ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше3 334
Подписчики
+2524 часа
+3407 дней
+72430 дней
Архив постов
በየቀኑ የህይዎት መሰዋዕትነት በሚከፈልበት በአማራ ፋኖ የትጥቅ ትግል ላይ፣የስራ ኃላፊነት (ሹመት) ሲሰጥ በበቂ መስፈርቶች ተመዝኖ ሊሆን ይገባል። ለአብነትም፦
-ለትግሉ ያለው ታማኝነት (loyality/allegiance)
-የጀርባ ታሪኩ (The background story)
-የትምህርት ደረጃው (The level of education)
-በትግሉ የነበረው ፖለቲካዊና ወታደራዊ ቆይታ ( The duration of the struggle)
-ዝንባሌውና ችሎታው (leaning & capability)
- የህልውና ትግሉን የሚረዳበት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አቅም (Political and military intelligence)
- በሚሰጠው የስራ ኃላፊነት ላይ፣ ያለው ወይም ሊኖረው የሚችለው የመምራት/የማስተዳደር አቅም (Ability to lead or manage)
- የትጥቅ ትግሉን መነሻና መዳረሻ ግብ በቅጡ የለየ እና
-የትጥቅ ትግሉ የሚጠይቀውን እውቀት፣ ፅናት፣ቁርጠኝነትና ድፍረት የተላበሰ መሆን አለበት።
ይህ መሆኑ፦
በእውቀት ክፍተት ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ቸግሮችን አስቀድሞ ለማረቅ ይረዳል። ድርጅትንና መሪን ይጠብቃል። የትግሉን አንኳር መርሆች ያለ ማዛነፍ ለመተግበር ይረዳል። በቀጣይ የዴሞክራሲ መርሆችን ለመተግበር ልምምድን ይፈጥራል። ከአድርባይነት፣ከእከክልኝ ልከክልህና ከአስመሳይነት ያላቅቃል። በጦሩ፣በህዝቡና በህልውና ትግሉ ባለ ድርሻ አካላት ላይ፣ በዘፈቀደ የሚደረግ የስራ ኃላፊነት ምደባ የሚፈጥረውን መጠራጠር ይቀንሳል። ሁሉም እንደየ አቅሙ፣ዝንባሌውና መክሊቱ ትግሉን እንዲያግዝ ይረዳል። በአባሉ፣በአመራሩና በህዝቡ መካከል መከባበርን ይፈጥራል።የመሪና የተመሪን መንፈስ ያዳብራል።
መናናቅን፣ አለመታዘዝን፣ ጥላቻን፣ ተገቢ ያልሆነ አቻዊ ፉክክርንና በትግሉ ተስፋ መቁረጥን ያስቀራል። ከአካባቢያዊነት፣ ከጓደኛ፣ ከዘመድ፣ ከትውውቅና ከጥቅም የስራ ኃላፊነት ምደባ ወጥቶ፣ ችሎታንና እውቀትን (merit based) ሲሆን መዳቢውን አካል ተገቢ ካልሆነ ሐሜት፣ጥርጣሬና ስድብ ያላቅቃል።የመዳቢውን አካል ኃቀኛ አቋም፣አቅምና ለትግሉ ያለውን ታአማኒነት ይገልፃል። የመምራት አቅሙንም ጠንቅቆ ያሳያል።እና ይህ ቢሆን የሚል ምክረሐሳብ እናቀርባለን።
በስተመጨረሻ፦ ህዝባዊ መልክ ይዘው የሚጀመሩ የነፃነት ትግሎች ከግብ ለመድረስ ያላቸው ጠንካራ ጎን እጅግ የላቀ ቢሆንም፣ትልቁ ደካማ ጎናቸው፦ አድርባዩን፣ሌባውን፣ዱርዬውን፣ዘማዊውን፣አስመሳዩን፣ወንጀለኛውንና ደንቆረውን ከንፁሃኑ ታጋይ (ትግሉ የሚጠይቀውን አቅም፣ፅናትና ታማኝነት ካላቸው) ጋር አደባልቀው መያዛቸው ነው።
ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው
+3
ሰበር ዜና!
በቀን 25/7/2018ዓ.ም በወገራ ወረዳ 208ኛ ኮር ሌባዎች ላይ እርምጃ ወሰ*ደ!
