ru
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Открыть в Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Больше
3 279
Подписчики
+3924 часа
+3057 дней
+69830 дней
Архив постов
የፋኖን ብትር መቋቋም ያቀተው የብልፅግና ሰራዊት ንፁሀንን በይፋ ከቤት አውጥቶ ረሽኗል። ........................................... ሚያዚያ 07/2018 ዓ.ም በቀጥታ መዋጋት ያልቻለው የብልፅግና ሰራዊት እና የሰርአቱ አሽከሮች የበቀል ጥሙን የንፁሀንን ህይወት ከቤት በማውጣት እየቀጠፈ ይገኛል አገር ሰላም ነው ብለው ከቤታቸው ተቀምጠው የነበሩ ባል እና ሚስት እንዲሁም ልጃቸውን አንድ ቤት ውስጥ የነበሩትን አርሶአደሮች በአደባባይ የገደለ ሲሆን፦ 1.ታዴ ቢነጋ......ዕድሜ... 51....አባወራ 2.አንችኔ ዘለቀ....ዕድሜ .48..ሚስት 3.ምንታምር ታዴ .ዕድሜ ..22.ልጅ ሲሆኑ በሞጣ ሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ደብር ሚካኤል ቀበሌ ሚያዚያ 03/2018 ዓ.ም ጥቃቱ የተፈፀማቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪወች አስክሬናቸውን በማንሳት ስርአተ ቀብር እንዲፈፀም ተደርጎል። ስርአቱ አማራ ጠል ነው የምንለው በምክኒያት ነው ዛሬም አረመኔነቱን በይፋ አሳይቷል። የአፋብን ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ሰበር ዜና! ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ከተማን በከፊል በቁጥጥር ስር በማዋል ታላቅ ድል አስመዘገበ:: ምኒልክ ዕዝ 102ኛ ኮር በጥላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በራያ ቆቦ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎችንና የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና መቀመጫን ቆቦ ከተማን በከፊል ተቆጣጥሮ ውሏል። በተጨማሪም የ102ኛ ኮር እስከ ቆቦ ከተማ ዘልቆ በመግባት 105 የፌደራል ፖሊስና ከ250 በላይ የመከላከያ ሰራዊት ደምስሷል። ተወርዋሪዋ ልዩ ዘመቻ በቀይ አፈር በነበረው ተጋድሎ 89 የመከላከያ ሰራዊት ደምስሳለች። ጠላት ከጧት ጀምሮ በድሮን፣ በቢ-ኤም፣በዙ-23፣ በመድፍና በታንክ የተጠናከረ ማጥቃት ቢያደርግም አይበገሬዎቹን ማቆም ተስኖት ውሏል። የወገን ሀይል የ102ኛ ኮር እንድሁም ተወርዋሪ የሆነችው ልዩ ዘመቻ በጥምረት ባደረጉት ማጥቃት በሰሜን ወሎ ቆቦ ከተማን በከፊል በመቆጣጠር የአብይ አህመድን ስልጣን አስጠባቂ የፌደራል ፖለስና የመከላከያ ሰራዊት በከፍተኛ ደረጃ ተመትቶ ሙትና ቁስለኛውን በአንፑላን ወደ ቆቦ ሆስፒታል ሲያመላልስ ውሏል። በጧት የጀመረው ተጋድሎ በጥላት ላይ ወታደራዊና  ፖለቲካዊ የስበት ማዕከሉን በመለየት የ102ኛ ኮር በጮቢ በር የጥላትን ድሽቃ በወገን ሞርተር ሙሉ በሙሉ በማውደም፣ በካራይላና በጠዘጠዛ ካምፕ  በከፍተኛ ደረጃ እርምጃ የተወሰደበት ሲሆን በተወርዋሪዋ ልዩ ዘመቻ በቀይ አፈርና አባሆይ ጋሪያ በተመሳሳይ የወገን ጦር የሀይል የበላይነትን በመውሰድ ከላይ የተጠቀሱትን የገጠር ቀበሌዎችንና ከተሞች በቁጥጥር ስር አውሏል። በመጨረሻም የወገንን ሀይል መቋቋም ያቃተው የአብይ አህመድ ጨፍጫፊው አገዛዝ 01 ቆቦ ዙሪያ የቀመሌ ተክለሀይማኖት ቤተ-ክርስቲያንን ሆን ብሎ በመድፍ በመምታት እንድሁም የንፁህ አማራዎችን ቤት ታርጌት በማድረግ ፋኖን ለማስለቀቅ በሚል ስሌት የበርካታ ሲቪሊያንን ህይወት በከባድ መሳሪያ ቀጥፏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ሚያዚያ 7/2018 ዓ/ም

ምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ ራያ ቆቦ እና ጊዳን ወረዳ አቅራቢያ ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ:: የጊዳን ወረዳ መቀመጫ ከሆነችው ሙጃ ከተማ እና ከወንዳች በርካታ እግረኛ ሃይል እና ቢ ኤም 107 እና ዙ23 መካናይዝድ እንዲሁም በአየር ሃይል በሁለት ድሮኖች ታጅቦ ውጊያ የከፈተውን የፋሽስቱ ሰራዊት በሚገባ በመመከትና መልሶ ማጥቃት በማድረግ በርካታ የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ከባድ ሰብዓዊ ኪሳራ በማድረስ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::  የምኒልክ ዕዝ ልዩ ዘመቻ በቀይ አፈር በነበረው ተጋድሎ 89 በላይ የሚሆን የ61ኛ ክፍለ ጦር የመከላከያ ሰራዊት ደምስሳለች። ጠላት ከጧት ጀምሮ በድሮን፣ በቢኤም፣በዙ23፣ እንዲሁም በመድፍ የተጠናከረ ማጥቃት ቢያደርግም አይበገሬዎቹን ማቆም ተስኖት ውሏል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 7/2018 ዓ/ም

የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አካል የሆነው የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አሃዶች በአይዞሽ አሞራ ተራራማዎች ላይ ባደረጉት የተቀናጀ ውጊያ በርካታ የአገዛዙ አየር ወለድ ክፍለጦር አባላት ሙትና ቁስለኛ ማድረጋቸውን ኮሩ በግንባር መረጃው ገለፀ። ሚያዚያ 07/2018ዓ.ም የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አካል የሆኑት ከራንቦ ክፍለጦርና ከ7ለ70 ክፍለጦር በተወጣጡ ውስን ሻለቆች በተደረገ የቅንጅት የጨበጣ ውጊያ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የአገዛዙ ሰራዊት ከጥቅም ውጭ ማድረጉን ኮሩ አረጋግጧል። ጠላት መነሻውን ከደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር፣ ከጉዶበረት እና ከቀይት ከተማ በማድረግ በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ስር በሚገኘው ወደ ባሶና ወረና ወረዳ ልዩ ቦታው አይዞሽ አሞራ በተባለ አካባቢ በሞርተርና ዙ-23 ታጅቦ በድሮን እየጨፈጨፈው የሚገኘውን የአማራ ህዝብ በሀይል የምርጫ ካርድ ለማሰራጨት ከንጋቱ 12:00 ላይ በማቅናት ላይ እያለ በጀግናው ሰራዊታችን በተፈፀመበት ጥቃት በርካታ የብልፅግናው ሰራዊት ከጥቅም ውጭ ሆኗል። በደፈጣ ጥቃት የተጀመረው ውጊያ ወደ ጨበጣ ውጊያ ተቀይሮ ጀግናው የአማራ ፋኖ በአገዛዙ የቀይ ቦኔት ለባሽ ላይ በተጎናፀፈው ድል በሁለት (2) አንቡላንሶች የጠላትን አስክሬንና ቁስለኛውን ወደ ደብረብርሀን ከተማ ሲያመላልስ ውሏል። ይሕ ዜና እስከተጠናቀረበት እኩለ ቀን ድረስ በአይዞሽ አማራና አካባቢው አድማሱን ያሰፋው ውጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉን ኮሩ የገለፀ ሲሆን ጠላት በደረሰበት ከፍተኛ ምት በመደናገጥ በዘፈቀደ የሞርተር ቅንቡላ ወደ ማህበረሰቡ እየወረወረ ይገኛል። በተመሳሳይ ዜና በትላንትናው ዕለት የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የአጼ ዘር ዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለጦር ከደብረብረሀን ከተማ ቅርብ ርቀት ላይ ከኩኬለሽ እስከ በዞ ድርሰ በነበረው አውደ ውጊያ ክፉኛ የተመታው የጠላት ሀይል እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ ሙት እና ቁስለኛውን እየሰበሰበ ሲሆን በተያያዘ ዜና ናደው ክፍለጦር በመራቤቴ ቀጠና ባደረገው መጠነ ሰፊ የማጥቃት ዘመቻ ክፉኛ የተመታው ጠላት የበቀል እርምጃውን ዛሬም በ107 እና ሞርታር ተራራዎችን እየደበደበ ይገኛል ሲል የአፄ ዘር ዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር አስታውቋል።        ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''     ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ      ሚያዚያ 07/2018ዓ.ም

ሰበር ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ዐፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኘው ብርቱው ነጎድጓድ ክፍለ ጦር፣ ከማለዳው የፀሐይ መውጣት ጀምሮ የብልፅግናን ጦር አይቀጡ ቅጣት እየቀጣው ይገኛል። ​​ለ
+2
ሰበር ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ዐፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኘው ብርቱው ነጎድጓድ ክፍለ ጦር፣ ከማለዳው የፀሐይ መውጣት ጀምሮ የብልፅግናን ጦር አይቀጡ ቅጣት እየቀጣው ይገኛል። ​​ለመውደቅ "አንድ ሐሙስ" ብቻ እንደቀረው የሚነገረው የብልፅግና አገዛዝ፣ በዛሬው ዕለት የመጨረሻ ያለውን ኃይል አስተባብሮ ወጥቷል። በሻለቃ እሬና የሚመራውና ከደብረ ብርሃን ከተማ "አለኝ" የሚለውን ኃይል የኮማንዶ ክፍለ ጦርን፣ የአድማ ብተናንና ሚሊሻን አጣምሮ የያዘው ይህ ጦር በፋኖ ብርቱ ክንድ እየተገረፈ የሚገኝ ሲሆን ​የውጊያው ድባብና ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ለመያዝ ያሰበ የአገዛዙ ሰራዊት ሽንፈትን እያስተናገደ ይገኛል። ይህ አውደ ​ውጊያ ትላንት ማለዳ በ2:30 ላይ የጀመረ ሲሆን፣ እንደ እሳተ ገሞራ እየተፋፋመ እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ ቀጥሏል። ውጊያው የተደረገባቸው ቀጠናዎች ከኩኬለሽ እስከ ዘንዶጉር የተዘረጉ ሲሆን፣ የጠላት ጦር ዋና ፍላጎት "በዞ" የተባለውን ቀበሌ በቁጥጥሩ ስር ለማዋል ነበር። ሆኖም ግን የነጎድጓድ ክፍለ ጦር ተዋጊዎች የቀጠና ድንበር የጠላት መቃብር በማድረግ አድማሱን እያስከበሩ ይገኛሉ። ይህ አራዊት ሰራዊት በጀግኖቹ የዐፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ኛ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ብርቱ ክንድ እየተደቆሰ ፊት መቆም አቅቶት በመፈራረስ ላይ ከመሆኑም በላይ የሸዋ ምድር በጀግኖች ድምፅ እየተናወጠች የአማራ የመኖር ነፃነት ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አርበኛ አማረ ታዘዘ ሚያዝያ 07/08/2018 ዓ.ም

የጥንቃቄ መረጃ‼️ የሜጀር ጀኔራል ውባንተ 1ኛ ኮር ቀጠና ጠላት ከወረዳ ከተማዎች እየወጣ አፈና ከበባ ለመፈጸም እያቀደ ይገኛል።በመጀመሪያ እቅዱ ጉና ክፍለጦር ጠንካራዋ እስቴ ዴንሳ ብርጌድን ለመክበብ ማቀዱ ታውቋል። የወትሮ ዝግጁነት አይለያቹህ‼️                  ድል ለአማራ ፋኖ!

ከአባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት የተሰማ የፖለቲካ እስረኞች የድረሱልን ጥሪ፡ "ምግብና ውሃ ተከልክለናል" መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቂሊንጦ ወደ አባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት የተዛወሩ የአማራ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች፣ በማረሚያ ቤቱ እየተፈጸመባቸው ያለውን "ኢ-ሰብአዊ አያያዝ" በመቃወም ዛሬ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ። እስረኞቹ በችሎት ፊት ባሰሙት አቤቱታ፣ መሠረታዊ የሆኑት የምግብ፣ የንጹህ ውሃ እና የሕክምና አገልግሎቶች በመከልከላቸው ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውን ገልጸዋል። በተለይም ማረሚያ ቤቱ የሚሰጠው ምግብ ለፍርደኞች (ቅጣት ለተወሰነባቸው) ብቻ ተብሎ የተዘጋጀ መሆኑንና እስረኞች በራሳቸው ወጪ እንኳን ምግብ ገዝተው እንዳይመገቡ መታገዳቸውን አስረድተዋል። ቤተሰብ እንደ በሶ ያሉ ምግቦችንና አልባሳትን እንዳያስገባላቸው መከልከሉ ለከፍተኛ ረሃብና ለጤና መታወክ እንደዳረጋቸው በአጽንኦት ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የታሰሩበት "ዞን አራት" ቀደም ሲል ለከፍተኛ የዲስፕሊን ቅጣት ተብሎ የተለየ ክፍል መሆኑን የጠቀሱት እስረኞቹ፣ የውሃ አቅርቦት በቀን ለ15 ደቂቃ ብቻ በመገደቡ የግልና የአካባቢ ንጽህናን ለመጠበቅ እንዳልተቻለ ገልጸዋል። የመጸዳጃ ቤቶች መሙላትና የፍሳሽ ቆሻሻ በየክፍሉ ወለል ላይ መፍሰስ በፈጠረው ጠረን ለተላላፊ በሽታዎች እየተጋለጡ መሆኑንና በማረሚያ ቤቱ ያለው የሕክምና አገልግሎትም እጅግ ደካማ እንደሆነ አመልክተዋል። በተጨማሪም ክፍሉ ምንም ዓይነት የቤተ-መጻሕፍትም ሆነ የቴሌቪዥን አገልግሎት እንደሌለው ተገልጿል። የሕግ ባለሙያዎች እንደሚገልጹት፣ ገና ጥፋተኝነታቸው ባልተረጋገጠ "የቀጠሮ እስረኞች" እና ፍርድ ባረፈባቸው "ታራሚዎች" መካከል ግልጽ የሆነ የቦታና የአያያዝ ልዩነት ሊኖር ይገባል። ሆኖም በአባ ሳሙኤል የሚገኙት እነዚህ የአማራ የሕሊና እስረኞች፣ ከባድ ወንጀል ፈጽመው የረጅም ጊዜ እስራት ከተፈረደባቸው ግለሰቦች ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸው ለደህንነታቸው ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ለችሎቱ አስታውቀዋል።

የሙጎጉቱ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በአገዛዙ ሠራዊት በመድፍ ተመታ! (ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም - ኢትዮ 251 ሚዲያ) ከመካነሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘውና በቅርቡ የተመሰረተው የሙጎጉቱ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፣ በአገዛዙ 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ ምድብተኞች በተተኮሰ መድፍ መመታቱን የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ አስታወቀ። በመካነሰላም ከተማ "አሜጃ" በተባለ ስፍራ ላይ መድፍ አጥምዶ ወደ ገዳሙ በተደጋጋሚ ሲተኩስ የዋለው የጠላት ኃይል፣ በፈጸመው ጥቃት የገዳሙ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ጣራ በመድፉ ፍንጣሪ እንዲበሳሳ አድርጓል። ይህ አረመኔያዊ ጥቃት በሃይማኖት ተቋሙ ላይ ካደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በንጹሐን ዜጎች ላይም ከባድ ሰብዓዊ ጥፋት አስከትሏል። እንደ ዕዙ መረጃ ከሆነ፣ በመድፍ ጥቃቱ ሳቢያ ሁለት ንጹሐን ሰዎች ክፉኛ የቆሰሉ ሲሆን፣ ከቆሰሉት መካከል አንዱ በደረሰበት ከባድ ጉዳት ምክንያት የመትረፍ ዕድሉ አነስተኛ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል። የገዳሙ አካባቢ ነዋሪዎች በበኩላቸው የአገዛዙ ሠራዊት የሃይማኖት ተቋማትን እንደፈለገ ለወታደራዊ ምሽግነት እንደሚጠቀም፣ ካልሆነም ደግሞ ታርጌት አድርጎ በመምታት ሕንፃዎችን እንደሚያፈርስ በመጥቀስ ድርጊቱን በጽኑ አውግዘዋል። ምኒሊክ ዕዝ የአገዛዙ ሠራዊት በንጹሐንና በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚፈጽመው ይህ ዓይነቱ ጥቃት የሽንፈቱ ማሳያ መሆኑን ገልጾ፣ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

+3
በአንዱ የባንክ አካውንቱ ውስጥ ብቻ 17 ሚሊዮን ብር አለ። ስራው #አምቦ ከተማ ውስጥ እየዞረ በጉልበት ገንዘብ መሰብሰብ ነው። የአምቦ ከንቲባ የቅርብ ጓደኛ ነው። በጋራ ነው የሚሰሩትን ገንዘብ የሚካፈሉት። ዛሬ አብረው እንደነበሩ መረጃ አለ። ይህ ጨካኝ ማፊያ ከዚህ በፊት አንድ ሴት ልጅ አስገ ድዶ ከደፈረ በኃላ በጩቤ ወግቶ ገድ ሏ ታል። በፖሊስ ተይዞ ምንም ሳይጠየቅ ነው የተለቀቀው። ከዚህም የባሱ ዘንግናኝ ወንጀል የፈፀመ ነው። የተጠናከረ ማስረጃ በተከታታይ ይቀርባል። #ብልፄ ሀገሪቷን የማፊያዎች ፣ የወንጀለኞች ፣ ያሻቸውን በሚፈፅሙ ቡድኖች አዋቅሯታል። በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተደራጁ ለብልፄ ሽፋን የሚሰጡ ፣ በባለስልጣናት የሚደገፉ ፣ የዘረፋ ስኳዶች አሉ። የሁሉም በዝርዝር ይቀርባል። ህዝቡ ከዚህ በኃላ ይህንን የግፍ አገዛዝ #እምቢ ማለት አለበት። ከዚህ በላይ ምንም የሚመጣ ግፍና ጭካኔ የለም። በባለስልጣናትም በሰፈር ጋንግስተሮችም እጅ መስጠት ይብቃ ሸር ሸር

ከሌሊቱ 5:45 በደብረ ማርቆስ ከተማ እነማይ ሆቴል ፊት ለፊት የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በፈፀመው የቦምብ ጥቃት 5 አድማ ብተና አባላት ህይወታቸውን አጠዋል። ሚያዚያ 6 2018 ዓ.ም ======================================= የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት ከሌሊቱ 5:45 ከተማዋን በም/ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ፓትሮል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 9 የአድማ ብተና አባላት የጥቃቱ ሰለባ ሲሆኑ 5 ( አምስት) የሚሆኑት ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ ቀሪ 4 (አራት) የሚሆኑት ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል። የሰሌዳ ቁጥር 04251 (4) ንብረትነቷ የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ መምሪያ በሆነች ፓትሮል ተጭነው ሲንቀሳቀሱ ጥቃት የተፈፀመባቸው የአድማ ብተና አባላት የምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ዙሪያ ጥበቃ የሚያደርጉ መሆናቸውም ታውቋል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ሰበር ዜና አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተለያዩ ግንባሮች ድልን ተቀዳጀ።               ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያቆብ  ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር የአብይ አህመድ አገዛዝ ጅምላ ተጋላቢ አየር ወለድ ኮማንዶ ሀይሉን  ከተለያዩ የቡድን መሳሪያ ጋጋታ ጋር ማለትም ዙ *23 መቶ ሰባት ብዛት ያለው ዲሽቃና ሞርተር ከሁሉም አካባቢ ቀራርሞ በማምጣት  በሆድ አደር ሚሊሻ መንገድ መሪነት  በሸዋ ክፍለ ሐገር መርሓቤቴ አዉራጃ ታች ቤት ቀበሌ ፋኖ አለበት ወደተባለበት ቀጣና ከለሊቱ 9:30  ከዋና ከተማው መቀመጫ አለም ከተማ እና ፌጥራ ተጠራርቶ  ጨለማን ተገን አድርጎ በሶስት አቅጣጫ ማለትም በቡዮላይ ፣በሸፈሬ አንባ  እና በጮሬ ቀበሌ" በማድረግ  ወደ ጎራንዳ ከበባ ለማድረግና ለማጥቃት አቅዶ የገባው ሀይል የመርሐቤቴን ገደላገደልና አቀበት እንደ ሜዳ እየረገጡ፣ "ከፊታችን ሞት ቢኖርም ከኋላችን ታሪክ አለ" በሚል ወኔ የጠላትን ምሽግ የሚሰባብሩት የናደው ክፍለጦር ተርብ ተዋጊዎች፤ በፍጥነት ከበባውን በመክበብ ዕለታዊ ውሏቸው በባሩድ ጢስ ውስጥ የተጻፈ የጀግንነት ታሪክ አድርገውታል።    ናደው ክፍለ ጦርን እደመስሳለሁ ብሎ የመጣው የጠላት ሀይልም በእነ ሞት አይፈሬ  ነፃነት ክብራቸው  ክፉኛ ያልጠበቀው ጉዳት ደርሶበታል።የናደው ክፍለ ጦር ምክትል  ጦር አዛዥ  ቀኝ አዝማች አቡ አሳምረው የተመራው የዕለቱ ውጊያም የውጊያ ጥበብ እና  ብስለት በተሞላበት አውደ ውጊያ  ናደው ክፍለ ጦር ድል ማድረግ ችሏል።  ከናደው ክፍለ ጦር  ከሁሉም  ሻለቆች በተወጣጡ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ የመጣውን የጠላት ሀይል ሁሉንም አይነት አለኝ የሚለውን ስልትና ብቃቱን ለመጠቀም የሞከረ ቢሆንም ፤  ከሌሊቱ 9:30 የተጀመረ ውጊያ እስከ ቀኑ 10:00 ድርስ የነበረ ቢሆንም በወገን የስነ ልቦና  እና  የውጊያ የበላይነት በጠበቀ መልኩ  ሲያጪዱት ውለዋል።     በእዚህ አውደ ውጊያ  በጠላት ላይ  የደረሰው ጉዳት በዝርዝር እንደሚከተለው እንገልፃለን። 👉1ኛ,  አንድ ሲኖ መኪና ሙሉ የጠላት ሀይል ከእነ ተሽከርካሪዉ  በልዩ ኦፕሬሽን ልዩ ስሙ ቡዮ የተባለው ቦታ ላይ  መደምሰስ ተችሏል። 👉2ኛ. ሻንበል አመራሮችን ጨምሮ የተደመሰሰ የጠላት ሀይል 32 👉3ኛ,ከባድ ቁስለኛ 09  👉4ኛ,ቀላል ቁስለኛ  17 👉5ኛ,ቀንደኛ መንገድ መሪ ሚሊሻ 04 መደምሰስ ተችሏል። በእዚህ አውደ ወጊያ ከፍተኛ ኪሳራ ያስተናገደው ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ስራዓት ሽንፈቱን ሲከናነብ የተለመደውን  ዘግናኝ ድርጊቱን  ምንም  በማያውቁ ገበሬ እና የፋሲካ በአልን ምክንያት በማድረግ  ለማክበር  እና ሰርግ ላይ የተሰበሰቡ  ንፁሃኖችን  የበደል ብትሮችን በማሳረፍ እና ንፁሃን አርሶ አደሮችን  እየቀጠቀጠ ለፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያነት  ይዞ ሄዷል።    በእዚሁ አውደ ውጊያ  የተሸነፈው የአገዛዙ ጅምላ ተጋላቢ ሀይል የፋኖን ምት መቋቋም አቅቶት አስከሬኑን እያዝረከረከ በመፈርጠጥ ወደመጣበት ተመልሷል ። በሌላ የዕለቱ ዜና አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር የ7ተኛ ሃገር አቀፍ ምርጫ ካርድ በቁጥጥር ስር አውለውታል!!!! አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ጀግኖቹ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር 4ተኛ ሻለቃ ቃኘዎች በብልፅግና ጥምር ጦር የሚመራው የማጭበርበሪያ የ7ተኛ ሃገር አቀፍ የውሸት ምርጫ ካርድ በባሶና ወረና ወረዳ በደበሌና እሮብ  ገበያ ቀበሌ ህዝብን በግዳጅ የምርጫ ካርድ ለማስወጣት ሲሞክር የፋኖን ብትር መቋቋም ሲያቅተው ይዞት የመጣውን በርካታ የምርጫ ካርድ እያዝረከረከ እና አስማርኮ ወደ መጣበት ደብረ ብርሃን የእፈረጠጠ ተመልሷል። የመረጃ ምንጭ-አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን       ክብር ለተሰውት       ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

ከሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመካነሰላም ግንባር ከምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ጋር በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ የከፈተው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናገደ! ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ተጋድሎ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ድል ቀንቶታል:: የጠላት ኃይል ቁስለኛ እና አስከሬን በአምቡላንስ ጭኖ ወደ መካነሰላም አቅንቷል:: 11ኛ ዕዝ ከመሐል ሳይንት እና አማራ ሳይንት ወረዳዎች ጭምር ሰራዊቱን ወደ መካነሰላም አጓጉዞ መካነሰላም ለሚገኘው ፀረ ህዝብ ኃይል ድጋፍ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርግም ኦፕሬሽኑ በእነ ሞት አይፈሬ ብርታት ከሽፏል:: በዚህም የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት በተለምዶ አደሬ ቆቦ የተባለች ቦታ ላይ በትናንትናው ዕለት ክፉኛ የተመታ ሲሆን ሽንፈቱን ለማካካስ በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ መድፍ እና ሞርተር ወደ ገበሬዎች መንደር በመተኮስ በንፁሀን ላይ ጉዳት አድርሷል:: ትናንት አንድት እናት በሞርተር ተመታ ክፉኛ ቆስላ በህክምና ላይ እንደምትገኝ ተረጋግጧል:: ዛሬ ደግሞ አንድ ንፁህ ገበሬ በመድፍ ተመቷል:: መትረፍ እንደማይችልም ነው የህክምና ውጤቱ የሚያስረዳው:: ጠላት በተደጋጋሚ መድፍ ጭምር የተኮሰ ሲሆን ቢሊ ታዳጊ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የሙጎጉቱ ገብርኤል ገዳምን ህንፃ ቤተክርስቲያን ጣራ አውድሞታል:: የጠላት ኃይል የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር  ሰራዊትን ጥሶ አልፎ ቢሊ ታዳጊ ከተማን የመቆጣጠርና ለቀጣዩ ወር ምርጫ ቅድመ ዝግጅት የማድረግ እቅድ አቅዶ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ታዳጊ ከተማዋ ሳይደርስ በትናምትናው እለት መንገድ ላይ ተቀጥቅጦ የተመለሰ ሲሆን በዛሬው እለት ተመልሶ በመድፍ እና ሞርተር የከተማይቱን ነዋሪዎች ሲደበድብ ውሏል::  ጠላት የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ መግባቱን የሚያረጋግጥ ክስተት የተፈጠረ ሲሆን በዚህም የ87ኛ ክፍለ ጦር አመራር የሆነ 10 አለቃ ምስጋን የተባለ ወታደር እና ሌላ ጓዱ በበቃኝ ከጠላት ከድተው የወገን ኃይልን ተቀላቅለዋል:: አንድ 50 አለቃም የጠላት ኃይልን ከድቶ አድራሻውን አጥፍቷል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም

አጀብ የሚያስብል ድል አለን ሸር ሸር ሸር ሸር ከንጉሶች መንደር!!
አጀብ የሚያስብል ድል አለን ሸር ሸር ሸር ሸር ከንጉሶች መንደር!!

ከሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመካነሰላም ግንባር ከምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ጋር በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ የከፈተው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናገደ! ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ተጋድሎ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ድል ቀንቶታል:: የጠላት ኃይል ቁስለኛ እና አስከሬን በአምቡላንስ ጭኖ ወደ መካነሰላም አቅንቷል:: 11ኛ ዕዝ ከመሐል ሳይንት እና አማራ ሳይንት ወረዳዎች ጭምር ሰራዊቱን ወደ መካነሰላም አጓጉዞ መካነሰላም ለሚገኘው ፀረ ህዝብ ኃይል ድጋፍ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርግም ኦፕሬሽኑ በእነ ሞት አይፈሬ ብርታት ከሽፏል:: በዚህም የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት በተለምዶ አደሬ ቆቦ የተባለች ቦታ ላይ በትናንትናው ዕለት ክፉኛ የተመታ ሲሆን ሽንፈቱን ለማካካስ በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ መድፍ እና ሞርተር ወደ ገበሬዎች መንደር በመተኮስ በንፁሀን ላይ ጉዳት አድርሷል:: ትናንት አንድት እናት በሞርተር ተመታ ክፉኛ ቆስላ በህክምና ላይ እንደምትገኝ ተረጋግጧል:: ዛሬ ደግሞ አንድ ንፁህ ገበሬ በመድፍ ተመቷል:: መትረፍ እንደማይችልም ነው የህክምና ውጤቱ የሚያስረዳው:: ጠላት በተደጋጋሚ መድፍ ጭምር የተኮሰ ሲሆን ቢሊ ታዳጊ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የሙጎጉቱ ገብርኤል ገዳምን ህንፃ ቤተክርስቲያን ጣራ አውድሞታል:: የጠላት ኃይል የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር  ሰራዊትን ጥሶ አልፎ ቢሊ ታዳጊ ከተማን የመቆጣጠርና ለቀጣዩ ወር ምርጫ ቅድመ ዝግጅት የማድረግ እቅድ አቅዶ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ታዳጊ ከተማዋ ሳይደርስ በትናምትናው እለት መንገድ ላይ ተቀጥቅጦ የተመለሰ ሲሆን በዛሬው እለት ተመልሶ በመድፍ እና ሞርተር የከተማይቱን ነዋሪዎች ሲደበድብ ውሏል::  ጠላት የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ መግባቱን የሚያረጋግጥ ክስተት የተፈጠረ ሲሆን በዚህም የ87ኛ ክፍለ ጦር አመራር የሆነ 10 አለቃ ምስጋን የተባለ ወታደር እና ሌላ ጓዱ በበቃኝ ከጠላት ከድተው የወገን ኃይልን ተቀላቅለዋል:: አንድ 50 አለቃም የጠላት ኃይልን ከድቶ አድራሻውን አጥፍቷል:: ©ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!

‼️አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ⚠️ --ለአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ! በጎንቻ ወረዳና ግንደወይን አካባቢ የምትንቀሳቀሱ የወገን ጦር አመራርና አባላት እንቅስቃሴውን እና ወታደራዊ መረጃዎችን ጠላት ከውስጥ ባስቀመጣቸው #ኦፒዎች አማካኝነት መረጃ ስለደረሰው አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ማሳሰብ እወዳለሁ ‼️

በየዕዱውኃ ከተማ የሚገኘው ቅጥረኛ ሚሊሻ ወ/ሪት ፈንታነሽ አባቡ እና አቶ አባቡ ካስየ የተባሉ ልጅ እና አባት በግፍ እረሽኖል። 64ኛ ክ/ጦር ማያዚያ 06/2018 ዓ.ም በአማራ ህዝብ ላይ በረካታ ግ
በየዕዱውኃ ከተማ የሚገኘው ቅጥረኛ ሚሊሻ ወ/ሪት ፈንታነሽ አባቡ እና አቶ አባቡ ካስየ የተባሉ ልጅ እና አባት በግፍ እረሽኖል። 64ኛ ክ/ጦር ማያዚያ 06/2018 ዓ.ም በአማራ ህዝብ ላይ በረካታ ግፎችን እየፈፀመ የሚገኘው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት ልጅ እና አባት በግፍ እረሽኖል። ሚያዚያ 05/2018 ዓ.ም በየዕዱውኃ ከተማ ቁርስ ቤት የምትሰራ ወ/ሪት ፈንታነሽ አባቡ አፈቀርኩሽ በማለት ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ አባቷን አቶ አባቡን ጨምሮ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ልጆ ከአባቷ ጋር በግፍ ተረሽነዋል። በአስገዳጅ ሁኔታ የፍቅር ጥያቄ ትቀበይኛለሽ በማለት እርምጃ የወሰደው የአገዛዙ ቅጥርኛ ሚሊሻ #ካስየ  ወዲያውኑ በመከላከያ ኃይል ተረሽኖ በየዕዱውሃ ከተማ መነኃሪያ ላይ አስከሬኑ ወድቆ ማደሩን ተረጋግጦል። የአገዛዙ ኃይል አረመኔዊ እና ጨቋኝ መሆኑን የምንናገረው በምክንያት ነው በየዕድውኃ ከተማ የተረሸኑቱ አይነ ስውር እና በድህነት ውስጥ ሆነው ህይወትይ ለመምራት የሚደክሙ ንፁሃን መሆናቸውን አረጋግጠናል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!             ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