ru
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Открыть в Telegram

📈 Аналитический обзор Telegram-канала EEP Communication

Канал EEP Communication (@eepcommuication) языкового сегмента Амхарский является активным участником. Сейчас сообщество объединяет 15 696 подписчиков, занимая 8 017 место в категории Технологии и приложения и 2 152 место в регионе Эфиопия.

📊 Показатели аудитории и динамика

С момента создания невідомо проект демонстрирует стремительный рост, собрав аудиторию из 15 696 подписчиков.

Согласно последним данным от 31 августа, 2026, канал показывает стабильную активность. За последние 30 дней изменение числа участников составило 142, а за последние 24 часа — 2, при этом общий охват остаётся высоким.

  • Статус верификации: Не верифицирован
  • Уровень вовлечённости (ER): Средний показатель вовлечённости аудитории составляет 30.85%. В первые 24 часа после публикации контент обычно набирает 16.42% реакций от общего числа подписчиков.
  • Охват публикаций: В среднем каждый пост получает 4 842 просмотров. В течение первых суток публикация набирает 2 578 просмотров.
  • Реакции и взаимодействия: Аудитория активно поддерживает контент: среднее количество реакций на один пост — 10.

📝 Описание и контентная политика

Автор описывает ресурс как площадку для выражения субъективного мнения:
EEP Communication

Благодаря высокой частоте обновлений (последние данные получены 01 сентября, 2026) канал поддерживает актуальность и высокий уровень охвата публикаций. Аналитика показывает, что аудитория активно взаимодействует с контентом, что делает его важной точкой влияния в категории Технологии и приложения.

15 696
Подписчики
+224 часа
+237 дней
+14230 день
Архив постов
photo content
+7

ተቋሙ የኃይል ሽያጭ እና ስትራቴጂካዊ አጋርነትን የሚያጠናክሩ ሥምምነቶች ተፈራረመ ….…///…… የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከቻይናው ጂሲኤል ግሩፕ ሆልዲንግ ሊሚትድ ጋር የኃይል ሽያጭ እና የሀገሪቱን የኃይል ዘርፍ ለማጠናከር በሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ፡፡ ሥምምነቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እና የጂሲኤል ግሩፕ ሆልዲንግ ሊሚትድ ምክትል ፕሬዝዳንት ሹቢን ኒው እንዲሁም በኩባንያው የኢትዮጵያ ፒክ ግሮው ሆልዲንግ ሊሚትድ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ዮንግ ያንግ ተፈራርመዋል፡፡ የኃይል ሽያጭ ሥምምነቱ ጂሲኤል ግሩፕ ሆልዲንግ ሊሚትድ ከኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር በመተባበር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አካባቢ ለሚገነባው የዳታ ማይኒንግ ማዕከል ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን በሰነዱ ተመልክቷል፡፡  ሥምምነቱ ከኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ባለፈ በተለያዩ የኃይል ልማት ዘርፎች፣ በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ ግንባታ እና በአቅም ግንባታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል፡፡  ተቋማቱ በሀገሪቱ የኢነርጂ ዘርፍ ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ የኃይል ሥርዓት  ምርምር ኢንስቲትዩት ለመመስረት የሚያስችል መሆኑን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ሰነዱ ላይ ተጠቁሟል፡፡ ሥምምነቱ ኩባንያው በታዳሽ ኃይል ማመንጫ ላይ ያለውን የካበተ ልምድ በመጠቀም በሀገሪቱ  በፀሐይ እና በንፋስ የኃይል ልማት ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት ያስችላል፡፡ በተያያዘም በህዳሴ ግድብ አካባቢ የዳታ ማይኒንግ ለማልማት የሚያስችል ስምምነት በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና በጂሲኤል ግሩፕ ሆልዲንግ ሊሚትድ የኢትዮጵያ ፒክ ግሮው ሆልዲንግ ሊሚትድ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ዮንግ ያንግ ተፈርሟል፡፡ በሥምምነቱ ላይ የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቦርድ ሰብሳቢ አብርሃም በላይ (ዶ/ር)  ጨምሮ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሁም የጂሲኤል ግሩፕ ሆልዲንግ ሊሚትድ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                      💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+8

ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus Disease) ….///…. ሠላም ውድ የገጻችን ተከታታዮች እንደምን ሰንብታችኋል፡፡ ከሰሞኑ በጅንካ አካባቢ የተወሰኑ ሰዎችን ያጠቃ በቫይረስ የሚመጣ አደገኛ ወረርሽኝ የተከሰተ ሲሆን መንስዔው የማርበርግ ቫይረስ መሆኑን ተረጋግጧል። እኛም የተቋሙ ሠራተኛ ሥለ ቫይረሱ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ ከተቋሙ የጤና አገልግሎት ቢሮ ያገኘነውን መረጃ ለአንባቢያን በሚመች መልኩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፤ መልካም ንባብ! የማርበርግ ቫይረስ እንዴት ይተላለፋል? የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት የሚጀምረው በቫይረሱ ከተያዙ የሌሊት ወፎች እና አካባቢያቸው ወደ ሰው ሲተላለፍ ነው። በሌሊት ወፍ ሽንት፣ ኩስ እና ምራቅ የተበከሉ ነገሮችም ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ቫይረሱ አንዴ ሰው ጋር ከደረሰ በኋላ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል። ቫይረሱ የሚዛመተው ከታመመ ሰው ደም እና የሰውነት ፈሳሽ (ትውከት፣ ሰገራ፣ ሽንት፣ ምራቅ፣ ላብ፣ የጡት ወተት፣ የብልት ፈሳሽ ወዘተ) ጋር በቀጥታ ንክኪ ነው። በቫይረሱ የተያዘ ሰው የተጠቀመባቸውን መርፌ፣ ቁሳቁሶች፣ የተነካኩ ልብሶች ወዘተ ቫይረሱን ያስተላልፋሉ። በግብረ ስጋ ግንኙነትም ይተላለፋል። አስከሬንም መንካት ቫይረሱን ያስተላልፋል። የማርበርግ ቫይረስ ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው? ቫይረሱ ወደሰውነታችን ከገባ በኋላ የሰውነት የበሽታ ተከላካይ ህዋሶችን በማጥቃት በፍጥነት ይራባል፣ ይሰራጫል። የማርበርግ ቫይረስ ህመም የመጀመሪያ ምልክቶች እንደሌሎች ቫይረሶች ሁሉ ጉንፋን መሰል እንደ ከፍተኛ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ጉሮሮ መቁሰል፣ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም እና ድካም ናቸው።እነዚህ ምልክቶች ከታዩ ከጥቂት ቀናት በኋላ ጠንከር ያለ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ እና የሆድ ህመም የመሳሰሉ የጨጓራና አንጀት ህመም ምልክቶች ያሳያሉ። በመቀጠል በሽታው እየገፋ ከባድ ምልክቶች ይመጣሉ። በቆዳ ላይ፣ አፍና አፍንጫ ወይም የውስጥ የአካል ክፍል ላይ ደም መፍሰስ ያመጣል። ህመሙ እየጸና ሲሄድ የደም ግፊት ከልክ በታች መቀነስ፣ የጉበት፣ ኩላሊት እና ሌሎችም የሰውነት ክፍሎቻችን ይጎዳሉ። ሲብስ የብዝሃ-አካል መድካም ያመጣል። ከቫይረሱ የተረፉ ሰዎች ሙሉ ለሙሉ እስኪያገግሙ ድካም፣ ቁርጥማት እና የስነ ልቦና ጫና ሊሰማቸው ይችላሉ። የማርበርግ ቫይረስ ምርመራዎች የቫይረስ ህመሙን ለማረጋገጥ የማረጋገጫ ምርመራ ያስፈልጋል - የቫይረሱን ዘረመል የሚለዩ ፕ ሲ አር ሞለኩዩላር ምርመራዎች. የታካሚ ናሙናዎች እጅግ በጣም አደገኛ ስለሆኑ እነዚህ ምርመራዎች የሚከናወኑት በብሔራዊ የባዮሴፍቲ ፕሮቶኮሎች መሠረት በልዩ ላቦራቶሪ ማእከሎች ውስጥ ብቻ ነው። ማርበርግ ህክምና አለው? ህክምናው በአብዛኛው የሚያካትተው የሰውነት ፈሳሽ በግሉኮስ መተካት፣ በባለሙያ ክትትል ማድረግ እና ተጓዳኝ ችግሮችን ማከም ላይ ያተኩራል። እንዳስፈላጊነቱ የትኩሳት ማብረጃ እና የህመም ማስታገሻ መስጠት ይገባል። በጣም ደም መፍሰስ ላጋጠማቸው የደም ልገሳ ሊፈልጉ ይችላሉ። ከእነዚህ የህክምና ድጋፎች ባሻገር የሚሰጡ የጸረ-ቫይረስ ህክምናዎች