ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше3 931
Подписчики
+4524 часа
+1767 дней
+1 15530 дней
Архив постов
ከመከላከል በቅፅበት ወደ ማጥቃት የተቀየረው የኃይሉ ከበደ ክፍለ ጦር ፋኖዎች በድል የታጀበ አስደናቂ ተጋድሎ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር አካል የሆነው ጄኔራል ኃይሉ ከበዴ ክፍለ ጦር ፋኖዎች በወሰዱት አፀፋዊ ምላሽ የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት በተወሰደበት መብረቃዊ ጥቃት ከበባ ውስጥ አስገብቼ አፍናለሁ ብሎ የተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ራሱን ለመከላከል ተገዶ ሲደቆስ ውሏል።
የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት መነሻውን ከዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ ላልኪው ከተማ በማድረግ ወደ ዘውማርያም ቀበሌ በሦስት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰ ሲሆን አካባቢው ኔትወርክ የሌለው በመሆኑ የክፍለ ጦሩን አመራሮችና ሜካናይዝድ አፍናለሁ ብሎ ጥር 27 ለ28/2018 ዓ/ም ሌሊት 8:00 ሰዓት ላይ ከቦታው በመድረስ ጠላት በድሽቃ፣ሞርተርና ብሬን የታገዘ ተኩስ የከፈተ ሲሆን እስከ ጥር 28/2018 ዓ/ም ቀን 6:00 ሰዓት ድረስ በተደረገው ከፍተኛ ትንቅንቅ አካባቢያቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁት ፋኖዎቹ በመጣበት ሦስት አቅጣጫ የገባውን ኃይል በሦስት አቅጣጫ በመቁረጥ ጠላት እርስ በእርሱ እንዲመታታና ከፋኖዎች ጥይት የተረፈው ኃይል ራሱን እየተከላከለ ወደ መጣበት ተመልሷል።
በተደረገው ከባድ ትንቅንቅ 23 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ30 በላይ ቁስለኛውን ይዞ ተመልሷል፤ ዘጠኝ ክላሽንኮፍ፣540 የክላሽ ተተኳሽ፣16 የእጅ ቦምብ፣ሰባት የደረትና አምስት የወገብ ትጥቅ ተማርኳል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ መምህር ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 29/2018 ዓ/ም
ሰበር የድል ዜና!!!
የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ጥምር ሰራዊት በቋራ ምድር ተደመሰሰ!
የመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር 4ኛ ቀኑን ያስቆጠረ እልህ አስጨራሽ አውደ ውጊያዎችን በቀጠናው እየተፋለመ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ይገኛል። በትናንትናው እለት ጥር 28/2018 ከሌሊቱ 8:00 ስአት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ስአት ቋራ ወረዳ አባድግሱ ከምትባል ቦታ የተሰራው ጀብድ በአገዛዙ ግብስብስ ሀይል ላይ ከፍተኛ ሽንፈትን እንዲያስተናግድ አድርጓል።
በመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ማንዴላ እያዩና በኮሩ ከፍተኛ አመራሮች የተመራው ይህ አውደ ውጊያ ጠላትን ከበባ ውስጥ በማስገባት ክፉኛ ሲርበተበት ውሎ ያመሸ ሲሆን የፋኖ ሰራዊት አሰላለፍ: አድዋ ክ/ጦ ከጀርባ በስተምዕራብ ፣ የኮሩ ተወርዋሪ ከፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦ ከተውጣጡ ሰራዊቶች ጋር በመሆን በቀኝ በኩል ፣ ኦሜድላ ክ/ጦ ነብሮ ብርጌድ በግራ በኩል እና ካራማራ ክ/ጦ አሳምነው ብርጌድ ከጠላት ፊት ለፊት