በሰሜናዊ ጎንደር ቀጠና የሚንቀሳቀሰው 208ኛ ኮር በዘመቻ ማጥራት እና ማብቃት በአዲስ ሪፎርም ሰርቶ ከበቃ ማግስት ሌባን እና ወንበዴን የማጽዳት ዘመቻ አውጆ እያጸዳ ይገኛል!
የአፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ የ208ኛ ኮር አህዶች በየቀጠናቸው ሌባ የማጽዳት ዘመቻ በማወጅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ሲሆን አምባ ጊወርጊስ ወረዳ ስቅሞ ቀበሌ ጋሻው ነጋሽ እና ምህረት ሙሉ የተባሉ የፋኖን ስም ለማጠልሸት በአገዛዙ የተመደቡ ተላላኪ ወን*በዴ ሌቦች ከማህበረሰቡ 3በሬ በመስረቅ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይም ሁነው ሳለ በአርባ ጾሙ አንዱን አርደው ሲበሉ ሌሎች ሁለቱን ሳያር*ዱ ኮሩ በወሰደው ፈጣን እርምጃ ሁለት ክላሽ እስከሙሉ ትጥቃቸው ከሁለቱ በሬዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
የህዝብ ልጅ የሆነው ፋኖ ሌባቸዎን በመያዝ በሬዎቹን ለባለቤቶች የመለሱ ሲሆን በዚህ ተግባርም ትልቅ ምስጋና ከማህበረሱ ተችሯቸዋል አቀባበልም ተደርጎላቸዋል።
ምስል : ከፋሽስቱ የአብብይ አህመድ አገዛዝ የተላኩ ጋሸው ነጋሽ እና ምህረት ሙሉ የተባሉ የበሬ ሌቦች!
አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ
የ208ኛ ኮር ወታደራዊ ቃል አቀባይ አርበኛ ሳሚ አበራ
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
# አረመኔው አገዛዝ አብይ_አህመድ በዓለ ሲመቱን እያከበረ ባለበት ተመሳሳይ ቀን በአማራ ክልል የተደረገው ሰፊ ተቃውሞ ሰልፍ በስርዓቱ ላይ የሚከተሉትን 5 ጫናዎች ይፈጥራል! (ወይም በጥርጣሬ ሰመለከቱ ለነበሩ ሀይሎች ግልፅ ያደርጋል!)
••• !
የቅቡልነት (Legitimacy) ጥያቄ፦
*
ብልፅግና በዓለ ሲመቱን በሚያበስርበት ቀን እንዲህ ያለ ተቃውሞ መደረጉ፣ ብልፅግና በክልሉ የነበረውን ህዝባዊ ድጋፍ በከፍተኛ ሁኔታ ማጣቱንና ቅቡልነት የሌለው ስርዓት እንደሆነ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ለሀገር ውስጥ ኃይሎች በግልጽ ያሳያል።
*
የምርጫ ተግዳሮት፦
*
አብይ አህመድ በቅርቡ ለማድረግ ያሰበውን የይስሙላ ሀገራዊ ምርጫ (ቤተሰባዊ ቅርጫ) "ሰላም በሌለበት ምርጫ አይካሄድም!" የሚለው የሰልፈኞቹ መፈክር፣ ምርጫው በክልሉ የመካሄድ ዕድሉን አጠራጣሪ ከማድረጉም በላይ ውጤቱ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳይኖረው ያደርጋል።
*
የፖለቲካ ትርክት መናጋት፦
*
ስርዓቱ "ሁሉንም ያቀፈና ሰላማዊ" እንደሆነ አድርጎ የሚገነባው የሀሰት ትርክት እና ፕሮፓጋንዳ ዛሬ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያት ጥያቄ ውስጥ ከመግባቱም በላይ፣ በቀጣይ በሚደረግ ህዝባዊ ተቃውሞ እጅግ የሚፈተን ሲሆን፣ #ብልፅግና ክልሉን የማረጋጋት አቅም እንደሌለው አመላካች ይሆናል።
*
የኢኮኖሚና የመልካም አስተዳደር ጫና፦
*
