ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
前往频道在 Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
显示更多3 260
订阅者
+2224 小时
+2707 天
+65730 天
帖子存档
ከአባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት የተሰማ የፖለቲካ እስረኞች የድረሱልን ጥሪ፡ "ምግብና ውሃ ተከልክለናል"
መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቂሊንጦ ወደ አባ ሳሙኤል ማረሚያ ቤት የተዛወሩ የአማራ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች፣ በማረሚያ ቤቱ እየተፈጸመባቸው ያለውን "ኢ-ሰብአዊ አያያዝ" በመቃወም ዛሬ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ።
እስረኞቹ በችሎት ፊት ባሰሙት አቤቱታ፣ መሠረታዊ የሆኑት የምግብ፣ የንጹህ ውሃ እና የሕክምና አገልግሎቶች በመከልከላቸው ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸውን ገልጸዋል። በተለይም ማረሚያ ቤቱ የሚሰጠው ምግብ ለፍርደኞች (ቅጣት ለተወሰነባቸው) ብቻ ተብሎ የተዘጋጀ መሆኑንና እስረኞች በራሳቸው ወጪ እንኳን ምግብ ገዝተው እንዳይመገቡ መታገዳቸውን አስረድተዋል። ቤተሰብ እንደ በሶ ያሉ ምግቦችንና አልባሳትን እንዳያስገባላቸው መከልከሉ ለከፍተኛ ረሃብና ለጤና መታወክ እንደዳረጋቸው በአጽንኦት ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት የታሰሩበት "ዞን አራት" ቀደም ሲል ለከፍተኛ የዲስፕሊን ቅጣት ተብሎ የተለየ ክፍል መሆኑን የጠቀሱት እስረኞቹ፣ የውሃ አቅርቦት በቀን ለ15 ደቂቃ ብቻ በመገደቡ የግልና የአካባቢ ንጽህናን ለመጠበቅ እንዳልተቻለ ገልጸዋል። የመጸዳጃ ቤቶች መሙላትና የፍሳሽ ቆሻሻ በየክፍሉ ወለል ላይ መፍሰስ በፈጠረው ጠረን ለተላላፊ በሽታዎች እየተጋለጡ መሆኑንና በማረሚያ ቤቱ ያለው የሕክምና አገልግሎትም እጅግ ደካማ እንደሆነ አመልክተዋል። በተጨማሪም ክፍሉ ምንም ዓይነት የቤተ-መጻሕፍትም ሆነ የቴሌቪዥን አገልግሎት እንደሌለው ተገልጿል።
የሕግ ባለሙያዎች እንደሚገልጹት፣ ገና ጥፋተኝነታቸው ባልተረጋገጠ "የቀጠሮ እስረኞች" እና ፍርድ ባረፈባቸው "ታራሚዎች" መካከል ግልጽ የሆነ የቦታና የአያያዝ ልዩነት ሊኖር ይገባል። ሆኖም በአባ ሳሙኤል የሚገኙት እነዚህ የአማራ የሕሊና እስረኞች፣ ከባድ ወንጀል ፈጽመው የረጅም ጊዜ እስራት ከተፈረደባቸው ግለሰቦች ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጋቸው ለደህንነታቸው ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ለችሎቱ አስታውቀዋል።
የሙጎጉቱ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በአገዛዙ ሠራዊት በመድፍ ተመታ!
(ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም - ኢትዮ 251 ሚዲያ)
ከመካነሰላም ከተማ በቅርብ ርቀት የሚገኘውና በቅርቡ የተመሰረተው የሙጎጉቱ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፣ በአገዛዙ 11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ ምድብተኞች በተተኮሰ መድፍ መመታቱን የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ አስታወቀ።
በመካነሰላም ከተማ "አሜጃ" በተባለ ስፍራ ላይ መድፍ አጥምዶ ወደ ገዳሙ በተደጋጋሚ ሲተኩስ የዋለው የጠላት ኃይል፣ በፈጸመው ጥቃት የገዳሙ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ጣራ በመድፉ ፍንጣሪ እንዲበሳሳ አድርጓል።
ይህ አረመኔያዊ ጥቃት በሃይማኖት ተቋሙ ላይ ካደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በንጹሐን ዜጎች ላይም ከባድ ሰብዓዊ ጥፋት አስከትሏል።
እንደ ዕዙ መረጃ ከሆነ፣ በመድፍ ጥቃቱ ሳቢያ ሁለት ንጹሐን ሰዎች ክፉኛ የቆሰሉ ሲሆን፣ ከቆሰሉት መካከል አንዱ በደረሰበት ከባድ ጉዳት ምክንያት የመትረፍ ዕድሉ አነስተኛ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል።
የገዳሙ አካባቢ ነዋሪዎች በበኩላቸው የአገዛዙ ሠራዊት የሃይማኖት ተቋማትን እንደፈለገ ለወታደራዊ ምሽግነት እንደሚጠቀም፣ ካልሆነም ደግሞ ታርጌት አድርጎ በመምታት ሕንፃዎችን እንደሚያፈርስ በመጥቀስ ድርጊቱን በጽኑ አውግዘዋል።
ምኒሊክ ዕዝ የአገዛዙ ሠራዊት በንጹሐንና በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚፈጽመው ይህ ዓይነቱ ጥቃት የሽንፈቱ ማሳያ መሆኑን ገልጾ፣ መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
በአንዱ የባንክ አካውንቱ ውስጥ ብቻ 17 ሚሊዮን ብር አለ። ስራው #አምቦ ከተማ ውስጥ እየዞረ በጉልበት ገንዘብ መሰብሰብ ነው። የአምቦ ከንቲባ የቅርብ ጓደኛ ነው። በጋራ ነው የሚሰሩትን ገንዘብ የሚካፈሉት። ዛሬ አብረው እንደነበሩ መረጃ አለ።
ይህ ጨካኝ ማፊያ ከዚህ በፊት አንድ ሴት ልጅ አስገ ድዶ ከደፈረ በኃላ በጩቤ ወግቶ ገድ ሏ ታል። በፖሊስ ተይዞ ምንም ሳይጠየቅ ነው የተለቀቀው። ከዚህም የባሱ ዘንግናኝ ወንጀል የፈፀመ ነው። የተጠናከረ ማስረጃ በተከታታይ ይቀርባል።
#ብልፄ ሀገሪቷን የማፊያዎች ፣ የወንጀለኞች ፣ ያሻቸውን በሚፈፅሙ ቡድኖች አዋቅሯታል። በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች የተደራጁ ለብልፄ ሽፋን የሚሰጡ ፣ በባለስልጣናት የሚደገፉ ፣ የዘረፋ ስኳዶች አሉ። የሁሉም በዝርዝር ይቀርባል።
ህዝቡ ከዚህ በኃላ ይህንን የግፍ አገዛዝ #እምቢ ማለት አለበት። ከዚህ በላይ ምንም የሚመጣ ግፍና ጭካኔ የለም። በባለስልጣናትም በሰፈር ጋንግስተሮችም እጅ መስጠት ይብቃ ሸር ሸር
ከሌሊቱ 5:45 በደብረ ማርቆስ ከተማ እነማይ ሆቴል ፊት ለፊት የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በፈፀመው የቦምብ ጥቃት 5 አድማ ብተና አባላት ህይወታቸውን አጠዋል።
ሚያዚያ 6 2018 ዓ.ም
=======================================
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት ከሌሊቱ 5:45 ከተማዋን በም/ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ፓትሮል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 9 የአድማ ብተና አባላት የጥቃቱ ሰለባ ሲሆኑ 5 ( አምስት) የሚሆኑት ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ ቀሪ 4 (አራት) የሚሆኑት ከባድ ቁስለኛ ሁነዋል።
የሰሌዳ ቁጥር 04251 (4) ንብረትነቷ የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ መምሪያ በሆነች ፓትሮል ተጭነው ሲንቀሳቀሱ ጥቃት የተፈፀመባቸው የአድማ ብተና አባላት የምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ዙሪያ ጥበቃ የሚያደርጉ መሆናቸውም ታውቋል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
ሰበር ዜና
