ru
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

Открыть в Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

Канал ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 13 331 подписчиков, занимая 1 756 место в категории Транспорт и 2 541 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 13 331 подписчиков.

Согласно последним данным от 16 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 90, а за последние 24 часа — 8, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 40.85%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 15.40% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 5 439 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 050 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 17.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 17 июня, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Транспорт.

13 323
Подписчики
+824 часа
+217 дней
+9030 день
Архив постов
የዎላይታ ሶዶ ከተማ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ሶዶ፣ የካቲት 4፣ 2017 (ኢ መ አ):- በደቡብ የኢትዮጵያ ክልል  በዎላይታ ዞን የሚገኘው የዎላይታ ሶዶ ከተማ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ  እየተሰራ ይገኛል ። የከተማ መንገዱ 12 ነጥብ 39 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን፣የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በሁለት ሎት ተከፍሎ እየተሰራ ይገኛል። ሎት 1 ከሌዊ እስከ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ(7.14) ኪሎ ሜትር ሲሆን ሎት 2 ከጦና አደባባይ እስከ አረካመውጫ መገንጠያ ድረስ (6.3) ኪ.ሜትር  የሚዘልቅ ነው። አሁን ላይ የአፈር ቆረጣና እና ሙሌት ፣የውሃ ቱቦ ቀበራ፣ የድጋፍ ግንብ እና አርማታ ፣የቱቦ ማምረት ስራ እና ቤዝኮርስ ስራዎች ተሰርተዋል። አጠቃላይ አፈፃፀሙ 15 በመቶ ደርሷል።  ግንባታውን ለማከናወን መንግስት (2,620,119,958.46 )ሁለት ቢሊዮን ስድስት መቶ ሃያ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስምንት ብር ከአርባ ስድስት ሳንቲም ፈሰስ ያደርጋል። ግንባታውን ተረክቦ እያከናወነ የሚገኘው አለማቀፉ ቻይና ፈርስት ሃይዌ ኢንጂነሪንግ  ኮ. ኤልቲዲ /CFHEC/ነው ። ግንባታው  ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ ማድረስ ተችሏል። በ2018 ዓ .ም ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል ። ጂ.ኤን ዋይ ምህንድስና አማካሪ ከደወል አማካሪ መሃንዲሶች ጋር በጣምራ በመሆን የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን እያከናወኑ ይገኛሉ። የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ ከዚህ ቀደም የነበረውን  የትራፊክ መጨናነቅን ከመቀነሱም ባለፈ የከተማዋን ሁለንተናዊ ዕድገት ያፋጥናል። መንገዱ የእግረኛ እና የመንገድ አካፋይን ጨምሮ በከተማ 34 እና 21.5 ሲሆን በገጠር ከተማ 13ነጥብ 6 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ ነው። ከተማዋ በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኝና የደቡብ ክልል የፖለቲካና አስተዳደር ማዕከል በመሆኗ የመንገዱ መገንባት ከፍተኛ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አለው ። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

