ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
رفتن به کانال در Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
نمایش بیشتر4 136
مشترکین
+724 ساعت
+2087 روز
+1 20130 روز
آرشیو پست ها
ስለሌሎች መኖርን የተማርንባቸዉ አማራዎች!!!
" ለራስ ቅድሚያ የመሰጠት አስገዳጅ ተፈጥሯዊ ባህሪን አሸንፈው ለአማራ ህልውና ትግል ራሳቸውን አሳልፈው ከሰጡ ጀግኑች መካከል ፦
1 አስር አለቃ ኤፍሪም አጥናፉ እና
2 ፋኖ አዲሱ ቢተውን የመጀመሪያዎች ናቸው።
እኔ በብዙ መንገድ ሳስበው የእውነተኛ የዓላማና የትግል ሰው መሆናቸው የተገነዘብሁት በተወለዱበት ቀጠና ጎጃም አገው ምድር አከባቢ ስስ የፓለቲካ እሳቤ ያለበት እንደመሆኑ መጠን ማንም እኔነኝ ያለ ፓለቲከኛ የማይረዳውን የፓለቲካ እሳቤ ተረድተው ቀድመው ነቅተው አከባቢው ለማንቃት የሄዱበት ርቀት በጣም የሚገርም የሚደንቅ ነበር።እኔና ኤፍሬም አጥናፋ በሰኔ15ቱ አብረን ታስረን በነበርን ጊዜ ስለአከባቢው የትግል ሁኔታ መክረን ነበር ከዚያም አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፋ ፍ/ቤቱ ነፃ ተብሎ ከስር ቤት ከወጣ በኃላም ከአማራ ህዝባዊ ሀይል አመራሮች መካከል አርበኛ ጥላሁን አበጀን እንዲያገኛው በማድረግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሬለት ነበር። እሱም ለትግል ካለው ፍላጎት እና ተነሳሽነት አንፃር በአማራ ህዝባዊ ሀይል ስም በተለያዩ ከተሞች ወጣቶችን ወታደራዊ ስልጠና እንዲያሰለጥን በአርበኛ ዘመነ ካሴ እውቅና ተሰጦት ወጣቶችን በማሰልጠን ትግሉን እንዲቀላቀሉ ያደረገ ጀግና ነው ።በዚህ የስልጠና ወቅትም ወደ ጎጃም አገው ምድር ዳንግላ አከባቢም ስልጠና ማስጀመር እንዳለበት እኔንና ጓዶቹን እሰር ቤት ከተፈታ በኃላ ለመጠየቅ በመጣበት ወቅት ደግመን ተነጋግረን በተነጋገርነው መሰረት ወደ ዳንግላ አከባቢው አቅንቶም ከአገኛቸው የትግል አጋሮች መካከል አንዱ ፋኖ አዲሱ ቢተው ነው።
እነዚህ ሁለት ወንድሞቼም በአከባቢው ለወጣቶች ወታደራዊ ስልጠና መሰጠት ጀመሩ።አሰር አለቃ ኤፍሪም አጥናፉና ፋኖ አዲሱ ቢትዉ ሁለቱን ለየት የሚያደርጋቸው ተፈጥርሯዊ የሆነው የሰው ልጅ ለራሱ ቅድሚያ የመስጠት አስገዳጅ ተፈጥሯዊ ባህሪን አሸንፈው፤ ይብዛም ይነስም ለመርህ ተገዝተው ፤ዝቅ ብለው ወጣቱን ለማሰልጠን በመወሰን ያነቁትን ወጣት ፤የወጡትን የወረዱት መከራና ስቃይ ሳስብ ለእኔ ልዩ የትግል አርማ ናቸው።!
