ru
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
3 641
Подписчики
+2024 часа
+3787 дней
+1 08530 дней
Архив постов
አፋብን ያወጣውን የምህረት አዋጅ ሳይጠቀሙ ቀርተው የፋሽስቱን አገዛዝ ብልፅግና ተልዕኮ በማስፈፀም ላይ የነበሩ ታጣቂዎች ላይ የማያዳግም አስተማሪ እርምጃ ተወሰደ:: በመካነሰላም ዙርያ ማለትም ሙደለላ 031 ቀበሌ ከአምሃራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር አትሮንስ ሻለቃ እና ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር በተውጣጡ ሻለቃዎች የተናበበና የተቀናጀ ውጊያ በሙደለላ ታዳጊ ከተማ የተቀመጠ ከፓሊስ፣ ከሚኒሻና ከሰላም አስከባሪ ተጣምረው የተቀመጡትን የስርአቱ ወንበር ጠባቂወች ከህዝባቸው ይልቅ አለቃቸውን ያመኑ ከህሊናቸው ይልቅ በሆዳቸው የተገዙ የዘመናችን ደናቁርቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዶባቸዋል። በዚህም የፋኖን የምህረት አዋጅ ያልተቀበሉ የኦሮሞ የብልፅግና አገልጋይ ፖሊስና ሚሊሻ ላይ ዛሬ የካቲት 15/2018 ዓ.ም በተወሰደው የማያዳግም አስተማሪ እርምጃ ከሃያ በላይ ሙትና ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን 11 ክላሽ፣ አንድ ሽጉጥ እንዲሁም በርካታ የደረትና የወገብ ትጥቆች ተማርከዋል:: በተጨማሪም መካነሰላም ዙርያ በሰኞ ገበያ ተዋ መገንጠያ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ውጊያ ፋኖ በወሰደው መብረቃዊ ጥቃት በአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ላይ ግለቱን የጠበቀ ውጊያ ተደርጎ በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ ደርሶበታል። ፋኖም  ይዞታውን ያስጠበቀ ሲሆን ጠላት አንድ አንቡላስ ሙትና ቁስለኛውን ጭኖ ወደመጣበት ተመልሷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ የካቲት 15/2018 ዓ.ም

አማራ የሆነ ሁሉ ሊያደምጠው የሚገባ ጠባሳ ነው። Subscribed እንዳይረሳችሁ። https://youtube.com/watch?v=fY55nH6ySUI&si=XxhhB9t_nWf4ytoW

ታላቁ አርበኛ ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ ከከሰም ቀጠና አመራሮች ጋር በአአ አፍንጫ ስር ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ጊምቢቹ ወረዳ የሚገኙ የአማራ ፋኖ ሰራዊት እና ህዝቡን ባወያየን ጊዜ የተወሰደ ንግግር ነው። የተግባር አማራው ሳይደክመው ወጥቶ ወርዶ እውነተኛውን ታጋይ ማደራጀት ችለናል። በቀድሞ መጠሪያው ሃገር ማሪያም ከሰም ወረዳ ስር የሚገኙ አማራዎችን በማደራጀት ሻምበል ፈንታ ሃይል ክ/ጦር የሚል ስያሜን ያገኘ አማራዊ ሃይል ገንብተናል። ሻምበል ፈንታ ሃይል ክ/ጦር በከሰም ኮር ስር ተዋቅሮ ሰፊ ቀጠናን በመሸፈን አማራዊ ግዳጁን እየተወጣ ይገኛል። በሁሉም አካባቢ የሚገኘውን አማራ በማደራጀት፣በማሰልጠን እና በማብቃት የገጠመንን ብሔራዊ አደጋ እንመክታለን!! የነቃ እና የበቃ አማራዊ ሃይል ግንባታችን ተጠናክሮ ይቀጥላል🙏 ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ

እኔ፣ የትግል ጓዶቼ እና ከውስጥም ከውጭም ያላችሁ ደጋፊዎቻችን፤ እኛ በግንባር ተገኝተን የ"ፍኖተ አማራ" ሚዲያ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀን 24 ሰዓት፣ በአራቱም ማዕዘናትና በአዲስ አበባ ጭምር ለእናን
እኔ፣ የትግል ጓዶቼ እና ከውስጥም ከውጭም ያላችሁ ደጋፊዎቻችን፤ እኛ በግንባር ተገኝተን የ"ፍኖተ አማራ" ሚዲያ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀን 24 ሰዓት፣ በአራቱም ማዕዘናትና በአዲስ አበባ ጭምር ለእናንተ እያደረስን እንገኛለን። ከእነዚያ የቁርጥ ቀን የአማራ ልጆች ከሆኑት የትግል ጓዶቼ ጋር በመሆን፣ ከውጊያው ጎን ለጎን የሚዲያ ስራችንንም በቁርጠኝነት እየሰራን ነው፡፡ ​ሆኖም ግን፣ የውስጥና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን እንደ ትላንቱ ሁሉ ዛሬም ጉዟችንን ለማሰናከል እየሞከሩ ይገኛሉ። ውድ ደጋፊዎቻችን፤ ሚዲያችን እውነተኛውን የአማራ የህልውና ትግል ከመሬት ላይ እየዘገበች ትገኛለች። አሁንም አቅማችንን አሳድገን አስር ሺህ (10,000) ተከታዮችን ለማፍራት እየሰራን በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ደጋፊ የቻለውን ያህል "ሼር" እና "ጆይን" (Join) በማድረግ ትግሉን እንዲደግፍ ከልብ በመነጨ ምስጋና ጥሪያችንን እናቀርባለን። ​ውድ አማራውያን፣ አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!

