قَـــنَـــاةُ أُمِّ حَـــفْـــصَـــةَ الـــسَّـــلَـــفِـــيَّـــة
Открыть в Telegram
العَقَباتُ وَالانْكِساراتُ لَيْسَتْ نِهايَةَ الطَّريقِ بَلْ هيَ جُزءٌ مِن رِحْلَةِ النَّجاحِ. እንቅፋቶችና ስብራቶች የመንገዱ መጨረሻ አይደሉም ይልቁንም ወደ ስኬት ከሚያደርሰን ጉዞ አካል ናቸው https://t.me/htt_Aselefy
Больше1 717
Подписчики
+324 часа
+787 дней
+17530 дней
Архив постов
🍂ነገር ሲጠናባቸው 'እኔ ባርያው ነኝ ጥሎ አይጥለኝም ' ይሉ ነበር። ውዱ ነብያችን ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም። እኛም የምር የ አላህ ባሪያው እንሁን እንጁ ጥሎ አይጥለንም አብሽሩ
Repost from قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
' በህይወታችን
ትልቁ ድክመት ተስፋ መቁረጥ ነው።
ህይወት ሁሌም የትግል መድረክ ናት!
ተስፋ ያልቆረጠ የትግሉን መድረክ ያሸንፋል።
መልካም ውሎ
https://t.me/https_Aselefya
አልሐምዱ ሊልላህ‼
⇛ቃላቶቻቸው እንደ ልብስ ሁሉ የጠቀሙን ብዙ ወዳጆች አሉን፣ ሲበርደን ያለብሱናል፣ ሲከፋን ያፅናኑናል፣ ሲደዉሉልን ደህንነት ይሰማናል፣
እነርሱ ነገሮች ሲቀየሩብን አይቀየሩብንም፣
ሁኔታዎች ሲለወጡብን አይለወጡብንም፣
ስናጣም ሆነ ስንቸገር አይርቁንም፣ ግራ ሲገባን ሕይወታችንን መስመር ለማስያዝ ይጨነቁልናል መንገድ ጨልሞብን እያዩ ፊትለፊታችን ብርሃን እንደሆነ ለማሳመን ይከራከሩናል እኛ ተስፋ ቆርጠን እነርሱ እንዳንወድቅ ይገፉናል፣
አላህ ይጠብቅልን ...
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
የጀሀነም በር ጠባቂ መላዒካ ማሊክ ይባላል፡፡
የኔ ሴት አንች ባለፍሽበት የሂወት ውጣውረድ እስካላለፉና አች የቆምሽበት ላይ እስካልቆሙ ድረስ ህመምሽንና ድካምሽን ሊረዱሽ አይችሉም:: ስለዚህ ለማስረዳት አትድከሚ::ሁሉንም ነገር ወደጌታሽ አስጠጊው እሱዘንድ መፍትሄ አታጭም::
Repost from ስለ ቀልባችን
የዱንያ ልጆች አትሁኑ.....!
በኡስታዝ አቡ ሱፍያን አላህ ይጠብቀው!
ስለ ቀልባችን☑️
➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1
🌿 የእርጉዝ ሴት አምሮት በባህሪዋ ላይ ያለው ተፅዕኖ 🌸
📌 የሞሮኮ ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐሊ ፈርኩስ حفظه الله ተጠየቁ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌸 ጥያቄ፦
የሴት አምሮት (الوَحَم) በሴቶች ላይ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰተው እውነተኛ ነገር ነውን? ወይስ ተራ ምናብና ቅዠት ብቻ ነው?