ሆነው የተሰለፉ ሲሆን ፤ ይህ የፋኖ አሰላለፍ ያስደነገጠው የአገዛዙ የብርሀኑ ጁላ ደም መጣጭ ሰራዊት በጭንቀት መውጫ መግቢያ ሲያጣ በአንድ በኩል ከፊት ለፊት ለመውጣት ሙከራ ቢያደርግም የበረሀው ፈርጦች የአሳምነው ልጆች ወይ ፍንክች በማለት ትንቅንቁን አፏፉመውት የጠላት ሀይል ነብስ ውጭ ነብስ ግቢ ሆኖበት አዳሩን በእሳት አለንጋ ሲለበለብ አድሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ያልቻለውን በየቦታው እያዝረከረከ በየቦታው የድረሱልኝ ጥሪውን እየቀባጠረ ወደ መጣበት ወደ ፋርሽዋ ሊመለስ ችሏል።
በዚህ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ከፍተኛ አመራሮች 50 አለቃ ማዕረግ ያለው እስከ ወዲያኛው የተሸኘ ሲሆን በየቦታው ያዝረከረከውን አስክሬን የፋኖ ሰራዊት የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር ሊቀብር ችሏል።
በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የተገኘ ድል:
ሙት = 36
ቁስለኛ = 45
የተማረከ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ = 12
1የዲሽቃ አፈሙዝ
ተተኳሽ = 650 የክላሽ
በዚህ አንድ ሳምንት ከአገዛዙ ጥምር ሰራዊት ጋር በሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ አገዛዙ ከሽንፈት የማያድነውን የኔት ወርክ መዝጋት ዘመቻ እንደ አንድ አማራጭ በማድረጉ በግንኙነት ማነስ ከህዝብ ጀሮ ያላደረስናቸው አውደ ውጊያዎች የሚከተሉት ናቸው:
1.ጥር 26_27/2018 የአድዋ ክ/ጦ በጋዝጌ ቀጠና ሮብ ገበያ እና ኤረፍት በተደረገው የሁለት ቀን አውደ ውጊያ የአገዛዙ የመከላከያ ሰራዊት ተብየው እና ጋሻአጃግሬው ሚኒሻ ክፉኛ ሽንፈትን አስተናግዷል።
በዚህ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት መነሻውን ሰሜን አቸፈር ሊበን ተነስቶ ወደ ጋዝጌ ቀጠና አርሶአደሩን ትጥቅ ለማስፈታት እና ሁለንተናዊ ጀኖሳይድ ለመፈፀም አስቦ ቢንቀሳቀስም የመይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር አድዋ ክ/ጦ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ከፍተኛ ኪሳራን ከማስተናገዱ ባሻገር ከበባ ውስጥ ገብቶ እጅ መስጠት ሲጀምር በሁለት አቅጣጫ ከጃዊ ጃይማላ እና ከአለፋ ሻሁራ ተጨማሪ ሀይል ደርሶ ሊያስለቅቀው ችሏል።
በሁለት ቀን አውደ ውጊያ የተገኘ ድል: ከ20በላይ የታሰሩ ንፁሀን አርሶአደር መሳሪያ አላችሁ አስረክቡ በማለት በግፍ የታሰሩትን ማስፈታት ተችሏል። ከዚህ በተጨማሪ የአገዛዙ ሰራዊት ሙት እና ቁስለኛ እንደሚከተለው ይሆናል።
ሙት = 30
ቁስለኛ =ከ38 በላይ
5 ምርኮኛ ሰራዊት
የነፍስ ወከፍ መሳሪያ = 10
ከ3000በላይ ተተኳሽ
የአንድ ሬጅመንት ሙሉ የእጅ ስልክ
2.ስቦ በመምታት ኦፕሬሽን ከአድዋ ክ/ጦ ፣ ከፊውታራሪ ገበየሁ ክ/ጦ እና ከኮሩ ተወርዋሪ በተውጣጡ የፋኖ ሀይሎች የአገዛዙ ሰራዊት ከአባድግሱ ወደ ባርባስ ወደ ምትባል ገዥ ቦታ ለኩሶ ወደ ኃላ በመውጣት የሙት ወረዳ ላይ/ባርባስ ጥር 26/2018 ከቀኑ 9:00 ስአት ጀምሮ ለ2ስአት ያህል በተደረገው አውደ ወጊያ የጠላት ሀይል ኩምሽሽ ብሎ ሙት እና ቁስለኛ በመሆን እንደ ገና ወደ ኃላ አባድግሱ ወደ ምትባል ቦታ ሊመለስ ችሏል።
በዚህ አውደውጊያ የተገኘ ድል:
ሙት = 5
ቁስለኛ = 12
3.በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነጋዴ ባህር ከተማ አቸራበር በፊታውራሪ ገበየሁ ክ/ጦ ታጠቅ ብርጌድ 2ኛ ሻለቃ ቃኝ በሆነችው ሻንበል1 አንድ አስደማሚ ኦፕሬሽን ተደርጓል።
