ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 413
Подписчики
+2224 часа
+437 дней
+1 38430 дней
Архив постов
#የልዩ_ኮማንዶ_ምረቃ‼️
ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶዎች በድምቀት አስመረቀ‼️ የምረቃ ፕሮግራሙን ከታች ባለው ማስፈንጠሪያ ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/288Ay0SaUfI?si=n4mbwN5QGNLKqHkv
ብልጽግና በሊቦ ከምከም ወረዳ ንጹሃን አርሶ አደሮችን ጨፈጨፈ።
በትላንትናው እለት ጥቅምት 20 /2018 ዓ.ም በሊቦ ከምከም ወረዳ ቡራ እግዚአራብ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጭሮየ ከተባለው አካባቢ በመከላከያና የአማራ ህዝብ ጡት ነካሽ በሆነው ሚሊሻ አባት እስከነ ልጁን እና ከብቶችን ግጦሽ ላይ በማገት ላይ የነበረን የ8 ዓመት ህፃንን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ 7 በላይ ንጹሃን አርሶ አደር አማሮችን በአሰቃቂ ሁኔታ ረሽነዋል።
ከዚህም በተጨማሪ እዚሁ ቀበሌ ላይ ዘመድ ለመጠየቅ ከሌላ ቦታ የመጡ የቡራ እግዚአራብ ቀበሌ ነዋሪ ያልሆኑ ተጨማሪ አባትና ልጅም በግፍ ተረሽነዋል። ከተረሸኑት ንጹሃን አማሮች መካከል:-
1- ሞላ ታከለ
2-አስቻለው ሞላ
3- ሃብቴ አዲሴ
እንዲሁም ሌሎች ለጊዜው ስማቸው ያልደረሰን ወገኖቻችንም ተወልደው ባደጉበት ፣ ድረው ኩለውና አርሰው አንደፋርሰው በኖሩበት ቀያቸው በብልጽግና አረመኔ አሽከሮች የጭካኔ ጥግ በተሞላበት አኳኋን ተረሽነዋል።
ሌሎች
2 ንጹሃን አማሮችም ክፋኛ ቆስለው አምልጠው በህክምና ላይ ይገኛሉ።
ይህ ዘር የማጥፋት ዘመቻ አሁን ላይ የተጀመረ ባይሆንም ይበልጥ ተባብሶ አድማሱን እያሰፋ በመቀጠል ላይ ነው።
#Stop Amhara Gennocide !!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ጥቅምት 21/2018 ዓም
📌ጥብቅ መረጃ!
ባለፉት ሶስት ቀናት የመከላከያ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ ኃላፊዎች ስብሰባ ማድረጋቸውን የኢትዮ 251 የውስጥ ምንጮች ገለፁ።
የመከላከያ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ ኃላፊዎች ባደረጉት ስብሰባ በርካታ አጀንዳዎች ላይ እንደተወያዩ የገለፁ ሲሆን ሁለት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ እንዳሳለፉም የ251 ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል።
የመጀመሪያው የተመረዙ ምግቦችን (ሬሽኖችን) ስርጭት ማድረግ ነው። በመቀጠል የተመረዙ ሬሽኖችን ስርጭት በማድረግ እንዲማረኩና ፋኖ እንዲመገባቸው ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር የሚል ነው። ለዚህም የተመረዙ ምግቦችን ወደ ካምፕና ምሽጎች በማስገባት ፋኖ ላይ ትንኮሳ ማድረግ ፋኖ ጥቃት በሚከፍትበት ወቅት የተመረዙ ሬሽኖችን ካምፖችና ምሽጎች ላይ ጥሎ በመሔድ በፋኖ እጅ እንዲወድቁና ፋኖ እንዲመገባቸው ማድረግ እንደሆነ የ251 ሚዲያ የመረጃ ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
