ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
4 413
Подписчики
+2224 часа
+437 дней
+1 38430 дней
Архив постов
👉የኃዘን ቀን ያስፈልገናል። በሁሉም ቦታ በተመሳሳይ ዕለት 👉ምህላ እያደረግነ፤እየጾምነ፣እየጸለይነ፤ 👉በቤታችን፤ 👉በቤተ ክርስቲያናችን፤ 👉በሰንበት ት/ቤታችን 👉በማኅበራዊ ሚድያ፤ 👉በቲክቶክ፣በዩቱብ.. ✍️የሀዘን ምልክት የሆኑ አልባሶቻችንን በመልበስ አንድነታችንን አጽንተን እያዘንን እርማችንን ማውጣት ይኖርብናል። ✍️ብሔራዊ የሐዘን ቀን ለማድረግ የሚድያ አካላት መረባረብ እና ለሁም ክርስቲያን የኃዘን መልእክት በማድረስ መረባረብ ይኖርብናል። ✍️መችም ሲኖዶሳችን ይሄንን ያደርግልናል ብለን ተስፋ ስለማናደርግ በዚህ መልኩ አንድነታችንን ብንገልጽ ጥሩ ይመስለኛል። ✍️ከምህላችን ጎን ለጎን እና በኋላ ዘላቂነት ያለው የመፍትሄ መንገድ ብናበጅለት። ✍️በዚያውም የእመቤታችንን ስደቷን እያሰብን  ከጥቅምት ፳፬(24) እስከ፳፯(27) ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቆይ ቢሆን። ✍️ኦርቶዶክሳውያን፦ 👉ቲክቶከሮች 👉ዩቱበሮች 👉ፌስቡከሮች 👉ቴሌግራሞች 👉ኢንስታግራሞች 👉ትዊተሮች 👉ሳተላይት ቴሌብዥኖች 👉ባጠቃላይ የሚኅበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች በሙሉ ባለን አቅም ሁሉ መጮህ ብንችል። 👉በዚህ ሰባት ዓመታት፦በዝቋላ፣በበደኖ፣በአርባጉጉ፣በአሩሲ፣በጅጅጋ፣..ወዘተ  በሰማዕትነት ያለፉን ፎቶ በመለጠፍ የሰማዕታቱ ግፍዕ በሁሉም ቤት እንዲታወቅ ማድረግ። 👉ለሁሉም ለምናውቃቸው ሁሉ እያዳረስነ።ለሀገር ወዳድ የእስልምና ተከታዮችም ጭምር ኃዘናችንን እያዳረስነ የሚቀጥል ቢሆን። 👉የተሻለ ሀሳብ ካለ እንመካከር። ✍️ካህናት፣መምህራን፣ሰንበት ት/ቤት፣ማኅበራት፣..ሁሉም በየዘርፉ ድርሻውን የሚወጣበት እንዲሆን አድርገን ብናዝን። ©መምህር ገብረ መድኅን እንየው

#የጠላት እንቅስቃሴ መረጃዎች 💪 በምድር ታንክ-በሰማይ ጄት ቢደባለቅ አንዴ ገጥመን መስሎኝ ወዴት ልንላቀቅ? የጠላት እንቅስፋኖዎች አሁን ከመሸ ታኮች ተጭነዉ ከአዲስ አበባ 20 ኪሎ ሜትር በኬ ላይ
#የጠላት እንቅስቃሴ መረጃዎች 💪 በምድር ታንክ-በሰማይ ጄት ቢደባለቅ አንዴ ገጥመን መስሎኝ ወዴት ልንላቀቅ? የጠላት እንቅስፋኖዎች  አሁን ከመሸ ታኮች  ተጭነዉ  ከአዲስ አበባ 20  ኪሎ ሜትር  በኬ ላይ  ሰፍሮ ይገኛል በመሆኑም አናብስቶች ጥንቃቄ እንድታደርጉ ስንል በትህትና እንጠይቃለን። 20/02/2017 ዓ.ም

#ሰበር ዜና!!! #አፋብሀ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ እዝ #አንሻ ክፍለ ጦር ከወቄጣ እስከ አቃት ዘርግቶ የመጣውን የፋሽስቱን ሰራዊት በአንሻ ክፍለ ጦር እዳልነበር ተደርጓል። ከጋሸና እና ከፍላቂት በሁለት አቅጣጫ የመጣውን የወራሪውን ሰራዊት ቅንድብ ቅንድቡን በማውለቅ ሙትና ቁስለኛ አድርጋዋለች። ቁስለኛውን በኦራል ሸራ አልብሶ ወደ ጋሸና ሲያግዝ መዋሉን የክፍለ ጦሯ ቃል አቀባይ ገልጿል። በርካታ ኪሳራን ያስተናገደው ጥላት ከአምስት(5) የነፍሰወከፍ መሳሪያ በላይ የተማረከ ሲሆ በቁጥር ያልተረጋገጠ ተተኳሽም ማርከዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ከአንሻ ሰይድ ክፍለጦር ቃል አቀባይ መኩሪያ አጋዠ(መምህሩ) ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