ለአገዛዙ ሰራዊት አጋር የሆነው ሆድ አደር ሚኒሻ መነሻውን ከጭልጋ ወረዳ ወደ ነጋዴ ባህር ሲንቀሳቀስ ቀድመው መረጃን በማፈንፈን የሻለቃዋ ቃኝ በፍጥነት ደፈጣ በመያዝ በሚኒሻው ላይ መብረቃዊ ጥቃት በማድረስ ከቦታው መሰወር ችላለች።
በዚህ ልዩ ኦፕሬሽን የተገኘ ድል:
ሙት = 5
ቁስለኛ = 8
5 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እስከ መሉ ትጥቁ
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፈርጣጩ የአብይ ወንበር አስጠባቂ ጥምር ሰራዊት በማፊያ አመራሮች እየተመራ ፋኖን እናፅዳ እያለ እራሱ እየፀዳ የሀገሪቱን ወጣት በስሜት በሀገር መከላከያ ስም እየነገደ አማራ ላይ የተሰጠውን የአውሬውን ተልእኮ ለመፈፀም ቢሞክርም ከመጥፋት ግን አላዳነውም፤ የሀገሪቱን እንቁ ሀብት እያግበሰበሰ የወጣቱን ደም እየለገሰ በስልጣን መቆየት እንደማይቻል ክንደ ብርቱው የፋኖ ሰራዊት የሚያስመዘግበው ውጤት ማሳያ ነው።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብን ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ መይሳው ካሳ ፪ኛ ኮር
ጥር 29/2018
ታጋይ ይሞታል ትግል ግን ይቀጥላል!!
በደቡብ አማራ ቀጠና በመርሐቤቴ ወረዳ፣ በየይድመቆ መርከዥ ቀበሌ፣ ልዩ ስሙ ሞሐርባ በተባለ ስፍራ፤ የአንድ ጀግና ታሪክ በደም ተጻፈ። አርበኛ (ጎንደሬው አልታዩ) የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የደቡብ አማራ ቀጠና፣ አሳምነው ዕዝ፣ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ ኮር፣ ናደው ክፍለጦር ስልጠናና ክህሎት መምሪያ እንደ እሱ ብዙህ ጀግኖችን ያፈራ አዋጊ ተዋጊ የመከላከያ ተመላሽ ኮማንዶ የነበረው አርበኛ ጎንደሬው አልታዩ አጥሌ በሚባል የዛው አካባቢ ተወላጅ ባንዳ ሚኒሻ ተመርቶ ከመጣው የአረመኔው አብይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት ኃይል ጋር ገጥሞ የጀግንነት ጥግ ምን እንደሆነ ለዓለም አሳይቶ በትናንትናው ዕለት በክብር ተሰውቷል።
ለአላማው በቁርጠኝነት እና በጀግንነት ሰማዕትነትን የተቀበለው ይህ አንበሳ፣ "እኔ ልሙት አንቺ ግን ሰንበቺ ፤ አለሁልሽ ሀገሬ አንቺ አትሙቺ" የሚለውን ቃለ መሀላ በልቡ ሰንቆ በእሳት ሊፈተን ገባ። ለምን እንደሚዋጋ የማያውቀውን፣ ግራ የተጋባውንና የሕዝብን ብሶት የማይረዳውን የገዥውን ሥርዓት ሠራዊት ፊት ለፊት ተጋፈጠው።
"እኔ ወድቄ አንቺ ግን ሰንብቺ፣
አለሁ ሀገሬ አንቺ አትሙቺ፤
አንቺ ሙቺልኝ እኔ ጎሽዬ፣
ወጥቶ የለም ወይ ሰንደቅሽን ብዬ"
ብሎ በሞቱ ቆርጦ ከወጣው ከዚህ ረመጥ ፋኖ ጋር የገጠመው ጠላት፣ የእሳቱን ወላፈን መቋቋም አልቻለም። ወትሮም ወርቅ በእሳት ተፈትኖ ያልፋልና፣ ይህ ልበ ሙሉ ጀግና ለአንድ ሰዓት ያህል ብቻውን ሆኖ እሳት በሚተፋው አፈሙዝ ጠላትን አርበደበደ።
6 ጠላትን ጥሎ፣ ከ5 በላይ አቁስሎ ታሪኩን በወርቅ ብዕር ጻፈ። በመጨረሻም ጠላት በእጁ እንዳይነካው፣ በገዛ ጥይቱ ክብሩን ጠብቆ በጎማ ምድር የሰማዕትነትን አክሊል ደፋ።
የፈሪዎች ክፋት ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው፣ ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው" እንዲሉ፤ ጀግናው ካለፈ በኋላ እንኳን አስክሬኑ ያስፈራቸው ፈሪዎች፣ የተለመደውን የጭካኔ ተግባር በሬሳው ላይ ፈጽመው ውርደት በተሞላበት ቆራርጠው ጣሉት።
ታሪክ እሱንና መሰል የቁርጥ ቀን ልጆችን መቼም አትረሳም፤ በትውልድ ዘንድ ስማቸው እየታወሰ ለዘላለም ይኖራሉ። በጀግኖች ደም የሕዝባችን ነፃነት እውን ይሆናል! ክብር ለሕዝብ ነፃነት ለተሰዋው ሰማዕታት!
