ru
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

Открыть в Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

Больше
603
Подписчики
-324 часа
-87 дней
-1730 дней
Архив постов
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝               ✝ #ጥር ፪ (2) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጽያዊ_ጻድቅ በዓለም ላይ በንግሥና መኖርን ንቀው ለመነኑትና ብዙ ተአምራትን በማድረግ ለሚታወቁት #ለንጉሥ_ዐፄ_ይኩኖ_አምላክ ልጅ ለሆኑት #ለአቡነ_ገብረ_ክርስቶስ_ዘዳግና ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለሊቀ ሰማዕታት #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ_ለልደት በዓል በሰላም አደረሰን።                                                           ✝ ✝ ✝ ✝ #ፀሐይና_የአጥቢያ_ኮከብ የተባለ ታላቁና ክቡር የሆነ ሰማዕቱ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ፦  የዚህም ቅዱስ አባቱ መስፍን ነው ስሙም አንስጣስዮስ ይባላል ከቀጰዶቅያ አገር ነው የእናቱም ስም ቴዎብስታ ይባላል ከፍስጥዓዔም አገር ናት ታናሽ ሆኖ ሳለ አባቱ ዐረፈ። ሃያ ዓመትም በሆነው ጊዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉሥ ዱድያኖስ ዘንድ ሔደ። ንጉሡም ጣዖት አቁሞ ጣዖትን እንዲአመልኩ ሰዎችን ሁሉ ሲያስገድዳቸው አገኘው። ይህንንም አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ በእርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድኆች ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነፃ አወጣቸው። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #የተባረከ_የጥር_ወር_የመዓልቱ_ሰዓት_ዐሥር ነው ከእንግዲህ ይጨመርለታል።               ✝ #ጥር ፩ (1) ቀን። ✝ እንኳን #ለሊቀ_ዲያቆናት_ለቀዳሜ_ሰማዕት #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለልደቱና_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ከሶርያ_አገር_ለሆነ በከሀዲው መክስምኖስ ዘመነ መንግስት ሰማዕትነት ለተበቀበለ #ለቅዱስ_ለውንድዮስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክድርያ ስልሳ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_መቃርስ ዕረፍት፣ #ከከበሩ_ከአክሚም_ሰማዕታት የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ከፈጸሙ ስማቸው #ቅዱሳን_ዲዮስቆሮስና_ሰከላብዮስ ዕረፍት፣ በዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ከተቀበሉ ቊጥራቸው #ከካህናት_ስምትት_መቶ፣ #ከዲያቆናት_መቶ_ሠላሳ_ከመምህራን_ኃምሳ፣ #ከሦስት_ከቤተ_ክርስቲያን_ሹማምንት_ከሰማንያ_መሳፍንት_ከሠላሳ_ሁለት_ንፍቅ_ዲያቆናትና_ከመቶ_ኃምሳ_ሕዝባውያን ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨    

✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝              ✝ #ታኅሣሥ ፴ (30) ቀን። ✝ እንኳን #ለታላቁ_አባት ለተመሰገኑ አባት አርባ ዓመት ሙሉ የሴቶች ፊት ሳያይ ለኖረ #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ለሆነ ለከበረ አባት #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ ከመኰንኑ ከአርያኖስ የጥፍሮቹ ታላላቆች #ለቅዱሳን_ለኮርዮንና_ፊልሞና ከእናርሳቸው ጋር ካሉ #ከአርባ_ወታደሮች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ተጋድይ ለሆነ #ለአባ_ዘካርያስ ዕረፍትና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ኄሮድስ ከገደላቸው #ከከበሩና_ከነጹ_ሕፃናት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                 ✝ ✝ ✝ ✝ #አባ_ዮሐንስ፦ ይህም ተጋዳይ የምንኵስና ልብስን ከለበሰ ጀምሮ የትንቢትና በሽተኞችን የመፈወስ ሀብት ተሰጠው ዜናውም በአገሩ ሁሉ ተሰማ። ይህም አባ ዮሐንስ ሁል ጊዜ የሚጐበኘው አንድ መኰንን ነበረ የመኰንኑም ሚስት ወደ አባ ዮሐንስ ዘንድ እንዲወስዳት ባሏን ታምለውና ታስገድደው ነበር እርሱም "የከበረ አባ ዮሐንስ ከአርባ ዓመት ጀምሮ የሴቶችን ፊት አላየም" አላት።  ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሒዶ ሚስቱ ያለችውን ለአባ ዮሐንስ ነገረው አባ ዮሐንስም "በእግዚአብሔር ፈቃድ የፈለገችውን እፈጽምለሠታለሁ" አለው። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ታኅሣሥ ፳፱ (29) ቀን። ✝ እንኳን #ለተባረከና_ለተመሰገነ በሰማያት ያለ ምሥጢርን ለአየ፤ #ዐሥር_አስደናቂ_ቤተ_መቅደስን ከ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝           ✝ #ታኅሣሥ ፳፱ (29) ቀን። ✝ እንኳን #ለተባረከና_ለተመሰገነ በሰማያት ያለ ምሥጢርን ለአየ፤ #ዐሥር_አስደናቂ_ቤተ_መቅደስን ከዐለት ደንጋይ ላይ ላነፀ፤ ክብሩ ልክ እንደ ሐዋርያት ለሆነ #ለኢትዮጵያዊው_ለጻድቁ_ለካህኑ_ንጉሥ_ለቅዱስ_ላሊበላ_ለልደት በዓል፣ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_ለልደት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚችን ልደታቸው ከጌታችን ጋር አንድ ከሆኑ ከቅዱሳን፦ #ከቅዱስ_ነአኲቶ_ለአብ_ፍቅርተ_ክርስቶስ ቅዱሳን ነገሥታት #አብርሐ_ወአጽብሓ፣ አቡነ አካለ ክርስቶስ፣ አቡነ መዝራእተ ክርስቶስ፣ መስፍኑ ኢያሱ፣ የገርአልታው አቡነ ዳንኤል፣ አቡነ አብሳዲ፣ አቡነ ፄዋ ለጽድቅ፣ ዳግማዊ ቂርቆስ ዘቡልጋ  እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።  √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ መልአኩም እንዲህ  አላቸው እንሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚኾን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለኹና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።ሉቃስ2፡10-11)እንኳን ለብርሀነ  ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ ፡፡ ርዕስ የግርግም ባለቤት ወግ አቅራቢ እየሩሳሌም ታምራት ከኪነ ጥበብ ክፍል

የ2016 ዓ.ም የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደትን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ቀዳሚ በሆነው እና በ1905 ዓ.ም በንጉሥ ኢያሱ ዘመን በተሰራው በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴ
+8
የ2016 ዓ.ም የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደትን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ቀዳሚ በሆነው እና በ1905 ዓ.ም በንጉሥ ኢያሱ ዘመን በተሰራው በደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል በድምቀት ተከበረ። ++++++++++++++++++++++++++++++++++ በበዓሉ ላይ ከዋዜማ ጀምሮ ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሥፍራው በመገኘት ቀድስው ሕዝበ ክርስቲያኑን በማቁረብ አባታዊ ቡራኬን ሰጥተዋል። የጠቅላይ ቤተ ክህነት እና የሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች። የገዳማት እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መምህራን ዘማርያን እና ዘማርያት ከአራቱም አቅጣጫ በዓሉን ለማክበር በሥፍራው የተገኙ ምእመናን እና ምእመናት በተገኙበት በዓሉ በድምቀት ተከብራሯል። በዕለቱ በካቴድራሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያሬዳዊ ዜማ ቀርቧል። በማስከተልም በካቴድራሉ እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት አባላት በአባቶችሽ እግር ልጆች ተኩልሽ አንደተባለው በካቴድራሉ የሰንበት ቤት አባላት ያሬዳዊ መዝሙር ቀርቧል በማስከተልም በካቴድራሉ መስማት የተሳናቸው አባላት ያሬዳዊ ዜማ ቀርቧል። በበዓሉ ላይ በካቴድራሉ አስተዳዳሪ በሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ኪሮስ ፀጋዬ የዕለቱ ቃለ ወንጌል ተሰጥቷል። በመጨረሻም በአባቶች ቡራኬ እና ቃለ ምዕዳን ተሰጥቶ ታቦታቱ ሕዝቡን እየባረኩ በክብር ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል። መምህርት ኑኀሚን ዋቅጅራ ከደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል።

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል በድምቀት ተከበረ ! ታኅሣሥ 28
+3
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል በድምቀት ተከበረ ! ታኅሣሥ 28 ቀን 2016 ዓ.ም

💫የጌታችን ልደት በትንቢተ ነቢያት ፦ ከዓበይት ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የሚከተለውን ትንቢት ተናግሯል፡፡ "እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ( ኢሳ.7፥14፣ ሕዝ.44፥1) ፡፡ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና የተወልደው አማኑኤል ጌታ ነው፡፡ ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ነቢዩ በጎላና በተረዳ ነገር “ሕፃን ተወልዶልናል ወልድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ ስሙም ድንቅ መካር ኀያል አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል“ በማለት የሚወለደው ሕፃን የባሕርይ አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ሥልጣን የባሕርይ ገንዘቡ እንደሆነ እና ለሥልጣኑም ወሰን ድንበር እንደሌለው ተናግሯል፡፡ 💫ከደቂቀ ነቢያት መካከል አንዱ ሚልክያስም በቤተልሔም ስለመወለዱ፡- "የኤፍራታ ምድር አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ አለቆች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና" (ሚክ.5፥2፣ ማቴ.2፥6) ብሏል፡፡ 💫• ነቢየ እግዚብሔር ቅዱስ ዳዊትም "እነሆ በኤፍራታ ሰማነው ዛፍ በበዛበትም ቦታ አገኘነው እንግዲህስ ወደ እግዚአብሔር ማደሪዎች እንገባለን ብሎ የወመለዱን ምሥጢር ተናግሯል" (መዝ.131፥6) 💫• ነቢዩ ዕንባቆምም "አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም ዐይቼ አደነቅሁ በሁለት እንስሶች መካከል አየሁህ ዘመኑ እንደደረሰ አድርጌ አውቅህአለሁ ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ተገለጥክ" ብሎ በቤተልሔም በረት በተወለደ ጊዜ አድግና ላኅም እስትንፋሳቸውን እንደሚገብሩለት (ዕንባቆም 3፥1) ተናግሯል፡፡ ከዚህ በኋላ የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ እግዚአብሔር መልአኩን ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ድንግል ማርያም በመላክ አብሥሯታል፡፡ “ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል" በማለት፡፡ ሉቃ. 1፡32 እመቤታችንም በብዙ ኅብረ አምሳል ትንቢት ሲነገርለት፤ ምሳሌ ሲመሰልለት፤ ሱባኤ ሲቆጠርለት የነበረውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቤተልሔም ግርግም  ወለደችው፡፡ ይህንንም ብስራት በቤተልሔም ዋሻ መንጋቸውን ነቅተውና ተግተው ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች መጋቤ ሐዲስ አብሣሬ ትስብዕት ቅዱስ ገብርኤል ፤ እነሆ ዛሬ መድኀኒት በዳዊት ከተማ ተወልዶላችኋል ይኸውም ቡሩክ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሚያርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚያድል ከዓለም በፊት ንጉሥ የነበረ ዛሬም ከዳዊት ባሕርይ /ዘር/ በቤተልሔም ዋሻ ዓለምን ለማዳን የተወለደ የዳዊት ልጅ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ ሲል አበሰራቸው፡፡ (መዝ.73፥12) 💥 የጌታችንን ልደት ስናነሣ ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምናለን፡፡ እኒሁም ልደታት /ልደት ቀደማዊና/ /ልደት ደኃራዊ/ ናቸው፡፡ 💫 ልደት ቀዳማዊ ፦ ቅድመ ዓለም ከአብ አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት የተወለደው ልደት ሲሆን /ነቢዩ ዳዊት እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ "ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽ ባህ መዝ.109፥3 ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ወለድኩህ ፤አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድኩህ" (መዝ.2፥7)   💫ልደት ደኃራዊ ፦ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈፀም በዕለት ሐሙስ ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ እንዲል ቃሉ፡፡ ቅድስት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን እንበለ ዘርዓ ብዕሲ ያለ አባት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም የተወለደው ልደት ነው፡፡ ቀዳማዊ ልደቱ ጥንትና ፍጻሜ የሌለው የማይመረመር ስለሆነ ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለፅ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ እንደ ተወለደ ድኅረ ዓለምም ከእመቤታችን /እንበለ ዘርዓ ብዕሲ/ ያለ አባት ተወለደ፡፡ እሱም እመቤታችን ያለ አባት የወለደችው ፤ እግዚአብሔርም ያለ እናት የወለደው ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሰባቱ መስተጻርራን /ተቃራኒ ነገሮች አንድ ሆነዋል ሕዝብና አሕዛብ ፤ በጠብና በክርክር ይፈላለጉ የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ በጌታችን ልደት ታርቀዋል።                     ✨መልካም በዓል✨ 🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊

🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊 ✨ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ✨ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ
🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊      ✨ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ✨ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አይደለም፡፡ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ በመላእክት ፤ በነቢያት ሲነገር ፤ ሲሰበክ የመጣ ነው እንጂ፡፡ ማቴ.1፥18፡፡ ሰው የመሆኑን ምሥጢር ለመጀመሪያ ጊዜ በማዕከለ ገነት የተናገረ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወጥቶ ዕፀ በለስን በልቶ ከጸጋ እግዚአብሔር በተራቆተ ጊዜ /አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ/ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ.3፥22 ብሎ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው እንደሚሆን ተናግሯል፡፡ በዚህ ቃል መሠረት /መሪነት/ ቅዱሳን መላእክት ምሥጢረ ትንቢት ተገልጾላቸዋል፡፡ እነሱም የተገለጸላቸውን ምሥጢረ ትንቢት ኀላፍያትንና መጻእያትን ለሚናገሩ ነቢያት ነግረዋቸዋል፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም ከእግዚአብሔር ያገኙትን ከመላእክት የሰሙትን መነሻ አድርገው በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ምሳሌያት በተለያዩ ዘመናት የወልደ እግዚአብሔርን ሥጋዌ ሰብከዋል /ገልጸዋል/ ዕብ.1፥1፡፡ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፡፡    

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ታኅሣሥ ፳፰ እና ፳፱ (28 እና 29) ቀን። ✝ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለአምላካችን_ለጌታችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝          ታኅሣሥ ፳፰ እና ፳፱  (28 እና 29) ቀን። ✝ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለአምላካችን_ለጌታችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ #ከእመቤታች_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም_በሥጋ_ለተወለደበት የበዓላት ሁሉ ራስ ለሆነች #ለብርሃነ_ልደቱ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በእነዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከእንዴናው_አገር_ሰዎች ከሆኑ በሰማዕትነት ካዐረፉ #ከመቶ_ሃምሳ_ወንዶችና_ከሃያ_አራት_ሴቶች፣ #ከአባቶቻች_ከአብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ፣ #ከኤፍሬም_ወገን ከመስፋኑ #ከቅዱስ_ኢያሱ_ልደት፣ ከከበሩ #ከያዕቆብ_ከፈሊስ ከሌላው ሰማዕት፣ #ከቴዎድሮስ ከመታሰቢያቸው፣ #ከሮሀ_ንጉሥ_ከአቃርዮስ ዕረፍት፣ ሰምኑድ ከሚባል አገር ከሆነ ከገመላዊው #ከቅዱስ_ቆሪል ዕረፍትና #ከአክሚም_ሰማዕታት_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ✝ በዚች ቀን የከበረና የተመሰገነ ታላቅ #የልደት_በዓል_ሆነ_የጌታችንና_የመድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከእመቤታችን_ከከበረች_ድንግል_ማርያም_የተወለደባት_ዕለት_ከበዓላት ሁሉ ተለይታ ከፍ ከፍ ያለች ናት። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊✨🕊✨🕊✨ 💫እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ተወልዶላችኋል ሉቃ.2፥11 💫 🕊 እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክ
🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊✨🕊✨🕊✨ 💫እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ተወልዶላችኋል ሉቃ.2፥11 💫      🕊 እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡  🕊        ✨ " ጌና" ✨ ጌና እና ልደት {ዋዜማና ክብረ በዓል } /የተለያዩ ቀናት/ ቢኾኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ጌና ልደትን እየተካ እንጠቀምበታለን ፤ ነገር ግን ይህ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡ ልዩነት ስላለውም የኢትዮጵያ ብርሃን የተባለው አፈ ጳዝዮን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለጌናና ለልደት ለ2ቱም በዓላት ለየብቻቸው በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰት ደርሶላቸዋል፡፡ #ጌና ፤ የልደት በዓል ዋዜማ ቀን ሲኾን በዚህ ቀን ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የተባለለትን ‹‹የገና ጨዋታ›› እንጫወታለን፤ የምንጫወትበት የኳሱ ስያሜ ‹‹ሩር›› ሲባል ስያሜውን ያገኘው፤ ሰብዓ ሰገል እልፍ እልፍ ሠራዊት አስከትለው የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ ፍለጋ ወደ ንጉሡ ሔሮድስ ደርሰው ነበርና ፤ ሔሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ፈልጎና በውስጡ ሸሽጎ ለሰብዓ ሰገል ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ስታገኙትም ንገሩኝ ብሎ ሰድዷቸዋል ፤ ነገር ግን በዚያው ሳይነግሩኝ እንዳይሄዱ በማለት እነርሱ ሳያውቁ  ‹‹ሩር›› የተባለ ሰላይ በመሃላቸው አስገብቶ ነበርና ሰብዓ ሰገልን ይመራቸው የነበረው ኰከብ ተሠውሮባቸዋል ፤ ሰብዓ ሰገል ሠራዊታቸውን ቢያጣሩ ከመሃከላቸው የተቀላቀለ ሩር የተባለ የሔሮድስን ሰላይ አገኙ ይህንንም ሰላይ የሰብዓ ሰገል ሠራዊት አንገቱን በሰይፍ ቀልተውታልና ያን ለማስታወስ ዛሬ በገና ጨዋታ ላይ ሩር የተባለው ኳስ የሔሮድስ ሰላይን ‹‹ሩር›› እንዲያስታውስ አባቶች ሥርዐትን ሠሩ፡፡      ይቀጥላል.............

🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊እንኳን_አደረሳችሁ 🕊✨🕊✨✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊 « በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ እ
+3
🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊እንኳን_አደረሳችሁ 🕊✨🕊✨✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊 « በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ እንገናኝ » (ነህ .6 ፥ 10 ) አሕዛብ ሁሉ የእርሱን መምጣት ተስፋ የሚያደርጉት ሕያው ቃል ወደዚህ ዓለም መጥቶ ያለ ዘርዐ ብእሲ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ የእግዚአብሔር መልአክም መንጋቸውን በትጋት ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች ተገልጦ ‹‹ እነሆ ለእናንተና ለሕዝብ ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ። ›› በማለት ደስታ ርቆት ለነበረው ዓለም ሰውን ሁሉ ደስ የሚያሰኝ የምሥራች ተናገረ ። ( ሉቃ 2 ፥ 10 ) የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ምድረ ኤፍራታ ቤተ ልሔም ለተወለደው ንጉሥ መካነ ልደት በመሆኗ የምድራውያንና የሰማያውያን መገናኛ ፣ የእርቅ መጀመሪያ የጌትነቱ እጅ መንሻ ማቅረቢያ ሆነች ። ( ሚክ 5 ፥ 2 ) #መልካም_በዓል 🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊✨🕊

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ታኅሣሥ ፳፯ (27) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አስቀድሞ ሽፍታ ለነበሩና በኋላም በንስሓ ተመልሰው #ለሰባት_ዓመት_
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝          ✝ #ታኅሣሥ ፳፯ (27) ቀን። ✝ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አስቀድሞ ሽፍታ ለነበሩና በኋላም በንስሓ ተመልሰው #ለሰባት_ዓመት_ምንም_ውሃ_ሳይቀምስ እስከመኖሩ ድረስ በታላቅ ተጋድሎ ለኖሩ #ለአቡነ_በግዑ_ዘሐይቅ ለዕረፍት ዓመታዊ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ✝ #አባ_በግዑ_ዘሐይቅ፦ በመጀመሪያ ሽፍታ የነበረ ሲሆን በመንገድ ላይ ንብረት የያዘን ሰው ማንንም የማያሳልፍ ቀማኛ ሰው ነበር፡፡ ከኃይለኛነቱ የተነሳ ሕዝቡም ሁሉ ይፈራው ነበር፡፡ በእጁ ሰይፍና ጦር ይዞ ሊዘርፍ ወደ ወደደው አገር ይገባል፡፡ እየዘረፈ በሚያገኘው ገንዘብም ራሱን በተለያዩ ምግቦችና መጠጦች ያስደስት ነበር፡፡ ባማሩ ልብሶችም ይዋብ ነበር፡፡ ገንዘቡ የተወሰደበት ሰውም እርሱ እንደወሰደበት ባወቀ ጊዜ ዳግመኛ መጥቶ የተረፈውን ቀምቶ እንዳይወስድበት ምንም አይከሰውም ነበር፡፡ በጉልምስናው ኃይለኛና ብርቱ ስለነበር ወደ እርሱ ማንም አይቀርብ ነበር፡፡ √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ሰላማችንን እንመልስ፡፡ በመጨረሻም በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን በተከሠተው የድርቅና የሰው ሰራሽ ምክንያት በችግር ላይ የወደቁ ወገኖች በርካታ ናቸው በመሆኑም የወገን ደራሽ ወገን ነውና ሁሉም ካለው ብቻ
+2
ሰላማችንን እንመልስ፡፡ በመጨረሻም በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን በተከሠተው የድርቅና የሰው ሰራሽ ምክንያት በችግር ላይ የወደቁ ወገኖች በርካታ ናቸው በመሆኑም የወገን ደራሽ ወገን ነውና ሁሉም ካለው ብቻ ሳይሆን የቀን ቍርሱን ለተቸገሩ ወገኖች እንዲለግስና በመተጋገዝ ረኃቡን እንድንከላከለው ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡ መልካም የልደት በዓል ያድርግልን እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን። አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

"ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በሆነውም ባልሆነውም ከመተላለቅ ለምን ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በእኩልነትና በስምምነት መኖር አቃተን?" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ታኅሣሥ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ++++ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በዓለ ልደትን አስመልክቶ ለመላው የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው መልእክት አስተላልፈዋል። የቅዱስነታቸው ቃለ በረከት ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ፡ በፍጹም ፍቅሩ እኛን ወደ ሰላም ለማምጣት በእኛ ሰውነት በዚህ ዓለም የተወለደው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በደኅና አደረሳችሁ! “ትእምርተ ሰላምነ ወልድ ተወልደ ለነ፡ የሰላማችን ሰንደቅ ዓላማ የሆነው ወልድ ወይም ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ተወለደልን'' (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ) ዓለም ሁሉ በተለይም የክርስቲያኑ ዓለም በትክክል እንደሚያውቀው ቅዱስ መጽሐፍ በሰዎች የቋንቋ ዘይቤ የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል ነው፤ በመንፈሳዊም ሆነ በዓለማዊ ርእዮት ቋንቋ የመልእክት ማስተላለፊያና መግባቢ መሳሪያ እንደሆነ ይታወቃል፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ መልእክቱን በዚህ መንገድ ለሰዎች ሲያስተላል ኖሮአል፤ የሚያስተላልፈውም መልእክት እንዲሁ ተሰምቶ እንዲቀር ሳይሆን እንዲታወቅ፣ እንዲታመን እንዲተገበርና ሰዎች እንዲጠቀሙበት ነው፤ ከሚፈለገው ጥቅም ለመድረስም ሰዎች መልእክቱን በሚገባ መረዳት የግድ ይሆናል፤ ሰዎች እንዲረዱት ደግሞ በቋንቋቸውና በባህላቸው ዘይቤ ሊነገራቸው ይገባል፤ በመሆኑም እግዚአብሔር ቃሉን በሰዎች ቋንቋ ባህላዊ ዘይቤ መልእክቱን ለዓለም ሲያስተላልፍ ኖሮአል ቤተክርስቲያንም ይህንን መሠረት አድርጋ የእግዚአብሔርን ቃል በሰው ቋንቋ ዘይቤ ታስተምራለች፤ ከዚህ አንጻር በሰው ልማዳዊ የዘይቤ ቋንቋ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም "የሰላም ሰንደቅ ዓላማ" የሚል ቅፅል ተሰጥቶታል፡ ምክንያቱም ንጉሥም ወታደርም ተራው ሕዝብም የሀገሩ ነጻነትና ክብር፤ አንድነትና ሉዓላዊነት ምልክት የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ተከትሎ ስራ ይሰራል ክብሩንም ይገልፃልና ነው፤ ተከተል አለቃህን ተመልከት ዓላማህን የሚለው ብሂልም ይህንን ያንፀባርቃል፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! ጌታችን በመድኅንነቱ የሁላችን የሰላም ሰንደቅ ዓላማ በመሆኑ መምህራችን ቅዱስ ያሬድ የሰላማችን ሰንደቅ ዓላማ የሆነ ልጅ ተወለደልን ብሎ ይገልፀዋል፤ ጌታችን በዛሬው ዕለት በቤተልሔም ሰውነታችንን ሰውነት አድርጎ መወለዱ ራሱ የሰላም ማሳያ ምልክት ነው፤ ምክንያቱም ሳይወደን አይቀርበንም፤ አይዋሐደንምና ነው፤ በልደቱ ዕለት "ለዕጓለ እመሕያው ሠምሮ የሰው ልጅን ወደደው" ተብሎ በቅዱሳን መላእክት የተዘመረበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ጌታችን የተዋሐደው ሰውነት የወዳጁ አልነበረም የጠላቱ እንጂ፤ ቅዱስ መጽሐፍ ይህንን ሲገልፅ "ጠላቶቹ ሳለን እግዚአብሔር በልጁ ሞት ታረቀን" ይላልና ነው፡ በዚህ ዓለም የኖረውም ከሚያሳድዱት፣ ከሚከሱት፤ ስሙን ከሚያጠፉና ሊገዱሉት ከሚከጅሉ ጋር እንጂ ከወዳጆቹ ጋር ብቻ አልነበረም፤ እሱ ግን ሁሉንም በፍቅር ይቀበል ነበረ፤ ይፈውስና ያድን ነበረ፤ ያስተምርም ነበረ፤ ለሁሉም ስርየተ ኃጢአትን ሰጠ ለጠላቶቹም ጸለየ፤ ጌታችን በዚህ ሁሉ ለኛ አርእያና የተግባር መምህር በመሆኑ የሰላም ሰንደቅ ዓላማችን ነው፡ ምእመናንና ምእመናት ዓለም በጌታችን ዕለተ ልደት የተዘመረውን ሰማያዊውን የሰላም መዝሙር መዘመር ከጀመረች እነሆ ዛሬ ድፍን ሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመት ሆነ፤ የሰላሙ መዝሙር ዛሬም በመላው ዓለም በሚገኙ ክርስቲያኖች ይዘመራል፤ ይሁን እንጂ በዚህ ዓለም ሰላም ሰፍኖ እየታየ አይደለም፤ ይህ ለምን ሆነ ቢባል ደምበኛ መልስ ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔርን አለማመንና አለመፍራት ያመጣው ችግር ነው የሚል ነው፤ ምክንያቱም ሃይማኖትና ፈሪሐ እግዚአብሔር ከሌለ ፍትሕ ይጐድላል፣ ፍትሕ ከጐደለ ብሶት ይፈጠራል፣ ብሶት ካለ ሰላም ሊኖር አይችልም፤ በሁሉም የዓለማችን ክፍል ሃይማኖትና ፈሪሐ እግዚብሔር እየተዘነጋ በመሄዱ ቀውሱ ተባብሶ ይታያል፤ የሰው ልጅ ኑሮ በየትም ይሁን በየት በስጋት የተሞላ ሆኖአል፤ የሚወራው ሁሉ ስለ ግጭት ስለአየር ብክለት ስለ ረኃብና እልቂት ሆኖአል፤ ዓለም የጉልበተኞችና የባለ ሀብቶች ብቻ እንድትሆን የተፈጠረች እስክትመስል ድረስ ከባድ የፍትሕ መዛባት አጋጥሞአታል፤ የዝቅተኛው ማኅበረሰብ ሰብአዊ መብት ተዘንግቶአል፣ ከዚህ አኳያ ዓለም በዚህ እስከ ቀጠለች ድረስ ሰላም የማግኘቷ ዕድል በጣም አጠራጣሪ ነው፡ የክርስቶስ ልደት ያስተማረን ግን እንደዚህ አልነበረም፤ ጌታችን የተወለደው በተዋበና ምቹ በሆነ የሀብታም ቤት ሳይሆን በከብቶች በረት ነበረ፤ የተገለጠውም ለባለሥልጣኖች ሳይሆን ዝቅተኞች ለሚባሉ እረኞች ነበረ፤ ልዑላኑ ሰማያውያንና ትሑታኑ ምድራውያን በአንድነት አገናኝቶ ስለ ሰላም በጋራ እንዲዘምሩ አደረገ፤ አሳዳጅ ሳይሆን ተሳዳጅ ሆኖ በግብጽ አገር በመንከራተት አደገ፤ ይህን ሁሉ ያደረገው እኛ እሱን እያየን እንደ ሰንደቅ ዓላማ እንድንከተለው ነበር፤ ጌታችን ከባለሥልጣናቱና ከባለሀብቶቹ ይልቅ በድሆቹ ደረጃ የተወለደው ለድሆቹና ለዝቅተኞቹ ትኩረት እንድንሰጥ ለማስተማር ነው፤ የእኛ ድርጊት ግን ግልባጩ ሆኖ እየተስተዋለ ነው፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ክርስቲያን ነኝ ብሎ፤ በስመ እግዚአብሔር ተሰይሞ፤ መስቀልን በአንገቱ ተሸክሞ የእሱ መሰል በሆነው ወይም መስቀል በተሸከመው ወንድሙ እና እኅቱ እንዲሁም በመሰል ፍጡር ላይ ያለ ርኅራኄ ሲጨክን መታየቱ ነው፡ እንዲህ እየሆነ እንዴት ሰላም ይምጣ? እግዚአብሔርስ እንዴት በረከቱ ይሰጣል? ይህ እጅግ በጣም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት! እኛ ኢትዮጵያውያን ከእንዲህ ዓይነቱ የሃይማኖትና የሞራል ዝቅጠት በአስቸኳይ መውጣት አለብን፤ ጠቡ፤ መለያየቱ፣ መጨካከኑ፤ ለኔ ለኔ መባባሉ ከረምንበት፤ ሆኖም ያመጣልን ነገር ቢኖር ሁለንተናዊ ውድመት ብቻ ነው፡ ያስገኘልን ትርፍ ይህ መሆኑ እያወቅን በዚሁ ልንቀጥል አይገባም፡ ሰው ችግሩን በልቡ እያወቀ በዓይኑ እያየ እንዴት ገደል ውስጥ ይገባል? ዕርቅና ይቅርታ ማንን ጐዳ? ሰላምና አንድነት ማንን አከሰረ? ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በሆነውም ባልሆነውም ከመተላለቅ ለምን ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በእኩልነትና በስምምነት መኖር አቃተን? ሦስት ሺሕ ዘመናት አብረው የኖሩ ሕዝቦች እንዴት ችግራቸውን በጠባይና በብልሐት ማስወገድ አቃታቸው? ይህ ከቶ ሊሆን አይገባም፤ ሁላችንም ሰክን ብለን እናስብ፤ ለሁሉም የማሰቢያና የመመካከሪያ ጊዜ ፈጥረን ችግሩን በስፍሐ አእምሮ እንፍታው፡ ችግርን በምክክርና በይቅርታ መፍታት አማራጭ የሌለው ጥበብ ነው፤ የሃይማኖት መሪዎች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፤ ምሁራንና ልኂቃን በዚህ ተግተን ልንሰራ ይገባል፤ መንግሥትና የፓለቲካ ፓርቲዎችም ለዚህ የበኩላቸውን ድጋፍ ያድርጉ፤ በዚህም

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ታኅሣሥ ፳፮ (26) ቀን። ✝ እንኳን #ከሮሜ_አገር_ለሆነች_ለከበረች_ለቅድስት_አንስጣስያ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝          ✝ #ታኅሣሥ ፳፮ (26) ቀን። ✝ እንኳን #ከሮሜ_አገር_ለሆነች_ለከበረች_ለቅድስት_አንስጣስያ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረች ከሰማዕት #ከቅድስት_ዮልያና ከመታሰቢያዋና #ከጻድቁ_ከቅዱስ_አቦሊ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                              ✝ ✝ ✝ ✝ #ቅድስት_አንስጣስያ፦ የዚችም ቅድስት አባቷ ጣዖትን የሚያመልክ ነው እናቷ ግን ክርስቲያን ናት ይቺንም ቅድስት በወለደቻት ጊዜ አባቷ ሳያውቅ የክርስትና ጥምቀትን በሥውር አጠመቀቻት አውቆ ቢሆን ማጥመቅ ባልተቻላትም ነበር። ከዚህም በኋላ በበጎ አስተዳደግ አሳደገቻት በቀናች ሃይማኖት እስከ አጸናቻት ድረስ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማረቻት ጠባይዋን መለወጥ ለማንም አልተቻለውም። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

ከቋሚ ሲኖዶስ ነተሰጠ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፦ መንፈሰ ሰላም ማዕከለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወማዕከለ ቤተ ክርስቲያን… ውእቱ… የሰላም መንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ነው:፡ (መጽሐፈ ምሥጢር) ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በዚህ የሕይወት ቃል አማካኝነት የሰላም መንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል በየዘመናቱ ያለና የሚኖር መሆኑን እንመለከታለን፡፡ የዚህም መንፈሰ ኃይል በቤተ ክርስቲያን መኖር ሕማመ ነፍስ በሌለበት ምግባረ ሃይማኖት በፍቅር እንድንኖር ለምንሻው ሁሉ እግዚአብሔር በምልዓት በሚከብርበት ቤተ መቅደስ በኩል የሚሰማው የሰላም ጥሪ በማያቋርጠው የመንፈሳዊ ኑሮ ሂደት ለመንፈስ አንድነት፣ ለአካላዊ ሕብረት የሚጠቅም የሕይወት ምሰሶ ነው፡፡ በመሆኑም ‹‹ወብነ ክሂል ከመ ንቅትል ኅሊና ሰይጣናዌ …ሰላምን የሚያሳጣ ክፉ ሓሳብን በቤተ ክርስቲያናችን መካከል ባለው ሰላም ከእኛ የማራቅ ችሎታ አለን›› ተብሎ እንደተጻፈው ፍጥረተ ሰብእ ሕይወቱን ለበጎ በሚቀርጸው ሥርዓተ ሃይማኖት በመመራት፣ የሰላምን አስፈላጊነት በትምህርት በድርጊት በመግለጽ ባልተዛነፈ ሰብእና በተሟላ ሰላም መኖር የሚችልበት ክሂል ያለው ፍጡር መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ (ዜና አበው) የሰላም መንፈስ በመካከሏ ሆኖ ከስሕተት የሚጠብቃት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም አመለካከቱ ስሕተት ንግግሩ ሐሰት በሆነው ዓለም የጽድቅና የሰላም ባሕርይ መገለጫ ነው፡፡ ልጆቿ በሰላም በፍቅር በታነጸ ዕለታዊ ሕይወት እንዲኖሩ በማድረግ ሰላም የደግነት ሁሉ አክሊል የመንፈሳዊ ምግባራት ዘውድ መሆኑን ስታውጅ መኖሯን የታሪክ መዛግብት፣ ዕውነትን ለመግለጥ የሚተጉ ጸሐፍት ከመቅድም እስከ ህዳግ ይመሰክሩላታል። መሪዋና አጽናኟ ከሆነው መንፈስ ቅዱስ በተገኘው የሰላም እሴት በእምነታቸው ጸንተው በምግባር በትሩፋት አጊጠው የሚኖሩት ማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምእመናንም የረጅም ዘመናት የቅድስና ታሪክ ጉዞዋ ማሳያዎች ናቸው። የእውነትና የሰላም አምድ እንደመሆኗም በሀገራችን እየተከሰቱ ያሉ አለመግባባቶችንና የእርስ በእርስ ደም መፋሰሶች እንዲቆሙ የሰላም ጥሪ ከማድረግ ጀምሮ ምህላ፣ ጾምና ጸሎት በማወጅ እግዚአብሔር ለሀገራችንና ለሕዝባችን ሰላምን እንዲሰጥ ስትማጸን ቆይታለች። የየዕለት አገልግሎቷም ይህንኑ መሠረት ያደረገ ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላም መንፈስ በመካከሏ እንዲሆን አድርጎ ወኃቤ ሰላም መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት ስለሆነ በዓለም ሁሉ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ የክብር ስፍራውን ይዞ የሚቀጥል ቀዳሚና ዐቢይ ተልእኮዋ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን ። በመጨረሻም ሰላም የሚጸናው ማንኛውም ማኅበረሰብ እርስ በእርሱ በመተሳሰብና በፍቅር በእውነተኛ መግባባትና በፍትሕ በርኅራሄና በመከባበር አብሮ መኖር ሲቻል ነውና በወንድማማችነት መካከል ጠብን ከሚዘሩ ጥላቻንና መራራቅን ከሚያሰፉ ንግግሮችና ድርጊቶች በመቆጠብ ሁሉም የማኅበረ ሰብእ ክፍል እግዚአብሔር ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይሰጣት ዘንድ በጸሎት እንዲተጋ ቋሚ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ ከምን ጊዜውም በላይ ሰላምና ፍቅር በሀገራችን እንዲሰፍን በአንድነት ሆነን የምንሠራበት ወቅት ላይ በመሆናችን በመጪዎቹ ዐበይት በዓላት፣ በዘወትሩ መንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉም በየደረጃው ያላችሁ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶችና አገልጋዮች "ወፍሬሃኒ ዘጽድቅ በሰላም ይዘራዕ ለእለ ይገብርዋ ለሰላም ... የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ ሰዎች በሰላም ይዘራል" በሚለው ሐዋርያዊ ቃል መሠረት በየዐውደ ምሕረቱ ሰላምንና እርቅን በመስበክ በሀገራችን ኢትዮጵያ ያለው ችግር እንዲወገድ፣ ማኅበራዊ ሰላም እውን እንዲሆን የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል። ያዕ 3÷18 እግዚአብሔር ለሀገራችን ሰላምን ጽድቅን፣ፍቅርንና ፍትሕን ይስጥልን ታኅሣስ 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ታኅሣሥ ፳፭ (25) ቀን። ✝ እንኳን #ከግብጽ_ደቡብ_ፃ ከሚባል አውራጃ መንጹ ስብራ ከምትበል ከተማ ለሆነ ለከበረ አባት #ለአ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝          ✝ #ታኅሣሥ ፳፭ (25) ቀን። ✝ እንኳን #ከግብጽ_ደቡብ_ፃ ከሚባል አውራጃ መንጹ ስብራ ከምትበል ከተማ ለሆነ ለከበረ አባት #ለአባ_ዮሐንስ_ከማ ለዕረፍት በዓል፣ በሜዶናውያንና በሞዓባውያን ዘመን መንግሥት ለከበሩ #ለአምስቱ_መቃባውያን_ሰማዕትነት_ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ አባ ዮሐንስን ካመነኰሰው #ከአባ_ዳሩዲ ከመታሰቢያው፣ ከከበሩ #ከመኰንኑ_ከኒቆላዎስና_ከታማኝ_ሚስቱና ተገዳይ ከሆነ #ከታናሽ_መነኰስ_አባ_ከዳንኤል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትን በረከትን ያሳትፈን። √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨

✝ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝ ✝ #ታኅሣሥ ፳፬ (24) ቀን። ✝ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለሐዲስ_ሐዋርያ ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆኑት #ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ለልደ
✝ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ✝          ✝ #ታኅሣሥ ፳፬ (24) ቀን። ✝ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለሐዲስ_ሐዋርያ ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆኑት #ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ለልደት በዓል፣ ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ለከበረና ለተመሰገነ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ሰሎንቅያ በምትባል በምስ አገር ለሆኑ ሰይጣንን ገዝተው በግልጽ ላነጋገሩ ለታላቁ አባት #ለአባ_ጳውሊ ለዕረፍት በዓል፣ #ለአሚናዳብ_ልጅ_ለጻድቂቱ_ለቅድስት_አስቴር ለዕረፍቷ መታሰቢያና ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ቴዎድሮስ_ኃይለ_መነኰስ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአንጾክያ አገር ሊቀ ጳጳስ ከከበረ #ከአባት_ፊሎንጎስ ዕረፍት፣ የእግዚአብሔር መልአክ ከነገራቸው #በከዲህ_ከአሉ_ጻድቃን በአንዲት ቀን ዕረፍታቸው ከሆነና #ከአዝቂርም ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                           √ የዩቲዩብ ገጻችንን https://youtube.com/@FinoteBirhanzkidistarsema?feature=shared √ ፌስቡክ ገጻች https://www.facebook.com/finotebirhanzekidistarsema √ የቴሌግራም ገጻችንን https://t.me @Z_FINOTE_BIRHAN √ የኢንስታግራም ገጻችን https://www.instagram.com/ FINOTE BIRHAN Z KIDIST ARSEMA √ የቲክ ቶክ ገጻችንን tiktok.com/@finotebirhanzkidstarsema ✨✨✨ፎሎ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ ✨✨✨