ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 480
Подписчики
-524 часа
+677 дней
+84830 дней
Архив постов
ከ43_በላይ_የጥምር_ሰራዊት_ፋኖን_ተቀላቀለ‼️
የብልፅግና ስርዓት ዙፋን አስጠባቂ የመከላከያ እና የሚሊሻ አባላት በስቦ ማስከዳት እየተበታተነ ነው
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 5ኛ ክፍለ ጦር የነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ስቦ በማስከዳት የብልፅግናን ዙፋን አስጠባቂ የሚሊሻ እና የመከላከያ አባለትን እየበታተነ ይገኛል።
የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበረ መ/ወታደር ታደሰ ሞላ ለሚዲያችን እንደገለፁት ወደ ቋሪት ስንገባ ገነት አቦ ከተማ ላይ 28 ጌዜ ሞርተር ተኩሰናል፤ ፋኖ ላይ አንድም ጉዳት አልደረሰም ንፁሀን ነው የጎዳው፤ በዚህ ምክንያት ህዝብን ከሚወጋ ኃይል ጋር አልዋጋም ብየ ስርዓቱን ክጄ ከእነሙሉ ትጥቄ ፋኖን ተቀላቅያለሁ ብሏል።
እየፈራርሰ የመጣው የቋሪት ወረዳ የሚሊሻ አባል የነበረው ጌታሰው ተሰራ እንዳለው ነሐሴ 3/2017 ዓ.ም ነበልባሉ የገረመው ወንዳውክ ብርጌድ በገ/ማርያም ከተማ ባደረገው ውጊያ በርካታ የሚሊሻ አባል መበተኑን ገልፆ፤ መጀመሪያም ስገባ ከወንድሞቸ ጋር ልዋጋ ሳይሆን ትጥቅ ከጠላት ታጥቄ ወይም ነጥቄ ለመውጣት ነበር፤ አላማየና ሀሳቤ ተሳክቶ ከሚሊሻ መሳሪያ ነጥቄ ከፍኖ ወንድሞቼ ጋር ተቀላቅያለሁ ብሏል።
ሌላው የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ የሚሊሻ አባል የነበረ ወጣት ይከበር ጫኔ እንዳለው ወደ ሚሊሻ የገባሁ መሳሪያ ለመታጠቅ ነበር ነገር ግን ፋኖ በነሃሴ 3/2017 ዓ.ም ባደረገው ውጊያ ሚሊሻ ላይ ብቻ ትኩርቱን በማድረጉ በርካታ የሚሊሻ አባላት ላይ ከፍተኛ እርምጃ በመወሰዱ ሀሳቤ ሳይሳካ ህይወቴን ለማቆየት በጀሌ ወጥቻለሁ ብሏል።
አፋባኃ ምዕራብ አማራ ቴዎድሮስ ዕዝ 5ኛ ክ/ጦር ነበልባሉን የገረመው ወንዳውክ ብርጌድን ጳጉሜ 02/5017 ዓ.ም የተቀላቀሉ የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ የነበሩ የመከላከያና የሚሊሻ አባላት:-
1.መ/ወታደር ዘሪሁን መና 403 ኮር 71ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሻለቃ የነበረ
2. መ/ ወታደር ታደሰ ሞላ 403 ኮር 71ኛ ክ/ጦር 5ኛ ሻለቃ የነበረ
3. የሻምበል ንብርት ቀበሌ ግራርማ የሽል ሚሊሻ ቲም መሪ
4. ሀይማኖት በለጠ ቀበሌ ጎምት ድዋሮ ሚሊሻ
5. የቻለ አልፈር ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
6. ጌታሁን በቀለ ቀበሌ አ/ሌ ገደል ሚሊሻ
7. ይርጋ አዕምሮ ቀበሌ አ/ሌባ ገደል ሚሊሻ
8.ይከበር ጫኔ ቀበሌ አ/ሌባ ገደል ሚሊሻ
9. በላይ ደረበው ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
10 ካሳሁን ይታይህ ቀበሌ አ/ይበርት ሚሊሻ
11. ዘመኑ አየለ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
12. ይናገር ዋለ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
13. ይገርማል ዘርያቆብ ቀበሌ ጎምት ድዋሮ ሚሊሻ
14. አያና ደርበው ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
15. ጌታሰው ተሰራ ቀበሌ ጎምት ድዋሮ ሚሊሻ
16. ደጀኔ ወርቄ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
17. ይልቃል ወረቄ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
18. መኳንንት አንማው ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
19. ፋኖስ ጫኔ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
20. አትንኩት አለምነህ ቀበሌ ቦረዝ በስኮስ ሚሊሻ
22. አብርሃም ጉልማ ቀበሌ አየን ይበርት ሚሊሻ
23. ተስፋሁን ጫኔ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ
24. ሀብታሙ ጌታነህ ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ ሻምበል መሪ
25. ደጉ የኔነህ ቀበሌ ጎሞት ድዋሮ ሚሊሻ
26. ካሳሁን ይታይህ ቀበሌ አ/ይበረት ሚሊሻ
27. ገደፋው አሸብር ቀበሌ ወይበዬኝ ሚሊሻ ጋንታ መሪ
28. መላክ አያሌው ቀበሌ ወይበይኝ ሚሊሻ ቲም መሪ
29. ይከበር ጠብቄ ቀበሌ ወይበይኝ የወረዳው ሰላምና ደህንነት ኃላፊ (ዋሌ ቢተው) አጃቢ የነበረ
30. መልሰው አወቀ ቀበሌ ቦረዝ በስኮስ ሚሊሻ
31. እንየው የደሜ ቀበሌ ቦረዝ በስኮስ ሚሊሻ
32.ካሳሁን እንግዳ ቀበሌ አየን ይበርት ሚሊሻ
#ነሐሴ 04/2017 ዓ.ም ይፋ ያደረግናቸው
33ኛ. እንደግ ጋሻው __ ጀሌ
34ኛ. ይከበር ንጋቱ __ አንድ እግር ክላሽ
35ኛ. አዳነ ውባለም __ ጂንፎ ኤስኬኤስ
35ኛ. መኳንንት ተስፌ __ እንየው ከተባለ ሚኒሻ ክላሽ ነጥቆ የወጣ
36ኛ. እሱባለው መኮነን __ ጀሌ
37ኛ. አጠቃ አልፈር __ ጀሌ
38ኛ. ይግረም አንዷለም __ ጀሌ
39ኛ. በለው ገነት __ ጅንፎ ኤስኬኤስ
40ኛ. ግርማው መሰሉ __ ጀሌ
41ኛ. ጊዜው እውነቱ __ ጀሌ
42ኛ. ሚኪያሰ እንዳሌ __ ጀሌ
43ኛ. ዳንኤል
አሁንም የዘገያችሁ ፍጠኑ፣ እንቀበላለን።
