FutureX
📈 Аналитический обзор Telegram-канала FutureX
Канал FutureX (@futurexapp) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 26 514 подписчиков, занимая 7 320 место в категории Образование и 1 306 место в регионе Эфиопия.
📊 Показатели аудитории и динамика
С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 26 514 подписчиков.
Согласно последним данным от 11 сентября, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 905, а за последние 24 часа — 8, при этом общий охват остаётся высоким.
- Статус верификации: Не верифицирован
- Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 32.52%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 15.95% реакций от общего числа подписчиков.
- Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 8 617 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 4 226 просмотров.
- Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 109.
📝 Описание и контентная политика
Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
“The future starts here!”
Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 12 сентября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Образование.
Загрузка данных...
| Дата | Привлечение подписчиков | Упоминания | Каналы | |
| 12 сентября | +20 | |||
| 11 сентября | +8 | |||
| 10 сентября | +33 | |||
| 09 сентября | +124 | |||
| 08 сентября | +14 | |||
| 07 сентября | +9 | |||
| 06 сентября | +18 | |||
| 05 сентября | +17 | |||
| 04 сентября | +60 | |||
| 03 сентября | +18 | |||
| 02 сентября | +58 | |||
| 01 сентября | +19 |
| 2 | 🛑 ቅዳሜ በውጤት አንዱን ከፍ ሌላኛውን ዝቅ ያደሮጋል‼️
የ 2019 ኢንትራንስ ፈተና ውጤት ነሀሴ ላይ ሲመጣ መደሰት ነው ወይስ መቆጨት የምትፈልገው? ያ ውጤት ያ ደስታ በዛሬው ጥረትህ ይወሰናል። ሌሎች ቅዳሜና እሁድን ሲዝናኑ፣ ፈታ ሲሉበት አንተ ደግሞ ጥግ ድረስ ትጠቀምበታለህ። ከዛ ማለፍህ ይረጋገጣል።
ዛሬ ሁላችሁም G-10 Math's Unit 7 (የመጨረሻው እና ቀላሉ ቻፕተር) እናጠናለን። እሱን አጥንተን እንደጨረስን ትላንት ያጠናነው ላይ ፈተና እንፈተናለን። አደራ ቅዳሜህ እንዳይባክን፤ ቀኑን ሙሉ በሙሉ ተጠቀምበት።
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 3 646 |
| 3 | 🛑 ለ 2019 ተፈታኞች የተዘጋጀ ቪዲዮ!
በዓሉን አስመልክቶ ከስነወርቅ ታዬ ጋርና ከFutureX አንዳንድ መምህራን ጋር ልዩ ቆይታ አርገናል። ስለ ትምህርት፣ ስለ ህይወት፣ ስለብዙ ነገር አውርተናል።
በተለይ ለ 2019 ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በዚህ አመት እንዴት እንደምትዘጋጁ የሚያሳይ ቪዲዮ ነው ከታች ያለውን ሊንክ ተጭናችሁ ተመልከቱት። መልካም ቆይታ! 🙏
https://youtu.be/u4PoDtwb21M?si=rhhtjDToAqR2zKk6 | 4 150 |
| 4 | 🛑 የዲስፕሊን አመት ይሁንልን🙌
ዲስፕሊን ካለህ የማታሳካው ነገር የለም፤ በትምህርት ብቻ አይደለም ነገ በስራና በቢዝነስ ስኬታማ ትሆናለህ። ዲስፕሊን ማለት ደበረህ ደስ አለህ ደበረህ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ ማድረግ ነው።
በዓል ነው፤ ልደት ነው፤ ወይ ሌላ ምክንያት ወይ ሰበብ አርገህ ሳታጠና አትዋል፤ ቀን ካላጠናህ ማታ አጥና፤ የዕለቱን ዕቅድ ሳይጨርሱ መዋል አይቻልም። በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፤ በዚህ አመት ያሰባችሁት ሁሉ (ከክፋት በስተቀር) እንዲሳካ ምኞታችን ነው! ፈጣሪ ረድቶን ህልማችሁን ለማሳካት የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 4 354 |
| 5 | 🌻🌻🌻️ በአዲሱ አመት አዲስ ታሪክ እንሰራለን‼️ ይሄ አመት የኛ ነው! 🔥🔥🔥
እንኳን አደረሳችሁ🙌 አዲሱ አመት ህልማችሁ የሚሳካበት፣ ቤተሰብ በእናንተ ውጤትና ስኬት በደስታ የሚፈነጥዝበት ይሁንላችሁ! የዛሬ የጥናት ፕሮግራም ሁላችንም English Unit 8 ከዛ ሶሻሎች Eco — Unit 7 ነው። የትላንቱ ጥናት ላይ ፈተና ስሩ።
ይሄ አመት ታሪክ የምትሰሩበት ነው! ከዚህ በፊት በትምህርት ደከም ያለ ተማሪ ብትሆን ወይ መካከለኛ ተማሪ ብትሆን እሱ ያለፈ ታሪክ ነው፤ ታሪክህን መቀየር ትችላለህ፤የሚያኮራህን ውጤት ማምጣት ትችላለህ!