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በተለያዩ ግንባሮች ድልን ተቀዳጀ።
ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር የአብይ አህመድ አገዛዝ ጅምላ ተጋላቢ አየር ወለድ ኮማንዶ ሀይሉን ከተለያዩ የቡድን መሳሪያ ጋጋታ ጋር ማለትም ዙ *23 መቶ ሰባት ብዛት ያለው ዲሽቃና ሞርተር ከሁሉም አካባቢ ቀራርሞ በማምጣት በሆድ አደር ሚሊሻ መንገድ መሪነት በሸዋ ክፍለ ሐገር መርሓቤቴ አዉራጃ ታች ቤት ቀበሌ ፋኖ አለበት ወደተባለበት ቀጣና ከለሊቱ 9:30 ከዋና ከተማው መቀመጫ አለም ከተማ እና ፌጥራ ተጠራርቶ ጨለማን ተገን አድርጎ በሶስት አቅጣጫ ማለትም በቡዮላይ ፣በሸፈሬ አንባ እና በጮሬ ቀበሌ" በማድረግ ወደ ጎራንዳ ከበባ ለማድረግና ለማጥቃት አቅዶ የገባው ሀይል የመርሐቤቴን ገደላገደልና አቀበት እንደ ሜዳ እየረገጡ፣ "ከፊታችን ሞት ቢኖርም ከኋላችን ታሪክ አለ" በሚል ወኔ የጠላትን ምሽግ የሚሰባብሩት የናደው ክፍለጦር ተርብ ተዋጊዎች፤ በፍጥነት ከበባውን በመክበብ ዕለታዊ ውሏቸው በባሩድ ጢስ ውስጥ የተጻፈ የጀግንነት ታሪክ አድርገውታል። ናደው ክፍለ ጦርን እደመስሳለሁ ብሎ የመጣው የጠላት ሀይልም በእነ ሞት አይፈሬ ነፃነት ክብራቸው ክፉኛ ያልጠበቀው ጉዳት ደርሶበታል።የናደው ክፍለ ጦር ምክትል ጦር አዛዥ ቀኝ አዝማች አቡ አሳምረው የተመራው የዕለቱ ውጊያም የውጊያ ጥበብ እና ብስለት በተሞላበት አውደ ውጊያ ናደው ክፍለ ጦር ድል ማድረግ ችሏል። ከናደው ክፍለ ጦር ከሁሉም ሻለቆች በተወጣጡ ሰራዊት በሶስት አቅጣጫ የመጣውን የጠላት ሀይል ሁሉንም አይነት አለኝ የሚለውን ስልትና ብቃቱን ለመጠቀም የሞከረ ቢሆንም ፤ ከሌሊቱ 9:30 የተጀመረ ውጊያ እስከ ቀኑ 10:00 ድርስ የነበረ ቢሆንም በወገን የስነ ልቦና እና የውጊያ የበላይነት በጠበቀ መልኩ ሲያጪዱት ውለዋል።
በእዚህ አውደ ውጊያ በጠላት ላይ የደረሰው ጉዳት በዝርዝር እንደሚከተለው እንገልፃለን።
👉1ኛ, አንድ ሲኖ መኪና ሙሉ የጠላት ሀይል ከእነ ተሽከርካሪዉ በልዩ ኦፕሬሽን ልዩ ስሙ ቡዮ የተባለው ቦታ ላይ መደምሰስ ተችሏል።
👉2ኛ. ሻንበል አመራሮችን ጨምሮ የተደመሰሰ የጠላት ሀይል 32
👉3ኛ,ከባድ ቁስለኛ 09
👉4ኛ,ቀላል ቁስለኛ 17
👉5ኛ,ቀንደኛ መንገድ መሪ ሚሊሻ 04 መደምሰስ ተችሏል።
በእዚህ አውደ ወጊያ ከፍተኛ ኪሳራ ያስተናገደው ጨፍጫፊው የአብይ አህመድ ስራዓት ሽንፈቱን ሲከናነብ የተለመደውን ዘግናኝ ድርጊቱን ምንም በማያውቁ ገበሬ እና የፋሲካ በአልን ምክንያት በማድረግ ለማክበር እና ሰርግ ላይ የተሰበሰቡ ንፁሃኖችን የበደል ብትሮችን በማሳረፍ እና ንፁሃን አርሶ አደሮችን እየቀጠቀጠ ለፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያነት ይዞ ሄዷል።
በእዚሁ አውደ ውጊያ የተሸነፈው የአገዛዙ ጅምላ ተጋላቢ ሀይል የፋኖን ምት መቋቋም አቅቶት አስከሬኑን እያዝረከረከ በመፈርጠጥ ወደመጣበት ተመልሷል ።
በሌላ የዕለቱ ዜና
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር የ7ተኛ ሃገር አቀፍ ምርጫ ካርድ በቁጥጥር ስር አውለውታል!!!!
አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ጀግኖቹ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር 4ተኛ ሻለቃ ቃኘዎች በብልፅግና ጥምር ጦር የሚመራው የማጭበርበሪያ የ7ተኛ ሃገር አቀፍ የውሸት ምርጫ ካርድ በባሶና ወረና ወረዳ በደበሌና እሮብ ገበያ ቀበሌ ህዝብን በግዳጅ የምርጫ ካርድ ለማስወጣት ሲሞክር የፋኖን ብትር መቋቋም ሲያቅተው ይዞት የመጣውን በርካታ የምርጫ ካርድ እያዝረከረከ እና አስማርኮ ወደ መጣበት ደብረ ብርሃን የእፈረጠጠ ተመልሷል።
የመረጃ ምንጭ-አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን
ክብር ለተሰውት
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ከሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመካነሰላም ግንባር ከምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ጋር በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ የከፈተው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናገደ!
ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ተጋድሎ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ድል ቀንቶታል:: የጠላት ኃይል ቁስለኛ እና አስከሬን በአምቡላንስ ጭኖ ወደ መካነሰላም አቅንቷል::
11ኛ ዕዝ ከመሐል ሳይንት እና አማራ ሳይንት ወረዳዎች ጭምር ሰራዊቱን ወደ መካነሰላም አጓጉዞ መካነሰላም ለሚገኘው ፀረ ህዝብ ኃይል ድጋፍ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርግም ኦፕሬሽኑ በእነ ሞት አይፈሬ ብርታት ከሽፏል:: በዚህም የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት በተለምዶ አደሬ ቆቦ የተባለች ቦታ ላይ በትናንትናው ዕለት ክፉኛ የተመታ ሲሆን ሽንፈቱን ለማካካስ በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ መድፍ እና ሞርተር ወደ ገበሬዎች መንደር በመተኮስ በንፁሀን ላይ ጉዳት አድርሷል:: ትናንት አንድት እናት በሞርተር ተመታ ክፉኛ ቆስላ በህክምና ላይ እንደምትገኝ ተረጋግጧል:: ዛሬ ደግሞ አንድ ንፁህ ገበሬ በመድፍ ተመቷል:: መትረፍ እንደማይችልም ነው የህክምና ውጤቱ የሚያስረዳው::
ጠላት በተደጋጋሚ መድፍ ጭምር የተኮሰ ሲሆን ቢሊ ታዳጊ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የሙጎጉቱ ገብርኤል ገዳምን ህንፃ ቤተክርስቲያን ጣራ አውድሞታል::
የጠላት ኃይል የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊትን ጥሶ አልፎ ቢሊ ታዳጊ ከተማን የመቆጣጠርና ለቀጣዩ ወር ምርጫ ቅድመ ዝግጅት የማድረግ እቅድ አቅዶ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ታዳጊ ከተማዋ ሳይደርስ በትናምትናው እለት መንገድ ላይ ተቀጥቅጦ የተመለሰ ሲሆን በዛሬው እለት ተመልሶ በመድፍ እና ሞርተር የከተማይቱን ነዋሪዎች ሲደበድብ ውሏል::
ጠላት የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ መግባቱን የሚያረጋግጥ ክስተት የተፈጠረ ሲሆን በዚህም የ87ኛ ክፍለ ጦር አመራር የሆነ 10 አለቃ ምስጋን የተባለ ወታደር እና ሌላ ጓዱ በበቃኝ ከጠላት ከድተው የወገን ኃይልን ተቀላቅለዋል:: አንድ 50 አለቃም የጠላት ኃይልን ከድቶ አድራሻውን አጥፍቷል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ሚያዝያ 6 ቀን 2018 ዓ.ም
ከሚያዝያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመካነሰላም ግንባር ከምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ጋር በከባድ መሳሪያ የታገዘ ውጊያ የከፈተው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናገደ!
ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ተጋድሎ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ድል ቀንቶታል:: የጠላት ኃይል ቁስለኛ እና አስከሬን በአምቡላንስ ጭኖ ወደ መካነሰላም አቅንቷል::
11ኛ ዕዝ ከመሐል ሳይንት እና አማራ ሳይንት ወረዳዎች ጭምር ሰራዊቱን ወደ መካነሰላም አጓጉዞ መካነሰላም ለሚገኘው ፀረ ህዝብ ኃይል ድጋፍ ለማድረግ ሙከራ ቢያደርግም ኦፕሬሽኑ በእነ ሞት አይፈሬ ብርታት ከሽፏል:: በዚህም የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት በተለምዶ አደሬ ቆቦ የተባለች ቦታ ላይ በትናንትናው ዕለት ክፉኛ የተመታ ሲሆን ሽንፈቱን ለማካካስ በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ መድፍ እና ሞርተር ወደ ገበሬዎች መንደር በመተኮስ በንፁሀን ላይ ጉዳት አድርሷል:: ትናንት አንድት እናት በሞርተር ተመታ ክፉኛ ቆስላ በህክምና ላይ እንደምትገኝ ተረጋግጧል:: ዛሬ ደግሞ አንድ ንፁህ ገበሬ በመድፍ ተመቷል:: መትረፍ እንደማይችልም ነው የህክምና ውጤቱ የሚያስረዳው::
ጠላት በተደጋጋሚ መድፍ ጭምር የተኮሰ ሲሆን ቢሊ ታዳጊ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የሙጎጉቱ ገብርኤል ገዳምን ህንፃ ቤተክርስቲያን ጣራ አውድሞታል::
የጠላት ኃይል የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊትን ጥሶ አልፎ ቢሊ ታዳጊ ከተማን የመቆጣጠርና ለቀጣዩ ወር ምርጫ ቅድመ ዝግጅት የማድረግ እቅድ አቅዶ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ታዳጊ ከተማዋ ሳይደርስ በትናምትናው እለት መንገድ ላይ ተቀጥቅጦ የተመለሰ ሲሆን በዛሬው እለት ተመልሶ በመድፍ እና ሞርተር የከተማይቱን ነዋሪዎች ሲደበድብ ውሏል::
ጠላት የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ መግባቱን የሚያረጋግጥ ክስተት የተፈጠረ ሲሆን በዚህም የ87ኛ ክፍለ ጦር አመራር የሆነ 10 አለቃ ምስጋን የተባለ ወታደር እና ሌላ ጓዱ በበቃኝ ከጠላት ከድተው የወገን ኃይልን ተቀላቅለዋል:: አንድ 50 አለቃም የጠላት ኃይልን ከድቶ አድራሻውን አጥፍቷል::
©ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
‼️አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ⚠️
--ለአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ !
በጎንቻ ወረዳና ግንደወይን አካባቢ የምትንቀሳቀሱ የወገን ጦር አመራርና አባላት እንቅስቃሴውን እና ወታደራዊ መረጃዎችን ጠላት ከውስጥ ባስቀመጣቸው #ኦፒዎች አማካኝነት መረጃ ስለደረሰው አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ማሳሰብ እወዳለሁ ‼️
በየዕዱውኃ ከተማ የሚገኘው ቅጥረኛ ሚሊሻ ወ/ሪት ፈንታነሽ አባቡ እና አቶ አባቡ ካስየ የተባሉ ልጅ እና አባት በግፍ እረሽኖል።
64ኛ ክ/ጦር ማያዚያ 06/2018 ዓ.ም
በአማራ ህዝብ ላይ በረካታ ግፎችን እየፈፀመ የሚገኘው የአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት ልጅ እና አባት በግፍ እረሽኖል።
ሚያዚያ 05/2018 ዓ.ም በየዕዱውኃ ከተማ ቁርስ ቤት የምትሰራ ወ/ሪት ፈንታነሽ አባቡ አፈቀርኩሽ በማለት ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በአገዛዙ ቅጥረኛ ሚኒሻ አባቷን አቶ አባቡን ጨምሮ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ልጆ ከአባቷ ጋር በግፍ ተረሽነዋል።
በአስገዳጅ ሁኔታ የፍቅር ጥያቄ ትቀበይኛለሽ በማለት እርምጃ የወሰደው የአገዛዙ ቅጥርኛ ሚሊሻ #ካስየ ወዲያውኑ በመከላከያ ኃይል ተረሽኖ በየዕዱውሃ ከተማ መነኃሪያ ላይ አስከሬኑ ወድቆ ማደሩን ተረጋግጦል።
የአገዛዙ ኃይል አረመኔዊ እና ጨቋኝ መሆኑን የምንናገረው በምክንያት ነው በየዕድውኃ ከተማ የተረሸኑቱ አይነ ስውር እና በድህነት ውስጥ ሆነው ህይወትይ ለመምራት የሚደክሙ ንፁሃን መሆናቸውን አረጋግጠናል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!
ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ሚያዚያ 06/2018ዓ ም
በ102ኛ ኮር ከፍተኛ ምት የደረሰበት የአብይ አህመድ ተሸናፊ ሰራዊት መፈራረሱን ቀጥሏል ።
አዴት እና ጎንጅ በደረሰበት ምት የተደናበረው የብልፅግና ሰራዊት በዚህ ሳምንት ብቻ ከ11ኛ ክፍለጦር ቀጠና (ብራቃትና ከአዴት) ከ50በላይ የሚኒሻ አባላት ወገንን ተቀላቅለዋል ።
በዛሬው ዕለትም በቀን 06/08/2018 ዓ.ም አማኑኤል መኳንት የባተለ የአድማ ብተና vip ሻለቃ 2 አባል ከሳሀሊ ዋርካ በመነሳት ከነሙሉ ትጥቁ ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፈለጦርን ተቀላቅሏል።
+3
*የብልፅግናው ስርዓት መፍረሱ ቀጥሏል!