ነበልባሉ ገረመው ወንዳውክ ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት
ጳጉሜ 02/13/2017 ዓ.ም
02/13/2017 ዓ.ም
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#ዘመቻ_ሰማዕታት_እንደቀጠለ_ነው‼️
ጳጒሜን 02/2017 ዓ.ም
የአ.ፋ.ብ.ሃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር አባ ኮስትር ብርጌድ በቢቸና ከተማ፣የትመን ከተማ፣ወይራ ጠልማ ቀበሌ እንዲሁም ደባይ ጮቄ ብርጌድ እና የክፍለ ጦሩ ጥምር ኃይል በጋራ በመሆን በማህበረ ብርሃን ቀበሌ የሚገኜውን የአረመኔው ሰራዊት ላይ ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል።በየትመን ከተማ ጠላት ይጠቀምበት የነበረው ካንፕ #በቦንብ እና #RPG መሳሪያዎች በኮስትር ልጆች #ወድሟል_ተቃጥሎል።
ጳጒሜን 02/2017 ዓ.ም
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#መረጃ_ወለጋ ‼️
፨፨፨፨፨፨፨፨
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አቤ ዶንጎሮ ወረዳ ጫንጮ ቀበሌ ልዩ ስሙ ብጅት በዚህ ሳምንት አገዛዙ ጥምር ጦር እያለ የሚጠራዉ አራዊት ሰራዊት እንደ ለመደዉ ንፁሀን የአማራ አረሶ አደሮችን ለመጨፍጨፍ እና ለመዝረፍ ከኋላ ቄሮን አስከትሎ ቢመጣም በአርበኛ አደም ተፈራ የሚመራዉ የአማራ ፋኖ በወለጋ ህዝባችን ላይ የተቃጣዉን ጥቃት በተከታታይ ለአምስት ቀናት በመመከት የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ቁስለኛዉን እና ሬሳዉን ሳያነሳ ወደ ቱሉ ጋና መፈርጠጡን ቢዛሞ ሚዲያ ከቦታዉ መዘገባችን ይታወሳል ።
በዛሬው እለት ቢዛሞ ሚዲያ ከቦታዉ በደረሰን መረጃ ደግሞ ይህ የአማራ አጥፊ ሰራዊት ሎምጫ ቀበሌ አሩሲ ቤተክርስቲያን ዙሪያውን ምሽግ እየቆፈሩ ወደ አማራዉ መንደር እየተጠጉ እንደሆነ አረጋግጠናል ።
አሩሲ የቆላማዉን አማራ አርሶ አደር ለማጥቃት እንደ ወሳኝ ቦታ ተቆጥራ ነዉ ምሽግ መቆፈር የጀመሩት ይላሉ የቢዛሞ ምንጮች። አላማቸውም ብጅትን ጫንጮንና አሩሴ ዙሪያ ሙሉ ገጠሩን በቁጥጥር ስር አድርገው ያገኙትን አማራ እየገደሉ ቤት እያቃጠሉ ከብቱን ዘርፈው አማራውን ማፈናቀልና ማስለቀቅ ነው።
በአሩሲ ዙሪያ የምትገኙ የጋሬሮ ፣ መንደር 24 ፣ መንደር 25 እና ብጅት የአማራ ማህበረሰባችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ ቢዛሞ ሚዲያ መልክቱን ያስተላልፋል።
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥#የድሮን_አሰሳ_መረጃ‼️
በጎጃም ቀጠና ሰሜን አቸፈርና አካባቢው ላይ የድሮን አሰሳ እየተደረገ ሲሆን ሌሎች የአገዛዙ የእግረኛ ጦር እንቅስቃሴዎችም ከሌሊቱ 6:00 ጀምሮ ቀጥለዋል።
በተለይም ከበለን እስከ አለፋ ባለው ቀጠና ጥንቃቄ ይደረግ ተብሏል። አገዛዙ አሁን ላይ በሁሉም የክልሉ አካባቢ እንደ አዲስ የድሮን ጥቃት ለመፈፀም ዝግጅት ማድረጉም እየተነገረ ሲሆን ምንጮች ሁሉም የፋኖ ሀይሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
መልካም ሰንበት ውድ አማራዊያን
በአማራ ሰማይ ስር
አንድ ማንነት፣ አንድ ዓላማና አንድ ጠላት ያለን መቸም የማንለያይ በደም የተሳሰርን ወንድማማቾች ነን።
ወሎ ጎጃም ጎንደር ሸዋ አንድ አማራ‼
ድል ለአማራ ፋኖ!!
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
"የሀሳብ ልዩነቶችን እና አለመግባባቶችን ለመፍታት ሲባል በሁሉም አደረጃጀቶች ውስጥ ሲገጥሙን የነበሩ የስልክ ቅጅዎችን እንደ ንስኀ ወስደናቸው ለአንድነታችን ተግተን መስራት ይጠበቅብናል"
ፊታውራሪ ባዩ አለባቸው
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ
የአማራን ትግል ወደ አንድ እንዳይመጣ የትግላችን እንቅፋት የሆኑ የሀሳብ ልዩነቶችን እና አለመግባባቶችን ለመፍታት ሲባል በሁሉም አደረጃጀቶች ውስጥ ሲገጥሙን የነበሩ የስልክ እሪከርዶች እንደ ንስኀ ወስደናቸው በየቦታው ለብዙ ግዚያት የተረጩብንን መርዞች ነቅለን በመጣል ትግላችን ዛሬ ላይ ወደተሻለ የድርጅት አቋም መመለስ የቻልንበትን ጉልበት እና አቅም ፈጥረንበታል ። ስለዚህ ትግላችንን እና አቢወታችንን ሊነጥቁን በውስጥም በውጭም ያሰፈሰፉ ሃይሎችን ከእንጭጩ የቀጨንበት ጥበባዊ ስልትም ብልሀትም ነው።
✍️,ትግላችንን አንድ ቅርጽ፣አንድ መዋቅር፤አንድ ደርጅት፤ አንድ መርኅና የአሠራር መልክ ማስያዝ የኅልውና ትግላችን የማሸነፊያ ቁልፉን እንደመጨበጥ መሆኑን ሕዝባችን፤ ስራዊታችን እንዲሁም ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በጽኑ የሚያምንበት ጉዳይ ነው፡፡ አማራነትን የሚጸየፍ ኢትዮጵያዊነት እና አማራነት የጎደለው አውራጃዊነትን እንደምንጸየፈው ሁሉ ልዩነትን የማይታገስ አንድነትን እንዲሁም አንድነትን የማይቀበል ልዩነትንም እናወግዛለን። የአማራን ሕዝብ ትግል በአንድ ድርጅት ጥላ ሥር የማንበር፤ በአንድ መዋቅር የመሰብሰብ የመከሸፍ እንዲሁም በተመሳሳይ መርህ እና አስራር እንዲመራ ማድረግ በብዝኃ ሀሳብ የሚሰራውን ያክል በብዝኃ ሀሳቦች መካከልም ልዩነት እና ልዩነት እና መቻቻል የሚጠበቁ ጉዳዮች ናቸው:: ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው፡ ልዩነትን መግራት ደግሞ ብስለት ጥበብም ነው፡፡
ክብርና ሞገስ ለትግሉ ሰማዕታት!!!
