ru
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
2 943
Подписчики
-1024 часа
+77 дней
+37930 дней
Архив постов
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር ጎርጎን ከተማን መልሶ የተቆጣጠረ ሲሆን አፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር የነጎድጓድ ክፍለ ጦር በሚንቀሳቀስበት ሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ ደነባ ከተማ ላይ የአገዛዙ ኃይል እርስ ብራሱ ተጨፋጨፈ።    አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አ /ዕዝ   የብልፅግና ዙፋን አስጠባቂው እና እራሱን ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው ሃይል  በአንኮበር ወረዳ ጎርጎ ከተማ ላይ መሽጎ የንፁሀንን ሀብት ንብረት በመዝረፍና በከተማው ላይ ያገኛቸውን ማህበረሰብ በመደብደብ ንፁሃንን ሲያሰቃይ ከከረመ በኋላ ሰሞኑን በነበረው ውጊያ አመራሩን ጭምር በጀግኖቹ እስከወዳኛው የተሸኙበት ሲሆን በዚህ የተርበተበተው የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ሁለት ቀን ሙሉ ከምሽግ ሳይወጣ የድረሱልኝ ጥሪ ለበላይ አመራሮቹ ቢያቀርብም ተጨማሪ ሃይል ማስገባት አልተቻለም።  የመከላከያ ሰራዊት የጎርጎን ህዝብ በቀን 16/09/2018 ዓ.ም ሰብስቦ ስለምርጫ የውሸት ዲስኩር ለማካሄድ ስብሰባውን እያዘዘበት  በነበረበት ሰአት አይበገሬው ጀግናው ሰራዊታችን ከትናት ጠዋት ጀምሮ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር የእቴጌ ጣይቱ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ እና 4ኛ ሻለቃ በጋራ በመሆን ግራና ቀኝ ከተማዋን በመክበብ ማርፈጃውን መውጫ መግቢያ ሲያሳጡት ከዋሉ ቡሀላ ወደ አመሻሽ ላይ እምሽጉ ድረስ ዘልቆ በመግባት ጠላት ከከተማው ጓዙን ጠቅልሎ   ወደ መጣበት እዲፈረጥጥ አድረገውታል። ነበልባሎቹ በሰሩት ሰርጅካል ኦፕሬሽን ከምሽቱ 3 ሰአት ጀምሮ ጎርጎ ከተማን መቆጣጠር ችለዋል። የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው ጠላት በየጫካው ተዝረክርኮ እግሬ አውጭኝ እያለ ወደ መጣበት አልዩአምባ ከተማ ተመልሷል። ​   በሲያ ደብር እና ዋዩ ወረዳ ደነባ ከተማ  ላይ የአገዛዙ ሰራዊት ባደረገው የእርስ በእርስ ውጊያ  በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ:: የደነባ ከተማ  ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ኃላፊ የነበረዉ የኋሉ በልሁ ጣሴን ጨምሮ 4 የሚሊሻ አባላት እንዲሁም ከ4 በላይ የብልፅግና የግል ወታደሮች ተገድለዋል።ከዚህ በተጨማሪም ከ9 በላይ የመከላከያ አባላት እና በርካታ የፖሊስና የሚሊሻ አባላት ከባድ ቁስለኛ ሆነው በህክምና ላይ የሚገኙ ሲሆን ከውጊያው በኋላ 12 የሚሊሻ አባላት መክዳታቸውና የገቡበት እንዳልታወቀ የውስጥ የመረጃ ምንጫችን መረጃውን አድርሰውናል:: ከዚሁ ጋር በተያያዘ  አገዛዙ 7 የሚሊሻ ቤተሰቦችን ማሰሩና 4 የሚሊሻ አባላትንም በቁጥጥር ስር አውሎ እስረኛ አድርጕቸዋል። ​የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ሪፖርተር ባስተላለፈው መረጃ፣ ይህ ክስተት የብልፅግና ሰራዊት በአማራ ፋኖ መሸነፉንና የአገዛዙ መዋቅር እየተበተነ መምጣቱን በግልፅ የሚያሳይ ነው ብሏል። ድል ለተገፋው አማራ ህዝብ ክብር ለትግሉ ሰማዕታት አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ !! ቀን 16/09/2018 ዓ/ም

ለጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ የሚሆን ህትመቶችን በማዘጋጀት ላይ በሚገኙ የብልፅግና የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ አባትን ባጀቡ የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻና ፖሊሶች ላይ ምህታተኛው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የማያዳግም ርምጃ ወሰደ። አፋብን ሽ/ጠ/ግ/አ/ዕ የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም ቀን ከለሊት በሚታትሩ ሆድ አደሮች ላይ ድርጅታችን አፋብን ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልዕክት መሰረት የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ጀግናው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር አገዛዙ ወደ ኦሮሚያ ባካለለው በግራርያ (ፍቸ ሰላሌ) አውራጃ ደብረ ፅጌ ወረዳ ድረስ ዘልቀው በመግባት በትላንትናው ዕለት ከምሽቱ 3:30 ላይ በብልፅግናው አገልጋዮች ላይ የማያዳግም ርምጃ ሲወስድ የምርጫ ቁሳቁሶችንና የህትመት መሳሪያዎችን እንዲሁም 3 ክላሽኮቭ መሳሪያ፣ አንድ ምርኮኛ የኦሮሚያ ሚሊሻ እና የግፍ እስረኞችን በተኩስ ልውውጥ በማስለቀቅ ግዳጁን በሚገባ በመፈፀም ወደመጣበት ቀጠና ተመልሷል ሲል የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ገለፀ። አገዛዙ ህዝባችንን ለተጨማሪ 5 የመከራ ዓመታት ለመዳረግ ለጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ የሚሆን ህትመቶችን በማዘጋጀት ላይ በሚገኙ የብልፅግና የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ አባትን ባጀቡ የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻና ፖሊሶች ላይ ምህታተኛው የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አሃድ የሆነው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የማያዳግም ርምጃ መውሰዱን ኮሩ በግንባር መረጃው ገልጿል። ይህ በእንዲሕ እንዳለ በደነባ ከተማ የመሸጉት የሰርዓቱ አገልጋይ ሆድ አደሮች መካከል በተፈጠረ ያለመግባባት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በትላንትናው ዕለት ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ እርስበርሳቸው መጨፋጨፋቸውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር መረጃና መገናኛ ክፍል አስታወቀ። በሸዋ ክፍለ ሀገር በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ደነባ ከተማ ውስጥ መሸጎ የሚገኘው የፋሽስቱ ዓብይ ዓህመድ ወንበር አሰጠባቂ እረሱን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብሎ በሚጠራውና የኦሮሙማው ምንጣፍ ጎታች ሚኒሻ ጎራ ለይቶ ሲታኮሰ ያመሸ ሲሆን የደነባ ከተማ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆነው አቶ የኋሉ በልሁ ከነ አጃቢዎቹ በመከላከያ ሲገደል ፣ ሁለት የመከላከያ አመራሮችና 4አባላትን ጨምሮ፣ 2 የከተማ ፖሊስ እና 3 የሚኒሻ አባላት የተገደሉ ሲሆን፣ 7 የሚሊሻ አባላት፣ 3 መከላከያ በሞት አፋፍ ላይ ሆነው በደነባና ደብረ ብርሃን ሆስፒታል ይገኛሉ ሲል ኮሩ በመረጃው ገልጿል። አጅግ አስገራሚው ነገር የግጭቱ መንሰኤ በሆቴል ውስጥ እያሉ በከፍተኛ የአልኮል መጠጥ ላይ በነበሩበት ወቅት "ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል" እንደተባለው ምርጫን በተመለከተ ሲከራከሩ በመከላከያ ሰራዊት አመራሩ በኩል "ህዝብ የፈለገውን ይምረጥ አታሰገድዱት" የሚል የመከራከሪያ ሀሳብ በማምጣቱ ከወረዳው የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ ጋር ግጭት ውስጥ በመግባት የተጀመረ ሲሆን በተፈጠረው አለመግባባት ሁለቱም መሞታቸውን ኮሩ አረጋግጧል። በወረዳው አዲሰ አለም ቀበሌ ዜጎች የሚሰቃዩበትን ፖሊሰ ጣቢያ በጀግናው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለ ጦር ቃኝወች የተሰበረ ሲሆን ለሰርዓቱ ወንበር ማሰጠበቂያ እና ዜጎች የሚሰቃዩበት ሰነዶችና፣ የፓርቲ የገንዘብ መዋጮ ደረሰኞችን፣ የህትመት መሳሪያ በቁጥጥር ስር ያዋሉ ሲሆን በተጨማሪ የፖሊሰ ጣቢያው ዘበኞች ሲጠቀሙበት የነበረው የጦር መሳሪያም ጭምር በቁጥጥር አውሏል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 16/2018ዓ.ም

የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዱ ሁሴንን አጅቦት የተጓዘ ሰራዊት ላይ ጥቃት ተፈፀመ!! ጀንበር መለስ ሲል ይመጣሉ ማታ፣ አፈ ሾጤ ጥይት አቅመው በካርታ!! የተባለላቸው የአፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ፋኖዎች መካነሰላም ከተማን ከበው በማደር በማለዳው መብረቃዊ ጥቃት ፈጽመዋል:: የፋኖን መብረቃዊ ጥቃት ተከትሎ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዱ ሁሴን መድረሻ ጠፍቶታል ሲሉ የውስጥ ምንጮች የገለፁ ሲሆን 2 መድፍ፣ 1 ቢኤም፣ 2 ዙ-23 እና 4 ሞርተር የታጠቀ ሜካናይዝድ ኃይል ስፍር ቁጥር ከሌለው በርካታ እግረኛ ወታደር ጋር ወደ መካነሰላም የገባው አቶ አብዱ ሁሴን ከምዕራብ ወሎ ቀጠና የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ሚሊሻዎችንም ጠርንፎ ይጠብቁኛል በሚል ስሌት ከሳይንት እና ወግድ ጭምር ወደ መካነሰላም  ያጓጓዘ ቢሆንም መጨረሻው ሳያምር ቀርቶ ለከበባ ተዳርጓል:: የአፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለጦር ቃኝዎችን በመምራት ቀድሞ ወደ ከተማይቱ የገባው የመካነሰላሙ 29ኛ ክፍለ ጦር ዘመቻ መሪ አርበኛ መብራቱ ጫብሲ በማለዳው ሶዬ ክፍለ ከተማን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል:: የአማራ ክልል እና የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ወደ መካነ ሰላም ከተማ አቅንተው የምርጫ ቅስቀሳ ለማከናወን እና ሌሎች እኩይ ተግባራትን በመፈፀም የህልውና ትግሉን ሂደት በዚያ ግንባር ለማስተጓጎል ያደረጉት ጥረት ሳይሳካላቸው ቀርቷል። የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዱ ሁሴን እና የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መካነሰላም ከተማ ውስጥ እንዳሉ ሌሊቱን ተከበው ሊያድሩ የቻሉት ከአሸዋ የበዛ ሰራዊት አስከትለው ያጅበናል ብለው አምነው እንደተኙ ነው:: የ29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት የከተማይቱን ዙሪያ ገባ ሲይዝ የክፍለ ጦሩ ቃኝዎች ደግሞ ሰተት ብለው ወደ ከተማ ሊገቡ ችለዋል:: በማለዳው የተፈፀመውን መብረቃዊ ጥቃት ተከትሎ ባለስልጣናቱ ራሳቸውን ለመደበቅ እየተሯሯጡ መሆናቸውም ታውቋል። ንጉሥ በሰራዊቱ ብዛት እንደማይድን የዛሬ ክስተት አስረጅ ነው ያሉት የመረጃ ምንጮቻችን የፋኖን የማድረግ አቅም በትክክል ህዝብ የተረዳበት እለት ዛሬ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ​​©ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሰም ፪ኛ ኮር  አራተኛ ክፍለ ጦር ሲመሰርት መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክ/ጦር በሸዋሮቢት ድል ተቀዳጅቷል።   አፋብን ሽ/ጠ/ግ/አ/ዕ ግዙፉ ከሰም ፪ኛ ኮር ከዚህ በፊት በ3 ክፍለ ጦር ተመሥርቶ የአገዛዙን (ብልፅግናን) ሥርዓትን በማፍረሥ  የህልውና ትግሉ ላይ ከፍተኛ ሚናን የተወጣ ኮር  ነው። ከሰም ፪ኛ ኮር ከቀን ቀን የጦር መሳሪያውንና የሰው ኃይሉን በማዘመንና በመጨመር እየሰራና እያደራጀ  ያለ ትልቅ ኮር በመሆኑ :- የሻምበል ፋንታ ብርጌድና የየረር ብርጌድን አዋህዶ በከሰም ኮር ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣በከሰም ኮር አስተዳደር ጉዳዬች ኃላፊ፣በከሰም ኮር ወታደራዊ አዛዥና ሌሎች የከሩ አመራሮች  በተገኙበት በቀን 14/2018ዓ.