ለከፈላችሁት መሰዋትነት ሁሌም በአማራ የህልውና ተጋድሎ ስም ሲንዘክራቸሁ እኖራሉን። ለወደቃችሁለት የተቀደስው ዓላማችሁ ዳር ለማድረስ የድርሻችን ለመወጣት ቃላችን አክብረን በቃላችን ተገኝተን እየታገልን እያታገልን እንገኛለን። ትግላችን ቀራኒዎ ድረስ ነው።
ዝክረ ሰማዕታት ለጀግኖቻችን።
@highlight
አርበኛ ስለሺ ከበደ
ዲሽቃ ጠምዶ ሲሮጥ የነበረው መኪና ከነ ወታደሩ ተዘይሯል::ኮሌኔሉም ተከርብቷል።
መገን ሸዋ መርሓቤቴ አውራጃ ደራ‼️
ሽመልስ ንጉሴ
23/ዐ4/2018 ዓ.ም
የአማራን ህዝብ ጥቃት ለመከላከል የወሰንነው ከዛሬ 15 አመት በፊት ጀምረን ነው ።
ወደ ተግባር የገባነው 🔥
አርበኛ ዘመነ ካሴ 💪
አድነታችን ኋይላችን ነው
አንድነት የሰው ልጅ ለተመሳሳይ አላማ እና እቅዶችን ይዞ ከተነሳ አሸናፊነትን የበለይነትን ለመውሰድ አንድ መሆን መብት ሳይሆን ግዴታ ነው ። የአማራ ፍኖ ሁሉም ሰው ከሞቀ ቤቱ የወጠነው ለነፃነት እና ለፍትህ ነው ።
ስለዚህ በአንድ ተሰባስቦ ድርጅት መስርቶ በመርህ እና በአሰራር ተደራጅቶ በአንድ የእዝ ሰንሰለት መጓዝ ግዴታ ነው ። አንድ ስንሆን ሀይልም ብርታትም ይኖረናል አሸናፊም እንሆናለን ይሄም በመረዳት ሰፊ ሀሳብን ይዘን እየተጓዝን አንድ ሆነን ሀሳባችንን ማሳካት ግድ ይለናል።
አማራ ያልታገለበት ትግል የለም ስለሆነም አንድነት ላይ መስራት ይጠበቅብናል ። እስከ አሁን አማራ የራሱ ድሮጅት ባለመኖሩ በጀምላ ተረሽኗል ፣ተፈናቅሏል ፣ ንብረቱን ተዘርፋል እዲሁም በጀምላ ተደፍሯል ይህ ሁሉ በደል ሲደርስበት ቅሬተውን ሊቀርብበት የሚችል ድርጅት አለመኖሩ ነው ። ስለሆነም መደራጀት ማሸነፍ ግዴታ ነው ።
አማራው የራሱ ህልውና አደጋ ሲጋጥመው ሊቆረቆሮ የሚችል ድርጆት ያስፈልገዋል ። ይሄን በመረዳት የአማራ ፋኖ ተሰባስቦ ድርጅት መስርቶ ብልፅግናን ብናሸንፍም የተመሠረተው ድርጅት የአማራ ህልውና ጠባቂ ሆኖ መቀጠል አለበት አንድ መሆን ግዴታ ነው ያልኩት ከዚህ በመነሳት ነው።
የአማራ ፋኖ ብሶት የወለደው የጀግና ስብስብ እደሆነ ይታወቃል እናም አፋብኋ እና አፋህድ ሁለቱ ድርጅቶች ቤታቸውን ዘግተው ወደ አንድ መተው ወጥ ድርጅት ከተመሰረተ የአማራን ትግል የሚደግፍ ሁሉ አድነቱን ሲሰማ ሁሉም ሰው ሻማ ያበራል ።
በዚህም ትግል መሰዋትነት እየከፈሉ ያሉ ታጋዎች የውስጥ ደስታቸው ፈቅሎ በመውጣት በአለም አደባባይ ደስታቸውን እደሚገልፁ ሙሉ እምነት አለኝ ።
በዙዚህ ትግል የተሰው የጀግኖች ቤተሰቦችም አንድነቱን ሲሰሙ የለበሱትን የሀዘን ልብስ እደኩራት ያውታል ምክንያቱም ቤተሰቦቻችን የተሰውለት ትግል ዳር ይደርሳል ብለው ተስፋ ይኖራቸዋል ትግሉም ሲጠናቀቅ ጀግንነት እና አሸናፊነት ይሰማቸዋል ስለዚህ የአንድነት ጠቀሜተውን ዘርዝሮ መግለፅ ይከብዳል።
የቆሰሉት ወድሞቻችን አንድነቱ ሲመጣ በተሰውት አጥንት እና ደም መሰዋትነት በኛ መቁሰል ነው አንድነቱ የመጠው በማለት ይደሰታሉ ። እየታገልንም ያለነው ለመሞት እና ለመቁሰል እራሳችንን አዘጋጅተን እጠብቃለን ስለሆነም ይሄን በመረዳት አንድ መሆን አስፈላጊ ነው።
