1 318
Подписчики
Нет данных24 часа
+207 дней
+14930 дней
Архив постов
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ልዩየክረምት ስልጠና ያለምንም ክፍያ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
#ክህሎትዎን ያሳድጉ የነገ የህይወት አቅጣጫዎን ዛሬ በሚያገኙት ክህሎት ያስተካክሉ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ልዩየክረምት ስልጠና ያለምንም ክፍያ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
#ክህሎትዎን ያሳድጉ የነገ የህይወት አቅጣጫዎን ዛሬ በሚያገኙት ክህሎት ያስተካክሉ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ልዩየክረምት ስልጠና ያለምንም ክፍያ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
#ክህሎትዎን ያሳድጉ የነገ የህይወት አቅጣጫዎን ዛሬ በሚያገኙት ክህሎት ያስተካክሉ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ልዩ የክረምት የሙያ ስልጠና በአንጋፋው ኮሌጅ ክረምትን በክህሎት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ በሚል መርሀግብር የተዘጋጀ ልዩ የክረምት የስልጠና መርሐ ግብር በነጻ ይሳተፋ::
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ልዩ የክረምት የሙያ ስልጠና በአንጋፋው ኮሌጅ ክረምትን በክህሎት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ በሚል መርሀግብር የተዘጋጀ ልዩ የክረምት የስልጠና መርሐ ግብር ላይ ይሳተፋ::
‹‹የሥራ ዕድል ፈጠራን ወደ ሀብት ማፍሪያነት፣ ማኅበራዊ ተቋማትን ደግሞ ወደ ልማት ሞተርነት ለመቀየር የሁሉንም የዘርፉን አስፈፃሚ አካላት ቁርጠኝነትና ትጋት ይጠይቃል››
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ የ2018 ዓመት አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከክልሎች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የዘርፉን አዲስ እሳቤ መነሻ በማድረግ ለዘመናት የተጠራቀመውን ዕዳ የሚያቃልሉ፣ የዜጎችን አሁናዊ ፍላጎት የዋጁና የመጪውን ዓለም ነባራዊ ሁኔታ መሠረት ያደረጉ ተግባራት በበጀት ዓመቱ መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ከእነዚህም መካከል “ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ” ቀዳሚው መሆኑን ጠቅሰው ሥራ ፈላጊዎች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ልል ክህሎት (Soft Skills) እና ጠጣር ክህሎት (Hard Skills) ታጥቀው ወደ ሥራ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
የቤተሰብ ቢዝነስን በማስፋፋት፣ እሴት አካይ ምርትን በማሳደግ እንዲሁም የመስሪያ፣ የመሸጫና የካፒታል አቅርቦት ችግሮችን በማቃለል ከከ4.9 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ከአዳዲስ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም አስታውቀዋል፡፡
በኢኖቬሽን ላይ የተመሠረተ ስልት በመቀየስ ፈጣን የማደግ አቅም ያላቸውን ኢንተርፕራይዞች በቅርበት በመደገፍ ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ መቻሉን የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ለመሰል ኢንተርፕራይዞች የተሰጠው ልዩ ትኩረት “ከዳቦ በላይ” የሚለውን አዲስ እሳቤ ለማሳካት ዋነኛ ስልት ሆኖ መገኘቱንም አመላክተዋል፡፡
የሥራ ዕድል ፈጠራን ወደ ሀብት ማፍሪያነት፣ ማኅበራዊ ተቋማትን ደግሞ ወደ ልማት ሞተርነት ለመቀየር የሁሉንም የዘርፉን አስፈፃሚ አካላት ቁርጠኝነትና ትጋት እንደሚጠይቅም በአፅንኦት አንስተዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ዘርፍ የሀገራችንን ወደ ላቀ ብልጽግና ለማሸጋገር ያለውን አስተዋፅኦ በሚገባ በመገንዘብ የዘርፉን ተልዕኮዎች በክህሎትና ኢኖቬሽን ለመምራት ሁሉም አስፈፃሚ አካላት ዝግጁ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ክቡር አቶ ሰለሞን በንግግራቸው ማጠቃለያ ላይ አሳስበዋል፡፡
©️ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሀምሌ 5/2018 ዓ.ም
Repost from E-LMIS - ብቁ
📢 ለሁሉም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የሥራ ፈቃድ አመልካቾች በሙሉ
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የሥራ ፈቃድ ሂደት ላይ የማመልከቻ ሂደታችሁ ሳይጠናቀቅ ለቀረ አመልካቾች፤
ጉዳያችሁን በአግባቡ ለማጣራትና ተገቢውን መፍትሔ ለመስጠት እየሰራን ነው። ስለዚህ ከዚህ በታች በተቀመጠው ማመልከቻ ሊንክ በመግባት የሚጠየቀውን መረጃ በትክክል እንድትሞሉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
በተጨማሪም፣ ከኤጀንሲው ጋር ያደረጋችሁትን ግንኙነት፣ ሂደቱ የቆየበትን ጊዜ እና የተሰጣችሁን ምላሽ (ካለ) በዝርዝር እንድታስገቡ እንጠይቃለን።
የምትሰጡት መረጃ ጉዳያችሁን በፍጥነት ለማጣራትና ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ያግዘናል።
🔗 የማመልከቻ ሊንክ: https://forms.lmis.gov.et/agancy_form/
Repost from E-LMIS - ብቁ
🎓🌍የስልጠና እድል
🚀Yokogawa Electric Corporation ከInternational Organization for Migration (IOM) እና የኢትዮጵያ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች በነጻ የሚሰጥ ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና አዘጋጅቷል።
📚የስልጠና ዘርፎች
🔹Business Ethics & Professional Conduct
🔹Logistics & Supply Chain Management
🔹Import/Export Regulations
🔹የAfCFTA ንግድ እድሎች
🔹የGCC አገራት የስራ ገበያ እና የቅጥር እድሎች
🔹Entrepreneurship
🔹 Workplace Readiness
🔹የጥራት ማረጋገጫና የጥራት ቁጥጥር
🔹የጤና፣ ደህንነት እና አካባቢ ጥበቃ
👥መስፈርቶች
🔹ዕድሜ፦ ከ30 በታች
🔹ትምህርት፦ በ2018 ዓ.ም. የሚመረቁ የባችለር ወይም የማስተርስ ምሩቃን፣ ወይም ባለፉት 2 ዓመታት ውስጥ የተመረቁ።
🔹የትምህርት መስኮች፦
• Supply Chain Management
• Procurement
• Logistics
• Business Administration
• Trade Studies
• Sustainability
• ወይም ሌሎች ተዛማጅ የትምህርት መስኮች።
📍 ቦታ
Kaizen Excellence Centre (KEC)፣ አዲስ አበባ
📅የስልጠና ቀን- ከሐምሌ 6–8 ቀን 2018
🎁ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል 1 ተሳታፊ ተመርጦ በYokogawa Internship Program ከ2019
የልምምድ ፕሮግራም ይሳተፋል።
✅ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚኖሩ የተመረጡ ተሳታፊዎች፦
🔹የትራንስፖርት ወጪ
🔹በስልጠናው ቆይታ የማረፊያ ወጪ ይሸፈናል።
📝አመልካቾች በዚህ https://forms.lmis.gov.et/yokogawa_electric/ በመግባት ትክክለኛ መረጃዎችን ሞልተው ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
🚨 አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት
የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን በተመለከተ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወይም ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ውክልና ተሰጥቶናል በማለት በግል ስልክ፣ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፣ በቴሌግራም፣ በዋትስአፕ እና በሌሎች የማህበራዊ ትስስር ገፆች ገንዘብ በመጠየቅ ህብረተሰቡን የሚያጭበረብሩ ሕገ-ወጥ አካላት ተበራክተዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አገልግሎት በተመለከተ በስልክ፣ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፣ በቴሌግራም፣ በዋትስአፕ ወይም በሌላ ማንኛውም የማህበራዊ ትስስር ገፆች ገንዘብ እንዲከፍሉ በፍጹም አይጠይቅም፡፡
በመሆኑም እንዲህ ዓይነት የስልክ ጥሪ፣ የጽሑፍ መልዕክት ወይም በማህበራዊ ሚዲያ በኩል የገንዘብ ጥያቄ ከደረሰዎት፣
· ምን አይነት ገንዘብ አንዳይልኩና
· ምንም ዓይነት የግል ወይም የባንክ መረጃ እንዳያጋሩ እያሳሰብን ረጃውን በአቅራቢያዎ ለሚገኙ የሕግ አስከባሪ አካላት ወይም ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በየደረጃው ለሚገኙ መዋቅሮቹ በአስቸኳይ እንዲያሳውቁ እንጠይቃለን፡፡
ያስታውሱ
· በስልክ፣ በቴሌግራም፣ በዋትስአፕ፣ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) ወይም በማንኛውም ሌላ መንገድ ገንዘብ እንዲልኩ የሚጠይቅ ማንኛውም ሰው ወይም ቡድን የመንግስት ተቋምን አይወክልም፤
· የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አገልግሎትን ለማግኘት በአቅራቢያዎ ያሉ የመንግስት ተቋማትን ወይም ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎችን ብቻ ያነጋግሩ፤
· ሚስጥራዊ የግል መረጃዎችዎን፣ የባንክ ሂሳብ ቁጥር፣ የይለፍ ቃል (Password) ወይም የOTP ኮድ ለማንም አያጋሩ፤
· የውች ሀገር ሥራ ስምሪትን የተመለከቱ መረጃዎች ሚኒስቴሩ የሚያወጣቸውን ይፋዊ መረጃዎች ከተቋሙ ይፋዊ የመገናኛ አውታሮች ብቻ ይከታተሉ፤
ሕጋዊ ስምሪት፣ ለደህንነትዎ ዋስትና ነው!