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
ፊታውራሪ ባዩ አለባቸው
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ዋና ወታደራዊ አዛዥ
ጳግሜ 2/2017 ዓ/ም
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የቆላው አንበሳ!
-------
Teddy Afro ስለ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ የፃፈው ግጥም።
በሐጋይ በረሃ በከሰለው መሬት
ከሞቀው ጉልቻ ከቀለሰው ጎጆ ተለይቶ ከቤት
በረሃ ከትሞ ጠዋትን ከማታ
አደራዋን ወስዶ ለእናት ሀገሩ ሊከፍላት ውለታ
በጠረረ ፀሀይ የቀይ ጥቁር ሆኖ
አለትን ከአለት በላቡ ሲያጣብቅ እንዳይሆኑ ባክኖ
የማይረትመው ጉልበት ባገር ፍቅር ፅናት ደፋ ቀና እንዳለ
ሞተ ትላንትና ተለይቶን ሔዷል አትበሉ የታለ
ሳይጫነው አፈር ሳይገባ ከመሬት ገና በሩሕ ሳለ
በአባይ ወንዝ ላይ ባቆመው ሐውልቱ በኩራት ሲያገሳ
ዘለአለም ለሚኖር ስመአባይ ስመኘው የቆላው አንበሳ
ሐምሌ 22/2010 ዓ.ም.
ለኢንጂነር ስመኘው በቀለ
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+1
#የኦህዴድ ብልፅግና ቸርቾች የምስጋና ጉባኤ ጠሩ❗
የእምነት ተቋማት፣ ሙሉ በሙሉ የፋሽስታዊ አገዛዙ የፕሮፖጋንዳ መፍለቂያ ምንጭ ወደመሆን እየተሸጋገሩ ነው።
ከብልፅግና ቢሮ በሚሰጥ አቅጣጫ ጉባኤም ፀሎትም፣ መግለጫም በመሥጠት ወንጌላውያን ቸርቾች የመንግስት ኃይማኖት መሆናቸውን አስመስክረዋል።
በጥቅሉ፣ የወንጌላውያኑ ቸርቾች፣ የብልፅግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሆነው ማገልገል ከጀመሩ 7 ድፍን አመታት ተቆጠሩ።
የምርጫ ቅስቀሳ
የነገ ብልፅግናዊ ትንቢት
የጠላት እርግማን
የሀገራዊ እድገት እና ትንቢት በአገዛዙ አቅጣጫ ሰጭነት የሚነገረን በቸርቾቹ እና ፖስተሮቹ በኩል ከሆነ ሰነባብቷ።
ከፊታችን፣ ብልፅግና አቅጣጫ የሰጠበት የአደባባይ ፀሎት በመስቀል አደባባይ ይደረጋል ተብሏል።
ጳጉሜ 02/2017 ዓ.ም
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አንዳንድ አማራዎች አማራ መባል እንደ እራስ ዳሽን መግዘፍ መሆኑን ሳይረዱ ቀርተው በራሳቸው የህልም ቦታና ስዕል ከቆሙበት ራስ ዳሽን እንዳይፈጠፈጡ ሲመፃደቁ ወይም ሲደበቁ ብናይም ወደ ወገናቸው እንዲመጡ መጎትጎት፣ ማግባባት ህዝባቸው እንዲክሱ ማድረግን ጨምሮ የአማራን ህዝብ ትግልን በመሰላቸው መልኩ ሲደግፉ የተገፉ ካሉም መመለስና መሰባሰብን ስራዬ ብላችሁ እንድትይዙ አሳስባለሁ። የዲያስፖራ አባላትና ባለሃብተች እንዲሁም ደጋፊዎች የምትሰጡንን ድጋፍና አጠቃላይ ወገናዊ ድጋፍ የት ገባ? ማለትን ብታለማምዱ የድርጅታችንን ህልውና ያጠነክረዋል ብሎም ከሀሜትና ከመገፋፋት ወጥታችሁ በስርዓት ለመመራት የምታደርጉትን ጥረት ያበረታልና ድሬጅታዊ ተጠያቂነትን ማስፈን ያስፈልጋል።
5= ሰራዊታቸን በራሱ ቀየ በራሱ ጓዳና በራሱ ሜዳ ሰልጥኖ አሰልጥኖ ታጥቆና ወገኑን ጠብቆ፣ በእውቅና በሳይንስ ተጠምቆ ለቀጣዩ ህያው የስርዓት ማንበር ጉዞው ተዘጋጅቶ ይገኛል። ይህንን የአማረ ሰራዊት በቀጠና በአካባቢ ብሎም በጎጥ ለመከፋፈል እና ባለበት ብቻ እንቧለሌ እንዲዞር ለማድረግ የሚደረጉ የራሳችን ሀይሎች ሽኩቻና የጠላህ ሀይል ሴራ መለየትና መመከት ያስፈልጋል። ይሄንን የሴራ ድር አስቦ በመበጣጠስ ለአንድ አላማ የተሰለፈ አንድ ደም፣ አንድ አጥንት ፣አንድ ነፍስ፣ አንድ ምላስ፣ አንድ ትክሻ፣ አንድ ጭንቅላት ፣ ያለው እሱም የአማራ ሰራዊት ማድረግን ታሳቢ አድርገን መስራት ይጠበቅብናል።
