ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше2 951
Подписчики
+1424 часа
+247 дней
+38330 дней
Архив постов
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከሠም ፪ኛ ኮር ሀይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር በሀገረማርያም ቀጠና በአገዛዙ የሚሊሻ ና የፖሊሥ ኃይል ላይ ድል ተቀዳጀ።
ሰኔ 06/2018ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ
ከሰም ፪ኛ ኮር የኃይለ ማርያም ማሞ ክፍለጦር ሻለቃ አንድ እና የክፍለ ጦር ቃኚና መሃንዲሥ ሻለቆች በጥምረት በሀገረ ማርያም ወረዳ ንፋሥ አምባ ቀበሌ ልዩ ቦታው አሌሊቱ ድልድይ ተበሎ ከሚጠራው ሥፍራ ላይ በአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ የፋኖ ሰራዊት ደፈጣ በማድረግ በጠላት ላይ አካላዊና ቁሳዊ ኪሳራ አደረሰ።
ጠላት ሁል ጊዜ እንደለመደው የጥፋት ተልኮውን ለመፈፀም ወደ ንፋስ አምባና ሰኮሩ ቀበሌ መንቀሳቀሱን የደረሳቸው የኃይለ ማርያም ማሞ የምድር ተምዘግዛጊ ጦር የተንቀዠቀዠውን ጠላት ወደ መውደቂያው ጠብቆ በማሥገባት ድንገት ባላሰበው መልኩ መብረቃዊ ጥቃት ሲሰነዘርበት አንድ(1) የሚሊሻ አባል ሲደመሰስ፡ ቀሪ ሁለት ሚሊሻ አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በተጨማሪ አንድ (1) የፖሊሥ አባል ሥሙ ሳሳሁ የሚባል ከጉልበቱ በታች በነበልባሎቹ ተመቶ ቁስለኛ መሆኑ ታውቋል።
ይህ ዘገባ እስከተጠናቀቀበት ሰዓት ድረስ አውደ ውጊያው እንደቀጠለ ይገኛል። ጠላትም የፋኖ የሀይል ሚዛን ከአቅሙ በላይ በመሆኑ እያፈገፈገና ወደ ኋላ በመመለሥ ላይ ይገኛል።
" ክብር ለትግሉ ሠማዕታት"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን "
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
በ2እጅ እነሴ ወረዳ ጥሩሰላም ቀበሌ (አራጢ) ላይ በወቅታዊ ጉዳዮች ከህዝቡ ጋር የክ/ጦር አመራሮች በመገኘት ውይይት ተካሄደ።
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
ሰኔ05/2018ዓ.ም
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር በ2እጁ እነሴ ወረዳ ጥሩሰላም ቀበሌ {አራጢ} በጀግኖች የትውልድ ቀዬ የአመራር ውይይት አካሔደ።
የአብይ አህመድ ሰራዊት አራጢን ሲያስብ እንቅልፍ አይተኛም፤ጉልበቱ ይርዳል።
ቀጠናው በአማራ የትግል አብዮት ውስጥ ታሪክ ከሚዘክራቸው የእኔ ተፈራ ደምጤ(ተፌ) እና ሌሎች የትውልድ ቀዬ ነው።
ከ2ኛ ተፈራ ዳምጤ እስከ 54ኛ ክ/ጦር የቀጠለው የቀጠናውን ጀብደኝነት በወትሮው ግለት ማስቀጠል ብሎም ማሻሻል ላይ ከጥሩ ሰላም ቀበሌ ተዋጊ ኃይል ጋር የጋራ ውይይት ተደርጓል።
በቀጠናው የቀበሌ መዋቅርና ህዝባዊ አስተዳደርን ጨምሮ የተገመገመና የወደፊት አቅጣጫ የተቀመጠበት መድረክም ሲሆን
በውይይቱ የህዝባችንን የትግል አረዳድና ቁርጠኝነት የተረዳንበት መድረክ ነበር።
እናደራጃለን ! እንመክራለን! እንፈፅማለን!!
አዲስ ትውለድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
የድል ዜና ከወደ ደራ
ሰኔ 06/2018 ዓ.ም
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ኛ ኮር በፍቃዱ በላይ ክፍለ ጦር የበረሀው ጀግኖች ትናንት ከማለዳ አንድ(1:00) ሰዓት ከ30 ደቂቃ ጀምረው እስከ ምሽቱ አንድ(1:00) ሰዓት ድረስ በተደረገ እልሕ አስጨራሽ ውጊያ በሰረርኩላ እና በቱቲ ከተሞች መሽጎ በነበረው የአገዛዙ ኃይል ላይ እንደ እሳት እያቃጠሉ ጠንካራ ምት አድርገውበታል። ሆኖም የሥርዓቱ ጅምላ ተጋላቢ ኃይል በመሬት ላይ ሊቀበለው የሚገባውን ታሪካዊ ቅጣት ከጀግኖቹ ክንድ ተመግቧል።
የበረሀው ትንታግ በፍቃዱ በላይ ክፍለጦር አንዲት እሳት የለበሰች ሻለቃ ወደ ሰረርኩላ ከተማ በረገጠችበት ቅጽበት በአገዛዙ ጥርቅም ኃይል ላይ የወሰደችው ፈጣንና መብረቃዊ የማጥቃት ስልት ጠላትን ሙሉ በሙሉ ግራ አጋብቶታል። ከዚሕም የተነሳ ጭንቅ ውስጥ የገባውና መውጫ ያጣው የአገዛዙ ኃይል ጫካ ውስጥ ያደራጀውን ዘራፊውን የ"ሸኔ" ስብስብ ለአጋዥነትና ለሕይወት ማዳኛ የጋበዘ ሲሆን የአናብስቶቹ ክንድ የማይነካ በመሆኑ ነገሩ እዳሠበው ሳይሳካ ቀርርቶበታል።
በመጨረሻም ጠላት የሚያስማርከውን አስማርኮ የጓዶቹን አስከሬን እንኳን ሳይሰበስብ ከተማዋን ጥሎ ወደ ጫካ ፈርጥጧል። ጀግኖቹ የሰረርኩላን ከተማ እስከ ምሽቱ ሁለት(2:00) ሰዓት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ስር አውለዋታል።
በሌላ በኩል በቱቲ ከተማ በተደረገው አውደ ውጊያ እጅ በአፍ የሚያስጭን ነበር። የቱቲ ከተማ በተናዳፊዎቹ ሻለቆች የባሩድ ጢስ ስትታጠን፣ ባሩዱም ሲቆላ በዋለበት በዚያ አስፈሪ ሰዓት ጠላት ምሽጉን በመነጠቁ ከተማዋን ጥሎ ለመውጣት ተገዷል። የወገን ኃይል ከተማዋን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ድላቸውን አጣጥመዋል።
ይሕ በእንዲሕ እንዳለ ጠላት በእውር ድንብርና በፍርሃት ተውጦ ዙ-23 እና ሞርተሮችን እያጮኸ ቢውልም በጀግኖቹ የቦታ ቁጥጥርና በማይበገረው የስነ-ልቦና የበላይነት ግንባሩን ተመትቶ እንደ ቅጠል ሲረግፍ አምሽቶ ፣ በዚህ ደማቅ አውደ ውጊያ የተረጋገጠውና በጀግኖቹ እጅ የገባው የምርኮ ዝርዝር እንደሚከተለው ይፋ ሆኗል፦
➾3 ከፋኖ ከድተው ወደ አገዛዙ ገብተው የነበሩ ባንዳዎች
➾1 የአገዛዙ ካድሬ
➾3 የሚሊሻ አባላት
➾የተማረከ ንብረት ዝርዝር ፦
➾8 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች
➾4 የወገብ ትጥቅ
➾1 የደረት ትጥቅ
➾6 የእጅ ቦንቦች እና... በርካታ ተተኳሽ ጥይቶች በጀግኖቹ እጅ ገቢ ተደርገዋል።
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን "
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
አድሜን እፈልጋለሁ አድሜን መሆን የሚፈልግ እውነተኛውን የአማራ ትግል መምራት የሚችል ሰው ከታች በአለው ሊንክ አውሩን
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ከፍተኛ የአመራርና የክፍለ-ጦሮች የምክክር መድረክ አደረገ!!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር የአፋብን ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ እና ሁሉንም ክፍለ-ጦር ስራ አስፈጻሚዎችን ያካተተ የተልዕኮ ግምገማና የስትራቴጂክ አቅጣጫ ማስቀመጫ መድረክ አካሂዷል።
ከአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ካሉ የውጊያ ቀጠናዎች በከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነትና በጀግንነት ታሪኩ የሚታወቀው 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ተቋማዊ ሪፎርም መስራቱን ተከትሎ የሰራዊቱን የውጊያ ዝግጁነትና የዕዝ ሰንሰለት ይበልጥ ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገሩ ይታወቃል። ይህ የምክክር መድረክም በሪፎርሙ ማግስት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለመገምገምና የቀጣይ ስምሪቶችን እና ስልታዊ ግቦችን ለመቅረጽ ነበር።
በዚሁ መድረክ ላይ ባለፉት ሁለት ወራት በኮሩ የኃላፊነት ቀጠና ውስጥ የተከናወኑ ወታደራዊና አስተዳደራዊ ተግባራት በጥልቀት ተገምግመዋል። ኮሩ በስትራቴጂ፣ በሎጅስቲክስ አቅርቦትና በኃይል ግንባታ ረገድ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች የመዘነ ሲሆን፣ በተለይም የሰራዊቱን የውጊያ ስነ-ምግባርና ዝግጁነት በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚያስችል አዲስ የኮሩ መተዳደሪያ ደንብና የዲስፕሊን መመሪያ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም፣ መድረኩ የቀጣይ ወራትን ስልታዊ የክወና ዕቅድ ያጸደቀ ሲሆን፣ ወቅታዊ በሆኑ ቀጠናዊ የፀጥታ አጀንዳዎችና ስጋቶች ፣ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ፈተና ማስፈጸም ላይም ጥብቅ ወታደራዊ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
የአካባቢውን አስተማማኝ ሰላምና ደህንነት ለማስከበር በየደረጃው የሚገኘው የክፍለ-ጦር አመራርና መላው የኮሩ አባላት የተሰጣቸውን ግዳጅ በላቀ የውጊያ ጥበብና ቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በድጋሚ በማረጋገጥ፣ መድረኩ የተቀመጡትን ስልታዊ ግቦች በውጤታማነት ለመተግበር የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቋል።
ድል ለአማራ ህዝብ !!!
ድል ለአማራ ፋኖ !!!
አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል!!!
ዋግኸምራ ምድር ሐሙሲት ግምባር 303ኛ ኮር 14ኛ ክፍለጦር በጠላት ላይ ታላቅ ድል ተቀዳጁ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ኮር 14ኛ ክፍለጦር አካል የሆነችው ሁለተኛ ማንኩሽ ሻለቃ በዋግኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መቀመጫ ሰቆጣ ከተማ በስተደቡብ ምስራቅ 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ከምትገኘው ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ሐሙሲት ከተማ ላይ በመግባት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል።
ሰኔ 05 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት እስከ ረፋዱ 4:00 ሰዓት በተደረገ የደፈጣና ሽምቅ ውጊያ ዙሪያውን ከበባ በማድረግና በማፈን እንዲሁም መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በአገዛዙ ሚሊሻ አባላትና ራሳቸውን ስምረት ብለው በሚጠሩ በጌታቸው ረዳ የሚመሩ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ በማድረስ በጠላት ላይ ድል ተጎናፅፈዋል።
ራሱን ስምረት ብሎ የሚጠራው ኃይልም ሞርታር-82 ወደ ሐሙሲት ከተማ ሁለት ጊዜ በማስወንጨፍ ንፁሃንን የጨፈጨፈ ሲሆን በተወረወረው ቅምቡላ ስድስት ንፁሃን ውድ ህይወታቸውን ሲያጡ ከአስራ አምስት በላይ ንፁሃን ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ወደ ሰቆጣ ሆስፒታል ሪፈር እንደተባሉ የአይን እማኞች መረጃውን አድርሰዋል።
በተደረገው አውደ ውጊያ 15 ተደምስሶ፣ ሰድስት ሲቆስል፣ ሁለት ሚሊሻ ተማርኳል ፤ እንዲሁም ሁለት ጂምስሪ(GM-3)፣ አንድ ኤምፎርቲ(M-40) እና ዘጠኝ ክላሽንኮፍ በመማረክ ወደ ክፍለ ጦሩ ካዝና ገቢ መደረጉን የ14ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ አርበኛ ሐብቱ ማሞ (ራስታው) አስታውቋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ 05/2018 ዓ.ም
በ2እጅ እነሴ ወረዳ ጥሩሰላም ቀበሌ (አራጢ) ላይ በወቅታዊ ጉዳዮች ከህዝቡ ጋር የክ/ጦር አመራሮች በመገኘት ውይይት ተካሄደ።
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
ሰኔ05/2018ዓ.ም
የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 54ኛ ክ/ጦር በ2እጁ እነሴ ወረዳ ጥሩሰላም ቀበሌ {አራጢ} በጀግኖች የትውልድ ቀዬ የአመራር ውይይት አካሔደ።
የአብይ አህመድ ሰራዊት አራጢን ሲያስብ እንቅልፍ አይተኛም፤ጉልበቱ ይርዳል።
ቀጠናው በአማራ የትግል አብዮት ውስጥ ታሪክ ከሚዘክራቸው የእኔ ተፈራ ደምጤ(ተፌ) እና ሌሎች የትውልድ ቀዬ ነው።
ከ2ኛ ተፈራ ዳምጤ እስከ 54ኛ ክ/ጦር የቀጠለው የቀጠናውን ጀብደኝነት በወትሮው ግለት ማስቀጠል ብሎም ማሻሻል ላይ ከጥሩ ሰላም ቀበሌ ተዋጊ ኃይል ጋር የጋራ ውይይት ተደርጓል።
በቀጠናው የቀበሌ መዋቅርና ህዝባዊ አስተዳደርን ጨምሮ የተገመገመና የወደፊት አቅጣጫ የተቀመጠበት መድረክም ሲሆን
በውይይቱ የህዝባችንን የትግል አረዳድና ቁርጠኝነት የተረዳንበት መድረክ ነበር።
እናደራጃለን ! እንመክራለን! እንፈፅማለን!!
አዲስ ትውለድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!
አፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
📌የአገዛዙ 59ኛ ክፍለ ጦር የብልጽግና ታጣቂ ወታደሮች የፋኖ አባላትን መቀላቀላቸው ተገለፀ‼️
=========================
ሰኔ (5/2018ዓ.ም)
አፋብን ሰሜን አማራ በላይ ዕዝ ሜ/ጄኔራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ስር
አናብስቶችን የስርዓቱ ቡችላዎች ፀረ-አማራ የነበሩ ሃይሎች እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ፋኖን እንዲቀላቀሉ ተደርገዋል=====!!
በእስቴ ዴንሳ ብርጌድ አናብስቶች በተደጋጋሚ በደረሰባቸው ብርቱ ምት እና የአገዛዙ ስርዓትን አስከፊነት የተረዱ የኦህዴድ አገልጋዮች አሁንም ቢሆን አልመሽም በማለት እውነተኛውን የትግል መስመር በመምርጥ ዘመን ተሻጋሪና ተራማገጅ የትግል ጉዞ ተቀላቅለዋል።
👉ሁለት/2/ አድማ ብተና
👉አራት/4/ መከላከያ
በአጠቃላይ ስድስት/6/የአገዛዙ ታጣቂ ሃይል በዛሬው ዕለት እንደ ሰማይ ኮከብ የምትወረወረውን የእስቴ ዴንሳ ብረጌድ አካል ሁነዋል።
📌 የአገዛዙ ታጣቂ ሃይሎች ሰማቸው እንደሚከተለው ተዘርዝርዋል፦
👉ይመር እሽቱ ➔ አድማ ብተና
👉 መንግስቱ ዳንኤል ➔ መካላከያ
👉፲ አለቃ ክፍሌ ሃይሌ➔ መከላከያ
👉ኮንስታብል አለባቸው ስዩም➔ አድማ ብተና
👉ቀነኔሳ ደጀኔ ➔መከላከያ
👉ያሬድ አብዲ ➔ መከላከያ
ሲሆኑ ፣ሌሎች የታጠቁ የአገዛዙ ወታደሮች የፋኖን መንፈስ እንዲለበሱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
ሜ/ጀኔራል ውባንተ አባተ፩ኛ ኮር ጉና ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ
መምህር ያሬድ ገደፍው
የአፄ አምደ ፅዮን ኮር በስሩ ለሚገኙ የክፍለጦርና የሻለቃ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አመራሮች መሰረታዊ የICT ክህሎት አጭር ስልጠና ሰጥቶ ማጠናቀቁን አስታወቀ።
አፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አካል የሆነው የአፄ አምደ ፅዮን ኮር በስሩ ለሚገኙ የክፍለጦርና የሻለቃ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አመራሮች ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ እንዲሁም ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥን ለማሳለጥ ታሳቢ ያደረገ መሰረታዊ የአይሲቲ (ICT) ክህሎት ስልጠና በመስጠት ማጠናቀቁን ኮሩ ለዕዙ በላከው የስራ ሪፖርት መረጃ አስታውቋል።
ለተጀመረው የህልውና ትግል ዘመናዊ አሰራርን በማጎልበት በኮሩ ስር የሚገኙ ንዑሳን ክፍሎችን እያበቃ መሆኑን የገለፀው የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአፄ አምደ ፅዮን ኮር በስሩ ለሚገኙ የክፍለጦርና የሻለቃ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አመራሮች ለተከታታይ ቀናት የሰጠውን ስልጠና በስኬት ሲያጠናቅቅ ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በሟሟላት ለሰልጣኞች ስምሪት መሰጠቱን ኮሩ ገልጿል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ 05/2018ዓ.ም
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር የአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር ሰራዊትጥልቅ ውይይት እና ግምገማ አደረገ!!
ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም
የአስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር ሰራዊትና ከክፍለ ጦሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአፋብን ወታደራዊ ቃል አቀባይአርበኛ አበበ ሙላቱ እና የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ምክትል ዘመቻ መሪ መቶ አለቃ ኤርሚያስ ግጨው በቦታው በመገኘት በተደረገ ሰፊ ውይይት የሰራዊት የስነልቦና ግንባታ ስራ በመስራት ለቀጣይ ማንኛውም ድርጅታዊ ተልዕኮ ዝግጁ መሆኑን አረጋገጠ።
ዛሬ በተካሄደው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የአመራር አካላቱና አርበኞቹ ከሰራዊቱ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር የመከሩ ሲሆን፣ ሰራዊቱ የተሰጠውን ኃላፊነት በላቀ ብቃት መወጣት በሚችልበት አቅም ላይ ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሯል።
በተለይ በየሻለቃው ለሚገኘው ሰራዊት የተደረገው የስነ-ልቦና ማነቃቂያ መድረክ በከፍተኛ ስሜት ቀስቃሽነትና አነቃቂነት የተሞላ ነበር። ሰራዊቱም በተደረገለት በዚህ ሁለንተናዊ የማነቃቂያ ውይይት ታላቅ ደስታ እንደተሰማውና ዝግጁነቱን ይበልጥ እንዳጠናከረ ታውቋል።
ከውይይቱ ማጠናቀቂያ በኋላ የሰራዊቱ አባላት ባስተላለፉት መልዕክት በተደረገላቸው ወቅታዊና ስነ-ልቦናዊ ማነቃቂያ ውይይት መሪወችን አመስግነው በሂደቱም እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዋል። በቀጣይም ይህ ግንባታና ማበረታታት ይቀጥል። እኛም የድርጅታችንን ግብ ለማሳካት የዕዝ ሰንሰለት በመጠበቅ ነገም እንደ ትላንቱ ታሪክ መስራታችን ይቀጥላል። ሲሉ በሙሉ እምነትና በልበ-ሙሉነት ተናግረዋል።
የክፍለ ጦሩ አመራሮች በበኩላቸው ሰራዊቱ ላሳየው ከፍተኛ ተነሳሽነትና ልበ -ሙሉነት ምስጋናቸውን አቅርበው፣ መሰል የውይይት መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ 04/2018 ዓ.ም
የብልፅግና አገዛዝ ቡድን እርስ በርሱ መተኳኮስ እና መበተኑን ቀጥሎበታል !!
ሰኔ 04/2018 ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ብትር መቋቋም ያቃተው የአገዛዙ ሀይል በመጨረሻመም እርስ በርሱ በመጠራጠር እየተመታታ እየተበተነ መሆኑን የግንባር መረጃወቻችን ጠቁመዋል።
በመፈራረስ ላይ የሚገኘው የብልፅግናዉ ዘራፊ እና ጨፍጫፊ ቡድን በደብረ ብርሃን ከተማ እርስ በርስ በመተኳኮስ መጠፋፋቱ እንደቀጠለ ሲሆን ይህንንም ክፍተት በመጠቀም ቀኜ የሚፈለገው ሀይል ላይ እርምጃ ወስዷል።
ትናንት ማለትም በቀን 03/10/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 5:30 ገደማ ላይ በደብረ ብርሃን ከተማ ስር በሚገኙት በሁለቱ ክፍለ ከተሞች ማለትም፡ በአፄ ዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማና በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በነበረ የአገዛዙ የእርስ በርስ ተኩስን በመጠቀም ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንጠቅሰው የውስጥ ቀኜ አባሎች በወሰዱት እርምጃ የቆሰሉ እንዳሉ ቢታወቅም ፤ በነበረው የተኩስ ልውውጥ 2 የሚሊሻ አባላት እና 1 የፖሊስ አባል ሲገደሉ ፤ በነበረው የተኩስ ልውውጥ ውስጥ በውር ድንብር መውጫ መግቢያ የጠፋው የአገዛዙ ሀይል ከጉዳዩ ጋር ምንም ከማያገናኛት አንድ ንፁሃን የከተማ ነዋሪ ላይ በመተኮስ ያቆሰላት መሆኑ እና በህክምና እርዳታ ውስጥ እንዳለች መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህ የአገዛዙ ሀይል ወደ አለመተማመን የገባና በመጨረሻም እርስ በርሱ መጠፋፋቱ ወደ ለዬለት መተኳኮስ የሚያመራና የማይቀር በመሆኑ አሁንም ወደ ቤተሰብ የመቀላቀል ዕድላቸውን እየተጠቀሙ ወደ ፋኖ የሚገቡ የሚሊሻ እና አድማ ብተና አባላት ቁጥር እንደቀጠለ ነው። ይህን ዕድላችሁን ሁላችሁም የአገዛዙ መጠቀሚያ ሀይል አባላት ትጠቀሙ ዘንድ ውስን ጊዜ አላችሁ።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!
ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሰኔ 04/2018 ዓ.ም
50 አለቃ ካሳሁን ኃይሌ በመሐል ሳይንት ግንባር የአፋብን ወሎ ቤተ_አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ 47ኛ ክ/ጦር #አትሮንስ_ሻለቃን ተቀላቀለ:: 50 አለቃው የዲሽቃ ምድብተኛ ሻንበል መሪ ነበር።
50 አለቃ ካሳሁን ኃይሌ ስለጠላት አሁናዊ ቁመና ሲናገር "ለምንና በምን ምክንያት እንደሚዋጋ የማያውቅ፤ ዓላማ የሌለውና የጥቂት ግለሰቦችን ሥልጣን ለማስከበር መተኪያ የሌላትን አንድያ ህይወቱን የሚገብር በመሆኑ፣ መላው ሠራዊት በደመ_ነፍስ የሚቅበዘበዝ ሆኗል። ሞራሉም ዋዥቋል፤ ወታደር የሞራል ስንቅ ካልታጠቀ ደግሞ በየአውደ_ውጊያው የሽንፈትን ፅዋ ቢጎነጭ የሚደንቅ አይደለም" ብሏል።
የአፋብን ወሎ ቤተ_አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር የዘመቻ መምሪያ ም/ኃላፊው አርበኛ ጎሹ ታረቀ ኮብላዩን በክብር ተቀብሎታል!
ምንጭ:- የአፋብን ወሎ ቤተ_አማራ ምኒልክ ዕዝ 105ኛ 47ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ Eyob Ashenafi