ሁሌም አማራነት አርበኛ ኤፍሬም ባዩ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ለክፍለ ጦር አመራሮችና ለሰራዊት አባሎች ፖለቲካዊ ስልጠናዎችን ሰጠ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ለተከታታይ ሶስት ቀናት አጠቃላይ ለክፍለጦር፣ለሻለሻለቃ አመራሮችና አጠቃላይ ለሰራዊቱ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። እንደሚታወቀው የአብይ አህመድ አገዛዝ ወሮበላው የኦሮምማው ስብስብ አማራን ለማጥፋት በተለያዩ የአማራ ግዛቶችና ከአማራ ግዛቶች ውጭ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ፍጅት እያደርገ መሆኑን አለም የሚያቀው ሀቅ ነው።
ሆኖም ይህን የብልፅግና ፋሽስታዊ ስርዐት የአማራ ልጆች በነበልባል ክንዳቸው እየተፋለሙትና እየመከቱ የበላይነታቸው እየወሰዱ ይገኛል። ስለሆነም የአሳምነው አናብስቶች ከትግሉ ጎን ለጎን በተለያዩ ለሰራዊት ፖለቲካዊ ስልጠና ማለትም፦
*የሰራዊት ስነምግባር እና ስነስረዓት መወሰኛ ደንብ
*ጓዳዊ ዝምደና
*ባህል እና ጨዋነት
*ድርጅትና የድርጅት ምንነት
*የአማራ ህዝብ ምንነት እና *የገጠሙት ፈተናወች እና ያደረጋቸው ተጋድሎወች
*ፋኖነት እና መገለጫ ባህሪያት በሚሉ
አርዕስቶች ላይ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአሳምነው ዕዝ ምክትል ድርጅት ጉዳይ አርበኛ ኢያሱ ሙሉጌታ ፣የአሳምነው ዕዝ ህግ ክፍል ሀላፊ አርበኛ ተስፋዬ ገስጥ እና የአሳምነው ዕዝ ሎጀስቲክ ኃላፊ ሻለቃ ሞገስ ለማ በመሆን ከትምህርት እና ስልጠና መምሪያ በተሰጠው ዕቅድ መሰረት የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ክር አፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር የሻለቃ አመራሮች እና ለሰራዊት አባላት በበቂ ሁኔታ ስልጠና በመስጠት አመርቂ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
በስልጠናውም የተገኙት የዓፄ ዘርዓያዕቆብ ፩ ኮር ዓፄ ይኩኖአምላክ ክፍለ ጦር አመራሮችና የሻለቃ አመራር አባላት በስልጠናው የአማራን የሞኖር ነፃነት በቅርቡ እንዲሚያበስሩ እርግጠኛ እየሆኑ ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የሚሰጣቸውን ማነኛውምንም ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!
መረጃውን ያደረሰነ አርበኛ አማረ ታዘዘ የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነው
ታህሳስ 23/04/2018 ዓ.ም
ልደት 🎂🍰🧁
ክሪስ
* ዛሬ በብዙ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ያለው
* በአሁን ስአት በህመም ለሚሰቃየው
* እንዲሁም ያለ ፍርድ በእስር ቤት የሚማቅቀው
* ለያዘለት ዓላም እና ላመነበት ነገር የሚታገለው
የታላቁ የክርስቲያን ታደለ (ክሪስ) ልደት ነው::
እንኳን ተወለድክ.....ገብርዬ ...
መልካም ልደት
ይህ ምስል ሺህ ቃላት የሚተካ መራራ እውነትን ይናገራል። በአስከሬን ላይ መፎከር ጀግንነት ሳይሆን፣ የሥነ-ልቦና ስብራት እና የታሪክ ውርደት መሆኑን የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው
በዚህ ዘግናኝ ምስል ላይ የምናየው ትዕይንት የብልጽግና ሰራዊት፣ የሞራል ዝቅጠትና የአውሬነት ማረጋገጫ ነው። ነፍስ በሌለው እና ደሙ በፈሰሰ ንጹሕ ሰው አስከሬን ላይ ጠመንጃ ደቅኖ ለፎቶግራፍ መመቻቸት፣ ከጦርነት ሕግም ሆነ ከሰውነት ተራ መውጣትን ያበስራል።
በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እውነተኛ ጀግና ጠላቱን በክብር ያሸንፋል፤ የሞተን ሰው ደግሞ በክብር ይሸኛል። በአስከሬን ላይ መሳለቅ ግን በውጊያ ሜዳ ድል ለራቀው፣ በውስጡ ፍርሃት ላነገሰ እና ሰብዓዊነቱን ላራገፈ ኃይል የሚሰጥ የሽንፈት ማስታገሻ ነው። ጀግና ፊት ለፊት ካለው ኃይል ጋር ይገጥማል እንጂ፣ መሬት ላይ በወደቀ አስከሬን ላይ የጥይት አፈሙዝ አያሳይም። ይህ ጀግንነት ሳይሆን "የሞራል ኪሳራ" ነው።
ዛሬ እነዚህ የአገዛዙ ወንበር ጠባቂብም ወታደሮች በአስከሬን ላይ ቆመው የሚነሱት ፎቶ ለፕሮፓጋንዳና ለጊዜያዊ መዝናኛ ሊሆናቸው ይችላል። ነገር ግን ታሪክ አይረሳም፤ ቴክኖሎጂም አይደመስሰውም። እያንዳንዱ እንዲህ ያለ ምስል ነገ በፍትሕ አደባባይ የገዛ ወንጀላቸውን የሚያረጋግጥባቸው ዋነኛ የክስ ሰነድ ይሆናል።
ፋሽስት ጣሊያንና የናዚ ኃይሎች እንዲህ ያሉ የጭካኔ ድርጊቶችን በመፈጸም ሕዝብን ለማንበርከክ ሞክረው ነበር። ውጤቱ ግን ተገላቢጦሽ ሆነ፤ ጭካኔው የሕዝብን የነፃነት ወኔ አቀጣጠለው። ዛሬም በዚህ ምስል ላይ የሚታየው ግፍ የሕዝብን እንባ ወደ ቁጣ፣ ቁጣውንም ወደ ነፃነት ትግል ይለውጠዋል እንጂ አያሸንፈውም።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ሆይ፤ ይህ ምስል ብቻውን የጦር ወንጀል (War Crime) መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ህያው ማስረጃ ነው። ዝምታ ለገዳዮች እውቅና መስጠት ነው። በአስከሬን ላይ የሚሳለቅ፣ ንብረት የሚያቃጥልና ንጹሐንን የሚያድን ሰራዊት የሀገር መከታ ሊባል አይችልም። ዓለም ይህንን ግልጽ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊያወግዘውና ገዳዮችን ለፍርድ ሊያቀርብ ይገባል።
ንጹሐን ይሞታሉ፣ ቤቶች ይቃጠላሉ፣ አስከሬኖች ይረገጣሉ፤ ነገር ግን የእውነት ብርሃንና የነፃነት መንፈስ ፈጽሞ አይሞቱም። በአስከሬን ላይ ቆሞ የሚፎክር ሥርዓት የውድቀቱ ዋዜማ ላይ መሆኑን ይህ ምስል ምስክር ነው።
ፍትሕ ለተገደሉ ንጹሐን!
ውርደት በአስከሬን ላይ ለሚፎክሩ ጨካኞች!
ከኤልያስ በላቸው ገፅ የተወሰደ
@highlight:-👉 Estibel Alemu Zerihun
ደራሲ፣ አርበኛ እና ታዋቂው የፋኖ መሪ የነበሩት ኮማንደር አሰግድ መኮነን በአገዛዙ ተሰውረው እስከ-አሁን ድረስ የት እንዳሉ እንደ-ማይታወቅ እና ፍርድ/ቤት እንዳልቀረቡ ምዕራባውያን ሚዲያዎች ጭምር የአገዛዙን ወንጃል እያጋለጡ ይገኛሉ።
###
ሁላችንም ያለማቋረጥ እንጠይቅ.. ጋሽ አሰግድ የት ናቸው? ብለን ልንጠይቅ ይገባል። ጀግናውን የረሳ ማንነቱን እና ታሪኩን እንደረሳ ይቆጠራል!
ጀግናውን የረሳ ብቻውን ቢሮጥ እንኳ አያሸንፍም!
አሁንም እጠይቃለን where is he?
የቴሌግራም ገፃችን👉https://t.me/MerebMedia24
🔜ሰበር መረጃ ከግንባር:-👉👉👉
ፋኖ ወደ ጠላት ምሽግ ተስቦ በመግባት በፈፀመው የቦምብ ጥቃት በምሽጉ ውስጥ የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮችን ሙሉ በሙሉ መደ-ም-ሰ-ሱን አስታወቀ!
ፍጥነትን፣ ጀግንነትና ኃያልነት እንዲሁም ጥልቅ የሽምቅ ሳይንስ እውቀትን ያጣመረ ነው በተባለው በዚህ ኦፕሬሽን፡ ምሽጉ በቦ-ም-ብ ብትንትኑ የወጣበትና በምሽጉ ውስጥ የነበሩ የጠ-ላ-ት ወታደሮችም የእ-ሳ-ት እራት ሆነው የቀሩበት ድል መመዝገቡ ታውቋል::
በዝርዝር እንመለስበታለን።
ሠሞኑን በመላው አማራ ክልል -ህዝቡን እየሰበሰቡ '' ደውሉላቸው ፣ መቶ ሺ ብር እንሰጣችኋለን በሏቸው ፣ በሬ እንገዛላችኃለን ኑ ግቡ በሏቸው ፣ መንግስት መሬት ይሰጣችኃል በሏቸው ፣ ...'' እያሉ ማስገደድ ተጀምሯል!
በጣም ያሳፍራል! ይህ ትውልድ የሚታገልለትና የሚሞትለት ኮዝ እንዳለው እንኳ እስካሁን አልተረዱም። ወይ ደግሞ ለመረዳት አይፈልጉም። ዛሬም ይሄን ትንታግ ትውልድ ለገንዘብና ለጥቅም ጫካ እንደገባ አድርገው ነው የሚያስቡት!
ታዲያ በዚህ እሳቤ ላይ ካለ ሀይል ጋር በምንስ አይነት መልኩ በጥቂቱ እንኳ ልትግባባ ይቻልሃል?
ትናንት በአምባሰል ውጫሌ ከተማ በነበረው ስብሰባ ለህዝቡ ተመሳሳይ ሀሳብ አቅርቀው ሲነተርኩት '' አልናገርም '' በማለቱ በነዋሪዎች ላይ የጅምላ አፈሳው ተጠናክሮ መቀጠሉን ለማረጋገጥ ችያለሁ!
