ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Открыть в Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Больше4 138
Подписчики
+724 часа
+2087 дней
+1 20130 дней
Архив постов
\\\\\\\\\~ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በታሪኩ ጦርነት አሸንፎ አያቅም የምንለው ከበቂ መረጃ ጋር ነው። ለምን ካላችሁ በታሪክ ከኢትዮጵያ ጋር በተደረጉ ጦርነቶች ፋኖ የአንበሳውን ድርሻ ወስዷል። በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ጦርነቶች በድምር ከ85% እና ከዛ በላይ የሚሆነው የአማራ ገበሬ /ፋኖ ተዋጊ ነበር ።
እንጅ በተለይ አብይ አህመድ ያደራጀው ዘረኛና ደካማ ሰራዊት የንፁሀንን ንብረት ከመዝረፍና ንፁሀን ህፃንና እናቶችን ከመድፈር ያለፈ ምንም አይነት አቅም እንደሌለው ከዚህ በታች ከትግራይ ጋር በተደረገ ጦርነት የተማረከው የአምቦና የሰላሌ የባሌሮቤ ወጣት ምስክር ነው።
ለማንም ከእንግዲህ በኋላ ሰሜን ከሰሜንጋ ምንም አይነት ግጭት እንዳታስቡት!
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
ምሽት 2:30 ጠላት ከራሱ ምሽግ ላይ ተደመሰሰ❗
[ታሕሳስ 22/2018ዓ.ም]
አሸናፊነትን ከትግል አባታቸው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ በተግባር የተማሩት ውባንታዊያን ምሽት 02:30 ከደብረ ታቦር ከተማና ከማሕደረ ማርያም ከተማ መሐከል ካለው የጠላት ምሽግ ልዩ ቦታው ''ቴሌ'' ተብሎ ከሚጠራው ምሽግ ላይ ጠላት በቦምብ ተደምስሷል። ጠላት በተሰባሰበበት ሁኔታ ጥበበኞቹ የጥበብ ልጆች አምሐሮቹ የጠላትን ቀይ መሥመር ቀጠና አልፈው፣ ምሽጎቻቸውን ሁሉ አልፈው፣ ጠላት በብዛት በተሰባሰበበት ሁኔታ ብዛት ያለው ቦምብ በመጣል በአቢይ ሸኔ ዙፋን ጠባቂዎች እሣተ ገሞራ አዝንበውባቸዋል። ከቦንብ ፍንዳታዎች በኋላ በተኩሥ ልውውጥ አንድም ፋኖ ጫፉን ሳይነካና ዕቅዳቸው 100% ተሳክቶ ወደ መዳረሻቸው ተመልሰዋል።
የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ትውልድ ባርነትን እምቢኝ ሲል የዕውነት ለመታገል ቆርጦ፣ የአገዛዙን ተዋጊ አምበርክኮ፣ ቁማርተኞችን ሁሉ አናፍጦ፣ አእምሯዊና አካላዊ ብቃቱ ጎልብቶ፣ የሚሞትበትንና የሚገድልበትን አላማ ለይቶ ያወቀ፣ ከአገዛዙ መከላከያም ሆነ ከበፊቱ አምሐራ ልዩ ኃይል በተሻለ ሁኔታ የአሸናፊነትን ሥነልቦና ተላብሶ፣ ወታደራዊ ሥነምግባሮችን በትክክል ተግብሮ፣ ለትግሉ ዋጋ የከፈሉ የትግል ጓዶቹን ራዕይ አሥቀጥሎ፣ ሕዝባዊነትን አሥቀድሞ፣ ሥለ ዓምሐራዊ ትግል የትኛውንም ዋጋ ለመክፈል ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ፣ ለትግሉ እሥከ ሕይወቱ ሕቅታ ታምኖና በጥቅሉ ዓምሐራነትን አሥቀጣይ እሣተ ገሞራ ውባንታዊ ነፍጠኛ ትውልድ ተፈጥሯል።
የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ውባንተነትን ሲምልበት ለማሥመሰልና ሊነግድበት ሳይሆን የምር ውባንታዊ ግብርን የወጣበትን የተቀደሰ ፋኗዊ የትግል መንገድ በደሙ አክብሮ፣ ቁማርተኞችን በ360° አነጽሮ፣ ሐሳዊ ፖለቲከኞችንም በሰፌዱ አንጓሎ፣ ባሕር ማዶ ዳያሥፖራዎችንም በልካቸው ልክ እንዲያድቡ አድርጎ፣ ሐገርኛ ወይንም ጽንፍ የሄዱ ጎጠኞችን ዓምሐራነትን እንዲተነፍሱ አድርጎ፣ የአገዛዙ አራዊት ሰራዊትን ቀነፍጡ አድቅቆ፣ ዓምሐራዊ ዕሴቶችን አክብሮ፣ ለዕኩልነትና ለፍትሕ ከፊት ተሰልፎ፣ ጓዳዊ ፍቅርን ሲበዛ ተግብሮ፣ መነሻና መዳረሻ የትግል ግቡን አውቆ፣ በሞቱ ዓምሐራነትን አድኖና በጥቅሉ በተቀደሰው የአምሐራ ትግል ያለማጋነን በዓምሐራ ምድር ዕንቁና አብሪ ኮከብ ሆኖ የወጣ የፋኖነት ተምሣሌት ነው ሰራዊቱ።
ኅልውናችን በተባበረ ዓምሐራዊ ክንዳችን👊✊
አፋብኃ ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት
ፈለገ ውባንተ አባተ ፋኖ ኃቅአለው ዘ ብሔረ ዓምሐራ
ጎንደር/ዓምሐራ/ኢትዮጵያ
ታሕሣሥ 22/2018ዓ.ም ምሽት 02:30
ተወደደም ተጠላም ከዚህ በኋላ በየትኛውም የአማራ ግዛት ላይ እርስ በርሱ የሚታኮስ የፋኖ ዕዝ የለም!!
አንድነት ብቻ!! የጋራ ጠላታችን ከብርት በጠነከረ መንገድ መታገል መቻል አለብን ሞት ለብልፅግና መንግስት።
አሳምነው ፅጌን ለምን ገደሉት ?
ስጋውን ላይበሉት ደሙን ላይጠጡት 😭
አንድ ሁኑ ስላለ ድንገት ቢፈሩት ::
አንድ ሁኑ 🫵 የአደራ ቃሉ ነው 🙏
አንድነት ኃይል ነው !!!
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ 🫰
የኢትዮያንና የአማራ የሕዝብ ድምፅ ⚖️📷 ነው። ዴቭ
በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
"ምሁራን ወይስ እ ውራን...?"
በዋናነት "ፕሮፌሰር፣ዶክተር፣ኢንጂኔር..." ወዘተ.. የሚል መጠሪያ ከፊት ተሸክማችሁ "ምሁራን" እየተባላችሁ የምትጠሩ በውጭም በውስጥም ያላችሁ ግለሰቦች (በአማራ የሕልውና ትግል ውስጥ)
"ምሁር" ማለት ምን ማለት ነው?
- በአውራጃ፣በሰፈርና በጎጥ ተወሽቆ የአማራ የሕልውና ትግልን መከፋፈል ነው እንዴ?
-ፖለቲካዊ ሴራው ገብቶት ሳይሆን በተግባር የሚፈፀምበት አካላዊ ጥቃት አስገድዶት ራሱን ከመጥፋት ለመከላከል አንድያ ሕይወቱን የሚሰጠውን አርሶ አደር፣ ባልተገራ ፖለቲካዊ ሴራ፣በአካባቢና በመንደር ከፋፍሎ ማገዳደል ነው እንዴ?
- ሁሉን ነገር ትተው፣ መሬት ላይ ከአገዛዙ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ጥቃት፣ከድሮን፣ ከእባብና ጊንጥ ጋር እየታገሉ፤ማንነትን፣እምነትንና ባህልን ለማቆየት ዋጋ የሚከፍሉ የፋኖ መሪዎችን ሌት ከቀን መስደብ፣ማዋረድ፣መከፋፈልና ማጋጨት ነው እንዴ?