6= የተከበራችሁ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ሰዎች እስካሁን በግንባርና በስደት ሆናችሁ ያደረጋችሁት ትግል እጅግ ከፍተኛና ልኑ ነው። በራሳችሁ አቅም በራሳችሁ መስመርና በራሳችሁ እውነትና እምነት ሳይሆን በህዛባችን ጥያቄ ህልውናና በትግል መንገድ ለመጓዝ መምረጣችሁ ብዙ የሚያሳጣችሁ መሆኑን እረዳለሁ። የምታጡት ግን በህባችሁ ላይ ከተደቀነው አደጋ የሚያንስ አንጂ የሚበልጥ አደጋ አያመጣባችሁም እና ትግላችሁን ስራችሁን በጥንካሬ ቀጥሎ። ሚዲያ አራተኛ መንግስት ነው ቢባልም በእኛ ትግል ግን ይሄ አልታየምና በዠከሽኩቻ ከቡድንተኝነትና ከመጠላለፍ ወጥታችሁ የጠራ መስመር ይዛችሁ ትግላችንን ብታታግሉት በራሱ ጉልበት የሚቆም ልዩ በረከት ትሰጣላችሁ እንጅ አልፎ አልፎ አንድሚታየው ድካም አይሆንም። ሁልጊዜም በራሳችሁ አቅም ብቃትና በራሳችሁ ህዝባዊ እውነት ላይ በመቆም ዘመን ተሻጋሪ እንድትሆኑና ህዝባችንንም ለድል እንድታበቁ መሪ ሳትይሆን አቅጣጫ ተቋሚ ፣ አሳዳጅ ሳይሆን ለሚሳደዱት የምትደርሱ እንድትሆነ እውነትና ፍትህን በስሜና ይሁነኝ ብሎ ከማክሰምና ከማጥፋት እውነትን ፍትህን የተጠማችሁ ርሃብተኞች ፣ የመላያየት ሳይሀን የአንድነት አንደበቶች አንድትሆኑ ማሰብ መስራትና በዛ መስመር መጓዝ ይጠበቅባችሁዋል።
7. የአማራን ህዝብ ለአንድ ዓላማ ማሰለፍ ችለናል። ባለፉት ዘመናት ዋናው የህዝባችን ችግር "ፎከስ" ማጣት ነበር። በኢትዮጵያዊነት እና በአማራነት መሃል በመዋለል የመጣውን ተጨባጭ የህልውና ስጋት ለመመከት የሚደረገውን ትግል ውጤት አልባ አድርጎት ቆይቷል። አሁን ግን ኢትዮጵያን ማዳን የሚቻለው መጀመሪያ አማራው ራሱን ሲያድን መሆኑን፣ ቀጥሎም ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ሲተባበር እንደሆነ በግልፅ በመለየት በጠራ ዓላማ ላይ የቆመ ትግል ማድረግ ጀምረናል።
የተለያየ ኃይማኖት፣ የተለያየ ማህበራዊ አደረጃጀት፣ ሙያ ያለውን ህዝብ ለአንድ አላማ በአንድነት ማሰለፍ የተቻለውም ለዚህ ነው።ፖለቲካ በልኩ የሚረዳና ለተጨባጭ ጥቅም የሚታገል ትውልድም መፍጠር ችለናል።
8- ከተራ ፉከራ እና ለቅሶ ወጥቶ ለተጨባጭ ችግሮች ተጨባጭ የመፍትሔ ኃሳብ ማፍለቅና ለተግባራዊነቱም እስከ ህይወት መስዋዕትነት የሚከፍል ትውልድ መፍጠር ችለናል። የትግላችንን ዓላማ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን እና ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ በግልፅ ማስረዳትም ችለናል።
10."አልቃሾች ናቸው ሶፍት ስጧቸው፣ ሰበርናቸው" እያሉ ሲሳለቁብን የነበሩትን ወገባቸውን ሰብረን ባሉበት እንዲፏቀቁ ማድረግ ችለናል፣ ምላሳቸው ብቻ እንዲቀር አድርገናል። የትግላችንን ዓላማ እና የማሸነፋችንን አይቀሬነት በማሳየታችን የእራሳቸው ወንድሞች በመማረክ የትግላችን አካል አድርገናል። ህዝባችንን ከተቅበዝባዥነት እንዲወጣ የተስፋ ብርሃን ማሳየት ችለናል።
ሆኖም:-
ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ በልኩ አለመረዳት፣ በየጊዜው ከጫፍ እየደረስን የመክሸፋችን ጠባሳ ስላልሻረ የፈጠረብን ፍርሃት ትብብሮችን በልኩ ያለመረዳት፣ አሁንም ልንቀማ ነው፣ ተከታይ ልንሆን ነው የሚል ስጋት አለ።
የታላላቆቻችን ከነባሩ የፖለቲካ አመለካከት አለመላቀቅ
የእራሳችን ወንድሞች ለጠባብ የቡድን ፍላጎት መገዛት እና በመንገዳችን የተፈጠሩትን ችግሮች (ወደ ፊት በጋራ ከህዝባችን ጋር የምንፈታቸውን ችግሮች) ከአጠቃላይ ከህዝባችን ነፃነት በላይ ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ እና ውዥንብር መፍጠርም ከባዱ ፈተናችን ነው።
በመጨረሻም እኛ አመራዎች የአማራን ህግል በየዘርፉ እየመራን ያለን ባለድርሻዎች ዛሬም ነገም አረመኔውን የአብይ አህመድ አገዛዝ ለማወስገድ የምያደርገውን ትግል አጠናክረን መቀጥል ግድ ይለናል።
ትግላችንንና ለውጦችን መጠበቅ ከታሪካችን ልንማረው የሚገባ ያለፉት አመታት ጠባሳችን ነው። ስርዓቱን ትጥቁን ነጥቀን ስንቁን አሳጥተን አሁን የቀረው የሚናውዝ የደሃ ኢትዮጵያውያን ምግብ ፈልጎ የገባ ሰራዊት ነው። ይህንን ሰራዊት ለወረራ በህዛባችን ላይ ያዘመተው የአራት ኪሎው የጥቁር ናዚ ስብስብና ቅልብ ሀይል ደግሞ የውጊያ የዲፕሎማሲያ የሚዲያ አንዲሁም የእለት ተእለት ፖለቲካዊ ክዋኒያችን ዋና ኢላማ ይሆናል።
በዚህም አማራ ነፃነትን በክንዱና በራሱ አቅም ማንንም ሳይለማመጥና ደጅ ሳይጠና አረጋግጦ ለሎች ነፃ መውጣትና በጋራ መኖር ተባባሪና ቀዳሚ መሪ ይሆናል።
እንደ ግለሰብም እንደ አደረጃጀትም የተደቀነብንን አደጋ፣ የህዝባችንን ስነ ልቦና እና ታሪክ በሚመጥን አመለካከት እና ልበ ሙሉነት እንገኝ።
አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ !አዲስ ተስፋ
አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ
ከአፋብኃ ሴንትራል ኮማንድ
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
Amhara Revolution:
ይህ ትግል ከተቻለ ከሌሎች ሀገር ወዳዳድና አብሮ ኑዋሪ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ስርዓታዊና መዋቅራዊ ለውጥን በማምጣት ዘረፈጅነትን ከኢትዮ የፖለቲካ እንብርት የምንነቅልበት ትግል ነው።
መተባበሩ ካልታቸለም የዘረፈጁን አስኳልና እንብርት በራስ አቅምና በራስ የተሰላ ፖለቲካዊ ስልት ማስወገድ ምርጫችን ሳይሆን ግዴታችን ነው።
ለዚህ ሁሉ የሚያበቃን ግን የጀመርነው ትግል እና የአማራ ህዝብ የፀና አንድነት ነው። የጀመርነው ትግል ከአሰብነውና መሆን ከተመኘነው ብሎም ከጠበቅነው ውጤት አንፃር የተለያየ ስሜትና መልክ ቢሰጠንም ባለፉት ሁለት አመታት ግን አለምን ያስደመመ ልዩ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አቅም ገንብተናል። በዚህ በራሳችን አቅም በገነባነው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሀይል ስማቸንን ብቻ ሳይሆን ስራችንን ፣ አላማችንን ለመላው አለም አሳውቀናል።
ትናንት ስማችንን መጥራት የማይፈልጉ ፣አማራ በዳይ ነው እንጂ ሊበደል አይችልም ያሉንን፣መደራጀት አይችሉም ተበተነዋል ያሉንን ሁሉ በስርዓት ባደረግነው ትግል ለጆሯቸው ቅርብ.. ለአይናቸው ግልፅ.. ለልባቸው አስፈሪ ሆነንባቸዋል።
አማራ በወንዞች በተራሮች እና በሸንተረሮች በድሮን በአየር ብሎም በታንክና በአልሞ ተኳሽና ጀምላ ጨራሽ መሳሪያዎች የሚገደልበት ጊዜ አብቅቶ አሁን የአባቱን ተራሮች ፣ ወንዞች ፣ ሸለቆዎች ፣ ዋሻዎች በእየለቱ የሚዳስሳቸውን የሚዋጋባቸውን የሚመክርባቸው ብሎም የሚሰልጠንባቸውና የሚፀናባቸው ነፃ ግዛቶቹ አድርጓል።
ትናንት ቁጥራችንን በቀላሉ የሚታወቅ ፣ አቅማችን በቀላሉ የሚገመት ፣ ውሏችንና ስራችን በተራ የሚቆጠር የነበረ ሲሆን አሁን ቁጥራችን ያልተገመተ አቅማችን አስደማሚና አስደንባሪ ፣ ውሏችን የጀብድና ተቆጥሮ የማያልቅ ገድል የበዛበት ልዩ ታሪክ በየቀኑ በየቦታው የሚፃፍበት ሆኗል።
ይህ የሆነው አማራ ለአማራ በአማራ በአማራነት በሰራው ስራ ነው።
👉 የተከበራችሁ የአፋብሃ አመራሮች፤ የዲያስፖራ አባላትና የትግላችን ደጋፊዎች
አማራ አሁን ባለበት ደረጃ የምሰራቅ አፍሪካን ሚዛን የሚያስጠበቅ ፣ ለቀጠናው ልዩ ክስተትን ያላበሰ ፣
ሀገራት ፣ ተቋማትና የፖለቲካ ሳይንቲስቶች ለቀጠናውና ለኢትዮጵያ አዲስ ፖለቲካዊ እይታን እንዲሰጡ ፣የበረውን እንዲፈትሹና ምርምሮቻቸውን እንደ አዲስ አንዲበይኑ ፣ አዲስ መንገድ እንዲጀመር ያስቻለ ልዩ የህልውና ትግልን እያደረገ ይገኛል።
አስቀድመን በፖለቲካ ያሸነፍነው ወራሪው ስርዓት በአሁኑ ሰዓት አንድነት ባለማስፈናችና ዲፕሎማሲ ላይ ደካማ በመሆናችን ነፍስ ያለው ስርዓት መስሎ እንዲታይ በር ከፍተንለታል።
የአብይ አህመድ አገዛዝ በፖለቲካ የተሸነፈውና ያበቃው ገና በውልደቱ አራስ ቤት እያለ ነው። ይህም መዋቅራዋና ስርዓታዊ ለውጡን ድጋሜ በጉልበትና አማራን በማዳከም ከፋፍሎ በማግዛት ብሎም ሁሉን የሀገሪቱን ሀይሎች በጉልበት በመውጋትና በማንበርከክ ተገዥ አደርጋለሁ ብሎ የወሰነ እለት ነው። ስርዓቱ በህፃናት ፣ በተማሪዎች ፣ በገበሬው ፣ በከተሜው ብሎም በሰራዊቱና በመንግስት ሰራተኛው ውስጥ የለም። በእነዚህ አካላት ልብ ውስጥ ያለነው እኛና ሌሎች መሆናችንን ብንናገር ስህተት አይሆንም።
ሰርዓቱ ያለው በእኛ ደካማነት በእኛ ልዩነት በእኛ አውቆ አጥፊነት በእኛ ተጎታችነትና በእኛ እያደሩ ማነስ ላይ ነው። ይህንን ማስቆምና ስርዓቱን በአጭር ጊዚ ከአራት ኪሎ በመንቀል የፀናችና ለአማራ ህዝብ ጥያቄና ህልውና በቂ ዋስትና ያላትን ኢትዮጵያ መመስረት ግድ የሚለን ጊዜ ላይ እንገኛለን።
ፋኖ በመሬት በሚያደርገው ውጊያ ከበቂ በላይ አቅም ያለው መሆኑን አስመስክሯል ፤፥ ለወደፊቱም ከማስደመም የሚያቆመው አንዳች ሀይል የለም።ዛሬ የጀመርናቸውን ቀጫጭን የአንድነት መንገዶች በማስፋት ግለሰቦቸና ጥቂቶች ብቻ ሳይሆን ህዝባችን የሚተማመንባቸው ሰፊ ጎዳናዎች ብሎም የሚሰበሰብባቸው ሰፊ አደባባዩች ማድረግ ይጠበቅብናል።
