ፍኖተ-አሻራ ሚዲያ (Finote Ashara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 134
Подписчики
Нет данных24 часа
+4247 дней
+1 14930 дней
Архив постов
ሰበር ዜና
ባሕር ዳር ቀበሌ 14 በተኩስ እየተናጠ ነው።
የጎርደማ ቅዱስ ገብርኤልን እየሸኘ ባለ ሕዝብ የተኩስ እሩምታ ተከፍቷል።
ሕዝቡ ታቦቱን ትቶ ወደ ቤት እየገባ ነው።
ህዝባችን እንዳይደናገር
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ቴወድሮስ ዕዝ ከአንድነታችን የምስረታ ሂደት ጎን ለጎን ህዝብን የሚያማርሩ፣ የጠላትን ተልዕኮ ተቀብለው የአቆርቋዥነት ሚና የሚጫወቱ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን ስርዓት የማስያዝ ስራ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት የጠራ ድርጅታዊ ተልዕኮውን በመፈፀም ላይ የሚገኘው የእዙ 206 ኛ ኮር በባሶ ሊበን አካባቢ የሚንቀሳቀሰው የአብራጂት ሻለቃ አካል የነበረው አስጨነቅ የሚመራው ቡድን ላይ የህግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ይታወቃል።
ለኮሩ ህግ አስከባሪ ኃይል እጅ በመስጠት በስርዓት እና በድርጅት ከመታገል ይልቅ ለአረመኔው ጠላታችን እጅ መስጠትን የመረጠው አስጨነቅ ጥቂት የስጋ ዘመዶቹን እና የሻለቃዋን የቡድን መሳሪያ በመያዝ ፈርጥጦ ለጠላት እጁን ሰጥቷል።
ህዝባችን ይህንን ተከትሎ በሚለቀቅ ሀሰተኛ የፕሮፖጋንዳ ሱናሜ እንዳይደናገር እናሳስባለን።
+5
☦እንኳን_ለጥምቀት_በዓል_አደረሰን☦
ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዕምነት ተከታዬች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ ፣አደረሰን🙏
#መልካም_የጥምቀት_በዓል
11/ዐ5/2018 ዓ.ም
እንኳን ለመላው ኦርቶዶክስ የመድኃኔዓለም እየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
የአርበኛ እሸቱ የፊስቡክ ፒጅ ስለተዘጋ follow በማድርግ ይወዳጁን
https://www.facebook.com/share/p/19PQwqrkkv/
+2
ታላቅ ስቦ የማስከዳት ዜና
የጥምቀት ስጦታ፤
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በተመሰረተ ማግስት 11/05/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦ ደጋ ዳሞት ሻለቃን ሁለት ክላሽ አንድ #ስናይፐር በመያዝ ተቀላቅለዋል ::
1.አወል መኩሪያ 1 ጥቁር ክላሽ 2 ካዘና 90 ጥይት
2. ተሾመ ግርማ - 1 ማይካ ክላሽ 90 ጥይት 2 ካዘና
3.በደው ደገፈ 1 እስናይፐር በመያዝ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
# አንድ አማራ
# ድል ለተገፋው ለአማራ ሕዝብ
# ድል ለፋኖ
Dejen M Endale
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ፤
ጥር 11/2018 ዓ/ም
√ ትግላችን ቁሳዊ ሳይሆን ሰዋዊነትን መፍጠር ነው !