ድል ለአማራ ሕዝብ!!!!
መንፈሶች ነን!!
የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከምሽቱ 4:45 በአምበር ከተማ በፈፀመው ኦፕሬሽን መርጌታ ጌታነህ ያየህ እና ፈንታ አበነህ የተባሉ ባንዳዎችን አፍነው በማውጣት አስደናቂ ጀብድ ፈፅመዋል።
ጥር 29/2018 ዓ.ም
===================================
መንፈሶች የ206ኛ ኮር አዳኝ ቡድን ከምሽቱ 4:45 በአምበር ከተማ በወሰደው አስደናቂ ኦፕሬሽን ፈንታ አበነህ የተባለውን የሚኒሻ ብሬን ተኳሽ እና የጠለት የመረጃና ደህንነት አባል በመሆን የአረመኔውን ሰራዊት ከፊት በመሰለፍ መንገድ በመምራትና በርካታ ንፁሐንን እየጠቆመ ሲያሳስር ሲያስረሽን የነበረውን መርጌታ ጌታነህ ያየህን በቁጥጥር ስር በማዋል ከባዱን ተልዕኮ በብቃት ተወጠዋል።
የአረመኔው ሰራዊት የሚመካባቸውን አገልጋዮችን በማናጠል ተደጋጋሚ ጥቃት የፈፀመው የኮሩ አዳኝ ቡድን ከአፍታ ቆይታ በኋላ በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሌሊቱ 5:10 በወንቃ ትምህርት ቤት በመሸጉት ሚኒሻዎች ላይ በፈፀመው የቦንብ ጥቃት 2 (ሁለት) ቀንደኛ ሚኒሻዎች ሲገደሉ 4(አራት ) ከባድ ቁስለኞች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተረጋግጧል።
በቀጠናው አዲስ ክስተት የሆነው 206ኛ ኮር በሞት አይፈሬ ነበልባል ተዋጊዎችና በጀብደኛ የሰራዊት አባላቱ አኩሪ ድል እያስመዘገበ ሲሆን ከትናት በስተያ በአድማ ብተናና የፖሊስ አሰልጣኝ የሆነውን ፻ አለቃ በየነ ጌትነትን በመግደል በደብረ ማርቆስ ከተማ በመሸገው የአረመኔው ሰራዊትና ካድሪ ላይ ከፍተኛ ሽብር መልቁም የሚታወስ ነው።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
Repost from ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት ለመላው የፋኖ አመራሮች!"
