Don Bosco School G9 (2016)
Открыть в Telegram
Больше
Страна не указанаКатегория не указана
351
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
-130 день
Архив постов
☝ ት/ቤታችን ከዚህ በኋላ ለወላጆች መረጃዎችን የሚያደርሰው በዚህ ሊንክ በሚገኘው የቴሌግራም ቻናል ነው ስለሆነም join በማለት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ።
ውድ ተማሪዎቻችን እና የተከበራችሁ ወላጆች
ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በተላለፈ መመሪያ መሰረት ነገ ዓርብ መስከረም 25 /2016 ዓ.ም በኢሬቻ በዓል ምክንያት ትምህርት ቤት ዝግ ሆኖ የሚውል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም መደበኛ ትምህርት የሚቀጥል ስለሆነ ተማሪዎች በሰዓቱ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
ት/ቤቱ
ለዶን ቦስኮ ካቶሊክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና ወላጆች በሙሉ
እንኳን ለ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!!
ውድ ተማሪዎች እና የተከበራችሁ ወላጆች ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በወረደው መመሪያ መሰረት ትምህርት ሰኞ መስከረም 7 /2016ዓ.ም እንደሚጀመር የተገለጸ ቢሆንም በት/ቤታችን እየተደረገ ባለው የመማሪያ ክፍሎች እድሳት ምክንያት በዕለቱ ትምህርት የማይጀመር መሆኑን እያሳወቅን ከ11ኛ ክፍል በሰተቀር ማክሰኞ መስከረም 8/2016ዓ.ም ትምህርት የሚጀመር እና በዕለቱ የግማሽ ቀን ት/ት(2 :00 _ 6 :10) የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ፡
1. ውድ ተማሪዎች በዕለቱ የመማሪያ ቁሳቁስ በሟሟላት እና የት/ቤቱ ስርዓት በሚፈቅደው መሰረት የደንብ ልብስ(uniform)በሟሟላት በሰዓቱ ት/ቤት እንድትገኙ እናሳስባለን።
2. የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የመማሪያ ክፍሎች ዕድሳት ያልተጠናቀቀ ስለሆነ የ11ኛ ክፍል ትምህርት የሚጀምረው ረቡዕ መስከረም 9/2016ዓ. ም መሆኑን እንገልፃለን።
ት/ቤቱ
🌻ውድ ተማሪዎቻችን እና ወላጆች🌻
እንኳን ለ2016ዓ.ም አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!! በዓሉ የሰላም፣የደስታ የስኬት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን።
ት/ቤቱ