አላህ መልካም ዋጋ ይክፈልዎትና።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌿 መልስ፦
الحمد لله رب العالمين، والصلاة والسلام على من أرسله الله رحمة للعالمين، وعلى آله وصحبه وإخوانه إلى يوم الدين، أما بعد:
የእርጉዝ አምሮት (الوَحَم) በአረብኛ ቋንቋ የታወቀ ቃል ሲሆን፣ እርጉዝ ሴት የምትመኘውንና በዚያ ወቅት የምትፈልገውን ነገር ያመለክታል። ይህም በታዋቂ የአረብኛ መዝገበ ቃላት የተጠቀሰ ትርጉም ነው።
🌿 ነገር ግን ዛሬ ሰዎች ስለ «አምሮት» የሚናገሩት ሌላ ነገር አለ።
እሱም እርጉዝ ሴት አንድን ነገር በጣም ከፈለገች፣ ያ ፍላጎቷ ካልተሟላላት፣ በሆዷ ያለው ልጅም እርሷ የፈለገችውን ነገር የሚመስል ምልክት ወይም ጥቁር ምስል በሰውነቱ ላይ ይዞ ይወለዳል ይጠቁራል የሚለው እምነት ነው።
ይህንን ግን በሸሪዓ ውስጥ መሠረት የሌለው ነገር ነው። እንዲሁም ይህ እምነት በሚታመን የሸሪዓ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን አላውቅም።
🌿 ይህ ነገር በተለይ በሴቶች አንደበት የሚዘወተር እምነት ነው።
እንደዚህ ያለው ነገር በሸሪዓ ውስጥ የታወቀና አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ፣ በዲን ውስጥ የታወቀ ይሆን ነበር፤ ነቢዩ ﷺም ለሰዎች በግልጽና በበቂ ሁኔታ ያስረዱት ነበር። ምክንያቱም ሰዎች ይህንን ጉዳይ በጣም ይፈልጉት ነበር፤ ለሁሉምም የሚመለከት ጉዳይ ነውና።
🌿 ነቢዩ ﷺ የተላኩትን መልዕክት በሙሉ አድርሰዋል፣ አደራውንም በትክክል ተወጥተዋል።
አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ብሏል፦
﴿ٱلۡيَوۡمَ أَكۡمَلۡتُ لَكُمۡ دِينَكُمۡ وَأَتۡمَمۡتُ عَلَيۡكُمۡ نِعۡمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلۡإِسۡلَٰمَ دِينٗاۚ﴾
“ዛሬ ዲናችሁን ለእናንተ ሞልቼላችኋለሁ፤ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ሞላሁ፤ እስልምናንም ለእናንተ ዲን አድርጌ ወደድኩላችሁ።”
📖 [ሱረቱል ማኢዳህ፡ 3]
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌿 ነቢዩ ﷺ መልዕክቱን በሙሉ ማድረሳቸውን እንዲህ ብለው ለሰሐቦቻቸው አረጋግጠዋል፦
«أَلَا هَلْ بَلَّغْتُ؟»
“እኔ መልዕክቱን አድርሻለሁን?”
እነርሱም፦ “አዎን!” አሉ።
እንደገና፦ «أَلَا هَلْ بَلَّغْتُ؟»
“እኔ መልዕክቱን አድርሻለሁን?”
እነርሱም፦ “አዎን!” አሉ።
ከዚያም ነቢዩ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«اللَّهُمَّ اشْهَدْ، فَلْيُبَلِّغِ الشَّاهِدُ الْغَائِبَ»
“አላህ ሆይ! መስክር! እዚህ ያለው ለሌለው ያድርስ።”
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌸 ነገር ግን እርጉዝ ሴት በዚያ ወቅት ልዩ እንክብካቤ አያስፈልጋትምን?
በእርግጥ ያስፈልጋታል። 🌷
ሸይኹ رحمه الله እንደሚገልጹት፣ ሴቷ በዚያ ወቅት ተጨማሪ እንክብካቤ፣ ፍቅር፣ ርኅራኄና ትኩረት ልትፈልግ ትችላለች።
ስለዚህ ባል የባለቤቱን ሁኔታ ሊያስተውል፣ በርኅራኄ ሊያስተናግዳት፣ በተቻለውም መጠን የምትመኘውን ነገር ሊያሟላላት ይገባል። ብለዋል።
🌿 በዚህ ጊዜ እሷን ማስጨነቅ ማለት በእርግዝናዋ ላይ ተጨማሪ ጫና ማስገባት ነው።
ስለዚህ ባል ከባለቤቱ ጋር በመልካም ሁኔታ ይኑር፤ ሁኔታዋንም ያስተውል፤ የሚያስፈልጋትንም ነገር በቻለው መጠን ያሟላላት።
💎 ይህንን ሲያደርግም ከአላህ ዘንድ ምንዳን በመፈለግ ያድርገው።
አላህ سبحانه وتعالى ምንዳን የሚሰጥ ከሁሉ የተሻለ ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌿 ለጀግና ለባሎች የሚሆን ማስታወሻ
ሚስትህ እርጉዝ ስትሆን በሰውነቷ ውስጥ አንድ ሕይወት እየተሸከመች ነው።
ስለዚህ በዚያ ወቅት የምትፈልገውን በማድረግ ደስ ብሎህ አግዛት፤ ድካሟን በርኅራኄ ተመልከት፤ በቃልህም አጽናናት።
🌷 እርግዝናዋ የሚያልፍ ወቅት ነው፤ ነገር ግን በዚያ ወቅት ያሳየኸው ርኅራኄ በልቧ ውስጥ ረጅም ጊዜ ሊቀር ይችላል።
🌿 ትዳር የሚያምረው በደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ አንዱ ሲደክም ሌላው እጁን ሲይዘው ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
اللَّهُمَّ احْفَظْ نِسَاءَ الْمُسْلِمِينَ وَأَجِنَّتَهُنَّ وَارْزُقْهُنَّ الصِّحَّةَ وَالْعَافِيَةَ، وَأَصْلِحْ بُيُوتَهُنَّ، وَاجْعَلْ بَيْنَ الْأَزْوَاجِ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً وَسَكِينَةً.