በክልሉ የታየው የህዝብ እምቢተኝነትና የስራ ማቆም አድማ ከሰላምና ፀጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ የመንግስትን የገቢ ምንጭ ከማዳከሙም በላይ፣ የፌዴራል መንግስቱ በአማራ ክልል ያለውን አስተዳደራዊ ቁጥጥር ከነበረው በበለጠ ሁኔታ እንዲላላ ያደርገዋል።
*
የውጭ ግፊት መጨመር፦
*
በሰልፉ ላይ የተነሱት የሰብአዊ መብት ጥሰትና የድሮን ጥቃቶች
ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር ምስራቅ አማራ ቀጠና ወታደራዊ ተዋጊ መሃንዲስ የሰራዊት አባላትን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ‼️
ጀብደኛው የ102ኛ ኮር ዛሬም እንደትናንቱ ለሰራዊታችን የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የሚታወቀው ለተከታታይ 3 ወራት ያሰለጠናቸውን የተዋጊ ማሀንድስ ሰልጣኞችን አስመረቀ።
የምረቃ ፕሮግራሙን የመክፈቻ ንግግር በአርበኛ ዘውዱ ዳርጌ የ102ኛ ኮር ም/ወታደራዊ አዛዥ የተደረገ ሲሆን ለሰልጣኞት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ወታደራዊ አዛዡ አያይዘው እንደተናገሩት ከሆነ የብልፅግናን ጨፍጫፊ አገዛዝ በአጭር ጊዜ ለማስወገድ የቴክኖሎጅ ሽግግር በማድረግ የተለያዩ ስልጠናዎች በየክፍለጦሮች ያለ ማቋረጥ እንደሚቀጥሉ ጠንከር ያለ ሀሳብ አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም ከ101ኛ ኮር፣ከ102ኛ ኮር እንድሁም ከልዩ ዘመቻ የተወጣጡት የተዋጊ ማሀንድስ አሰልጣኞች አርበኛ ሀየሎም ሲሳይ፣አርበኛ ዮሴፍ ሲሳይ፣ አርበኛ ፋሲል ፀጋየ፣ አርበኛ ዳዊት ፀጋየና አርበኛ አዳነ መኮነን እንደተናገሩት ያለጦርነት መኖር ከማይፈልገው የብልፅግና አገዛዝ የአማራን ህዝብ በቀላሉ ነፃ ለማውጣት ከ102ኛ ኮር በሁሉም ክፍለ ጦሮች የተወጣጡ ሰልጣኞችን በተግባርና በንድፈ ሀሳብ የተደገፈና ውጤታማ የሆነ የተዋጊ መሃንዲስ ስልጠና ለሰልጣኞች መስጠታቸውን ተናግረዋል።
በመጨረሻም 102ኛ ኮር የፖለቲካ መምሪያ ሀላፊ አርበኛ ሻንበል አሌና የ102ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ አታሎ ሙሉጌታ ለተዋጊ ማሀንድስ ሰልጣኞች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ የአማራን ህዝብ በምርጫ ስም በሀይል ለማንበርከክ፣ ህገ-መንግስታዊና መዋቅራዊ በደል ለማስቀጠል እንዲሁም በምርጫ ካርድ የአማራን ጭፍጨፋ ለማስቀጠል የመጣውን የብልፅግና አገዛዝ ለማስወገድ በሌሎች ኮሮች ለሚገኙ ክፍለጦሮች ስልጠናው ጥሩ ተሞክሮ መሆኑን ገልፀዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
25/ዐ7/2018 ዓ.ም
ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር ምስራቅ አማራ ቀጠና ወታደራዊ ተዋጊ መሃንዲስ የሰራዊት አባላትን በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።
ጀብደኛው የ102ኛ ኮር ዛሬም እንደትናንቱ ለሰራዊታችን የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የሚታወቀው ለተከታታይ 3 ወራት ያሰለጠናቸውን የተዋጊ ማሀንድስ ሰልጣኞችን አስመረቀ።