እንደ መረጃ ምንጮቻችን ገለጻ "እነዚህን የተመረዙ ምግቦች (ሬሽኖች) በሚጓጓዙበት ወቅት በፋኖ እንዲማረኩ ማድረግና በፋኖ እጅ እንዲገቡና ለምግብነት እንዲያውላቸው ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር የሚል ነው።" ብለዋል።
እነዚህ የተመረዙ ምግቦች በዚህ ወር መጨረሻ ድረስ ወደ አማራ ክልል እንዲገቡና ስርጭት እንዲደረግ ውሳኔ መተላለፉን የኢትዮ 251 ሚዲያ የውስጥ ምንጮች ገልፀዋል።
ሁለተኛው ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ "አነስተኛ የሆኑ አጥፍቶ ጠፊ ድርኖችን ወደ ስምሪት ማስገባት ላይ ውሳኔ አሳልፈዋል፤ በዚህም ወደ 700 ገደማ የሚጠጉ ወደ አማራ ክልል የገቡ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ስምሪት እንዲያደርጉ መግባባት መድረሳቸውን" የ251 ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል።
"ወሎ የገቡት 160 አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች በአስቸኳይ ወደ ስራ እንዲገቡና ሙከራ እንዲደረግባቸው ውጤታማነታቸው ሪፖርት እንዲደረግ መመሪያ ማውረዳቸውን" የ251 የውስጥ ምንጮች ገልፀዋል።
"መሳሪያዎች በምድርና በሰማይ ተጠቅሞ የፋኖን ግስጋሴ ባለመግታቱ በመርዝና በአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ተጠቅሞ ፋኖ ላይ ጉዳት አደርሳለሁ ብሎ እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ መረጃዎቹ በፍጥነት እንዲሰራጩ እና ፋኖ አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርግ" ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።
ኢትዮ 251 ሚዲያ ያናገራቸው Drone Systems Engineer ባለሙያ በበኩላቸው "እነዚህ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች በአነስተኛ ዋጋ ገበያ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው አገዛዙ በስፋት ሊጠቀምባቸው ይችላል ያሉ ሲሆን፤ ፋኖም በቀላሉ መትቶ መጣል የሚችላቸው የድሮን አይነቶች ናቸው ብለዋል።
ባለሙያው አክለውም እነዚህ ድሮኖች ዝቅ ብለው (low altitude) ስለሚበሩ ድምፃቸውን በመስማትና ዝግጁ ሆኖ በመጠበቅ ፋኖ እጅ ላይ ባለ መሳሪያ ዲሽቃ፣ ስናይፐር አልያም በክላሽ ተመትተው ሊከሰከሱና ሊፈነዱ ስለሚችሉ ፋኖ ሰማዩን በመከታተል አለርት ሆኖ በመጠበቅ ድሮኖቹ ኢላማቸውን እንዳይመቱና ጥቃት መፈፀም እንደሚችል ገልፀዋል። ፋኖ በነፃነት በሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ፋኖ መትቶ ለመጣል ዝግጁ ባልሆነበት ሁኔታ እነዚህን ድሮኖች በመላክ ጥቃት ሊፈፀም ስለሚችል በማንኛውም ሁኔታ ሰማዩን አስሰው ጥቃት መፈፀም የሚችሉ የሰማይ ዋርድያዎችን መመደብ እንዳለበት" ገልፀዋል።
ሌላው እነዚህን ድሮኖች ለመጣል የሚያስች ፀረ ድሮን መሳሪያዎች ከ4 ሺህ ዶላር በታች ገበያ ላይ ስለሚገኙ በውጪ የሚገኙ የፋኖ ትግል ደጋፊዎች እነዚህን መሳሪያዎች ለፋኖ ቢያደርሱ ፋኖ እነዚህን ፀረ ድሮን መሳሪያዎች በመጠቀም በ 3 እና በ4 ኪ.ሜ ርቀት የአገዛዙን አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ጃም ማድረግ እንደሚቻል ገልፀዋል።