የተሰራጨውን የግጭት ትርክት በበተኑት መሪዎቸ ኩራት ተሰምቶኛል። የአማራን ህዝብ የህልውና አደጋ ቀልብሰን አማራው በየትኛውም የአለም ጠርዝ ፣በእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ፍፁም ተከብሮ ምልዑ እና ህልው ሁ
+1
የተሰራጨውን የግጭት ትርክት በበተኑት መሪዎቸ ኩራት ተሰምቶኛል። የአማራን ህዝብ የህልውና አደጋ ቀልብሰን አማራው በየትኛውም የአለም ጠርዝ ፣በእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ፍፁም ተከብሮ ምልዑ እና ህልው ሁኖ እናየዋለን ስንል ከታች በምስሉ እንደሚታየው የአርበኛ ዘመነ ካሴ እና ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው የሰሞናኛ እንቅስቃሴ የራዕያችንን ፍፃሜ የሚያመላክት ሁኖ እናገኘዋለን። አለቆቻችን !! አማራው በሌሎች ብሔሮች የተሰራበትን የጠብ ግድግዳ በመናድ በታጣቂዎች የታገቱ ሴቶችን በማስለቀቅ የጉምዝንና የአማራውን አንድነት የሚያረጋግጥ ሰፊ ስራዎችን በመስራት የመሪነት አደራቸውን በሚገባ እያሳዩን ነው። የአማራ ብሔርተኝነት ለሌሎች ማንነቶች ስጋት ሳይሆን የአብሮነትና የፍቅር ምህዳር መሆኑን ባሳዩበት የውይይት መድረክም የአማራው ትግል የአማራን ህዝብ ነፃ ከማውጣት ባሻገር የሌሎችን መብት ለማስጠበቅና ብሔራዊ አንድነትን በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ ለማምጣት የተሰራጩ የግጭት ትርክቶችን ለመበተን የሚተጋ መሆኑንም ከአርበኞቻችን አንደበት ሰምተናል። በዚህም ትልቅ ውጤት ተመዝግቧል ቀጠናውም ከግጭት ወደ ፍቅር ተቀይሯል እናም በቀጠናው ያላችሁ ሌሎች አስተባባሪ አመራሮች አርበኛ ምናልባት እና ዶ/ር ጋሹ እንዲሁም ጓደኛየ አርበኛ ብርሀኑ ቻሌ እና ሌሎች የኮርና የክ/ጦር አመራሮች በእናተ ኩራት ተሰምቶኛል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ

የአማራ ትግል ወደ አንድ መምጣቱን ሲጠባበቁ የነበሩ እና የአፋብን የምህርት አዋጁን ጥሪ የተቀበሉ #ስምንት የአገዛዙ ሰራዊት አባላት 64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቀሉ። ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ የካቲት 15/2018 ዓ.ም 1ኛ. ይበልጣል አይዋ ሸበል በረንታ የጥሀና ቀበሌ 2ኛ. አቃተ አስረስ ሸበል በረታ አባ ሰልማ ቀበሌ 3ኛ. እያዩ መሰረት ሸበል በርንታ ቦንያ ሰቀላ ቀበሌ 4ኛ. ንጉሱ ደመቀ ሸበል በረንታ የሚሊሻ አባል ሲሆኑ 5ኛ. ይላቅ ወንዳለ 6ኛ ዕዝ 601ኛ ኮር 52ኛ ክ/ጦር 6ኛ. ይልቃል አበጀ 6ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር 7ኛ.ክንዱ አማኑኤል 6ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር 8ኛ.10 አለቃ እሱባለው አትንኩት 6ኛ ዕዝ 206ኛ ኮር 75ኛ ክ/ጦር ስር ከሚገኙ 6ኛ፣ 2ኛ ፣4ኛ ሻለቃ ላይ ሻምበል መሪና ቲም መሪ በመሆን አገዛዙን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። በመሆኑም 10 ቁጥር ክላሽ ከ30 ጥይት ጋር፣ አንድ ኮሪያ ክላሽ፣ አንድ እስኬስ መሳሪያ፣ አንድ ክላሽ መሳሪያ ከ90 ጥይት ጋር ከየዕዱውኃ ከተማ እና መርገጭ ከተማ ከሚገኘው የአረመኔዊ አገዛዝ የመከላከያ ተቋም እና ሚሊሻ ተቋም በመክዳት የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር #64ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቅለዋል። በሸበል በርንታ ወረዳ የሚገኜው የአገዛዙ ሰራዊት አባላትን በመክዳት 64ኛ ክፍለ ጦር የተቀላቀሉ የአገዛዙ ሰራዊት አባላት እንደተናገሩት አገዛዙ በዚህ ሰዓት በየቦታው እየፈራርሰ እንደሚገኝና በማህበርሰቡ ላይ ለአይን የሚዘገንን ግፎችን፣ በደሎችን እየሰራ ይገሉ ብለዋል። በተለያየ ምክንያት ከየከተማው እና ገጠሩ በጉልበት ታፍነው የታፈሱት ብዙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ቅጥርኛ ሚሊሻ ወደ ፋኖ ይቀላቀላል ብለዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!! የካቲት 15/2018 ዓ ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት

አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ። በኢትዮጵያዊነቱ ላፍታም የማያመነታውን እና ዝንፍ የማይለውን የአማራን ህዝብ በሁሉም ዘርፍ ማህበራዊ ረፍት እንዲያጣ ያደረገውን መዋቅራዊ ጥቃት ለመመከተ ህዝባዊ ትግል በማድረግ ላይ መሆናችን ግልጽ ነው፡፡ ፀረ-አማራ የሆነው ስርዓት አማራን የማጥፋት ህልሙን ለማሳካት እርስ በርሳችን እንድንገዳደል በማድረግ በግጭትና በድህነት አረንቋ ውስጥ እንድንቆይ ሁሉንም የክፋት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ በብርቱ መሰዋእትነት የተገነባውን ልዩ ኃይላችን ከበተነ በኋላ ብአዴናዊነት እና የአጎብዳጅነት ልክፍት ውስጥ እንድንቆይ ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልቧጠጡት አቀበት የለም። አማራን በጦርነት ውስጥ ማቆየት ብቻ ሳይሆን እልቂቱን እርስ በራስ በማድረግ በማይደርቅ ጥቁር ደም አዙሪት እንድንማቅቅ ማድረግ ዋና አላማቸው እንደሆነ ራሳቸው እየነገሩን እንኳን ልንረዳ አልቻልንም፡፡ ድፍን ሶስት ዓመት ሙሉ ሚሊሻ ወይንም አድማ ብተና ከፋኖ ጋር እልቂት ውስጥ ኖረናል፡፡ ነገር ግን ሁሉም የአማራ ልጆች ሲሆኑ አንደኛው ለህዝቡ ነፃነት ሌላው ደግሞ ፀረ-አማራ ለሆነ አገዛዝ ወንበር ለማስጠበቅ መሆኑ ነው፡፡ በሌላ በኩል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተልዕኮው ሀገር በውጭ ወራሪ ስትደፈር መጠበቅ ሆኖ እያለ በየቀበሌው እየገባ የአማራን ቤት ማቃጠልና አርሶ አደር መግደል፣ ሴቶችን መድፈር፣ ክምር ማቃጠል ስራየ ብሎ ከጀመረ ሶስት አመት ሊሞላው ነው፡፡ ስለሆነም በሰው ደም ወንበሩን ማጽናት ለፈለገው ስርዓት እርስ በእርስ መገዳደሉ ተገቢ አለመሆኑን ተረድቶ ወደ ህዝብ መመለስ ብልህነት ነው፡፡ ስለሆነም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ባለፋት አስራ አምስት ከቀናቶች የሚቆይ የምህረት አዋጅ ማውጣቱን ተከትሎ ከሁሉም የመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ወንድም እህቶቻችን ከዚህ በሰማይ በምድር ትርፍ ከሌለው መገዳደል የሚያስቆም ዘለቂ መፍትሔ ነውና የተቀመጠውን የምህረት አዋጁ ተጠቃሚ በመሆን ወደ ሚፈልጉት የማህበራዊ ኑሯቸውም እንዲመለሱ አድርገናል። እያደርግንም ቆይተናል። አሁንም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር እሚከተሉትን ወቅታዊ ጥሪዎችን ማቅረብ ይፈልጋል። 1. ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለአድማ ብተና፣ለፖሊስና ሚሊሻ አባላት በሙሉ:- ህዝባችሁን አስጨፍጭፋችሁ የምታገኙት ማዕረግ፣ ቤት፣ መኪና፣ ደመወዝና ጥቅማጥቅም አንዳቸውም እናተንና ቤተሰቦቻችሁን መታደግ የሚችሉ እንዳልሆነ ይልቁንስ የባሰ ተጠያቂነት ከፍ ሲልም አሟሟትን የሚበላሽ ነውና ከየካቲት 01—14/2018 ዓ.ም ድረስ ከደብረ ታቦር እስከ ጨጨሆ፣ ከስማዳ እስከ እስቴ ደራና ፎገራ ቀጠናዎች ብቻ የጠፋው የወንድማማቾች ህይወት ይበቃልና በአፋብን የተሰጠውን የምህረት አዋጅ መሰረት አድርጋችሁ ነገ ዛሬ ሳትሉ በኮሩ ስር ባሉ የክፍለ ጦር አደረጃጀቶች በኩል በስልክ አመራሮችን በማግኘት ወይንም ቤተሰብ/ጓደኛ በመላክ ግንኙነት ፈጥራችሁ ህዝባችሁን እንድትቀላቀሉ  ስንል እናሳስባለን፡፡ 2. ለአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ክፍለ ጦሮች:- ትግላችን ብዙ ወንድሞችና እህት አርበኞቻችን የገበርንበት ነው። እናም የአማራ ህዝብ የመኖር መብቱ እስኪረጋገጥለት ፣ ፍትሐዊ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ እዲሁም የማንነትና የርስቱ አምዶች ተከብረውለት እስክናይ ድረስ የሚቆም ትግል አይደለም። ታዲያ ሁሉንም ጠላት ብለን ፈርጀን በመግደል ብቻ ለውጥ ልናመጣ እንደማንችል ድርጅታችን ገምግሞ የምህረት አዋጅ አውርዶልናል፡፡ ስለሆነም ለሚቀላቀሉን የመከላከያ፣ የአድማ ብተና፣ ፖሊስና ሚሊሻ አባላት እንዲሁም በስርዓቱ ውስጥ አገልጋይ የነበሩ አመራሮች የትግሉን ሁለተናዊ ገጽታ እንዲረዱት በማድረግ መልካም አቀባበል እንድታደርጉላቸው በጥብቅ እናሳስባለን። እስካሁን የቆዩበት መንገድ ፍጹም ስህተት መሆኑን ተረድተው የአማራን ህዝብ ድጋሜ ላለመውጋት ከወንድሞቻቸው ጋርም ላለመገዳደል በማሰብ የሚመጡ ወንድምና እህቶችን በፍጹም ፍቅርና ርህራሄ በመቀበል የአዋጁ ውሳኔ ሳይሸራረፍ ከእነ ሙሉ ክብራቸው የምህረት የምስክር ወረቀት እያገኙ ወደ ቤተሰብ እንዲቀላቀሉ ማድረግ ይገባል፡፡ በሂደት ሁኔታውን በውሉ እየተረዱ ወደ ትግላችን የሚቀላቀሉ ካሉም ተገቢ ተሃድሶ ተሰጥቷቸው እንዲገቡ ማድረግ ይገባል፡፡ በአፈጻፀሙ ላይ ብዥታ ካጋጠማችሁም ኮሩንም ሆነ ዕዙን ተጨማሪ ማብራሪያ በመጠየቅ ያለ ምንም እንግልት ማስተናገድ እንደሚገባችሁ እናሳስባለን፡፡ ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የካቲት 15/ 2018 ዓ.ም

የደብረ ታቦር ከተማ ብልጽግና፣ የደቡብ ጎንደር ዞን ብልጽግና እና አጠቃላይ የአቢይ አሕመድ ኮርቻ አማሮች ዋይታ [የካቲት 15/2018ዓ.ም] የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በቀን 14/06/2018ዓ.ም ከጋ
የደብረ ታቦር ከተማ ብልጽግና፣ የደቡብ ጎንደር ዞን  ብልጽግና እና አጠቃላይ የአቢይ አሕመድ ኮርቻ አማሮች ዋይታ                 [የካቲት 15/2018ዓ.ም] የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በቀን 14/06/2018ዓ.ም ከጋሳኝ እሥከ አርሴማ፣ ከዘበራ እሥከ ክምር ድንጋይ በአምሐራ ፋኖ ዛብሯል፣ ተገርፏል፣ ተማርኳል፣ ተደምስሷል፣ ከቁሳዊ እሥከ አካላዊ እና ከሞራላዊ እሥከ መዋቅራዊ መፈራረሥ ደርሶበታል። በዚህ የተነሳም ብዛት ያለው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ሙትና ቁሥለኛ ሲሆን ጫካ ወድቀው ከቀሩት ውጭ በጅምላ ሆሥፒታል የተወሰዱት ላይመለሱ ማሸለባቸውን ተከትሎ አገዛዙ ደብረ ታቦር ሆሥፒታል በአቢይ አራዊት ሰራዊት አሥከሬን ሞልቶብኛልና የደብረ ታቦር ከተማ በተለይም የሰኞ ገበያ በጎ ፈቃድ ሰጭ ወጣቶች ኑና አቃብሩኝ፤ ብቻዬን አልቻልኩም ያለበት መልዕክት በውሥጥ የመረጃ ምንጮቻችን መሰረት በዚህ ልክ ደርሶናል። የጊዜ ጉዳይ ሆኖ ትግሉ ሊረዝም ይችላል እንጅ ፀሐይ በምሥራቅ የመውጣቷን ያክል የዓምሐራ ሕዝብ ትግልም አሸናፊ እንደሚሆን 100% ዕናምናለን እናውቃለን። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗ ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA👊✊ አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ መምሪያ ፋኖ ኢንጅነር ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው ቋሚ ምሥል፦ የአገዛዙ አቃብሩኝ ጥሪ ለሚቀርቡት ወዳጆቹ Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የደብረ ታቦር ከተማ ብልጽግና፣ የደቡብ ጎንደር ዞን  ብልጽግና እና አጠቃላይ የአቢይ አሕመድ ኮርቻ አማሮች ዋይታ                 [የካቲት 15/2018ዓ.ም] የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት በቀን 14/06/2018ዓ.ም ከጋሳኝ እሥከ አርሴማ፣ ከዘበራ እሥከ ክምር ድንጋይ በአምሐራ ፋኖ ዛብሯል፣ ተገርፏል፣ ተማርኳል፣ ተደምስሷል፣ ከቁሳዊ እሥከ አካላዊ እና ከሞራላዊ እሥከ መዋቅራዊ መፈራረሥ ደርሶበታል። በዚህ የተነሳም ብዛት ያለው የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ሙትና ቁሥለኛ ሲሆን ጫካ ወድቀው ከቀሩት ውጭ በጅምላ ሆሥፒታል የተወሰዱት ላይመለሱ ማሸለባቸውን ተከትሎ አገዛዙ ደብረ ታቦር ሆሥፒታል በአቢይ አራዊት ሰራዊት አሥከሬን ሞልቶብኛልና የደብረ ታቦር ከተማ በተለይም የሰኞ ገበያ በጎ ፈቃድ ሰጭ ወጣቶች ኑና አቃብሩኝ፤ ብቻዬን አልቻልኩም ያለበት መልዕክት በውሥጥ የመረጃ ምንጮቻችን መሰረት በዚህ ልክ ደርሶናል። የጊዜ ጉዳይ ሆኖ ትግሉ ሊረዝም ይችላል እንጅ ፀሐይ በምሥራቅ የመውጣቷን ያክል የዓምሐራ ሕዝብ ትግልም አሸናፊ እንደሚሆን 100% ዕናምናለን እናውቃለን። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን❗ ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA👊✊ አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ መምሪያ ፋኖ ኢንጅነር ኃቅአለው ፀጋ አለባቸው ቋሚ ምሥል፦ የአገዛዙ አቃብሩኝ ጥሪ ለሚቀርቡት ወዳጆቹ

🔊የስልጠና ጥሪ🔊 የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ የሕልውና ፈተና ለማስወገድና የሕዝባችን ሕልውና በዘላቂነት ይረጋገጥ ዘንድ የአማራው የቁርጥ ቀን ልጆች ከአማራው ጠላት ጋር እየተናነቁ በየዱር ገደሉ፣ በየተራራውና በየከተማው ውድ የሆነ የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ የሕዝባቸውን የዘመናት ጥያቄ ለመመለስ የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ እነሆ 3 ዓመታትን አስቆጥረዋል። በእነዚህ ዓመታት የአማራ ትግል በአዕምሮ ከሚገመተው በላይ በሆነ የድል ግስጋሴ እንደ ንጋት ኮከብ አንጸባራቂ የሆነ ድል እየተጎናጸፈ ይገኛል። በቀጣይም ቀሪዎቹ የትግል ምዕራፎች በሚጠበቅባቸው ልክ ይጓዙና ትግሉ ያለውን ቀጠናዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የአማራን ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥያቄ ከመመለስ ባሻገር ለመላው ኢትዮጵያውያን መዳኛና ለሀገሪቱ የልዕልና መንገድ ይሆን ዘንድ ትግላችን የሚፈልገውንና የሚያስፈልገውን ነገር መሸከም የሚያስችል በሁለንተናዊ መንገድ የሰለጠነና የተገነባ ወታደር የግድ አስፈላጊ ነው። በመሆኑም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ እያከናወነው ባለው የኃይል ግንባታ መሠረት የቴዎድሮስ ዕዝ ምዕራብ አማራ ቀጠና 206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር አዲስ ሰልጠኞችን በመመልመል ለማሰልጠና አቅዷል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የመመልመያ መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ ወደ ተዘጋጁ ሶስት የመመዝገቢያ ጣቢያዎች እየመጣችሁ ስንል በአክብሮት እናሳስባለን። የመመልመያ መሥፈርቶች 1/ፆታ ------ወድ 2/ዕድሜ---------ከ20 - 35 ዓመት የሆነዉ 3/ ከተለያዩ ሱሦች ነፃ የሆነ 4/ ምንም አይነት የጤና ችግር የሌለበት 5/ በትክክል ማየት እና መሥማት የሚችል 6/ ከማንኛውም ወጀል ነፃ የሆነ 7/ በስነ ምግባሩ በማህበረሠቡ ዘድ ምንም አይነት አቤቱታ የማይቀርብበት 8/ የታወቀ የቅርብ ተጠሪ ማቅረብ የሚችል 9/ ከጠላት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለዉ 10/ ከዚህ በፊት የትኛዉንም የፋኖ አደረጃጅት ላይ ያልተሣተፈ 11/ ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ የሆነ ( የማያጨስ፣ የማይቅም፣ የማይስክር ...) 12/ ስልጠና ካጠናቀቀ በኋላ በሚመደብበት የትኛውም ቦታ ተንቀሳቅሶ ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ የሆነ ከላይ የተዘረዘሩትን መሥፈርቶችን የምታሟሉ ሠልጣኞች የምዝገባ ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21/06/2018 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አዉቃችሁ የእድሉ ተጠቃሚ እድትሆኑ ስንል በአክብሮት እናሣዉቃለን። የመመዝገቢያ ቦታ፦ የሶስቱም ወረዳዎች የጊዚያዊ መንግስት መቀመጫዎች ላይ። የአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮሥ ዕዝ 206ኛ ኮር 14ኛ ክፈለ ጦር

የ32ኛ ክ/ጦር 4ኛ ሬጅመንት ዲሽቃ ተኳሽ የሆነው በላይ ተፈራ የምህረት አዋጁን በመቀበል የ206ኛ ኮርን ተቀላቅሏል። የካቲት 15/2018 ዓ.ም ===================================== አፋብን ለ15 ቀናት ይቆያል ባለው የምህረት አዋጅ መሰረት በርካታ የአረመኔው ሰራዊት፣ አድማ ብተና፣ ሚኒሻና ፖሊሶች ትግሉን የተቀላቀሉ ሲሆን በአለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 7 (ሰባት) የአረመኔው ሰራዊት አባላት 206ኛ ኮርን መቀላቀላቸው ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለም በዕለተ ዕሁድ ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት በላይ ተፈራ የተባለው የ32ኛ ክ/ጦር አራተኛ ሬጅመንት ዲሽቃ ተኳሽ 206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል። በ14ኛ ክ/ጦር የምረት አዋጅ አስተባባሪ ግብረ ኃይል በኩል ደማቅ አቀባበል የተደረገለት በላይ ተፈራ በበኩሉ ለአብይ አህመድ ስልጣን የሚሞቱ ወጣቶች ስርዓቱን ትተው ህዝባቸውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት በሸበል በረንታ ወረዳ የክፍለ ጦር አመራሮች በተገኙበት ከሬጅመንቷ አመራርና አባላት ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዶል። ➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛
+6
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ሬጅመንት በሸበል በረንታ ወረዳ የክፍለ ጦር አመራሮች በተገኙበት ከሬጅመንቷ አመራርና አባላት ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዶል። ➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛ ➛➛➛➛➛➛ የካቲት 15/2018 ዓ.ም በውይይት መድርኩ በ64ኛ ክፍለ ጦሩ ስር የሚትገኘዋ 1ኛ ሬጅመንት ውስጣዊ ቁመናዋን በመፈተሽ፣ በመገምገም በሻለቀዋ የኦዲት ሪፖርት በማቅርብ 1ኛ ሬጅመንት የጎደሉ አመራር በማሟላት የአማራ ህዝብ ከአብይ አህመድ አርመኔዊ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት ወታደሩ የፖለቲካ ግንዛቤውና አስተምዕሮው ከፍ ያለ መሆን እንዳለበት ግንዛቤ ተሰጥቷል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!! አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙ

ሶስቱን የአማራ ክልል ዞኖች እሚያገናኘው ቦታ አባይና በሽሎ መገናኛ ለፋኖ መሰረታዊ የአንድነት ሰንሰለት ነው። ይሄ አካባቢ ሦስቱን የአማራ ዞኖች (ደቡብ ጎንደር ፣ ምስራቅ ጎጃም ፣ ደቡብ ወሎ) ወይ
ሶስቱን የአማራ ክልል ዞኖች እሚያገናኘው ቦታ አባይና በሽሎ መገናኛ ለፋኖ መሰረታዊ የአንድነት ሰንሰለት ነው። ይሄ አካባቢ ሦስቱን የአማራ ዞኖች (ደቡብ ጎንደር ፣ ምስራቅ ጎጃም ፣ ደቡብ ወሎ) ወይም ስማዳ + እነብሴ ሳር ምድር + አምሐራ ሳይንት፣መቅደላ፣ መሃል ሳይንት ወረዳዎችን ያስተሳስራል። በዋናነት ግን ዓባይና በሽሎ የሚገናኙበት ቦታ አምሐራ ሳይንት ወረዳ(ደቡብ ወሎ)፣ስማዳ ወረዳ ደቡብ ጎንደር እና እነብሴ ሳርምድር ምስራቅ ጎጃም ናቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ደግሞ ዓባይ በሽሎንና ሌሎች ትናንሽ ወንዞችን አዝሎ መሃል ሳይንት ወረዳን እና ቦረና ወረዳን ከምስራቅ ጎጃም እነብሴ ሳርምድር እያገናኘ ይጓዛል። ከዚያም ወግዲ ወረዳን ከሸበል በረንታ ወረዳ ያገናኝና ደቡብ ወሎን ለቆ ወደ ሸዋ ደራና ሸበል በረንታ እንዲሁ በደጀን ወረዳ አድርጎ ዓባይ ጉዞውን ይቀጥላል።

አርበኛ ስለሽ ከበደ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ከፍለ ጦር አስር አለቃ ኤፍሪም አጥናፋ ሻለቃ ልዩ ኮማንዶ ምርቃት ላይ በመገኘት ይህን መልዕክት አስተላልፏል የተከበራችሁ የአፋብን የቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች፤ የተከበራችሁ የቴዎድሮስ ዕዝ 105 ኮር ከፍተኛ አመራሮች፣የተከበራችሁ የቴዎድሮሰ ዕዝ 105 ኮር የ44 ከፍለ ጦር አመራሮቸ፣የተከበራቸሁ የጊዮን ሻለቃ አመራሮች እና የኤፍሬም አጥናፋ ሻለቃ አመራርና አባላት የተከበራችሁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ኮማንድ እጩ የሰራዊት አባላት፣ የተከበራችሁ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ክቡራት እና ክቡራን በቅድሚያ አድካሚ የሆነውን ወታደራዊ ስልጠና በብቃት በመውሰድ እና የታለፈባቸውን ውጣ ውረዶች በማለፍ ለዚህ የምረቃ እለት የበቃችሁ እጩ የኮማንዶ ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ! ከሁሉ አስቀድሜ በአጭር ጊዜ ተፀንሶ ፤ ተረግዞና ተወልዶ እንዲሁም ለአቅመ አዳም እድሜ ደርሶ በህዝባችን ላይ የጭቆና ቀንበር ተጭኖ የቆየውን እድሜ ጠገብ እና ጨቋኝ ስርዓት ለመገርሰስና በምትኩ ዘመኑን የዋጀ ትውልዱን የሚመጥን ፤ እኩልነትና ፍትሐዊነትን የዓላማው አልፋና ኦሜጋው አድርጎ ትግል የተነሳው የአማራ ፋኖ ብዙ ውስብውስብ እና ፈተኝ መንገዶችን በከፍተኛ ትግስት፤ እና አርቆ እሳቢነት በመፅናት ወጥ ድርጅት በመሰረትንበት ማግስት እንዲሁም ለአማራ የድል ብርሐን በፈነጠቀበትና በተቃራኒው በጠላቶቻችን ሰፈር የጨለማ ድባብና የሽንፈት መንፈስ በተዘራበት ወቅት ላይ በመመረቃችሁ የዛሬው የእናንተ ምርቃን በአይነቱም ሆነ በይዘቱ ልዩ ስለሆነ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ። ዛሬ ይህን ታላቅ ቀን ለመድረስ ያደረጋችሁትን ጥረት፣ ያቀረባችሁትን መስዋዕትነት፣ የተጋፈጣችሁትን ከባድ ስልጠናዎችና ውጣ ውረዶች ሁሉ ድርጅታችን በልዩ ክብር እውቅና እንሰጣለን። በሌሊት ተኝታችሁ ተነስታችሁ፣ በዝናብና በፀሐይ፣ በረሃብና በጥማት፣ በአካላዊና በአእምሮአዊ ጫና ሁሉ ተቋቁማችሁ ዛሬ የኮማንዶ ባልደረባ ማዕረግ የተቸራችሁ ሲሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ! እናንተ ዛሬ የተመረቃችሁት የአማራ ህዝብ የነፃነት በሮች የእናት ኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት ጠባቂዎች ናችሁ። የህዝባችን ነፃነት፤ ሰላምና ደህንነት በእጃችሁ ነው። የድንበራችን ደህንነት፣ የሀገራችን አንድነት፣ የዜጎቻችን ህይወት በእናንተ ብቃትና ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ ነው። ዛሬ የእናንተ ቀን ነው። የብዙ ወራት አድካሚ ስልጠና፣ የማይታመን ጽናት፣ ፍርሃት የሌለበት ልብ፤ የማይሸራረፍ ግብረ ገብነት፤ የማይናወጥ ታማኝነት፤ የማያፈገፍግ ቁርጠኝነት፤ የማይታጠፍ ጀግንነት፤ የማይወላውል የዓላማ ወጥነት ፤ የማይዝረከክ ሰራዊትነት፤ በዘረኝነትና በጎጠኝነት የማይርመጠመጥ በሳልነት፤ ወዘተ ሁሉም ዛሬ በዚህ መድረክ ላይ ፍሬያቸውን አፍርተዋል። ኮማንዶ መሆን ማለት ቀላል አይደለም። በባህሪው እና በተልእኮ ዝግጁነቱ፤ በስምሪት አሰላለፉ፤ በተግባር አፈፃፀሙ ለየት ያለ ቁመና ያለው ወታደራዊ አደረጃጀት ነው። ኮማንዶ ማለት ለቆመለትና ለተሰለፈለት ዓላማ ውድ እና መተኪያ የሌላትን ህይወቱን ለመስጠት ዝግጁ መሆን ማለት ነው። ኮማንዶ ማለት በጨለማ ውስጥ ብርሃን መሆን፣ በፍርሃት ውስጥ ደፍረትን መሆን፣ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ተስፋ መሆን ማለት ነው። እናንተ ዛሬ ያንን ቃል ኪዳን ገብታችኋል። የአማራ ህዝብ ብሎም መላው ኢትዮጵያውያን ነፃነቱ ያለው በእናንተ እጅ ነው። የልጆቻችን የወደፊት ተስፋ በአጠቃላይ የአዲሱ ትውልድ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በእናንተ እጅ ነው። ህዝባችን በአቅመ ቢሱ እና በልፍስፍሱ ስርዓት ጊዚያዊ የአፈና መዋቅር ውስጥ ሆኖ ዝም ያለ ቢመስልም እየተነፈሰ ያለው በእናንተ ሳንባ ነው። እየራበው ጠግቦ የሚያድረው በየቀኑ በሚመዘገቡ ጀብድና ድሎቻችን ነው፤ እየቆሰለ የሚያገግመው በየሰከንዱ በምናፈሳት ደምና ላባችን ነው። እየተፅናና ያለው በእኛ ጀግንነት ነው። ተስፋ አድርጎ እና ተማምኖ እየጠበቀ የሚገኘው የእኛ የትግል ግስጋሴ ነው። ልፍልስፍሱ የብልፅግና ስርዓት የቆመ የሚመስለው የአማራ ፋኖ የውስጥ መከፋፈልን እንደ ዋና እድል አድርጎ በመቁጠር ነበር፤ ጥንካሬውን እና ድክመቱን የሚለካው በእኛ አንድነትና መከፋፈል ነበር፤ ዛሬ የእኛ አንድነት በእሳት ተፈትኖ እንደ ወርቅ ነጥሮ ምርትና ገለባው ተለይቶ ፍንትው ብሎ ሲወጣ ምርቶ በዝቶ ገለባው አንሶ ሲያገኘው ሳይታዩ አብረው በቅለው የነበሩ ኢምንት እንክርዳዶችን ይዞ በድርድር ታርቂያለሁ እያለ ሲጮህ ህዝቡ አፉን በእጁ ይዞ እየተሳለቀባቸው ነው። የሚናገሩትን ፕሮፖጋንዳ እንኳን ለእኛ ለህፃናት የማይመጥን ነው በማለት ህዝቡ ንቀቱን እያሳያቸው ይገኛል። የቀነጨረ እና የጨነገፈ የፖለቲካ ስልትን ተጠቀምኩ እያለ አምስት የማይሞሉ እንክርዳዶች በሰሩት የባንዳነት ስራ አፍረውና ተሸማቀው ሞታችን ዛሬ ይሆን ነገ እያሉ በየጥሻው እንደ ፍልፈል ሲደበቁ ቆይተው ያገኟትን ቀዳዳ ተጠቅመው እጃቸውን ለምርኮ ፈቅደው ሲሰጡ ለብልፅግናም ለእነሱም እኩል የአፍረተቢስ ፕሮፖጋንዳን ለመጠቀም ተፍጨረጨሩ። የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ነን ባዮች ነገሩን በውል ሳይረዱ ውሸትን እንደ ፖሊሲ የሚከተለው ብልፅግና አደናግሯቸው ከተሰጣቸው ሃላፊነት ወርደው እንክርዳዶቹ ጋር ቆመው መታየታቸው የህብረቱን ሃላፊነት ጭምር ጥያቄ ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል። እኛም በእዚህ አጋጣሚ ለአፍሪካ ህብረትም ሆነ ለሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የምናስተላልፈው መልእክት ስራችሁን መሬት ላይ ካለው እውነት ጋር በትክክል መስማማቱን አረጋግጡ፤ አይቶ አልቃሽ አትሁኑ ፤ የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያን እንደ ሐገር ያቆመ እና እስከ አሁን ያቆየ፤ ለመላው አፍሪካ እና የዓለም ጥቁር ህዝቦች ኩራትና የሞራል ከፍታን ያረጋገጠ ፤ የቅኝ ገዥዎች የአለም መጨረሻ እቅዳቸውን በየዘመኑ እያሳፈረ ከዚህ የደረሰ እንደ ሚስማር ሲመቱት እየጠበቀ የሚቀጥል የአድዋ ድል ባለቤት ህዝብ ነው። ነገ የድል ጮራ ሲፈነጥቅ የአህጉሩን ጥቅሞችና መብቶችን በተመለከተ አብሮ ቆሞ የሚሟገተው የአማራ ፋኖ እንጅ አስመሳዩ ብስልፅግና ስርዓት አለመሆኑን ተረድታችሁ እውነት ላይ እንዲትቆሙ ጥሪ እናስተላልፍለን። ስለዚህ በአራቱም የአማራ ንፍቀ ክበብ ማለትም ጎንደር፤ጎጃም ወሎና ሸዋ መላው የህዝባችንን ነፃነት ለማረጋገጥ እየተዋደቀ ከሚገኘው ታሪካዊ ሰራዊታችን ጋር ስትቀላቀሉ የእናንተን የጋለ ስሜት ለወንድሞቻችሁና ለእህቶቻችሁ ተጨማሪ ሞራል እንዲሆን አስችሉ!!! ሁልጊዜ ብቃታችሁን አሳድጉ!!! ሁልጊዜም ዲሲፕሊናችሁን አትተዉ!!! ሁልጊዜም የቡድን መንፈስን ጠብቁ!!! ሁልጊዜም ለሀገርና ለህዝብ ብቻ ታማኝ ሁኑ!!! ሁልጊዜም በሁሉም ሁኔታ ክብርን ተጎናፀፉ!! የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች፣ የህዝባችን የብረት አጥሮች፣ የማትበገሩ ጀግኖች! የዛሬ ተመራቂ ልዩ ኮማንዶ አባላት በሙሉ እንኳን ለዚህ ታሪካዊ የምረቃ ቀን አደረሳችሁ። በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ። አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!! የካቲት 14/06/2018ዓ/ም

አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ታላቅ ጀብድ በመፈጸም ላይ ነው። የካቲት14/2018 ዓ.ም ከደብረ ታቦር  ወደ ክምር ድንጋይ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረን የአገዛዙ ሰራዊት በተራራው ራስ ጉና  ክፍለ ጦር  አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ነው። ከዲሽቃ እስከ ዙ-23 የታጠቀው የጠላት ኃይል ክምር ድንጋይን የቀመጫ ማኢከል ለማድረግ እና ንፋስ መውጫ ካለው ኃይል ጋር በጥምረት ቀጠናውን እቆጣጠራለው የሚል የህልም አለም ቅዠት ቢኖረውም  ሳይሳካለት እተቀጠቀጠ ይገኛል። ከጋሳይ እስከ ዘበራ ባለው የአውደ ውጊያ ውሎ  የጫነው ዙ -23 ከጥቅም ውጭ ሆኖበት ከ30 በላይ ሙት አስተናግዶ አስከሬኑን እያዝረከረከ በማፈግፈግ ላይ ነው። ቁጥሩ በውል ያልታወቀ ቁስለኛ  ደግሞ ወደ ደብረታ ቦር ሆስፒታል ሸኝቷል። እስካሁን ገቢ የሆኑ በምርኮዎች:- ## 1==ብሬን ## 1===m14 ## 15===ክላሽ ኮፕ በሌላኛው አውደ ውጊያ ደግሞ አፋብን ጎጠግዕ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ከንፋስ መውጫ ከተማ ተነስቶ  ወደ ክምር ድንጋይ ከደብረ ታቦር ለሚንቀሳቀሰው ኃይል ለመድረስ እና ሽፋን ለመስጠት ወደ  ጎብጎብ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ የጀግኖቹን ብርቱ ክንድ አስተናግዶ ሙትና ቁስለኛውን ታቅፎ  ወደ ተነሳበት ንፋስ መውጫ ከተማ መልሶ እንዲገባ ተደርጓል ። በዚህ አውደ ውጊያ ከፍተኛ ቀጠናዊ ትስስር የተጋመደበት ወታደራዊ ግዳጅ የነበር ሲሆን አንበሳው ጋይንት ክፍለ ጦር  መኳቢያ ፣ኡራኤል ፣ማደያ ፣ጣሪያ ጊዬዎርጊስ አካባቢ  ትንቅንቅ ሲያደርግ ገብርዬ ክፍለ ጦር ደግሞ ከየደሮ አቅጣጫ እና ክሬቸር አካባቢ የጠላትን ኃይል ከፍተኛ ኪሳራ እንዲያስተናግድ ሲያደርገው  በሌላኛው የአውደ ውጊያ ግንባር ደግሞ  አፋብን ወሎ ቤተ አማራ ሚኒሊክ ዕዝ ደጋው መብረቅ ኮር ከሦስት ክፍለ ጦር የተውጣጣ ኃይል እና ሌሎች በቀጠናው እሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት ደግሞ በአምባ ማርያም አቅጣጫ  የተናበበ ምትን አሳርፈውበት ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዷል ። በነዚህ የአውደ ውጊያ ግንባሮች:- ## ከ20 በላይ ክላሽ ኮፕ ## በርካታ የዲሽቃና የክላሽ ኳፕ ተተኳሾች ## 10 የሚሊሻ እና ፖሊስ ምርኮ ## ከ35 በላይ ሙት ## 55 ቁስለኛ ታቅፎ ንፋስ መውጫን የሙጥኝ ብሏል። ድል ለአማራ ፋኖ!!! ድል ለአማራ ህዝብ!!! የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ህዝብ ግንኙነት !!! የካቲት 14/ 2018 ዓ.ም