es
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

Ir al canal en Telegram

EEP Communication

Mostrar más

📈 Análisis del canal de Telegram EEP Communication

El canal EEP Communication (@eepcommuication) en el segmento lingüístico de Amárico es un actor destacado. Actualmente la comunidad reúne a 15 555 suscriptores, ocupando la posición 8 397 en la categoría Tecnologías y Aplicaciones y el puesto 2 165 en la región Etiopía.

📊 Métricas de audiencia y dinámica

Desde su creación el невідомо, el proyecto ha mostrado un crecimiento acelerado, reuniendo a 15 555 suscriptores.

Según los últimos datos del 21 junio, 2026, el canal mantiene una actividad estable. En los últimos 30 días la variación de miembros fue de 10, y en las últimas 24 horas de 1, conservando un alto alcance.

  • Estado de verificación: No verificado
  • Tasa de interacción (ER): El promedio de interacción de la audiencia es 25.74%. Durante las primeras 24 horas tras publicar, el contenido suele obtener 14.94% de reacciones respecto al total de suscriptores.
  • Alcance de las publicaciones: Cada publicación recibe en promedio 4 003 visualizaciones. En el primer día suele acumular 2 323 visualizaciones.
  • Reacciones e interacción: La audiencia responde de forma activa: el promedio de reacciones por publicación es 9.

📝 Descripción y política de contenido

El autor describe el recurso como un espacio para expresar opiniones subjetivas:
EEP Communication

Gracias a la alta frecuencia de actualizaciones (últimos datos recibidos el 22 junio, 2026), el canal mantiene la vigencia y un amplio alcance. La analítica demuestra que la audiencia interactúa activamente con el contenido, lo que lo convierte en un punto de referencia dentro de la categoría Tecnologías y Aplicaciones.

15 555
Suscriptores
+124 horas
+87 días
+1030 días
Archivo de publicaciones
photo content
+5

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዐባይ ልጆችን በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስብ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው -ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ …..///…… የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የታላቁ የኢትዮጵያ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዐባይ ልጆችን በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስብ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው -ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ …..///…… የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃትን አስመልክቶ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ኢትዮጵያውያን ያላቸውን የማደግ መሻት በላባቸው፣ በእንባቸው፣ በደማቸው እና በክብራቸው ያሳኩበት ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው ብለዋል። ህዳሴ ግድብ የዐባይ ልጆችን አንድ የሚያደርግ የኢትዮጵያውያን የፅናት ሽልማት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ግድቡ የኢትዮጵያ የቀጣይ ጊዜ ታላላቅ ስኬቶች ጅማሮ ነው ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመላ ኢትዮጵያውያን የላብ፣ የደም፣ የእንባ ጠብታ ድምር ውጤት ነው! 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethio
+2
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመላ ኢትዮጵያውያን የላብ፣ የደም፣ የእንባ ጠብታ ድምር ውጤት ነው! 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት እየተካሄደ ነው ….///…. ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ኃይል ማመንጫ ግድብ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት በይፋ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የአሁንና የቀድሞ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር መሀመድ ዓሊ የሱፍ፣ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህን ጨምሮ ሌሎችም የሀገራት መሪዎች እና ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ ቀጣናዊ ፣ አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የክብር እንግዶቹ የግድቡን የተለያዩ ክፍሎች እና የኃይል ማመንጫ ቤቶቹን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ተርባይኖቹንም በይፋ ሥራ አስጀምረዋል። በፕሮጀክቱ ስፍራ የተገነባውን ሀውልትም መርቀዋል። እኛም የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱን በመከታተል መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡ ላለፉት 14 ዓመታት በግንባታ ላይ የቆየው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በ13 ተርባይኖች 5 ሺ 150 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አለው፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