በአፍሪካ ቀንድ በአሁኑ ሰዓት አለምን ያስጨነቀው አንድ ጉዳይ አለ። ይህም ለቀጠናው የጋራ ደህንነት ወይም (Collective Security ) አለም አቀፋዊ መርህ የሚሰራ ሀገር ፣ የፖለቲካ ቡድን ወይም ጦር አለመኖሩ ነው። ቀጠናው እንደ አንቧይ ካብ ተንዶ አንዱ በአንዱ ላይ የተነሳው በዋናነት የኢትዮጵያ ምሰሶ ስለተናጋ ነው ቢባል ሀሰት አይደለም።
ይህንን የኢትዮጵያ ምሰሶ ማንበርና ቤቱን መልሶ ማቆም የሚያስችል ትግል እያደረገን ነው ብለን እናምናለን። በዚህም ፋኖ በአለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚዋ የአፍሪካ ቀንድ ተመራጭ ሀይል ሆኖ ይወጣል ፣ መንገዱንም ጀምሯል።
እኛ የምንመሰረተው መንግስትም ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ፣ ለህዝቡም አንድነት ፣ በአባቶቻችን ለተመሰረቱ የአለም አቀፍ ተቋማት መርሆዎች ማለትም ለተባበሩት መንግስታት እኛ የአፍሪካ ህብረት መርሆዎችና አላማዎች ሰፊ ሚና የሚጫወት ይሆናል።
👉 የተከበራችሁ የሲንፖዜሙ ተካፋዮች
ዛሬ ይህንን ሲምፖዜም ስከፍት የሚከተሉትን መሰረታዊ ነጥቦች ማንሳት ግድ ይለኛል።
1= እኛ አማራዎች በሁሉ በኩል የተሟላ ፀጋ አለን። ከአፈርም አፈር ከወንዝም ወንዝ አለን። ከስልጣኔም ስልጣኔ ከእውቀትም እውቀት ከሰውም ሰው አለን። ከጀግናም ጀግና ከታሪከም ታሪክ አለን። የጎደለን ስርዓና መዋቅር ነው። ይህንን ስርዓትና መዋቅር ለማበጀት ይህ ቀረው የማይባል ንቁ ተሳትፎና ራስ በቅ ትግል ማድረግ ያስፈልገናል።
2= ለአለም ስርዓት መርህና ህግጋትን ያካፈለንና ሲበጁም በዛ የነበርን እኛ አማራዎች እነዚህን ተቋማት በዲፕሎማሲ በተለያዩ የመገናኛ ስልቶች መጠቀም ግድ ይለናል። አንኳኩ ይከፈትላችኋል የሚለው አምላካዊ ቃል በአለም አቀፍ ተቋማት የሚሰራ መርህ መሆኑን ማወቅ ግድ ይላል ። ደጋግመን በተደራጀና በተጠና መንገድ በእውቀትና በብቃት አለም አቀፍ ተቋማትን መንግስታትን የጥናትና የመብት ድርጆቶችን ፣ ሚዲያዎችን ማንኳኳት አለብን። ይህም በህብርትና በተደራጀ ተቋም መመራት አለበትና ይህንን መፍጠና ማበጀት የሚሰራውን ቆጥሮ መስጠትና ቆጥሮ መቀበል ይጠበቅብናል። በዚህ ረገድ ያሉንን ማጠናከር አዳዲሶቹን ከነባሮቹ ማዋሃድ እናም ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ብሂል በመጠቀም የአንበሶችን ትብብር መፍጠር ይጠበቅብናል።
3= ድርጅታችን አፋብሃና መሰል ተቋማት ገና በልጅነት ከሚገጥማቸው ፖለካዊ ልምሻ ድነውና አገግመው የታሰበውን ስርዓት ይፈጥሩ ዘንድ በቅንነት በእውቀትና በፍፁም ወንድማማችነት መታከም አለባቸው። አሁን ብዙ መስለን የምንታይ አመራሮች ትናንት ህዝባችን የመሪ ያለሽ ሲል የነበረበትን ጊዜ በማስታውስ ብዙ ሳንሆን ገና ብዙ አመራር ማፍራት የሚጠበቅብን ፈር ቀዳጆችና ባላደራዎች ጭምር መሆናችንን መገንዘብና ለዚህ ተቋም ድርጅታዊ ቅርፅ መስጠት የሚያስችሉንን ደንቦች ህግጋትና አሰራሮችን ማበጀት ይጠበቅብናል። አፋብሃን ማጠናከርና ተቋም ማድረግ ግዴታ ነው።
4= የተከበራችሁ የድርጅታችን ደጋፊ ዲያስፖራዎች ባለሃብቶችና ራስ በቆች አሁን ካላችሁበት የወከባ የመሳደድ የእስር ጊዚያትና ሁኔታ ከራስ የህይወት ጥያቄዎች ጎን ለጎን የአማራን ህዝብ ህልውና ለማስጠብቅ እረፍት አልባና እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን በማሳረፍ እንደምትለፉ እንረዳለን።
የተከበርከው የአማራ ህዝብ፣
የተከበራችሁ የአማራ ማህበራት አመራሮችና አባላት
የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ኮማንድ አባላት
የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ የሰራዊት አባላት
የተከበራችሁ የዚህ ሲንፖዜም አዘጋጆች እኛ ተሳታፊዎች
የተከበራችሁ በስደት ሀገር የምትገኙ ወገኖቻችን
ዛሬ ይሄንን ሲምፖዜም ስናካሂድ የነበርንበትን ቦታ ፣ጊዜና ሁኔታ እንዲሁም የነበረብንን ታላቅ መከራ፥ መፈናቀል ፣ ስደት፣ ግድያ ፣ ዘረፋና መሰል ስርዓትና መዋቅር ወለድ ችግሮች ማስታወስ ግድ ይላል።
