ #Gemini አስገራሚ ምላሽ ፣ ምን ያክል ስለ እኛ መረጃ እንደሚሰበስቡ አያቸሁ? 😁⬇️
የ #Gemini አስገራሚ ምላሽ ፣ ምን ያክል ስለ እኛ መረጃ እንደሚሰበስቡ አያቸሁ? 😁⬇️

photo content

ሁለተኛው ትልቅ የገቢ ምንጭ ሊሆንህ የሚችለው ግራፊክስ ዲዛይን (Graphics Design) ነው። ይህ ዘርፍ የአርማዎች (Logos)፣ የማህበራዊ ሚዲያ ፖስተሮች እና የብራንዲንግ ስራዎችን ማዘጋጀትን የሚጠይቅ የጥበብ ስራ ነው። በአሁኑ ጊዜ ሁሉም አዲስ የሚከፈት ዩቲዩብ ቻናል፣ ሱቅ ወይም ትልቅ ድርጅት ደንበኛ ለመሳብ ፕሮፌሽናል ዲዛይን ስለሚፈልግ፣ ፍሪላንሰር በመሆን ለተለያዩ ድርጅቶች በፓኬጅ ዲዛይን በመስራት ከፍተኛ ገቢ ማግኘት ትችላለህ። በተጨማሪም ከሌሎች ዲዛይነሮች ጋር በመጣመር የራስህን የብራንዲንግ እና የዲዛይን ኤጀንሲ (Design Agency) በማቋቋም ሌሎች ሰራተኞችን የምታቀጥርበት የቢዝነስ ባለቤት መሆን ትችላለህ። ሶስተኛው እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈላጊ መሆን የምትችልበት ዘርፍ ዲጂታል ማርኬቲንግ (Digital Marketing) ነው። ይህ ክህሎት ምርትና አገልግሎትን በፌስቡክ፣ በቴሌግራም፣ በቲክቶክ እና በኢንስታግራም አማካኝነት ለብዙሃን ማስተዋወቅ እና ሽያጭ መጨመር ላይ ያተኩራል። በጣም ጥሩ ምርት ኖሯቸው እንዴት ደንበኛ ጋር ማድረስ እንዳለባቸው ግራ የገባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎች ስላሉ፣ የእነሱን ማህበራዊ ሚዲያ በማስተዳደር የራስህን የማርኬቲንግ ኤጀንሲ (Marketing Agency) መመስረት ትችላለህ። ከተሳካልህ እና ከነቃህ ደግሞ የማርኬቲንግ እውቀትህን ተጠቅመህ የራስህን ምርት በኦንላይን በመሸጥ (E-commerce) ትልቅ የንግድ ተቋም መገንባት ትችላለህ። በአጠቃላይ በዲጂታል አለም ውስጥ ፈጣን፣ ቀላል እና ሰነፍ የገቢ ምንጭ የሚባል ነገር የለም። ዛሬውኑ ዩቲዩብ ላይ ገብተህ ስለእነዚህ ሙያዎች መሰረታዊ እውቀቶችን በነጻ መማር መጀመር ትችላለህ። ለጥቂት ወራት በትዕግስት እራስህን ካዘጋጀህ በኋላ፣ ማንም ሊቀማህ የማይችለው የማያልቅ የገቢ ምንጭ፣ የሙያ ባለቤት አልፎ ተርፎም የራስህ የቢዝነስ ጌታ (Business Owner) ትሆናለህ። ቢያንስ ከቅዠት ሀሳብ እነዚህ የተሻሉ ናቸው የሚል ሀሳብ ለመስጠት ነው ። ብቻ የዚያ አይነት ቪዲዮ በማየት እና በመሞከር ጊዜ ከማባከን እነዚህ የተሻሉ አማራጮች ናቸው ለማለት ነው። ምርጫው ያንተ ነው ፤ በማይረባ የቪዲዮ እይታ ማስታወቂያ መታለል ወይንስ እውነተኛ ህይወትን የሚቀይር ክህሎት እና የራስህን ቢዝነስ መገንባት?