ም  በኢትዮጵያ ታሪክ ውሥጥ ጉልህ ሚና የነበራቸውና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር  ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒሥትር  እንዲሁም ዕውቅ ተዕፅኖ ፈጣሪ ዲፕሎማት በነበሩት ''በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ኃብተወልድ'' ሥም ክፍለ ጦሩ መሰዬሙን ስናበስር በደስታና በኩራት ነው። በሌላ በኩል የብልፅግናው  ዙፋን አሥጠባቂ ሰራዊት በከሰም ቀጠና በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በነበልባል ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራር የሆነውን የአርበኛ መለሰ ውቤን  የ3 ዓመት ህፃን ልጅና ሚሥት እንዲሁም :ወንድሙን አግተው መውሰዳቸውን ኮሩ በመረጃው አረጋግጧል።ይህ አገዛዝ እንደሚታወቀው ሽንፈቱን በፀጋ  ላለመቀበል በእውር ድንብር እየተመራ ሎሌዎቹን በማዘዝ ንፁሐንን  በማገት ሽንፈቱን እና የሞራል ዝቅጠቱን አሳይቷል ። በዚህ አይነት  ህፃንና፣አረጋውያን ፣ነፍሰ ጡርን እና ንፁሀንን በማገት እና ህዝብን አለኝ በሚለው መሳሪያ በዕብሪት ለማሰቃዬት ቢሰራም በዚህ አረመኔያዊ ድርጊቱ  ሽብረክ የሚል ታጋይ ያለን ሳይሆን ከሚጨክንበት ጠላት እጥፍ የሚጨክንና የሚበረታ ታጋይና ህዝብ ያለን መሆኑን ሊያውቀው ይገባል። በሌላኛው ቀጠና በሸዋሮቢት ከተማ 06 ቀበሌ ለሁለተኛ ተከታታይ ቀን የቆየው አውደ ውጊያ አይበገሬዎቹ የደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለ ጦር በድል አጠናቀዋል። በሸዋሮቢት ከተማ 06 ቀበሌ  የስርአቱ ወንበር አስጠባቂ የታፈሱና በቂ ስልጠና ያልሰለጠኑ የድሃ ልጆችንና ከባድ መሳሪያ ቢያሰልፍም የደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ልጆች የተለመደውን አቀባበል አድርግውላቸዋል። የደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለጦር አናብስቶች ጠላትን ሁለት ቀን ሙሉ በመከላከል ሲፋለሙ ቆይተው አመሻሽ ላይ መብረቃዊ የማጥቃት ኦፕሬሽን በማድረግ ጠላት አስፍቶ ይዞት የነበረውን ሙሉ በሙሉ በማስለቀቅ ቦታውን መቆጣጠር ተችሏል። በአጠቃላይ በነበረው አውደ ውጊያ ለብልፅግና ስርዓት ውድቀት በወገን ሃይል የድል የበላይነት ተጠናቋል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!! አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ቀን 15/09/2018 ዓ/ም

ከፍኖተ አማራ ሚዲያ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት! ​የአማራ ልጅ ፋኖ በየቀኑ፣ በአራቱም ማዕዘናት እያደረገ ያለው ተጋድሎና እየከፈለ ያለው ታላቅ ዋጋ የሁላችንም ኩራት ነው። ይህንን ሀቅ ማንም አይክ
+1
ከፍኖተ አማራ ሚዲያ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት! ​የአማራ ልጅ ፋኖ በየቀኑ፣ በአራቱም ማዕዘናት እያደረገ ያለው ተጋድሎና እየከፈለ ያለው ታላቅ ዋጋ የሁላችንም ኩራት ነው። ይህንን ሀቅ ማንም አይክደውም። ነገር ግን፣ አንድ ልናሰምርበት የሚገባ ትልቅ መስመር አለ፦ ጀግኖችን በማጥላላትና በመሳደብ የሕዝባችንን ነፃነት ማረጋገጥ አይቻልም! ​ስለሆነም፣ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ የፍኖተ አማራ ሚዲያ ደጋፊዎችና ወንድሞቻችን በሙሉ፤ የጀግኖችን ስም ማጠልሸት በፍጹም ሊቆም ይገባል። ​የእኛ ጥሪ የአንድነት ነው፦ ​🤝 ኑ አብረን እንስራ! ​💬 ኑ በሃሳብ እንወያይ! ​🏆 ኑ በጋራ እናሸንፍ! ​የመከፋፈል ሳይሆን የአሸናፊዎች ጊዜ ላይ ነን። ድል ለአንድነታችን!

