ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Открыть в Telegram
1 321
Подписчики
+124 часа
+67 дней
+14830 дней
Архив постов
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ዳይሬክቶሬት ለአሰሪና ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ። በመድረኩም ከተለያዩ የአስተዳደሩ ኢንዱስትሪዎች ለተወጣጡ አሰሪና ሰራተኞች በሁለትዮሽ ማህበራዊ ምክክር ዝርጋታ እና በአሰሪና ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል። በዚህም አዋጁን በመረዳት የአሰሪውንና ሰራተኛውን ግንዛቤ ማሳደግ ዓላማው አድርጎ ከዚህ ጎን ለጎን የኢንዱስትሪውን ሰላም በማረጋገጥ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚኖሩ አለመግባባቶችን በመቀነስ የስራ ክርክሮችን በምክክር መፍታት የሚያስችላቸው ይሆናል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+7

የተቋማትን አቅም በማጠናከር የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግቡ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሰልጣን EAC ፕሮጀክት ለኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተለያዩ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሰልጣን EAC ፕሮጀክት ከሚተገብራቸው ስራዎች አንዱ የተቋማትን አቅም መገንባት መሆኑ ይታወቃል፡፡ከነዚህ ተቋማት አንዱ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ በዚህ መሰረት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚገኘው EAC ፕሮጀክት በዛሬው እለት ለኮሌጁ አምስት ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች፣አንድ ኤልሲዲ ፕሮጀክተር እና አንድ ፕሪንተር ድጋፍ አድርጓል፡፡ በድጋፍ ርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሰልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱ መሀመድ ድጋፉ ከኮሌጁ ጋር የምንሰራቸውን ስራዎች ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር በአንጻሩ ከኮሌጁ የምናገኛቸውን የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች አሰተማማኝ ደረጃ ላይ ያደረሰ ብለዋል፡፡ የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በበኩላቸው ከአካባቢ ጥበቃ EAC ፕሮጀክት የተደረገው ድጋፍ ተቋማትን በስራና በቴክኖሎጂ ለማስተሳሰር ያለው ሚና የላቀ እና በሌሎችም ተቋማት ሊለመድ የሚገባው ምሳሌ የሚሆን መልካም ተግባር ነው ብለዋል፡፡ የኮሌጁ ዲን አክለውም ያለን የስራ ግንኙነት የላቀ ደረጃ የደረሰ መሆኑን ማሳያ ሲሆን ኮሌጁም ለፕሮጀክቱ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በአይነትና በጥራት አንዲጨምር ትልቅ ኃላፊነት ለኮሌጁ የሰጠ ነው ብለዋል፡፡ የEAC ፕሮጀክት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ በላይነህ ደስታ የተሰጡት ድጋፎች ከኮሌጁ ጋር አብሮ ለመስራትና የፕሮጀክቱን አላማዎች በቀላሉ ከምናሳካባቸው መንገዶች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ለስራው መሳካት የተባበሩትን አካላት ሁሉ አመስግነዋል ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሰልጣን ያደረሰን መረጃ ያመላክታል #DGC

<<የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከድሮ እሳቤ በመውጣት ትምህርትና ስልጠናቸውን የአሰራር ሂደታቸውን የስራ ፈጣሪነት የተላበሰ እንዲሆን ሊሰሩ ይገባል ተባለ፡፡>> #ዜና|በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተቋሞችን ስርዓቶች አስተሳሰብ እና ስራ ፈጣሪነት ሚናዎች እንዲሁም ልምዶችን መለወጥ የሚያስችል ስልጠና ለኮሌጁ ማህበረሰብና ለባለ ድርሻ አካላት በዛሬው እለት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ተቋማትን ስንገነባ የስራ ፈጣሪነት የተላበሱ ሆነው እንዲገነቡ በርካታ ስራዎችን እየሰራን