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******
በኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ከ5 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ ገልጸዋል።
ከእነዚህ መካከል 4.9 ሚሊዮን የሚሆኑት በሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል ያገኙ ሲሆኑ፣ ከ101 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ የሆኑ ናቸው።
በተጨማሪም በልዩ የክህሎትና ሙያ ዘርፍ የተሰማሩ 40 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።
የየዘርፉን የሥራ ዕድል ፈጠራ ድርሻ በተመለከተም፥ ግብርና ከ2 ሚሊዮን በላይ፣ አገልግሎት፣ ንግድ እና ዲጂታላይዜሽን 1.8 ሚሊዮን እንዲሁም ኢንዱስትሪ ከ900 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውን አብራርተዋል።
የሥራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸም በሀገር ውስጥ የ13 በመቶ እንዲሁም በውጭ ሀገራት ስምሪት የ27 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።
የፋይናንስ ዘርፉ በዲጂታላይዜሽን መታገዙ ያመጣውን ከፍተኛ ለውጥ ተከትሎ የሀገራችን አጠቃላይ ቁጠባ ከነበረበት 2.6 ትሪሊዮን ብር አሁን ላይ ወደ 4 ትሪሊዮን ብር ገደማ መድረሱን ተናግረዋል።
አዲሱ የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ተግባራዊ ከሆነ ወዲህ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ባንክ ገበያውን ለማረጋጋት 2.7 ሚሊዮን ዶላር ለገበያ ማቅረቡንና የፋይናንስ ዘርፉ በአሁኑ ወቅት በትሪሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚንቀሳቀስበት ግዙፍ ሴክተር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
Repost from E-LMIS - ብቁ
🚀 ሜድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ.የተ.የግል ማህበር በሥራና ክህሎት ሚኒስትር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት E-LMIS በኩል ከታች በተዘረዘሩት የሥራ ዘርፎች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
👷 ክፍት የስራ መደቦች
🔹 HR/Admin Officer – 2 ቦታ
ትምህርት፡ BA Degree በManagement፣ Accounting ወይም ተዛማጅ ዘርፍ
የስራ ልምድ፡ 3–4 ዓመት
የቅጥር አይነት፡ ኮንትራት
🔹 Store Keeper – 2 ቦታ
ትምህርት፡ Degree በSupply Chain Management፣ Accounting፣ Management ወይም ተዛማጅ ዘርፍ
የስራ ልምድ፡ 3 ዓመት
የቅጥር አይነት፡ ኮንትራት
🔹 Excavator Operator III – 15 ቦታ
ትምህርት፡ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ
የስራ ልምድ፡ በExcavator Operator 8 ዓመት
የቅጥር አይነት፡ ቋሚ
🏫 ስለሆነም በዚህ የሥራ እድል መወዳደር ለምትፈልጉ በመጀመሪያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር /Labor ID/ ከያዛችሁ በዚህ https://forms.lmis.gov.et/midroc-construction-ethiopia/ በመግባት ትክክለኛ መረጃዎትን ሞልተው ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
📆 አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 29/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ማመልከት ይችላሉ።
☎️አስተያየት እና ጥቆማዎን በ9138 የሥልክ መስመር ይደውሉ።
+1
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ ለኢትዮጵያ ልጆች
*******
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላለፉት አምስት ዓመታት በፓርላማ ቆይታቸው ኢትዮጵያን ላገለገሉ የብልጽግና ፓርቲ አባላት እና የሌሎች ፓርቲ አባላትን በከፍተኛ አክብሮት አመስግነዋል።