“አላህ ሆይ! የሙስሊም ሴቶችንና በማህፀናቸው ያሉትን ልጆቻቸውን ጠብቅልነረ፤ ጤናና ደህንነትን ስጣቸው፤ ቤቶቻቸውንም አስተካክልላቸው፤ በባሎችና በሚስቶች መካከልም ፍቅር፣ ምሕረትና ሰላም አድርግላቸው።” 🌸
📌 ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐሊ ፈርኩስ حفظه الله
🇩🇿 አልጀሪያ — 22 ረጀብ 1426ሂ / 17 ኦገስት 2005
🌿 العِلْمُ عِنْدَ اللهِ تَعَالَى 🌿
الحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
⚠️ አስተውሉ❗️
በእስልምና የመጀመሪያው ኸሊፋ ማን ነው?
🍂📚ሶሐቦች ቁርአንን ሌት ተቀን ያነቡታል አይለዩትም፤ በአንድ ቀን ዉስጥ ሙሉ ቁርአንን የሚያኸትሙ አሉ ሁሉ ሲባል ስሰማ ይገርመኝ ነበር።
እንዴት አይደክማቸዉም! እንዴትስ አይሰለቻቸዉም? እንዴትስ ይታመናል? እል ነበር።
📱ዛሬ ላይ ሌትና ቀኑን ሙሉ ሞባይል ላይ ተደፍተን ስንውል ባየሁ ጊዜ ጉዳዩ ትክክልና ቀላልም እንደሆነ ገባኝ። አንድን ነገር የወደደ ሰው ያዘወትረዋል፤ መለየቱም ይከብደዋል።
ኢላሂ…
https://t.me/Asselefya6
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ሰለፍይ ወሰለፍያት እህት ወንድሞች ኢንሻአሏህ ነገ ረቡዕ ምሽት ሙሀደራ ፕሮግራም ይኖረናል ፡፡
⏰"በዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን
➊ ኡስታዝ አቡ ሀሳን
🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል
➋ ኡስታዝ አቡ ሻኪራ
🔖ርዕስ "በሰዓቱ
❸ ኡስታዝ አቡ ኡባይዳ
🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል
❹ ወንድም አቡ ሂበቱላህ
🔖ርዕስ "በሰዓቱ
❺ ኡስታዝ አቡ አመቲ ረህማን
🔖ርዕስ በሰዓቱ
❻ ወንድም አቡ ሹራ
🔖ርዕስ በሰአቱ ይነገራል
❼ ወንድም ኑረድን አቡ ፋሩቅ
🔖ርዕስ "በሰአቱ ይነገራል
❽ ወንድም አቡ ኢምራን
🔖ርዕስ "በሰአቱ ይነገራል
📖ቲላዋ የሚጋብዙ ወንድሞች
🎤ወንድም አቡ ኢምራን
🎤ወንድም አቡ ሀይደር
🎙 የፕሮግራሙ መሪ ወንድም አቡ ማሂ
🗓ቀን እለት ረብዑ ምሽት
⏰ ሰአት
🇪🇹በኢቶ 3:00
🇸🇦በሳዑዲ 9:00
🇵🇸በዱባይ 10:00
ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ሊንክ👇
👇👇👇👇👇
https://t.me/Asselefiyah_Channel
https://t.me/Asselefiyah_Channel
🍂ያስጨነቀሽ ሁሉ ያሳሰበሽ ሁሉ ያስፈራሽ ሁሉ ወጥሮ የያዘሽ ሁሉ ...
