ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Открыть в Telegram
1 330
Подписчики
Нет данных24 часа
+97 дней
+8030 дней
Архив постов
#አሁን_Happening_Now #የሰልጣኝ_ተማሪዎች_ምረቃ
#አሁን_Happening_Now #የሰልጣኝ_ተማሪዎች_ምረቃ

ከ ሆለታ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የEASTRIP ፕሮጀክት አስፈጻሚ ቡድን አባላት እና የኮሌጁ ማኔጅመንት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥና የመስክ የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ በመስክ ጉብኝቱ እና
+6
ከ ሆለታ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የEASTRIP ፕሮጀክት አስፈጻሚ ቡድን   አባላት  እና የኮሌጁ ማኔጅመንት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ   የልምድ ልውውጥና የመስክ የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ በመስክ ጉብኝቱ እና በልምድ ልውውጡ   ወቅት የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የEASTRIP ፕሮጀክት አፈጸጸም  እንዲሁም የልህቀት ማእከሉ የግንባታ ሂደት  እስካሁን የደረሰበት ደረጃ  የቀረበ ሲሆን በልምድ ልውውጡ ወቅት የተሳተፋ  አካላት ለሚያነሱዋቸው የተለያዩ ጥያቄዎች የኮሌጁ የፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ቡድኑ አባላት ለተሳታፊዎቹ ገለጻ ተደርጓል ። የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም  ድሬዳዋ

photo content

#MesiratEthiopia ድሬዳዋና ሃዋሳ ቢዝነሱን ማሳደግ ለሚፈልግ ⬇️ - በፋይናንስ፣ - በማርኬቲንግ፣ - ችሎታን በማዳበር፣ - በቴክኖሎጂ፣ - በኔትወርኪንግ፣ - የባለሙያ አማካሪዎችን በማግኘት፣ - በፖሊሲ፣ - በአገልግሎት ሰጪነት እና - በአማካሪነት ድጋፍ ለማግኘት https://bit.ly/3BGeH75 ላይ ተመዝገቡ። የመስራት ስራ ፈጠራ ፕሮግራም አባል ይሁኑና ቢዝነስዎ እንዲያድግ አጠቃላይ ድጋፍን ያግኙ። ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ!

photo content

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ለምስራቅ ዕዝ መከላከያ ሪፈራልና ማስተማሪያ ተቋም በሥሩ ለሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በአሰልጣኝነት ለተመደቡ የጤና ባለሙያዎች የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠን ስነ ዘዴ/ TVT Methodology / ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፤ በዚህም ስልጠና ባለሙያዎቹ ውጤትን መሰረት ያደረገ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና በንድፈ ሃሳብ እና በተግባር የተደገፈ እንደመሆኑ ስልጠናው በቴ/ሙ/ስ ተቋማት ውስጥ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና የማሰልጠን ሥነ-ዘዴውን በሚገባ ተረድተው በ2017 ዓ.ም ከመላው አገሪቱ የሚመደቡ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን አቅም የሚገነባ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ቢሮው ለምስራቅ ዕዝ መከላከያ ሪፈራልና ማስተማሪያ ተቋም በሥሩ ለሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በአሰልጣኝነት ለተመደቡ የጤና ባለሙያዎች የሚሰጠው ስልጠና ለ7 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በስልጠናው ማጠናቀቂያ በሚኖራቸው ምዘና መሰረት ብቁ የሆኑትን ሰርቲፋይ በማድረግ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን የሚሰጡ ዕውቅና ያገኙ አሰልጣኞች ያደርጋቸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

🏆እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን🏆 የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በISO 9001 2015 QUALITY MANAGEMENT SYSTEM የአሰራር ስርዓቱን ለማሻሻልና እውቅና ለማግኘት ባለፉት
🏆እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን🏆 የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በISO 9001 2015 QUALITY MANAGEMENT SYSTEM የአሰራር ስርዓቱን ለማሻሻልና እውቅና ለማግኘት ባለፉት ጊዜያት እንደ ተቋም የተለያዩ ስራዎችን  እየሰራ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ላለፉት 10ቀናት ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በተመደበ የኦዲት ባለሙያ የEXTERNAL OR CERTIFICATION AUDIT ሲካሄድ ቆይቶ በዛሬው ዕለትም በተደረገው የCLOSING MEETING ኮሌጃችን የISO 9001 2015 ሰርተፊኬት እውቅና ለማግኘት ብቁ መሆኑንና RECOMMEND መደረጉን በኦዲተሩ በኩል ተረጋግጧል:: ይህ ስኬት በሁሉም የጋራ ጥረትና ድካም የተገኘ በመሆኑ የኮሌጃችን ማህበረሰብ በሙሉ በድጋሚ እንኳን ደስ አለን::🔥🔥🏆🏆🏆 ©️ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን

🏆እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን🏆 የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በISO 9001 2015 QUALITY MANAGEMENT SYSTEM የአሰራር ስርዓቱን ለማሻሻልና እውቅና ለማግኘት ባለፉት
🏆እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን🏆 የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በISO 9001 2015 QUALITY MANAGEMENT SYSTEM የአሰራር ስርዓቱን ለማሻሻልና እውቅና ለማግኘት ባለፉት ጊዜያት እንደ ተቋም የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ላለፉት 10ቀናት ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በተመደበ የኦዲት ባለሙያ የEXTERNAL OR CERTIFICATION AUDIT ሲካሄድ ቆይቶ በዛሬው ዕለትም በተደረገው የCLOSING MEETING ኮሌጃችን የISO 9001 2015 ሰርተፊኬት እውቅና ለማግኘት ብቁ መሆኑንና RECOMMEND መደረጉን በኦዲተሩ በኩል ተረጋግጧል:: ይህ ስኬት በሁሉም የጋራ ጥረትና ድካም የተገኘ በመሆኑ የኮሌጃችን ማህበረሰብ በሙሉ በድጋሚ እንኳን ደስ አለን::🔥🔥🏆🏆🏆

"ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ፡፡ በዚህም 17ኛውን የብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በዓል የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞች ቃለ-መሃላ በመግባት አክብረዋል፡፡ በበዓሉ ማጠናቀቂያ በአንድነት ለሰንደቅ ዓላማ  ክብር በሰጠና የብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ እንዲሁም የሉአላዊነታችንና የኢትዮጵያ ከፍታ ምልክት መሆኑን በሚያሳይ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የታጀበ የባንዲራ መስቀል ስነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+6

"ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!" በሚል መሪ ቃል የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ፡፡ በዚህም ለ17ኛውን የብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን በዓል የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ እንዲሁም የኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞች ቃለ-መሃላ በመግባት አክብረዋል፡፡ በበዓሉ ማጠናቀቂያ በአንድነት ለሰንደቅ ዓላማ  ክብር በሰጠና የብሔራዊ አንድነታችን መገለጫ እንዲሁም የሉአላዊነታችንና የኢትዮጵያ ከፍታ ምልክት መሆኑን በሚያሳይ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የታጀበ የባንዲራ መስቀል ስነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ "ብቃት" የወጣቶች ሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ አምስተኛው  ዙር የአቻ ለአቻ ውይይት ተደረገ፤      ወጣቶቹ  በየወሩ የአቻ ለአቻ  ውይይት  በማድረግ  በየጊዜው ያገኙትን እውቀት  የገጠማቸውን ችግሮች  ለይተው የተወያዩበት መድረክ  ሲሆን ይህ  ለአምስተኛ ጊዜ የተዘጋጀ  ውይይት የተደረገ ሲሆን የሥራ ላይ ልምምዱን ሲያጠናቅቁ  በተቀጠሩበት ወይም በሚቀጠሩበት ድርጅቶች በሰለጠኑት ሞያ መሰረት ለማገልገል እራሳቸውን የሚያዘጋጁበትና እርስበርሳቸው የሚመካከሩበት ይሆናል፡፡     በተለይ ወጣቶቹ በተመሳሳይ ዕድሜ ላይ የሚገኙ እንደመሆናቸው በነጻነትና በግልጽ መወያየት የቻሉ ሲሆን ከሥራ ባህልና ባህሪ ጋር የተገናኙ ጉዳዮችና የገጠሟቸውን ገጠመኞች ያነሱበት ነበር ለቀጣይ ጉዟቸውም የተማማሩበትና ትኩረት ማድረግ የሚገባቸው ነገሮች ላይ እንዲያተኩሩ ከፕሮግራሙ አስተባባሪዎች የሚደረግላቸው ድጋፍና ክትትልም ይቀጥላል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት  2/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+5

የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ "ብቃት" የወጣቶች ሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ትግበራ አምስተኛው  ዙር የአቻ ለአቻ ውይይት ተደረገ፤      ወጣቶቹ  በየወሩ የአቻ ለአቻ  ውይይት  በማድረግ  በየጊዜው ያገኙትን እውቀት  የገጠማቸውን ችግሮች  ለይተው የተወያዩበት መድረክ  ሲሆን ይህ  ለአምስተኛ ጊዜ የተዘጋጀ  ውይይት የተደረገ ሲሆን የሥራ ላይ ልምምዱን ሲያጠናቅቁ  በተቀጠሩበት ወይም በሚቀጠሩበት ድርጅቶች በሰለጠኑት ሞያ መሰረት ለማገልገል እራሳቸውን የሚያዘጋጁበትና እርስበርሳቸው የሚመካከሩበት ይሆናል፡፡     በተለይ ወጣቶቹ በተመሳሳይ ዕድሜ ላይ የሚገኙ እንደመሆናቸው በነጻነትና በግልጽ መወያየት የቻሉ ሲሆን ከሥራ ባህልና ባህሪ ጋር የተገናኙ ጉዳዮችና የገጠሟቸውን ገጠመኞች ያነሱበት ነበር ለቀጣይ ጉዟቸውም የተማማሩበትና ትኩረት ማድረግ የሚገባቸው ነገሮች ላይ እንዲያተኩሩ ከፕሮግራሙ አስተባባሪዎች የሚደረግላቸው ድጋፍና ክትትልም ይቀጥላል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት  2/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