የmላት ሰራዊት እየፈረሰ ክፍለ ጦራችንን እየተቀላቀለ ነው ። የአረመኔው የአብይ አህመድ ሰራዊት አባላት ከማእከላዊ ጎንደር ሻውራ ከተማ በመውጣት ወደ አፋብን ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/
+1
የmላት ሰራዊት እየፈረሰ ክፍለ ጦራችንን እየተቀላቀለ ነው ። የአረመኔው የአብይ አህመድ ሰራዊት አባላት ከማእከላዊ ጎንደር ሻውራ ከተማ በመውጣት ወደ አፋብን ቴዎድሮስ እዝ 105ተኛ ኮር 55ተኛ ክ/ጦር ተቀላቅለዋል። 1, ፲አለቃ /ዳንኤል ተስፋየ ጋንታ መሪ 2, አሸናፊ በጅ 3, ፈይሳ ቀጀላ የ118ተኛ ክ/ጦር 3ኛ ሬጅመንት አባላት የነበሩ ሲሆን የአማራ ህዝብ እያደረገ ያለውን የህልውና ትግል በመረዳት እስካሁን የበደሉትን ህዝብም ለመካስ መወሰናቸውን መልክታቸውን አስተላልፈዋል ። ምስጌ ዘድንግል የ55ተኛ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት

የአርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ አቋም፡ የፋኖ የትግል ምዕራፍና የህልውና ተጋድሎ ጥንካሬ ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) አመራር አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ፣ ከጋዜጠኞችና ከሕዝብ ለተነሱላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች በሰጡት አጠቃላይ ምላሽ፣ የንቅናቄውን የትግል አቅጣጫና የአገዛዙን የመጨረሻ ፍጻሜ የሚያመላክቱ ቁልፍ ጉዳዮችን አንስተዋል። ​በሱዳን ተካሄደ በተባለው "ጽምዶ" የተባለ ስምምነት ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት አርበኛው፣ አፋብን ስለ ስምምነቱ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለና በሂደቱም እንዳልተሳተፈ በግልጽ አስታውቀዋል። አያይዘውም የአማራ ክልል 90 በመቶ የሚሆነው አካባቢ በአሁኑ ወቅት በፋኖ ሙሉ ቁጥጥር ሥር መሆኑን በመጥቀስ፣ አገዛዙ በአማራ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ በደል ለማስቆም ብቸኛው መንገድ ሥርዓቱን ማስወገድ መሆኑን በጽኑ አቋም አረጋግጠዋል። ​ከድተው አገዛዙን የተቀላቀሉ የቀድሞ ፋኖ ታጋዮች የሚያቀርቡትን "ትግሉ ተጠልፏል" የሚል ክስ በተመለከተ ሲናገሩ፣ ግለሰቦቹ ከአገዛዙ የሚሰጣቸውን የምግብ ኩፖን ለማሳደስና ሹመት ለማግኘት የሚናገሩት የፈጠራ ወሬ እንጂ ሕዝቡ የሚቀበለው እውነታ አለመሆኑን ገልጸዋል። የፋኖ ዛሬ ያለበት ቁመና ማንም ሊጠለፈው ወይም ሊያዳክመው የሚችልበት ምዕራፍ እንዳልሆነም አርበኛው አስምረውበታል። ​የፋኖ ትግል ተራዝሟል በሚል ለሚሰነዘሩ ትችቶች ምላሽ የሰጡት አርበኛ አስረስ፣ አስተያየት ሰጪዎቹ የትግሉን ዳራና የጠላትን አቅም ያልተረዱ መሆናቸውን በመጠቆም፣ “የኢትዮጵያን መደበኛ ካፒታል በጀት ለጦርነት ያዋለ፣ ድሮንና ዘመናዊ መሳሪያዎችን ከኢምሬትስ የሚረዳ አገዛዝን በሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አመናምነን፣ የቀጠናውን ግዙፍ ፕሮፌሽናል ሰራዊት የገነባንበት ታላቅ ታሪካዊ ተጋድሎ ነው እያካሄድን ያለነው” ሲሉ የትግሉን ስኬት አብራርተዋል። ​በመጨረሻም አፋብን ከላይ እስከ ታች በፖለቲካ የበሰሉ፣ ትግሉን ሳይንሳዊ ያደረጉ ስትራቴጂክ አሳቢዎች የሚመሩት የትውልድ ክስተት መሆኑን በመግለጽ፣ ሕዝቡ ከጎናቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። ከሩቅ ሆነው ትግሉን ለሚከታተሉ ደጋፊዎችም "ትግሉ በብልህና በትጉህ መሪዎች የሚመራ በመሆኑ አትስጉ" የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

ዛሬ ግንቦት 15 ቀን2018 ዓ. ም ጠዋት ከአሶሳ ወይም ባህርዳር የተነሳ የUAE አኪንች ድሮን የሱዳኗ ብሉ ናይል ግዛት ዋና ከተማ የሆነችውን ደማዚንን ለስምንት ጊዜ ያህክል ደብድቧል። ለዘጠነኛ ዙ
ዛሬ ግንቦት 15 ቀን2018 ዓ. ም ጠዋት ከአሶሳ ወይም ባህርዳር የተነሳ የUAE አኪንች ድሮን የሱዳኗ ብሉ ናይል ግዛት ዋና ከተማ የሆነችውን ደማዚንን ለስምንት ጊዜ ያህክል ደብድቧል። ለዘጠነኛ ዙር ድብደባ አየር ላይ እያለ ቀሪ 4 ተተኳሽ እንደያዘ ተመቶ ወድቋል። የዩናይትድ አረብ ኢምሬት አኪንች ድሮን በዚህ አካባቢ ተመቶ ሲወድቅ የዛሬው ለ2ኛ ግዜ ነው።

​📌 የመጨረሻው የህልውና ጥሪ! ​በአሁኑ ሰዓት በአብይ አህመድ ስርዓት ጥላ ስር ሆናችሁ፣ የህዝባችሁን ስቃይ በመዘንጋት ለግል ጥቅማችሁ የቆማችሁ ሆዳም አማራዎች፣ ካድሬዎችና የመከላከያ አባላት ሆይ፤ ጊዜው ሊያበቃ ነው። አሁን መወሰን ያለባችሁን ወሳኝ ውሳኔ የምትወስኑበት የመጨረሻው ሰዓት ላይ ትገኛላችሁ። ​ማንም አያድናችሁም! ህዝባችንን እና እናንተንም ጭምር ከፈተና ሊያወጣ የሚችለው ብቸኛው ሀይል መስዋዕትነት እየከፈለ ያለው የአማራ ልጅ ፋኖ ብቻ ነው። ​ከታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን አሁኑኑ ከፋኖ ጎን ቁሙ! ​#አማራ #ፋኖ #ህልውና

​📌 የመጨረሻው የህልውና ጥሪ! ​በአሁኑ ሰዓት በአብይ አህመድ ስርዓት ጥላ ስር ሆናችሁ፣ የህዝባችሁን ስቃይ በመዘንጋት ለግል ጥቅማችሁ የቆማችሁ ሆዳም አማራዎች፣ ካድሬዎችና የመከላከያ አባላት ሆይ፤ ጊዜው ሊያበቃ ነው። አሁን መወሰን ያለባችሁን ወሳኝ ውሳኔ የምትወስኑበት የመጨረሻው ሰዓት ላይ ትገኛላችሁ። ​ማንም አያድናችሁም! ህዝባችንን እና እናንተንም ጭምር ከፈተና ሊያወጣ የሚችለው ብቸኛው ሀይል መስዋዕትነት እየከፈለ ያለው የአማራ ልጅ ፋኖ ብቻ ነው። ​ከታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን አሁኑኑ ከፋኖ ጎን ቁሙ! ​#አማራ #ፋኖ #ህልውና

በዘፈቀደ በከባድ መሳሪያ የተጨፈጨፉ አማራዎች በራያ ግንባር የተፈፀመ ግፍ
+5
በዘፈቀደ በከባድ መሳሪያ የተጨፈጨፉ አማራዎች በራያ ግንባር የተፈፀመ ግፍ

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አስቸኳይ‼️   የድሮን ቅኝት ተደርጓል በሙሉ  ኤፍራታና ግድም ወረዳ የድሮን ቅኝት አሰሳ  ተደርጓል ጥንቃቄ!!

አብይ አስጨረሰዉ የድሃዎቹን ልጆች አማራ ክልል ገብተዉ አለቁ
+8
አብይ አስጨረሰዉ የድሃዎቹን  ልጆች አማራ ክልል ገብተዉ አለቁ

ሰበር!...በራያ ግንባር በተደረገ ተጋድሎ 84 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ 22 ወታደሮች ደግሞ እጅ ከፈንጅ መማረካቸው ታወቀ! አገዛዙ ምንም ነገር ቢጠቀም ከአማራ ፋኖ አቅም በታች መሆኑ የወሎ ቤተ አማራ አናብስቶች ዛሬ በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የአፋብን ወሎ ቤተ አማራ ምኒልክ ዕዝ ጀብደኛው 102ኛ ኮር አናብስቶች አረጋገጡ! ግንቦት 14/2018ዓ/ም ጠላት ሌሊቱ 10 ሰዓት የ102ኛ ኮር አናብቶች በአራት አቅጣጫ ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር ትንቅንቅ በማድረግ አኩሪ ገድል ፈፅመዋል። የ12ኛ ክፍለጦር ቃኝ በጠላት ላይ መብረቃዊ ማጥቃት በማድረግ በአስደማሚ ሁኔታ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጨፍጫፊውና የአምባገነኑን ሰራዊት በመደምሰስ ሀያ ሁለት(22) የሚሆኑትን የአገዛዙ ስልጣን አስጠባቂ የሰራዊት አባላት በአስደናቂ መናበብ ገቢ ማድረግ ተችሏል። በአውደ ውጊያው የጠላት የሻለቃና የሻምበል አመራሮችን ጨምሮ የተደመሰሱ ሲሆን  አስከሬኑን እንኳ ሳያነሳ እያዝረከረከ ፈርጥጧል። የ102ኛ ኮር አካል የሆነችው ነበልባሏ 65ኛ ክፍለጦር ሙሉ ሀይል በማስጠጋት በተለምዶ ዋልካ መንደር በመባል ወደ ሚታወቀው አካባቢና ጮቢ በር በሞርተርና በድሽቃ በአስገራሚ ሁኔታ ተኩስ በመክፈት ጠላትን ስትቀጠቅጠው ውላለች። በዚህ ትንቅንቅ የ65ኛ ክፍለጦር መካናይዝድ በሞርተር 82 ኢላማውን የጠበቀ ድብደባ በማድረግ በጠላት የጮቢ በር ምሽግ የሞርተር 120ን  ሙሉ በሙሉ በማውደም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። በተጨማሪም  የ12ኛ ክፍለጦር መካናይዝድ በሞርተር 82 ጮቢ በር እና አዩብ  የጥላት ምሽግ ላይ ኢላማውን የጠበቀ ድብደባ በማድረግ ተኳሾችን እና የጠላትን ሞርተር ሙሉ በሙሉ በማቃጠል፣ በጮቢ በር የመጣውን ዙ-23 በድሽቃ በአልሞ ተኳሾች ግማሽ ጎኑን በመምታት ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ በማድረግ ከፍተኛ ድል አስመዝግበዋል። ከጧቱ 3 ሰዓት በኋላ የሀይል ሚዛን ለማዛባት የ12ኛ ክፍለጦር ቃኝ በጌደሩ እና በአማያ አድስ አለም ተጨማሪ ሀይል በማስጠጋት ጠላት ባልጠበቀውና ባላሰበው ሁኔታ በመብረቃዊ ጥቃት ተመቷል። በመሆኑም የጠላት ግትልትል ሰራዊት በሁሉም አቅጣጫ ወደ ኋላ በመመለስ ወታደራዊ መረጃ እና ኦፒ የሌለው የብልፅግና መራሹ አምባገነኑ ስርዓት በቸልተኝነት እና በዘፈቀደ የከባድ መሳሪያ ድብደባ በማድረግ በአማራ ህዝብ ላይ በዋጃ ከተማ በቅርብ ርቀት ሀብሎ መንደር ላይ በርካታ ህፃናትን፣ አርሶአደሮችን በግፍ ጨፍጭፏል። ከተሰውት ሲቪሎች መካከል የአንድ ቤተሰብ አባል አባትና ልጅ አቶ ደሳለ ሞላ እና የ10 ዓመት ልጅ ፉአድ ደሳለ እንዲሁም ጎረቤት አማረ መለሰን የገደለ ሲሆን አባት አቶ መለሰ መስፍን ከባድ ቁስለኛ በመሆን በሞትና በህይወት መካከል ይገኛሉ። ጠላት ከተኩለሽ እና ሺዎች ማሪያም እስከ ጮቢበር አስፍቶ ለመምጣት ቢሞክርም ነበልባሏ የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ እና ሀውጃኖ ክፍለጦር በምዕራብ በኩል የመጣውን ሀይል እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ የአንበሳውን ድርሻ በመወጣት በቀይ ቀለም ታሪክ ፅፈዋል። ዙ-23 ማራኪዎቹ የቀድሞው ካላኮርማ ክፍለጦር የአሁኑ 49ኛ ከፍለጦርና የ102ኛ ኮር ቃኝ በጋራ በመሆን የጥላትን የሀይል ሚዛን ለማዛባት በምስራቅ በኩል ጎለሻ ፣ ቀዩ ጋሪያ፣ አደር ቀበሌና መንደፈራ በመግባት ከጨበጣ እስከ ድሽቃና ሞርተር 82 ተኩስ በመክፈት በጥላት ላይ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ ከፍተኛ ድል አስመዘገቡ። ጠላት ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ሙሉ አቅሙን ቢጠቀምም የ49ኛ ክፍለጦር ክንደ ብርቱዎቹን መቋቋም ባለመቻሉ ገሚሱን ሜዳ ላይ በመቅበርና እድለኛ ያልሆኑትን በየ መንገዱ በማንጠባጠብ ሁለት ኦራል መኪና አስከሬን ወደ ቆቦ ከተማ ይዞ በመሸሽ አካባቢውን ለቆ ወጥቷል። ጀብደኛው  102ኛ ኮር በአርበኛ ጌታቸው መልኩና በአርበኛ ዘውዱ ዳርጌ ወታደራዊ አዛዥነት እየተመራ እንዲሁም በአርበኛ ዋሴ ጫኔና በአርበኛ በላይ መንግስቱ ዘመቻ መሪነት እየተመራ ዛሬም በከፍታ ማማ ላይ እየበረረ ሞርተር 82ን እንደ እስናይፐር የሚጠቀሙት ልማደኞቹ የ49ኛ ከፍለጦር ዛሬም እንደ ትናንቱ የጥላትን ድሽቃ ሙሉ በሙሉ አውድመዋል። በመጨረሻም በዛሬው እለት በ12ኛ ክፍለጦር በዚህ አውደ ውጊያ የተገኙ የጥላት ንብረትና በዝርዝር የሚከተለው ነው ። ✅ ክላሽንኮቭ መሳሪያ--------16 ✅ የክላሽ ጥይት ተተኳሽ-----632 ✅ የመትረየስ ጥይት ተተኳሽ-- 695 ✅ የድሽቃ ጥይት ተተኳሽ-----274 ✅ የክላሽ መጋዘን-------------23 ✅ ወታደራዊ ሻንጣ-----------74 ✅ ሬን ኮት/የዝናብ ልብስ-----52 ✅ የውሀ ኮዳ-------------------61 ✅ F1 ቦንብ------------------ 13 ✅ አንድ ሞርተር 82 የተቃጠለ ✅ አንድ ሞርተር 120 የተቃጠለ ✅ የተደመሰሰ የጥላት ሰራዊት--84 ✅ የተማረከ የጠላት ሰራዊት----22 ምንጭ፦በአፋብን ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!