ዞብል አምባ ክፍለጦር 5ኛ ሻለቃ ከፋሽስቱ አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር ደላንታና ጋሼና መካከል ላይ ከባድ ትንቅንቅ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ:: ዞብል አምባ ክፍለጦር 5ኛ ሻለቃ ዛሬ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም ከደላንታ ወደ ጋሼና ሃይል ለመጨመርና ለማጠናከር ሲጓዝ የነበረውን የአገዛዙን ዙፍን ጠባቂ ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድባቅ የመታችው ሲሆን ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ በመካናይዝድ ጭምር በመታገዝ ከስድስት ሰዓት ያላነሰ ፊት ለፊት ከባድ ውጊያ ቢከፍትም ባግባቡ በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ አንገቱን በማስድፋት ድል ተቀዳጅተዋል:: ስለሆነም አገዛዙ በእግረኛ ሰራዊቱ ድሮውንም እምነት ስለሌለው የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ኢላማውን ህዝብ ወደሚበዛባቸው አካባቢዎች ያደረገ የመካናይዝድ መሳሪያ መድፍ ዙ23 እንዲሁም በ107 የታገዘ ድብደባ በማድረግ ሲዋጋ ቢውልም ዞብል አምባ 5ተኛ ሻለቃ በርካታ ሃይሉን በመምታት ወደ ነበረበት መልሳዋለች:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ሶስት (3)ቀናትን የወሰደ የአዉደ ዉጊያ ጥልቅ ዳሰሳ:- በእየጊዜዉ ሽንፈትን እየተከናነበ ያለዉ አረመኔዉ የአገዛዙ ስርዓት ከተለያዩ ቦታዎች በብዛት የሰበሰባቸዉን ወንበሩን ጠባቂ እረኛ ወታደሮች በመያዝ ወደ ጃዊ ወረዳ ማቡልክ ቀበሌ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ከባድ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናግዶ ወደ መጣበት ለመመለስ ቢሞክርም የበረሃ መብረቆቹ የጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ከበባ ዉስጥ በማስገባት እየቀጠቀጡት ይገኛሉ። ከ 16/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ 18/02/2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት በተደረገ ፍልሚያ በጃዊ መተከል ቀጠናዎች የተደረጉ ዉጊያዎች:- 1. በ 16/02/2018 ዓ.ም :- _ብሔራዊ ቀጠና ፍልዉሃ (አባሆይ ድንግራ)ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ በተደረገ ዉጊያ በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። _ጃዊ ፈንድቃ ከተማ ሞሰቢት ከተባለ የጠላት ካምፕ ላይ በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ማድረስ ተችሏል። _ወርቅ ሜዳ እና ደቅ ላይ በተደረገ ዉጊያ የጠላት ሃይልን ማሽመድመድ ተችሏል። 2.በ17/02/2018 ዓ.ም:- _ማቡልክ ቀጠና የጀግኖች አምባ ተራራ ላይ በተደረገ ከባድ ተጋድሎ አንድ ኦራል ሙሉ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። አንድ ኦራል መኪናም ከጥቅም ዉጭ ማድረግ ተችሏል። _በተመሳሳይ ወርቅ ሜዳ እና ደቅ ላይ የወገን ጦር በወሰደዉ የሰርጎ ገብ ድንገተኛ ጥቃት በጠላት ላይ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። 3.በ18/02/2018 ዓ.ም:- _ደረቅ ወንዝ ከተባለ ቦታ ላይ በተደረገ ትንቅንቅ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። እንደ እብድ ዉሻ እየተክለፈለፈ የገባዉ የጠላት ኃይል እንደ ቅጠል ረግፏል። _ይህንን የተከበበ የጠላት ኃይል ለማዉጣት ተጨማሪ ኃይል የተጨመረ ቢሆንም ቦታዉ ላይ ሳይደርስ በመንገድ ላይ ተቀጥቅጧል። _በተመሳሳይ ጃዊ ፈንድቃ ከተማ ሞሰቢት ከተባለ የጠላት ካምፕ ላይ በድጋሜ በተደረገ ድንገተኛ ጥቃት ጠላትን መግደል እና ማብረክረክ ተችሏል። _ወርቅ ሜዳ፣ ደቅ፣ መንደር 11፣ መንደር 12፣ መንደር 14፣ መንደር 26 ከተባሉ የፓዊ ወረዳ ቀበሌዎች ላይ በተደረጉ ድንገተኛ ተመሳሳይ የሰርጎ ገብ ጥቃት በጠላት ላይ ድል መቀዳጀት ተችሏል። በተለይ መንደር 11 ከተባለ ቦታ ላይ ሰባት(7) የሚሊሻ አባላት እስከ ትጥቃቸዉ ተማርከዋል። ዉጊያዉ ዛሬም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የጠለት ኃይል ለመዉጣት እየተፍጨረጨረ ይገኛል። "አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ"                   ፋኖ ያዕቆብ ጌታሁን የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ

የተቃውሞ ትችት ኃላፊነትን መወጣት እንጂ ባንዳነት አይሆንም! ( ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ) ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ በፓርላማ ያቀረብኳቸው ጥያቄዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ሕይወት የሚመለከቱ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው። እኔ እንደ ሕዝብ ተወካይና ተቃዋሚ ፖለቲከኛነቴ፣ የመንግሥትን ሥራ መተቸትና ለሕዝብ ጥቅም መቆም ስራየም፣ ግዴታዬም ጭምር ነው። የምመራባቸው ብቸኛ መርሆዎች የአማራ ሕዝብ ህልውናና የኢትዮጵያ ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅሞች ናቸው። ከዚህ በመነሳት ማክሰኞ ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረብኳቸው ጥያቄዎች ላይ የገዢው ፓርቲ የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት እና ወዶ ገብ መሸጦ "ተቃዋሚዎች" ላቀረቡት ሦስት ክሶች ግልጽ ምላሽ እሰጣለሁ። ይሄን የማደርገው የተነሱት ክሶች ክብደት ምላሽ የሚገባቸው በመሆናቸው ሳይሆን አጋጣሚውን በመጠቀም ባቀረብኋቸው በርካታ የፖሊሲና የትግበራ ጉዳዮች ላይ የበለጠ ግንዛቤ እንዲፈጠር ውይይት እንዲካሄድባቸው ምልከታዎቼን በተብራራ ሁኔታ ለማጋራት ነው። ክስ አንድ፦ የአስመራ መንግሥት ወኪል፣ አገልጋይና ባንዳ ነህ ይህ ክስ መሰረተ-ቢስ፣ ተራ ስም ማጥፋት ነው። የፖለቲካ ትችትን በባንዳነትና በክህደት ስም ለመምታት የሚደረግ አሳፋሪ ሙከራም ነው። የቤተሰቤ ታሪክ የጀግንነት ታሪክ፣ በላብና በጥረት ሰርቶ የማደር እንጂ በመሸጦነት እና በባንዳነት የማደር አንዳችም ነገር የለበትም። አባቴ ወታደር ጫኔ ዳኜው በዘውዳዊ ስርዓቱ፣ ወንድሜ መቶ አለቃ አያሌው ጫኔ (የሀረር ጦር ት/ቤት ምሩቅ እና የነብሮ ክፍለ ጦር መኮንን) በወታደራዊ ደርግ ዘመን፣ እንዲሁም ሌላው ወንድሜ ተስፋሚካኤል ጫኔ (የሁርሶ ወታደራዊ ት/ቤት አሠልጣኝ) በኢሕአዴግ ዘመን፣ ሶስቱም ኢትዮጵያን በከፍተኛ ጀግንነት እና ብቃት ያገለገሉ ወታደሮች ናቸው። ቅድመ አያቶቼም በሁለቱም በኩል እነ ቀኛዝማች ደስታ ብሩ እና ብላታ ጥሩነህ ኪዳኑ እንደአብዛኛው የጎጃም፣ አማራ ገበሬ አርበኞችም ነበሩ። ቤተሰቤ ለሀገር ሉዓላዊነትና አንድነት በደም ዋጋ የከፈለ ነው። ባንዳነት ከእኔም ሆነ ከቤተሰቤ ታሪክና እሴት ጋር ባዳ ነው። ስለዚህ ባንዳ ያላችሁኝ ተቺዎቼ ባንዳነት ይኖርባችሁ ከሆነ በዙሪያችሁ ፈልጉ፣ ከኛ ቤት ባንዳ የለም ነው መልሴ። ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረብሁት ጥያቄ ዓላማው አጣዳፊ የውስጥ ችግሮችን ከማስቀደም ይልቅ የባሕር በር አጀንዳን በማስቀደም በውጭ ጉዳይ ላይ ትኩረት ማድረጉ ስልታዊ ስህተት መሆኑን ለማሳየት ነው። ስለዚህም የሀገሪቱ የፖለቲካ ጉልበት በመጀመሪያ የውስጥ ሰላም ግንባታ ላይ እንዲውል አሳስቤያለሁ። ከዚህ በተረፈ እግዚአብሔር ይመስገንና በሙያዬ የትም ዓለም ሂጄ ሰርቼ ኑሮዬን ማሸነፍ የምችልበት የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ አለኝ። በፖሊሲ አውጪነት እና ከፍተኛ አመራርም በቂ ልምድ አለኝ። ስለዚህ ኑሮዬን ለመደጎም የየትኛውም አካል ቅጥረኛ የመሆን ግዴታ የለብኝም። ለጊዜው ግን እኔ የባሕር ዳር ሕዝብና የአማራ/የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካይ እንደራሴ ነኝ፤ የምወክለውም የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ብቻ ነው! ክስ ሁለት፦ ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘቷን ትቃወማለህ በፓርላማው ንግግሬ "ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር የሚደረግ ማንኛውንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን የምቀበለው ነኝ" ብዬ በግልጽ አመላክቻለሁ። የባሕር በር ማግኘት ብሔራዊ ጥቅም መሆኑን እንኳን እኔ 8ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ የአንድ መስሪያ ቤት ፖስተኛ እንኳን ይገነዘበዋል። ተቃውሞዬ ያለው የባሕር በርን በተመለከተ በጉዳዩ አያያዝ ዘዴ ላይ ነው። መንግስት የባሕር በርን እንደ "ህልውና ጥያቄ" በማቅረብ ሀገሪቱን ወደ ጦርነት አፋፍ እየመራ መሆኑን ተችቻለሁ። የእኔ አቋም የባሕር በር ጥያቄው በሰላማዊ፣ በሕጋዊና ሰጥቶ መቀበልን መሠረት ባደረገ አካሄድ ብቻ መፈታት አለበት የሚል ነው። ሀገራችን አሁን በውስጥ ጦርነት ተወጥራ ባለችበት ሁኔታ፤ የውስጥ ዘላቂ ሠላምን ማረጋገጥ ሲገባት በባሕር በር ስም ተጨማሪ የውጪ ጦርነት ውስጥ በመግባት በዚህ ጉዳይ ሌላ የዜጎች ደም እና ሕይዎት መክፈል የለባትም ነው። ጦርነትን የሚጋብዝ አካሄድ መቃወም የሀገር ፍቅር እንጂ ባንዳነት አይደለም። በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ሕወኃት/የትግራይ ኃይሎች በወገኖቼ ላይ ማይካድራን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የፈጸሙትን የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት እና ሁለንተናዊ የጦር ወንጀል በመቃወም አማራ ክልል ውስጥ የተደረገውን ራስን የመከላከል ጦርነት ደግፌያለሁ፣ ግን አልኩራራበትም (በአማራ ህዝብ ላይ የጦር ወንጀል የፈጸሙ የትግራይ ኃይሎች በፍትህ አደባባይ መቅረብ እንዳለባቸው በተደጋጋሚ እንደገለጽሁት ሁሉ፣ በትግራይ በንጹኃን ተጋሩዎች ላይ በተፈጸመው የጦር ወንጀል ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውም አካልም በተመሳሳይ በፍርድ አደባባይ እንዲዳኝ እፈልጋለሁ)። ስለዚህ ራስን የመከላከል የግዴታ ጦርነት ካልሆነ፣ አባቱ የጦርነት ሰለባ የሆነ ወታደር ልጅ እንደመሆኔ ጦርነትን በየትኛውም ምክንያት አልደግፍም። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ስላረበበው የጦርነት ስጋት ላቀረብሁት ጥያቄ በምላሻቸው የባህር በር ለማግኜት የግድ ጦርነት ውስጥ መግባት የለብንም የሚለውን ነገር አስረግጠው ተናግረዋል (ዛቻውን እንደ ባርጌይኒንግ ችፕና የዲፕሎማሲ ቀዳዳ መፍጠሪያ ጫና ማድረጊያ ታክቲክ አድርጌ ነው የተረዳሁት)። ክስ ሦስት፦ ሁልጊዜ ትችት ብቻ እንጂ አማራጭ ሀሳብ የለህም ይህ ሀሳብ አብዛኛውን ጊዜ የፖለቲካ ሀሁ ከማይረዱ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በተደጋጋሚ የሚነሳ ነው። አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ የሕዝብን ችግሮች እና እሮሮዎች እንዲሁም የመንግሥትን ክፍተት ማሳየት ዋናው ሥራው ቢሆንም፣ በጥያቄዎቼ እና በንግግሬ ግን ከመተቸት ያለፈ ግልጽ አማራጭ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን አቅርቤያለሁ። ሀ) የጸጥታ ጉዳይን የተመለከተው አማራጭ፦ ለአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከወታደራዊ አማራጭ ውጪ የተለየ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈለግ ጠይቄያለሁ። ከትግራይ ኃይሎች፣ ከፋኖ እና ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር መንግስት የገባበትን ሁኔታ በአርቆ አስተዋይነት በድርድር እንዲፈታ ግልጽ ጥሪ አቅርቤያለሁ። ለ) የኢኮኖሚ ጉዳይን የተመለከተው አማራጭ፦ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር መንግሥት አዲስና አስቸኳይ ዕቅድ እንዲያቀርብ እንዲሁም ወሳኝ ማኅበራዊ ወጪዎችን ሳይቀንስ የውጭ ዕዳውን ለመክፈል ሚዛናዊ የፊስካል ፖሊሲ እንዲከተል ግፊት አድርጌያለሁ። ሐ) የውጭ ግንኙነት ጉዳይን የተመለከተው አማራጭ፦ የመንግሥት ከፍተኛ የፖለቲካ አቅም የውስጥ የፖለቲካ ግጭቶችን ለመፍታትና ከዜጎች ጋር ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር እንዲውል በግልጽ ጠቁሜያለሁ። የኢህአዴግ የውጪ ፖሊሲ ጠንካራ ጎን የነበረው መርሆ "የውስጥ ሰላም የውጭ ስኬት መሰረት ነው!" የሚለውን እኔም የምገዛው የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ መርህ ነው። እንደ ማጠቃለያ፦ በገዢው ፓርቲ ላይ በማንኛውም ጊዜ የማቀርበው ትችቴ ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም ቆሜ የምጠይቀው ሕጋዊ የፖለቲካ ትችት እንጂ በቅጥረኝነት የመጣ አይደለም። የገዢው ፓርቲ ኃላፊነት የፖለቲካ ትችትን በአላዋቂዎች የብሔራዊ ክህደት ክስ ለማኮላሸት ከመሞከር ይልቅ ለቀረቡት ወሳኝ ጥያቄዎች አሳማኝና ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ነው። የእኔ የፖለቲካ ሥራ ትኩረት ደግሞ በተረዳሁት ልክ የሕዝቤን ህልውና እና የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ማስከበር ነው! (ፎቶ፦ የተቃዋሚ የፓርላማ አባላት የሆኑ ወዳጆቼ አቶ ባርጠማ እና አቶ ብርሐኑ ጋር ፤ በምክር ቤቱ ጥያቄ ባቀረብሁበት ወቅት የተወሰደ።)