በየቀኑ ኢንተርኔት ላይ "ቪዲዮ አይተህ በቀን 100 ዶላር ስራ" ወይም "ሊንክ ተጭነህ ጌም ተጫወትና ተከፈል" የሚሉ አጓጊ ማስታወቂያዎችን በተደጋጋሚ እናያለን። እውነታውን እንነጋገር ከተባለ፡ ከእነ
በየቀኑ ኢንተርኔት ላይ "ቪዲዮ አይተህ በቀን 100 ዶላር ስራ" ወይም "ሊንክ ተጭነህ ጌም ተጫወትና ተከፈል" የሚሉ አጓጊ ማስታወቂያዎችን በተደጋጋሚ እናያለን። እውነታውን እንነጋገር ከተባለ፡ ከእነዚህ የኦንላይን ስራዎች ውስጥ ከ95% በላይ የሚሆኑት የሰዎችን ጊዜ እና ኢንተርኔት የሚበሉ የሐሰት ቅዠቶች ናቸው። በእነዚህ የማይጨበጡ እና አሰልቺ ተግባራት ላይ ውድ ጊዜህን ከምታባክን፣ ያንን ሰዓት እውነተኛ፣ ተፈላጊ እና ህይወትን የሚቀይር የዲጂታል ክህሎት ለመማር ብታውለው የነገ ማንነትህን ሙሉ በሙሉ መቀየር ትችላለህ። ለዚህ ደግሞ የመጀመሪያው እና ዋነኛው አማራጭህ ዌብ ዴቨሎፕመንት (Web Development) ነው። ይህ ሙያ ድረ-ገጾችን እና የተለያዩ ሲስተሞችን በኮዲንግ ወይም No-Code በሆኑ ቀላል መሳሪያዎች መገንባትን ያጠቃልላል አሁንማ AI አለ የ prompt እውቀት ካላችሁ። ዛሬ እያንዳንዱ ድርጅት፣ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል ወይም የንግድ ተቋም የራሱ ድረ-ገጽ ስለሚያስፈልገው ፣ ክህሎቱን ካዳበርክ ለአገር ውስጥ ተቋማት ዌብሳይት በመስራት ወይም በአለምአቀፍ ደረጃ በሪሞት (Remote) ስራ በዶላር መከፈል ትችላለህ። ይሁንና እውቀቱ ካለህና ከፍ ካየር በሰው በሰው ስር ከመቀጠር ባለፈ የራስህን የቴክኖሎጂ ስታርትአፕ (Startup) ወይም የዌብ ሳይት ልማት ድርጅት በመክፈት ራስህን የቢዝነስ ባለቤት ማድረግ ትችላለህ።