Call for side event
Call for side event

ሀገር  አቀፉ  የመንገድ  ሴክተር  ጉባኤ  ምክክር   ተካሄደ ጎንደር ፣ የካቲት 1፣ 2017 (ኢመአ):- ሀገር  አቀፉ  የመንገድ  ሴክተር  ጉባኤ  ምክክር  ከፍተኛ   የፌደራል እና  የክልል  የሥራ ኃላፊዎች  እንዲሁም  የከተማ አስተዳደሮች  በተገኙበት  ተካሄዷል። በጉባኤው  ላይ የፌደራል  የክልሎች እና የከተማ  መስተዳድር   የመንገድ ኤጀንሲዎች  የ 2017  በጀት  ዓመት   የስድስት ወራት መደበኛና  ወቅታዊ  የመንገድ  ግንባታ  እና  ጥገና እቅድ  አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል። የመንገድ  ኤጀንሲዎቹ  በበጀት  አመቱ  ያከናወኑትን  አጠቃላይ  የመንገድ  ግንባታ  እና  ጥገና  አፈፃፀም  አስመልክቶም  ግምገማ  ተደርጓል። መድረኩ  በመላው  ሀገሪቱ  የዜጎችን   ፍላጎት  የሚመጥን  የመንገድ  ሽፍን  ለማሳደግ  መንግስት  በሰጠው ልዩ  ትኩረት  የመንገድ ልማት  ማዕቀፍን  በመተግበር  ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት  የሚያግዝ  መሆኑን የከተማና  መሰረተ ልማት ሚኒስቴር  ሚኒስትር  ክብርት ጫልቱ ሳኒ ገልፀዋል። አያይዘውም በመንገድ ዘርፋ የታየው ስኬት አመርቂ  ውጤት የታየበት በመሆኑ ለህብረተሰቡ  ተገቢውን  ምላሽ  ለመስጠት የዘርፉ  አስፈፃሚዎች  የጋራ  ቅንጅት   በመፍጠር  መሥራት ይገባቸዋል ብለዋል። በሀገሪቱ የተከሰቱ  የፀጥታና አለመረጋጋት ችግሮች ፣ የበጀት እና የግብአት እንዲሁም የማሽነሪ መለዋወጫ እጥረቶች የመንገድ ግንባታዎችን እና  ጥገናዎች ለማካሄድ ችግሮችን መፍጠራቸው ታውቋል። ይህንን ለመፍታት የመንገድ ፈንድ ገቢን ለማሳደግ እና በቀጣይ የመንገዶች ጥገና  ሽፋንን ለመጨመር  የሚያስችል ስትራቴጂክ እቅድ  ተይዞ እየተሰራ  እንደሚገኝ ተጠቁሟል። በአስር አመቱ መንገድ ልማት ዘርፍ  ፕሮግራም የተገኘውን ውጤት የበለጠ ለማሻሻል እና የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት  አስፈላጊው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል። ከዚህም ባሻገር በዘርፉ የተነሱ  ችግሮችን  ለመፍታትና  ደረጃ  በደረጃ  መፍትሄ ለማምጣት  የመንገድ ኤጀንሲዎች ፎረም ምስረታ ተከናውኗል፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የሀሚድ ድልድይ ተለዋጭ መንገድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ የወልድያ ሮቢት የመንገድ ክፍል የሆነው የሀሚድ ድልድይ ተለዋጭ መንገድ ተሰርቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። በድልድዩ ጉዳት የተፈጠረውን የትራ
የሀሚድ  ድልድይ  ተለዋጭ  መንገድ   አገልግሎት  መስጠት  ጀመረ የወልድያ  ሮቢት  የመንገድ   ክፍል የሆነው   የሀሚድ   ድልድይ  ተለዋጭ  መንገድ   ተሰርቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። በድልድዩ  ጉዳት   የተፈጠረውን   የትራንስፖርት  መስተጓጎል   ለመፍታት  በተደረገው  ከፍተኛ  ጥረት  የተለዋጭ  መንገዱ ለአነስተኛ እና  ለትላልቅ  መኪኖች አገልግሎት  እየሰጠ ይገኛል። ለድልድዩ ዘላቂ መፍትሄ  እስኪገኝ  ድረስ ድልድዩን  የሚጠቀሙ  ተሽከርካሪዎች በመጠባበቅ እንዲተላለፉ የኢትዮጵያ  መንገዶች አስተዳደር  ያሳስባል።