- ለአማራ ሕዝብ የሕልውና ትግል የሚጠቅመውን ሐቅ ትቶ፣ የግል ፖለቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያው ጥቅማችሁን ብቻ ሊያሳካ ይችላል የምትሉትን ግምታዊ መሰመር እርስ በእርስ እያገዳደሉ መከተል ነው እንዴ? አይመስለኝም።
ይልቁንስ፦
- ምሁርነት፦ በየዘርፉ ጥናትና ምርምሮችን በማድርግ ሕቀኛ፣የተፈተነና ለውጥ ሊያመጣ የሚችልና የሚያመጣ ስራ መስራት ነው። ይህንን ትርጓሜ ወደ ትግላችን ስንለውጠው የሕልውና ትግሉ አሁን ያሉበትን መሰረታዊ ችግሮች ምሁራዊና ሙያዊ( ፖለቲካዊና ወታደራዊ) በሆነ መንገድ በጥናትና ምርምር ነቅሶ በማውጣት በቅንነት ችግሮቹን ፈትቶ ለግብ እንዲበቃ መስራት ማለት ነው።
- በጥናትና ምርምር ላይ በመመርኮዝ የጋራ መግባቢያ የትግል ሰነዶችን፣ ምክረሐሳቦችን፣ ፍኖተ መርኆችንና ሌሎች ለፋኖ የሕልውና ትግል ጠቃሚ ሰነዶችን ማዘጋጀት፣በተዘጋጁት ሰነዶች ዙሪያ እንደያመችነቱ በጋራ፣በተናጥልም ሆነ በቡድን ስልጠናዎችን መስጠት፣ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣የትግል ሂደቱንና ለውጡን እየተከታተሉና አየገመገሙ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ... ወዘተ..እንጂ...
-ምሁርነት፦ በተለይ በሕልውና ትግል መንደሬነትን፣አካባቢያዊነትን፣ ጎጠኝነትንና በሰፈር መርመጥመጥን አብዝቶ ይጠላል። ቧልተኝነትን፣አድር ባይነትን፣አስመሳይነትንና ሆዳምነትን ይፀየፋል።የኀሊናና የሆድ እስረኝነትን አያዎድም። ቅጥፍናንም ይታገላል።
- ምሁርነት ከተለመደው ዘፈቀዳዊ ሁናቴ እራስን መለየት ነው። ፊት ለፊት ሁሉም የሚያየውን ሳይሆን ከመጋረጃው በስተጀርባ የማይታየውን የሚያይ ነው።
- ምሁርነት ከድንቁርና አይጣባም። ጨለማ ከብርሃን ሕብረት እንደሌለው ሁሉ ምሁርነትም ከድንቁርና አይተዋዎቅም።
-ምሁርነት በየ ድግስ ቤቱ እንደ ወደላ ዝንብ ድንኳን ሰባሪነት አይደለም። "...ፋርፋሪ ጣሉልኝና፣ለውሸት ኀሊናዬን ላከራያችሁ"ነትም አይደለም። ቀና የሆነ ኩራት፣ቁጥበነትና እጅግ አርቆ አስተዋይነት እንጂ።
ይህንን መነሻ በማድረግ አሁን ላይ በተለይም በውጭ የሚኖሩ "አማራ ነን" የሚሉ ባለ ማዕረግተኞችን ስንፈትሽ ግን በተቃራኒው ሆነው አግኝተናቸዋል።
በአማራ ፋኖ የሕልውና ትግል ውስጥ መፍትሔ ከመሆን ይልቅ በሽታው ሆነዋል።
የአማራ ፋኖ አንድነት ችግሩን ለይተው መውጫ መንገዱን ከማሳየት ይለቅ ራሳቸው ዋነኛ ችግሮች ሆነዋል።
ሙያዊ ስነምግባራቸውም ሆነ ምሁራዊ ስሪታቸው ባይፈቅደውም መንደራቸው ውስጥ ገብተው ይርመጠመጣሉ። እንደተራው መደዴ ቧልት ሲያመላልሱ፣ ሲሳደቡ፣ትግል ሲከፋፈሉ፣የፋኖ መሪዎችን ሲያብጠለጥሉና በየ ድድ ማስጫው ተሰልፈው ሌላው(ተራው) የሚችለውንና የሚያውቀውን አብረው ሲያቀረሹ ይውላሉ።
ምሁር ሆኖ ቧልት ማመላለስ? ኧረ! እንዴት ይቀፋል። ምሁር ሆኖ ከድንቁርና መጣባት፣ ኧረ! እንዴት ይሆናል? ምሁር ሆኖ የሕልውና ታጋዩን፣ፋኖን፣አርሶ አደሩንና ሌሎችን በተሳሳተ መንገድ በመምራት ማገዳደል፣ተስፋ ማስቆረጥና እንዲበተኑ መስራት ለምን? ምሁር ሆነ ለግል ጥቅምና ዝና በማይሆን መንገድ መራኮት እንጂ በየቀኑ በድሮንና በአገዛዙ ቅጥረኛ ሰራዊት ለሚያልቀው አማራ ኬሬዳሽነት? ለምን? አሁን እናንተን "የአማራ ምሁራን" ወይስ "የአማራ እውራን" እንበላችሁ?