የሉም። እስካሁን ለማርበርግ የተረጋገጠ እና ፍቃድ ያገኘ ጸረ-ቫይረስ መድሃኒት የለም። ማርበርግ ክትባትም አልተገኘለትም። በምርምር ደረጃ ያሉ ጥቂት እጩ የማርበርግ ክትባቶች ጥናት እየተሰራባቸው እና እየበለጸጉ እንደሚገኝ የሚጠቅሱ መረጃዎች አሉ። የማርበርግ ቫይረስ መከላከል መንገዶች በሽታው እንዳይዛመት ዋና መከላከያ መንገዱ በቫይረሱ የተጠረጠረን ሰው መለየት ነው። በበሽታው ከተያዙ ግለሰብ የሰውነት ፈሳሾች ጋር ንክኪን ማስወገድ ይገባል። የታመመን ሰው በቤት ለማከም ከመሞከር ይልቅ ወዲያዉኑ ወደጤና ተቋም ሄዶ እንዲታከም ማድረግ የተሻለ ነው። እያንዳንዱ ሰው እጁን በአልኮል ወይም በሳሙና በደንብ በመታጠብ ንጽህና መጠበቅ አለበት። ከታማሚ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን አልባሳት፣ እቃዎችና እና ምንጣፎችን በክሎሪን በረኪና ዘፍዝፎ ማጽዳት ይገባል። በጤና ተቋማትም ከመደበኛ ጥንቃቄዎች ባሻገር የኢንፌክሽን መከላከያ እርምጃዎች ካልተተገበሩ የጤና ባለሙያዎች ለከፍተኛ አደጋ ይጋለጣሉ። የተሳለጠ የቅድመ ልየታ ስርአት መዘርጋት ይፈልጋል። ከጓንት እና ማስክ በተጨማሪ አይን እና ፊት መከላከያ ማድረግ ያስፈልጋል። የተለያዩ ኤሮሶል ብናኞችን የሚፈጥሩ የህክምና ፕሮሲጀሮች ሲሰሩ የአየር ወለድ ጥንቃቄዎች (ለአብነትም N95 ማስክ) መተግበር አለባቸው። የመርፌ እና ሌሎች ቆሻሻ አወጋገድም ጥንቃቄ ይፈልጋል። በማህበረሰብ ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ የቀብር ሥነ ሥርዓቶች መተግበር አለባቸው። በበሽታው ምክንያት የሞተ ሰውን አስከሬን አለመንካት። በባለሙያ በሚገባ በአስከሬን መጠቅለያ እንዲሸፈን በማድረግ ወዲያውኑ በባለሙያ መቅበር ይመከራል። የማርበርግ ቫይረስ ምን ያህል አሳሳቢ ነው? ማርበርግ ቫይረስ ገዳይነቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ሲወዳደር በጣም ከፍተኛ ቢሆንም ቅሉ በጠንካራ የመከላከል እርምጃዎች መቆጣጠር የሚቻል ህመም ነው። የሚተላለፈው ከሰውነት ፈሳሾች ጋር በቅርበት በመነካካት እንጂ በገበያ፣ በአውቶብስ ወይም በመንገድ ላይ በቅጽበታዊ አልፎ ሂያጅ ግንኙነት አይደለም። አሁናዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ማርበርግ እንደኮሮና ወይም ጉንፋን በቀጥታ አየር ወለድ ተላላፊ አይደለም። የማርበርግ ተዛማችነት (transmission rate, Ro) መጠነኛ ነው። ለማነጻጸር ያህል በቅርቡ ከነበረው ኮቪድ ቫይረስ ጋር እንኳ ብናወዳድረው የኮቪድ የመዛመት / የስርጭት ምጣኔው ከሁለት እስከ ሶስት እጥፍ ከማርበርግ ይበልጣል። ይህ ማለት አንድ በማርበርግ የተያዘ ሰው በአማካኝ ሌሎች ስንት ሰዎችን ሊበክል ይችላል ተብሎ ሲሰላ ትንሽ ነው ማለት ነው። ሌላው የቫይረሱ ጥሩ ጎኑ ደግሞ አንድ በማርበርግ የተያዘ ሰው ቶሎ አስተላላፊ አይሆንም። ኡደቱ ቀርፋፋ ነው።ማጠቃለያ መልእክት ሁለም የተቋሙ ሰራተኞች እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸው ከዚህ አስከፊ በሸታ እንድንጠብቅ ፤አስፈላጊ ዉን የመከላከያ እርምጃ እንዲወስድ እንዲሁም የበሽታው ምልክት ሲታይ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋማት መሄዱ ያስፈልጋል ። በሀይል ማመንጫ ጣቢያ የሚገኙ ጤና ባለሙያዎች አስፈላጊ ጥንቃቄ በማድረግ ስለበሽታው ምንነት ግንዛቤ እንዲሰጡ በተጨማሪም ከበሽታው ጋር ተመሳሳይ ምልክት ሲኖሩ በፍጥነት ወደ ሚመለከተው ጤና ተቋም እንድትልኩ እናሳስባለን ። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም

በጣቢያው የሚከናወነው የማስፋፊያ ሥራ አዲስ ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ ኃይል ለማቅረብ ይረዳል ‎…......///…...... ‌‎በጎዴ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እየተከናወነ የሚገኘው የማስፋፊያ ሥራ በኢትዮጵያ  መንግሥት እና በዳንጎቴ ግሩፕ አማካኝነት ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ እንደሚረዳ የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ። ‎ ‎ሥራ አስኪያጁ አቶ ጌዲዮን አበራ እንደገለፁት በማከፋፈያ ጣቢያው እየተከናወነ የሚገኘው የማስፋፊያ ሥራ ተጨማሪ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ለማግኘት የሚረዳ ነው። ‎ ‎የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የማስፋፊያ ሥራ ሲጠናቀቅ በአካባቢው ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ  ኤሌክትሪክ እንደሚያቀርብ ነው የተናገሩት።  ‎ ‎በጣቢያው ተጨማሪ 25 ሜጋ ቮልት አምፒር የመጫን አቅም ያለው ትራንፎርመር ለማስቀመጥ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም ነው የጠቀሱት። ‎ ‎ጣቢያው ከራይቱ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ኃይል ተቀብሎ በ132 ኪሎ ቮልት ለቀብሪደሃር እንዲሁም በ33 ኪሎ ቮልት ለጎዴ፣ ሀዳዋይ እና  አዳዲሌይ ከተሞች እና በዙሪያው ለሚገኙ አካባቢዎች ኃይል እያቀረበ ይገኛል። ‎ ‎የማስፋፊያ ግንባታው በሪጅኑ አቅም መከናወኑን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ ይህም አዳዲስ መሐንዲሶች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ልምድና የዕውቀት ሽግግር እንዲያገኙ መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን አብራርተዋል። ‎ ‎በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው እየተከናወነ የሚገኘው የማስፋፊያ ሥራ ሲጠናቀቅ የጎዴ ከተማን የኢንቨስትመንት ፍሰት ከማሳደጉም ባሻገር ለኤሌክትሪክ ፍላጎት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል። ‎ ‎እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያውን የማስፋፊያ ሥራ በአንድ ወር ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ ነው።                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                      💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+3