የሀሚድ ድልድይ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል የወልድያ ሮቢት የመንገድ ክፍል በሆነው የሀሚድ ድልድይ ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የተስተጓጎለውን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማስጀመር
የሀሚድ  ድልድይ  አገልግሎት እንዲሰጥ  ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል የወልድያ   ሮቢት   የመንገድ   ክፍል   በሆነው   የሀሚድ   ድልድይ  ላይ  ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የተስተጓጎለውን የትራንስፖርት  አገልግሎት  ለማስጀመር  እየተሰራ  ይገኛል። የሀሚድ  ወንዝ  የብረት ድልድይ  ላይ  ጉዳት  ያጋጠመው  ከተፈቀደው  በላይ  ትርፍ  ጭነት  በጫነ  ተሽከርካሪ  የተነሳ  ሲሆን   ይህም   የትራንስፖርት   መስተጓጎል  እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል። በድልድዩ  ጉዳት   የተፈጠረውን  የትራንስፖርት  መስተጓጎል   ለመፍታት    በጊዜያዊነት  የተለዋጭ  መንገድ   ተሰርቶ አነስተኛ  ተሽከርካሪዎች  እንዲሸጋገሩ  የተደረገ  ሲሆን   ትልልቅ  መኪኖች  እንዲያልፉ  ለማስቻል  ጥረቶች  ተጠናክረው  ቀጥለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት  ለድልድዩ   ዘላቂ  መፍትሄ   ለመስጠት  ይቻል  ዘንድ   በኢትዮጵያ  መንገዶች  አስተዳደር  በኩል  ከፍተኛ  ክትትል  እየተደረገ  ይገኛል። የድልድዩ   ተጠቃሚዎችም  መስሪያቤቱ   ድልድዩን  ጠግኖ  አገልግሎት  እስኪሰጥ  ድረስ  በትእግስት እንዲጠባበቁ  መልእክቱን  ያስተላልፋል፡፡

ከአዲስ  አበባ  የሚወጡ  4  የፍጥነት መንገዶች ለመገንባት ጥናት እየተደረገ ይገኛል ከአዲስ    አበባ   በተለያዩ   መስመሮች   የሚወጡ   4   አዳዲስ   የፍጥነት   መንገዶችን  ለመገንባት  የሚያስችል  ጥናት እየተደረገ  ይገኛል፡፡ ጥናቱ   እየተደረገ   የሚገኘው    ከአዲስ  አበባ ደሴ ፣ከአዲስ  አበባ  ጅማ ፣ከአዲስ  አበባ  ደብረማርቆስ  እና  ከአዲስ አበባ  ነቀምት    በሚዘልቁት   መንገዶች  ላይ  ነው፡፡ እነዚህ    የፍጥነት  መንገዶች   የሚገነቡበት   የጥራት  ደረጃ ፣ የሚኖራቸውም   አጠቃላይ የጎን  ስፋት  ከፍ  ያለ  እና  የሚገነቡበት  መልክአ  ምድር  አብዛኛውን   ተራራማ  ቦታዎችን  የሚሸፍን  በመሆኑ  ከፍተኛ  የሆነ   ወጪ እና   የቆረጣ   ስራዎችን  የሚጠይቁ  ናቸው፡፡ በጥናቱ   መሰረት   ፕሮጀክቶቹ   የሚኖራቸው   ርዝመት   በአማካይ   300  ኪሜ   ሲሆን   ግንባታቸውም   በተለያዩ  ምዕራፎች  እና  በተወሰነ   ኪሎሜትር ተከፋፍሎ የሚጀመር ይሆናል፡፡ በአሁኑ  ወቅት  የፕሮጀክቶቹ  የአዋጭነት፥ እንዲሁም  መሰረታዊ  የዲዛይንና  የዝግጅት ሥራ እየተከናወነ ሲሆን ለዝግጅት  ሥራው  የሚያስፈልጉ   የጥናት  ስራዎችንም  ለማጠናቀቅ  እየተሰራ ነው። አራቱን  የፍጥነት  መንገዶች  ለመገንባት የሚያስፈልገው   ወጪ  የሚሸፈነው  በመንግስትና   የግል   አጋርነት  ትብብር   ነው፡፡ ከፍጥነት  መንገዶቹ  መካከል  የአዲስ  ጅማ እና አዲስ ደብረ ማርቆስ ፕሮጀክቶች ለገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት የግል  አጋርነት  ቦርድ  የቀረቡ  ሲሆን  ቀሪዎቹም  በቅርቡ  ይቀርባሉ  ተብለው ይጠበቃል ። ፕሮጀክቶቹም   በገንዘብ  ሚኒስቴር  የመንግስት  የግል  አጋርነት  ትብብር  ቦርድ   ከጸደቁ  በኋላ  ወደ ቀጣይ ስራ ይገባሉ። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads