ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше3 011
Подписчики
+2324 часа
+367 дней
+41430 дней
Архив постов
የአሰቦት ገዳም ካህን ተገደሉ‼️
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ አንድ ካህን ተገደሉ።
ተኩሱ የተከፈተው ከገዳሙ ታችኛው የእናቶች ገዳም ሲሆን ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም 9:00 አካባቢ ነው።
ታጣቂዎቹ ዙሪያውን ከበው በከፈቱብን ተኩስ አንድ ካህን ተገድለዋል አስከሬንም ማንሳት አልቻልንም ያሉት መረጃ ሰጫችን እስካሁኗ ሰዓት የጸጥታ ኃይሎች አልደረሱም ብለዋል።
ገዳማውያኑ “እኛ ገዳማውያን ነን መሳሪያ የለንም፤ አባቶቻችን ለሚመለከታቸው አካላት መረጃውን በፍጥነት ያድርሱልን” በማለትም ጥሪ አቅርበዋል።
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም ተመሳሳይ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ገዳማውያኑ እና የአካባቢው ምእመናንን እየተሰደዱ እንደሆነም ተገልጿል።
Via- Mahibere kidusan broadcasting servuce
የአሰቦት ገዳም ካህን ተገደሉ‼️
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ አንድ ካህን ተገደሉ።
ተኩሱ የተከፈተው ከገዳሙ ታችኛው የእናቶች ገዳም ሲሆን ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም 9:00 አካባቢ ነው።
ታጣቂዎቹ ዙሪያውን ከበው በከፈቱብን ተኩስ አንድ ካህን ተገድለዋል አስከሬንም ማንሳት አልቻልንም ያሉት መረጃ ሰጫችን እስካሁኗ ሰዓት የጸጥታ ኃይሎች አልደረሱም ብለዋል።
ገዳማውያኑ “እኛ ገዳማውያን ነን መሳሪያ የለንም፤ አባቶቻችን ለሚመለከታቸው አካላት መረጃውን በፍጥነት ያድርሱልን” በማለትም ጥሪ አቅርበዋል።
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም ተመሳሳይ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ገዳማውያኑ እና የአካባቢው ምእመናንን እየተሰደዱ እንደሆነም ተገልጿል።
©️ማህበረ ቅዱሳን
በአማራ ፋኖ ክንድ ክፉኛ የተመታውና የውድቀት ዋዜማ ላይ የሚገኘው የአብይ አህመድ አገዛዝ ሰራዊት እርስ በእርሱ መበላላት ጀምሯል።
አጥቢያ ለሊቱን በሰሜን ወሎ ዞን ኮን ከተማ በአድማ ብተና እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተቀሰቀሰ ከባድ የእርስ በእርስ ተኩስ ከተማዋ ስትናጥ ያደረች ሲሆን፡ በጋሸና ከተማ ደግሞ "ወደ ፋኖ ልትቀላቀሉ ነው" በሚል ሰበብ ሁለት የአማራ ተወላጅ ወታደሮች በገዛ አዛዦቻቸው አረመኔያዊ ግድያ ተፈፅሞባቸዋል።
አጥቢያ ለሊቱን የተካሄደው የኮን ከተማ የእርስ በእርስ ውጊያና ጋሼና ከተማ ውስጥ በሁለቱ ወታደሮች ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የብልፅግና ሰራዊት በጥልቅ መፈረካከስ ውስጥ መግባቱን በገሃድ ያሳየ ነው ተብሏል።
ከጦላይ የመከላከያ ማሰልጠኛ ተቋም ለሽምቅ ውጊያ ስልጠና ወደብርሸለቆ ማስልጠኛ ተቋም የመጡ 8 የመከላከያ አባላት አፋብን 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር ተቀላቀሉ።
1ኛ _አምሳያው አበበ
2ኛ-ፈንታሁን እሸቴ
3ኛ_ ጋሻው ያሴ
4ኛ_እንዳልክ አየን
5ኛ_ አድማሱ አየን
6ኛ _ሙልጌታ ተገኘ
7ኛ _ዘዉደ አላዩ
8ኛ _እሱባለው መልኬ
በዛሬው ዕለት የአረመኔው አገዛዝ ስርዓቱን በመጥላት ከአገዛዙ ማሰልጠኛ ካምፕ በመውጣት አፋብን 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለጦር 5ኛ ሻለቃ ተቀላቅለዋል። በመውጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ሌሎች አባላትም በተመሳሳይ የመውጣት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።
#ድል ለአፋብን💪
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 3/2018 ዓ.ም
ኮረኔል Mulatie Sisay እንደፃፈው ✍️
ወቅቱ ወሳኝ የትግላችን የመታጠፊያ ምዕራፍ ላይ ነን በዚህ ወቅት እጅጉን መረጋጋትና መናበብ ይጠበቅብናል ።
በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል ይሉ ዘንድ በእጃችን ያለውን ፀጋ በአግባቡ እንጠቀምበት ዘንድ ወንድማዊ ምክሬ ነው ።
መተላለክ እና መወነጃጀል ማናችንም አሸናፊ አያደርገንም ፤ መሪወቻችን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በስክነትና በብልሀት መመዘንና ማጤን ፤ በግብረ ገብነትና በትህትና መምራት ይጠበቅባቸዋል ።
ይህ ትግል ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል በሌላ በኩል ላይቀለበስ የህዝባችንም ሁኗል ፤ እያንዳንዱ የነፃነት ታጋይ ትግሉን የመጠበቅ ፤ በአይነ ቁራኛ መከታተልም ይጠበቅበታል ።
እውነት ነው ከዚህ በኃላ ትግላችን ያልተመቻቸው እና ፍላጎታቸው ያልተሳካላቸው ወንድሞች የሚበትኑት ትግል ከመሆን ወጥቷል !!!!
#ከቤንሻንጉል አሶሳ ለፋኖ የተላከ ምስጋና!!
እኔ ባለሁበት ከተማ ይላል መልክቱን የላከልኝ!! እኔ ባለሁበት ከተማ አሶሳ ላይ የአንድ ወረዳ አመራሮች ህዝብ ሰብስበው ፋኖን እያነሱ ያው የተለመደውን ዘራፊ ቀማኛ የወያኔ ተላላኪ በጣም ጨካኝ ገዳይ ናቸው እያለ ስማችሁን ያብጠለጥላል።
ይህን የሰማ አንድ የአካባቢው ተወላጅ/የበርታ ብሔረሰቤብ/አካሔድ ብሎ የወረዳውን አስተዳዳሪ ንግግሩን አቋረጠው ይህ ሰው ልጅ መከላከያ የነበረና በመካነ ሰላም ግምባር ተማርኮ የቤተ አምሓራ ፋኖ ልብስ ገዝተውና ቀይረው፤ገንዘብ ሰተው በደምብ ተንከባክበው ወደ አትውልድ አካባቢው ለመላክ ለጎጃም ፋኖዎች አሸጋግረው በመስጠት ወደ አካባቢው እንዲደርስ ያደረጉት።
ልጁም ወደ ትውልድ ቦታው ደርሶ ለወላጆቹ ፋኖ ያደረገለትን ይነግራቸዋል። ቀጥሎ ለአካባቢው ማህበሰብ በመናገሩ ለአካባቢው ህ/ሰብ የፋኖን መልካምነትና ተግባር ይመሰክራል።ይህ በእንድህ እንዳለ ወደ አባቱ ስመለስ ይህን የሰማ አባቱና የአካባቢው ሰዎች ፋኖማ የተማረከውን ልጃጅን ልብስ አልብሶ አብልተው በደንብ ተንከባክበው ነው የሸኙት።
ገዳይ አደሉም። እናንተ እንደምትሉት ዘራፊም አይደሉም። መንገድ አይዘጉም። በማለት አስተዳዳሪውን አፉን ሲያሲይዙት ሊያስተባብል ቢሞክርም ባለመግባባት ስብሰባው ተበትኗል። የአሶሳ ማህበረሰብም ከስብሰባ አዳራሽ ሲወጣ በመፈከር" ፋኖ ገዳይ አይደለም! ብልፅግኔ ጋፎ ወደ ሞት የወሰደብንን የነጠቀንን ልጆቻችንን ፋኖ ወልዶ ሰቶናል!! ፋኖ አራት ኪሎ ገብቶ የኢትዮጲያን ሰላም ያምጣልን!" በማለት ድምፃቸውን እያሰሙ ከአዳራሹ ወጡ!