photo content
+8

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሰለ ግድብ ምርቃት ድባብ በከፊል 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመቻል ትዕምርት ነው ….///…. ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ልጆች ጥሪት፣ ላብ፣ ዕውቀት እና ደም የተገነባ የመቻል ትዕምርት መሆኑን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡ አገልግሎቱ የግድቡን ምርቃት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ እንደገለፀው የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ ለምርቃት መብቃቱ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን በፍትሐዊነት በመጠቀም የታላቁ ግድብ ባለቤት እንጂ የወንዙ ባለቤት ብቻ አለመሆኗን ዐቢይ ማሳያ ነው፡፡ ህዳሴ የኢትዮጵያ የተሰናሰለ ብዝኃነት አቅም የታየበት፣ በየክፍለ ዘመኑ የዓለምን ታሪክና ፖለቲካ የሚቀይር ተምሳሌታዊ ጥረትና ድል ከኢትዮጵያ እንደሚመነጭ ያስመሰከረ ነውም ብሏል፡፡ ኢትዮጵያውያን ህልማቸዉን ከማሳካት የሚያስቆማቸዉ አንዳች ምድራዊ ኃይል እንደሌለ በግድቡ አሳይተዋል ያለው አገልግሎቱ የውኃ ፍትኃዊ አጠቃቀምን “ከህዳሴ ግድብ በፊት እና በኋላ፣ የአፍሪካ ፖለቲካ ከህዳሴ ግድብ በፊት እና በኋላ፣ ዓለምአቀፍ ዲፕሎማሲ ከህዳሴ ግድብ በፊት እና በኋላ” ብሎ መክፈል የሚችል ታላቅ ድል የተመዘገበበት መሆኑንም አብራርቷል፡፡ ህዳሴ የኢትዮጵያን የመልማት አቅም እና የአፍሪካዊያን ራስን የመቻል ብስራት እንዲሁም የታዳሽ ኃይል በማመንጨት በካይ የኃይል ምንጮችን የሚያስቀር በኢትዮጵያውያን የጋራ ጥረት የተሳካ ልዩ ፕሮጀክት መሆኑንም ገልጿል፡፡ ግድቡ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በትነት ይባክን የነበረዉን ውኃ በመቆጣጠር እና ዓመቱን ሙሉ ከድንገተኛ ጎርፍ የፀዳ የተመጠነ ውኃ እንዲያገኙና ግድቦቻቸዉ በደለል እንዳይሞሉ የሚያደርግ መሆኑንም አመልክቷል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

ስንተባበር እንጠነክራን! በአንድ ልብ አስበን አንድ ቃል ስንናገር እንደመጣለን! በጋራ ስንሰራ ሀገር እንለውጣለን! ይህ ዛሬ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያሳየነው እውነታ ነው። ከነበርንበት አንሰራርተናል። በአንድነት ጸንተን የጀመርነውን ፈጽመናል። የዚህ ታሪክ ሰሪ ትውልድ አካል ከመሆን በላይ የሚያኮራ ምን ነገር ይኖር ይሆን! የግድቡን ግንባታና ይህን ግንባታ በላይነት የመራውን ተቋም በኃላፊነት መምራት በተገኘው ውጤት እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። ስሜቴ በቃላት ከምገልፀው በላይ ነው። ለተቋማችን ሠራተኞች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የሥራ አመራር ቦርድ እና ለመላው ኢተረዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ! አሸብር ባልቻ(ኢንጂነር) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

የውስጣዊ ፍስሃ፥ ደስታ፣ እንባ–ሲቃ፣ ሳቅ፣ ብርሃን የዘመናት የቁጭት ስሜት፣ የስኬት ተድላ፤ አሁናዊ የሚሰማኝ ስሜት!! በቅድሚያ፥ የሀገሬ ኢትዮጵያ የኔ ትውልድ ዓድዋ፣ የላቀ የታሪክ ምዕራፍ–ታሪክ ቀያሪ  ጉዞ አካል ላደረገኝ  ፈጣሪ ተመስገን! 🙏🏾 የዓመታት ምኞት፥ የዘመናት ፅኑ ሕልም፣ የመጪው ትውልድ ደማቅ ብርሃን እውን ሆኖ በአዲስ ዓመት መባቻ ከላቀ ገፀ-በረከት ጋር አዲስ ዓመቱን ስንቀበል፥ ድርብ ደስታ ነው። እንኳን ደስ አለን፥ እንኳን አደረሰን። ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ፥  እንኳን ደስ አለን፥ እንኳን ደስ አላችሁ።  እንኳን በደስታ ሲቃ ለምንቀበለው አዲስ ዓመት አደረሳችሁ። እኛ የዚህ ዘመን ትውልድ፥ ለትውልድ የምናወርሰው መቻልን፣ ብርታትን እና የልማት አርበኝነትን ነው። የተጣመመ ትርክት አቃንተን፥ በዕዳ  የተረከብነውን ለውጠን ወረት እና ምንዳን እናስረክባለን:: እንኳን ደስ አለን! አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዋዜማ መርሐ ግብር በልዩ ድምቀት ተከናውኗል .......///......... ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃት የዋዜማ መርሃግብር በድሮን ትርኢት እና በርችት ዝግጅቶች በደመቀ ድባብ ተከናውኗል። የዋዜማ መርሀግብሩ የተለያዩ ህብረ ቀለማዊ ትርኢቶች ቀርበውበታል። በመርሃ ግብሩ ላይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የቀድሞው ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል። ዛሬ የሀገራት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የግድቡ ምርቃት በይፋ የሚከናወን ይሆናል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

ጳጉሜን -3 የእመርታ ቀን እመርታ ለዘላቂ ከፍታ የወረስነው ዕዳ ብዙ፤ የምንጓዝበት መንገድ ረዥም፤ የሕዝባችንም ፍላጎት ሰፊ ነው፡፡ ቀስ በቀስ በሚደረግ የተለምዶ ጉዞ ወደምንፈልገው የብልጽግና ምዕራ
ጳጉሜን -3 የእመርታ ቀን እመርታ ለዘላቂ ከፍታ የወረስነው ዕዳ ብዙ፤ የምንጓዝበት መንገድ ረዥም፤ የሕዝባችንም ፍላጎት ሰፊ ነው፡፡ ቀስ በቀስ በሚደረግ የተለምዶ ጉዞ ወደምንፈልገው የብልጽግና ምዕራፍ አንደርስም፡፡ ያለን አማራጭ አንዳንድ እርከኖችን መዝለል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ፈጠራና ፍጥነት ወሳኞች ናቸው፡፡ ከተለመደው መንገድ ወጣ ማለት፣ ከተለመደው ጊዜ በላይ መሥራት፣ ከተለመደው ዋጋ በላይ መክፈል ያስፈልገናል፡፡ ዓላማችን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ መሻገር አይደለም፡፡ ከትናንት ዘለን ወደ ነገ መድረስ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 3 ቀን 2017 ዓ.ም

ጳጉሜን -2 የኅብር ቀን ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ ኢትዮጵያ በብዙ ጸጋዎች የተሞላች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ጸጋዎቿ የተለያዩ ሳይሆኑ ልዩ ልዩ ናቸው፡፡ የባህል፣ የቋንቋ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔ፣ የእምነት
ጳጉሜን -2 የኅብር ቀን ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ ኢትዮጵያ በብዙ ጸጋዎች የተሞላች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ጸጋዎቿ የተለያዩ ሳይሆኑ ልዩ ልዩ ናቸው፡፡ የባህል፣ የቋንቋ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔ፣ የእምነት፣ የጾታ፣ የአመለካከት፣ ወዘተ ብዝኃነት ያለንን የጸጋ ብዛት የሚያመለክት ነው፡፡ ብዝኃነት የኢትዮጵያ ታሪኳ እና መልኳ ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም

በከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ሥር ግንባታ ማከናወን አደገኛ መሆኑን ምን ያህል ያውቃሉ? ከአዲስ ዌስት ወይም ከኮልፌ ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ጥቁር አንበሳ ማከፋፈያ ጣቢያ በሚሄደው መስመር ሥር አደገኛ የህንፃ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ተመልክተናል፡፡  ግንባታው ከአደገኛነቱ ባሻገር በቸልተኝነት የተከናወነ ተግባር ለመሆኑ የምትመለከቱት ምስል አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ግንባታው ከከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ ሥር መከናወኑ እንደ ፈሮ ብረት እና ቆርቆሮ ያሉ ኤሌክትሪክን የመሳብ አቅም ያላቸው የግንባታ ግብዓቶች ኤሌክትሪክን በመሳብ በቀጥታ በሰዎች አካል እና ህይወት ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ይህ ግንባታ ትናንት በልደታ፣ በቂርቆስ እና በአራዳ ክፍለከተማ የተወሰኑ አካባቢዎች በተለይም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እና በሜክሲኮ አካባቢ የኃይል መቋረጥ እንዲከሰት ምክንያት ሆኖ ነበር፡፡ አሁን ላይ ግንባታው በሰው ህይወትም ሆነ አካል ላይ ጉዳት ባያደርስም መስመሩ ከሚያሰተላልፈው ከፍተኛ ቮልቴጅ አንፃር አደጋ መድረሱ የሚቀር እንዳልሆነ እናምናለን፡፡ በቀጣይም ከዚህ መስመር ኃይል የሚያገኙ አካባቢዎች በተደጋጋሚ ኃይል እንዲቋረጥባቸው፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳይችሉ የሚያደርግ እና ህብረተሰብን ለእግልት የሚዳርግ በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ “በቡሃ ላይ ቆሮቆር” እንዲሉ አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት በቸልተኝነት የሚከናወኑ አደገኛ ግንባታዎች በበዓል ወቅት ህብረተሰቡን ኃይል በማሳጣት የበዓል ድባብን ሊረብሹ ስለሚችሉ የግንባታ ፍቃድ የሰጡ አካላት ውሳኔያቸውን በማጤን ግንባታውን ሊያስቆሙ ይገባል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ በዚሁ መስመር ሥር የሚከናወኑት የድንጋይ ማውጣት ሥራዎች የአፈር መንሸራተት እያስከተሉ ስለሆነ እንቅስቃሴዎቹ ተገተው የእርምት እርምጃ ካልተወሰደ የኃይል መቋረጥ ሊያመጣ ስለሚችል የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡት እንጠይቃለን፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል! 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” 📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ዩትዩብቻናል↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ቲክቶክአካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power 📌ድረ- ገፃችንንም ይጎብኙ https://www.eep.com.et ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1