ትግላችን ለስልጣን ፣ ለቁሳዊ እና ለቅንጦት ሳይሆን በሴራ ፖለቲካ ( conspiracy politics) የጠፋን ሰዋዊነትን ወይም ትውልድን መፍጠር እና አሁን ያለውን ትውልድ ከጨርሶ መጥፋት ማዳን ነው ። ይህ ትውልድ የዘር ማጥፋት ፣ የህይወት ምስቅልቅል ፣ ለዘመናዊ ባርነት እና የሰው ልጅ የህይወት መሰረት የሆነውን ትምህርትን እንዳያገኝ / እንድጠቀምበት ሳይሆን በሴረኞች ለሴራ ፖለቲካ እንድጠቀሙበት ለሰው ሳይሆን ለቁስ ቅድሚያ እንድሰጥ አድርገውታል እያደረጉትም ነው ። ይህ ማለት ትውልዱ ሰዋዊ ሳይሆን ቁሳዊ ትውልድ ነው ማለት ነው ። ይህ አይነት ቁሳዊ አስተሳሰብ ያለው የአንድት ሀገር ትውልድ መፈጠር ለሀገርም ይሁን ለህዝብ እጅግ አደገኛ ነው ፣ ይህ ትውልድ የሴራ ፖለቲከኞች ቤንዚን / the conspiracy politics gasoline / ይባላል ።
የሴራ ፖለቲከኞች ቤንዚን የሆነው ትውልድ ከሳይንስ የራቀ (ከፖለቲካዊ አስተሳሰብ / እውቀት / ነፃ የሆነ ነገር ግን ለፖለቲካ ሴራው ጥሩ ቤንዜን እንድሆን ፊደል ብቻ እንድቆጥር ተደርጎ የተፈጠረ ነው ። ይህ ትውልድ አሁን በዚህ በኛ ትግል ቁልጭ ብሎ እያየነው ያለ ነው ። ትግል ምን እንደሆነ ሳያውቅ ፣ ፖለቲካ ምን እና እንደት መካሄድ እንዳለበት የማያውቅ በእሱ አስተሳሰብ ግን ትግል ማለት መተኮስ እና መግደል የሚመስለው ስለ ትግል እና ስለ ፖለቲካ ሲተነትን አስተያየት ሲሰጥ ፣ እኔ ያልኩት ካልሆነ ይልሃል ነገር ግን እሱ ያለው በምን እና በማን እንደመጣ አያውቅም እሱ ተቀብሎ መ ማገር ብቻ እንጅ ምክንያቱም ትውልዱ the conspiracy politics gasoline ስለሆነ እና ተሰላቢ ስለሆነ ነው ።
ብዙ ውጣ ውረድ እና ብዙ መፅዋነት ተከፍሎበት የተመሰረትን ድርጅት እንደቀላል ሲተች ሲሳደብ ታየዋለህ ፣ ከዛ በፊት ግን እሱም አንድ ሁኑ እያለ ሌት ተቀን ሲለፈልፍ ነበር ። አማራ አንድ እንድሆን ይፈልግ ይሆናል ። ግን አንድ የሚሆንበትን መንገድ እንደት እንደሆነ አያውቅም ምክንያቱም ፊደል መቁጠሩን እንጅ መረዳቱን አያውቅም ። ስለዚህ የአማራ ትግል ቁሳዊ ጥቅምን ሳይሆን ሰውን መፍጠርና ትውልድን መታደግ ነው ። ይህንን ትውልድ የምንታደገው ደግሞ ዘርፈ ብዙ ትግል በማድረግ ነው ። ታጋይ ማለት መተኮስ ማለት ሳይሆን ታጋይ ማለት መምህር ነው ፣ ተማሪ ነው ፣ ፈጣሪ ነው ተራማጅ ነው ፣ ፊደል አስቆጣሪ ነው፣ ረህሩህ ነው ፣ ታጋይ ማለት ሰዋዊ ነው .....ስለዚህ ታጋዮች ታጋይ መሆን ይገባቸዋል ።
ትግል ማለት ምን ማለት እንደሆን እንወቅ ፣ ፖለቲካ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንወቅ ፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን አሁን ባለንባት በብልፅግና ዘመን የሴራ ፖለቲካ ተሰላቢ እና የሀያላን ሀገሮች የመተኮሻ ጥይት ሆነናል ምክንያቱም ሀገራችን እንደገር ትክክለኛ መንግስት ስለሌላት ። አንድ ሀገር ጠንካራ መንግስታዊ መዋቅር ለኖረው የሚችለው ጠንካራ ድፕሎማሲ እና ህዝባዊ ድጋፍ ሲኖረው ነው ፣ ጠንካራ ፖለቲካዊ ሀይል እና ጠንካራ ወታደራዊ ሀይል ሶኖረው ነው ፣ስለዚህ ብልፅግና በየትኛውም ሀይሉ ነው ሀገርን እንድ ሀገር መምራት የሚችለው ? ብልፅግና የሀገር ዘብ ሳይሆን የሀያላን ሀገሮች መተኮሻ ጥይት ነው ። ብልፅግና መቀበል እንጅ መወሰን አይችልም ምክናየቱም ከላይ የዘረዘርኩዋቸው ስለሌሉ ፣ ይህ ሊሆንበት የቻለው በብልፅግና ውስጥ ፖለቲካዊ ሀይል ስለሌለ የብልፅግና አመራሮች የፖለቲካን ሽፍጥ ሳይረዱ በሌሎች ሀገሮች ተልዕኮ ሌላ ሀገር በመግባት ጦርነት ስለሚገቡ ይህ ደግሞ እጅግ አደገኛ የድፕሎማሲ ማሳጫ የፖለቲካ ስልት ነው ።
በመጨረሻም ብልፅግና በየትኛውም ቦታ ትንኮሳ ቢመጣበት እንዴ ኤርትራ እና ሱዳን ጦርነት ቢስነዝሩ የጦርነቱ ምላሽ የሚወሰነው በብልፅግና ሳይሆን በተኮሾቹ በሀያላን ሀገሮች ነው ። ይህ ማለት ብልፅግና ተተኳሽ እንጅ ተኳሽ እና ወሳኝ አይደለም ማለት ነው ። እናም ወገኔ የፖለቲካን ሴራ እና የትግልን ምንነት ሳታውቅ አማራ ከኤርትራ እና ከህውሃት ጋር ይሰራል ልትል አትችልም ፣ አማራ አይደለም ሳይወድ በግዱ መስራት ካለበት ከህውሃት ጋር ይቅርና ለትግላችን አስፈላጊ ከሆነ ከሰይጣንም ጋር ለመስራት ዝግጅት ነን ። የአማራ ትግል ለዘር ወይም ቀለም ሳይሆን ለሰዋዊነት ይታገላል ።
ትግላችን ይቀጥላል ።
በደብረ ማርቆስ ከተማ በ4ኛ ፖሊስ ጣቢያ በተደረገ ኦፕሬሽን ሀሰን የተባለው ፖሊስን ጨምሮ 3 የሚኒሻ አባላት በቦንብ ጋይተዋል"
ጥር 10/2018 ዓ.ም
===============
የአረመኔው የአብይ አህመድን ስርዓት በአዲስ መንፈስ እያፍረከረከው የሚገኘው የአፋብን ምስረታ አስመልክቶ 206ኛ ኮር በቁይ እና ደብረ ማርቆስ ከተሞች ከሌሊቱ 6:00 ጀምሮ ከባድ ጥቃት በመክፈት የጠላትን ሰራዊት በተኛበት አፈር ካለበሱት በኋላ የከተራን በዓል ወጣቱ የአርበኛ ዘመነ ካሴን ስም በማውሳት በከተሞች የሚከበረውን የከተራን በዓል አጅበውት ውለዋል።
የጠላትን ሰራዊት በምሽጉ እንዲያደፍጥ በማድረግ በተመረጠ ቦታ ላይ አስደናቂ ጥቃት የከፈተው የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከሌሊቱ 6:40 በአደረጉት የቦንብ ጥቃት ሀሰን የተባለውን ፖሊስ ጨምሮ 3 ሚኒሻዎች ሲገደሉ ሁለት ከደብረ ኤልያስ ከተማ የመጡ ሚኒሻዎች ከባድ ቁስለኛ ሁነው አንሙት የሚባል የአድማ ብተና አባል በጣረ ሞትላይ ይገኛል።
ጠላትን በማናጠል የተጠና ኦፕሬሽን የሚፈፅመው 206ኛ ኮር ደብረ ማርቆስ ከተማ የመሸገውን ጠላት እያፍረከረከ መግቢያ መውጫ እያሳጣው ነው።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+1
ውዱ መሪያችን ዋርካዉ ምሬ ወዳጆ እንዲህ ደምቆ ከተራን ታድሟል‼️💪💪💪
በሁለት አመቱ የትግል ታሪክ ዉስጥ ብቸኛዉ ሁለት የአብይን ክፍለጦርን በአንድ ቀን ዉጊያ አመድ ያደረገ አብይ አህመድ ተመድ ድረስ ከሻቢያ ጋር ወጋኝ ብሎ እንዲያለቃቅስ ያደረገ ብቸኛዉ ሰዉ
ዋርካዉ ምሬ ወዳጆ እንኳን አደረሰህ
ለመላው የማራ ህዝብ፥ ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ፥ ለመላው ፋኖ አባላትና አመራሮች እንኳን ለ 2018 አ. ም የከተራና የጥምቀት በአል በሰላም አደረሳችሁ፥አደረሰን!!
የአብይ አህመድን አገዛዝ ከስሩ ነቅሎ በማስወገድ የአማራን ህልውና በዘላቂነት ማረጋገጥና ሁሉም ኢትዮጲያውያን ወገኖች በፍትህ፥ በነፃነት፥ በእኩልነትና በአንድነት የሚኖሩበት ዴሞክራሲያዊ ዘመንን ማብሰር ከሆነው ዋናው ግባችን አንድ ጋት ርቆ አንድ ወሳኝ፥ የግድ ቀድሞ መከናወን ያለበት መለስተኛ ግብ ነበረን፦ የአማራን ትግል መዋቅራዊ አንድነት ማረጋገጥ።ከብዙ ጥረትና ጥበብ በኋላ ትናንት ጥር 9/2018 አ.ም ይህን አሳክተናል።
መላው የአማራ ህዝብ፥ መላው የአማራ ፋኖ አባላትና አመራሮች እንዲሁም መላው ኢትዮጲያዊ ወገናችን እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ ያለን!!
ጠላትን በአውደ- ፖለቲካ አሸንፈነዋል፥ በአውደ-ውጊያም አዝረክርከነዋል፥ በስነ-ግንኙነት(ዲፕሎማሲ) አሳጠነዋል፥ በኢኮኖሚ ራቁቱን አስቀርተነዋል። ያም ሆኖ የትግሉ ወታደራዊ፥ ፖለቲካዊና ሁሉን አቀፍ አቅም በአንድ ቋት ባለመሰብሰቡ ምክንያት አብይ አህመድና ቡድኑ ተጨማሪ ቀናትን እድሚያቼው ላይ እየጨመሩ እስከ ዛሬ ህዝባችን እየጨፈጨፉ መዝለቅ ችለዋል።አንድነት ሁሌም በየትኛው ሁኔታ ውስጥ በማንኛውም ወገን ይከወን ትክክለኛ ነገር ነው። ለአማራ ህዝብ ግን አንድነት ዘላለማዊ የግዴታ እጣፋንታው ነው።አንድነት አማራዊ አካላችን የሚያንቀሳቅስ ነፍሳችን ነው። በመሆኑም ዛሬ አንድ በመሆናችን ከነገ ጀምሮ ሞት ላይ እንስቃለን፥ ሞትን እናሸንፈዋለን፥ ሞትን ራሱን እንገድለዋለን።ነፃም እንወጣለን።
የአማራ ትግል አንድ ሆኗል፥ስለ ነገዋ ኢትዮጲያ በጎ ምኞት ካለን ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም። ልዩ ልዩ ኢትዮጲያውያን ወገኖችን የሚወክሉ ልሂቃንና የፖለቲካ ቡድኖች በይፋ መቀራረብ፥መምከር መጀመርና ስለነገ የጋራ ስእል መፍጠር ይኖርባቸዋል።
የቀጠናው ሃይሎች ዛሬ ስለቀጠናው በጥባጭ አብይ አህመድና ቡድኑ መወገድ በጋራ መታገልና መፍትሄ ማዋለድ ይኖርባቸዋል።ስለነገ መጠበብ ይገባቸዋል። ምክንያቱም የአፍሪካ ቀንድ በታሪኩ አይቶት ወደማያውቀው ትብታብ ውስጥ እየገባ ሲሆን ለቀጠናው ህዝቦች ልማትና የጋራ በጎ ተስፋ ልሂቃኑ መቀራረብና የጋራ ህልም ማለም ያስፈልጋቸዋል።በዚህ ረገድ ፋኖ የበኩሉን ገንቢ ሚና ይጫዎታል።
ታላላቅ አሳቢዎች እንዳስተማሩን አንድ ህዝብ ከውጫዊ ወረራ እኩል ወይንም በላይ በሞራል መበስበስ ይወድቃልና ሞራላችን፥ ባህላችን፥የጋራ ማህበረሰባዊ ትውስታዎቻችን፥ እሴቶቻችንና ታሪካችን እንወቅ፥በርትተን እንጠብቅ።አላማና እሴት ያለው ህይወት እንኑር።
"አንድ ማህበረሰብ የሚወድቀው ሁሉም የማህበረሰቡ አባል መጥፎ ስለሆነ ሳይሆን በጎ ሰዎች የዳር ተመልካች ሲሆኑ ነው" ይባላልና "እነ በጎ" በዚህ ትግል ውስጥ የምትችሉትን አድርጉ።ቆሞ መመልከት ቆሞ ከመሞት ውጭ ሌላ ፍች የለውም።
አቢዮቱ የመሳሪያም የቅንነትም ነው። ስለዚህ የምር ቅን እንሁን። ቀደምቶች ሞክረውት የጣላቸውን የክፋት፥ የተንኮል፥ የመጠፋፋት፥ የቅናትና የመጠላለፍ አዳላጭ መንገድ እንፀየፈው።በመደጋገፍ እንጅ በመጠላለፍ ዛሬን ማለፍ አይቻልም።ነገ ላይም አይደረስም፥ ቢደረስም መልካም አይሆንም።
ይህ ድንቅና ለአማራ ህዝብ ከኦክስጅን እኩል ያስፈልገው የነበር አንድነት እንዲሳካ ማስተዋልን የሰጠንን እግዚአብሄር እናመሰግነዋለን።
ይህ ቀን እንዲመጣ ሌት ተቀን የሰራችሁ፥ የገፋፋችሁን፥ የመከራችሁን፥ የገሰፃችሁን፥ ስንደክም ያበረታችሁን የፋኖ አመራርና አባላት በሙሉ፥ በቅርብም በሩቅም ያላችሁ አማራዎችና ሌሎች ኢትዮጲያውያንን ወገኖች ከልብ እናመሰግናለን።
ከግለሰባዊ ሰዋዊ ጉጉት በፊት የአማራን ትግል እና አንድነቱን አስቀድማችሁ ለሃላፊነት ከኔ ጓዴ ይቅደም፥ አንድነቱ ይረጋገጥ እንጅ ለኔ የሚሰጠኝ ቦታ ትልቅ ጉዳይ አይደለም ያላችሁ ጀግኖች መሪዎች ታላቅነታችሁን ዛሬ ልባችን መዝግቦታል ነገ ትውልድ ይኮራበታል።
በተረፈ በእጦጦ ከጅዎች የሚጠናከር እንጅ ለአንድ ደቂቃ እንኳን ወደኋላ የሚቀር ትግል የለምና በያለንበት እንበርታ።አሁን ሁሉም ወደ ስራ ይግባ!
መልካም የከተራና የጥምቀት በአል!
ክፋት ለማንም፥ በጎነት ለሁሉም!
አንድ አማራ!
እስከምፃት አማራ!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አዲስ ትውልድ፥ አዲስ አስተሳሰብ፥ አዲስ ተስፋ!
አርበኛ ዘመነ ካሴ
ጥር 10-2018 አም
#የጠላት_እንቅስቃሴ_መረጃ‼️
ከፍኖተሰላም ወደ ጅጋ ሁለት ዙ .23 እና ሁለት ፒካፖ ከ30 ደቂቃ በፊት ወጧላ ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀዋል‼️
ከምሽቱ 12:55
10/ዐ5/2018 ዓ.ም
#ሴት_ፋኖ፦ #የትግሉ_ሞተር፣ #የነፃነቱ_ማገር
የታሪክ ማህደር ሲገለጥ፣ የድል አውድማው ሲቃኝ፣ በጀግንነት ስም ዝርዝር ውስጥ የሴት ፋኖ አሻራ የጎላ ነው። እርሷ ለትግሉ ድምቀት ብቻ ሳትሆን፣ መላውን እንቅስቃሴ ወደፊት የምታስፈነጥር "ሞተር" ናት።
በአንድ እጇ ቤቷን፣ በአንድ እጇ ነጻነቷን የጨበጠችው ሴት ፋኖ፤ በቁጭት ስትነሳ ተራራ የምታንቀጠቅጥ፣ ስትራመድም ምድርን የምታናውጥ የጽናት ተምሳሌት ናት። ሰንቀው ለሚዘምቱት ወንድሞቿ ስንቅ ብቻ ሳትሆን፣ ለውጊያው ወኔ፣ ለድሉም ተስፋ የምትዘራ የብርታት ምንጭ ናት።
የእርሷ የትግል ሞተርነት በሁለት መልክ ይገለጣል፦
#በግንባር፦ እንደ ጥይት ተኳሽነቷና እንደ ስትራቴጂ ነዳፊነቷ፣ ጠላትን የምታስበረግግ ቆራጥ ተዋጊ ናት።
#በጀርባ፦ እንደ እናትነቷና እንደ እህትነቷ፣ የትግሉን ማገዶ አቀጣጥላ፣ ተስፋው እንዳይከስም የምታደርግ የህልውና ዋስትና ናት።
#ሴት_ፋኖ ስትታጠቅ፣ ትጥቁ የብረት ብቻ ሳይሆን የሞራልና የማንነት ጭምር ይሆናል። እርሷ በሌለችበት ትግል ውስጥ ትንፋሽ የለም፤ እርሷ ባልቆመችበት አውድማ ላይም ፅናት አይታሰብም። በእውነትም፣ የነፃነት ጉዞው ጋሪው ህዝብ ከሆነ፣ ያንን ጋሪ አድካሚውን ዳገት አስወጥታ ለድል የምታበቃው ብቸኛዋ ሞተር "ሴት ፋኖ" ናት!
🔥#የድል_ዜና‼️
ተጠናክሮ በቀጠለው የህልውና ተጋድሎ አራት መቶ አለቃ ማዕረግ ያላቸውን ጨምሮ 34 የጠላት ኃይል በመደምሰስና 21 ክላሽንኮፍ በመማረክ ተከዜ ክፍለ ጦር ታላቅ ጀብዱ ፈፀመ‼️
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ክንፍ የሆነው ተከዜ ክፍለ ጦር ከጥር 08 እስከ ጥር 10/ 2018 ዓ/ም ለተከታታይ ሦስት ቀናት ከጠላት ጋር ባደረገው እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ የላስታ ሰንሰለታማ ተራሮች የጠላት መቀበሪያ የወገን ከለላና መከታ ሆነው ተከዜዎቹ የብልፅግናን ወንበር አስጠባቂ ምስለኔ አንገት በማስደፋት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል።
ጠላት በሜካናይዝድ የታገዘ በመድፍ፣ በ107 ፣በዙ-23(አየርመቃወሚያ)፣በሞርታር-120፣በሞርታር-82 ታግዞ ከላስታ ወረዳ ኩልመስክ ዙሃባ-ኪዳነ ምህረት እና ከገነተማርያም ቻይና ካምፕ ቀጭንአበባ ደባራይ ድረስ ያካለለ አውደ ውጊያ ያደረገ ሲሆን ተከዜዎቹ በሚያውቁት መልከዓምድር በመውጣትና በመውረድ ጠላትን ሲያደባዩት ውለው አድረዋል።
በዚህ አውደ ውጊያ አራት የመቶ አለቃ ማዕረግ ያላቸው አመራሮችን ጨምሮ 34 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ20 በላይ መቁሰላቸው ታውቋል፤በተያያዘም 21 ክላሽንኮፍ፣685 የድሽቃ ተተኳሽ፣520 የብሬን ተተኳሽ፣760 የክላሽ ተተኳሽ፣18 የእጅ ቦምብ፣26 የደረትና የወገብ ትጥቅ ተማርኳል።
ድንጋጤ ውስጥ የገባው የብርሃኑ ጁላ የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ከፋኖም ጭምር መልከዓምድሩም እየተዋጋኝ ነው በማለት የአማራ መሬቶችን በመድፍ፣በ107፣በሞርታርና በዙ-23 በመደብደብ ለዘመናት ተጠብቆ የነበረውን የእመኪና መድሃኒአለምን ጥብቅ ደን እና ከአንድ አካባቢ የሚገኙ የአምስት አርሶ አደር ቤቶችንና ሙሉ ንብረት ማቃጠሉና ማውደሙ ታውቋል።
በመጨረሻም ለአመታት ስንናፍቀው የነበረው እና ደማችን አፍስሰን አጥንታችን ከስክሰን ያፀናነው አንድ አታጋይ ድርጅት ለጠላቶቻችን የሞት ደብዳቤ ለአማራውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት ቁልፍ ለሆነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስረታ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን፤ይህንን ድርጅት እንደ አይናችን ብሌን እንድንጠብቀውና እንድንንከባከበው እንዲሁም በዱሩ በገደሉ እየተዋደቃችሁ እየታገላችሁ ለምትገኙ ለሁሉም የፋኖ አባላትና አመራሮች እንኳን ለከተራና ጥምቀት በዓል አደረሳችሁ ሲል የተከዜ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ መልካም ምኞቱን ገልጿል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብን)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 10/2018 ዓ/ም
10/ዐ5/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር የ2 ወር የግዳጅ አፈጻጸም ገመገመ:-
============
👉ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።
👉የአማራ ፋኖ አንድነት እንዲመጣ ሌት ከቀን ስትሰሩ ለነበራችሁ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮቻችን፤ ለሰራዊታችን፤ ለመላው የአማራ ህዝብና የትግል ደጋፊዎቻችን በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!!