"ከብልፅግና የደህንነት መሥሪያ ቤት (ከቁጥር 604) ለፋኖ አመራሮች ስልክ እየተደወለ ይገኛል። በመሆኑም ማንኛውም የአመራር አካል ከዚህ ቁጥር የሚመጣን ጥሪ በፍጹም እንዳያነሳ እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን። ይህ መረጃ ለሁሉም አመራሮች እንዲደርስ በከፍተኛ ፍጥነት 'ሼር' (Share) በማድረግ ተባበሩ።"
ይህ መልዕክት ለምን አስፈላጊ እንደሆነና ሊከተሉ የሚችሉ አደጋዎችን በሦስት ዋና ነጥቦች ማየት ይቻላል፡
1. የደህንነትና የመረጃ ጥበቃ
የደህንነት መሥሪያ ቤቶች አጭር ቁጥሮችን (እንደ 604) ተጠቅመው የሚደውሉት መረጃ ለመሰብሰብ ወይም የአንድን ግለሰብ ማንነት ለማረጋገጥ ሊሆን ይችላል። ስልኩ በሚነሳበት ጊዜ ተደዋዩ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ (Location) በቴክኖሎጂ ለመለየት ስለሚያመች፣ ጥሪውን አለማንሳት ለደህንነት ሲባል ተመራጭ ነው።
2. የስነ-ልቦና ጫና (Psychological Tactics)
እንዲህ ያሉ ጥሪዎች በአመራሮች መካከል ጥርጣሬን ለመፍጠር፣ ግራ ለማጋባት ወይም "ድርድር እንጀምር" በሚል ሽፋን መረጃ ለማውጣት ሊደረጉ ይችላሉ። ጥሪውን ባለመቀበል የጠላትን የመረጃ ምንጭ መዝጋት ይቻላል።
3. የመረጃው ተደራሽነት (Urgency)
"ሼር በፍጥነት ካልተሰራጨ፣ አንድ ወይም ሁለት አመራሮች ባለማወቅ ጥሪውን አንስተው ለአደጋ ሊጋለጡ ስለሚችሉ ነው። በመሆኑም መረጃውን በየደረጃው ላሉ የአደረጃጀት መዋቅሮች ማድረስ አስፈላጊ ነው።
በተጨማሪም ለጥንቃቄ ያህል፦ አመራሮች የዲጂታል ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ስልካቸውን በየጊዜው "Airplane Mode" ላይ ማድረግ ወይም ኢንተርኔት በማይጠቀሙበት ሰዓት መዝጋት ይመከራል።
❤Dawit fano አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉 https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
ሌላ የትም ቦታ የማያገኟቸውን የፋኖ አውደ ውጊያ መረጃዎች ይዞ በየዕለቱ ይቀርባል፣ በ30% ቅናሽ አሁኑኑ 1800 የደረሱትን ተከታታዮች ሰብስታክ ላይ ይቀላቀሉ። ሊንክ
ፋኖ ከወልድያ በቅርብ ርቀት በወሰደው የስቦ መምታት የጦር ታክቲክ በርካታ የአገዛዙ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ድል ተቀዳጀ!
የፋኖ አባላቱ የአገዛዙ ወታደሮችን ከወልድያ ከተማ ጃርሣ መድኃኒአለም ተብሎ ወደ ሚጠራው የከተማዋ አከባቢ ስበው ካስገቡ በኋላ 360° በመክበብ እንዳይወጡና እንዳይሸሹ በማድረግ ዶግ አመድ አድርገዋቸዋል።
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ ዐምሓራ ኮር1 አሳምነው ክ/ጦር ስር ከ4ኛ እና ከ5ኛ ሬጅመንት የተወጣጡ ጥቂት የፋኖ ኃይሎች ትናንት ጥር 27/2018 ዓ/ም የስቦ መምታት የውጊያ ታክቲክ ተጠቅመው በወሰዱት ብርቱ እርምጃ የጠላት ኃይልን አከርካሪ በመስበር ድል መቀዳጀታቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በአሳምነው ስም የሚጠሩትና በአሳምነው ስም እየፎከሩ የጠላት ምሽግን የሚንዱት የፋኖ አባላቱ፡ ጠላትን በተደጋጋሚ ጊዜ በመቱበት ወልድያ ከተማ ዙሪያ ዛሬም የፋሽስቱ ሰራዊትን በአፈሙዝ እሳት ገርፈው ቀብረውታል።