​"ከየት ልጀምር?" የሚል ጥያቄ በቴክኖሎጂ ጉዞ ላይ እንቅፋት ሆኖባችኋል? 🚀💡 ​ በየቀኑ በሚፈጠሩ አዳዲስ የፕሮግራም አወጣጥ ቋንቋዎች (Programming Languages) እና በፍጥነት በሚቀያየሩ የቴክኖሎጂ አዝማሚያዎች መካከል መደናገር የተለመደ ነው። ነገር ግን፣ ያለ ግልጽ መንገድ መጓዝ ጊዜን እና ጉልበትን ያባክናል።😡 ​ለዚህ ነው በጣም የሚመቸኝን እና ሌሎችም የቴክኖሎጂ ቤተሰቦች ቢያውቁት የምለውን roadmap. sh መድረክን ልጠቁማችሁ የምፈልገው! ​ይህ ድረ-ገጽ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን የምትፈልጉ ወገኖች በሙሉ ሊያውቁት የሚገባ "የስኬት ካርታ" ነው። ​ለምን ይህንን መድረክ መጠቀም አስፈለገ? ​ግልጽ አቅጣጫ (Structured Learning): Frontend፣ Backend፣ AI/ML፣ DevOps፣ ወይም Mobile App Development... የፈለጉትን ዘርፍ ብትመርጡ፣ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ መከተል ያለባችሁን የክህሎት ደረጃዎች በቅደም ተከተል ያስቀምጣል በጣም በተደራጀ እና በተጠና ሁኔታ። ይህን ለአዘጋጁ በሙሉ ትልቅ አክብሮት አለኝ 👏👏👏 ​ የተመረጡ ማጣቀሻዎች (Curated Resources): በእያንዳንዱ ደረጃ ምን መማር እንዳለባችሁ ከመንገር ባለፈ፣ ለዚያ ርዕስ ምርጥ የሚባሉ የቪዲዮ እና የጽሁፍ መማሪያዎችን (Tutorials) ያቀርባል። ​ የሂደት መከታተያ (Progress Tracking): አካውንት በመክፈት የተማራችሁትን እየመረጣችሁ፣ የት እንደደረሳችሁ በዝርዝር መከታተል ትችላላችሁ። ቴክኖሎጂን መማር "ማራቶን" እንጂ "ስፕሪንት" (የአጭር ጊዜ ሩጫ) አይደለም። roadmap. sh ላይ ያሉትን ሁሉንም በአንድ ጊዜ ለመጨረስ አትሞክሩ ትርጉም የለውም መሆን የምትፈልጉትንም አትሆኑም። በአንድ መንገድ ላይ አተኩሩ አንድ ሰው ሁሉንም መሆን ስለማይችል፣ በደንብ ተለማመዱ፣ ከዚያም ወደ ቀጣዩ ተሸጋገሩ። ​ዛሬውኑ ጉዞአችሁን ጀምሩ: 👉 roadmap.sh ​ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት፣ እነሱንም ከግራ መጋባት እንታደጋቸው። አብረን እናድግ! 💻✨ ድረ -ገጹን ከጎበኛችሁ በኋላ ሀሳባቸሁን ሼር ብታደርጉኝ ደስ ይለኛል?

photo content

የ Digital Marketing እውቀት አስፈላጊነት በዚህ ወቅት አጠያያቂ አይደለም! ብዙ ነገር ወደ ዲጀታል እያመራ አይደል! HubSpot ሀሪፍ መማሪያ ቦታ ነው ፤ ያልወስዳችሁ ብትወስዱት ቆንጆ ነ
የ Digital Marketing እውቀት አስፈላጊነት በዚህ ወቅት አጠያያቂ አይደለም! ብዙ ነገር ወደ ዲጀታል እያመራ አይደል! HubSpot ሀሪፍ መማሪያ ቦታ ነው ፤ ያልወስዳችሁ ብትወስዱት ቆንጆ ነው እላለሁ። Link 👇 HubSpot