#ይሄንን ጉዳይ ፋኖ እሸቱ አባተ ሚድያ ላይ አውልልን። ሲሉ በውስጥ መስመር ልከውልኛል። ሰፊው ህዝብ ሆይ ከአሶሳ የተላከውን የህዝብ ድምፅ እነሆ ብያለሁ።
ድል ለፋኖ!
ሞትና ውድቀት ለብልፅግና ስርዓት!
እሸቱ አባተ
ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ ከአውደ ውጊያ ጎን ለጎን ሕዝብ የማንቃት ስራዎችን እና ወቅታዊ የአማራ ፋኖ የትግል አንደምታ ላይ ውይይት ተደርጓል!
የምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር በሰሜን ወሎ ደጋማው ቀጠና የህዝብ መድረክ እና ወቅታዊ የጥላት እንቅስቃሴን የማክሸፍ ህዝባዊ ንቅናቄ ተካሂዷል። ግንቦት 2/2018 ዓ/ም በዋድላ ወረዳ በ016 ቀበሌ ከአንድ ሽህ በላይ የቀበሌው ማህበረሰቦች የተገኙበት ህዝባዊ ዉይይት ተካሂዷል።
በዚህ መድረክ በኮሩ አመራሮች ለህዝቡ የጥላትን የምርጫ እንቅስቃሴ እንደት ማክሸፍና የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ከፋኖው ጎን መቆም እንዳለበት ሀሳብ የተሰነዘረ ሲሆን ሙሉ ተሰብሳቢ ህዝቡ በአዎንታ ተቀብሎታል።
ከማህበረሰቡ የተሰነዘሩ ትግሉን እንደ አይን ብሌናቸው የሚጠብቁት መሆኑን የሚያሳብቁ ሀሳቦች ተሰዝረዋል። "ውስጣችሁን ከሰርጎ ገቦች አፅዱ! ትግሉ ወጣት፤ ሽማግሌዎች ሁላችን በየአቅማችን እየተሳተፍንበት ያለ ነው። አይዟችሁ ምንጊዜም ከጎናችሁ ነን።" በማለት የፋኖነት አብዮት ህዝባዊ መሆኑን በመድረኩ ገልፀዋል።
በዚህ መድረክ የተገኙ ተሰብሳቢዎች 731 ወንዶች
273 ሴቶች የተሳተፉ ሲሆን በጠቅላላ 1004 ሰዎች ተሳትፈዋል።
©ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
+3
#ዛሬም_አፋብን_ሸዋ_ጠቅላይ_ግዛት_አሳምነው_ዕዝ_ጠላትን_ስቦ_በማሥከዳት_እያፈረሱት_ይገኛሉ‼️
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አ/ዕዝ
ግንቦት 03/2018ዓ.ም
ከ450 በላይ የብሬን ተተኳሽና ከነ ሙሉ ትጥቁ የያዘ የ104ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ አባል አፄ አምደፂዎን ኮርን የተቀላቀለ ሲሆን ከ120 በላይ የክላሽ ጥይትና ከነ ሙሉ ትጥቁን ይዞ የመጣው የአድማ ብተና ፖሊሥ ደግሞ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ጣይቱ ክፍለ ጦር ፋኖን ተቀላቅሏል። አባላቶቹም በክፍለጦሩ አመራሮች ደማቅ አቀባል ተደረገላቸው።