የጠላት ኃይል ከየጁገነት ወልድያ መነሻውን አድርጎ በከተማዋ ዙሪያ ጃርሳ መድኃኒአለም ተብላ ወደምትጠራው አከባቢ ያቀና ሲሆን፡ የፋኖ አባላቱም መንገድ ከፍተው አሳልፈውታል።
የአገዛዙ ወታደሮች ጃርሳ ከደረሱ በኋላ የተተናኮሳቸው ኃይል ባለመኖሩ ድንጋጤና ጥርጣሬ ተጋብቶባቸው በአስቸኳይ አከባቢውን ለቀው ወደ ወልድያ ለመፈርጠጥ ሲሞክሩ፡ የፋኖ አባላቱ "መግባት እንጂ መውጣት የለም" በሚል የጥቃት ዶፍ አውርደውባቸዋል።
በዚህም በርካታ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን፡ ከወልድያ መቻሬ ተጠምዶ ሲሰጣቸው በነበረው የከባድ መሣሪያ ሽፋን ተጠቅመው ሙትና ቁስለኛቸውን ተሸክመው ወደ ወልድያ ከተማ ፈርጥጠዋል።
የጠላት ብልፅግና ወታደራዊ ኃይል ወልድያ ዙሪያን ጨምሮ በምስራቅ ዐምሓራ ቀጠና በፋኖ በሚወሰድበት ጠንካራ እርምጃ፡ ለሰዓታት ቆሞ መዋጋት በማይችልበት ሁኔታ ተሽመድምዶ ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላቂ ኪሳራን እየተከናነበ ይገኛል።
በሸዋ ደራ የተፈፀመ የግፍ ግፍ
ጥር 26 ቀን በደራ ወረዳ "ካራ ኦሮጎ" በተባለ ስፍራ በኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች የጭካኔ ጥግ የታየበት ግፍ ተፈፅሟል። ታጣቂዎቹ ንጹሃንን እያፈሱ ወደ እገታ ስፍራ ሲነዱ፣ አንዲት የ6ወር ጨቅላ ህፃን የታቀፈች ውብዬ ተፈራ ይተባለች እናትን ለይተው አቁመዋታል። ታጣቂዎቹም ጨቅላውን ሕፃን ከእናቱ እቅፍ ቀምተው ማንም በሌለበት ምድረ በዳ ጣሉት ልጇን ጥሎ መሄድ ያላስቻላት እናት ግን በእናት አንጀቷ እየተንስፈስፈች ልጄን እያለች እየጮኸች ተማጸነች ግፈኞች ግን ጩኸቷን ችላ ብለው ልጇን መሬት ላይ ጥለው እሷን በጉልበት ወደ ከእገታው ስፍራ መሳሪያ ደግነው ወደ በረሃው ነዷት።
በኋላም ወደ ጫካው በረሃ እየገፉ ሲሄዱ፣ እናቲቱ በሐዘንና በድካም በመዛሏና እነሱ ከሚጓዙበት ፍጥነት ጋር መሄድ ባለመቻሏ፣ እንደማይጠቅም ዕቃ እሷንም እንደ ልጇ መንገድ ላይ ጥለዋት ሄደዋል። ይህች እናት በታአምር ከአውሬ ተርፋ በስዎች እርዳታ ጉንደ መስቀል ገባች፣ የ6 ወር ጨቅላ ልጇ ግን መሬት ላይ ተጥሎ ቀረ እናትም የሐዘን ሲቃ እያሰማች የቁም ሞት ሞተች።
ይህ ሁሉ ድርጊት በሚፈፀምበት ወቅት የመንግስት የፀጥታ ኃይል በቅርብ ርቀት እያለ ምንም ዓይነት እርምጃ አለመውሰዱ ታጣቂዎቹ በነፃነት እንዲጨ*ፈጭፉ ፈቃድ እንደተሰጣቸው ማረጋገጫ ነው።
የአማራ ፋኖ አውደ ውጊያዎች ለመከታተል ከታች ያለውን ሊንክ ይወዳጁ!!
@abcdefghijklmnopqrstuvwxyz071167
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምስረታን አስመልክቶ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ በበርካታ ሚዲያወች ለህዝብ እንዲደርስ ሆኗል።
ስርጭቱን ላስተላለፋችሁ መድረኩን ላስተባበራችሁ፣ ዝግጅቱ እንዲሳካ በተለያዬ መንገድ እገዛ ላደረጋችሁ፣ በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ጥያቄወችን በማቅረብ ጭምር ለተሳተፋችሁ የሚዲያ ሰወች እና ጋዜጠኞች ምስጋና እናቀርባለን።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
የአረመኔው አብይ አህመድ ኃይል በመርሐቤቴ የፋኖ አመራር ቤተሰቦች ላይ እገታና የንብረት ውድመት አደርስ!!