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+4
ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶዎች በድምቀት አስመረቀ::
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ልዩ ኮማንዶዎች ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል::
የአማራን ህዝብ ህልውና ለማረጋገጥ ሁለንተናዊ ተጋድሎ እያደረገ ያለው ፋኖ አዳዲስ ምልምል ፋኖዎችን በእግረኛ እና በልዩ ኮማንዶ ብሎም በመካናይዝድ ደረጃ እያሰለጠነና እያስመረቀ ነባሩን የፋኖ ሰራዊት በሰው ሃይል እያጠናከረ ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም የዕዙ ስልጠና መምሪያ በበርካታ ቀጠናዎች ምልምል ፋኖዎችን እያሰለጠነ እያስመረቀ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል::
ሰልጥነን እንዋጋለን እየተዋጋን እንሰለጥናለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
አገዛዙ ኃይል ለአርሲው ግድያ “ ይቅርታ እንዲጠይቅና ካሣ እንዲከፍል ” ኢሕአፓ ጠየቀ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ይህንን ያለው ዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣውና ለአዲስ ማለዳ በላከላት መግለጫ ላይ ነው፡፡
ፓርቲው በመግለጫው “ በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ አርሲ ዞን አስተዳደር እና ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በጉና እና በመርቲ ወረዳዎች 17፣ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በሽርካ ወረዳ 3፣ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳ 5 በድምሩ 25 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ” ብሏል፡፡
ኢሕአፓ በምዕመኑ ላይ የተፈጸመው ግድያና አካላዊ ጉዳትን አውግዞ መንግስት ተጠያቂነቱን እንዲያምን እና ወንጀሉን የፈጸሙት አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ አሳስቧል፡፡
ለደረሰው ግድያና አካላዊ ጉዳት የተሰማውን ሐዘን የገለጸው ፓርቲው መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅና አስፈላጊ ያለውን ካሳ ለሚመለከታቸው ሁሉ እንዲከፍል ጠይቋል፡፡ የፓርቲው መግለጫ ሲቀጥል ጉዳት ከደረሰባቸው ባለፈም የዕምነቱን ተከታዮች፣ የእስልምና ተከታዮች ላይ ለደረሱት ጉዳቶች በተመሳሳይ ይቅርታ እንዲጠይቅ አሳስቧል፡፡
ከጥቂት አመታት ወዲህ የተባባሱት መጠነ-ሰፊ በዕምነትና በዘር ልዩነት ላይ የተመሠረቱ ግድያዎች፤ አፈናዎች፣ እገታዎች፣ ማፈናቀሎች፣ የንብረት ንጥቂያዎችና ውድመቶች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤት ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ መንግስት የዜጎችን የመኖር መብት እንዲያረጋግጥ ጠይቋል፡
+3
የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ በጠላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈፅሟል።