ቆይተናል ያሉት በስልጠናው ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ክቡር አቶ ሮቤል ጌታቸው ሲሆኑ የቢሮው ኃላፊ አያይዘውም መንግስታችን ኢንተርፕሩናል መንግስት እንደመሆኑ መጠን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ይህንን ተረድተው ከተለመደው አሰራር በመውጣት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡ይህንንም እሳቤ በማህበረሰቡ ዘንድ በማስረጽ ረገድ EDI የሚሰራው ስራ ትልቅ ነው ብለዋል፡፡በመጨረሻም በዚህ ስልጠና የተገኘውን ግብአት በመጠቀም ኮሌጁን ኢንተርፕሩናል ኮሌጅ እንዲሆን ሁሉም የኮሌጁ አካላቶች እንዲሁም ባለ ድርሻ አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡ ይህ በዛሬው እለት ከ EDI ጋር በመተባባር የሚሰጠው ስልጠና ከመንግስት እንደ ቢሮ ያለ እሳቤ ነው ይህንን እሳቤ ደግሞ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም በለ ድርሻ አካላቶች ከወቅቱ ጋር መራመድ የሚችሉና የስራ ፈጣሪነትን የተላበሱ ሊሆኑ ይገባል ያሉት የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ሲሆኑ አያይዘውም ከዚህ በፊት ስንሰራበት የነበረውን አሰራር በመቀየር ከአዲሱ እሳቤ ጋር ትምህርትና ስልጠናዎችን አስተሳስረን ልንሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡ አዲሱ የቴክኒክና ሙያ እሳቤ በርካታ ጉዳዮችን ይዞ የመጣ እንደ መሆኑ መጠን ኮሌጃችንን በአዲሱ እሳቤ የተቃየኘ የትምርትና ስልጠና ስራዎችን ለመስራት ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ተግባር ለማስገባት እየሰራ ይገኛል ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ የኮሌጁ ዲን አያይዘውም በተያዘው በጀት አመት የዘርፉን እሳቤ መቀየር የሚችሉ እንዲሁም የኮሌጁን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ሊለውጡ የሚችሉ በርካታ ስራዎችን እየሰራን ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስፈልጉ ለውጦችን ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡ በዛሬው እለት በኮሌጁ እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ከEntrepreneurship Development Institute(EDI) ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ስልጠና ሲሆን ስልጠናውንም ከEDI በመጡ አሰልጣኝ አቶ ቴዎድሮስ አበበ አማካኝነት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በስልጠናው ላይም የሽራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች፣ከፍተኛ ባለሙያዎች፣የኢንዱስትሪ አማካሪ የቦርድ አባላት፣የኮሌጁ ሰራተኞች እና አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን የዘርፉን ለውጥ የመምራት አስተሳብን የመላበስ እንዲሁም የተቋሙን የኢንተርፕራይዝ ልማት አስተዳደርና የራስን ገቢ በዘላቂነት የማመንጨት ሂደት ውስጥ የሚገጥሙ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ሰለባለ ድርሻ አካላቶች በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚያስችል ስልጠና እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የአርዳይታ ግብርና ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ አመራሮችን ያቀፈ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡ የአርዳይታ ግብርና ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ የEASE ፕሮጀክት ከሚተገበርባቸው 24 የሚሆኑ የሀገሪቱ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አንደኛው ሲሆን በዚህም የኮሌጁን ዲኖች ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት እንዲሁም በEASE ፕሮጀክት ትግበራ ያለውን ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን የስራ ልምድ ልውውጥ በኮልጁ ማካሄድ ችለዋል:: ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ የEASE ፕሮጀክት ትግበራን ጨምሮ ጠቅላላ በተቋም የተመዘገቡ የአፈፃፀም ውጤቶችን በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከምስረታው አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል:: ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው አቀባበልና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት ትግበራ ካሳየው የስራ አፈፃፀም ብዙ ልምዶችን መቅሰም መቻላቸውንም ገልፀዋል:: በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን በኮሌጃችን ማድረግ ችለዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኮሌጁ እየሰለጠኑ የሚገኙ ሰልጣኞች ከዘመኑ ጋር እኩል እንዲራመዱ እና ለቀጣይ የስራ ጊዜ ዝግጁ እንዲሆኑ እየሰራ እንዳለ ገለጸ፡፡ #ዜና|የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች በዘንድሮ አመት ኮሌጁን ከተቀላቀሉ እንዲሁም ከነባር ሰልጣኞች ጋር የጋራ ውይይት በዛሬው እለት ተከናወነ፡፡ በውይይ መድረኩ ላይ በመገኘት እንዲሁም ከሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ እንዲሁም ማብራሪያ የሰጡት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ በንግግራቸውም ወጣቶች ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት እንዲሆኑ እንዲሁም ቀጣዩን የስራ ጊዜ በICT የተደገፈ እንደመሆኑ መጠን ሰልጣኞች ለዚህ ደግሞ ዝግጁ እንዲሆኑ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራን ከነዚህም ውስጥ የኢንተርፕሩነርሺፕ፣የዲጂታላይዜሽን፣የስራ አፈላለግ እና የህይወት ክህሎት ስልጠና እየሰጠን እንገኛለን ያሉ ሲሆን የኮሌጁ ዲን አያይዘውም ከኮሌጃችን ሰልጥነው የሚያጠናቅቁ ሰልጣኞቻችን በሙሉ ከሚሰለጥኑት ስልጠና በተጨማሪ ሌሎች የሙያ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ እና በተለያዩ ስራዎች እንዲሳተፉ ሰፊ ስራዎችን ሰርቷል ብለዋል፡፡ ሰልጣኞች ስልጠናቸውን አጠናቀው ወደ ስራው አለም ሲቀላቀሉ በአግባቡ የተጣለባቸውን ኃፊነት እንዲወጡ ለስራ ዝግጁ የሚያደርጉ ስልጠናዎችን ከመደበኛው ስልጠና ጎን ለጎን እንዲወስዱ እየተደረገ እንዳለ ለሰልጣኞቹ ያብራሩ ሲሆን በመጨረሻም በኮሌጁ የሚሰለጥኑ ሰልጣኞች ከዘመኑ ጋር እኩል የሚራመዱ እና ለቀጣይ የስራ ጊዜ ዝግጁ እንዲሆኑ እንዲሁም ሃገር ወዳድ ዜጎች እንዲሆኑ ሁሉም አካላት በጋራ በመሆን መስራት ይገባናል ብለዋ፡፡ በዛሬው እለት በተደረገው የጋራ የውይይት መድረክ ላይ ሰልጣኞች ከኮሌጁ ጋር ስላላቸው የግንኙነት አግባብና መብትና ግዴታ ሰነድ የቀረባ ሲሆን በተጨማሪም 5 ሚሊዮን ዜጎች ስለሚሳተፉበት Ethio coders ስልጠና ማብራሪያ ተሰጥቷል በቀጣይም ከመደበኛ ስልጠናው ጎን ለጎን ሰልጣኞች ስልጠናውን እንደሚወስዱ በእለቱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ታህሳስ 6/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ሶሻል ሚዲያ ላይ በተሰራጨው ሀሰተኛ መረጃን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሰፊ የሪፎርም ማዕቀፍ ነድፎ በመተግበር ላይ ነው። ይህም ሰባት ዋና፣ ዋና አምዶች ያሉት ነው። አምዶቹም፦ 1. የኢንዱስትሪ፣ ሙያ ምድብ እና ክፍያና ጥቅማ ጥቅም ማሻሻል 2. የሙያ ብቃት ግንባታ 3. የአገልግሎት ማላቅ 4. ዘመናዊ የሰው ኃይል አመራር 5. የብዝሃነትና አካታችነት ማረጋገጥ 6. ዲጂታላይዜሽ ማስፋፋት እና 7. የአመራር አቅም መገንባት ናቸው። እነዚህ ሥራዎችን ለማስተግበር ፈጻሚ እና ባለቤት ተቋማት በዌቮች (Wave I, Wave II & Wave III) ተከፋፍለው ወደ ትግበራ የተገባ ሲሆን አፈጻጸሙም ተስፋ ሰጪ ነው። ከሰባቱ የሪፎርም አምዶች አንዱ የአገልግሎት አቅርቦት ሂደቱን ማላቅ ነው። በተደረገው የአፈጻጸም እንቅስቃሴ ተጨባጭ እና በኢትዮጵያ የመንግስት አገልግሎት ማሻሻል ብቻ ሣይሆን ማላቅም እንደሚቻል በተግባር ታይቷል። የፌዴራሉን ጨምሮ እሰከ እዚህ ወር ባለው ጊዜ 21 የመሶብ (MESOB:-Modern Ethiopia Services for Organized Benefits) ተገንብተው በሥራ ላይ ናቸው። በየማዕከላቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝድ የሆኑ አገልግሎቶች ብቻ ናቸው። የICT እውቀት የሌላቸውን ዜጎች የሚታገዙበት ሥርዓት እንዲኖረው ተደርጎ የተነደፈም ነው። በአሁኑ ሰዓት ይህንኑ ወደ ሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች ለማስፋፋት በመረባረብ ላይ እንገኛለን። ይህንን ሥራ የሚመራ እና በአፍሪካ ተምሣሌታዊ ተግባር እና ቁመና ያለው አደረጃጀት እና ሥርዓት ለመፍጠርም ጥረት እየተደረገ ነው። ከእነዚህ ተግባራት አንዱ የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ግንባታ ማካሄድ ነው። የግንባታ የጨረታ ሰነድ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሳይሆን በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) ተዘጋጅቶ እና በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ጸድቆ በ egp.mofed.gov.et አለም አቀፍ ጨረታው ወጥቷል። ለእዚህም ዲዛይን እና ግንባታ ግልጽ ጨረታ ውድድር የዓለም አቀፍ እና የኢትዮጵያ ተቋራጮች እየተሳተፉ ነው። በጨረታው ሂደት ማን እንደሚያሸንፍ የሚታወቅ ነገር የለም። ተወዳዳሪዎቹ ለመገምገም ከኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC)፣ ከከተማ ልማትና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተውጣጡ ባለሙያዎች ተደራጅቶ በሥራ ላይ ናቸው። አሸናፊው ከሂደቱ ይለያል ተብሎ ይጠበቃል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሂደቱን የሚያደናቅፍ እና መሠረት የሌለው እና የተዛባ መረጃ በአንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቷል። ትክክለኛ መረጃው ከላይ የገለጸው ስለሆነ ለእራሱ ታዕማኒነት ሲል ማህበራዊ ሚዲያው የተዛባውን መረጃ እንዲስተካከል እመክራለሁ። ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

የመንግስት ሰራተኛው በለውጥ ትግበራው ሂደት ላይ የራሱን ሚና መወጣት እንዲችል ተገቢውን መረጃ መስጠትና ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደሚገባ ተገለፀ:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በበጀት አመቱ ከመደበኛ ስራዎች ጎን ለጎን በመንግስት አቅጣጫ መሰረት ትኩረት ተደርጎባቸው በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ መፍጠርያ መድረክ አካሄደ:: በመድረኩ ላይ እንደ ሀገር በቀጣዮቹ 2ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅደው ከተጀመሩ ቁልፍ ተግባራት መካከል እንደ ቴክኒክና ሙያ ተቋም እንዲተገበሩ ከተቀመጡ ዝርዝር ተግባራት ውስጥ በተቋም ደረጃ የተዘጋጀው እቅድና አሁን የደረሰበት አፈፃፀም ቀርቦ ለኮሌጁ ማህበረሰብ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል:: ይህ የግንዛቤ መድረክ በዋናነት ያስፈለገው የመንግስት ሰራተኛው በመንግስት የሚወርዱ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ግልፅነት ተፈጥሮለት ታች ፈፃሚው ድረስ እንዲወርድ ለማስቻል ነው ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ አክለውም ሀገራችን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ስርዓትን እየዘረጋች እንደምትገኝና ጊዜው ከሚሰጠን ቴክኖሎጂዎች ጋር በመጣጣም የአገልግሎት አሰጣጣችንን የተቀላጠፈ በማድረግ እንደ ተቋም የተገልጋይ እርካታን በዘላቂነት ማረጋግጥ ይጠበቅብናልም ብለዋል:: በግንዛቤ መስጫ መድረኩ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ከተቀመጡት የ100% ግቦች.. የ "1" ግቦች እና የ "መቀነስ"ግቦች ጋር ተያይዞ የሚተገበሩ ዝርዝር ተግባራት ላይ በኮሌጁ ዲን አማካኝነት ገለፃ የተደረ ሲሆን በተጨሚሪም የ5million Initiative Program በተመለከተ አጠቃላይ ሰራተኛው የሚሰለጥንበት አግባብ ላይ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠርም ተችሏል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ታህሳስ 2/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