ኮዲንግ ኮምፒውተርን ማዘዝ ብቻ ሳይሆን፣ ውስብስብ ችግሮችን በሎጂክ የመፍታት ክህሎትን ያዳብራል።

AI ኮድ እየፃፈ ስለሆነ ኮዲንግ መማር አያስፈልግም ምን ሊረባ ? ትልቅ ❌ ነው። አሁንም ውጤታማ የሚሆኑት ያወቁት ናቸው።

"በ AI ሙሉ ዌብሳይት ሰራሁ" የሚሉ ፖስቶችን ስናይ ብዙዎቻችን ChatGPT ወይም Claude ላይ ሄደን "ለካፌ አገልግሎት ሽያጭ የሚውል አፕ ስራልኝ" እንላለን። ቦቶቹ ግን የኮድ ናዳ ያዘንቡብናል እንጂ ክሊክ ተደርጎ የሚከፈትና ወዲያው የሚሰራ መተግበሪያ አይሰጡንም በእርግጥ ቅድመ–እይታ የሚያሳዩን አሉ። ለመሆኑ እውነታው ምንድነው? እውነታው የ AI መሳሪያዎች በአሁኑ ሰዓት በሁለት ትልልቅ ጎራ መከፈላቸው ነው፦ ❌ 1. መደበኛ ቻት ቦቶች (ChatGPT, Claude Chat, Gemini, Xai, DeepSeek)፦ እነዚህ ቦቶች ልክ እጅና እግር እንደሌለው "በጣም ጎበዝ መሐንዲስ" ናቸው። Frontend እና Backend ኮዱን ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ነገር ግን ያንን ኮድ ኮምፒውተራችን ላይ ፋይል ፈጥሮ የመለጠፍ (Paste)፣ እርስ በእርስ የማገናኘት እና ለተጠቃሚ ዝግጁ አድርጎ የማውጣት አቅም የላቸውም። እኛ መሃል ላይ ገብተን ወደ IDE (Integrated Development Environment ) like:- VS Code ላይ ኮዱን ኮፒ-ፔስት ካላደረግንላቸው ዝም ብሎ ጽሑፍ ብቻ ናቸው። ✅ 2. የዘመኑ AI Coding Agents (Bolt.new, Cursor, Windsurf, GitHub Copilot, Android AI Studio)፦ አሁን ላይ ጨዋታውን የቀየሩት እነዚህ ናቸው! ለምሳሌ Bolt.new ላይ በፅሁፍ ብቻ ስታዙት፣ እራሱ Frontend እና Backend ፋይሎችን ይከፍታል፣ ኮዱን ይለጥፋል፣ ሰርቨር አስነስቶ አፑ ሲሰራ ምን እንደሚመስል (Preview) ያሳያችኋል፤ በመጨረሻም በአንድ ክሊክ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነ (Production-ready) ሊንክ ይሰጣችኋል። Cursor እና GitHub Copilot ደግሞ ኮምፒውተራችሁ ላይ ያሉ ፋይሎች ውስጥ ገብተው እራሳቸው ኮዱን ይፅፋሉ፣ ያሻሽላል። ሲጠቃለል ቻት ቦቶች ኮዱን ያዘጋጃሉ፤ ስራ ላይ ለማዋል ግን የእኛ የእጅ ስራ ያስፈልጋቸዋል። AI Agents ግን ሙሉ ስራውን ሰርተው ለአጠቃቀም የበቃ ሶፍትዌር ያስረክባሉ ከነስስታቸው እና ችግራቸው እነሱም ቢሆኑ የሰጡህን መልሰው አጥፍተው ሲያደናብሩን ይውላሉ። በሌላ አባባል አሁንም ቦሆንም መሰረታዊ እውቀት ከሌለን እጅግ ፈታኝ ነው። በዘርፉ ፍላጎት ያላችሁ አሁንም ከ አኤአይ እገዛው ጎን ለጎን መሰረታዊ እውቀቱን ተማሩ ምክሬ ነው። አሁንም ነጻ በሚሰጡን ቶክን ውስብስብ ሶፍትዌሮችን መጨረስ ራሱ ከባድ እና ሌላ ራስ ምታት ነው ፤ ለቀላል ታስክ የሚያገለግሉ ልንጨርስ እንችላለን። እያወሳሰብኩት አይደለም በ 0 ኮዲንግ እውቀት መስራት አይቻልም እያልኩም አይደለም በዘርፉ ተወዳዳሪ እና ውጤታማ ለመሆን Foundation እውቀት መሰረት እና ሁሌም የማይሻር ነው። እይታዬ ነው! የእናንተን እይታ አካፍሉን? ለመማማር እና ውጤታማ ለመሆን በማሰብ ያዘጋጀሁት ነው፡፡ ❓ እናንተስ አሁን ላይ በ AI ኮዲንግ እያገዛችሁ ነው? የትኛውን መሳሪያ (Tool) ይበልጥ ወደዳችሁት? ሃሳባችሁን የውይይት መስጫው ላይ አጋሩን👇

