ru
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

Открыть в Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

Больше

📈 Аналитический обзор Telegram-канала ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

Канал ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 13 373 подписчиков, занимая 1 756 место в категории Транспорт и 2 532 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 13 373 подписчиков.

Согласно последним данным от 21 июня, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 131, а за последние 24 часа — 4, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 38.97%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 15.25% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 5 211 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 039 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 11.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 22 июня, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Транспорт.

13 375
Подписчики
+424 часа
+707 дней
+13130 день
Архив постов
Invitation for Bid Consultancy Service for Concept Design and Feasibility Study of Expressway Road Projects /International Competitive Bidding/

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ሥራ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል፡፡ የግንባታ ሥራውን ማስጀመሪያ ሥነሥርዓት ላይ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመሰገን ጥሩነህ፣ የትራንስፖርት ሚኒስተር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢነጂነር ሃብታሙ ተገኘ እንዲሁም የፌደራል የክልል የስራ ሃላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ ገጽታ * የውል ስምምነት ፡- መጋቢት 18 ቀን 2011 ዓ.ም * የሥራ ተቋራጭ ፡- አለማቀፉ የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ /CCCC/ China communication construction company * አማካሪ ድርጅት ፡- ቦቴክ ቦስፈረስ የተባለ የቱርክ አማካሪ ድርጅት ከስታዲያ ኢንጅነሪንግ ስራዎች ድርጅት ከተባለ አገር በቀል ንኡስ አማካሪ ጋር በጋራ በመሆን ያከናውኑታል /Botek Bosporus techni￾cal consulting in JV with Stadia Engineering Worksconsultant plc. * የግንባታ ወጪ ፡- 1,437,000,000 ብር * የግንባታውን ወጪ የሚሸፍነው፡- በኢትዮጵያ መንግስት ተሸፍኗል፡፡ * የግንባታው አይነት ፡- ዲዛይንና ግንባታ /ተቋራጭ ድርጅቱ ዲዛይና ግንባታን በጋራ አካቶ የሚሰራበት የኮንትራት ውል አይነት ነው/፡፡ * የድልድዩ አይነት ፡- የተንጠልጣይና የሳጥን ቅርፅ ያላቸውን ረጃጅም ድልድዮችን ዲዛይን በማዋሀድ በአዲስ የዲዛይን ጥበብ የሚገነባው ኤክስትራዶስድ extradosed የተባለውን አይነት ድልድይ ነው፡፡ * ርዝመት ፡- 380 ሜትር * የጎን ስፋት ፡- 43 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን በግራና በቀኝ በአንድ ግዜ 6 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የብስክሌት ተጠቃሚዎች መስመር በሁለቱም አቅጣጫ እንዲሁም 5 ሜትር የእግረኛ መሄጃን ያካተተ ነው ፡፡ * የድልድዩ ግንባታ ስራ፡- ከድልድዩ ግንባታ ጎን ለጎን ተያያዥ የኮንክሪት ስትራክቸር ስራዎችና፣ የተሽከርካሪ መወጣጫ /ramp/ ፣ የትራፊክ ምልክቶች፣ የድልድይ ላይ መብራቶች ስራም ያካተተ ነው ፡፡ * ለግንባታ የተሰጠው ጊዜ ፡- ሶስት አመት የኘሮጀክቱ ሁለንተናዊ ፋይዳ * በአሁኑ ወቅት ከአቅሙ በላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘውን ነባሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ ላይ ይደርስ የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ እና ጫና ያስቀራል፡፡ * ከባህርዳር ከተማ እድገት እና ውበት ጋር ያልተመጣጠነ የነበረውን እና ረጅም እድሜ ያስቆተረውን ድልድይ በመተካት ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚሄድ ደረጃውን የጠበቀ የመሠረተ ልማት ተጠቀሚ እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ ይወጣል፡፡ * አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ ከሀገራዊ ፋይዳውም አልፎ ከጎረቤት ሀገር ሱዳን ጋር የሚያገናኝ በመሆኑ የሁለቱን ሀገሮች የንግድና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ያስተሳስራል፡፡ * ለሀገሪቱ የገቢ ወጪ የንግድ እንቅስቃሴም የበኩሉን አስተዋጽዖ ያበረክታል። * ድልድዩን ለሚያቋርጡ እግረኞች የትራፊክ አደጋ ሳያሰጋቸው በተዘገጀላቸው 5 ሜትር ስፋት ባለው መሄጃ ላይ በመጠቀም ከስጋት ነጻ ያደርግላቸዋል፡፡ * ብስክሌት ለሚጠቀሙ የአካባው ነዋሪዎችም ሆኑ ቱሪስቶች ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። * በተጨማሪም በባህርዳር ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቅረፍ የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡ * ብዙ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ላላት ባህርዳር እና አካባቢዋ አዲሱ ድልድይ እራሱን የቻለ የቱሪስት መስህብ በመሆን አወንታዊ ሚናውን ይወጣል፡፡

የባህርዳር -ጢስ እሳት የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ዛሬ ተጀመረ፡፡ የመንገድ ግንባታውን ያስጀመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ናቸው፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመሰገን ጥሩነህ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢነጂነር ሃብታሙ ተገኘ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ እንዲሁም የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ጨምሮ ሌሎች የፌደራል የክልል የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ነበሩ። ጢስ እሳት በአማራ ክልል ከባህርዳር ከተማ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ታሪካዊ ከተማ ናት። ከተማዋ ምንም እንኳን ልዩ ልዩ ተፈጥሮዓዊ የቱሪስት መስህቦች እና ከፍተኛ የግብርና ምርቶች መገኛ ብትሆንም፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዘመናት በመንገድ መሰረተ ልማት ችግር ሲንገላቱ መቆየታቸዉ ሀቅ ነዉ፡፡ መንግስት ይህንን ችግር ከግንዛቤ በማስገባት እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የባህርዳር ጢስ እሳት የመንገድ ፕሮጀክትን በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ለመገንባት ዛሬ ስራ ጀምሯል፡፡ ይህ መንገድ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የአገር ዉስጥና የዉጭ ጎብኚዎችን ቁጥር በመጨመር ለአካባቢዉ ብሎም ለክልሉ ህዝብ ገቢ በማስገኝት ረገድ የላቀ ሚና ይጫዎታል፡፡ ይህን የመንገድ ፕሮጀክት አገር በቀሉ ሜልኮን ኮንስትራክሽን ከ767 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚያከናውን ሲሆን ሙሉ ወጪውም በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፍን ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በዚህ አካባቢ ጤፍ፤ በቆሎ እና ሌሎች የአዝዕርት ምርቶች የሚመረቱ ሲሆን፣ ይህ መንገድ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የአካባቢው አርሶ አደር ያመረተውን ምርት በአቅራቢያው ወደ ሚገኝ ገበያ ወይም የንግድ ማዕከል በማውጣት ካለ ምንም እንግልት ከምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡

የባህር ዳር - ዘማ ወንዝ -ፈለገብርሃን አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል፡፡ በሁለት ኮንትራት ተከፍሎ ግንባታው ሲካሄድ የቆየው የባህርዳር -ዜማወንዝ -ፈለገ ብርሃን 175 ኪ.ሜ አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ ነው ዛሬ የተመረቀው፡፡ ለመንገዱ ግንባታ ሙሉ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን ከ2.4 ቢሊየን ብር በላይ የግንባታ ወጪንም ጠይቋል፡፡ የዚህ መንገድ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነው የባህርዳር -ዜማወንዝ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ሲኖሃይድሮ በተባለ የቻይና አለም አቀፍ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ሲከናወን የቆየ ሲሆን፣ የምህንድስ የቁጥጥርና የማማከር ስራውን ሲያካሂድ የቆየው ደግሞ አገር በቀሉ ኔት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ነው፡፡ በተጨማሪም የዚህ መንገድ ቀጣይ ኮንትራት የሆነው የዜማ ወንዝ-ፈለገብርሃን የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ China Railway 7th Group በተባለ የቻይና አለም አቀፍ የስራ ተቋራጭ ድርጅት ሲከናወን የቆየ ሲሆን፣ አገር በቀሉ አይኮን ኢንጂነሪንግ ደግሞ የመንገዱን የምህንድስና ቁጥጥርና የማማከር ስራ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ የባህርዳር -ዜማ ወንዝ-ፈለገብርሃን መንገድ የቀድሞ ገፅታ ለትራንስፖርት አመቺ ያልነበረ በመሆኑ ተሽከርካሪዎች ለተደጋጋሚ ብልሽት ይዳረጉ ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም ከባህርዳር -ደብረማርቆስ -አዲስአበባ ለመድረስ 540 ኪ.ሜ መጓዝ ይጠይቅ ነበር፤ ይህ መንገድ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ይህን ርቀት በ80 ኪ.ሜ የሚያሳጥር በመሆኑ ከዚህ ቀደም በነዋሪዎችና በአሽከርካሪዎች ላይ ይደርስ የነበረውን እንግልት እና የትራንስፖርት ወጪ ከመቀነስ አንፃር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም የዚህ መንገድ ግንባታ መጠናቀቅ ከዚህ በፊት የነበረውን የትራንስፖርት ችግር በመቅረፍየ አካባቢው ነዋሪ በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ ፈለገው ቦታ የሚንቀሳቀስበትን ሁኔታ የሚያመቻች ከመሆኑም በተጨማሪ፣ የቀዬው አርሶ አደሮች ምርታቸውን ካለምንም ችግር በአፋጣኝ ወደ ማዕከላዊ እና የውጭ ገበያ በማውጣት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡ የዚህ ፕሮጅክት እውን መሆን ጠቀሜታና ደስታው ለአካባቢው እና ለክልሉ ብቻም ሳይሆን ለሀገራችን የገበያ መረጋጋት ጭምር እንድምታው ላቅ ያለ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር የአካባቢው ትንንሽ መንደሮች በከተማ ደረጃ እንዲስፋፉ ከማድረግ እንዲሁም የጤና፣ የትምህርት እና ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት እንዲስፋፉ ከማድረግ አኳያ የሚኖረው ሚናም ከፍተኛ ነው፡፡ በሞጣ ከተማ በተካሄደው የመንገድ ምረቃት መርሃግብር ላይ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመሰገን ጥሩነህ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢነጂነር ሃብታሙ ተገኘ መልዕክት አስተላልፈዋል እንዲሁም የፌደራል የክልል የስራ ሃላፊዎችና የሃይማኖት አባቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ነበሩ ።

እንኳን አደረሳችሁ መልካም አዲስ አመት 🌼🌼🌼
እንኳን አደረሳችሁ መልካም አዲስ አመት 🌼🌼🌼

እንኳን ለ2012 አዲስ አመት አደራሣችሁ መልዕክት የኢመባ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ አስተላልፈዋል ።

Gohatsion Dejen road

Invitation for Stakeholder discussion To Whom It May Concern
+1
Invitation for Stakeholder discussion To Whom It May Concern

Invitation for Stakeholder discussion To Whom It May Concern
+1
Invitation for Stakeholder discussion To Whom It May Concern