ባለፉት በርካታ አስርት አመታት አማራ በምድር ላይ አሉ የተባሉና በየዘመናት የተፈፀሙ የአገዛዝ ጭካኔዎች ፣ የማደከሚያና የማጥፊያ መንገዶች ሁሉ እንደተፈፀሙበት ብንናገር ስህተት አይሆንም።
የውጭ ጠላቶችን አሳፍሮ በመላክ ታሪኩን ከሌሎች በላይ ወይም እኩል የፃፈውና ያስፃፈው አማራ ከውጭ
ጠላቶች እጅግ አያሌ ሴራዎችና አንበርክኮ የማደከሚያ መንገዶች ተነድፈውለታል፣ አንዳንዶቹም ተተግበረውበታል።
በቀጥታ አልሆን ሲል የውስጥ ጠላት በማስነሳትና ለቀሰቀሱት ጠላት አማራን በበዳይነት የሚፈርጁበትን መንገድ በመትለም ብሎም በቅኝ ገዥነት የሚከሱትን በማገዝ ፣ በማጉላት ፣ በማስታጠቅና እቅድና በመስጠት ፀረ አማራ ስርዓትን ማንበር እንዲቻል ተደርጓል።
ጣሊያን የተከለው እሾህ እያዘነበለ አማራን መውጋት የጀመረው ገና በንጉሱ ስርዓት ውስጥ ሰርገው በገቡ የራስ ወገን ጠላቶቻችንና የጠላትን ትርክት በልባቸው ባነበሩ የደጃችንና የታዛችን ስር ባንዳዎች ነበር። ከንጉሱ ስርዓት መገርሰስ ጀምሮ በሀገር ውስጥ የተተካው ሶሻሊስት ነኝ የሚል ሀይል አማራን የማሳደድ የማዳከም ስርዓታዊ ተግባር መሰረት እየጣለ መጥቷል።
👉 ክቡራን አማራዎች
አማራ በደርግ ዘመነ መንግስት ፥ በህወሓት ኢህአዴግ ዘመነ መንግስት የደረሰበት በደል ደረጃው ይለያይ እንጂ ጠላት ተደርጎ መሳሉን የሚያረጋግጥ ስርዓትን በማንበር የተፈፀመ ነው።- ስርዓትን በመትከል ስርዓታዊና መዋቅራዊ በደል የተፈፀመበት አማራ በየዘመኑ በቂ ትግል አድርጓል ተብሎ ባይታመንም ከትግል የራቀበትና ለውጥን የተፀየፈበት ጊዜ ግን የለም።
የደርግ ስርዓት በወሰዳቸው ሁለት ዋንኛ ለውጦች በብዙዎቹ የተመሰገነ ቢሆንም አማራ ግን በዚህ ለውጥ ውስጥ የመጥፋት ትልም የተተገበረት ሁኖ እናገኘዋለን ። መሬት ላራሹና የከተማ ቤትንና ትርፍ ሀብትን በተመለከተ የተወሰኑት ውሳኔዎች በአብዛኛው አማራውን ተጎጂ እንዳደረጉት ግልፅ ነው።
በዚህም በብዛት ባለርስትነት ፍረጃ ከርስቱና ከመሬቱ የተነቀለው አማራ ሆኖ ተገኝቷል። በከተማ የትርፍ ቤት መውረስን ስርዓት ደርግ ሲያወጅ ትርፍ ቤት ሀብት የነበረው እና በገዛ ጥሪት መያዝንና ሀብት ማፍራትን የህይወቱ መመሪያ አድርጎ የኖረው አማራ ማህበራዊ ፍትህ ብቻ የሚያክመው በደል ደርሶበታል ።
ምንም እንኳን ደርግን ወደ ስልጣን ለመምጣት ያስቻለው የዘመኑ ትግል ላይ አማራው በተለያየ መልኩ የነቃ ተሳትፎ ቢያደርግም በውጤት የመጀመሪያ ሰለባ ያደረገው ራሱን አማራውን ነው። ይሄም ትግልንና ስርዓት በሌሎች ማስጠለፍን የተለማመድንበት አንድ ክስተት እና የታሪክ እጥፋት ነው ማለት እችላለሁ።
ህወሓት ኢህአዴግ በስልጣን መንበር ላይ የሌለውንና ያልነበረውን አማራን ገና ከጥንስሱ የደርግ ስርዓት ባለቤት አድርጎ በማቅረብ እና ጦርነቱን ከአማራ ጋር እንደሚደረግ በማስተጋባት በበረሃ ያበቀለውን መሰረተ ቢስ ቂም በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ቁጭ ብሎ ህገ መንግስት ብሎ በማቅረብ ፀረ አማራ ስርዓት ነበረ።
በዚህም አማራው ከርስቱ በደርግ ቢነቀልም ድጋሜ የመሬት ባለቤትነት መብቱን ከክልሉ ውጭ በመላው ሀገሪቱ አጣ። በዚህ ስርዓት የተፈጠሩ ተቋማት አጠቃላይ የመንግስት ተግባራት ሙሉ በሙሉ በግላጭ ፀረ አማራ ሆነው ሲገድሉን ሲያፈናቅሉን ሲያጠፉን ርስቶቻችን ሲነጥቁን ህገ መንግስታዊና ህጋዊ በማለት ነበር።
ይህንን ህወሓታዊ ኢህአዴግን ለመታገልና ለመጣል ትግል ያልተደረገበት አመት የለም ቢባል ሀሰት አይሆንም። ከቀዳሚዎቻችን እነ ፕሮፌሰር አስራትንና መሰል ነፍስ አወቅ አማራዎችን መጥቀስ መዳፍን የማየች ያህል ቀላል ሀቅ ነው።
ህወሓት ኢህአዴግን ከአራት ኪሎ ፣ከባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ደብረብርሀን ለማባረር የተከፈለው መስዋእትነት ቀላል የሚባል አይደለም። ይህንን በትግላችን የፈጠርነውን የለውጥ እድል የራሳችን ናቸው የተባሉ ወዶ ገብ አማራዎች አሳልፈው ለአብይ አህመድ የጭካኔ አገዛዝ በመስጠታቸው የለውጥ ኃይል የተባለው ቡድን የነበረውን ፀረ አማራ ስርዓት ለማስቀጠል እና አጋጣሚውን ወደ ሙሉ ፀረ አማራ ስርዓት ለመቀየር ወራት አልወሰደበትም።
👉 የተከበራችሁ አማራዎች፣ ታጋዮቻቻንና አመራሮች