አደብ ግዙ። ከቻላችሁ ስለ እውነት፣ ሙያችሁና ብቃታችሁ የሚፈቅደውን በሕልውና አደጋ ውስጥ ላለው አርሶ አደር አበርክቱ። ካልሆነ ግን እንደ ልማዳችሁ ሕሊናችሁን ለከርሳችሁ ገርዳችሁ ኑሩ።እኛን ተውን።
በነገራችን ላይ "ፋኖ ግቡን እንዲመታ..! የሚለውን ምክረሐሳቤን ለእነዚህ "ምሁር ነን" ባይ እ ውራን አድርሱልኝ እና ከዛ ይማሩ።
እየታበይኩ እንዳለሆነ መቼም የሚያውቅ ያውቀዋል።
የሕልውና ትግሉ ባለቤት የአማራ ሕዝብ ነው!!!
ድል ለሰፊው ሕዝባችን!!
#ትንቅንቁ_አሁንም_እንደቀጠለ ነው!!
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
ከሰዴ ወረዳ በሌሊት በተለያዩ አቅጣጫ በመዉጣት ወደ አንድነት ማሪያም ቀበሌ ወጦ የነበረዉ የጠላት ሀይልን የ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር እንዳ አውሬ አሯሩጦ በመመለስ ተሜ ወንዝ የምትባል ቦታ ላይ ከፍተኛ የሆነ ትንቅንቅ በማድረግ ጠላትን አንገት አስደፍቶ አሳፍሮ መልሶታል።
በተደረገው ልዩ የደፈጣ ጥቃት የጠላት ሀይል የተለመደውን የሀሰት ዶክመንት ለመስራት እና የአርሶ አደሩን ንብረት ለመዝረፍ የዉሸት ፕሮበጋንዳ ለመስተላለፍ ቢሞክርም በጀግኖች ፋኖወች ጠካራ ክንድ ባደረጉት የደፈጣ ዉጊያ መመለስ ተችሏል።
የፋኖ ሀይልን መቋቋም ያቃተዉ የጠላት ሀይል ተመልሶ ወደ ሰዴ ወረዳ ከተማ ጭኖ ይዞት የመጣዉን ድሽቃ ይዞ እየሮጠ ተመልሶገብቷል።
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ
ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በደፈጣ ጥቃት ጥላት ኪሣራ ደረሰበት
በ20/04/18 ከስማዳ ወገዳ ከተማ በመነሳት ወደ ባዝራ ቀበሌው የአርሶ አደር ግብር ለመሠብሰብ የተንቀሳቀሰው ሆድ አደር ሚኒሻ በነበልባሎቹ ስማዳ ሃገረ ቢዘን ከብርጌድ ሻለቃው 3 አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ወደመጣበት ተመልሷል።
የአርሶ አደር ንብረት አልግባብ እየሰበሰበ የጥይትን የድሮን መግዣ የሚያደርገው ሆድ አምላኪው ስርአት የተለመደውን የአርሶ አደሩን ለማዋከብ ቢሞክርም ሳይሳከለት በግብር ፈንታ ሙትና ቁስለኛውን አዝሎ ተመልሷል።
የስርአቱ አገልጋይ የነበሩ ሚኒሻ በየጊዜዉ እየፈረሱ እየወጡ መሆኑ ተላላኪው የኦሮሙማ ፈረስ አመራርን ያስደነገጠ ሲሆን
ሚነሻና ፖሊስን ጨምሮ ባንዳ አመራር በአራዊት ሰራዊቱ ግዞት ሆነው መቀመጣቸውን ፈርሰው የወጡት ሚኒሻዎች አስረድተዋል።
እስካሁን በስህተት ህዝባችን ስንጨፈጭፍ በመቆየታችን ያለአግባብ ስለሆነ አሁን ለተገፋው በየቀኑ የጥይት አሩር ለሚዘንብበት ህዝብ የማይተካ ሂወታችን ልንሰጥ መጥተናል ሲሉ ማህበረሰቡን ይቅርታ ጠይቀዋል!!
ድል ለተገፋው
ስማዳ ሃገረ ቢዘን ሚዲያ ክፍል
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምኒልክ ዕዝ ዋና አዛዥና ሴንትራል ኮማንድ ከፍተኛ አመራር ዋርካው ምሬ ወዳጆ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ትከሻህ ላይ የተሸከምከውን የኮከብ ማዕረግ ነገ ሸምጥጠህ ከኪሥህ ትከተዋለህ!!
ዋርካው ምሬ ወዳጆ በሰል በሰል ያሉ ሀሣቦችን በማንሣት ጠንከር ያሉ አቅጣጫዎችን በሚከተሉት ዙሪያ አስቀምጧል !
-በላሊበላ ክብረ በዓል ስለታሠበዉ ሴራ
-ለሀገር ሽማግሌዎች አቅምና ሀላፊነት
-ወልደያ ዩኒቨርሲቲ ስለተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ
-ለፋኖ አመራርና አባላት
-ለአማራ ብልፅግና አመራሮች
-ለአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ መፍረስን በተመለከተ
-ለአማራ ሚሊሻና ፖሊስ ጠንከር ያሉ ጉዳዮችንና አቅጣጫዎችን በሳል በሆነ ንግግር ዳሶበታል።
ዋርካው እውነተ ዋርካ !✊
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ጎጃም ዞን ዋሸራ አካባቢ ቦይንቁ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የተጣለው ድሮን ተተኳሽ ስብርባሪ!
በተጣለው ድሮን የደረሰው ጉዳት:- ትምህርት ቤቱ ወድሟል።
አንዲት ወጣት ልጅ ሞታለች።
ብዙ ንፁሃንን ቆስለዋል።
+3
#ኦህዴድ የፈለገውን ቢል ከዚህ ሽንፈት ማገገም በፍጹም አይቻልም! አይታሰብምም።
➬ ይህ የማራቶን ሩጫ ኣደለም 😁ምርኮኛው የጁላው ሰራዊት ነው !!😁😁
+2
ከአባት አረበኞች ጋር ውይይቶች ተካሂዳዋል‼️
ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር #74ኛ_ክፍለ_ጦር_አመራሮችና_የጎንቻ_ሲሶእነሴ ወረዳ ግዚያዊ መንግስት አመራር በጌቴሰማኒያ ቀበሌ የሚገኙትን በማወያየት የማደራጀት ሰራ የተሰራ ሲሆን
➦የህልውና ትግል ማለት ምን ማለት ነው
➦የህልውና ትግላችን ተግዳሮቶች ምንድናቸው?
➦የህልውና ትግል ነው ካልን ሁሉም ህዝብ እንዲሳተፍ ያላደረግነው ለምንድነው?
#ለአባት_አረበኞች_ስልጠና_የተሰጠ_ሲሆን በጌቴ ሰማያ ከዚህ በኋላ በቁርጠኝነት ህዝባቸውን እና ራሳቸውን ከጠላት ለመጠበቅ ከቲም ጀምረው እስከ ሻለቃ ድረስ በመደራጀት የጠላት መምጫ በሮችን በመዝጋት እና የሌሊት ደፈጣ በመጣል ከትግሉ ጎን እንደሚሆኑ አሳውቀዋል።
አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ለጀግናው የአማራ ፋኖ ሰራዊትና ለአማራ ህዝብ በሙሉ በድሮን ጥንቃቄ ዙሪያ የምፅፈው የመጨረሻውና የተጠቃለለ መረጃ !