ይኽ ሕፃን ተአምራት አውግቸው ይባላል። ገና የ ፪ ዓመት ሕፃን ሲኾን ከናኖ ጃዊው የአሩሲ ፍጅት በእግዚአብሔር ተአምር ተርፏል ። እናቱ ወ/ሮ ስምረት ሸዋንግዛው በሰማዕትነት ስታርፍ እርሱ በጀርባዋ
+1
ይኽ ሕፃን ተአምራት አውግቸው ይባላል። ገና የ ፪ ዓመት ሕፃን ሲኾን ከናኖ ጃዊው የአሩሲ ፍጅት በእግዚአብሔር ተአምር ተርፏል ። እናቱ ወ/ሮ ስምረት ሸዋንግዛው በሰማዕትነት ስታርፍ እርሱ በጀርባዋ ታዝሎ ነበር። ሰዎች ሲደርሱ ከእናቱ አስከሬን ላይ ተጣብቆ ተገኝቷል። አባቱም ተሰውቷል። እግሩ ላይ የደረሰበት አደጋ ከመክበዱ የተነሣ ይቆረጥ አይቆረጥ የሚለው የሐኪሞች ውሣኔ እየተጠበቀ ነው። ከኃይለ ማርያም ማሞ ሆስፒታል ወደ ወላይታ ክርስቲያን ሆስፒታል ሪፈር ተደርጓል ። ኹለቱ ከፍጅቱ የተረፉት ሕፃናት ያለ ወላጅ ቀርተዋል። ሕፃን ስንታየሁ ሸዋንግዛው በኃይለ ማርያም ማሞ ሆስፒታል ሕክምናዋን እየተከታተለች ትገኛለች ።