ስህተትን በስህተት ለማረም የሚደክሙ ከንቱ ፍጡራን!😥
በ54ኛ ክ/ጦር ባሉ ሻለቃዎች በወትሮ ዝግጁነትና በወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ምክክር ተደርጓል ።
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም
የሻለቃዎችን ወትሮ ዝግጁነት በመፈተሽ የ54ኛ ክ/ጦር የሻለቆችን የአደረጃጀት ስራዎች በመዋቅሩ ለአባሉ በዓላማቸው ላይ በስርፅት በመንገር ህዝባችን እና ድርጅታችን የመጠበቅ እና የማዳን ተግባር በመተባበር በአንድነት መስራት የጋራ ሀላፊነታችን መወጣት እንዳለብን አስተውሎት እንዲኖራቸው ተደርጓል።
ከአባሉ ጋር በጥልቀት በመወያየት ችግሮችን በጥልቀት በመለየት በመፍታት መግባባትና የትግሉን ዕድገት በተሻለ ግለት ማስቀጠል እንዲሁም በቀጠናው የተሻለ ከወትሮው በበለጠ በስነምግባር በማነፅ የወጣንለትን አላማ በማስገንዘብ በጥምረት ኦፕሬሽን መደረግ እንዳለበት የመግባባት ስራ ተስርቷል።
ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ
የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
"ወ/ሮ አየሁ አበባየሁ እና ወ/ሮ አታላይ አንቴ በጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን ትዕዛዝ ተገደሉ"
206ኛ ኮር ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም
ወ/ሮ አየሁ አበባየሁ እና ወ/ሮ አታላይ አንቴ የ57 እና የ55 ዕድሜ ላይ ያሉ እናቶች ሲሆኑ ትዳር ቀልሰው ልጆችን ወልደው ባሳደጉበት ቂየ ጥቅጥቅ ባለው ጨለማ በ6ኛ ዕዝ አዛዥ ጀነራል ብርሀኑ ጥላሁን ትዕዛዝ በአረመኔው ሰራዊት ተገድለዋል።
ወ/ሮ አየሁ አበባየሁ በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ በነብር ገደል ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ የአረመኔው ሰራዊት ከሌሊቱ 5:00 ሰዓት ቤታቸውን በኃይል ገንጥሎ በልጆቻቸው እና በባለቤታቸው በአቶ ግዛቸው ወንዴ ፊት በጭካኔ ተረሽነዋል።
የአማራን ህዝብ ስነልቦና ለማድቀቅ በጭካኔ እናቶችን እየገደለ የሚገኘው የአረመኔው ሰራዊት የ6ኛ ዕዝ ዋና አዛዥ ብርሀኑ ጥላሁን ባስተላለፈው ትዕዛዝ እናቶችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈፀመ ነው።
ይህ የጭካኔ ተግባር በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋባል ወረዳ የረብረብ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩት የ55 ዓመቷ ወ/ሮ አታላይ አንቴ በአረመኔው ሰራዊት ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት በቤታቸው ሳሎን ከልጇቸው ፊት ለፊት ተንበርክከው ልጅችን አጥብጠው ባሰደጉባቸው ጡቶች የጥይት በረዶ ዘንቦባቸዋል።
አስገድዶ መድፈር እና ንፁሀንን በጭካኔ መግደል እንደ ትልቅ የጦርነት ስልት በመጠቀም የአማራን ህዝብ ለማንበርከክ ግልፅ ትዕዛዝ ያስተላለፉት ጀነራሎች በጭካኔ በሚገድሉት ህዝብ መሀል የሰላም አምባሳደር ሁነው መቅረባቸው በህዝቡ ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል።
ማይክ ጨብጠው ከሰንበቴ አፍሰው አዳራሽ ባስገቡት ህዝብ ፊት የሰላም መናንያን ሁነው የተገኙት እነ ብርሀኑ ጥላሁን ሰራዊታቸውን ልከው እናቶችን መጨፍጨፋቸውን ሊያቆሙት ግን አልቻሉም።
የአማራ ህዝብ ይህን ትግል እንደ አራስ ልጁ አቅፎ ይዞታል የሚታለል የሚሸወድ ለአረመኔዎች የሚገዛ የድሮው ህዝብ ዛሬ የለም አዲሱ ትውልድ በአዲስ የትግል ስልት ስርዓቱን ነቅሎ ነፃነቱን ይተክል ዘንድ አምርሮ መታገሉን አጠናክሮ ይቀጥላል።
አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አዲስ ተስፋ
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
+1
በምዕራባዊ ቤተ ዐማራ ቀጠና የሚንቀሳቀሰው ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር እንደ ንስር ታድሶ እየመጣ ነው።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ከደሴ ከተማ በስተምዕራብ በሚገኙ 11 ወረዳዎች የሚያካልል ሰፊ ቀጠና የሚሸፍን ነው።
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ የንስሮች ስብስብ ነው ስንል ያለ ምክንያት አይደለም!!
ዓላማችን ተባብረን መዳን ነው!!
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