በተለይም በዘንድሮ በሚመሠረተው መንግሥት አካል ለማይሆኑት የፓርላማ አባላት በሌላ የመንግሥት ኃላፊነት እንዲያገለግሉ የመንግሥታቸው ፍላጎት መሆኑን ጠቁመዋል።
“አንዳንዶቻችሁ በሚቀጥለው ምክር ቤት ከእኛ ጋር የማትቀጥሉ መሆኑን የዘንድሮ ምርጫ ያሳየ ቢሆንም ክቡር አቶ ደሳለኝ ጫኔ የመጨረሻ ያሉት ንግግር የመጨረሻ ባይሆን የመንግሥትት ምኞት መሆኑን እና ከምክር ቤት ውጪ እነዚህ አባላት ከመንግሥታችን ጋር በጋራ ሆነን ኢትዮጵያን እንድናገለግል በተከበሩ ምክር ቤት ፊት ጥሪ ላቀርብላችሁ እፈልጋለሁ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
“መንግሥትታችን እናንተን አካትቶ ኢትዮጵያን ማልማት ይፈልጋል። ኢትዮጵያ የጋራ ሀገራችን ናት። እኛም፣ እናንተም ልጆቿ በምክር ቤት ብቻ ሳይሆን በተለያየ ዘርፍ ተባብረን ኢትዮጵያን እንድናበለጽግ አብረን እንድንሠራ ጥሪ ላቀርብላችሁ እፈልጋለሁ” ብለዋል።
Repost from E-LMIS - ብቁ
🔊🗣️አስደሳች ዜና ለስራ ፈላጊዎች!
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከE-LMIS ጋር በመተባበር ከዚህ በታች በተገለጹት ክፍት የስራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ ፣ በዝውውር; እና በኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል።
🏫 ስለሆነም በዚህ የሥራ እድል መወዳደር ለምትፈልጉ በመጀመሪያ lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ የአገልግሎት መስጫ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር /Labor ID/ ከያዛችሁ በዚህ https://forms.lmis.gov.et/federal_-civil_services_three/ በመግባት ትክክለኛ መረጃዎትን ሞልተው ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
📆 አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 29/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 7ቀናት ማመልከት ይችላሉ።
☎️አስተያየት እና ጥቆማዎን በ9138 የሥልክ መስመር ይደውሉ።
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+8
በGermeny Development Bank/KFW እና AUDA-NEPAD አማካኝነት ተግባራዊ የሚደረገው የSIFA ፕሮጀክትን የህንጻ ግንባታ ክትትልና ግምገማ እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍ ለድረግ ያለመ በዶ/ር ማውሪዚዮ ፒሮኒ የተመራ ከፍተኛ ባለሙያ ቡድን የመስክ የስራ ጉብኝት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አከናወነ፡፡
የከፍተኛ ልኡክ ቡድኑን የተቀበሉትና የኮሌጁን አጠቃላይ ስራ ያስጎበኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ እንዳሉት የSIFA ፕሮጀክት በኮሌጃችን ተግባራዊ መሆኑ የአካባቢውን ብሎም የቀጠናውን ወጣቶች በICT የዳበረና እውቀት ያለው ትውልድ ለመገንባት ያስችለናል ብለዋል።ይህንንም ለማድረግ ሁሉም በርብርብ እየሠራ እንዳለ አብራርተዋል።
ከፍተኛ ልኡክ ቡድኑን የመሩት በAUDA-NEPAD የSIFA ፕሮጀክት ከፍተኛ የህንጻ አርክቴክት ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ማውሪዚዮ ፒሮኒ እንዳሉት የህንጻ ግንባታው ስራ በጥሩ ሁኔታ እና በጥራት መሰራቱን ያደነቁ ሲሆን ግንባታውን ለመጨረስ በቀረው 6 ወር ውሰጥ በጋራ መረባረብ ያሰፈልጋል ያሉ ሲሆን በእኛ በኩልም ስራውን ቶሎ ለመጨረስ ኃላፊነታችንን እነወጣለን ብለዋል።
ልኡክ ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኘውንና ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘውን የICT ልህቀት ማእከልን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን በኮሌጁ በነበራቸው ቆይታ እጅግ ደስተኛ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ሰኔ 27/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