ህዝባዊ አደረጃጅቱ እንደቀጠለ ነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ከትግሉ ጎን ለጎን የህዝብን አደረጃጀት እየሰራ
+7
ህዝባዊ አደረጃጅቱ እንደቀጠለ ነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ከትግሉ ጎን ለጎን የህዝብን አደረጃጀት እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም ክፍለ ጦሩ በሚያስተዳድራቸው ቀበሌውች የህዝብን አደረጃጀት የአማራ ፋኖ እስትራቴጂካዊ ስራቱን በሚመጥን መልክ በኤፍርታ ግድም ወረዳ በየሰርዶ ቀበሌ ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በመውጣት አደረጃጃት ተፈጥሯል። በመድረኩም አሁን የፋኖ ቁመና ምን ይመስላል በሚል ከደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩና እና የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር አመራሮች ግንዛቤ የተሰጠ ከመሆኑም በላይ ማህበረሰቡ ፋኖ በሚያስተዳድረው ቀጠና በሰላም እየወጣ በመግባት ላይ ሲገኝ ጠላት መከላከያ በሚገኝበት ቀጠና ደግሞ አሁን የገበሬው የሰብል ወቅት ከመሆኑም በላይ ሰብላቸውን ለመሰብሰብ እንደተቸገሩም ከማህበረሰቡ መሰረታዊ ጥያቄውችም ተሰንዝረዋል። ህዝቡም እኛ ፋኖ ነን ከልጆቻችን ጋር አብርን እንሞታለን አማራ ነፃ ሲወጣ ነው አገር ሰላም የምትሆነው ስለዚህ እንዲያውም እኛንም አደራጁን አብርን እንዋጋለን በማለት ህዝባዊ ውይይቶች በሰላም ተጠናቀዋል። መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ‎      ጥቅምት 20/ዐ2/2018 ዓ.ም

ህዝባዊ አደረጃጅቱ እንደቀጠለ ነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ከትግሉ ጎን ለጎን የህዝብን አደረጃጀት እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም ክፍለ ጦሩ በሚያስተዳድራቸው ቀበሌውች የህዝብን አደረጃጀት የአማራ ፋኖ እስትራቴጂካዊ ስራቱን በሚመጥን መልክ በኤፍርታ ግድም ወረዳ በየሰርዶ ቀበሌ ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ በመውጣት አደረጃጃት ተፈጥሯል። በመድረኩም አሁን የፋኖ ቁመና ምን ይመስላል በሚል ከደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩና እና የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር አመራሮች ግንዛቤ የተሰጠ ከመሆኑም በላይ ማህበረሰቡ ፋኖ በሚያስተዳድረው ቀጠና በሰላም እየወጣ በመግባት ላይ ሲገኝ ጠላት መከላከያ በሚገኝበት ቀጠና ደግሞ አሁን የገበሬው የሰብል ወቅት ከመሆኑም በላይ ሰብላቸውን ለመሰብሰብ እንደተቸገሩም ከማህበረሰቡ መሰረታዊ ጥያቄውችም ተሰንዝረዋል። ህዝቡም እኛ ፋኖ ነን ከልጆቻችን ጋር አብርን እንሞታለን አማራ ነፃ ሲወጣ ነው አገር ሰላም የምትሆነው ስለዚህ እንዲያውም እኛንም አደራጁን አብርን እንዋጋለን በማለት ህዝባዊ ውይይቶች በሰላም ተጠናቀዋል። መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ‎አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ‎ ጥቅምት 20/ዐ2/2018 ዓ.ም

🔥የአገዛዙ ሥርዓት በግልፅ መሸነፉን የሚፈፅማቸዉ ድርጊቶች  ተናገሩ  " "‼️ (  ወምበርማ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት መመሪያ ጥቅምት 20 /2018 ዓ.ም ) ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 5ኛ ክ/ጦር ወምበርማ ብርጌድ  ሽንዲ ከተማ የመሸገዉን የአገዛዙ  አገልጋዮች  በሽንዲ ከተማ የሚኖሩ የፋኖ ቤተሰቦችን እያሰሩ እና እያገላቱ ፣ እያገቱ ፣ አስረዉም ለእስረኞች ምግብናም እንዳይገባ ከልክለዋል ። የሚፈፅሙት ተግባር በህዝባችን ላይ ከባድ እንቅስቃሴ ነዉ  ከዚህ ተግባር የማይይታረሙ ከሆነ እርምጃችን ከባድ ነዉ ብለዋል የወምበርማ ብርጌድ አመራሮች ። በተጨማሪም ጥቅምት 18/02/2018 ዓ.ም ለሽንዲ ከተማ በቅርብ በሚገኝ ባይታ ልዬ ቦታ ደንቦዝን ጫካ ላይ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብሶችን እያስቆሙ ዝርፊያ ፈፅመዋል ። በዚህ ተግባራቸዉ የተበሳጩት የህዝብ  ልጆች የቡሬ ዳሞት ፋኖዎች  ከኬላ ስራቸዉ መጠዉ ተኩስ በመክፈት አንድ ተለላኪ ወደላይኛዉ ተሸኝቷል ዘረፋቸዉንም አቁመዉ ወደ ምሽጋቸዉ  ሽንዲ ከተማ ፈረጠጡ ። ዛሬም ይህ ተግባራቸዉ አልበቃ ብሎ ንፁሐንን ከስራ ቦታቸዉ በማዉጣት አቶ አሊ አስራት የተባለን የወቦ ለገሠማ ቀበሌ ኗሪ የግፍ ግፍ አገዳድል ገድለዋል ሀይማኖት መላኩ የተባለ በሹፍርና ኑሮዉን እየመራ የሚተዳድርን ንፁሐን ያለምንም ምክንያት አገዛዙ ባደረሰበት ከባድ ድብደባ እና ምት ህክምና ላይ ይገኛል ። እንዲሁም አቶ ደሳለዉ ሞሴ የዴንድ ቀበሌ ኑሪ ሴት ልጁን እየተጋገዙ የሥርዓቱ አገልጋዮች አሰቃቂ ድርጊት ፈፅመዉባታል።