የምረቃ ፕሮግራሙን የመክፈቻ ንግግር በአርበኛ ዘውዱ ዳርጌ የ102ኛ ኮር ም/ወታደራዊ አዛዥ የተደረገ ሲሆን ለሰልጣኞት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ወታደራዊ አዛዡ አያይዘው እንደተናገሩት ከሆነ የብልፅግናን ጨፍጫፊ አገዛዝ በአጭር ጊዜ ለማስወገድ የቴክኖሎጅ ሽግግር በማድረግ የተለያዩ ስልጠናዎች በየክፍለጦሮች ያለ ማቋረጥ እንደሚቀጥሉ ጠንከር ያለ ሀሳብ አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም ከ101ኛ ኮር፣ከ102ኛ ኮር እንድሁም ከልዩ ዘመቻ የተወጣጡት የተዋጊ ማሀንድስ አሰልጣኞች አርበኛ ሀየሎም ሲሳይ፣አርበኛ ዮሴፍ ሲሳይ፣ አርበኛ ፋሲል ፀጋየ፣ አርበኛ ዳዊት ፀጋየና አርበኛ አዳነ መኮነን እንደተናገሩት ያለጦርነት መኖር ከማይፈልገው የብልፅግና አገዛዝ የአማራን ህዝብ በቀላሉ ነፃ ለማውጣት ከ102ኛ ኮር በሁሉም ክፍለ ጦሮች የተወጣጡ ሰልጣኞችን በተግባርና በንድፈ ሀሳብ የተደገፈና ውጤታማ የሆነ የተዋጊ መሃንዲስ ስልጠና ለሰልጣኞች መስጠታቸውን ተናግረዋል።
በመጨረሻም 102ኛ ኮር የፖለቲካ መምሪያ ሀላፊ አርበኛ ሻንበል አሌና የ102ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ አታሎ ሙሉጌታ ለተዋጊ ማሀንድስ ሰልጣኞች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ የአማራን ህዝብ በምርጫ ስም በሀይል ለማንበርከክ፣ ህገ-መንግስታዊና መዋቅራዊ በደል ለማስቀጠል እንዲሁም በምርጫ ካርድ የአማራን ጭፍጨፋ ለማስቀጠል የመጣውን የብልፅግና አገዛዝ ለማስወገድ በሌሎች ኮሮች ለሚገኙ ክፍለጦሮች ስልጠናው ጥሩ ተሞክሮ መሆኑን ገልፀዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 25/2018ዓ/ም
ደብረ ማርቆስ
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 7:00 ሰዓት በፈፀመው የቦምብ ጥቃት ዘጠኝ የአድማ ብተና አባላት ተደመሰሱ።
መጋቢት 25/2018 ዓ.ም
======================================
አነፍናፊዎች የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከቀናት በኋላ በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት በተለምዶ ስላሴ ካምፕ ተብሎ ከሚጠራው ወታደራዊ ግቢ ተነስተው በአንድ ፓትሮል ተጭነው ወደ መሐል ከተማ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የአድማ ብተና አባላት ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ቲም መሪውን ጨምሮ ዘጠኝ አባላት መደምሰሳቸው ታውቋል።
ሌሊቱን በተፈፀመው የተጠና ጥቃት አስክሬኑን የታቀፈው የአረመኔው ሰራዊት ከጥቅም ውጭ ሁና በቦምብ የጋየችውን ፓትሮል ሲገትት ያደረ ሲሆን ከቀናት በፊት በንጉስ ተክለሃይማኖት ክ/ከተማ በተፈፀመ ጥቃት እንዲሁ 23 አድማ ብተና አባላት መደምሰሳቸው ይታወሳል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሰበር ቁርስ ዜና
=============
ምስራቅ ደንቢያ ቆላድባ ሱፋን ቃራ የኦሕዴድ ቅጥረኛ ሰራዊት ከነ አመራሩ ተደመሰሰ
ዝርዝሩን እንመለስበታለን
በፌጥራ ከተማ በተሰራ ልዩ ኦፕሬሽን የፌጥራ ከተማ አመራሮች ተማረኩ!