በህገወጥ መንገድ ያለ ፈቃድ በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ህገወጥ ኤጀንሲዎች ላይ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ወደ ሕጋዊነት እንዲመጡ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ በህገወጥ መንገድ ያለ ፈቃድ በመንቀሳቀስ በግል ሥራና ሰራተኛ አገናኝነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ህገወጦች በአስተዳደሩ እየተበራከቱ ስለመጡ በእነዚህ ኤጀንሲዎች በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የመብት ጥሰት ለመከላከል አስፈላጊውን ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ ፍቃድ ሳይኖራቸው ቢሮ ከፍተው የሚሰሩትን ወደ ሕጋዊነት እንዲመጡ ቢሮአቸው እንዲታሸግ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ ቢሮው ወደዚህ እርምጃ ከመምጣቱ አስቀድሞ መንግስት በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት በማድረግ ኤጀንሲዎች አገልግሎት የሚሰጡበትን መመሪያ ቁጥር 45/2013 አውጥቶ ሥራ ላይ እንዲውል አድርገጓል፤ ይህም መመሪያ ለተግባራዊነቱም ይረዳ ዘንድ በአስተዳደሩ የሥራና ክህሎት ቢሮ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ በተለያዩ መድረኮች ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ተሰርቷል ፡፡ በቀጣይም ቢሮው በሀገር ውስጥ በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሚሰጠውን የሥራ ስምሪት አገልግሎት በብቃትና በተገቢው በመከታተል፣ በመቆጣጠርና በመደገፍ፣ በሥራ ላይ የሚሠማሩ ሠራተኞች መብት፣ ደህንነትና ጥቅም የሚጠበቅበትን ሁኔታ መፍጠር እና የኢንዱስትሪ ሠላምን ማስፈን  ላይ ትኩረት አድርጎ የሚንቀሳቀስ ይሆናል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+5

የ EASTRIP ፕሮጀክት የልህቀት ማእከል የህንጻ ግንባታ የስራ አፈጻጸም ከስራና ክህሎት ሚንስቴር እና ከEASTRIP National Project Coordinator ቢሮ በተውጣጣ የSupervision
+6
የ EASTRIP ፕሮጀክት የልህቀት ማእከል የህንጻ ግንባታ የስራ አፈጻጸም   ከስራና ክህሎት ሚንስቴር እና ከEASTRIP National Project Coordinator ቢሮ በተውጣጣ የSupervision team ግምገማ  በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተከናወነ፡፡ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስር መተግበር ላይ ያለው የEASTRIP ፕሮጀክት  ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች የልህቀት ማዕከሉን የህንጻው ግንባታ አፈጻጸም ገመገሙ፡፡ ለግምገማው የመጣውን ልኡክ ቡድን የተቀበሉትና የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እንዲሁም የኮሌጁን ሁኔታና የፕሮጀክቱን ሁኔታ  ለልኡክ ቡድኑ ያብራሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ሳሊም ኡስማን ሲሆኑ በንግግራቸውም በኮሌጁ እየተተገበረ ያለው ይህ የ EASTRIP ፕሮጀክት መሳካት በኮሌጁ ማኔጅመንት ትልቅ ድጋፍና ክትትል እየተደረገበት አሁን ላለበት ደረጃ ደርሷል ሆኖም ግን በሚፈለገው ፍጥነት ልክ ተሰርቶና በአግባቡ ተጠናቆ ለታለመለት አላማ እንዲውል የከተማ አስተዳደሩ በቅርበት እየተከታተለው እንዲሁም የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም ስለ ልህቀት ማእከሉ የህንጻ ግንባታ እንዲሁም አሁን ያለበትን ሁኔታና በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች የአማካሪ ድርጅቱ መሐንዲስ ዮሃንስ እቁባይ አማካኝነት ቀርቧል፡፡ ከሪፖርቶና ከመስክ ጉብኝቱ በኋላ በቀረበው አፈጻጸም ላይ ልኡክ ቡድኑ የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን በመጨረሻም በፕሮጀክቱ የስራ አፈጻጸም ላይ የSupervision ቡድኑ  አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን መስከረም  28/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content

የ2017 ዓ.ም የሥራ ፈላጊዎች ምዝገባ በሁሉም የአስተዳደራችን ወረዳ አንድ ማዕከላት እየተካሄደ ይገኛል። በዚህም ሥራ ፈላጊ የአስተዳደራችን ነዋሪዎች አቅራቢያችሁ በሚገኙ አንድ ማዕከላት(ቀበሌ) በመሄድ እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን።                የድሬዳዋ አስተዳደር                የሥራና ክህሎት ቢሮ