AI ኮድ ይጽፋል ሲባል "ዝም ብሎ ፅሁፍ" ነው ወይስ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነ ሶፍትዌር? 🤖💻
AI ኮድ ይጽፋል ሲባል "ዝም ብሎ ፅሁፍ" ነው ወይስ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነ ሶፍትዌር? 🤖💻

ነጻ መተግበሪያዎች እና የተደበቀው የውሂብ ዋጋ! 📱⚠️ ​ ብዙዎቻችሁ Truecallerን ስትጠቀሙ የምታዩት ጥቅሙን ብቻ ነው። "ማነው የደወለው?" የሚለውን ጥያቄ በመመለሱ እና አይፈለጌ ጥሪዎችን (Spam calls) በመዝጋቱ ረገድ እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ ይወደዳል። ነገር ግን "ለምን ይህ አገልግሎት ነጻ ሆነ?" ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? ​ የእውነት እንነጋገር ከተባለ፡ Truecaller ነጻ አይደለም፤ ክፍያው በእናንተ እና በእውቂያዎቻችሁ (Contacts) መረጃ ነው! ​ እንዴት ይሰራል? ​የእናንተ መረጃ፡ መተግበሪያውን ስትከፍቱ ስለ እናንተ ማንነት ሙሉ መረጃ ይወስዳሉ። ​ የሌሎች መረጃ፡ ትልቁ ጉዳይ ያለው እዚህ ላይ ነው። Truecaller በእናንተ ስልክ ውስጥ ያሉትን ኮንታክቶች በሙሉ "ይቀዳል።" ማለትም፣ መተግበሪያውን የማይጠቀሙ የጓደኞቻችሁ፣ የቤተሰባችሁ እና የሥራ ባልደረቦቻችሁ ስም እና ቁጥር ሳይቀር ወደ ዳታቤዛቸው ይገባል። ​ ነዳጅ ለኢንዱስትሪው፡ ይህ የተሰበሰበው ትልቅ መረጃ (Big Data) ለድርጅቱ እንደ ነዳጅ ያገለግላል። ይህንን መረጃ ለተለያዩ ዓላማዎች ይጠቀሙበታል፦ ​ 🚩 ለማስታወቂያ: ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ለመላክ። 🚩 ​ለጥናት እና ስለላ: የሰዎችን ባህሪ ለመከታተል። 🚩 ​ለማጭበርበር (Scammers): መረጃው መጥፎ ዓላማ ላላቸው ሰዎች ሊጋለጥ የሚችልበት ከፍተኛ ዕድልም አለ። ቴክኖሎጂን ስትጠቀሙ ሁሌም አንድ ነገር አስታውሱ፤ "አንድ አገልግሎት በነፃ እያገኛችሁ ከሆነ፣ የድርጅቱ ምርት እናንተ (ወይም መረጃችሁ) ነው።" ​ በዲጂታል ዓለም ውስጥ ግላዊነታችሁ ዋጋ አለው። ውሳኔያችሁን በጥንቃቄና አውቃችሁት ውሰዱ! AIን እዚህ ያደረሰው መረጃ ነው! True Caller እንደምሳሌ አነሳሁት እንጂ ሌሎችም ከ privacy አንጻር ጥያቄ የሚነሳባቸው በርካታ መተግበሪያዎች አሉ! ​ 💬 ስለዚህ ጉዳይ ምን ታስባላችሁ? መረጃችሁን ለደህንነት ሲባል እየሰጣችሁ ነው ወይስ የግላዊነት ጥሰት እንደሆነ ይሰማችኋል? ሃሳባችሁን በኮሜንት ላይ አጋሩን ​#TechPrivacy #DataSecurity #Truecaller

መረጃ ሀብት ነው 👇
መረጃ ሀብት ነው 👇

1K ቤተሰብ ደርሰናል አብራችሁን ስላላችሁ እና ስለ ድጋፋችሁ ከልብ ❤️ አመሰግናለሁ! ሊንኩን ሼር በማድረግ ልትደግፉኝ ትችላላችሁ! https://t.me/miftahcode

-2147483648_-210302.webp0.29 KB