በአፋብኃ ምዕ.አ.ቀ.ቴ.ዕዝ የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ በጠላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈፅሞ ድል ተቀናጅቷል።
ጥቃቱ የተፈመው በትላንትናው እለት መንግስት ተብዮው የህዝብ ጠላት ከአዴትና ከሌላም ቦታ በመሰባሰብ የተለመደ ፕሮፖጋንዳውን ለመርጨት በሚዶልቱበት ወቅት ለዙሪያ ጥበቃ ባስቀመጧቸው ሆድ አደሮች ላይ ነው።
ጥቃቱ የተፈፀመው ጠላትን ከሁለት አቅጣጫ በመክበብ ሲሆን በዚህ ጥቃትም 5 የመከላከያ አባላት ሲሞቱ 3ቱ ቁስለኛ ሆነዋል።
በዚህ የተበሳጨው የአገዛዙ ሰራዊት በዙ-23 ደብረ -ፅላሎ ወደተባለ ቀበሌ አርሶ አደሮች ለስራ እንደተሰማሩ ፣ህፃናቱና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች በተበተኑበት ህዝቡን ለመምታት በታሰበ መልኩ ከርቀት ሲደበድብ ውሏል።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
የዮሐንስ አለማየሁ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ፋኖ በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት ከደላንታ ወደ ጋሼና ሲንቀሳቀስ በነበረ የአገዛዙ ሜካናይዝድ ኃይል ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተነገረ።
ድንገተኛ ጥቃቱን ተከትሎ አገዛዙ በዙ23ና በሌሎች የሜካናይዝ መሣሪያዎች ታግዞ ለ6:00 ሰዓታት የዘለቀ ማጥቃት ለማደግ ቢሞክርም ነገር ግን ተጨማሪ ወታደሮቹን ሙትና ቁስለኛ ከማስደረግ የዘለለ ውጤት ሳይገኝ ወደ ኋላ መፈርጠጡ ተገልጿ።
(ምስል ከማህደር)
+1
የብልፅግናው ቀኝ እጅ ጋማ ተደረገ❗️❗️❗️
ጋሻ ቸሬ የሚባል ሁለት አባ ዲቢሳ ተወላጅ የሆነ
የአጥቦ አይለብስ ሚኒሻ እና ለጡት ቆራጩ መረጃ እና ደንነት
1ኛ የባንዳ ይርጋ ብዙአለም
2ኛ የባንዳ ስማቸው ይዋን
3ኛ የባንዳ አሞኘ ዳኘ የሚባሉ ቀኝ እጅ መረጃቸው እና አረመኔውን አገዛዝ መንገድ እየመራ እና የፋኖ ቤተሰብ ነው እያለ ጥቆማ እየሰጠ ሲያሳስር፣ሲያስገድል፣ሲያዘርፍ የነበረ እደለመደው ለአጥቦ አይለብሴ እና ለጡት ቆራጭ መረጃ ሊሰጥ ሲብል በመልበስ ተመሳስሎ ሲክለፈለፍ በጀግናው አባ ኮስትር ብርጌድ ጠቅል ሻለቃ እጅ ከፍንጅ ጋማ አድርገዋለች።
ባንዳ መጨረሻው ውርደት ነው።
21/02/2018 ዓ ም
amare bamlaku
አባ ኮስትር ብርጌድ ህ/ግንኙነት
⛔የአማራ ፋኖ በተቆጣጠራቸው የተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የድሮን አሰሳ ስላለ ጥንቃቄ አይለየዎ!
የቤተአማራ ወሎ ትግል መርህን መሰረት ያደረገ አንድነት በማምጣት እነሆ 100% በምኒልክ ዕዝ ሥር ሆኗል። ዝርዝር መረጃው ነገ በመግለጫ ይቀርባል።
በልበ-ቀናዉ እና ትዕግስተኛዉ መሪያችን ዋርካዉ ምሬ ወዳጆ አማራዊ ጨዋነትና አስተዋይነት ያለምንም የግጭት ጠባሳ በአንድ መዋቅር ገብተናል። ወሎ ምድር ላይ ከእንግዲህ ሰርጎ ገብ እጆች ሁሉ ተቆርጠዋል።
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
አማራነት ይለምልም
#አማራ በራሱ ብር እራሱን ይገድላል!!
እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ በይፋ ከተጀመረ ድፍን ሁለት አመታትት አልፎ በጀግኖች ልጆቹ ታሪክ እየተፃፈ በየቀኑ ተገድሎ እየተደረገ ይገኛል:: ነገር ግን የእናት ጡት ነካሽ የሆኑት መዠገሮች ደግሞ በንፁሀኑ ማህበረሰብ ላይ አያሌ ግፎችን እየፈፀሙ ይገኛል :: አገዛዙ አንድም በድሮን ሁለትም ሁለትም በከባድ መሳሪያ(መድፍ ፣ታንክ፣ bm፣ ሞርተር እና ድሽቃ ) በመጠቀም በፋኖ በሚደርስበት ሽንፈት መወጣጫ (በቀል) ነፃ እርምጃ በመውረድ ርካሽ ተግባሩን እየፈፀመ ይገኛል። በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ ይህ ሁሉ ግፍ እና በደል የሚፀመው ደግሞ በእራሱ ገንዘብ(ብር) ከኪሱ በሚያወጣው (በሚከፍለው ) ክፍያ ነው።
#ይህን ተግባር በዋናነት የሚፈፅሙ አካላት ደግሞ የክልል የዞን እና የወረዳ አመራሮች እና የጡት ቆራጩ ስርዓትአስኀዓሚ ባንዳ ሆድ አደር ሚሊሻ አድማ ብተና እና ፖሊሶች ናቸው።
#ዛሬ በደረሰን መረጃ መሠረት ደግሞ
1, ሆድ አደር ባንዳ (የክብር ስም) ሰብስቤ ታደሰ የገቢዎች ሀላፊ
2.ሆድ አደር ባንዳ (የክብር ስም)ታምሩ ካሳሁን የመዘጋጃ ምክትል እና ሌሎችም #የዳንግላ ከተማን ማህበረሰብ የድሮን ተተኳሽ መግዣ፣ ልጆቻችሁን ለምንገድልበት ጥይት መግዣ፣ ልጆቻችሁን ለሚገድሉልን አድማ ብተና ሚሊሻ እና ፖሊስ አበል እና ደሞዝ የምንከፍለው ብር (#በአጠቃላይ_ያልሰራችሁበትን_ግብር) ክፈሉ በማለት የከተማውኝ ማህበረሰብ በማሰር ለታሰረበትም ክፍያ በመክፈል እና ማዋከብ እና ድብደባ በመፈፀም ላይ እንደሚገኙ የአሻራ ሚዲያ የውስጥ ምንጮች መረጃውን አድርሰውና።
#ይሰማል_የቢትወደድ-መንገሻ_ጀንበሬ_ልጆች
እኛም እንላለን እናንተ ሆድ አደር የጡት ቆራጩ አገዛዝ ደጋፊወች ይህ የህዝብ ማዕበል አንዴ ተነስቷል ብትችሉ ከህዝባችሁ ጎን ቁሙ ባትችሉ ደግሞ አፋችሁ ብትቀመጡ ጥሩ ነው
#
©አሻራ ሚዲየ
🔥#በተጠና_ልዩ_አፕሬሽን_5_መሳሪያ_ተማረከ‼️
አፋብኃ ቴወድሮስ እዝ ፩ኛ ክ/ጦር ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ የጀግኖች ሻምበል መማር ጌትነት ሻለቃ አባላት መራዊ ከተማ ላይ የተወሸቀውን ወንበር አስጠባቂ የሰራዊቱን እንቅስቃሴ ክትትል በማድረግ በተጠና መንገድ እርምጃ ወስደዋል።
በቀን 19 ለ20/02/2018 ዓ. ም እያንዳንድን እንቅስቃሴ በጥልቀት ክትትል ሲያደርጉ ከቆዩ በሗላ ባካሄዱት ድንገተኛ ኦፕሬሽን 5 ሙትእና ከ7 በላይ ከባድና ቀላል ቁስለኛ በማድረግ 5 የጦር መሳሪያ ምርኮ ማግኘት ተችሏል።
በተደጋጋሚ በከተማ ልዩ ኦፕሬሽን በመስራት የሚታወቁት ዛሬም በሚሊሻወች ላይ ባደረሱት ከፍተኛ ጉዳት በጠላት ሰፈር ፍርሃትና አለመረጋጋት የእርስ በእርስ አለመተማመን መፍጠራቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል።
ሌላኛው የአበራ ሙጨ ሻለቃ በደንገተኛ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ጠላትን አንጠባጥበውታል ከመራዊ ወደ አጣሪ ሬሽን በማድረስ ላይ የነበረውን የጠላት ሀይል በመምታት 2 ሙት 9 ቁስለኛ ማድረግ ችለዋል በደረሰባቸው ጉዳት ፋኖ እንዳለ ለምን አልነገራቹህንም በማለት በአካባቢው ካሉ ነዋሪወች 2 ንፁሀንን ከቤት አውጥተው ይዘዋቸው ሄደዋል።
©ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴድሮስ ዕዝ 1ኛ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት
20/ዐ2/2018 ዓ.ም
#ሠበር ዜና
#በርካታ የልዩ ኮማንዶ ሰልጣኞች ተመረቁ!!
ከስድስት ወራቶች በላይ የኮማንዶ ስልጠናን ሲዎስዱ የነበሩ የልዩ ኮማንዶ አባላቶች በዛሬው እለት በርካታ ህዝብ በተገካደመበት መድረክ ተመርቀዋል።
#አፋብሀ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ክፍለ ጦር ከስድስ ወራቶች በላይ ልዩ የኮማንዶ ስልጠና ሲሰጣቸው የቆዩ ልዩ ኮማንደዎችን ጥቅምት 20/2018 ዓም አስመርቋል። የተለያዩ ትርዒቶችን ያሳዩ በአማራ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን የዘር ጭፍጨፋ ተመራቂዎቹ በግጥም አዋዝተው ለተመልካች ህዝቦች ገልፀዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ልዩ ኮማንዶዎቹ በአማራ ህዝብ ፊት ቃለማህላ መሀላ ፈፅመዋል።ለአማራ ህዝብ የህልውና ዘቦች መሆናቸውን ጭምር ተመራቂዎች ገልፀዋል።
በምርቃት ፕሮግራም ላይ የፋኖ ከፍተኛ አመራሮች፤
የክብር እንግዶች፤
የአማራ ህዝቦች እና የትግሉ ደጋፊዎች የተገኙ ሲሆን ልዩ ኮማዶዎቹ ያሳዩት ትርዒት ህዝቦችን በደስታ እና ለካም እንችላለን በሚል ቁጭት አዘል ያስነባ ትርዒት ሆናል።
እውቀትንና ጥበብን በተካኑት አሰልጣኞች
#በመቶ አለቃ ሲሳይ መልካሙ
#በኮማንዶ ጋሻው ቢያርጎ
#በኮማንዶ ይልቃል አስማረ እና በርካታ የማሰልጠን ብቃት ያላቸው አሰልጣኞች ሙያቸውንና ጥበባቸውን ሙሉ ተጠቅመው ያሰለጠኗቸው የልዩ ኮማንዶ አባላቶች በስነ-ምግባርና በራዕይ ተገብተው የአማራን ህዝብ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ ሌት ተቀን የተጋረጠበትን የህልውና አዳጋ ለመመከት ብቁ የነፃነት ፍሬ እዳፈሩ ተደርገው ታንፀዋል።
ተመራቂ ልዩ ኮማንዶዎቹ በእሳት ላንቃ መሀል እንደ አቦሸማኔ እየተምወገዘጉ፤የእጅ ለእጅ የሳንጃ ግጥሚያን ፤የካታ አርትን ትርዒቶችን በማሳየት ከስድስት ወራቶች በላይ ዋጋ የከፈሉበትን ውጤታቸውን ለህዝባቸው ሲያሳዩ የአማራ ህዝብ ወደር አልባ ደስታ ከፊታቸው ሞልቶ ይታፈስ ነበር።
በዚህ የምርቃት ፕሮግራም ላይ አርበኛ ተመስገን አለባቸው፤ሻለቃ ሀብቴ እባቡ፤አርበኛ ጨለፍ ተስፋው እና በርካታ የፋኖ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው የምርቃት ስነ ስርዓቱን የከፈቱት ሲሆን፤ከፍተኛ አመራሮቹም "ከዚህም በላይ እናሰለጥናለን፤እንደራጃለን፤ጥላታችንን ደምስሰን የአማራን ህዝብ ነፃ እናዎጣለን። ለዚህ ደግሞ ሁሉም አቅሙ የሚፈቅድ አመራ ሁሉ መሰልጠን አለበት። እደ ህዝብ ሊያጠፋን የመጣን ወራሪ ሀይል እደ ህዝብ ልንመክተው ይገባናል።" ሲሉ ገልፀዋል።
የከባቢውን ወጣትና ህዝብ ሞራል የሚነሽጠው የልዩ ኮማንዶ የምርቃት ፕሮግራም ከምንጊዜውም በላይ አማራ የይቻላል የሞራል ተነሳሽነትን ያሳዩበት ንቅናቄም ነበር። ከምርቃት ፕሮግራሙ በኋላም የከባቢው ማህበረሰብ የልዩ ኮማንዶ ተመራቂዎችን በስስት አጅቦ ብሮ ወሸባዬ ያለበት አማራዊያን አውድ ሆኗል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ
የደጋው መብረቅ ክፍለጦር!!!
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
ፋኖ 💪💪💪💪 ክተት ✊
" አንድ እኩል ካልሆነ ያ'ንድ አገር ችሎቱ
ክንድ ላይ ብቻ ነው ያለ መድሀኒቱ
በሀገር ማንነትህ በእምነትህ ከመጣ
ፀበል ሁነው እና አጋንንቱ ይውጣ "
ወሎ ቤተ-አማራ ሚኒሊክ ዕዝ ✊
+2
ፋኖ 💪💪💪💪 ክተት ✊
" አንድ እኩል ካልሆነ ያ'ንድ አገር ችሎቱ
ክንድ ላይ ብቻ ነው ያለ መድሀኒቱ
በሀገር ማንነትህ በእምነትህ ከመጣ
ፀበል ሁነው እና አጋንንቱ ይውጣ "
ወሎ ቤተ-አማራ ሚኒሊክ ዕዝ ✊