ያ እንዲሆን ከፈለክ ዛሬ ወስን! "ከዚህ በኋላ በሙሉ አቅሜ ከኔ የሚጠበቀውን ሁሉ አደርጋለሁ ፈጣሪም ያግዘኛል!!" በል። አንተ ከቆረጥክና የዲስፕሊን ሰው ከሆንክ እኛም እናግዝሀለን፤ ከዛ የምትፈልገው ሁሉ ይሳካል!
🙌 የFutureX ቤተሰቦች (እህት ወንድሞች) ለእናንተ እና እናንተን እዚህ ለማድረስ ብዙ ዋጋ ለከፈሉ ለውድ ወላጆቻችሁ መልካም አዲስ አመት እንዲሆን ተመኘን!
መልዕክቱ: ከFutureX መምህራን እና ሰራተኞች ነው፤ እንወዳችኋለን!❤️
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 5 296 |
| 6 | 🛑 በፕሮግራም ስታጠና ጊዜህ አይባክንም! ጥሩ እየሄድን ነው በርቱ‼️
ቆራጥ የሆነ ተማሪ በፕሮግራም ያጠናል፣ ዲስፕሊን እና ትከረት አለው!! ስልካችንን ከትምህርት ውጪ ለምንም ነገር አንጠቀምም! ⭐️ "ይሄ አመት ለህይወታችን በጣም ወሳኝ ነው!" ይሄንን መቼም እንዳትረሱ።
የዛሬን ጥናት እና የትላንቱን ፈተና ጨረስክ? ጊዜያዊ ስሜትህን ተቆጣጥረህ ለኢንትራንስ ዋጋ ከከፈልክ ዕድሜ ልክህን በራስህ ትኮራለህ! አይቆጭህም! ሁላችሁም የሚገርም ጥረት እያረጋችሁ ነው፤ ጀግኖች በርቱ!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 5 147 |
| 7 | 🛑 ብታጠናም ባታጠናም ክረምቱ አልቋል‼️ ለመስከረም ምን አሰብክ❓
ክረምቱ ሮጦ ዛሬ የአመቱ የመጨረሻ ቀን ነው፤ ክረምቱን በፕሮግራም ሲያጠና የነበረ አይጨነቅም! ምንም ያልጀመረው ደግሞ አሁንም ከዜሮ ለመጀመር እስከ ሰኔ ድረስ ሙሉ 10 ወር አለው፤ ከመስከረም ጀምሮ የሚኖርህ ጥረትህና ልፋትህ ብሔራዊ ፈተናን በምርጥ ውጤት ያሳልፉሀል!
የዛሬ የጥናት ፕሮግራማችን የ 10ኛ ክፍል ወሳኙ የጂኦሜትሪ ዩኒት ነው፤ Maths Grade 10 Unit 6 ፤ ወሳኝ ቻፕተር! ሁሉም ተማሪ ማለፍ ይፈልጋል፤ ፍላጎት በቂ አይደለም፤ ፈተና የሚያልፈው አላማውን ለማሳካት ዋጋ የሚከፍለው ነው! የሚባክን ጊዜ የለም! መልካም የጥናት ቀን!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 5 723 |
| 8 | 🛑 ለ 2019 ብሔራዊ ፈተና በቆራጥነት ተዘጋጁ‼️
የFutureX አባላት የዛሬ ጥናት እንዴት ነው? በሞራል የምታጠኑ ፈተናውን የምትፈተኑ ሁላችሁም ጀግኖች ናችሁ! በፕሮግራም ማጥናታችሁን ቀጥሉ! ልክ ሞዴል ፈተና ስንፈትናችሁ ኢንትራንስን በቀላሉ እንደምታልፉ ኮንፊደንስ ይኖራችኋል። ከመስከረም በኋላ 11ኛ እና 12ኛን ስናጠና ደግሞ ማለፍ ብቻ ሳይሆን ከ 500 በላይ ማምጣት እንደምትችሉ እርግጠኛ ትሆናላችሁ!
የሚባክን ጊዜ የለም! በየቀኑ እናጠናለን፣ እንፈተናለን፣ ስንጨርስ ፈታ እንላለን! በርቱ ሁሌም ከጎናችሁ ነን! ያልጀመራችሁ ቆራጥ ሆናችሁ ጀምሩ! 10 ወር አለን! ለ 2019 ብሔራዊ ፈተና አብራችሁን ተዘጋጁ! ዳይ ወደ ዝግጅት!
✅ የሶሻል ተማሪዎች የ10ኛ፣ 11ኛ እና 12ኛ ክፍል History እና Geography መምህርት ወይናብ ታስተምራችኋለች፤ አታስቡ እናንተ ብቻ በርቱ!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 5 843 |
| 9 | 🛑 ከመስከረም ጀምሮ 10 ወር አለን! የቀረህን ጊዜ ተጠቀምበት! አልረፈደም‼️
መስከረምን ልንጀምር 2 ቀን ቀረን። ጥናት ምንም ያልጀመራችሁ ልጆች "ወደኋላ ቀረው፣ ገና ነኝ" ብላችሁ አትጨነቁ ከእናንተ የሚጠበቀውን ሁሉ አርጉ፣ ከዛ ፈጣሪ ያግዛችኋል። ብዙ ልጆች የኢንትራንስ ውጤት ሲመጣ የሚቆጫቸው ጊዜዬን ብጠቀም ኖሮ ብለው ነው። እስካሁን አልጀመርኩም ካልክ አሁን ጀምር! አልረፈደም‼️
ዛሬ ሁላችንም የምናጠናው English Unit 7 Writing Skill ነው። ይሄ ቻፕተር ለ English ብቻ ሳይሆን ለ SAT ብሔራዊ ፈተና በጣም ጠቃሚ ነው። English ስትጨርሱ ከዛ የትላንት ጥናታችሁ ላይ ፈተናውን ስሩ።
መልካም የጥናት ቀን!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 6 603 |
| 10 | 🛑 ለተማሪዎች ጥያቄ መልስ‼️
በዚህ ድምፅ እነዚህን ወሳኝ 4 ነገሮች ይመልሳል።
✅ መስከረም ላይ ስለሚኖርን የጥናት ፕሮግራም፤ እንዴት ነው 12ኛ እና 11ኛ ክፍልን ለኢንትራንስ ዝግጅት የምናጠናው?
✅ ወደኋላ የቀረን ተማሪዎች ወይም አዲስ ጀማሪዎች እንዴት ከ 9ኛ ጀምሮ እናጥና?
✅ ክረምትን 9ኛ እና 10ኛ ክፍል የምናጠና ተማሪዎች 12ን ከመጀመራችን በፊት የክለሳና የሞዴል ፈተናችን መቼ ነው?
✅ አፕሊኬሽኑ ላይ ቪዲዮ Download ያስቸገረን ተማሪዎች ምን እናርግ?
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 7 410 |
| 11 | 🛑 በመጪው አመት ቆራጥና ዲስፕሊን ያለው ይሳካለታል‼️
እዚህ ጋር ለመድረስ 12 ዓመት ለፍተሀል፣ ከሰኔ 2019 በፊት ያለው 10 ወር ለብሔራዊ ፈተና ውጤትህ ወሳኝ ነው! ራስህን አዘጋጅ! ቀን 12ን ስትማር 12ን አብረን እናጠናለን፤ ከዛ 11ንም እንከልሳለን። 9 እና 10ንም ደግመን እናጠናለን። ወስነህ ጀምር፤ በብሔራዊ ፈተና ታሪክ ትሰራለህ!
ዛሬ ሁላችንም Math's Grade 10 Unit 5 እንጨርሳለን። 10ኛን ጥሩ እያሄድን ነው በደምብ ጨርሱ። ከሰኔ በፊት ቀጣዩን 10 ወራት ለኢንትራንስ ዋጋ ከከፈልክ ዕድሜ ልክህን በራስህ ሁሌም ትኮራለህ! ቤተሰብህን ታስደስታለህ! መቼም አይቆጭህም!
መልካም የጥናት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 7 961 |
| 12 | 🛑 ክረምቱ አለቀ! ማጥናት ያልጀመራችሁ ጀምሩ!
በፕሮግራም የምታጠኑ ልጆች ጀግና ናችሁ! ጥናት ያልጀመራችሁ ልጆች "ለምን እስከዛሬ ጥናት አልጀመርኩም? ሰነፍ ነኝ! አልረባም!" አትበል። ትላንት ላይመለስ አልፏል፤ ራስህን መውቀስ አቁም! መጪውን መስከረም አብራችሁን ለማጥናት ተዘጋጁ!
ቀጣይ አመት ተፈታኝ ከሆንክ በዚህ እስከ ሰኔ ባለው 10 ወር ሁሉንም መቀየር፣ ውጤትህን ማሳመር፣ ህልምህን ማሳካት፣ ቤተሰቦችህን ማኩራት ትችላለህ! በፕሮግራም ከኛ ጋር ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ያለውን ብታጠና ፈተና ብትሰራ ሳትጨነቅ ኢንትራንስን ታልፋለህ! የFutureX አባላት የዛሬን ጥናት ጨርሱ! ፈተናም ተፈተኑ!
መልካም የጥናት ምሽት!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 7 809 |
| 13 | 🛑 8ኛ ሳምንት የጥናት ፕሮግራም ዛሬ ተጀመረ‼️
እንዴት አደርክ የነገው የዩኒቨርስቲ ተማሪ🫡 ? ይሄ ሳምንት በብሔራዊ ፈተና ውጤታማ ለመሆን ወሳኙ ነው!! በዚህ ክረምት ዝግጅት ብቻ የብሔራዊ ፈተና ውጤታችሁን ከግማሽ በላይ ማምጣት ትችላላችሁ! እስካሁን ካልጀመርክ አሁን ወስነህ ጀምር፤ 10 ወር አለህ ተጨቀምበት!
በዛሬ ፕሮግራም ናቹራሎች Grade 10 Biology Unit 6 እና Physics Unit 4 ፤ ሶሻሎች ደግሞ History Unit 4 እና Econimics Unit 6 እናጠናለን። እነሱን አጥንተን ስንጨርስ ናቹራሎች ትላንት የተማርነው ላይ ፈተና ትሰራላችሁ። በርቱ ፈጣሪ ይርዳችሁ! መልካም የጥናት ሳምንት!🙏
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 8 361 |
| 14 | 🛑 ዕቅድ + ዲስፕሊን = ምርጥ የኢንትራንስ ውጤት‼️
መጪው አመት የሁሉም ተማሪ ህይወት የሚቀየርበት ነው። ከ 9ኛ ክፍል ጀምሮ የረሳኸውን፣ ያልገባህን ሁሉ ገብቶህ መጨረስ አለብህ። ከዛ ወደ 10ኛ ክፍል እንቀጥላለን። የቀን ት/ት ስትጀምሩ ደግሞ 12ንቀን እየተማርን ማታ 11ን እንከልሳለን።
ከእናንተ የሚጠበቀው የምንላችሁን በዲስፕሊን ማድረግ ነው። የዛሬው ጥናት እንዴት እየሄደ ነው? የዛሬውን ጨረሳችሁ? የትላንቱን ፈተናዎቹንስ ተፈተናችሁ? የጨረሳችሁ ልጆች ፈታ በሉ፤ ነገ እንቀጥላለን፤ ያልጨረሳችሁ አሁኑኑ በሞራል የዛሬን ጥናት ጨርሱ! ዳይ ወደ ጥናት!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 8 213 |
| 15 | 🛑 ነሀሴ ተፈፀመ! ከ 5 ቀን በኋላ መስከረም ነው‼️
7ኛው ሳምንት ማብቂያ ደረስን። አራተኛው ሳምንት ዛሬ ይፈፀማል። 10ኛ ክፍልን እያጋመስን ነው፤ በሚቀጥሉት ሳምንታት ያልቃል። በዓላማ ተነስ። እሁድ የእረፍት ቀን ሳይሆን የሳምንቱ ቁልፍ ቀን ነው። በዚህ ከቀጠልክ አይምሮህ ውስጥ ወዳሰብከው የኢንትራንስ ውጤት እየተጠጋህ ነው፤ ካቆምክ ግን ጸጸት ይጀምራል።
ዛሬ ናቹራሎች G-10 Chem Unit 4
እና ሶሻሎች Eco Unit 4 & 5 ታጠናላችሁ። ከዛ እሱን ስንጨርስ የትላንቱ ጥናት ላይ ፈተና እንፈተናለን። ዛሬ የእሁድን ጨርሳችሁ በደምብ እረፍት አርጉ፤ ወደኋላ የቀራችሁ ይሄን ቀን ተጠቀሙበት! ዳይ ወደ ጥናት!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 8 860 |
| 16 | 🛑 ዲስፕሊን ካለህ የማታሳካው ነገር የለም‼️
የዛሬ ጥናት እንዴት ነው? በሞራል እያጠናችሁ ፈተናውን እየተፈተናችሁ ነው! 9ኛ እና 10ክፍልን በዚህ ክረምት ለመጨረስ በፕሮግራም እያጠናችሁ ነው! ልክ ስንጨርስ ኢንትራንስን እንደምታልፉ ኮንፊደንስ ይኖራችኋል። ቀጣይ አመት 11ኛ እና 12ኛን በደምብ ነው የምንዘጋጀው።
ጀግና ናችሁ! ክረምታችሁን በአግባቡ ተጠቅማችሁበታል። አሁንም 10ኛ ክፍልን እስክንጨርስ አብረን እናጠናለን፣ እንፈተናለን፣ ስንጨርስ ፈታ እንላለን! በዚህ ክረምት ለማጥናት መወሰናችሁ በህይወታችሁ የምትኮሩበት ትልቁ ውሳኔ ነው! በርቱ ሁሌም ከጎናችሁ ነን! አልከፍት ያሉ ቪዲዮዎችን እያሟላን ነው፤ በዚህ ሳምንት እንጨርሳለን።
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 8 701 |
| 17 | 🛑 ቅዳሜን በዲስፕሊን መጠቀም ግዴታ ነው‼️
500, 000 የሚጠጋ ተማሪ በየአመቱ ብሔራዊ ፈተናን ይፈተናል፤ 50ሺው ብቻ ወደ ዩኒቨርስቲ ያልፋል። በውጤት ያ ደስታ በዛሬው ጥረትህ ይወሰናል። ሌሎች ቅዳሜና እሁድን ፈታ ሲሉበት አንተ ደግሞ ጥግ ድረስ ትጠቀምበታለህ። ከዛ ማለፍህ ይረጋገጣል።
ዛሬ ናቹራሎች G-10 Phy Unit 3 & Chem Unit 3 እና ሶሻሎች G-10 Geo Unit 3 & 4 እናጠናለን። እነሱን አጥንተን እንደጨረስን ትላንት ያጠናነው ላይ ጥያቄ እንሰራለን። አደራ ቅዳሜህ እንዳይባክን፤ ቀኑን ሙሉ በሙሉ ተጠቀምበት።
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 9 656 |
| 18 | 🔥 2019 ኢንትራንስ የኛ ነው‼️
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 9 684 |
| 19 | 🛑 ዛሬ SAT Maths እንጀምራለን‼️ክረምት እያለቀ ነው፤ ስለዚህ ተጠቀምበት‼️
ክረምቱ እየተፈፀመ ነው፤ ነሀሴ ሊያልቅ 2 ቀን ቀረው፤ አንተም በፕሮግራም እያጠናህ ነው፤ ስለዚህ መጨነቅ የለም! የዚህ ክረምት ቀናት ልፋትህ ብሔራዊ ፈተናን በምርጥ ውጤት ያሳልፉሀል!
ዛሬ ሁላችሁም SAT Maths Unit 1 & 2 (6-8 የኢንትራንስ ጥያቄ ይወጣበታል) ፤ እነሱን አጥንተን ስንጨርስ ትላንቱት የተማርነው ላይ ፈተና እንፈተናለን። ዛሬ ካንተ ከፍተኛ ጥረት ይፈለጋል፤ ሌሎች ሲያርፉ አንተ ጥረትህንጨምር። እያንዳንዱን ሰከንድ ተጠቀም። የሚባክን ጊዜ የለም!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 10 951 |
| 20 | 🛑 በፕሮግራም ስታጠና ጊዜህ አይባክንም! ጥሩ እየሄድን ነው በርቱ‼️
ቆራጥ የሆነ ተማሪ በፕሮግራም ያጠናል፣ ዲስፕሊን እና ትከረት አለው!! ስልካችንን ከትምህርት ውጪ ለምንም ነገር አንጠቀምም! ⭐️ "ይሄ ወቅት ለህይወታችን በጣም ወሳኝ ነው!" ይሄንን መቼም እንዳትረሱ።
የዛሬን ጥናት እና ፈተና ዛሬ ጨርሱ። ጊዜያዊ ስሜትህን ተቆጣጥረህ ለኢንትራንስ ዋጋ ከከፈልክ ዕድሜ ልክህን በራስህ ትኮራለህ! አይቆጭህም! ሁላችሁም የሚገርም ጥረት እያረጋችሁ ነው፤ ጀግኖች በርቱ!
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል! | 10 122 |