ዞብል አምባ ክፍለጦር 5ኛ ሻለቃ ከፋሽስቱ አገዛዝ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ጋር ደላንታና ጋሼና መካከል ላይ ከባድ ትንቅንቅ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ:: ዞብል አምባ ክፍለጦር 5ኛ ሻለቃ ዛሬ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም ከደላንታ ወደ ጋሼና ሃይል ለመጨመርና ለማጠናከር ሲጓዝ የነበረውን የአገዛዙን ዙፍን ጠባቂ ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድባቅ የመታችው ሲሆን ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ በመካናይዝድ ጭምር በመታገዝ ከስድስት ሰዓት ያላነሰ ፊት ለፊት ከባድ ውጊያ ቢከፍትም ባግባቡ በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ አንገቱን በማስድፋት ድል ተቀዳጅተዋል:: ስለሆነም አገዛዙ በእግረኛ ሰራዊቱ ድሮውንም እምነት ስለሌለው የምርኮኛው ብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ኢላማውን ህዝብ ወደሚበዛባቸው አካባቢዎች ያደረገ የመካናይዝድ መሳሪያ መድፍ ዙ23 እንዲሁም በ107 የታገዘ ድብደባ በማድረግ ሲዋጋ ቢውልም ዞብል አምባ 5ተኛ ሻለቃ በርካታ ሃይሉን በመምታት ወደ ነበረበት መልሳዋለች:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

‎የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን የትምህርት ተቋማትን መሰረት ያደረገ የሞርተር ጥቃት ፈፀመ! ‎የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን የፋኖ ኃይች በሌሉበት በአሳግርት ወረዳ የትምህርት ተቋማትን መሰረት ያደረገ የሞርተር ጥቃት በመፈፀም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዲስተጓጎሉ አድርጓል:: ‎ ይህ የጥፋት ቡድን ጥቅምት 19/2018 ዓ ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ በአሳግርት ወረዳ ታሞ ቀበሌ ከፈፀማቸው ስድስት የሞርተር ጥቃቶች መካከል ሁለቱ በታሞ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ÷ አራቱ በመሀል ታሞ ከተማ ላይ ወድቋል:: ‎ ‎ በዚህም የሞርተር ጥቃት የተደናገጡ ተማሪዎችና መምህራት የትምህርት ገበታቸውን በማቋረጥ ተበትነዋል:: ‎ ‎የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን በዘፈቀደ በጣለው በዚህ የሞርተር ጥቃት አንድ አርሶ አደር ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ሲደርስ አንድ የቤት እንሰሳት ደግሞ ተገድሏል::      መረጃውን ያደረሰን  አርበኛ ቦጋለ ምንዳ የቡልጋ ክ/ጦር ሪፖርተር ነው።      ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ‎የአፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዜና ክፍል    ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም

"የህዝብ የንቅናቄ መድረኮች ተጠናክረው እንደቀጠሉ ነው" የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የስናን አባጂሜ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸ
+2
"የህዝብ የንቅናቄ መድረኮች ተጠናክረው እንደቀጠሉ ነው"         የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር የስናን አባጂሜ ብርጌድ በሚያስተዳድራቸው ቀበሌዎች ተከታታይነት ያለው ህዝባዊ ውይይት እያደረገ ይገኛል። በጥቅምት 19/2018 ዓ.ም ከጉድያሜ ቀበሌ ጋር ህዝባዊ ውይይት ተደርጓል። በዚህ ህዝባዊ ውይይትም ➟አሁናዊ የፋኖ የትግል ሁኔታ በተመለከተ   ➟የማህበረሰቡን የችግር አፈታት በተመለከተ ➟የፋኖና የማህበረሰቡን ግንኙነት በተመለከተ ውይይት የተደረገ ሲሆን የቀበሌ መዋቅሩንም በመፈተሽ የአመራር ሪፎርም ተሰርቷል።    ማሕበረሰቡም ለፋኖ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም  ድል ለአማራ ፋኖ! "አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ"

ሰበር ዜና! አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ጠንካራ አውደ ውጊያ በምእራብ ጎንደር ቋራ ወረዳና በማእከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ 3ኛ ቀኑን የያዘው ትንቅንቅ የበዛበት አውደ ውጊያ አሁንም በድል አንደቀጠለ ይገኛል። የአገዛዙ ጥምር ግብስብስ አራጅ ቡድን በልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ከተወሸቀበት 3 ከተሞች ደለጎ፣ሻሁራና አፀደማርያም ከጥቅምት 17/2018 ማታ ጀምሮ ስቦ ወደ ሞት ቀጠና በማስገባት እስከ አሁኗ ስአት ድረስ ከፍተኛ በትር እያረፈበት ይገኛል። በቋራ ወረዳ ደለጎ ከተማ ያለው ፣ በአማራ ደም የሰከረው አራጅ ቡድን በተለያየ አቅጣጫ ከሽንፈት የማያድነውን የሀይል ጭማሬ እያደረገ የድረሱልኝ ጩኸት ላይ ቢሆንም፣በሰማይ በድሮን እገዛ ቢደረግለትም፣ ክንደ ብርቱ የመይሳው ካሳ ልጆችን ቋራ ኦሜድላ ክ/ጦ እና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የፋኖ ሰራዊት በሚያደርጉት ጥምረታዊ ውጊያ ከፍተኛ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ እየተደረገ የጠላት ሀይል ክፉኛ ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ይገኛል። በተመሳሳይ ከሻሁራና ከአፀደማርያም ከተማ ተሰቦ ወደ መግደያ ቀጠና የገባው ይህኑ ግብስብስ በአማራ የግፍ ደም የጨቀየው ዙፋን አስጠባቂ አራጅ ቡድን ያለየሌለ ሀይሉንና የድሮን እገዛዎችን ጨምሮ ወደ ነበረበት ከተማ ተመልሶ ለመግባት ጥረት ቢያደርግም በነበልባሎቹ የአድዋ ክ/ጦር ልዩ ወታደራዊ ጥበብ ከፍተኛ ሽንፈትን እያስተናገደ መውጫ መግቢያ አጥቶ ይገኛል። ሁሉም የአውደ ውጊያ ግንባሮች ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ስአት እንደ ቀጠለ ይገኛል። አህዛዊ የድል ዜናዎችን አውደ ውጊያ እንደተጠናቀቀ የምናቀርብ ይሆናል።                 ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ህ/ግ ፋኖ መ/ር አስታውል አምሳሉ

"መሪጌታ በላይ አዳሙ ተደብድበዋል ፤  ቄስ በላይ መኮንን ከተከበሩ መሪጌታ በላይ አዳሙ የማይከበሩበት ምክንያቱ ምንድን ነው?"        (የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው) የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጥቅምት 18/2018 በነበረው ችሎት በቂሊንጦ ማ/ቤት እና በተለይም በተቋሙ ጥበቃ እና ደህንነት ኃላፊ በኢ/ር ድሪባ ሰንበታ ላይ ካቀረቡት ክስ መካከል በከፊል ፦   የወገብ እና የእግር በሽተኛ ነኝ ፤ ፍ/ቤቱ ፈቅዶልኝ በዋና በር እየገቡ ቤተሰቦቼን አገኝ ነበር ፤ ኢ/ር ድሪባ ሰንበታ ከመጡ በኋላ ነው የተከለከልኩት። እኔ ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቤ ጭምር ተሰድቦ እንኳ ችግሩን በሰላም ተነጋግረን እንድንፈታ ነበር ጥረትና ፍላጎቴ ይሁን እንጅ ሊታረሙ ስላልቻሉ ነው ክሱን ወደ ፍ/ቤት ለማምጣት የተገደድኩት። በእስር ቆይታዬ በበደረሰብኝ እንግልት ቆሜ ማናገር አልችልም ፤ አሁንም ቁጭ ብዬ ቤተሰቦቼን እንዳነጋግር ይፈቀድልኝ። "ቅዘናም አማራ " ብለው ተሳድበዋል ፤ ዳኝነት ካለ ይማሩ ብለን ነው ያመጣናቸው ፤ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩን በምርመራ እንዲያጣራው ትዕዛዝ ይሰጥልን። ከላይ እስከ ታች እኛው ነን ምንም አታመጡም ብለውናል። መሪጌታ በላይ አዳሙ ተደብድበዋል ፤  ቄስ በላይ መኮንን ከተከበሩ መሪጌታ በላይ አዳሙ የማይከበሩበት ምክንያቱ ምንድን ነው? በብሔራችን ተሰድበናል ፤ ተዋርደናል ፤ በእኛ ምክንያት ሕዝባችን ሊሰደብና ሊዋረድ አይገባም። በፍተሻ ወቅት ባልታጠበ እጃቸው ነው እንጀራውን የሚነኩት ፤ ዞን 4 እና ዞን 5 ላይ የተለዬ ጫና እያደረጉብን ነው። በእኛ ስም የተያዘ ሕገ ወጥ ነገር የለም ፤ አለ ካሉ ተጨማሪ ክስ አድርገው ያምጡ በማለት ተናግረዋል።   በመሀል ችሎቱ እንዳይናገሩ ሲከለክላቸው ፦ ተዉ ይህ ጊዜ ያልፋል ፤ እኔ ብሞት መልሱ ለትውልድ ነው፤ እኛ ያልነውን ብቻ ሰምታችሁ ፍረዱ አላልኩም ፤ ግን ከዚህ በላይ ምን እንሆናለን? ቅዘናም አማራ እየተባልን ነው። በእርግጥ ይህ ችሎት ስዩም ተሾመን በጓዳ አነጋግሮ የመለሰ ነው ፤ በደል እየተፈፀመብን ነው ፤ አድሎ አለ። ካጠፋሁ ይቅርታ የሚያናግረኝ ግን ግፉ ነው ፤ በእኔ ብቻ ሳይሆን በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እና በደል ፣ ስቃዩ ነው የሚያናግረኝ። (አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 19/2018)