#vacancy የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ......///...... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሾፌር-1ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማ
+1
#vacancy የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ......///...... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሾፌር-1ኛ የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም የውጪ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት ስማችሁ ከላይ የተገለጸው አመልካቾች በሙሉ ህዳር 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው በዋናው መ/ቤት የመሰብሰብያ አዳራሽ የጽሁፍ ፈተና የሚሰጥ በመሆኑ ለፈተና እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም

በጣቢያው የሚከናወነው የማስፋፊያ ሥራ አዲስ ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ ኃይል ለማቅረብ ይረዳል ‎…......///…...... ‌‎በጎዴ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እየተከናወነ የሚገኘው የማስፋፊያ ሥራ በኢትዮጵያ  መንግሥት እና በዳንጎቴ ግሩፕ አማካኝነት ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ እንደሚረዳ የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ። ‎ ‎ሥራ አስኪያጁ አቶ ጌዲዮን አበራ እንደገለፁት በማከፋፈያ ጣቢያው እየተከናወነ የሚገኘው የማስፋፊያ ሥራ ተጨማሪ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ኃይል ለማግኘት የሚረዳ ነው። ‎ ‎የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው የማስፋፊያ ሥራ ሲጠናቀቅ በአካባቢው ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ  ኤሌክትሪክ እንደሚያቀርብ ነው የተናገሩት።  ‎ ‎በጣቢያው ተጨማሪ 25 ሜጋ ቮልት አምፒር የመጫን አቅም ያለው ትራንፎርመር ለማስቀመጥ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውንም ነው የጠቀሱት። ‎ ‎ጣቢያው ከራይቱ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ኃይል ተቀብሎ በ132 ኪሎ ቮልት ለቀብሪደሃር እንዲሁም በ33 ኪሎ ቮልት ለጎዴ፣ ሀዳዋይ እና  አዳዲሌይ ከተሞች እና በዙሪያው ለሚገኙ አካባቢዎች ኃይል እያቀረበ ይገኛል። ‎ ‎የማስፋፊያ ግንባታው በሪጅኑ አቅም መከናወኑን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ ይህም አዳዲስ መሐንዲሶች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች ልምድና የዕውቀት ሽግግር እንዲያገኙ መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን አብራርተዋል። ‎ ‎በኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው እየተከናወነ የሚገኘው የማስፋፊያ ሥራ ሲጠናቀቅ የጎዴ ከተማን የኢንቨስትመንት ፍሰት ከማሳደጉም ባሻገር ለኤሌክትሪክ ፍላጎት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል። ‎ ‎እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያውን የማስፋፊያ ሥራ በአንድ ወር ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ ነው።                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                      💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+7

ተቋማቱ የጡረተኞችን ጥያቄ ለመመለስ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ገለፁ ….....///....... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋማቱ በጡረታ የተገለሉ የቀድሞ ሠራተኞቻቸውን ጥያቄ ለመመለስ በትብብር እየሰሩ መሆኑን የሁለቱ ተቋማት ሥራ አስፈጻሚዎች ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቀድሞ ሠራተኞች የተመሠረተው ‎የመብራት ኃይል የጡረተኛ ሠራተኞች ማህበር ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል። ‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በጉባዔው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የማህበሩ አባላት በእድሜ ገደብ በጡረታ ቢገለሉም ለተቋማቱ እዚህ ደረጃ መድረስ ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈል ጭምር ረጅም ዘመን ያገለገሉ በመሆናቸው መከበር እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ተቋማቱን አገልግለው ጡረታ የወጡ ሠራተኞች መደገፍና መታገዝ አለባቸው በሚል መንፈስ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ ፋይናንስ የሚፈልጉ ሥራዎችን የሚያከናውኑ መሆናቸውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በጡረተኞቹ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ በትብብር እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ጡረተኞች እውቀትና ልምዳቸውን በማካፈል ተቋማቱን ለማሳደግ በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ ያቀረቡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጡረተኞችን ለመደገፍና ተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በበኩላቸው ጡረተኞቹ ለሁለቱ ተቋማቱ ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ተቋማቱን ለማሳደግና ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ በመሆኑ ጡረተኞች ይሄን በማገዝ በኩል ሚናቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል፡፡ በጡረተኞች የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ሁለቱ ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን የተናገሩት ኢንጂነር ጌቱ ለትውልድ የሚሻገር አሻራ ጥሎ ለማለፍ ከጡረተኞች ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                      💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+5

ማህበሩ የአባላቱን ጥቅም በዘላቂነት ለማስጠበቅ በትብብር እየሰራ ነው ‎......///....... ‎የመብራት ኃይል ጡረተኞች ማህበር የአባላቱን ጥቅም በዘላቂነት ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ በትብብር እየሰራ መሆኑን የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ተሾመ መርዕድ ገለጹ። ‎ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቀድሞ ሠራተኞች የተመሠረተው ‎የመብራት ኃይል የጡረተኛ ሠራተኞች ማህበር ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል። ‎ ‎በጉባዔው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ተሾመ መርዕድ ‌‎እንደ አቻ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጡረታ የወጡ የቀድሞ የሁለቱ ተቋማት ሠራተኞችን የሚወክል ማህበር ባለመኖሩ እርስ በእርስ ለመገናኘት እንዲሁም ጡረተኞቹ ከድርጅቶቹ ማግኘት የሚገባቸውን ድጋፍ ለማግኘትና አብሮ ለመስራት ክፍተት ተፈጥሮ መቆየቱን አስታውሰዋል። የመብራት ኃይል ጡረተኞች ማህበር በጡረተኛ ሠራተኞች ላይ የሚስተዋለውን‎ ችግር ለመቅረፍ እና ተበታትኖ የሚገኘውን የቀድሞ ሠራተኛ በማሰባሰብ ለመብቱና ለጥቅሙ እንዲታገል እንዲሁም እርስ በእርሱ እንዲረዳዳ ለማድረግ መመስረቱን ጠቅሰዋል። አባላቱ ከወጣትነት ጊዜያቸው ጀምሮ እወቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ልምዳቸውን ሳይቆጥቡ በማገልገል ለሀገርና ለማህበረሰቡ እድገት የጀርባ አጥንት የሆኑ ሁለቱ ድርጅቶችን አሁን ላሉበት ደረጃ ማድረሳቸውን አብራርተዋል። ‎ማህበሩ አንድ የተሟላ የጡረተኞች ማዕከል መገንባት የሚያስችል ፕሮጀክት በመንደፍ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሉን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆኑን የገለጹት አቶ ተሾመ ነጻ የህክምናና መብራት ጨምሮ ሌሎች በአባላቱ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለማስመለስ ከሁለቱ ተቋማትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጎፋ በሚገኘው የድርጅቱ መ/ቤት ለማህበሩ ቢሮና ቁሳቁስ ማመቻቸቱም ተናግረዋል። ‎የማህበሩን ሂሳብ ለአሰራርና ለቁጥር አመች በሆነ መንገድ ለመስራት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ለአቢሲኒያ ባንክ በጻፈው ደብዳቤ የማህበሩ አካውንት ተከፍቶ በሥራ ላይ እንደሚገኝም አብራርተዋል። በዕለቱ የተሻሻለው የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብን ጨምሮ የፋይናንስና የኦዲት ሪፖርት፣ የፋይናንስና የውስጥ ኦዲት ሪፖርት እንዲሁም የወርኃዊ ክፍያ ተመን እና የሥራ አስፈጻሚ አባላት የትራንስፖርት አበል ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                      💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+9

photo content

“የኃይል መሰረተ ልማት ደህንነትን ማስጠበቅ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ ነው” ‎ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ………///……… የኃይል መሰረተ ልማት ደህንነትን ማስጠበቅ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ በመሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ገለፁ፡፡ ‎በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ለተመለመሉ የኃይል መሰረተ ልማት ጥበቃ አባላት ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና የተቋሙን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጨምሮ የመከላከያ ሚኒስቴር እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተጠናቋል፡፡ ‎ በሥልጠናው ማጠናቀቂያው ላይ ለሠልጣኝ አባላቱ የሥራ መመሪያ የሰጡት ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርስ ጉዳት የኦፕሬሽን ሥራዎችን በማስተጓጎል በሀገር ሁለንተናዊ ዕድገትና ሠላም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ተናግረዋል፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ሆነው ከ30 ዓመት በላይ ሀገርን ያገለገሉት ሠልጣኝ አባላቱ ወደ ተቋሙ መምጣት የኃይል መሰረተ ልማትን ደህንነት ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ተጨማሪ ጉልበት የሚሰጥ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ ከፍተኛ የኃይል መሰረተ ልማት ሥርቆት የሚስተዋሉባቸው አካባቢዎች በዘርፍ ተለይተው የከፍተኛ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችንና ማስተላለፊያ መስመሮች ጥበቃ መጀመሩን ጠቁመዋል። የኃይል መሰረተ ልማት ደህንነትን ማስጠበቅ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ በመሆኑ ሠልጣኝ አባላቱ በሕብረተሰቡና በተቋሙ መካከል ድልድይ ሆነው በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል። ለሥራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ ለማሟላት ጥረት እንደሚደረግ የተናገሩት ኢንጂነር አሸብር ተቋሙ በኃይል መሰረተ ልማት ደህንነት ጥበቃ ላይ ለውጥ ለማምጣት የመከላከያ ሚኒስቴር እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን ጨምሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የመከላከያ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች በበኩላቸው ሠልጣኝ አባላቱ በተመደቡባቸው ሪጅኖች በኃይል መሰረተ ልማት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችን በመለየት፣ ትክክለኛ መረጃ በማሰባሰብና ሕብረተሰቡንና መንግስታዊ መዋቅሩን በማሳተፍ በዕቅድ ላይ ተመስርቶ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን ማከናወን ይገባል ብለዋል። የኃይል መሰረተ ልማት ደህንነትን ማስጠበቅ የተቋማቱ ሕገ-መንግሥታዊ ኃላፊነት መሆኑን የጠቆሙት የሥራ ኃላፊዎቹ በቀጣይም በመረጃ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታና መሰል ሥራዎች ከተቋሙ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በተቋሙ፣ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና በመከላከያ ሚኒስቴር ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በተቋሙ ርዕይና ተልዕኮ፣ አሰራርና አደረጃጀት እና በቁልፍ ተቋማት መሰረተ ልማት ጥበቃ እንዲሁም በደህንነት ስጋት የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ነበር።                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                      💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም

photo content
+1

photo content
+9

በከርሰምድር እንፋሎት ኃይል ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት ይገባል .......///....... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የከርሰምድር እንፋሎት ኃይልን በአግባቡ ለመጠቀም በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት እንደሚገባ በተቋሙ የጂኦተርማል ልማት ቢሮ ገለፀ፡፡ ተቋሙ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተከፈተው 4ኛው ዓመታዊ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ (MINTEX Ethiopia 2025) ላይ በከርሰምድር እንፋሎት የኃይል ልማት ላይ እያከናወናቸው የሚገኙ ሥራዎችን እና የዘርፉን የወደፊት ዕቅዶች የሚያሳዩ መረጃዎችን ለዕይታ አቅርቧል። የኤግዚቢሽኑ አስጎብኚ የጂኦተርማል ከፍተኛ ባለሙያው አቶ ሰለሞን ከበደ እንደተናገሩት ተቋሙ የኃይል ስብጥርን ለማሳደግና የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት የሚያስችሉ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ በከርሰምድር እንፋሎት ሀብት በተፈጥሮ የታደለች መሆኗን የጠቀሱት ባለሙያው ይሁን እንጂ ዘርፉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል የሚፈልግ በመሆኑ እምቅ ሀብቱን በአግባቡ መጠቀም እንዳልተቻለ ገልፀዋል፡፡ በዚህም ተቋሙ የከርሰምድር እንፋሎት ኃይል ግንባታ ዘርፍን ለማሳደግ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት ላይ ጠንክሮ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡ እንደ አቶ ሰለሞን ገለፃ ኤክስፖው የከርሰምድር እንፋሎት በኃይል ልማት ዘርፉ ላይ ያለውን ድርሻ እና ፋይዳ ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ ይረዳል፡፡ በማዕድን ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት እና በማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በጋራ የተዘጋጀው 4ኛው ዓመታዊ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ እስከ ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለጎብኝዎች ክፍት መደረጉም ታውቋል። ኤክስፖውን የተቋሙ  ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ጎብኝተውታል።                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                      💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም