ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 132
Подписчики
Нет данных24 часа
+4577 дней
+1 19430 дней
Архив постов
መዝባሪው የብልጽግና አግዛዝ የፋኖ ሀብት ነው ያለውን ቁሳቁስ መከፋፈል ጀመረ
═════════════🕊❁✿❁🕊═════════════
(ጥር 01/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ)
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ የመሸገው ዘር አጥፊ እና ዘራፊ የብልጽግና ቡድን በገበዘ-ማርያም ከተማ የፋኖ ሀብት ነው ያለውን ቁሳቁስ ከሱቅ አውጥቶ መከፋፈሉን ታማኝ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
በዛሬው ዕለት በገበዘ-ማርያም ከተማ ፋኖ ደረጃው አርጋቸው ሲሠራበት የነበረውን ጠቅላላ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና ሱቅ ገንጥለው በመግባት በውስጡ የነበረውን ቁሳቁስ ተከፋፍለው ወስደዋል ሲሉ ዕማኞች ተናግረዋል።
የተዘረፈው ግለሰብ ፋኖ ደረጃው አርጋቸው በሰጠው መረጃ መሠረት ቀጥሎ የተጠቀሱ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ከሱቁ ተቆልፎባቸው ተቀምጠው ነበር።
🏒 ለጥገና የመጡ አራት የግለሰቦች TV
🏒 አንድ አስትራ ኮሪያ ጀኔረተር
🏒 ሶስት 780 ሞዴል ኮምፒውተሮች
🏒 ሁለት ሆት ኤር ገን
🏒 ሀለት Dc ፓውር ሳፕላይ
🏒 30 ለጥገና የመጡ ቴክኖ 528 ሞዴል ሞባይሎች
🏒. አምፒሊፋየር ሞንታርቦ
🏒 አንድ ጂፓስ
🏒. አንድ ሰላሳ ሽህ ብር የተሰራ ዲሲፕላይ ሸልፍ
🏒. ሁለት ከግድግዳ ላይ የሚለጠፍ ዲሲፕላይ ከነ ሻተር ብረቱ
🏒 ፍሬ ለጥገና የመጡ የደንበኞች አራት ሳምሰንግ ተች ስልኮች
🏒 80 ሽህ ብር የሚጠጋ የኤሊክትሮኒክስ መለዋወጫ አክሰሰሪ
ከሱቅ አስቀምጧል።
መዝባሪነት፣ አውዳሚነት፣ ሴሰኝነት እና ሌብነት የጨፍጫፊውና ዘር አጥፊው የብልጽግና ወምበዴ ሠራዊት መገለጫዎች ናቸው።
አፋብኃ በላይ እዝ የ4ተኛ ደጅ አዝማች ኮር የጎቤ ክፍለ ጦር ሁለት ብርጌዶች(ጠራ እና ዋክሺም) በአንድነት ዛሬ ጥር 01/2018 ዓም በማእከላዊ ጎንደር ጠገዴ ወረዳ አዲስ አለም ቀበሌ ከጧቱ 2:05 ሰዓት ጀምሮ በተደረገ የደፈጣ ውጊያ ጠላት ተደመሰሰ።
የጠላት 92ኛ ክፍለ ጦር አካል የሆኑት ሁለት ሬጅመንቶችን የተወጣጣ ኃይል የተመታ ሲሆን 12 የተደመሰሰ እና 52 ቁስለኛ ሁኗል።
የአብይ ሰራዊት ያለው ብቸኛ አማራጭ በየቀኑ መሳሪያውን ለፋኖ እያስረከበ በሰላም ቤተሰቦቹ ጋር መኖር ነው ።
ከታህሳስ 01_ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም ድረስ
ወደ 201ኛ ኮር የተቀላቀሉ
➦በታህሳስ ወር!!
1ፍቅሩ አበባው............መከላከያ
2 ፉአድ ሚፍታህ...........መከላከያ
3 ሐሰን አብዲ.................መከላከያ
4 ሙጭየ ገዛኸኝ...........ሚሊሻ
5 ደርሶ ተሜ...................ሚሊሻ
6 አየለ ጌቴ....................ሚሊሻ
7 ሙሉ ድረስ..................ሚሊሻ
8 መሌ ካሴ...................ሚሊሻ
9 በለጠ አታለል..............ፓሊስ
10 ሹመት ወለላው...........ሚሊሻ
11 እሻለሁ ሱሌራ .............መከላከያ
12 ይበልጣል አለኸኝ..........ሚሊሻ
13 ፀሀው አለባቸው...............ሚሊሻ
14 መስፍኔ መለሰ............መከላከያ
15 ዳንኤል ዋለ...............መከላከያ
16 ጌትነት ፀጋው..........መከላከያ
17 ስጦታው ሙሌ.........መከላከያ
18 ፲ አለቃ ሰለሞን አለምነው ...መከላከያ
19 ፲አለቃ ደሳለኝ አባይ.......መከላከያ
20 እሸት ይመር......መከላከያ
21 ይሁን ብሬ ...... ሚሊሻ
22 በለጠ አለማየሁ ......ሚሊሻ
23 ፲አለቃ ጊደታ እረታ ......መከላከያ
24 ፲አለቃ አሰግድ አስጠራው.....መከላአያ
25 አክሊሉ ባይነስ.............መከላአያ
26 ደረሸ ዋለ ...............ሚሊሻ
27 ክንዱ አበባው .........ሚሊሻ
28 ጌትነት ሙሉ ..........ሚሊሻ
29 ሙጭየ በላቸው.......ሚሊሻ
30 ታዴ ይደግ ........ሚሊሻ
ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል ።
© ማርሸት ፀሐይ ደምሴ
🔜የ75 ዓመቱ አባት አርበኛ መሀመድ ስምኦን በፋኖ የትግል ሜዳ!!
ከሶማሌ መጥተው የአፋብኃ👉ቴወድሮስ ዕዝ🔜11ኛ ክ/ጦርን በመቀላቀል የክ/ጦሩ ቃኝና መሀንዲስ ኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊው '' መሀመድ ስምኦን'' ጦሩን በየቀኑ የፖለቲካ ንቃተ ህሊና እየሰጡ ተጨባጭ ለውጥ አምጥተዋል።
የፋኖ ትግል ለሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ብቸኛ መዳኛ መንገድ ስለሆነ ሌሎችም የአርበኛ መሀመድ ስምኦንን ፈለግ ተከትላችሁ ኑ የፋኖን ትግል ተቀላቀሉ!!
+1
ከእንግዲህ እንደ ተበደለ አማራ ህዝብ ብልፅግናንና ሌሎች ፀረ-አማራ ጠላቶቸን ለመጣልና ለማሸነፍ የምፅፈውና የምታገለው በብዕር ሳይሆን በ ጠብ-መንጃ ነው !!!
ትግላችንን በጋራ እንጠብቅ!
መዳረሻችንን እንወቅ!!
ከምን ጊዜውም በበለጠ የትግላችንን አረሞች እና ሾተላዮች እየተከታተልን ትግላችን ለሚደርስበት መዳረሻ የየበኩላችንን መወጣት አለብን።
ለዘመናት የአማራ ህዝብ ለመብቱ ለማንነቱ ሲታገል ቆይቷል። ነገር ግን ሚያዚያ 3 2015 ዓ.ም ህዝባችንን አነሳስተን ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁሉም በፊት አገዛዙን ዘጠኝ ትጥቅ ብቻ ይዘን ፊት ለፊት ገጥመነዋል። በወቅቱ የተሰራው ስራ በታሪክ ማህደር ላይ የተቀመጠ፤ በሌሎች ግዛቶች እና ከክልሉ ውጪ ያለውን የአማራ ህዝብ ያነቃቃና ወደ ትጥቅ ትግሉ ያስገባ ተዓምር ነበር። በራሱ አላማ እና በራሱ አጀንዳ አማራው ለራሱ በራሱ ተነስቶ ጫካን ቤቱ አደረገ።
በትግል ሂደቱ ውስጥ አሁን ያለንበት ደረጃ ከመድረሳችን በፊት የአማራ ፋኖ በሸዋን በጠራ የትግል መስመርና ስልት ላይ እንዲቆም አድርገናል።
👉ስልታችን፦ ፖለቲካዊ የትጥቅ ትግል
👉መስመራችን፦ አማራነት
የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች የሚመለሱት እና የህልውና አደጋው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀለበሰው #በጥገናዊ ለውጥ ሳይሆን ስር ነቀል ለውጥ በማምጣት ነው ብለን በማሰብ ዘር አጥፊውን አገዛዝ ነቅለን በምትኩ ሁሉን አካታች ስርዓት ለመትከል በፍፁም ታማኝነት ትግላችንን እየመራን እንገኛለን።
የአማራ #ብሄርተኝነትን የትግል መስመራችን አልፋ እና ኦሜጋ ስናደርግ አማራውን በማንነቱ ለይቶ በሀገሪቱ የትኛውም ቦታ ሲጨፈጭፍ እና ሲያስጨፈጭፍ የነበረው ኃይል መንግስታዊ መዋቅሩን በመጠቀም እና ሀሰተኛ ትርክት በመቅረፅ በመሆኑ በርካታ መስዋዕትነት ተከፍሏል።
ዛሬ ላይ የደረሰውን ትግል የአማራ ታጋይ ሰራዊት፣ የአማራ ህዝብ፣ የአማራ ዲያስፖራ፣ የትግሉ መሪዎች በማንኛውም ዋጋ ትግሉን ጠብቀው በድርጅታዊ ማዕቀፍ ወደፊት ማስኬድ ይኖርባቸዋል።
የእኛ ትግል #ሙሉ_ስርዓታዊ_ለውጥ ለማምጣት እስከሆነ ከዚህ ውጪ የሚቀሳቀስ የትግል መሪም አባልም በጋራ ሁላችንም ልንታገለው ይገባል። ጉዟችንን ወደ ምንፈልግበት፤ የአሸናፊነት ዋንጫ ወደምናነሳበት ከባቢያዊ እና ፖለቲካዊ የስበት እንዲሄድ ሁሉም መስራት አለበት። ለዚህም የትግሉ መስመር በእንቅፋትነት የተጋረጠ ማንኛውንም አካል ገለል ማድረግ ያስፈልጋል። ከአገዛዙ ጋር የሚደረጉ ንግግሮች ውይይቶች በሚል ሽፋን የሚካሄዱ ፖለቲካዊ ግልሙትናዎች ትናንት ስናወግዝ ነበር ዛሬም እናወግዛለን ነገም እንታገላለን።
ብሩክ ስለሺ ዘአስቻለው ደሴ
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ
የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
ትግላችንን በጋራ እንጠብቅ
መዳረሻችንን እንወቅ!!
ከምን ጊዜውም በበለጠ የትግላችንን አረሞች እና ሾተላዮች እየተከታተልን ትግላችን ለሚደርስበት መዳረሻ የየበኩላችንን መወጣት አለብን።
ለዘመናት የአማራ ህዝብ ለመብቱ ለማንነቱ ሲታገል ቆይቷል። ነገር ግን ሚያዚያ 3 2015 ዓ.ም ህዝባችንን አነሳስተን ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁሉም በፊት አገዛዙን ዘጠኝ ትጥቅ ብቻ ይዘን ፊት ለፊት ገጥመነዋል።
በወቅቱ የተሰራው ስራ በታሪክ ማህደር ላይ የተቀመ፤ በሌሎች ግዛቶች እና ከክልሉ ውጪ ያለውን የአማራ ህዝብ ያነቃቃና ወደ ትጥቅ ትግሉ ያስገባ ተዓምር ነበር። በራሱ አላማ እና በራሱ አጀንዳ አማራው ለራሱ በራሱ ተነስቶ ጫካን ቤቱ አደረገ።
በትግል ሂደቱ ውስጥ አሁን ያለንበት ደረጃ ከመድረሳችን በፊት የአማራ ፋኖ በሸዋን በጠራ የትግል መስመርና ስልት ላይ እንዲቆም አድርገናል።
ስልታችን: ፖለቲካዊ የትጥቅ ትግል
መስመራችን: አማራነት
የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች የሚመለሱት እና የህልውና አደጋው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀለበሰው #በጥገናዊ ለውጥ ሳይሆን ስር ነቀል ለውጥ በማምጣት ነው ብለን በማሰብ ዘር አጥፊውን አገዛዝ ነቅለን በምትኩ ሁሉን አካታች ስርዓት ለመትከል በፍፁም ታማኝነት ትግላችንን እየመራን እንገኛለን።
የአማራ ብሄርተኝነትን የትግል መስመራችን አልፋ እና ኦሜጋ ስናደርግ አማራውን በማንነቱ ለይቶ በሀገሪቱ የትኛውም ቦታ ሲጨፈጭፍ እና ሲያስጨፈጭፍ የነበረው ኃይል መንግስታዊ መዋቅሩን በመጠቀም እና ሀሰተኛ ትርክት በመቅረፅ በመሆኑ በርካታ መስዋዕትነት ተከፍሏል።
ዛሬ ላይ የደረሰውን ትግል የአማራ ታጋይ ሰራዊት፣ የአማራ ህዝብ፣ የአማራ ዲያስፖራ፣ የትግሉ መሪዎች በማንኛውም ዋጋ ትግሉን ጠብቀው በድርጅታዊ ማዕቀፍ ወደፊት ማስኬድ ይኖርባቸዋል።
የእኛ ትግል ሙሉ ስርዓታዊ ለውጥ ለማምጣት እስከሆነ ከዚህ ውጪ የሚቀሳቀስ የትግል መሪም አባልም በጋራ ሁላችንም ልንታገለው ይገባል። ጉዟችንን ወደ ምንፈልግበት፤ የአሸናፊነት ዋንጫ ወደምናነሳበት ከባቢያዊ እና ፖለቲካዊ የስበት እንዲሄድ ሁሉም መስራት አለበት። ለዚህም የትግሉ መስመር በእንቅፋትነት የተጋረጠ ማንኛውንም አካል ገለል ማድረግ ያስፈልጋል። ከአገዛዙ ጋር የሚደረጉ ንግግሮች ውይይቶች በሚል ሽፋን የሚካሄዱ ፖለቲካዊ ግልሙትናዎች ትናንት ስናወግዝ ነበር ዛሬም እናወግዛለን ነገም እንታገላለን።
ብሩክ ስለሽ(ኢ/ር)
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
አማራነትን -ማንበር ዛሬ ነው!!
--------------------------
የታላቁ አብዮታችን ቋሚ ፎርሙላ አማራነት ብቻ ነው።
ከዚህ ውጭ ያለው ልዋጭ መንገድ አይጠቅምም!!
በሁኔታዎች መለዋወጥም ይሁን በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች የማይቀየረው የትግላችን ቋሚ ፎርሙላ አማራነት ብቻ ነው።
የግዙፉ አብዮታችን መሰባሰቢያ የትግል መስመራችን አማራነት ብቻ ነው።
ስለ አማራነት መስመራችን ትውልድ ሁሉ መሰረታቸው ስለመሆኑ በዘመናችን ታላቁ አብዮት ውስጥ በቀደምትነት ከምንሰራችን ስራዎች ውስጥ አንዱ ነው።
ትግላችን ትክክለኛው መስመር ውስጥ ነው የምንለው ጊዜ የማይሺረውን፣ሁኔታዎች የማይለውጡትን እና የቀጣይ ጉዟችን ግብ የምናሳካበት አማራዊ አስተሳሰብ ስናስቀድም ብቻ ነው። የትግላችን ዋና መርህ አድርገንም ስንገዛበት ብቻ መሆኑን ልብ ይሏል!!
ስለ አማራነት የምንከፍለው ዋጋ ሁሉ በደም ይፀና ዘንድ መንገዳችን እና መዳረሻችንን የሚበይነውን አማራነት እናስቀድም!!
የታላቁ አብዮታችን ቋሚ ፎርሙላም እናድርገዋለን!!
የአማራ ህዝብ ትግል ታላቁ አብዮት ከሚመራባቸው ቀዳሚ ፎርሙላዎች ውስጥ አማራነት አንዱ መሆኑን ህዝባችን፣የትግሉ ባለቤቶች እና ደጋፊዎችም በጥልቅ እንዲገነዘቡት ማድረግ ይበጃል!!
አማራዊ ዕሳቤን ማፅናት የአንድ ሰሞኑን ስራም አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
በታላቁ አብዮታችን ውስጥ ቀድመው ከሚሰመሩ ነገሮች ውስጥ መስመር፣ስልት እና ግብ ዋናኞቹ ናቸው።
በመሰረታዊነት የአማራ ህዝብ ትግል ቀደም ባሉት ዘመነ -መንግስታት በሀሰት ትርክት በርከታ ያሉ ግፎችን ማስተናገዱ ይታወቃል።
በስቆቃው እና ሰው ሰራሺ ጥቃቱ ደግሞ ታላቁ የአማራ ፋኖ አብዮት ተወልዷል።
ስለዚህ የአብዮታችን የመጨረሻው ግብ ደግሞ ስርዓታዊ ለውጥ ነው። በትግሉ ውስጥ የሚታዩ በጎ ያልሆኑ ነገሮችን በተለይም የመስመር ብዥታን፣የዓላማ ጥራት እና ስልተ ግብን ሁሉም ባለድርሻ በዓይን ጥቅሻ እስኪግባባ ድረስ መስራት ይኖርብናል።
ዕሳቤ ሂደታዊ እንጅ እለታዊ አለመሆኑ የሚታወቅ ነው።
የትግላችን ፎርሙላ እና ማጠንጠኛው እንደት እየሆነ ነው የሚለውን በጥልቀት እና በጥራት መገምገም አንዱ መሰረታዊ ተግባራችን መሆን ይኖርበታል።
በአማራነት መስመራችን ላይ በእጅጉ ጠንክረን ልንሰራ ይገባል።
የብሄርተኝነት አስተሳሰብ ለአማራ ህዝብ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ በመቆየቱ በቶሎ ለማስረፅ አስቸጋሪ እንደነበረ ብዙዎቻችን እናውቀዋለን።
ስለዚህ የአብዮቱ መሪ የሆን የትግሉ መሪዎች መበርታት፣ዘመኑን መዋጀት እና የሀገረ መንግስታት በሉላዊነት ዘመን እያደገ በመምጣቱ ህዝባችንን ከባርነት የምናወጣበት ጊዜው አሁን ነው።
ሁሉ! ነገራችን ከአማራነት በታች መሆኑንም ማመን ያስፈልጋል።
በአማራነት ያልተሰበሰበ እና እንደ አማራ መቆም ያልቻለውን ሁሉ ወደ መስመር ማስገባት ላይ ልናተኩር ይገባል።
አማራ ብሄርተኝነት-መስመራችን
የፓለቲካ ትጥቅ ትግል-ስልታችን
ስር ነቀል ለውጥ -ግባችን መሆኑን መላው የአማራ ህዝብ ሰራዊታችን ሊያውቃቸው እና ፎርሙላዎቹም እነዚህ መሆናቸውን ለተከታዮቻችን በደንብ ልናሰርፅ ይገባል!!
አማራነት ዕጣ ፋንታችን ብቻ ሳይሆን ግደታችን ነው።
"አማራነትን-ማንበር" ዛሬ ነው።
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
ጥር 01-05-2018
የምኒልክ ዕዝ 2ኛ ዙር የፓለቲካ መኮነን ሰልጣኞችን በደማቅ ሁኔታ ተመረቀ::
የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ምኒልክ ዕዝ "ፀሀፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ" የፓለቲካ መኮነኖች ማሰልጠኛ ማዕከል በምዕራብ ወሎ ግንባር ሰሞኑን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል::
ይህን አስመልክቶ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ቃለአብ ወርቅዬ መልዕክት አስተላልፏል::
በቅድሚያ ውድ የዛሬ ተመራቂዎች እንኳን ለዚች ቀን አደረሳችሁ አደረሰን::
ከምረቃው በተጨማሪ በምዕራብ ወሎ ግንባር ስምንት ወረዳዎችን ያካለለ የማጥቃት ቅንጅታዊ ዘመቻን ተከትሎ በኮራችን ሰራዊት በተፈፀመው የጦር ሜዳ ጀብዱ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፦ ለክርስትና እምነት ተከታይ አርበኞች እና ለመላው የእምነቱ ተከታዮች በሙሉ የመልካም የገና በዓል ምኞቴን የምገልፅላችሁ "የእዳ ደብዳቤያችን ይቀደዳል፣ አማራ ዳግም ይወለዳል!" በማለት የዕዛችን የፖለቲካ መምሪያ ያሰራጨውን የበዓል መልዕክት አርዕስት በማስታወስ ጭምር ነው::
የዕዛችን የፓለቲካ መምሪያ በመልዕክቱ የድርጅታችን እና በተዋረድ ያለዉ መላው የፖለቲካ አመራሩ ወታደራዊ ኃይሉ ያገኘውን ድል በፖለቲካውም መድገም ግድ ነው። ስለሆነም እንደ ትናንቱ ሁሉ ነፃ በወጡ ቀጠናዎች ህዝብን ማደራጀትና ንቅናቄ መፍጠር፣ አዲስ ኃይል መመልመል፣ የህዝብ ተቋማትን በመጠበቅ፣ የሲቪል አደረጃጀት ማዋቀር እና ሌሎች ፖለቲካዊ ተግባራት አበክራችሁ እንዲትሰሩ በጥብቅ እናሳስባለን ማለቱ ይታወሳል:: ይህን የአደራ መልዕክት እና የዕዛችንን የፓለቲካ መምሪያ ትዕዛዝ በማክበር ተቆጥረው የተሰጡ ስራዎችን በእውቀት እና በእውነት መስራት የሚችል ብቁ እና ንቁ ኃይል ለማፍራት በማሰብ የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲሰራ እንደነበር ልብ ይሏል::
በዚህም መሰረት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የፓለቲካ መምሪያ ከዕዙ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ጋር በመተባበር ከንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር 5 ክፍለ ጦሮች ለተውጣጡ አርበኞች የፓለቲካ መኮነንነት ስልጠና ሲሰጥ መሰንበቱ ይታወቃል:: ብቃት ያላቸውና የመውጫ ፈተናውን ከግማሽ በላይ ውጤት በማምጣት ማለፍ የቻሉት ሰልጣኞች በትናንትናው እለት ለምረቃ ዝግጁ ሆነው ቀርበው ሊመረቁ ችለዋል::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ትምህርት እና ስልጠና መምሪያ የመደባቸው ባለሙያዎች ስልጠናውን ሰጥተዋል::
ስልጠናው ፓለቲካዊ ብቻ ሳይሆን ወታደራዊ መልክ የነበረው ሲሆን ጄኔራል ተፈራ ማሞ ጭምር ለሰልጣኞች ልምዳቸውን አካፍለዋል:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ኃላፊ ኮማንዶ ዮሴፍ አስማረ እና ምክትሉ ኮማንዶ ጌታቸው ሲሳይ በአካል ተገኝተው ለፓለቲካ መኮንኖች የወታደራዊ ስልት ስልጠና ሰጥተዋል:: የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ወታደራዊ ባለሙያ እና አሰልጣኝ የሆነው የቀድሞው አማራ ልዩ ኃይል የአባይ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራር ሻለቃ ክንዱ ሰውነት እንድሁም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሜካናይዝድ ሞርተር አሰልጣኝ መቶ አለቃ ታደሰ አስፋው ለፓለቲካ መኮንኖች ወታደራዊ ትምህርት እና ስልጠና ሰጥተዋል:: ሰልጣኞች በፓለቲካው ብቻ ሳይሆን በወታደራዊው ዘርፍ ብቁ እንድሆኑ የማድረግ ስራ ተሰርቷል::
የጀመርነው የህልውና ትግል በትጥቅ የታገዘ የፓለቲካ ትግል እንደመሆኑ መጠን ፓለቲካው ጠብመንጃውን ማዘዝ እንዳለበት፣ እያንዳንዱ የምንተኩሰው ጥይት የፓለቲካ ውጤት ስሌት ውስጥ መግባት እንዳለበት፣ ጦርነቱ በፋኖ በኩል ፍትሐዊ ጦርነት ሊባል የሚችል ስለሆነ የፍትሐዊ ጦርነት መለኪያዎችን በሙሉ ከግምት ባስገባ መልኩ ትግሉ እንድቀጥል ማድረግ እንደሚገባ፣ ፋኖ የአማራ ህዝብ ተስፋ እና የደህንነት ዋስትና ሆኖ እንድቀጥል ሁሌም የህዝብን ፍላጎትና ክብር መጠበቅ እንደሚገባ፣ ትግሉ በእውቀት፣ እውነት እና በጠንካራ አመክንዮ መመራት እንዳለበት፣ ለፋኖ የሚያስፈልግ የገንዘብ እና ቁሳቁስ ድጋፍ አሰባሰብ ሂደት መቀየር እንዳለበት እንድሁም ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንድሰፍን፣ የአማራ ህዝብ ራሱን በራሱ እንድያስተዳድር፣ ፋኖ በሲቪል አስተዳደር መዋቅር ውስጥ ጣልቃ የማይገባበትና ህዝባችን ለአካባቢያዊ ችግር አካቢያዊ መፍትሔ የሚሰጥበት የፓለቲካ ምሕዳር እንዲፈጠር ወዘተ አይነት የትግሉ መፍትሔ የተባሉ ሀሳቦችን በተግባር መተርጎም ይችሉ ዘንድ የንድፈ ሀሳብ እና ፅንሰ ሀሳብ ስልጠና የተሰጣቸው የፓለቲካ መኮንኖች ከምረቃቸው ዕለት ቀደም ባሉት ተከታታይ 2 ሳምንታት ከ20 በላይ ህዝባዊ መድረኮችን እንድመሩ ተደርጓል።
ሰልጣኞች ፓለቲካ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና የመንግስት ኃላፊነት ከምን እስከ ምን እንደሆነ ጭምር ተረድተው ትግሉን በእውቀት ለማስኬድ የሚችሉበት ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል።
ሰልጣኞች የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያን የሰራ እና ሉዓላዊነቷን ያስከበረ ባንዲራዋንም ያላስደፈረ ህዝብ መሆኑን በአግባቡ ይገነዘቡ ዘንድ የሚያስችል ትምህርት የተሰጣቸው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ስለ ማህበረሰብ እና መንግስት ግንኙነት፣ ስለ ዜጎች መብት እና ነፃነት ስለ አማራ ብሔርተኝነት ውልደት እና እድገት፣ እድሎች እና ተግዳሮቶች፣ ስለ አማራነት እና ኢትዮጵያዊነት፣ ስለ ፀረ አማራ ትርክት፣ ስለ አማራ ዘር ፍጅት እና የህልውና ትግል፣ ስለ ፋኖነት ከትናንት እስከ ዛሬ፣ ስለ አማራ ፋኖ ትግል ስረ ምክንያት፣በትግሉ ሂደት ማለትም ከ2015-2018 ዓ.ም ስለተስተዋሉ ችግሮች መነሻ እና ውጤት እንድሁም የማስተካከያ እርምጃዎችን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል::
የእምዬ ምኒልክን የአመራር ጥበብ በማስታወስ በምኒልክ መንገድ ሀገር የማትረፍ እና የመስራት እንድሁም አማራን ከፈጽሞ ጥፋት የማዳን ኃላፊነት የተጣለባቸው የዛሬ ተመራቂዎች ከፀሀፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የፓለቲካ መኮንኖች ማሰልጠኛ ማዕከል ያገኙትን እውቀት ወደ መሬት አውርደው ችግር ፈቺ እንድሆኑና ፋኖን ከህዝብ ጋር ማቀራረብ እንድችሉ ይጠበቃል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም
ልክ በዚህ ስዓት 8:20
በደብረ ማርቆስ ከተማ የደፈጠው የአረመኔው ሰራዊት አገልጋይ የሆነው ታዘብ ምን ይዋብ የተባለ ፖሊስ በራሱ ጓደኛ በጥይት ተመቶ ሆስፒታል ቢገባም ህይወቱ አልፎ በሆስፒታሉ የአስክሬን ማውጫ በር በኩል በኬንዳ ተጠቅልሎ በፖሊሶች ታጅቦ እየወጣ ነው።
ሌላኛው የፌዴራል ፖሊስ አባል የሆነው ሲሳይ ገነነ ደግሞ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ከመጠን በላይ በመጠጣት ተማሪዎችን እያመሳቸው መሆኑን አረጋግጠናል።
@ Baye Desta per
ሰበር የድል ዜና
🔶 ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር የቡድን መሳሪያዎችንና የመገናኛ ሬድዮችን ጨምሮ በርካታ የጠላትን ኃይል መማረኩ ታወቀ።
ዛሬ ጥር 01/2018 ዓ.ም ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር አካሎች በምስራቅ በለሳዊቷ ጣይመን ከተማ ሰፍሮ የሚገኘውን የብልጽግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት በ3 አቅጣጫ ወደ ካምፑ ዘልቆ በመግባት ሲያበራዩት አርፍደዋል።
በጨበጣ ዉጊያ የጠላትን 2 ምሽጎች በመደረማመስ የአብይን ግብስብስ ኃይል እያራወጡ ሻምበል መሪዎችን በመደምሰስ ቁሪዎቹን አባላት ሙት ቁስለኛና በመጨረሻም ምርኮኛ አድርገዋቸዋል ።
🔶 በዚህ አውደ ዉጊያ ላይ የኮሩ ተወርዋሪ ኃይል ፣ አፄ እያሱ ክ/ጦር ፣ ዞዝ አምባ ክ/ጦርና የንስር በለሳ ክ/ጦር የተወሰኑ አካላት እንዲሁም የኮሩ የስራ አስፈፃሚ አካላት በውጊያው በመሳተፍ ጠላትን አንገት ያስደፋ ድል እንዲመዘገብና ጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦር የቆረጣ ውጊያ ስልትን በመጠቀም የጠላትን ኃይል አንገት አስደፍቶ እንዲማረክ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል ።
🔶 በውጊያው ከተገኙ ድሎች መካከል
** 1000 የብሬን ተተኳሽ ተማርኳል
** 2000 የክላሽኮኘ ተተኳሽ ተማርኳል
** 100 የእጅ ቦንብ /f1 ማለት ነው /ተሟርኳል
** 2 የመገናኛ ሬድዮ
** 3 ብሬን /መትረየስ /
** ከ55 በላይ ክላሽኮኘ ጠመንጃዎች ተማርኳል።
ከወታደራዊ ቁሳቁሶች መካከል ገቢ የተደረጉ ሲሆን በሰው ኃይልም ከደረሰበት ኪሳራ መካከል
** 25 መከላከያ እስከ ሙሉ ትጥቁ ተማርኳል።
** 37 በላይ መከላከያ እስከ ወዲያኛው ተሸኝተዋል
** 35ቱ ደግሞ ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን በዚህ ምክንያትም የጓህላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልና አርባያ ሆስፒታል በቁስለኞች መጥለቅለቁም ታውቋል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ
ዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
አብነት ሞላ
ጥር 01 /2018 ዓ.ም
የገና በአል በመጫወትላይ በነበሩ 5 ህፃት በሚኒሻ ተተኩሶባቸው ቁስለኛ ሆነዋል።
➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺
በአማራ ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል እየፈፀመ ይገኛል ንፁሃንን ህፃናትን ሳይቀር እየቀጠፉ ነው የበዓል ጨዎታቸውን ተጫውተው መግባት አልቻሉም በዚህ ቀን ልጆቹ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ጨዋታዎችን የሚያደርጉበት ልዩ ስጦታ ቀን ነች።
የአማራ ባህል እንዲታይ አገዛዙ ፍፁም አይፈልግም በተግባርም ሰዴ ወረዳ ላይ በገና በዓል በአገዛዙ ትዕዛዝ ኃይማኖታዊና ባህላዊ የህፃናት ጨዋታ ስርዓት ላይ የተኩስ ሩምታ በመክፈት ህፃናት ቀስለኛ ሆናዋል።
ከአገዛዙ ትዕዛዝ ተቀበለው በህፃናት ላይ በጥይት የአካል ጉዳትና በህዝባችን ዘንድ የሞራል ስብራት አድርሷል ከ12 ዓመት በታች ባሉ ህፃናት ላይ እንደሆነ ማረጋገጥ ችለናል።
ሰዴ ላይ በሚሊሻ ተተኩሶባቸው የቆሰሉ ህፃናት ስም ዝርዝር ፦
1ኛ አታላይ ተሾመ =11ዓመት
2ኛ ኤርሚያስ ይርጋ=12ዓመት
3ኛ በቃሉ ሞላ=10ዓመት
4ኛ ይኸነው ስማቸው=9ዓመት
5ኛ ይረፉ አስናቀ=12ዓመት ሲሆኑ
ቀጥታ ከአገዛዙ አረመኔ ሰራዊት ትዕዛዝ ትዕዛዝ ተቀብሎ ህፃናትን ያቆሰሉ የሚኒሻ ስም ዝርዝር ፦
1ኛ በላይነህ 2ኛ ይገርማል 3ኛ ድረስ ግዛ 4ኛ ፈጠነ አድማስ 5ኛ ታረቀኝ አበባው የሚባሉ ናቸው። ከህዝባችን የሚሰወር አንዳችም ነገር የለም ሁሉም ዋጋቸውን የሚያገኙ ይሆናል።
አዲሱ ትውልድ፣በአዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
አፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም
በአገዛዙ በድሮንና በመድፍ የታገዙ ሁለት የኮማንዶ ክፍለጦሮችንና የሁለት ዕዝ ሰራዊትን ከሚኒሻና አድማ ብተና አባላት ጋር አጣምሮ አስልፎ የተዋጋበትና፡ ይህ ሁሉ ግትልትል ሰራዊት የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት "ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም" የተባለበትን ሽንፈት የተከናነበበት አውደ ውጊያ!
ከላላ ወረዳን ጨምሮ በበርካታ የምዕራብ ወረዳዎች ላይ ታህሳስ 28/2018 ዓ/ ም ከንጋት ጀምሮ እስከ ምሽት ከባድ ውጊያ መደረጉን በእለቱ መረብ ሚዲያ በሁሉም የማህበራዊ ትስስር ገፆቹ መዘገቡ ይታወቃል።
በውጊያው፡ አገዛዙ ከድሮን ጀምሮ በመድፍና በቢኤም እንዲሁም በሞርተርና በዙ23 የታገዙ ሁለት የኮማንዶ ክፍለጦሮችን እና ከሁለት ዕዝ የተወጣጣ ሰራዊትን አሰልፎ የነበረ ቢሆንም፡ ነገር ግን "ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ" የተባለው አባባል ደርሶበት በጥቂት የፋኖ አሃዶች የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋምም ባለመቻሉ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላዊ ኪሳራን ተከናቧል።
ውጊያው የተካሄደው በጃማ፣ በከላላ፣ በልጓማ፣ በደብረዘይት፣ በለገሂዳ፣ ገነቴ፣ በመኃል ሳይንት ደንሳ ከተማ፣ በተንታ አጅባር፣ በመቅደላ ማሻ፣ በጉጉፍቱ፣ ካቤ እና በሰኞ ገበያ ላይ ነው።
በአፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ከሶስት ኮሮች ማለትም ከንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር፣ ከልጅ እያሱ ኮር እና ከደጋው መብረቅ ኮር፣ እንዲሁም የዕዙ ልዩ ዘመቻ አሃድ ከሆነችው ከበላጎ ተወርዋሪ ሻለቃ የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች እና ከአፋህድ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝና ከወሎ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተወጣጡ የፋኖ አሃዶች ጥምረት በመፍጠር ነው በጠላት ብልፅግና ቡድን ወታደሮች ላይ ጥቃት የከፈቱት።
በአገዛዙ በኩል በአየር ወለድ ኮማንዶ መምሪያ የ105ኛ እና የ107ኛ ክ/ጦር ኮማንዶዎችን ጨምሮ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የ801ኛ ኮር ሰራዊትና የ11ኛ ዕዝ ወታደሮች እንዲሁም የደቡብ ወሎ ዞን "መከታዎቼ" ሲል የሚመካባቸው <ፓራ ኮማንዶ> የሚል መጠሪያ ያላቸው የሚኒሻ አባላትና የአድማ ብተና አባላት በወረዳ ካድሬዎች መንገድ መሪነት የድሮንና የመድፍ፣ የዙ23ና የሞርተር እንዲሁም የቢኤም ሽፋን እየሰጠ ያሰለፈ ቢሆንም፡ ነገር ግን "ሺ ፈሳም አንድ ጎማ አይነፋም" ነውና ነገሩ ይህ ሁሉ ግትልትል ሰራዊት የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቶት ከባድ ሽንፈትን ተከናንቦ ውሏል።
በውጊያው አራት ብሬን፣ አንድ ስናይፐር እና 170 ክላሽንኮቭ መሣሪያ፣ ሁለት ወታደራዊ ኦራል ተሽከርካሪዎች ከነጫኑት ሬሽንና ተተኳሽ እና 146 ወታደሮችና በርካታ ወታደራዊ መገንኛ ራዲዮኖች በፋኖ መማረካቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በተጨማሪም የጠላት ብልፅግና ቡድን ከላላ ወረዳ ውስጥ ለገና በዓል ለእርድ አዘጋጅቷቸው የነበሩ አራት ሰንጋ በሬዎችና በርካታ ኩንታል የምግብ እህል በፋኖ ቁጥጥር ስር ውሏል።
በዚህ ውጊያ ከተገደሉት በመቶዎች የሚቆጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የሚኒሻ እንዲሁም የአድማ ብተና አባላት በተጨማሪ መንገድ ሲመሩ የነበሩ በርካታ የወረዳ አመራሮችም ተገድለዋል፡ከፊሎቹም በከባድ ሁኔታ ቆስለዋል።
መከላከያን መንገድ ሲመሩ ተገኝተው ከተገደሉ የወረዳ አመራሮች መካከል የከላላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት እቃ ግምጃ ቤት ሃላፊ አቶ አሚኑ አህመድ፣ የወረዳው ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አሊ አህመድ የሱፍ፣ እንዲሁም የወረዳው ሚልሻ ፅ/ቤት የሰላም አስከባሪ ሂደት ኃላፊ ሳጅን አልዩ አህመድ አብዲን ጨምሮ ሌሎች የወረዳው ፀጥታ ቢሮ አመራሮችና አባላት እንደሚገኙበት ታውቋል።
ይሄንን ተከትሎ የከላላ ወረዳ አስተዳደር ከታህሳስ 28/2018 ዓ/ም ምሽት ጀምሮ እስከ ትናንት ታህሳስ 30/2018 ዓ/ም ለአምስተኛ ጊዜ የሐዘን መግለጫ ማውጣቱን መረብ ሚዲያ ከወረዳው ይፋዊ የማሕበራዊ ትስስር ገፅ ተመልክቷል።
ወረዳው በመግለጫው፡ ከአመራሮቼ መካከል አንዳንዶቹ በተኙበት ነው የተገደሉት ያለ ሲሆን፡ ሌሎቹ ደግሞ በውጊያ መኃል የተገደሉብኝ ናቸው ማለቱን ነው መረብ ሚዲያ የተመለከተው።
(ምስል፦ በእለቱ በፋኖ ከተማረኩ የጦር መሣሪያዎች መካከል ጥቂቱ)
መረብ ሚዲያ