መፍትሔው፣ ከጥቂት ዓመታት በፊት በወለጋ አማሮች በዋናነት በወሎ ሙስሊሞች ላይ ሲደርስ የነበረውን የዘር ማጽዳት የቆመበትን ተሞክሮ መውሰድና በአርሲ አካባቢ ያሉ ኦርቶዶክሳውያንና አማሮች ከሚቀርባቸው የአማራ ክልል የፋኖ አደረጃጀት ጋር ተቀናጅተው ራሳቸውን መከላከል አለባቸው፡፡ በአርሲ ሀገረ ስበከት ያለውን ግድያ የፈለግነውን ያህል ብንጮህም መንግሥትም ምላሽ አይሰጥበትም፣ ቤተ ክህነትም ጫና አድርጎ እስከ መጨረሻ የሚፈታበትን መፍትሔ ሊያመጣ አይችልም፡፡ በአጭሩ አሁን ያለው ሥርዓት የወሮበሎች ስብስብ ስለሆነ ሰላማዊ የሚባል ትግል አይገባውም ተብሏል፡፡ የመጨረሻ አማራጭ አድርገን ከልምድ እንዳየነው ይኸንን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ሊያስቆመው የሚችለውን መንገድ ብቻ ነው መጠቀም ያለብን ተብሏል፡፡ መፍትሔው፣ ከጥቂት ዓመታት በፊት በወለጋ አማሮች በዋናነት በወሎ ሙስሊሞች ላይ ሲደርስ የነበረውን የዘር ማጽዳት የቆመበትን ተሞክሮ መውሰድና በአርሲ አካባቢ ያሉ ኦርቶዶክሳውያንና አማሮች ከሚቀርባቸው የአማራ ክልል የፋኖ አደረጃጀት ጋር ተቀናጅተው ራሳቸውን መከላከል አለባቸው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዐመታት ብቻ ቤተሰቦቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው የተጨፈጨፉባቸው ወጣቶች ቢሰባሰቡ ከኮር በላይ ኃይል መመሥረት ይችላሉ፡፡ የዚህን ያህል ነው አካባቢውን እያጸዱት ያለውም ተብሏል፡፡ እነዚህ ነዋሪዎች ዱር ቤቴ ብለው ቢወጡ አሁን በመንግሥትና ታጣቂ ተብየው ሁሉ ከሚገደሉት በላይ አይገደሉም፡፡ ዛሬ ላይ የቢዛሞ ዕዝ የሚባለው የፋኖ አደረጃጀት ወለጋ ውስጥ የነበረውን በሼኔ ሲሳበብ የነበረውን ግድያ ቀጥ አድርጎ አስቁሞታል፡፡ አርሲ ደግሞ ለሰሜን ሸዋ በጣም ቅርብ የሆነ ቦታ ነው፣ በሸንኮራ፣ በአረርቲ ወዘተ ከሚቀርቡት የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር መጣመር ይችላሉ፡፡ ኦርቶዶክሳውያንም ሆኑ አማራዎች ቀላል የማይባል ቁጥር ያለባቸው አካባቢ ነው፡፡ ምርጫው ተደራጅቶና ታጥቆ ራስን ማዳን ነው፡፡ ለዚህ ጋጠ ወጥና ገዳይ ሥርዓት ያለው ብቸኛ ቋንቋ በሚገባውና በጉልበት ብቻ ማናገር ነው፡፡ እዚህ ላይ ነው መሠራት ያለበት፡፡ ተደራጅቶ ራስን መከላከል፣ ሊገድል የመጣን በመጣበት አግባብ መመለስ ነው። የተደረጉትን ጭፍጨፋዎች እንደማሳያ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች፣ በጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም ብቻ የ2 ዓመት ሕፃንና የ75 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 25 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች "ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች" መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በይፋ አረጋግጧል። የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቭዥንም በተከታታይ ሽፋን ሲሰጥ ነበር። የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ታምራት ወልዴ ለቤተ ክርስቲያኗ መገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት፣ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ከተለያዩ ወረዳዎች የደረሱትን ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ፣ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ዝርዝር መረጃውን ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በደብዳቤ ልኳል። ሪፖርቱ እንደሚያሳየው፣ በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚደርሰው ጥቃትና የንብረት ውድመት ለዓመታት የቆየ ችግር ቢሆንም፣ በጥቅምት ወር የተፈጸመው ግድያ መጠኑ ከፍተኛና ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ተብለው በሚታሰቡ አካባቢዎች ላይ መሆኑ ሁኔታውን እጅግ አሳሳቢ እንዳደረገው ተገልጿል። በሀገረ ስብከቱ ሪፖርት መሠረት በጥቅምት ወር የተፈጸሙት ዋና ዋና ጥቃቶችም፦ በጉና እና መርቲ ወረዳዎች ድንበር፡ ጥቅምት 14 ለ15 አጥቢያ ሌሊት 17 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል። የ12ቱ የቀብር ሥነ ሥርዓት በመርቲ ወረዳ፣ የቀሪዎቹ 5 ደግሞ በጉና ወረዳ ተፈጽሟል። በሽርካ ወረዳ፡ በሄላ ዘንባባ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን አጥቢያ፣ ጥቅምት 17 ለ18 አጥቢያ ሌሊት 3 ሰዎች ቤታቸው ውስጥ እንደተኙ ተገድለዋል። በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፡ ጥቅምት 18 ለ19 አጥቢያ ሌሊት 5 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል። በድምሩ በወሩ ውስጥ የተገደሉት 25 ንጹሐን ዜጎች ናቸው። ሀገረ ስብከቱ ያወጣው መግለጫ፣ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች መንግሥት አስፈላጊውን የጸጥታ ጥበቃ እንዲያደርግ ሲጠይቅ መቆየቱን አስታውሷል። አሁን የተፈጸመው ጥቃት ቀደም ሲል ሰላማዊ በነበሩ አካባቢዎች ላይ መሆኑ፣ የችግሩን ስር መስደድና አሳሳቢነት እንደሚያሳይ ገልጿል። በመሆኑም፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጉዳዩን በከፍተኛ የመንግሥት አካላት ደረጃ በማቅረብ ዘላቂ መፍትሔ እንዲገኝ እንዲሰራ ሀገረ ስብከቱ ጥሪውን አቅርቧል።

ዛሬ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም ከጨዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ የብልጽግና አራጅ ሰራዊት ከጓህላ በቅርብ ርቀት ላይ ከምትገኘው ሊሊ ከተባለችው አካባቢ ላይ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር ንስር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር ተክለ ሃይማኖት ብርጌድ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ለማድረስ የተንቀሳቀሰውን የጠላት ኃይል በደፈጣ መምታት ችለዋል።     ጠላት መንቀሳቀሱን መረጃ የደረሳቸው ንስሮቹ ገዥ መሬቶችን በመያዝ በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስደውበታል። በጥቃቱ የተደናገጠው ጠላት አግር አውጭኝ በመፈርጠጥ ወደ ምስራቃዊቷ ጓህላ ከተማ በመጣበት እግሩ እየተራወጠ ሊመለስ ችሏል። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ ጥቅምት 20/2018ዓ.ም