~~~~~~
በአብይ አህመድ የሚመራውን አረመኔያዊ የብል(ፅ)ግና ስርዓትን በማገልገል ላይ የነበሩ ሰራዊቶች አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር ተቀላቀሉ።
ከነዚህም መካከል :-
1-ሽመላሽ ቻሌ ፋራ ኮማንዶ
2-አይሸሽም ሽፈራው ፋራ ኮማንዶ
3-መንግስቱ ጥላየ ፈራ ኮማንዶ
4_ፍቅሩ በላይ ፋራ ኮማንዶ የተባሉ ፍኖተሰላም ከተማ ከመሸገው የጠላት ሀይል ጋር በመሆን አምባገነኑን የብልጽግና ስርዓት ሲያገለግሉ የነበሩ ሲሆን አብይ አህመድ ከአዘርባጃን በብድር ያመጣውን ክላሸንኮቭ ከእነ ተተኳሹ በመያዝ አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77 ኛ ክፍለጦር ህ/ግንኙነት
ሚያዚያ 6/2018ዓ.ም
ባለፉት 3 የትጥቅ ትግል ዓመታት ውስጥ በርካታ ታጋዮችን የማግኘት እድሉ ነበረኝ።
ካገኘኋቸው መካከል አንድ አንዶቹ በትግሉ ሽፋን ወጣ ገባ እያሉ የሚያዳክሩ ናቸው።ገሚሱ በትግሉ የሚኖር ነው። የተቀሩት (በጣም ጥቂቶቹ) ደግሞ ለትግሉ የሚኖሩ ናቸው።
ለትግሉ ከሚኖሩት በጣም ጥቂቶች መካከል እጅግ በሳልና ጠንካራ፣ ለሆዱ ግድ የሌለው፣ ለሚመራው ሰራዊት፣ ህዝብም ሆነ ለተሰጠው ኃላፊነት እጅግ የሚጠነቀቅ፤ የማኀበረሰቡን እሴት፣ ባህልና እምነት የሚያከብርና የሚጠብቅ፣ ዝሙትን፣ ስካርንና ስርቆትን የሚፀየፍ፤ ሰዎችን (ታጋዩን) እንደየ አቅሙ የሚመዝንና የሚያከበር፣ ሰውን እንዴ ካመነና ከወደደ ዋጋ ለሚከፍልው ጀግና ሰው ዛሬ ጥቂት ምስክርነት እሰጣለሁ።
በነገራችን ላይ ይህ ሰው ከኤርትራ በረሃ ጀምሮ በኢትዮጵያ በነበረው ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ጭምር የአማራና የኢትዮጵያ ህዝብን በታማኝነት ሲያገለግል የቆየ ነው። ዛሬ ላይ ስንቶቹ በአገዛዙ እየተደለሉ ከቀበሌ ሊ/መንበርነት አስከ ሚኒስትርነት ደረጃ ማንነታቸውን ክደው በሚሾሙበት በዚህ ወቅት ይህ አርበኛ የነበረውን ከፍተኛ ኃላፊነት ለህዝብ ሲል ጥሎ ጫካ የገባ ነው። በነገራችን ላይ በአገዛዙ ከፍተኛ የስልጣን ቦታ ታጭቶ የነበረ ቢሆንም አልፈልግም በማለት ጥሎ ወጥቷል።
ጫካ ከመግባቱ አስቀድሞ በርካታ ታጋዮችን በየቦታው አደራጅቷል። በዚህም በአገዛዙ ከ6 ወራት በላይ በባህርዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት ታስሮ ተሰቃይቷል።
በነገራችን ላይ እያወራሁ ያለሁት ስለ ጀግናው አርበኛ ተፈሪ ካሳሁን ነው። ይህ ስም በአደባባይ ብዙም አይታዎቅም። አርበኛ ተፈሪ ካሳሁን ቅጥረኛ የማኀበራዊ ሚዲያ ሰራዊት የለውም። ኧረ እንዲያውም ሚዲያ የሚባል አይዎድም።
አንድ ታጋይ ዓለማና ግቡን የሚያሳካው በማኀበራዊ ሚዲያ ግርግርና ቧልት ሳይሆን በተግባር ሜዳ ላይ አድምቶ በመስራት ነው የሚል ፅኑ እምነት አለው። በዚህ ፅኑ አቋሙ ተፈሪ ካሳሁንን አብዛኛው ታጋይም ይሁን ህዝብ እምብዛም በሚዲያ አያውቀውም። የግል ፎቶዎቹን እንኳን እስከ ቅርብ ጊዜ ለማገኘት እጅግ ይቸግር ነበረ።