አገዛዙ አለኝ የሚለውን አየር ወለድ ኮማንዶ በሚሊሻ መንገድ መሪነት ወደ ጎራንዳ በፋኖ ላይ ጥቃት ለመፈፀም ቢያስገባም በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያቆብ ኮር ናደው ክፍለ ጦር አናብስቶች ያልጠበቀውን ሽንፈት ተከናንቧል ።
መነሻውን መርሀቤቴ ፌጥራ ከተማ አድርጎ በሶስት አቅጣጫ ወደ ጎራንዳ ቀበሌ ስምሪት ቢያደርግም በሶስቱም አቅጣጫ ከባድ ኪሳራ አስተናግዶ ሙትና ቁስለኛውን በቅጡ ሳይሰበስብ ፈርጥጧል።
በዚሁ ቅፅፈት ልዩ ስምሪት ወስደው ፌጥራ ከተማ የገቡት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አጼ ዘርያቆብ ኮር ናደው ክፍለ ጦር ተወርዋሪ አባላት በሰሩት ልዩ ኦፕሬሽን 1, የፌጥራ መሪ መዘጋጃ ቤት ኃላፊ ልጁወንድራድ ዝቅ አድርግ
2,የፌጥራ መሪ መዘጋጃ ቤት ም/ኃላፊ ተኮላ ክብረት ጨምሮ ሌሎች ለአገዛዙ አድረው አገዛዙን ሲያገለግሉ የነበሩ የሚሊሻ አባላቶችንና በአገዛዙ የደህንነት መዋቅር የነበሩ ካቢኔዎች በመማረክ ከከተማ ይዘው ወጥተዋል።
በዚህ የተበሳጨውና የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው አገዛዝ የበቀል በትሩን ባልታጠቁ በንፁሀን አማራዎች ላይ እያሳረፈ ይገኛል።
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕ/ግኙነት መምሪያ
#የዶሽቃ_ሻምበል👏👏👏👏
#የደጃዝማች_ተሰማ_እርገጤ_ክፍለጦር_2ኛ_ሻለቃ_የዶሽቃ_ሻምበል👏👏👏
#የህዝባችንን_የተቃውሞ_ድምፅ_ለማፈን_የሞከረው_የብልፅግናው_አየርወለድ_ሰራዊት_ተገርፎ_ተመለሰ🚫
👉በትላንትናው ዕለት የተደረጉትን ህዝባዊ ትይንቶች ለማደናቀፍ በተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ አየር ወለድ ሰራዊት ላይ #በጀግናው_የአማራ_ፋኖ_ሰራዊት ክንድ እግር በእግር ተከታትሎ ተገርፎ ወደመጣበት ፈርጥጦ ሲመለስ ህዝባችንም የአደባባይ ተቃውሞውን ያለማንም ከልካይ በነፃነት አሳይቷል።
#የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር:-
#ቃኝ_ሰራዊት 👏
#የደጃዝማች_ተሰማ_እርገጤ_ክፍለጦር👏
#የዕዙ_ቃኝ_ንስር_ሻለቃ👏
ትግሉ ተሸጧል
እች ትግሉ ተሸጧል የምትባል የማትገባኝ ቋንቋ አለች ደግሞ ፤ ለማን ነዉ የሚሸጠዉ ፣ትግሉን የሚገዛዉ ማን ነዉ፣ ለመሆኑ ደላላስ ይኖረዉ ይሆን ? " ጠላቴ ነህ ብየ ስታገለዉ ህዝቤን ሲገድል ስዋጋዉ ለኖርሁት ጠላቴ እንዴት አቤቱታ ላቀርብ እችላለሁ"
ተልእኮዉን ሲጨርስ እና አሰራር እንዲሁም ተጠያቂነት ሲጠነክር እንደፈለጉ በሌሎች ድካም በቲክቶከ በተገነባ ስብእና ማጭበርበርና መለመን አልቻል ሲል እሩጠዉ ጠላታችን ሲሉት ለነበረ ስርአት ትግሉ ተሽጧል ቅብጥርሴ የሚል የተለመደች የባንዳ ተግባርና ሀላፊነት አለች እሱዋን እንደቃለማህላ አድርገዉ ይቀባጥሯታል ።
ወዳጀ አንተ መሸከም አቅቶህ ጥለህ የፈረጠጥክበትን ትግል የሚገዛ የለም ሁሉም የየራሱ ሸክም አለበት እኛ ብልፅግናን ይፋዊ ጠላታችን ነዉ ብለን ፈርጀን ስንታገለዉ ብልፅግናና የሻቢያ መንግስት ወዳጅ ነበሩ ህዉሀትና ብልፅግናም ስምምነት በሚል ቀልድ ሽታየ ሽታየ ይባባሉ ነበር ።
ፋኖም እንደዛሬዉ የጋራ አላማ ሳይሆን በጠላትነት የተፈረጀ የጋራ ጠላት እንዳለዉ አምኖ ትግል አቀጣጠለ ።
ታድያ በጊዜዉ አንድ ድርጅት ሳይኖር እያለ በጋራ መግባባት የተቀመጠ አላማና ግብ ሳይኖር የትኛዉ የትግል የጋራ አላማ በምን አይነት መንገድ ወደየትስ ይስታል ? ያልነበረ በጋራ ያልተቀመጠ አላማ ወደየትስ ይጠለፋል ?
አማራዉ ወደአንድ አላማ ወደ አንድ ድርጅት ሲመጣ የተበታተነ የነበረዉ ድርጅት በጋራ አላማ ሲሰለፍ ትግሉ ተጠለፈ ካልክ ላንተ ትግልህ ዝርፊያ ልመና ሀብት ማካበት ነበር ማለት ነዉ ።
ታድያ የአማራ ፋኖ እራሱ ጀምሮ እዚህ ባደረሰዉ ትግል ላይ የስርአቱ ተንኳሽነት ሁልጊዜ ስጋት ሆኖባቸዉ ለጠላትነት ጋብዞ ወደጦርነት እያስገባቸዉ ያሉትን አካላት በነኝህ ለጠላት ባደሩ ፋኖ መሳዮች አንደበት የፋኖን ትግል ዘዋሪ ለማስመሰል ሲላላጡ ከማየት በላይ ምን የጅልነት ማሳያ አለ ?።
ብልፅግና ወፈረ ቀጠነ ማብዛት አያስፈልግም በራሳችን እቅድ ፈንቅለን ባናትህ ተክለን ለኢትዮጰያ የሚበጅ ስርአት ልንገነባ እየሰራን ነዉ ።
በወዶገብነት ያደሩልህን ዉሽልሽሎች እንደቁራ ማስጮሁ ከንቱ ድካም ነዉ ።
ፋኖ የሚታገልበት የጠራ ምክንያት አለዉ እሱም የአማራ ህዝብ ህልዉና እንደህዝብ የመኖርና ያለመኖሩ ጉዳይ ስጋት ዉስጥ መዉደቁ ነዉ ።
ፋኖ የሚታገለዉ የታወቀ ጠላት አለዉ እሱም ህዝባችንና እኛነታችን ሊያጠፋን የተነሳ እንደህዝብ ለመቀጠል ስጋታችን የሆነ ብልፅግና የተባለ የኦሮሙማ የመንግስት ስርአት አለ ።
ፋኖ ግብ አለዉ ይህን አንከሊስ የሆነ ፀረ ህዝብ ስርአት አፈራርሶ በኢትዮጵያ ምድር ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር አማራዉም ሌላዉ ኢትዮጵያዊም ያለስጋት የሚኖሮበት ስርአተ መንግስት መገንባት ነዉ ።
ታድያ ይህን አላማ የሚቀበል ወዳጃችን የማይቀበልና እንቅፋት የሚሆን ደግሞ ጠላታችን ነዉ ።
ከአረብ ኢሚሬት በግዥና በሀገር ጥቅም በመዋዋል በሚያመጣዉ ድሮን ህፃን ከትልቅ እየጨፈጨፈ ሀገሩና ህዝቡ ላይ ጦርነት ላወጀ ስርአት አድሮ ትግሉ ተሸጧል ከነ እገሌጋር ይገናኛሉ ብለህ የምታጎበድድ ወስላታ በጊዜ ሂደት ግብርህ ተገለጠ እንጅ ቀድሞዉንም ባንዳ የባንዳ ልጅ ነህ ።
አጠረም ረዘመም ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን አስተባብረን ስርአት ነቅለን ስርአት እንተክላለን አራት ነጥብ ።
አርበኛ ሳሙኤል ባለ እድል
የአፋብን ስልጠና መምሪያ ሀላፊ
ከሰው መርጦ ለሹመት፤ ከእንጨት መርጦ ለታቦት ይባላል:: የአማራ ህዝብ የጀመረውን የህልውና ትግል ይመሩ ዘንድ ከፊት የተሰለፉ ወንድሞቻችን ማወቅ ያለባቸው ፍሬ ነገር ቢኖር መሪ ማለት መንገዱን የሚያውቅ፣ በመንገዱ የሚጓዝ እና መንገዱን ለተከታዮቹ ማሳየት የሚችል መሆን እንዳለበት ነው::
ይህን ትግል ምሩ ተብለው ሲሰየሙ የደም አብዮት እየመሩ መሆናቸውን ተገንዝበው እጃቸውን ንፁህ፣ ልባቸውን ደግሞ ለወገን ሩህሩህ ለጠላት ድፍን ቅል ነው ማድረግ ያለባቸው:: ለወዳጅ ማር ለጠላት እሬት ማለት ይህ ነው:: "ትመር እንደሆነ ምረር እንደ ቅል ባይመር አይደለም ወይ ዱባ 'ሚቀቀል" እንደተባለው መራራ ትግል ማድረግ ካልቻልን እንደምንጠፋ መገንዘብም አለባቸው:: በዚህ ልክ አዕምሯቸውን አሳምነው መረር ያለ ትግል ለማካሄድ ማለትም ታግሎ ለማታገል ቁርጠኛ ሲሆኑ የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት ይችላሉ::
በአርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ እና በአርበኛ ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ ትልቅ ተስፋ አለን:: በሸዋ እና ጎንደር ግንባሮች ትግሉ ይበልጥ ይሰምር ዘንድ ሰበብ እንደሚሆኑ ተገማች ነው::
ከወንድሞቻቸው ጋር የነበራቸውን ቅራኔ በሰለጠነ አግባብ የፈቱበት መንገድም ለመሪነት የሚፈለገው ኳሊቲ እንዳላቸው አስረጅ ነው:: ይህ ትግል ውስጣዊ አንድነትን በእጅጉ ይሻል::
አንድነት ደግሞ በውይይት እና ምክክር እንድሁም ሰጥቶ በመቀበል እንጅ በእብሪት እውን አይሆንም:: እኛ የተመደብንበት ቦታ ላይ እንሰራለን ወደ ድርጅት እነ እከሌ ከፍ ይበሉ ብሎ ለእነ እከሌ እድል መስጠት የተቻለበት አግባብ እንዳለ ይሰማኛል:: ይህ ደግሞ አማራዊ ትሕትና ነው:: ትሑት ባይሆኑ ኖሮ እኛም አፋብን ላይ ቦታ እንሻለን የሚል ሙግት ገጥመው ድርጅቱ እውን ሳይሆን ይቀር ነበር:: ለህዝብ ሲሉ መተናነስን እና ትግልን ለመጠበቅ ዝግ ማለትን ባህል ማድረግ አለብን:: የትኛውም ግለሰብ ከህዝብ አይበልጥም:: የግል ኢጎን እየገደሉ ለወል ጥቅም እና ፍላጎት ተገዥ መሆን ደስ ይላል::
በአንድነቱ እና በአመራር ምደባው እጅጉን ከተደሰቱ አማሮች መካከል ነኝ::
ትግሉ መስመር እየያዘ መሆኑን ማሳያዎች አሉ:: በፋኖ ስም የሚነግዱ ጥቂት ግለሰቦችም ድርጅታችን ሲጠነክር ይወገዳሉ:: ድርጅት ሲኖር ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ይሰፍናል::
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝን እንድመራ የተሰየመው አርበኛ ኢንጅነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ ልክ እንደ ነብዩ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ አስተዋይ፣ ደፋር እና የእውነት ሰው ሆኖ ያታግለናል የሚል እምነት አለኝ::
በስም የከበረ እና በውሀ የሰከረ ስለሌለ ዝም ብሎ በስምህ ልጠራ ማለት ሳይሆን ተግባርህን ልፈፅም ታሪክህንም ልድገም የሚል ቁርጠኝነት ያስፈልጋልና ይህን ቁርጠኝነት ደግሞ ኢንጅነሩ ተላብሶታል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ::
በተመሳሳይ መልኩ የጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዘለቀ ዕዝን እንድመራ የተመረጠው አርበኛ ዮሐንስ የአባ ኮስትር በላይን ማንነት በማስታወስ እሱን ሆኖ እንደምናየው አምናለሁ::
መድፍ መትረየሱን ጎዝጉዘኸው ተኛ፣
አባ ኮስትር በላይ የፋሽስቱ ዳኛ።