ድሮኖች አሁን ላይ በሌሊት ጭምር ጥቃት ማድረስ በመጀመራቸው እያንዳንዱ ተዋጊ ራሱንና ጓደኛውን ለመጠበቅ እነዚህን ስልቶች በሚገባ ሊያውቃቸውና ሊተገብራቸው ይገባል።
የድሮን ጥቃትን ለመከላከል ትልቁና ቀዳሚው ስልት ተሰባስቦ አለመታየት ነው፤ ምክንያቱም ድሮን ካላየች አትመታም።
ሌላው ድሮኖች በምሽት፣ በጭጋግ ወይም በደመና ውስጥ ሆነው ሰዎችንና መኪኖችን የሚለዩት በብርሃን ሳይሆን ዕቃዎቹ በሚረጩት የሙቀት መጠን (thermal energy) መሆኑን ጠይቄ መረዳት ችያለሁ። ማንኛውም ሞቅ ያለ ነገር ማለትም የሰው አካል፣ የሞተር፣ መኪና ወይም በቅርቡ የተተኮሰ የጦር መሣሪያ ኢንፍራሬድ የተባለ ጨረር ይረጫል፤ የድሮን ካሜራ ደግሞ ይህንን ጨረር ወደ ምስል በመቀየር ኢላማውን ይለያል።
ይህንን የሙቀት ጨረር ለመሸፈን ሙቀትን ወደ ውጭ እንዳይወጣ የሚከላከሉ ልዩ የሙቀት መከላከያ ሸራዎችን (Thermal Blankets) መጠቀም ወሳኝ ሲሆን እነዚህ ሸራዎች በሌሉበት ደግሞ ተራ ወፍራም ብርድ ልብሶችን በመጠቀም የሰውነትን ወይም የሞተርን ሙቀት ለተወሰነ ጊዜ መደበቅ ይቻላል።
የተሻለው አማራጭ ደግሞ ከተፈጥሮ መከለያዎች አንዱ የሆነውን ጥቅጥቅ ያሉ ዛፎች ስር መሆን፣ ዋሻዎችን መጠቀም እና በጭጋጋማ ወይም ዝናባማ የአየር ሁኔታ መንቀሳቀስ የድሮን እይታን በእጅጉ ይጋርዳል። የዛፍ ቅጠሎች የሙቀት ጨረርን የመበተን ባህሪ ስላላቸው የድሮኑ ካሜራ ግልፅ ምስል እንዳያገኝ ያደርጉታል ይላሉ ባለሙያዎች።
ሌላው እጅግ ወሳኝ ነጥብ ድሮኗ ቅኝት ላይ ባለችበት ጊዜ በቡድን ሆኖ ፍፁም አለመንቀሳቀስ ነው። ድሮን በአየር ላይ ባለችበት ሰዓት ፍፁም ተገትሮ መቆም ወይም መተኛት ይገባል ምክንያቱም አብዛኞቹ የድሮን ሶፍትዌሮች የሚለዩትና ትኩረት የሚያደርጉት በሚንቀሳቀስ ነገር ላይ ነው።
በተጨማሪም በቡድን ተሰባስቦ ከመጓዝ ይልቅ ርቀትን ጠብቆ ተራርቆ መንቀሳቀስ የጥቃቱ ሰለባ የመሆን እድልንና የጉዳቱን መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።
ከዚህም ባለፈ ድሮኑን የማታለያ ዘዴዎችን መጠቀም ውጤታማ ነው። ለምሳሌ ልክ እንደ እውነተኛ መኪና ወይም የሰው ስብስብ የሚመስሉ የውሸት ምስሎችን መሬት ላይ በማስቀመጥ ድሮኑ ጥይቱን በከንቱ እንዲያባክን ማድረግ ይቻላል።
ድሮኑን ለማደናገር በተለያዩ ሰው በሌለባቸው ቦታዎች ትናንሽ እሳቶችን በማንደድ ወይም ሞቅ ያሉ ቁሶችን በማስቀመጥ የድሮኑ ካሜራ ትክክለኛውን የሰው ኃይል እንዳይለይ ማድረግ ይገባል። በዚህም ቦንብ አባክኖ እንዲሄድ ያደርገዋል።
የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተመለከተ የሞባይል ስልኮችንና የሬዲዮ ግንኙነቶችን መቀነስ ወይም ፍፁም ማቆም የህልውና ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ድሮኖች የሞባይል ሲግናልን (RF signal) ተከትለው ኢላማን በትክክል ሊመቱ ይችላሉ።
ሌላው ባህላዊ ዘዴ ደግሞ ድሮን ሲመጣ የሚፈጥረውን ድምፅ በንቃት የሚከታተሉ ፋኖዎችን ወይም ቀኘዎችን በተራራ ጫፎች ላይ በመመደብና መረጃን በፍጥነት ለተዋጊው ማድረስና አስቀድሞ በመሸሸግ ከአድጋ መከላከል ይቻላል።
ድል ለአማራ ፋኖ !
ይህ መረጃ ለሁሉም የሰራዊቱ አባላት እንዲደርስ ሼር በማድረግ የድርሻችንን እንወጣ።