መነሻውን ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ በማድረግ የአፋብን ሸዋ ጠቅለይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራንቦ ክፍለጦርን የተቀላቀለው የብልፅግናው 104ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባል ለፈፀመው ጀግንነት በክፍለጦሩ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአድማ ብተና ፖሊሱም ከአንኮበር አለዩ አምባ ከ29ኛ ሻለቃ ሻምበል (2) ከጋንታ ቲም (2) ምክትል ቲም መሪ ሥሙ ተሥፋዬ ቼሬ የተባለ አድማ ብተና ሁለት እግር ክላሽ፣ ከ(3) መጋዘንና ከ120 የክላሽ ጥይት ጋር የዕዙ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ጣይቱ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
ፋኖን የተቀላቀለው የኮማንዶ አባሉ:-
✅ሁለት የደረት ትጥቅ
✅450 የብሬን ተተኳሽ
✅375 የክላሽ ተተኳሽ
✅8 ካዝና እና
✅አንድ ዘመናዊ የኮማንዶ ጥርጥር ክላሽ
በመያዝ ጀግናው የራንቦ ክፍለጦርንና ጣይቱ ክፍለ ጦርን መቀላቀላቸውን የሁለቱም ኮሮች በላኩት የግንባር መረጃ ገልፀዋል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
#ዛሬም_አፋብን_ሸዋ_ጠቅላይ_ግዛት_አሳምነው_ዕዝ_ጠላትን_ስቦ_በማሥከዳት_እያፈረሱት_ይገኛሉ‼️
አፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አ/ዕዝ
ግንቦት 03/2018ዓ.ም
ከ450 በላይ የብሬን ተተኳሽና ከነ ሙሉ ትጥቁ የያዘ የ104ኛ አየር ወለድ ኮማንዶ አባል አፄ አምደፂዎን ኮርን የተቀላቀለ ሲሆን ከ120 በላይ የክላሽ ጥይትና ከነ ሙሉ ትጥቁን ይዞ የመጣው የአድማ ብተና ፖሊሥ ደግሞ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ጣይቱ ክፍለ ጦር ፋኖን ተቀላቅሏል። አባላቶቹም በክፍለጦሩ አመራሮች ደማቅ አቀባል ተደረገላቸው።
መነሻውን ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ በማድረግ የአፋብን ሸዋ ጠቅለይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር የራንቦ ክፍለጦርን የተቀላቀለው የብልፅግናው 104ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አባል ለፈፀመው ጀግንነት በክፍለጦሩ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአድማ ብተና ፖሊሱም ከአንኮበር አለዩ አምባ ከ29ኛ ሻለቃ ሻምበል (2) ከጋንታ ቲም (2) ምክትል ቲም መሪ ሥሙ ተሥፋዬ ቼሬ የተባለ አድማ ብተና ሁለት እግር ክላሽ፣ ከ(3) መጋዘንና ከ120 የክላሽ ጥይት ጋር የዕዙ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ጣይቱ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል።
ፋኖን የተቀላቀለው የኮማንዶ አባሉ:-
✅ሁለት የደረት ትጥቅ
✅450 የብሬን ተተኳሽ
✅375 የክላሽ ተተኳሽ
✅8 ካዝና እና