ሲባል የነበረው አባ ኮስትር በላይ ዘለቀ የነጩን ፋሽስት ጣልያን ጦር ስላንቀጠቀጠ ነው:: የጥቁሩን ፋሽስት (አብይ አህመድን) ጦር በማንቀጥቀጥ የአባ ኮስትር ልጅነቱን በተግባር በማሳየት ስም እና ተግባርን ያጣጣማል ብዬ በአርበኛ ዮሐንስ አምንበታለሁ::
በተረፈ ሁለቱም መሪዎች እንደ መሪ ለሁሉም እኩል እይታ ኖሯቸው ፍትሀዊ እና ግልጽነት ያለው አሰራርን ያሰፍናሉ የሚል እምነት አለኝ:: አንተ የእስክንድር አንተ የዘመነ ነበርክ በማለት በዘመነ - እስክንድር የጎራ ክፍፍል እሳቤ ተበርዘው ሰራዊት እና ድርጅት ይረብሻሉ ብዬም አላምንም:: እከሌ ከዚህ በፊት እንዲህ አድርጎኛል የሚል የቂመኝነት ዝንባሌም ይኖራል ብዬ አልሰጋም:: እርቁ እና አንድነቱ ይገዛናል ብለው እነሱም ሰራዊታቸውም ማመን አለባቸው::
ሽማግሌ እኮ ሰማይ ቢቀደድ ይሰፋል:: የኛ ሽማግሌ ደግሞ ታላቁ የአማራ ህዝብ ነውና የአማራ ህዝብን ማስቀየም የለብንም::
በሼህ እና በቄስ እንድሁም በሀገር ሽማግሌ እና በህዝብ ፊት
ታርቆ ተለቃልቆ እንደገና ነገር መቅመል የለም::
ትግሉን ለመምራት ንፅህና እና አስተውሎት እንድሁም እውቀት እና እውነት ወሳኝ ናቸው::
ወንድሞቼ ሆይ መልካም የትግል ምዕራፍ እንድሆንላችሁ እመኛለሁ::
በድሮን እና መድፍ ለሚጨፈጨፍ ህዝብ ምርጫ ቅንጦ ነው!!
በጎጃም እነማይ የቀበኃና፣ ዴንሳ እነቆራ እና ሸበል በረንታ ህዝባዊ ተቃውሞ
መጋቢት 24 ጥቁር ቀን
የስምንት ዓመታት የእልቂትና የሰቆቃ ዘመን
◈በጣም የሚያስፈራው ልክ መጠን የሌለው የጥፋት ልምምዳችን ነው።
◈በእነዚህ ስምንት የዕልቂት ዓመታት ከትናንት እስከ ዛሬ የሆነብን እና የእኛን መረዳት ስመለከተው አስፈሪም አሳፋሪም ልምምድ ላይ እንኛለን።
◈ሁኔታውን መቀየር እየቻልነ የበዛ ልምምዳችን የጥፋት ዕጣ ፈንታ የወደቀብን አስመስሎናል።
◈የምእመናንን፣የገዳማትን፣የአብነትን..ውድመት ሰምነትን በልምምድ እያሳለፍነው ነው።
◈ሞትን ውድመትን መልመድ፤
◈መጠቃትን፣መዋረድን መለማመድ፤
◈እልቂትን ፍጅትን መለማመድ፤
◈መሳደድን መሳቀቅን መለማመድ፤
◈ትርክትን ስደትን መለማመድ፤
◈ግፍን ሰቆቃን መለማመድ፤
◈ኢ ቀኖናዊነትን፣መለካዊነትን መለማመድ፤
◈ሁለንተናዊ ጥፋትን መለማመድ ከጀመረን በተለየ መልኩ ስምንት የሞት ዓመታት ተቆጥረዋል።
◈በልምምድ በሽታ ተሸፍነን እውነታውን መርሳት አይቻልም።
◈ክርስቲያን መሰል ድንዙዛን ኦርቶዶክሳውያንም የጥፋቱ ዱላ ሁነው አብረው ራሳቸውን፣ታሪካቸውን፣ወገናቸውን.. ሲያጠፉ ይስተዋላሉ።
◈ሁሉም ሰው በሞት ልምምድ ወጥቶ በያለበት እንደየ አቅሙ በጸሎት እግዚአብሔርን ከመጠየቅ ጀምሮ የመፍትሄ መንገድ መፈለግ አለበት።
◈ማስመሰልና ራስን ማታለል ግን አደገኛ የሞት ልምምድ ነው።
◈ከጥፋት ልምምዱ ወጥተን ወደ ጠቃሚ ልምምዱ ስንመሰል ሁሉም መልክ ይይዛል።
◈ክርስቲያን የምድር ጨው ነው ሁሉንም ማጣፈጥና መለወጥ አለበት።ማቴ.፭፥፲፫ ጨምሩበት ቤተሰብ