የአረመኔው አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ኃይል የአማራ ፋኖዎችን ብትር መቋቋም ሲያቅተው ደቡብ አማራ ቀጠና መርሓቤቴ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር በበፍቃዱ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ አርበኛ በላቸው እሸቴ ቤተሰቦች ላይ ያነጣጠረ የግድያ፣ የአፈና እና የንብረት ማውደም ድርጊት እየፈፀመ ይገኛል።
በመሆኑም ድርጊቱ የተፈጸመው መርሐቤቴ አውራጃ፣ ደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ሰረር ኩላ አካባቢ ጥቃቱ የተፈጸመ ሲሆን ከአርበኛ በላቸው እሸቴ ጋር ያላቸውን የሥጋ ዝምድና መሠረት በማድረግ ሲሆን፤ በወቅቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚከተሉት ግፎች ተፈፅመዋል። ይሁንና የአርበኛው የቅርብ ቤተሰቦች የሆኑት አቶ ተሰማ ካሰኝ (አጎቱ) እና ወይዘሮ ፀሃይ ታለማ (የታናሽ ወንድሙ ባለቤት) ታፍነው ወደ ጉንዶ መስቀል ተወስደዋል።
እንዲሁም የአርበኛው አባት የሆኑት የአቶ እሸቴ አቢ ሶስት የቁም ከብቶች የተገደሉ ሲሆን፣ የመኖሪያ ቤት በአገዛዙ ኃይሎች ቃጠሎ ደርሷል። በተጨማሪ፣ ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ቤቶችም በቃጠሎ እንዲወድሙ አድርጓል። ጥቃቱ የተፈፀማባቸው ግለሰቦች ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ነገር ግን የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ በሚል ምክንያት የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ኃይል የአሳምነው አናብሶቶችን ፊት ለፊት ገጥሞ ማሸነፍ ሲያቅጠው በህዝባችን ላይ ግፍ እየፈፀመ ይገኛል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!,ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
አርበኛ አማረ ታዘዘ
ጥረ 28/05/2018 ዓ.ም
ጀነራሎች እና የክ/ጦር አዛዦች የተሰው የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ደሞዝ ለ6 ወራት ይቀበላሉ።
206ኛ ኮር ጥር 28/2018 ዓ.ም
===================================
አለሙ አንዳርጌ ይባላል የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ፋይናስ ቡድን ኃላፊ ሲሆን ከአረመኔው ሰራዊት በመክዳት 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር ተቀላቅሏል። ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ የመከላከያ ሰራዊት በከፈታቸው የእርስበርስ ጦርነቶች ሁሉ የተሳተፈው አለሙ አንዳርጌ ለአምስት አመታት በቀጠለው ውጊያ የመከላከያ ሰራዊት የራሱን ህዝብ ከመጨፍጨፍ ባለፈ አንዳችም ለውጥ እንዳላመጣ ይናገራል።
በተለያዩ ከተሞች በተለይም ከኦሮሚያና ደቡብ ታፍሰው ወደ ጦርነት የሚማገዱ ታዳጊዎችን ሞት ተመልክቻለው የሚለው ነባሩ ወታደር ከማሰልጠኛ ወጠው ወደ ግንባር የተሰለፉ ምልምል ወታደሮች እልቂት በመከላከያ ሰራዊት ታሪክ እጅ አስከፊ እንደሆነም መስክሯል።
በአለፉት 3 አመታት ከአማራ ህዝብ ጋር በተደረገው ውጊያ የሰራዊቱ ሞትና ፍለስት ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ ጀነራሎችና የክ/ጦር አዛዦች የተሰው የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ደሞዝ ለ6 ወራት በማንቀሳቀስ ለራሳቸው ጥቅም እንደሚያውሉ ባደረግነው የፋይናስ ምርመራ ውጤት ማረጋገጡን ተናግሯል።
የምዕራብ ዕዝ 401ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ፋይናስ ቡድን ኃላፊ በመሆን ለሶስት አመታት ያገለገለው አለሙ አንዳርጌ በንፁሃን ፍጅትና ሰቆቃ መካከል የሚደረገውን ጦርነት እንደ ትልቅ ካምፓኒ የሚጠቀሙት የጦር መኮንኖችና ጀነራሎች በጦር መሳሪያ እና በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ንግድ እንደበለጸጉ ገልጿል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