ኃጢአትሽን እያረገፈልሽ ነው ለሁሉም ጊዜ አለው ታገሽ።
ጥያቄ ? 📮📮
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።
📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።
የጀነት በር ጠባቂ መላዒካ ረድዋን ይባላል፡፡
Repost from ስለ ቀልባችን
ኢብራሂም ቢን አድሃም رحمه الله እንዲህ ይላሉ፦ በተውበት መስታወት ውስጥ ዘወትር እራስህን ብትመለከት፣ የወንጀል ክፋትና አስቀያሚነት በግልጽ ይታይሃል።
⚠️ አስተውሉ❗️
በቁርአን ውስጥ "ኸሊሉላህ" ተብሎ የተጠራው ነቢይ ማን ነው?
✅:ሶባ ቢላል መስጅድ ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ ላይ የተደረገ ሙሀደራ
🎀 :-በ'ወንዲም 'አቡ ኢምራን ሙራድ( 🕋)
✅ :-ርዕስ: ጥፍጥና ቆራጩ ሞት
〰〰〰〰〰
كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَن زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ
ሊዳመጥ የሚገባው ሙሀደራ 👂
https://t.me/sobabilelmesjide
https://t.me/sobabilelmesjide
Repost from 📚መንሀጅ ሰለፍ የጄነት መንገዴ〰〰📝
ሀቢብቲ 🌻ብትስቂ ብታለቅሽ ህይወት መንገዷን አታቆምም...ነፍስሽን ጭንቀት አታሸክሚያት ከጭንቀትሽ ምንም አታተርፊም ! ከሌሎች ሰዎች የተሻልሽ ለመሆን አታስቢ ነገር ግን መጀመርያ ከነበርሽበት ማንነትሽ የተሻለች ለመሆን ጣሪ !!!
አሏህ ስህተቶችሽን ይቅር ይልሻል ቁስልሽንም ያክምልሻል::ሰዎችግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ቁስልሽ እዳገረሽ ያደርጋሉ::ስለዚህ አብሽሪ ከጌታሽ እዝነት ተስፋ አትቁረጭ
🍂እሱ ያለው ሊሆን…‼️
⊙ ዩሱፍን ሊገድሉት አስበው ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ዩሱፍ አልሞተም። በአላህ ፈቃድ ተረፈ ።
⊙ከሚወደው አባቱ ነጥለውና ከዐይኑ አርቀው እንዲረሳው ብለው ከአገር አስወጡት፤ ጭራሽ የአባቱ ፍቅር ጨመረ። በናፍቆት ብዛትም ዐይኑ ሊጠፋ ደረሰ።
⊙ ባሪያ ሆኖ እንዲቀር ብለው በትንሽ ገንዘብ አሳልፈው ሸጡት፤ ጭራሽ ቤተመንግሥት ገባና ሚንስቴር ሆኖ አረፈው።
.
⊗የሚገርመው ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ቅናትና ምቀኝነት ያቃጠላቸው የገዛ ወንድሞቹ ናቸው።
.
⊕ግና የአላህ መሻት ከሰው ልጅ መሻት በላይ ነውና ምንም ሊያደርጉት አልቻሉም።
የአላህ እጅ ከሌለበት፤ ሰዎች ሁሉ ሊጎዱህ ቢሰባሰቡና ቢያሴሩ ምንም ሊያደርጉህ አይችሉም።
እናም አትዘን ወንድሜ
አትዘኝ እህቴ!!
رعــايــة الــقـلــوب
🎙:-ሁለተኛው 2️⃣ኛው ፕሮግራማችን ቀጥታ ስርጭት 😂😘
ተ
ጀ
መ
ረ
በኡስታዝ አቡ ኢምራን 🕋
ርዕስ :-ጥፍጥና ቆራጩ ሞት
ገባ ገባ በሉ ሊንኩን ሸር ሸር አድርጉት
https://t.me/sobabilelmesjide?videochat=683efb49fe7589c890