ስለ አርበኛ ተፈሪ ካሳሁን ከላይ ለማወራው ነገር ምስክር እራሴው ነኝ።በሶስተኛ ወገን ያገኘሁት መረጃ አይደለም። ከአርበኛ ተፈሪ ካሳሁን ጋራ ከ12 ወራት በላይ አንድ ካምፕ ኖረናል። በነበረኝ ቆይታ ካጠናኋቸው የአርበኛው ጥቂት ጠባዮች መካከል ነው እያነሳሁ ያለሁት።
አርበኛ ተፈሪ ካሳሁን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና የኢንተለጀንስ ( intelligence) አቅሙ ከፍተኛ ነው። በከንቱ ጊዜውን አያሳልፍም። በነገራችን ላይ አርበኛ ተፈሪ ካሳሁን ቁጡና የሚፈራ ሞገስ ያለው ነው። ተኳሽም ነው። ውጊያ የማንበብ ብቃቱም የተለየ ነው። የተረጋጋና ድምፁ የማይሰማ አርበኛ ነው።ስንፍናም አይዎድም።በቀን አንድ ጊዜ ብቻ በልቶ የማደር የቆዬ ልማድም አለው።ክብሩን አብዝቶ የሚጠብቅ ነው።በዓላማ ካልሆነ በስተቀረ ከማንም ጋራ እከክልኝ ልከክልህ አይዎድም። ጀግናን፣ምሁራንና ሐቀኞችን ይዎዳል፤ ያከብራልም።
እንደዚህ አማራዊ ለዛና እሴትን የተላበሱ ጀግና ወንድሞቻችንን ጠንካራ ጎኖቻቸውን እያነሳን እንደ ሰውኛ ደግሞ ያሉባቸውን ጥቂት ክፍተቶች እየሞላንላቸው ልንደግፋቸውና እያበረታታን ልናታግላቸው ይገባል። እኔ ስለ ግለሰቦች ብዙም አውርቼ አላውቅም። ተፈሪ ካሳሁን ግን ሊወራለት የሚገባ ጀግና ወንድማችን በመሆኑ ኃላፊነት እዎስዳለሁ።
አርበኛ ተፈሪ ካሳሁን በርታ!!!
ፎቶ👉 (የመጀመሪያው በኤርትራ በረሃ ለአማራ ህዝብ የነፃነት ትግል ሰራዊት እያደራጀ በነበረበት አካባቢ የተወሰደ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለህልውና ትግላችን ወደ ጫካ ከወጣ በኋላ እዚህ ኢትዮጵያ የተወሰደ ነው።)
ሚያዚያ 05/2018 ዓ.ም
አርበኛ ወግደረስ ጤናው
የንጉሱ አልበሙ ከመውጣቱ በፊት መራሹን የብልፅግና ስርዓት እያስጨነቀው ነው!!
የጥበብ ፀሐይ ስትወጣ - ኢቶሪካ!
"ዘፈንን ከዘመን አዋህዶ... ፍቅርን ከሰላም አጋምዶ" ማስደመም የሚችልበት ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ከ8 ዓመታት ረጅም የናፍቆት ጉዞ በኋላ በድንቅ ስራው ተመልሷል።
ይህ አልበም ዝም ብሎ ሙዚቃ ሳይሆን፣ የጥበብ እርካታ ነው! ቴዲ "ኢቶሪካ" በሚለው አዲስ ስራው የሁላችንንም ቀልብ ሊገዛ ዳግም ቀጠሮ ይዟል።
የ8 ቁጥር ምስጢር በነገሰበት በዚህ ታላቅ ቀን፣ የኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ይጽፋል።
ሐሙስ ሚያዝያ 8 | ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ
በቴዲ አፍሮ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል
ጥበብን ለሚናፍቁ፣ ፍቅርን ለሚጠሙ ሁሉ የሚሆን የምስራች ነው!
እንዴት አምሮባታል ዛሬ..." የሚለው ዜማው አሁንም በልባችን እያስተጋባ፣ አዲሱን ስራ ለመቀበል ዝግጁ ናችሁ ?