የአብይ አህመድን አገዛዝ አስቀድመን መስመሩን ጠብቆ ለውጡን ወደ ግብ እንዲወስድ ለራስ እውነት በመርህ መደገፍ ጀምሮ በግልፅ ተቃውሟችንን ያሰማነው ብዙ ቀናትን ሳይወስድብን ነበር። የአማራ ህዝብ አስተውሎት በተፈጥሮ የተሰጠው ፀጋ በመሆኑ እንኳን ደህና መጣህ ያለውን የአብይ አዲስ አገዛዝ በወራት ውስጥ ለማስጠንቀቅ አዳባባዮችን በሰላማዊ ሰልፍ አጨናንቋል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እኛ አሁን በትግሉ ሜዳ ያለነውና አንዳንድ የአማራ ፖለቲከኞች ፣ አመራሮችን፣ ወታደራዊ ሰዎች ፣ስርዓቱ ያልሻረና ፀረ አመራ መሆኑን ተረድተን በተለያዩ መንገድ ለመታገል ወስነን ታግለነዋል።
በሀይል ያባረርነውን የህወሓት ገዥ ሀይል በተጠባባቂ ሀይልነት ለመጠቀም ሲጠብቀው የነበረው ፀረ አማራው ሀይል ሰራዊቴ ተደፈረ በማለቱ ለሀገርና ለህዝብ፣ ለአፅመ እርስቶቻችንና ለበቀል መወጣጫ ላለመሆን ስንል የህወሓትን ወረራ ለመቀልበስ እጅግ በርካታ ወገን፣ ሀብት ፣ ንበረትና አያሌ መስዋትነት ከፍለናል።
ነገር ግን ቁስሉ ያልደረቀውን አማራ ፣ አፅሙ ያልተነሳውን አማራ ፣ ያልታከመችውን የተደፈረች የአማራ እህት፣ የልጇችንና የባሏን መርዶ ያልተረዳችውን የአማራ እናት ፣ የተፈናቀለውን የተሳደደውን የአማራ ወጣት ገበሬ ፣ ሀኪም ባለሃብት ለዘላለም ባሪያ ለማድረግ አረመኔው የብልፅግና አገዛዝ ጦርነቱን ትጥቅ አስፈታለሁ በማለት የብልፅግና ወራሪ በአጣዳፊ ሁኔታ ወረራ ከፈተብን።
አስቀድሞ የነበሩን አንቅስቃሴዎችን ለማጣጣል ፣ለማሳነስ፣ ለማፍረስ እረፍት ያልነበረው አገዛዙ በመዋቅር ደረጃ የአማራ ህዝብ ብዙ ዋጋ ከፍሎ በስርዓት ያቋቋመውን የአማራ ልዩ ሀይልን ከስምሪት ቦታው ሳይመለስ፣ ከሄደበት ቀየ "ለውሻ መጠበቂያ እንጨት ቆርጠህ ያዝ" በማለት ትጥቁንና ሞራሉን ለማስፈታት ሞክሯል።
በዚህ ጊዜ ነው ፋኖ ለአማራ ህዝብ እንደተቋም መሸሸጊያ ከለላ ብሎም ተተኪ መንግስት መሆኑ የታወቀው። ፋኖ በሰአቱ በነበረው የራሱ አደረጃጀት በሜዳ የተበተነውን የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ የያኔው የአማራ ልዩ ሀይል የአሁኖቹን ጓዶቻቸንን ከመበተን እና ተራሟች ከመሆን አትርፎ ፋኖ አቅፎና በወንድምነት ተቀብሎ ድጋሜ አሰልፎ የህዝብ ሀይል ማድረግ ችሏል።
የተከበራችሁ የአፋብሃ አመራሮች ደጋፊዎች አባላት
ክቡራት የአማራ ማህበር በአሜሪካ አመራሮችና የዲያስፖራ አባላት፦
እኛ የምናደርገው ትግል ስርዓታዊና መዋቅራዊ ለውጥን ለማምጣት ያለመ መሆኑ መቼም በምንም ሁኔታ ሊረሳ የሚገባ አይደለም። ይህ ስርዓታዊና መዋቅራዊ ለውጥ እንዲመጣ በሰላማዊ ሰልፍ፣ በመፈናቀል ፣ በመገደልና ሟች በመሆን፣ በመታሰር ተሰዳጅ በመሆን ጭምር ብዙዎች ብንጠይቅ የሚሰማን በማጣታችን የጀመርነው የትጥቅ ትግል ነው ።
አስር አለቃ ሀቢብ የሱፍ በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የነብሮ ኮማንዶ ምክትል ወታደራዊ አዛዥ ✊
ሀቢብ በአማራ ልዩ ሃይል መብረቅ ኮማንዶ ክፍለ ጦር ምርጥ ተዋጊ የነበረ አሁን በፋኖ ደረጃ ምርት አዋጊ ጀግና ልጅ!!!
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
🔥የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን ለመደገፍ‼️
👉Zelle = 202 528 6749
👉E transfer (Canada)
708 802 5536
በዌብሳይት https://amharafanonationalforce.org/
ሸር ሸር አድርጉ ፕሮግራም ስለተጀመረ
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የለንደን ፋኖ የአፋብኃን የሲምፖዚየም ጥሪ በደብዳቤ አጋርነቱን የገለፀ ሲሆን አፋህድ ደግሞ ለዛሬ ይዞት የነበረውን የበይነ መረብ ውይይት ለአፋብኃ ሲምፖዚም ሲል ቀኑን አራዝሟል።
መልካም ተግባር !🙏
ከትግል ሚዳ( ከግንባር) ዋግነር የአማራው ፋኖ በመወዳጀት መረጃዎቻችን በሁሉም አማራጭ ተደራሽ እንሆን ዘንድ የበኩሉዎን አስተዎፆ ያድርጉ ‼️
ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ‼️
የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ እንወያያለን እንማማራለን እንደራጃለን አብርን እናሸንፋለን አድራሻችን👇👇👇👇
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