✅አንድ ዘመናዊ የኮማንዶ ጥርጥር ክላሽ
በመያዝ ጀግናው የራንቦ ክፍለጦርንና ጣይቱ ክፍለ ጦርን መቀላቀላቸውን የሁለቱም ኮሮች በላኩት የግንባር መረጃ ገልፀዋል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የተባበሩት ኢምሬቶች አዲሷ ኢምፔሪያሊስት ሆናለች። ከግማሽ ምዕተ ዓመት የማይበልጥ እድሜ ያላት፤ የአዲስ አበባን ሩብ ያህክል የህዝብ ቁጥር የሌላት ሀገር የሺህ ዘመናት የስልጣኔ ባለቤት እና በአፍሪካ የነፃነት አባት የሆነችዋን ኢትዮጵያ ቅኝ እየገዛች ትገኛለች። ትክክለኛ ሊደር ሺፕ እና የጋራ ርዕይ የሌለው ህዝብ እንዲህ ነው ሚሆነው።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከደመወዝ እስከ ቁሳቁስ በኢምሬቶች ይሸፈናል። ስራ ላይ ካሉት ድሮኖች መካከል ከአንቴና ውጭ ሳትኮም (ሳተላይት) እንዲጠቀሙ ተደርገው የተሻሻሉት TB2 ድሮኖች እና ከ 4 እስከ 24 ሮኬት ቦንቦች መሸከም የሚችሉ ዘመናዊወቹ አኪንቺ ድሮኖች ባለንብረቶች የሆኑት ኢምሬቶች ደብረ ዘይት፣ ባህርዳር እና አሶሳ ላይ የራሳቸውን ድሮኖች ኦፕሬት እያደረጉ ከትመዋል።
AI ሲስተም የተገጠመላቸው እነዚህ እጅግ ዘመናዊ ድሮኖች ውድ ከመሆናቸው የተነሳ ኢትዮጵያ መታጠቅ ያልቻለቻቸው ናቸው። በግዜያዊነት ለስልጠና እና ክትትል የሚመጡትን ሳይጨምር ዛሬ ላይ ከ125 በላይ የአረብ ኤምሬት አየር ሃይል ስታፍ አባላት በደብረ ዘይት እና በሌሎች አየር ኃይል ግቢወች ይገኛሉ። በተለይ ከኢትዮጵያ ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚደረገው ድንበር ዘለል የድሮን ኦፕሬሽን የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በUAE ዜጎች ሲሆን የሀገር ውስጥ ሰወች ምንም አይነት ተሳትፎ የላቸዉም።
ምግብ ሳይቀር ከዱባይ የሚመጣላቸው እነኝህ የUAE ዜጎች አልፎ አልፎ የወርቅ ንግድ ቱጃሩ የሐምዳን ዳጋሎ ወንድም ከሚደግፋቸው በስተቀር የነዳጅ፣ የተተኳሽ እና የስታፍ ወጭ በሙሉ በሀገራቸው ይሸፈናል። የጀነራል ይልማ መርዳሳ ቢሮ መንደርደሪያወችን ከመፍቀድ የዘለለ ሚና የለውም።
ከፖርት ሱዳን እስከ ዳሬ ሰላም ያሉ ፖርቶችን በመቆጣጠር የወደብ ተስፋፊ (Port- imperialist) ለመሆን የምትደክመው ሀገር በሊቢያ ጀነራል ቃፍታርን፣ በሱዳን ዳጋሎን፣ በሶማሊያ ጁባ ላንድ እና ፑንት ላንድ የመሳሰሉ ራስ ገዝ ክልላዊ ኃይሎችን፣ በቻድ የመሃማት ኢድሪስ ዴቢን ሽግግር መንግስት እና ሌሎችንም ስፖንሰር በማድረግ የአፍሪካን ወርቅ በመልቀም ላይ ትገኛለች።
ኢትዮጵያ ውስጥም በሀገር ላይ ያመፀውን አብይን የምትደግፈው እና በተለይም የአማራን ህዝብ የምትወጋው ይህች ሀገር ፍላጎቷ ከእርሻ መሬት ፍለጋም አለፍ ያለ ፀረ-ኢትዮጵያዊ ፕሮጀክትንም ያካትታል።
በነገራችን ላይ ፕሮፌሰር Alex de Waal ከመለስ ዜናዊ ጋር በተለያዬ ግዜ በነበረው ውይይት የያዘዉን ማስታወሻ እ.ኤ.አ 2018 ባካተተበት "The Future of Ethiopia: Developmental State or Political Market Place" በሚለው መጣጥፉ ስር መለስን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ትልቁ ስጋትህ ምንድን ነው ሲል መጠየቁን አስፍሯል። መለስም ...ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት አንፃር የሚያስቃዠኝ ጉዳይ ቢኖር የባህረ ሰላጤው ዘውዳዊ አገዛዞች (Gulf Monarchies) የአፍሪካ ቀንድን የፉክክር ሜዳቸው ሊያደርጉ የሚችሉበት እድል መኖሩ ነው... በተለይም ታዛዥነትን (loyalty) በስልጣን ሊያከራይ የሚደፍር አመራር ከመጣ ከባድ ችግር ይከተላል የሚል ይዘት ያለው ምላሽ ሰጥቷል። ይህ ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ይከሰት ዘንድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ስሌት ውስጥ ትልቅ ፖለቲካዊ ውስልትና በመስራት የፀረ-ኢትዮጵያዊ ኃይሎች አቅም ከልክ በላይ እንዲፈረጥም በሰራው ስትራቴጅካዊ ስህተት እርሱም ከደሙ ንፁህ ባይሆንም በበቂ ትንተና ላይ የተመሰረተው የሰውዬው የፖለቲካ ትንበያ አስገራሚ ነበር።
ያ የተሰጋው የኢትዮጵያ ናሽናል ሴኩሪቲ አደጋ በመሐመድ ቢን ዛይድ እና በአብይ አህመድ ጥምረት እውን ሆኗል። ማንም ሀገሩን ማትረፍ የሚፈልግ ቢኖር ይህንን ስትራቴጅካዊ አሰላለፍ ተከትሎ ማስላት ይጠበቅበታል።
ግብዝ ካልሆንን በስተቀር መወረር እና ቅኝ መገዛት ከዚህ በላይ መገለጫ ሊኖረው አይችልም። ደሃው የአማራ ገበሬ፣ ለነፍሱ ማይሰስተው ፋኖ እየተዋጋ ያለው የውስጥ አረመኔወችን ብቻ ሳይሆን የውጭ ቅኝ ገዥወችን ጭምር ነው።
አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ
ድልና ነፃነት ለአማራ ህዝብ
የአማራ ህዝብ ባለፉት ስምት (8)አመት ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በአረመኔው ብልፅግና ስርአት ጆኖሳይድ ተፈፅሞበታል ይሄን የተፈፀመበት ብልፅግና ባዋቀራቸው ቡድኖች እና በተለምዶ ጥምር ጦርነኝ በሚለው አሽከሮቹ እና በአማራ የእግዴ ልጆች ነው ። አማራ ሲተርት ከቻልክ እደበሬ ሁን ካልቻልክ እዳህያ ከመሆን ሞትን ምረጥ ይላል ። ይህ ሲባል በሬ የጓደኘውን ደም ወይም ፈርስ ካገኘ ያጓራል የጓደኘው ደም እና ፈርስ ይከረፈዋል አማራ ከሆክ የወድሞችህ ደም በአደባባይ የተገደሉት ይከርፋህ ። ካልሆነ ግን እደአህያ አትሁን ያሲ ባል አህያ የጓደኛውን ደም እና ፈርስ ላይ ሳር ካገኘ እያሸተተ ሳሩን ይበላል እደአህያ ከመሆን ሞትን መምረጥ ጀግንነት ነው ። ለዚህ ደሞ አማራ ሆናችሁ ጥም ጦር እና ካድሬ(ካብኔ) ሆነህ የብልፅግና ስርአት ዳይበር የሆናችሁ ከቀልባችሁ ሁኑ ካልሆነ ግን ቀኑ ሊዘገይ እጂ በአማራ ህዝብ እና በአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ትጠየቃላችሁ ።የኬሚሴ ሚኒሻ ከመከላከያ ጋር የመከላከያ ልብስ ለብሰህ ማጀቴ ክላስተር ላይ የበደላችሁትን በደል በጥፍ ይከፈላል ይህ ሲባል በህዝባችን ላይ የደረሰ በደል ።
1ኛ. የአርሶ አደሩን ከብት ዘርፋል።
2ኛ. የህዝቡን አትክልትና ሰብል ዘርፍል
3ኛ.በስራ ላይ ያሉ ንፁሀን ተገድለዋል (ተረሽነዋል)
4ኛ.መስቀልበር ቀበሌ የገብረኤል ቤተክሪስታን ቁሳቁስ እና መጠበቂያውን መሳሪያ ወስደዋል
5ኛ.ነጌሶ ቀበሌ ሞላሌ ላይ አምስት ሰው ረሽነው ከብቶች ተወስደዋል
6ኛ.በመድፍ ህብረተሰቡን ያለበትን ቦታ በመደብደብ ንፁሀን ገሏል ቤት አቃጥሏል
7ኛ.ወጀድ ት/ቤትን በድሮን ደብድቦታል ተማሪዎችን አልሞ ለመምታት የታቀደ ነበረ
አገዛዙ ብልፅግና የተባለ አረመኔ ስርአት ያሰማራቸውን ጥምር ጦርን የተደራጀው የአማራ ህዝብና የአማራ ፍኖ ከላይ የተጠቀሱትን በደሎች ለመቀልበስ የተሰሩ ስራዎች ።
1ኛ.በሽምቅ የግዴ ልጆች የሆኑትን ሚኒሻ እና ፖሊስ ካራለጎማ ቀበሌ ለመግባት ሲፈልጉ አይቀጡ ቅጣት ተቀጡ
2.የማጀቴ ህዝብ መከላከያ የተባለ ገዳይን በአይናችን ማየት አንፈልግም አሏቸው በፈጠሩት ስብሰባ
3.ካራቆሪ ሚኒሻ በወጣበት ዋርድያ ሲጠብቁ እቅልፍ ወሰዷቸው በፋኖ በትር ተቅልፋቸው ሳይነቁ በዚያው አሸለቡ
4. ማጀቴን ለመቆየት አፈሩ ሁሉ እሳት ሆነባቸው በፋኖ በትር
5.ህዝብ ሰብስበው ስሐምርጫ ሲወሩ አገር እየፈረሰ ሰው እየሞተ ምን አይነት ምርጫ ነው ብለው አፋጠጧቸው
6.የመከላከያ አባል የሆኑት ሰራዊቶች እየሰረጉ ጠፉ
የአገዛዙ አሸከሮች ምን ወሰኑ
1.ማጀቴ ከቆየን በትሩም ይጠነክራል ህዝቡ ይመታናል ሰራዊታችን ጨርሶ ከድቶ ብቻችንን ነው የምቀረው ብሎ ውልቅ አለ
2.ማጀቴ ያለን ንብረት የዘረፉትን ሀብት ሳያሳቸው ከቱርክ መገድ በታች ማንም እዳይወርድ ብለው ሲያስተላልፉ የሚቀበላቸው ሲያጡ የሚመጠውን ሲረዱት ቶሎ አፈተለኩ
3.ኤፉራታና ግድም ምርጫ መረጠ አልመረጠ እኛ ቀድመን አሸንፈናል በማለት ሀዘናቸውን ገልፀው ህዝብ እደጠላቸው አረጋግጠው ሄደዋል
የፋኖ የትጥቅ ትግል ህዝባዊነቱን ያረጋግጣል
ድል ተተጨቆነው ለአማራ ህዝብ
+4
አድዋ ክፍለጦር ግዙፍ የሆነ እግረኛ የፋኖ ሰራዊት ለ11ኛ ዙር አስመረቀ‼️
በአፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ኮር አድዋ ክ/ር ከፍተኛ አመራሮች ባሉበት ማለትም አፋብን በፓሊት ቢሮ የስልጠና መምሪያ ኃላፊ፣ የበላይ ዕዝ አመራሮች፣ የመይሳ ካሳ ኮር አመራሮችና የአድዋ ክ/ር አመራሮች በተገኙበት በደማቅ መልኩ ማክበር የተቻለ ሲሆን በአርበኛ ተመስገን ወለላው ወ/አዛዥነት የሚመራው የአድዋ ክ/ር እንደከዚህ ቀደሙ በተሻለ መንገድ የሰለጠነ የፋኖ ሰራዊት ከማፍራት አንፃር ታስቦና ታቅዶ አመርቂ በሆነ መንገድ በሁለንተናዊ ዘርፍ የሰለጠነና ብቁ የሆነ ሰራዊት እንዲሁም እዝ እና ሰንሰለትን የጠበቀ መርህን ተከታይ የሆነ ስልጡን ጠንቀቅ ያለ የአማራን ክፉ አሚካላ ስርአት በሁለንተናዊ ዘርፍ የሚጋፈጥ ግዙፍ ሰራዊት 11ኛ-ዙር በማስመረቅ የአድዋን ክ/ር አሀድ መቀላቀል ችሏዋል።
©አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ህዝብ ግንኙነት ክፍል!
03/ዐ9/2018 ዓ.ም
በአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት የአሰምነው ዕዝ ቁጥጥር ስር በዋሉ አካባቢዎች አፋብን ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት ታሪካዊ የሆኑ የህዝብ ውይይቶች በድምቀት እየተካሄዱ ይገኛሉ።
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!” በሚል መሪ ቃል፣ በትግሉና በህዝቡ መካከል ያለውን ትስስር የሚያጠናክሩ ሰፊ መድረኮች በመርሀቤቴ አውራጃ በሦስት ቀበሌዎች ተካሂደዋል። በዚህም በመርሓቤቴ ወረዳ፦ የታች ቤት እረመሽት ወርካንባ ቀበሌ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ስለ ብሔራዊ ህልውናው መክሯል። እንዲሁም በአፈዘዝ በርቃቶ፦ የመርሓቤቴ ህዝብ ከትግሉ ጎን መቆሙንና በፖለቲካዊ ንቃት ራሱን እያደራጀ መሆኑን ዳግም ያረጋገጠበት መድረክ ተካሂዷል በለሚ እንሳሮ (በይድኖ በሬሳ ቀበሌም በተመሳሳይ ሁኔታ ህዝባዊ ውይይቱ የቀጠለ ሲሆን፣ የአማራ ህዝብን ብሔራዊ ማንነትና ጥያቄ የሚያነቁ ስራዎች ተከናውነዋል።
የፋኖን ምት መቋቋም ያልቻለውና በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኘው የአማራ ጠሉ የአብይ አህመድ "የብልፅግና" ስብስብ፣ እነዚህን ህዝባዊ ስብሰባዎች ለመበተን አስነዋሪ ሙከራዎችን አድርጓል።
በዚህም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሽዋ ጠቅላ ግዛት አሳምነው ዕዝ ከማህበርሰቡ ጋር ስብሰባ እያካሄደ ባለበት ቅፅበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ የአምባገነኑ ስርአት ሰራዊት ስብሰባውን ለማደናቀፍ በወረወረው የሞርተር ቅንቡላን፣ አንድ ንፁህ ከብት እረኛ ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ አድርሷል። ይህ ድርጊት ስርዓቱ ህዝብን ለማሸበር ያለውን ጽኑ ፍላጎት ቢያሳይም፣ በየቀበሌው የቀጠለው ህዝባዊ መነሳሳት ግን ከምንጊዜውም በላይ እየጠነከረ መሄዱን የደረሰን መረጃ ያረጋግጣል።
''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት''
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ግንቦት 02/2018ዓ.ም