8 8 8 2018 18 ትራክ
ኢትዮሪካ Teddy Afro
የፋሽስቱ ብልፅግና ሰራዊት ብሬን ተኳሹን ጨምሮ 18 ጠላት ሲደመሰስ ከ25 በላይ ቁስለኛ አስተናገደ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ 303ኛ አሳምነው ኮር አካል የሆነው ነብሮ ተወርዋሪ ኮማንዶ በአሁኑ 16ኛ ክፍለ ጦርና እሸት ክፍለ ጦር በአሁኑ 19ኛ ክፍለ ጦር የተውጣጡ በቁጥር አነስተኛ ፋኖዎች የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ መከላከያ ጦርን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት በጥምረት ታላቅ ድል ተጎናፀፉ።
ሚያዚያ 03 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ መነሻውን ከላሊበላ ከተማ በማድረግ ወደ ጋሸና ከተማ ሬሽን ለማሳለፍ የተንቀሳቀሰው የጁላ ሰራዊት ባላሰበውና ባልጠበቀው ሁኔታ ከአወባይ ዳቦ ከተማና ከድብኮ ቆጋ በተደረገበት የደፈጣ ጥቃት ጠላት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አስተናግዷል።
በዚህ አውደ ውጊያ 18 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ25 በላይ ቁስለኛ ያስተናገደ ሲሆን ከላሊበላ ከተማ ተጨማሪ ሦስት መኪና ኃይል በመጨመርና ሽፋን እንዲሰጡት በማድረግ የተረፈው ኃይል ራሱን በማውጣት ያሰበውን ሳያሳካ ወደነበረበት ላሊበላ ከተማ ተመልሷል።
ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 05/2018 ዓም
የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ኮማንዶ ፋኖ ላመነው ሰጤ !!!
ኮማንዶ ላመነው ሰጤ በእንኳን አደረሳችሁ የብአል መልክቱ ላይ ከሰራዊቱ አባላት ጋር ባደረገው ቆይታ ያስተላለፈው መልክት ፦ እኛ የአማራ ፋኖወች አማራ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ ብለን መሳሪያ ታጥቀን ጫካ የወረድነው ከማንም ማህበረሰብ እና ህዝብ ጋር ጸብ ኑሮን አይደለም እኛ ፋኖወች ከማንኛውም ማህበረሰብ ጋር ጸብ የለንም ። ከትግራይ ፣ ከኦሮሞው ፣ ከሲዳማው ፣ ከወላይታ ፣ ከአፋሩ ፣ ከሶማሌው ፣ ከጋቤላው እና ኩራጌው እንዲሁም ከማኔኛው ኢትዮጵያዊ ጋር ጸብ የለንም ማንኛውም ኢትዮጵያዊይም ሆነ ብሔር ለአማራ ህዝብም ሆነ ለኛ ለፋኖወች ጥላታችን አይደለም ።
የኛ ጥላት ወይም በሰፊው ህዝባችን በአማራ ህዝባችን ላይ የህልውና አደጋ የደቀነው ሰርአት ወይም አገዛዝ ጋር ነው ጸባችን ይህ ስርአት ለየትኛው ህዝብ የማይበጅ ሀገር አፍራሽ አደገኛ ስርአት ነው ይህን ስርአት አምርረን መታገል አለብን ጓዶች !??
ይህ ስርአት ውሎ ካደረ ለኢትዮጵያም የህልውና አደጋ ለጋረጠበት የአማራ ህዝብም ፈጽሞ ጥፋት ነው የሚሆነው እናም እኛ አንዴ ወተናል ይህን ስርአት አምርረን ልንታገለው ይገባል ።
በአካባቢ፣ በሰፈር እና በዘመድ አዝማድ ማሰብ የፋኖ ባህሪ አይደለም ።
ተባብረን ይህን የኢትዮጵያ ነቀርሳ ካንሰር የአማራ ህዝብ የሆነ ጥላት ተባብረን ነቅለን መጣል አለብን ?
ግልጽ ነው ጓዶች ....?
እኛ አላማችን አፍ ያለ ነው በአካባቢያችን በጎጥ እና በሰፈር በክልል የምንወሰን ሳይሆን አላማችን ትልቅ ነው ። አባቶቻችን ያስረከቡንን ሀገር ማስጠበቅ ነው አላማችን የአማራን ህልውና ማረጋገጥ ብቻ አይደለም አለማችን ዙፋኑን ተረክበን የፈረሰውን ሀገረ መንግሥት ማቆም አለብን ለዚህ እንዘጋጅ !!
ኮማንዶ ፋኖ ላመነው ሰጤ
ሚያዝያ 5/2018 ዓ/ም
ድል ለተገፋው አማራ ድል
ለጀግናው ፋኖ 💪!!