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር አመራሮች እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ተናበውና ተቀናጅተው ስራን ቆጥሮ ሰጥቶ ቆጥሮ በመቀበል እና ከመልሶ ማደራጀቱ ጎን ለጎን ከቴዎድርስ ዕዝ ከማንዶ ሀይል ጋር በመቀናጀት ከብልጽግና ተልዕኮ በመቀበል ሲዘርፍ የነበረ ሌባን በማጽዳት አደረጃጀቱን ሙሉ በሙሉ ሰርቶ አጠናቋል።
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር የመልሶ ማደራጀቱን ከጠላት ጋር ሌት ከቀን እየተፋለመ ከነፍስ ወከፈ መሳሪያ እስከ ዲሽቃ በመማረክ እንዲሁም የተፐወዘውን ጦር ወደ አሀዱ በማስገባት አደረጃጀቱን ቀድሞ በመጨረስ በስሩ ያሉ ክፍለጦሮቹን የስራ አፈጻጸም እየገመገመ ይገኛል።
👉 የ109ኛ ኮር በውስጡ ከሚገኙት ግዙፍ ክፍለጦሮች መካከል 88ኛ ክ/ጦርን ከቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች ጋር በመቀናጀትና የመጀመሪያውን የ2 ወር የግዳጅ አፈጻጸም በመገምገም የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ማጠናቀቁ ይታወቃል።
👉አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር የ77ኛ ክ/ጦር ከተቋቋመ በኃላ የሁለት ወር የግዳጅ አፈጻጸም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በማንሳት ለተከታታይ 3 ቀናት በጥልቀት ሲገመግም ከቆዬ በኃላ በዛሬው ዕለት መክሊትን ታሳቢ ያደረገ የአመራር ሽግሽግ/ሪፎርም በመስራት አጠናቋል።
የ109ኛ ኮር አመራሮች እና የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ስሜነህ ሙላቱ፣የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ስትራቴጅ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ተሰማ ካሳሁን፣የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ሎጀስቲክ መምሪያ ሃላፊ ሻለቃ ይርሳው ደምስ፣ የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ክፍተኛ አመራር ሻለቃ ደምስ በመድረኩ የተሳተፉ ሲሆን የወደፊት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የዕለቱ ፕሮግራም በስኬት ተጠናቋል።
አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ!አዲስ ተስፋ!
109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
ጥር 10/2018 ዓ.ም
ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም
የከተራ እና ጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2018 የከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል።
የድርጅታችንን መመስረት ተከትሎ ሰራዊታችን፣ መላው የአማራ ህዝብ፣ የዳያስፖራው ማህበረሰብ እና የትግሉ ደጋፊወች በከፍተኛ ስሜት እና ደስታ መቀበላቸውን ስናረጋግጥ ከፍተኛ ኩራት ይሰማናል። በአንድነታችን ከፍተኛ ልባዊ ደስታን የተጎናፀፈው ሰራዊት እና ህዝብ የድሉን ፅዋ ያነሳ ዘንድ የጠላትን አከርካሪ መስበር የሚችል ስልታዊ አመራር ለመስጠት መዘጋጅታችንን በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሀገራችን ባህል እና ትውፊት እንዲጠበቅ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባህሉን እና እምነቱን በነፃነት የሚያራምድበት ሀገር እንዲኖረን የጀመረውን ፀረ አገዛዝ ተጋድሎ በአዲስ መንፈስ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም በዚህ አጋጣሚ እንገልፃለን።
መላው ሰራዊታችን እና አመራሩ በተቆጣጠርናቸው አካባቢዎች ሁሉ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከህብረተሰቡ ጋር በትብብር እንድትሰሩ እናሳስባለን።
በድጋሚ መልካም የከተራ እና የጥምቀት በዓል!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
